Forwarded from Awda Hasab - አውደ ሓሳብ (vvbat)
#ከምኞት ወደ #እውነት - 2018❗
("ሰው ያስባል - ያቅዳል፤ እግዚአብሄር ይፈጽማል")
.
.
.
". . . ምኞቴማ የትና የት
ሰው ሊያደርገኝ የቃጣበት
የጠወለገው የተስፋ ዕፅ በምኞት ካቆጠቆጠ
የተጣለው መጋረጃ በተስፋ ከተገለጠ
የትና የት! የትና የት!
አካሌ ተወሰነ እንጂ በነባራዊው ሒደት!"
ከበደች ተክለአብ “የት ነው?” /1983/ የግጥም መድብል "የትና የት" በሚል ርዕስ ከጻፈችው ግጥም የተቀነጨበ አንጓ ነው::
በሶማሊያ እስር ቤት የተጻፉት የከበደች ግጥሞች ስሜት ጎርጓሪ፣ አጥንት ሰርሳሪ፣ እውነት አብሳሪ ናቸው:: ማንሳት የፈለግኩት ግን ስለከበደች እና ግጥሞቿ አይደለም፤ ስለራሴው ነው። ምኞቴ እና ሀሳቤማ የት የት . . . ለማለት ነው፤ ገጣሚዋ እንዳለችው "አካሌ ተወሰነ እንጂ በነባራዊው ሒደት!" እቅዴማ፣ ጥረቴማ . . . የትና የት . . . ::
ነገሩ ሁሉ እናንተም "ሰው ያስባል - ያቅዳል፤ እግዚአብሄር ይፈጽማል" እንደምትሉት ሆነ እንጂ በእርግጥም ውስጤ ያለውማ የትና የት . . .
.
.
.
🤗
Forwarded from Awda Hasab - አውደ ሓሳብ (vvbat)
Awda Hasab - አውደ ሓሳብ
#ከምኞት ወደ #እውነት - 2018❗ ("ሰው ያስባል - ያቅዳል፤ እግዚአብሄር ይፈጽማል") . . . ". . . ምኞቴማ የትና የት ሰው ሊያደርገኝ የቃጣበት የጠወለገው የተስፋ ዕፅ በምኞት ካቆጠቆጠ የተጣለው መጋረጃ በተስፋ ከተገለጠ የትና የት! የትና የት! አካሌ ተወሰነ እንጂ በነባራዊው ሒደት!" ከበደች ተክለአብ “የት ነው?” /1983/ የግጥም መድብል "የትና የት" በሚል ርዕስ ከጻፈችው…
#ከምኞት ወደ #እውነት - 2018❗
("ሰው ያስባል - ያቅዳል፤ እግዚአብሄር ይፈጽማል")
.
.
.
በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ቢሆንም ወደዓለም ተጠግቶ ከመራመድ አንጻር ግን እጅግ ሰፊ ክፍተት ነው ያለው።
የችግሩ መሰረታዊ መንስኤ ደግሞ የዘርፉ መረጃዎች የሚገኙት አብዛኛው ህዝባችን አቀላጥፎ በማይችላቸው የውጭ ቋንቋዎች መሆኑ ነው። ብዙዎቻችሁ ደጋግማችሁ የምትገልጹልኝ እና እኔም በተጨባጭ እንደማስተውለው ችግሩ እጅግ ሰፊ እና ጥልቅ ነው:: ይህም ብዙዎች ቴክኖሎጂ ነክ ጉዳዮችን በተሻለ ሁኔታ እንዳይረዱ፣ ክህሎት እንዳይጨብጡና እንዳይጠቀሙ እንቅፋት ሆኖባችኋል።
ስለሆነም በተለያዩ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች መረዳት በሚያስችል ቀላል መንገድ ቢቀርብ ክፍተቱን ከማጥበብ ባለፈ ለቋንቋዎቹ እድገትም ወሳኝ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ገበያን በማጠናከር፣ የፈጠራ ሥራዎችን በማበረታታት እና የዲጂታል ኢትዮጵያ ግብን በማሳካት ረገድም የማይተካ ድርሻ ይኖረዋል።
ከዚህና ከምታቀርቡልኝ ጥያቄዎች/ሀሳቦች በመነሳት ወደ ስራ ለመግባት ቢዝነስ ፕላን ያዘጋጀሁት ከአራት ወራት በፊት ነበር።
በግልጽ ባላሳውቃችሁም ከጉዳዩ ጋር በተያያዛ ጠቋሚ መረጃዎች አጋራችሁ እንደነበርም የሚታወቅ ነው።
ባዘጋጀሁት ቢዝነስ ፕላን መሰረት ቀድሜ ለመጀመር ያቀድኩት #ድረገጽ ነው። ከድረገጹ በመቀጠል በስድስት ወራት ውስጥ #ቲክቲክ እና #ዩቱዩብ የመጀመር መርሃ ግብር ነበረኝ።
