AlltechUp.com
#ታላቅ_የምስራች "ቴሌክላውድ (telecloud)" አገልግሎቶች በሚያስደንቅ ዋጋ - #ከኢትዮቴሌኮም . . . ከዚህ ቀደም "ቴክኖሎጂክስ-አፍሪካ-ኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ አንድ ጽሁፍ አጋርቻችሁ ነበር። (ሙሉ ጽሁፉ https://www.facebook.com/share/p/1Fdww1JR1D/ ላይ ይገኛል ) በጽሁፉ ማጠቃለያ ላይ እንደ ቅሬታ ያቀረብኩት Ethio telecom በሁዋዌ የተገነባ ከፍተኛ አቅም ያለው…
#ታላቅ_የምስራች
"ቴሌክላውድ (telecloud)" አገልግሎቶች በሚያስደንቅ ዋጋ - #ከኢትዮቴሌኮም
.
.
.
---
#ኢትዮ_ቴሌኮም በ"ቴሌክላውድ (telecloud)" ያቀረባቸው አገልግሎት:-
🙋 Computer Services (የኮምፒዩተር አገልግሎቶች) : - ይህ አገልግሎት ኮምፒውተሮችን፣ ሰርቨሮችን እና የቨርቹዋል ማሽኖችን ከኢትዮ ቴሌኮም የዳታ ማዕከል (data center) #በሊዝ መከራየት (መጠቀም) የሚያስችል ነው፤ ግለሰቦች ወይም ተቋማት የራሳቸውን ውድ ኮምፒውተሮች ከመግዛት ይልቅ ተከራይተው ለመጠቀም ያስችላቸዋል።
🙋 የStorage Services (የመረጃ ማከማቻ አገልግሎት):- ድርጅቶች እና ግለሰቦች የራሳቸውን ውድ የሆኑ ሃርድዌር ከመግዛት ምንም ዓይነት የጥገና ወጪ የሌለው የኢትዮ ቴሌኮም #የCloud መሠረተ ልማት ላይ መረጃዎቻቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ ማከማቸትና መጠቀም የሚያስችሉበት አገልግሎት ነው።
🙋 Network Services (የኔትወርክ አገልግሎቶች):- ይህ አገልግሎት ከኢንተርኔት ግንኙነት በተጨማሪ ድርጅቶች የራሳቸውን ቨርቹዋል ኔትዎርክ (VPN) ወይም ሌሎች የኔትወርክ አገልግሎቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም የCloud ማዕከል ተከራይተው መጠቀም የሚያስችል ነው።
ይህ በመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ የሚወጣን ወጪ በመቀነስ ትኩረታቸውን በዋና የንግድ ስራቸው ላይ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።
🙋 Security Services (ደህንነት አገልግሎት):- ግለሰቦች ወይም ተቋማት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቀውን የራሳቸው የሳይበር ደህንነት ቡድን እና መሳሪያ ከማዘጋጀት ይልቅ የኢትዮ ቴሌኮምን የደህንነት አገልግሎቶች በመጠቀም የሳይበር ጥቃቶችን መከላከል እና መረጃዎቻቸውን መጠበቅ የሚችሉበት ነው።
🙋 Backup Services:- ይህ አገልግሎት ወሳኝ መረጃዎች እና ፋይሎቻቸው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ በኢትዮ ቴሌኮም #Cloud ላይ ለማስቀመጥ ያስችላቸዋል። ድንገተኛ አደጋ፣ የሃርድዌር ብልሽት ወይም ሌሎች ችግሮች ቢፈጠሩ ከዚህ ተቀማጭ መጠባበቂያ በቀላሉ ለመመለስ ያስችላል።
🙋 Container Services:- ይህ አገልግሎት አፕሊኬሽኖችን እና ሶፍትዌሮችን በ"ኮንቴይነር" (container) ውስጥ በማስቀመጥ በቀላሉ እና በፍጥነት ከተለያዩ ሲስተሞች ጋር እንዲሰሩ ያደርጋል። ይህም ገንቢዎች (developers) አፕሊኬሽኖችን መገንባትና አገልግሎት መስጠት ያስችላቸዋል።
🙋 Database Services:- ተቋማት የራሳቸውን ውድ እና ውስብስብ የዳታቤዝ ሲስተሞችን ማቋቋም አይጠበቅባቸውም፤ ይህን አገልግሎት በመጠቀም #በCloud የተመሰረቱ ዳታቤዝ አገልግሎቶችን በቀላሉ ለመጠቀም ያስችለል።
🙋 Enterprise Application:- ይህ የንግድ ተቋማት የሚፈልጓቸውን የተዘጋጁ ሶፍትዌሮች እና አፕሊኬሽኖች በቀጥታ ከCloud ጋር ለማገናኘት የሚያስችል አገልግሎት ነው። ለምሳሌ እንደ የደንበኞች አገልግሎት (CRM)፣ የሂሳብ አያያዝ (ERP) እና ሌሎች የንግድ ሥራዎችን ለማስተዳደር የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮችን ያካትታል።
.