#ድረ_ገጽን አማርኛ፣ ኦሮምኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን በቀጥታ (#Auto) እንዲተረጉም ነበር። ነገር ግን ስራው ከተጋመሰ በኋላ በክፍያ #የgoole_Cloud መጠቀም ግድ እንደሆነ ከመታወቁም በላይ ትርጉሙም ቢሆን የተሟላ እንዳልሆነ (Goole translator የሚተረጉመው ዓይነት እኔም ባለሙያቹም አረጋገጥን:: ትክክለኛ ትርጉም የሚሆነው ቋንቋውን ከማወቅ ባለፈ የቴክኖሎጂ ቃላትን መረዳትና መግለጽ የሚችሉ ባለሙያዎች በመጠቀም እንደሆነ ታመነበት::
ከዚህ በመነሳት ከወጪ አንጻር በሂደት ሌሎች ቋንቋዎችን ለማካተት በማሰብ ለጊዜው በአማርኛ ቋንቋ ብቻ ስራው ቀጥሏል::
ይሁንና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ፣ ስራውን ለማሳደግ፣ ሌሎች ቋንቋዎችንም (ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ አፋርኛ እና ሶማሊኛ) ለማካተት የሚያስችሉ ባለሙያዎችን ለመቅጠር እንዲሁም በቲክቶክ እና በዩቱዩብ ስራዎች የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ሲባል ከነፃ መረጃዎች ባሻገር የክፍያ (Subscription/Premium) ሥርዓት ማካተት አስፈላጊ ሆኗል። የአገር ውስጥ እና የውጭ ድጋፍ (Donation)ን ጨምሮ የማስታወቂያ ክፍያዎችም የተካተቱበትም ይሆናል።
በነገራችን ላይ አንድ ሰው Subscribe ሲያደርግ በቀጥታ መለያ #Code ይደርሰውና ሌሎችን ኮዱን እያስገቡ Subscribe እንዲያደርጉ የሚያስችልና ኮሚሽን የሚያገኝበት ነው። በኮዱ Subscribe ከሚያደርጉት ብቻ ሳይሆን የጋበዛቸው ከሚጋብዟቸውም የማይቋረጥ ገንዘብ የሚያገኝበት ይሆናል። እነዚህ ስራዎች ከታቀደው በላይ ጊዜ ጠይቀዋል።
ከዚህ ጎን ለጎንም ህጋዊ የገንዘብ ልውውጥ ስርዓት ውስጥ መግባት ግድ በመሆኑ ፍቃድ የማውጣት፣ ምዝገባዎችን የማድረግ፣ ከቴሌ Api ወስዶ #ቴሌብር የመጠቀም ስራዎች ተጀምረዋል።
#የSubscriptoin ክፍያን በተመለከተ ማንም ሰው መክፈል በሚችለው ደረጃ እጅግ ዝቅ በማድረግ ብዙ ተጠቃሚ የማግኘትና ጉድለቱን ከማስታወቂያ የመሸፈን ስትራቴጂ የሚከተል ይሆናል። እስከአሁን ባለው እቅድ በወር #ከብር 7 (በዓመት 210 ብር) ለማድረግ ነው። በቀጣይም ቢሆን የእናንተን አስተያየት መነሻ በማድረግ ከበዛ የመቀነስ እንጂ የሚጨመር አይኖርም። ምክንያቱም ዋና ግቤ #ብዛት! ነው። (እናንተን ይዤ በሁለት ወራት 100,000 በዓመት አንድ ሚሊዮን #Subscribers መድረስ ነው - ዋና ግቤ። እናንተ ከጎኔ እስካላችሁ ከፈጣሪ ፍቃድ ጋር እንደማሳካው እርግጠኛ ነኝ)
በተጨማሪም በማንኛውም መጠን ማበረታታትና መደገፍ የሚፈልጉ #Donate ማድረግ ስለሚችሉ የሚያንስ አይኖርም።
የሆነው ሆኖ አጠቃላይ ሂደቱን በማጠናቀቅ ቢያንስ በአዲስ ዓመት መባቻ ለሙከራ ማጋራት ባለመቻሌ በጣም ተከፍቻለሁ። ምንምን እንኳን በእያንዳንዱ ምድብ (Category) የሚጋሩ ጽሁፎች አዘጋጅቼ የነበረ ቢሆንም የድረ ገጹ አጠቃላይ ግንባታ ባለመጠናቀቁ "ሀሳቤማ፣ እቅድማ የትና የት . . . " እንድል አስገድዶኛል።