.
.
እያንዳንዱ ከላይ የተጠቀሱት አገልግሎቶች ደግሞ የተለያዩ አማራጮች አሏቸው።
ለምሳሌ #የሁለቱን ልጥቀስላችሁ🙏
1. #የኮምፒውተር_አገልግሎቶች (Computer Services)
ይህ አገልግሎት የሚከተሉትን ያካትታል።
👌 Elastic Cloud Server (ECS):- ይህ አገልግሎት የተፈለገውን ኦፕሬቲንግ ሲስተም (እንደ ዊንዶውስ ወይም ሊኑክስ) መርጣችሁ መጠቀም የምትችሉበት ቨርቹዋል ሰርቨር (Virtual Server) ነው። እንደ ፍላጎታችሁ ሲፒዩ፣ ራም እና ስቶሬጅ በቀላሉ መጨመር ወይም መቀነስ ትችላላችሁ።
👌 Bare Metal Server (BMS):- ይህ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በግል ብቻ የምትጠቀሙበት ፊዚካል ሰርቨር ነው። ከቨርቹዋል ሰርቨር ውጭ ምንም አይነት የመሃል ሶፍትዌር (virtualization layer) የለውም። ከፍተኛ ፍጥነት ለሚጠይቁ ስራዎች ሙሉ ሰርቨሩን ልክ እንደግል ኮምፒዩተር/ላፕቶፕ መጠቀም ይችላል።
👌 Image Management Service (IMS):- ይህ አገልግሎት የሰርቨር ምስል (image) ለመፍጠር፣ ለማስተዳደር እና ለማጋራት ያስችላል። ሰርቨሩን አንድ ጊዜ ካዘጋጁ ትክክለኛ ቅጂ (image) በመያዝ፣ ሌሎች ሰርቨሮችን በፍጥነት ለመፍጠር የሚያስችል ነው።
👌 Auto Scaling (AS):- ይህ አገልግሎት የአፕሊኬሽን ወይም የድረገጽ የትራፊክ ፍሰት በመከታተል፣ ሲጨምር ተጨማሪ ሰርቨሮችን በራሱ ይጨምራል፤ ሲቀንስ ደግሞ ይቀንሳል። (በጣም ወድጄዋለሁ)
---
2. #የክላውድ_ማከማቻ_አገልግሎቶች (Cloud Storage Services)
እነዚህ አገልግሎቶች የሚያካትቱት:-
👉 Elastic Volume Service (EVS):- ይህ አገልግሎት ለECS እና BMS ሰርቨሮች የብሎክ ስቶሬጅ (block storage) ያቀርባል። EVS ልክ እንደ ኮምፒውተር ሃርድ ድራይቭ ነው። በተለይም ሰርቨር ለመጫን እና የፕሮግራሞችን መረጃ ለማስቀመጥ ተመራጭ ነው።
👉 Object Storage Service (OSS):- ይህ አገልግሎት እንደ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች እና ሌሎች ፋይሎችን ለማስቀመጥ ይጠቅማል። OSS ብዙ መረጃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማስቀመጥ ጥሩ አማራጭ ነው።
👉 Scalable File Service (SFS):- ይህ አገልግሎት የብዙ ተጠቃሚዎች መረጃ በአንድ ላይ እንዲቀመጥ ያደርጋል። SFS ልክ በኔትወርክ ላይ እንዳለ ሼር (network share) ይሰራል፤ ይህም ፋይሎችን ከብዙ ሰርቨሮች በአንድ ጊዜ ለመድረስና ለመጠቀም ያስችላል።
.