በዚህ አጋጣም የድረገጹ የመረጃ ምድብምድቦች/Categories/ አቢይ ርዕስ (In-depth Analysis)፣ ዜናዎች (News)፣ ወርክሾፕ (Workshop)፣ የቴክኖሎጂ ግምገማ (Product Review)፣ የአጠቃቀም መመሪያዎች (How-to Guides)፣ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ (FinTech)፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ ጨዋታ (Gaming)፣ እና ቅምሻ (Tips) ያካትታል።
👉 የሰው ኃይልና ቁሳቁስ ስለሚጠይቅ ለጊዜው ባይጀመርም በአጭር ጊዜ ውስጥ #ቃለምልልስ (Interview) ይካተትበታል። ይህ ምድብ ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ኤክስፐርቶች፣ ስኬታማ ስታርትአፖች፣ የቴክኖሎጂ ተቋማት ስራ አስኪያጆች፣ ምሁራን ስፔሻላይዝ ባደረጉበት ጉዳይ አጠር ያለ ቃለ ምልልስ የሚቀርብበት ይሆናል።
በተጨማሪም በእናንተ እና በባለሙያዎች አስተያየት ላይ በመመስረት የሚደመሩ (አንድ ላይ የሚሆኑ)፣ የሚቀነሱ፣ የሚሻሻሉ፣ ሌሎች የሚጨመሩ ይኖራሉ።
ትልቅ ነገር እንዳልም - በተግባር እንድነሳሳ - ስላደረጋችሁኝ፣ ስለገፋፋችሁኝ፣ አንዳአንዶቻችሁም ስለጨቀጨቃችሁኝ . . . የማመሰግንበት ቃላት የለኝም።
.
.
.
በመጨረሻም 2018 የይቅርታ የመቀራረብ፣ የመተማመን፣ የአንድነት፣ የትጋት፣ የብልፅግና፣ የስኬት እና የፍቅር ዓመት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ። (በዚህ አጋጣሚ በማወቅ ወይም ባለማወቅ ያስቀየምኳችሁ፣ ያስከፋኋችሁ፣ ቅር ያሰኘኋችሁ ሁሉ . . . ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ🙏)
በድጋሚ ከነተወዳጅ ቤተሰቦቻችሁ እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ❗🤗
❤3
AlltechUp.com
"ዓለምን የሚገዛው የ27 ዓመት ታዳጊ ንጉስ"
"ዓለምን የሚገዛው የ27 ዓመት ታዳጊ ንጉስ"
በታሪክ "ቡርዧ" የሚለው ቃል በኢንዱስትሪ አብዮት ወቅት የነበሩትን የካፒታሊዝም ባለሀብቶች፣ የመሬት ከበርቴዎች እና የንግድ ሞኖፖሊስቶች . . . ያመላክታል። በአብዛኛው አያሌ ሰራተኞችን በአነስተኛ ክፍያ ቀጥረው ጉልበትና እውቀት በዝባዦች ተደርገው ይገለጻሉ።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ "ቴክ ቡርዧ" (Tech Bourgeoisie) የሚል አዲስ ቃል ተከስቷል። የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪውን በከፍተኛ ደረጃ የሚቆጣጠሩ፣ የሚያንቀሳቅሱ እና ከፍተኛ ትርፍ የሚያጋብሱ በኃያላን አገራት ሳይቀር (ጂኦግራፊያዊ ድንበሮች የማይገድባቸው) ከፍተኛ ፖለቲካዊ ተፅእኖ የሚፈጥሩ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን ወይም ድርጅቶችን ያካትታል። አንዳአንዶች '#ቴክ_ማፈያ (Tech Mafia)' በማለት የሚጠሯቸው ሲሆን ዋና ዙፋናቸው #ሲሊከን_ቫሊ (Silicon Valley), ካሊፎርኒያ, አሜሪካ ይገኛል።
በዚህ ቦታ ከተከማቹት የዘመናዊው ቴክኖሎጂ ዓለም ገዢዎች መካከል Google (Alphabet Inc.)፣ Apple፣ Meta Platforms (Facebook)፣ Nvidia እና Intel ይገኙበታል።
በዚህ ጽሁፍ Google የሚባለውን የ27 ዓመት እድሜ ያለው የዓለም ገዢ ላስተዋውቃችሁ። ጎግል ላይ ያለው መረጃ እንደሚጠቁመው Google መስከረም 4, 1998 ነው የተመሰረተው። የያዝነው ወር መረጃ እንደሚያመላክተው አጠቃላይ የሀብቱ መጠን $2.84 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ደርሷል።
በቴክኖሎጂው ዓለም ውስጥ አብዮታ ከሳች ተደርጎ የሚቆጠረው ጎግል ዘርፈ ብዙ ንጉስ ነው። ጎግል አሲስታንት (Google Assistant)፣ ጎግል ፎቶስ (Google Photos) እና ጎግል ትራንስሌት (Google Translate) ያካተተው የፍለጋ ኢንጅን (search engine)፣ ቴንሰር ፍሎው (TensorFlow) እና ጀሚኒ (Gemini) የመሳሰሉ የላቁ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎች፣ የAI ቺፖች (TPUs) ወይም የሃርድዌር ልማት፣ የክሎውድ አገልግሎት (Cloud Services)፣ የአልፋቤት (Alphabet Inc.) . . . በመሳሰሉት ታላቅ የገዢነት ዙፋን የተቆናጠጠ ወጣት ንጉስ ነው።
የጎግል የእናት ኩባንያ የሆነው አልፋቤት (Alphabet)፣ ከሴፕቴምበር 2021 እስከ ሰኔ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ 1.5 ቢሊዮን ዶላር በብሎክቼይን ላይ ኢንቨስት አድርጓል። ይህም በምድራችን ከሚገኙ ይፋዊ ኩባንያዎች ትልቁ ኢንቨስትመንት እንደሆነ ተነግሯል።
ይህ ኢንቨስትመንት ለብሎክቼን መሰረተ ልማት ( Block chain infrastructure)፣ ለዲጂታል ንብረት ማከማቻ (digital asset custody) እና ለዌብ3 (Web3) ጨዋታዎች የወጣ እንደሆነ ተነግሯል።
በተጨማሪም የጎግል ክላውድ (Google Cloud) አገልግሎቶችን ለብሎክቼይን ኖዶች (blockchain nodes) ገንቢዎች የEngine አገልግሎት ይሰጣል። በቅርቡም ጎግል ክላውድ አዲስ የብሎክቼይን መድረክ የሆነውን Google Cloud Universal Ledger (GCUL) ስራ አስጀምሯል። ይህም በዋናነት ለፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አቻና ተወዳዳሪ የለውም። በቀጣይነትም ጎግል የክሪፕቶፕስ (cryptos) አጠቃቀምና ደህንነት ለማረጋገጥ፣ የጎግል መለያዎችን በመጠቀም የቢትኮይን (Bitcoin) ቦርሳዎችን (wallets) እንዲያገኙ እና የክሪፕቶ ክፍያዎች ከGmail ወይም Google Pay ጋር በሚመሳሰል ቀላልነት ክፍያዎች እንዲፈፀሙ ለማድረግ ከፍተኛ በጀት መድቦ እየሰራ ነው።
በአጠቃላይ ጎግል የዘመናዊው ዓለምን የስልጣን እና የተፅዕኖ መመዘኛዎች በከፍተኛ ፍጥነት ከመሰረቱ የለዋወጠ ነው።
ጎግል በተለመደው ባህላዊ መንገድ ባይነግስም በዲጂታል ዓለም ባለው እጅግ የላቀ ስልጣን በማያጠራጥር "ንግስናው" የዓለምን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በከፍተኛ ደረጃ እየቀረጸ ይገኛል። ይህም የኃይል ማዕከላዊነት፣ የፖለቲካ ጣልቃገብነት፣ የግላዊነት ስጋቶች እና የሥነ-ምግባር ጥያቄዎች በስፋት የሚያስነሳ ሆኗል።
.