.
.
#ኢትዮቴሌኮም እነዚህን የዘመኑ አገልግሎቶች በሚያስደንቅ ዋጋ አቅርቦ በአገር ውስጥ ቋንቋዎች በስፋት አለማስተዋወቁ ግርምትና ግርታ የሚፈጥር። ተቆነጃጅቶ ጨለማ ውስጥ መቀመጥ ምን ይሉታል❓ በፍጹም የማይጠበቅ!😪
.
.
.
በግል ወይም በተቋም ደረጃ መጠቀም ለምትፈልጉ ለየትኛው አገልግሎት የትኛውን መምረጥ እንደሚጠበቅባችሁ እና ተያያዥ የምክር አገልግሎቶችን ለአንድ ወር በነጻ እሰጣለሁ። በውስጥ ልታናግሩኝ ትችላላችሁ🙏

❤4👍3🔥1
AlltechUp.com
አሜሪካ የመንግስታ መስሪያ ቤቶች ላማ (Llama) እንዲጠቀሙ ፈቀደች . . .
አሜሪካ የመንግስታ መስሪያ ቤቶች ላማ (Llama) እንዲጠቀሙ ፈቀደች
.
.
.
ላማ (Llama) የተሰኘው የሜታ (Meta) ሰው ሰራሽ ልህቀት ሥርዓት (Ai system) በአሜሪካ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የእለት ተእለት ስራዎች ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ አገኘ
ሮይተርስ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣንን ጠቅሶ ዛሬ እንደዘገበው መንግስት መስሪያ ቤቶች የሜታ ፕላትፎርምስ (Meta Platforms) ላማ (Llama) Ai እንዲጠቀሙ የተፈቀደው የትራምፕ አስተዳደር የንግድ ሰው ሰራሽ ልህቀቶችን በመንግስት ስራዎች ለማካተት የሚያደርጉት ጥረት አካል ነው::
በዚህም መሰረት የአሜሪካ የመንግስት ጠቅላላ አገልግሎት አስተዳደር (General Services Administration - GSA) ላማን በፌደራል መስሪያ ቤቶች ጥቅም ላይ እንዲውል በግዢ ዝርዝር ውስጥ እንደሚያካትት ይፋ አድርጓል::
የአሜሪካ የመስሪያ ቤቶች ላማን በነጻ መሞከር የሚችሉበት ሥርዓት የተዘረጋ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ውስጥ GSA ላማን የመንግስትን የደህንነት እና የህግ መስፈርቶች የሚያሟላ መሆኑን ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል:
ላማ የጽሁፍ፣ የቪዲዮ፣ የምስሎች እና የድምጽን ጨምሮ ማናቸውም ውስብስብ ሥራዎች በፍጥነትና በጥራት የማከናወን አቅም ያለው ትልቅ የቋንቋ ሞዴል (large language model - LLM) ነው።
GSA ከዚህ ቀደም የሜታ ተወዳዳሪዎች የሆኑት አማዞን ዌብ ሰርቪስስ (Amazon Web Services)፣ ማይክሮሶፍት (Microsoft)፣ ጎግል (Google)፣ አንትሮፒክ (Anthropic) እና ኦፕን ኤአይ (Open AI) የመሳሰሉ ድርጅቶች የፈጠሯቸውን የሰው ሰራሽ ልህቀቶች (AIs) በግዢ ዝርዝር ውስጥ ማካተቱን ሮይተርስ በዘገባው አስታውሷል::
ለተጨማሪ ተመሳሳይ መረጃዎች ተቀላቀሉ 👇👇
.
.
.
#Telegram👇
https://t.me/horntechcom
#የፌስቡክ_ገጽ 👇
https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/
Horntech.com - የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ምርጫ - በቅርብ ቀን🚀
Telegram
Horntech.com
Horntech.com የቴክኖሎጂ አለምን ያዳርሳል! 🚀
የቅርብ ጊዜ ፈጠራዎች፣ ጥልቅ ትንታኔዎች፣ ዜናዎች፣ ወርክሾፖች እና ምርጥ የዘርፉ ምርቶችን ይከታተሉን💻📱
ከAI እስከ ፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ ከAi እስከ ጌሚንግ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም መመሪያዎች—ሁሉንም አካትተናል። 💡

👏3👍2🥰1
✅ የAi "ቀይ መስመር" እንዲሰመር ተጠየቀ
.
.
.
200 ታላቅ ሰዎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዓለም አቀፍ "ቀይ መስመር" እንዲሰመር ጥሪ አቀረቡ
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ 8 የቀድሞ የአገራት መሪዎች፣ 10 የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች፣ 70 ዓለም አቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎች፣ እና ሌሎችም 120 ታዋቂ የቴክኖሎጂ ሰዎች በቡድን ባቀረቡት ጥሪ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ላይ ህጋዊ አስገዳጅ ዓለም አቀፍ ገደቦች ካልተጣሉ መጪው ጊዜ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጸዋል።
ከታዋቂ ቴክኖሎጂስቶች መካከል የAi አባቶች በመባል የሚታወቁት ካናዳውያኑ የኮምፒውተር ሳይንቲስቶች ጂኦፍሬይ ሂንተን እና ዮሹዋ ቤንጊዮ (በ2018 በጋራ የዲጂታል ዓለም የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች) እንዲሁም እና የኦፕንኤአይ ተባባሪ መስራች ዎይቺክ ዛረምባ ይገኙበታል።
ለመንግስታት ባቀረቡት ጥሪም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ የስራ አጥነት፣ ሰው ሰራሽ ወረርሽኞች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለመከላከል ዓለም አቀፍ "ቀይ መስመር" እንዲዘረጋ አስገንዝበዋል።
በAi የሚሰሩ የጦር መሳሪያዎች፣ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃቶች እና ከሰው ቁጥጥር ውጭ ማሰብ፣ መስራትና መፈጸም የሚችል ጠቅላላ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AGI) እንዲታገዱም በአጽንኦት ጠይቀዋል።
ለዚህም ሲባል በ2026 መጨረሻ ላይ ዓለም አቀፍ የቁጥጥር አካል እንዲቋቋም እና በመመሪያዎቹ ላይ ስምምነት እንዲደረስም አሳስበዋል።
.
.
.
ለተጨማሪ ተያያዥ መረጃዎች ተቀላቀሉ 👇
🙏🙆
#Telegram👇
https://t.me/horntechcom
#የፌስቡክ_ገጽ 👇
https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/
❤4
AlltechUp.com
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ . . . 🚀
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ . . .
ገመና ለማየት የሚንጋጋ ህዝብ ሁልጊዜ የወጥመድ ሰለባ ነው። ቁምነገር ሲጋራ ዞር ብሎ የማያይ ህዝብ የሴት ራቁት ሲባል ይርመሰመሳል። (ምን ያህል ሰው #React ፣ ምን ያህል #Comment እና ምን ያህል #Share እንዳደረገ ተመልከቱ - በነገራችን ላይ ይሄን #Mekdii የሚል አካውንት Unfollow በማድረግ ራሳችሁን አርቁ)
የሆነው ሆኖ #Comment ላይ የተቀመጠው ማስፈንጠሪያ (#link) (is.gd/j72BFq) የቴሌግራም አይደለም:: የቴሌግራም ሊንክ '#በt.me . . . ' ነው የሚጀምረው::