.
.
እንዲህ ዓይነቱ ንጉስን የ27 ዓመት "ጎረምሳ" ብሎ ማጣጣል ግሳፄ ሳይሆን ኩናኔም ሊያስከትል እንደሚችል ለብዙዎቻችን ግልጽ ነው።
❤8
የክሪፕቶ ዘገባዎችን ስናጋራበት የነበረው ይህ ቻናል በቀጣይነትና በዘላቂነት የቴክኖሎጂ እና ተያያዥ ምርጥ መረጃዎችን የምናጋራበት ይሆናል።
❤2
ማይክሮሶፍት በAI የታገዘ ሳይበር ደህንነት ይፋ አደረገ
ማይክሮሶፍት በሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) የታገዘ የደህንነት ስርዓት አስተዋወቀ።
በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ስር ነቀል ለውጥ የተባለለት ይህ የማይክሮሶፍት ሴኪዩሪቲ ኮፓይሎት (Microsoft Security Copilot) የተሰኘ ስርዓት የደህንነት ስጋቶችን በአስተማማኝነት መከላከል የሚያስችል ነው።
በተለይም በራሱ ተነሳሽነት፣ ሊከሰቱ የሚችሉ የደህንነት ጉድለቶችን፣ ስህተቶችን እና የኮምፒዩተር ቫይረሶችን ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት መለየት እና ማጥፋት መቻሉ አስደናቂ አድርጎታል።
በተለይም የማልዌር አይነቶችን በተናጠል የመለየት፣ የመተንተን እና የማጽዳት ልዩ ችሎታው በሳይበር ደህንነት ዘርፍ አዲስ እመርታ ተደርጎ ተቆጥሯል።
ይህ ሥርዓት የሳይበር ደህንነት ብቻ ሳይሆን በኮድ ውስጥ የሚያጋጥሙ የደህንነት ስህተቶችን (bugs) በፍጥነት ለይቶ በማሳወቅ እና በማስተካከል ለሶፍትዌር ፕሮግራመሮች ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ታውቋል።
ምንጭ - #Geekwire

GPT-5 በiOS 26 ይካተታል
አፕል iOS 26ን ከGPT-5 ጋር እንደሚያዋህድ አስታወቀ።
አፕል በሚቀጥለው ወር ከiPhone 17 ጋር አብረው በሚለቀቁት iOS 26፣ iPadOS 26 እና macOS Tahoe 26 ውስጥ GPT-5 እንደሚካተትበት ገልጿል።
ይህ ውህደት "Apple Intelligence" የተሰኘው የአፕል ሰው ሰራሽ አስተውሎት ይበልጥ ብልህና ፈጣን እንደሚያደርገው ይጠበቃል።
GPT-5 የOpenAI የቅርብ ጊዜ እና ምርጥ ሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) ሲሆን በሚሰጠው ፈጣን ምላሽ፣ ውስብስብ ችግሮችን በመፍታት ብቃቱ፣ በጥልቅ የማሰብ ችሎታው እና በውጤታማነቱ እስከአሁን ካሉት ተመሳሳይ ሞዴሎች በእጅጉ የላቀ እንደሆነ ተነግሮለታል።
ምንጭ: Technology News

ማይክሮሶፍት GPT-5 ሞዴልን በምርቶቹ ያካትታል
ማይክሮሶፍት የOpenAIን GPT-5 ሞዴል መጠቀም እንደሚጀምር አስታወቀ።
ማይክሮሶፍት ከOpenAI ጋር ባለው ልዩ ትብብር GPT-5 የተባለውን የአዲስ ትውልድ AI ሞዴል በቅርቡ እንደሚለቅ አሳውቋል።
ይህ ሞዴል የማይክሮሶፍት ሶፍትዌሮች እና ሌሎች አገልግሎቶች በማስላት እና በአፈጻጸም እጅግ የላቀ እንደሚያደርጋቸው ገልጿል።
የቴስላ እና የxAI (Grok) ባለቤት ኢሎን መስክ አስተያየት ተጠይቆ "ማይክሮሶፍት ይሄን አዲስ ሞዴል ቀድሞ መጠቀሙ ከሌሎች የቴክኖሎጂ ድርጅቶች የተሻለ ገበያው ገበያ ለመሳብ ያስችለዋል" ሲል መልሷል።
ምንጭ: Tech News

AlltechUp.com pinned «የክሪፕቶ ዘገባዎችን ስናጋራበት የነበረው ይህ ቻናል በቀጣይነትና በዘላቂነት የቴክኖሎጂ እና ተያያዥ ምርጥ መረጃዎችን የምናጋራበት ይሆናል።»
Horntech.com: የቅርብ ጊዜውን የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች፣ መረጃዎችና መፍትሄዎች ለማግኘት ምርጡ መድረክዎ!
የምናጋራቸው መረጃዎች:-
👉 አቢይ ርዕስ: በጥልቀት የተተነተኑ ርዕሶች
👉 ዜናዎች: አገራዊና ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ዜናዎች
👉 ወርክሾፕ: ተግባራዊ የክህሎት ማሻሻያ ስልጠናዎች
👉 የቴክኖሎጂ ግምገማ: የሀገር ውስጥና የውጭ ምርቶች ግምገማ
👉 የአጠቃቀም መመሪያዎች: ደረጃ በደረጃ የሚሰጡ መመሪያዎች
👉 ፋይናንስ ቴክኖሎጂ (FinTech): የዲጂታል ፋይናንስና ክሪፕቶ መረጃ
👉 ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI): የአጠቃቀም ስልጠናዎች
👉 ጌሚንግ: ለጨዋታ (Game) አፍቃሪዎች
👉 ቅምሻ: አጫጭርና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ ምክሮች
👉 ቃለ ምልልስ: ከኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ጋር እና ሌሎችም ይሆናሉ👏
ከኛ ጋር ሆነው የቴክኖሎጂውን ዓለም ይቃኙ! #Horntech #Technology #Ethiopia

🔥3❤1
ክቡራን እና ክቡራት . . .
በአገራዊ ቋንቋ በቴክኖሎጂ ዓለም ውስጥ የሁሉም ሰው ቀዳሚ ምርጫ እንደሚሆን የማያጠራጥረው horntech.com እየተጠናቀቀ ነው:: 🚀
❤2
AlltechUp.com
ክቡራን እና ክቡራት . . . በአገራዊ ቋንቋ በቴክኖሎጂ ዓለም ውስጥ የሁሉም ሰው ቀዳሚ ምርጫ እንደሚሆን የማያጠራጥረው horntech.com እየተጠናቀቀ ነው:: 🚀
ክቡራን እና ክቡራት . . .
በአገራዊ ቋንቋ በቴክኖሎጂ ዓለም ውስጥ የሁሉም ሰው ቀዳሚ ምርጫ እንደሚሆን የማያጠራጥረው horntech.com እየተጠናቀቀ ነው:: 🚀
ከድረገጹ ጋር በማቀናጀት ላይ በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች ተያያዥ መረጃዎች ይጋራሉ::
🙌 ድረ-ገፁ:-
* አቢይ ርዕስ (In-depth Analysis):- ስለ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ጥልቅ ትንታኔ
* ዜናዎች (News):- የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ዜናዎች
* ወርክሾፕ (Workshop):- አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር የሚያግዙ ተግባራዊ የሥልጠና መረጃዎች
* የቴክኖሎጂ ግምገማ (Product Review):- የሀገር ውስጥ እና የውጭ የቴክኖሎጂ ምርቶች ዝርዝር ግምገማ
* የአጠቃቀም መመሪያዎች (How-to Guides):- ነገሮችን በቅደም ተከተል (Step by Step) እንዴት መጠቀም ወይም መስራት እንደሚችሉ የሚያሳይ መመሪያ
* ፋይናንስ ቴክኖሎጂ (FinTech):- የዲጂታል ፋይናንስ፣ ክሪፕቶከረንሲ እና የክፍያ ሥርዓቶች ዙሪያ መረጃዎች
* ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI):- የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አጠቃቀም ላይ የሚያተኩሩ መረጃዎች እና ስልጠናዎች
* ጨዋታ (Gaming):- የቪዲዮ ጨዋታዎች፣ ኮንሶሎች እና ተዛማጅ መረጃዎች
* ቅምሻ (Tips):- አጫጭር ነገር ግን ጠቃሚ የቴክኖሎጂ ምክረ ሀሳቦች
* ቃለ ምልልስ (Interview):- ከኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ጋር የሚደረጉ ቃለ-መጠይቆች እና ሌሎችም . . . ይቀርቡበታል::
ጠቃሚ እና አዲስ መረጃዎችን ለማግኘት ዛሬውኑ :-
#የፌስቡክ_ገጽ 👇
https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/ ተቀላቀሉ!