ይህ ማስፈንጠሪያ (#link) አጭር ሊንክ (Shortened URL) ሲሆን is.gd በሚባለው አጭር ሊንኮችን ለመፍጠር የሚያገለግል ታዋቂ አገልግሎት ሰጪ ድረ ገጽ የተቀየረ ነው። አጭር ሊንኩ ወደ የትኛው ድረ-ገጽ እንደሚያመራ ወይም Redirect የሚሆንበት ድህረ ገጽ URL expander ወይም URL unshortener ላይ አስገብተን ስናረጋግጥ https://www.google.com/search?q=obqj2.com ሆኖ እናገኘዋለን:: ይሁን እንጁ ይህ የድረገጽ አድራሻ ምን ሊሆን እንደሚችል በማየት ብቻ ማረጋገጥ አይችልም::
-----
ሆኖም ግን የፌስቡክ ገጹ በራሱ በማማለል ለማጭበርበር የተዘጋጀ እንደሆነ የሚያመላክቱ ይዘቶች በብዛት ስላሉት የተጠቀሰው ማስፈንጠሪያ (#link) አደገኛ የመሆን እድሉ እጅግ ሰፊ ነው::
#አደገኛ ሲባል:-
1. የማልዌር (Malware ድህረ ገጽ:-
ይህ ማለት ስትነኩት ወደ ኮምፒውተራችሁ ወይም ስልካችሁ ቫይረስ ወይም ሌላ አደገኛ ሶፍትዌር የሚያስገባ ድህረ ገጽ ሊሆን ይችላል::
2. የፊሺንግ (Phishing) ድህረ ገጽ:-
የግል መረጃችሁን (የይለፍ ቃል/Password፣ የቴሌ ብር፣ የባንክ መረጃ . . . ) ለመስረቅ የተዘጋጀ ሐሰተኛ ድህረ ገጽ ሊሆን ይችላል::
3. አፀያፊ ወይም የማይፈለግ ይዘት (Obscene or Unwanted Content):- የራቁትና የወሲብ ወይም ሌሎች ከሞራልና ከስነምግባር የሚቃረኑ ይዘቶች የሚጋሩበት ሊሆን ይችላል::
#ማድረግ_የሌለባችሁ
ማስፈንጠሪያውን (Linkን) ከመንካት ተቆጠቡ:: በፌስቡክ የምታገኙት ተመሳሳይ ማስፈንጠሪያም ሆነ መንነቱ ከማይታወቅ ሰው በEmail፣ በWhatsApp፣ በTelegram ወይም በሌላ መንገድ የሚላኩላችሁን አጠራጣሪ ሊንኮች በፍጹም አትንኩ። ምንም የሚያጓጓ ነገር በሌለበት ሁኔታ ወይም የማታውቁት/የሌላችሁ ነገር የተጋራ ይመስል በመንጋ መንጋጋትም አግባብ አይደለምና ረጋ ብትሉ ቅቤ ይወጣችኋል። 👌
.
.
.
🙋ለተጨማሪ ተያያዥ መረጃዎች ተቀላቀሉ 👇
🙏🙆
#Telegram👇
https://t.me/horntechcom
#የፌስቡክ_ገጽ 👇
https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/
#Horntech #Technology #Innovation #Ethiopia

www.google.com
🔎 obqj2.com - Google Search
❤5👍1
ምን ትላላችሁ❓🙋
.
.
.
ምንም እንኳን ልብስ ሰፊ በሚያስንቁ ባለሙያዎች (ማዝገም) ምክንያት እንዳቀድኩት ባይፈጥንልኝም/ባይሆንልኝም ከቴክኖሎጂ፣ Ai እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከማዘጋጀው ድረገጽ በመቀጠል #ticktock እና #Youtube የመጀመር ሀሳቡ አለኝ። ይሁን እንጂ በተለይም በርካታ ሰዎች #በAi ዙሪያ ያለውን አስደናቂ ፈጣን ለውጥ ማወቅና መጠቀም ጊዜ የማይጠይቅ በመሆኑ ፍላጎት ካላችሁ በአንድ ሳምንት ውስጥ #ticktock እጀምራለሁ። (100 ኮሜንት ላይ ከደገፋችሁ ልክ የዛሬ ሳምንት እጀምራለሁ - ቀኑን Save አድርጉ)
ከተች ያለው ፎቶግራፍ #Ai እንዴት እንደለወጠው ተመልከቱ፤ እናንተም በትንሽ ተጨማሪ እውቀት የተቀደደ የድሮ ፎቷችሁን ሳይቀር መመለስ ትችላላችሁ።

👍3🥰3👏1
AlltechUp.com
የዊንዶውስ 10 መዘጋት (Crash) መንስኤዎች እና መፍትሄዎች . . .
የዊንዶውስ 10 መዘጋት (Crash) መንስኤዎች እና መፍትሄዎች
.
.
.
ዊንዶውስ 10 ድንገት ሊዘጋ (Crash ሊያደርግ) የሚችልባቸውን ሰባት ዋና ዋና ምክንያቶች እና ለእያንዳንዱም ትክክለኛ መፍትሄዎች ከዚህ በታች ቀርበዋል፦
---
🙋 1. የሙቀት መጨመር (Overheating)
ኮምፒውተርዎ ከልክ በላይ ሲሞቅ ስርዓቱን ከጉዳት ለመጠበቅ በራሱ ሊዘጋ ይችላል።
* መንስኤ: - የአየር ማናፈሻ ቀዳዳዎች መዘጋት፣ የአቧራ ክምችት፣ ወይም የማቀዝቀዣ ስርዓት (Fan) ብልሽት ሊሆን ይችላል።
መፍትሄዎች:-
* የኮምፒውተርዎን አየር ማናፈሻ ቀዳዳዎች ሁልጊዜ ንጹህ መሆናቸውን ያረጋግጡ።
* ኮምፒውተሩን ለስላሳ ቦታዎች (እንደ አልጋ ወይም ሶፋ) ላይ ከመጠቀም ይቆጠቡ።
* በየጊዜው የኮምፒውተርዎን ውስጠኛ ክፍል አቧራ ያጽዱ።
* ለላፕቶፖች የማቀዝቀዣ ፓድ (Cooling Pad) ይጠቀሙ።
---
🙋 2. የተበላሹ ወይም ያረጁ ድራይቨሮች (Outdated or Faulty Drivers)
ድራይቨሮች ሃርድዌርዎ ከዊንዶውስ ጋር በትክክል እንዲግባባ ያደርጋሉ። ሲበላሹ ወይም ሲያረጁ ስርዓቱ ሊዘጋ ይችላል።
* መንስኤ: - አዲስ የዊንዶውስ ዝመና፣ የተበላሸ የድራይቨር ጭነት ወይም ጊዜ ያለፈባቸው ድራይቨሮች
* መፍትሄዎች :-
ወደ Device Manager ይሂዱ እና ችግር ያለባቸውን ድራይቨሮች ያዘምኑ (Update ያድርጉ)።
* የቅርብ ጊዜው ድራይቨር ችግር ካመጣ፣ ወደ ቀድሞው ስሪት ይመለሱ (Roll Back Driver ያድርጉ)።
* የሃርድዌር አምራች (ለምሳሌ፡- NVIDIA፣ AMD፣ Intel) ድረ-ገጽ በመሄድ የቅርብ ጊዜውን ድራይቨር አውርደው ይጫኑ።
---
🙋 3. የሃርድዌር ብልሽት (Hardware Malfunction)
የኮምፒውተርዎ ዋና አካላት ሲበላሹ ዊንዶውስ ሊዘጋ ይችላል።
* መንስኤዎች : - የራም (RAM) ችግሮች፣ የሃርድ ድራይቭ/ኤስኤስዲ (HDD/SSD) መበላሸት፣ ወይም የኃይል አቅርቦት ክፍል (PSU) ብልሽት ሊሆን ይችላል።
* መፍትሄዎች:-
* ራም (RAM):- የዊንዶውስ Memory Diagnostic Tool (የማስታወሻ ምርመራ መሣሪያ) በመጠቀም ራምዎን ይሞክሩ።
* ሃርድ ድራይቭ/ኤስኤስዲ :- የዊንዶውስ Check Disk (chkdsk) ትዕዛዝን በመጠቀም ሃርድ ድራይቭዎን ለስህተቶች ይፈትሹ።
* PSU :- የሃይል አቅርቦትዎ በቂ ሃይል መስጠቱን ወይም አለመሆኑን ያረጋግጡ። በብልሽት ከተጠረጠረ በአዲስ ይተኩት።
* እርግጠኛ ካልሆኑ ባለሙያ ያማክሩ።
---
🙋4. ብዙ ፕሮግራሞችን በአንድ ጊዜ መክፈት (Too Many Programs Running)
በአንድ ጊዜ ብዙ ሃይል የሚጠይቁ ፕሮግራሞችን ሲከፍቱ ኮምፒውተሩ ከመጠን በላይ ይጫናል።
* መንስኤ:- በቂ ያልሆነ ራም፣ ወይም ሲፒዩ (CPU) በከፍተኛ አቅም መስራት ነው።
* መፍትሄዎች :- Task Manager ይክፈቱ እና ብዙ ሲፒዩ (CPU) ወይም ሜሞሪ (Memory) የሚጠቀሙ ፕሮግራሞችን ይዝጉ።
~ አስፈላጊ ከሆነ የኮምፒውተርዎን ራም ይጨምሩ።
~ በሚሰሩበት ጊዜ አላስፈላጊ የሆኑ የጀርባ ፕሮግራሞችን (Background Apps) ያጥፉ።
---
🙋 5. የሶፍትዌር አለመጣጣም (Software Conflicts)
* መንስኤ : - ሁለት ፕሮግራሞች ወይም አንድ ፕሮግራም ከዊንዶውስ ጋር በትክክል መስራት ሲያቅተው ወይም አዲስ የተጫነ ሶፍትዌር ወይም ዝመና/Update ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር አለመስማማት ነው።
* መፍትሄዎች :- ችግሩ የጀመረው አዲስ ፕሮግራም ከጫኑ በኋላ ከሆነ ያንን ፕሮግራም ያጥፉ ወይም Uninstall ያድርጉ።
* ፕሮግራሙን በአስተዳዳሪነት (Run as Administrator) ለመክፈት ይሞክሩ።
* የፕሮግራሙን Compatibility Mode (የተጣጣሚነት ሁኔታ) በመጠቀም በድሮው የዊንዶውስ ስሪት ላይ እንዲሰራ አድርገው ይክፈቱት።
---
🙋 6. የተበላሹ የስርዓት ፋይሎች (Corrupted System Files)
ዊንዶውስ ለመስራት የሚጠቀምባቸው ወሳኝ ፋይሎች ሲጎዱ።
* መንስኤ : - ያልተጠበቀ መዘጋት፣ የሃርድዌር ብልሽት፣ ወይም የተበላሸ የሶፍትዌር ጭነት።
* መፍትሄዎች : -
* System File Checker (SFC) ትዕዛዝን ይጠቀሙ። Command Promptን በአስተዳዳሪነት ይክፈቱ እና
* DISM መሳሪያውን ይጠቀሙ። ከ
---
🙋 7. ቫይረሶች ወይም ማልዌር (Viruses or Malware Attacks)
* መንስኤ : - አደገኛ ሶፍትዌሮች ዊንዶውን በማጥቃት ኮምፒውተሩን ሊያዘጉት ይችላሉ። መንስኤውም ተንኮል አዘል ድረ-ገጾችን መጎብኘት ወይም አጠራጣሪ ፋይሎችን ማውረድ ነው።
* መፍትሄዎች : - የተሟላ እና የዘመነ አንቲቫይረስ ፕሮግራም (እንደ Windows Defender) በመጠቀም ኮምፒውተርዎን ሙሉ በሙሉ ይመርምሩ (Full Scan) ያድርጉ
* የስርዓትዎ ፋየርዎል (Firewall) ሁልጊዜ በርቶ መሆኑን ያረጋግጡ።
* ከማይታመኑ ምንጮች ሶፍትዌር አይጫኑ።
---
እነዚህን መፍትሄዎች በቅደም ተከተል በመጠቀም የዊንዶውስ 10ን የመዘጋት ችግር መፍታት ይችላሉ። ችግሩ ከቀጠለ፣ ምናልባት ዊንዶውስን እንደገና መጫን (Format/Reinstalling Windows) የመጨረሻው መፍትሄ ሊሆን ይችላል።

sfc /scannow ብለው ይጻፉ። ይህ የተበላሹ ፋይሎችን ይጠግናል።* DISM መሳሪያውን ይጠቀሙ። ከ
sfc በፊት DISMን ማስኬድ ጥሩ ነው።---
🙋 7. ቫይረሶች ወይም ማልዌር (Viruses or Malware Attacks)
* መንስኤ : - አደገኛ ሶፍትዌሮች ዊንዶውን በማጥቃት ኮምፒውተሩን ሊያዘጉት ይችላሉ። መንስኤውም ተንኮል አዘል ድረ-ገጾችን መጎብኘት ወይም አጠራጣሪ ፋይሎችን ማውረድ ነው።
* መፍትሄዎች : - የተሟላ እና የዘመነ አንቲቫይረስ ፕሮግራም (እንደ Windows Defender) በመጠቀም ኮምፒውተርዎን ሙሉ በሙሉ ይመርምሩ (Full Scan) ያድርጉ
* የስርዓትዎ ፋየርዎል (Firewall) ሁልጊዜ በርቶ መሆኑን ያረጋግጡ።
* ከማይታመኑ ምንጮች ሶፍትዌር አይጫኑ።
---
እነዚህን መፍትሄዎች በቅደም ተከተል በመጠቀም የዊንዶውስ 10ን የመዘጋት ችግር መፍታት ይችላሉ። ችግሩ ከቀጠለ፣ ምናልባት ዊንዶውስን እንደገና መጫን (Format/Reinstalling Windows) የመጨረሻው መፍትሄ ሊሆን ይችላል።
❤5🥰1
AlltechUp.com
ቻትቦት እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
ቻትቦት እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
---
ብዙዎች 🤖 ቻትቦት (Chatbot) እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) አንድ ይመስላቸዋል፤ ነገር ግን ሁለቱ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሲሆኑ ተመሳሳይነትም ከፍተኛ ልዩነትም አላቸው።
✅ ተመሳሳይነታቸው
1. አውቶሜሽን - ሁለቱም የሰውን ድካም ለመቀነስና ስራዎችን በራሳቸው (Auto) ለማከናወን የተፈጠሩ ናቸው።
2. የመረጃ ሂደት - ሁለቱም የተሰጣቸውን መረጃ ወይም ትዕዛዝ ተንትነው ምላሽ ይሰጣሉ።
3. ግንኙነት - በጽሁፍ ወይም በድምፅ ከሰው ጋር መገናኘትና መረጃ መለዋወጥ ይችላሉ።
---
⚖️ ዋና ዋና ልዩነታቸው
1. አሰራር
ቻትቦት - አስቀድሞ በተሰጠው ደንብ (Rules) ወይም ስክሪፕት ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው። ልክ እንደ ባቡር ሀዲድ ከተሰመረለት መስመር ውጭ መውጣት አይችልም።
AI - ልክ እንደ ሰው አእምሮ የመማርና የመላመድ ችሎታ አለው። መረጃዎችን በማገናኘት አዳዲስ ግንዛቤዎችን ይፈጥራል።
2. የመማር ብቃት
ቻትቦት - አዲስ ነገር በራሱ አይማርም። አዲስ መረጃ እንዲያውቅ ከተፈለገ ድጋሚ በባለሙያ ፕሮግራም መደረግ አለበት።
AI - በሂደት ከሚመጡ መረጃዎች ራሱን ያስተምራል:: በተጠቀሙበት ቁጥር የመረዳትና የተሻለ ምላሽ ብቃቱ ይጨምራል።
3. የጥያቄ አቀባበል
ቻትቦት - "አዎ" ወይም "አይደለም" የሚሉ ግልጽ ምርጫዎች ላይ የተመሰረተ ምላሽ ይሰጣል።
AI - ውስብስብ ጥያቄዎችን ይረዳል፤ የቃላትን ፍሰትና ስሜትን (Context) ይለያል።
---
#ምሳሌ :-
አንድ የባንክ ወይም የውሃና ፍሳሽ ቴሌግራም ቦት ሂሳብ ሲጠየቅ "1" ቁጥርን ወይም ቀድሞ የተጫነውን ተጫን ይልላል። "1" ስትጫኑ ሂሳባችሁን ይናገራል። ነገር ግን "ዛሬ ደስተኛ አይደለሁም" ብትሉት ምን ማለት እንደሆነ ሊገባው አይችልም፤ ምክንያቱም ያ አልተፃፈለትም፤ አያውቀውም።
በአንጻሩ AI "ዛሬ ደስተኛ አይደለሁም" ብትሉት ስሜታችሁን ይረዳል፤ "ለምን? ምን ተፈጠረ? ላበረታታህ እችላለሁ?" የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ይጠይቃችኋል። ጥያቄው ግልጽ ሲሆንለትም ከሰው የተሻለ ምላሽ ይሰጣል። ከተሳሳተም ጥያቄውን ይበልጥ ግልጽ በማድረግ ምላሹን ያሻሽላል።
#Technology #AI #Chatbot #Horntech #AmharicTech #ArtificialIntelligence #Ethiopia #TechTips #digital2030

👍5❤1