በማስተዋወቅም የተለመደው ድጋፋችሁን እጠይቃለሁ፤ በጋራ የዘርፉን ሰፊ ክፍተት እናጠባለን🙏
#Horntech #Technology #Innovation #Ethiopia

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤3
#አስደሳች_ዜና
ስለቴክኖሎጂ ምርቶች ማወቅ ተጨባጭ እይታዎች ይሰጣል። በመረጃ ላይ የተመሠረተ የግዢ ውሳኔ ለማድረግ ይረዳል፤ ፍላጎት እና በጀት የሚያሟላ ቴክኖሎጂ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ያስችላል። የተለያዩ አማራጮች ጥቅም እና ጉዳቶችን በመረዳት ጊዜንና ገንዘብን ይቆጥባል።
የሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) ዘርፍ በፍጥነት እያደገ ነው። በእለት ተእለት ህይወት ያለው እንድምታ እና አጠቃቀም መረዳት ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል።
ስለ ዲጂታል ፋይናንስ፣ ክሪፕቶከረንሲና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አስተማማኝ መረጃ ማግኘት ግለሰቦች እና የንግድ ተቋማት እነዚህን ቴክኖሎጂዎች ለእድገትና ለፈጠራ እንዲጠቀሙ ያስችላል። በዘወትር በሚለዋወጠው የቴክኖሎጂ ምህዳር ውስጥ በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ማድረግ ከህልውና ጋር የተሳሰረ ነው።
ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትና ተያያዥ እውነታዎችን መሰረት በማድረግ በራስ ቋንቋ የሚዘጋጅ horntech.com ድረ ገጽ ለመጀመር ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ነው።
ከድረገጹ ባሻገር በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ዘርፈ ብዙ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ በቴክኖሎጂ እውቀት እና ክህሎት የበለጸገ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁሉን አቀፍ ምንጭ ለመሆን ያለመ ነው።
Horntech.com - በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ የሁሉም ግንባር ቀደም ምርጫ እንደሚሆን አያጠራጥርም🚀
ዛሬውኑ ተቀላቀሉ:-
#የፌስቡክ_ገጽ 👇
https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/

❤2🥰2
#ድንቅ❗
.
.
.
በጥቂት የቃላት ትእዛዝ #በAi የተሰራ ነው:: Ai ስትራክቸራል ንድፍ ሳይቀር ወደ ዲዛይን ይቀይራል::
እየተራዳችሁና እየተጠቀማችሁ በሄዳችሁ ቁጥር ትደመማላችሁ፤ በAi ዓለም ምን እየሆነ እንዳለ በቃላት መግለጽ ይከብዳችኋል።
በነገራችን ሁላችሁም እንዲህ አይነትና ሌሎችም አስደናቂ ዲዛይኖችን (ፎቶግራፎችን) መስራት ትችላላችሁ።
እንዴት ለሚለው ጥያቄ መልሱ በቀጣይ #http://xn--horntech-yv7a.com/ በማጋራቸው መረጃዎችና በምሰጠው ስልጠና ታገኙታላችሁ። ለጊዜው ከታች ያሉትን የቴሌግራምና የፌስቡክ አካውንቶች በመቀላቀል ጠብቁኝ። 🙏☺🙋
ዛሬውኑ ተቀላቀሉ:-
#Telegram👇
https://t.me/horntechcom
#የፌስቡክ_ገጽ 👇
https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/
#Horntech #Technology #Innovation #Ethiopia
Horntech.com - የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ምርጫ - በቅርብ ቀን🚀
.
.
.
ከላይ ያለው ዲዛይን :-
👌 በAutoCAD 2025
ወይም
👌 በAutodesk Revit 2025
ወይም
👌 በ3D SketchUp Pro 2025
ወይም
👌 በRhino for architectur 2025 ወይም በሌላ የታወቀ ፕሮፌሽናል የአርክቴክቸር ሶፍትዌር የተሰራ ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል::
በጥቂት የቃላት ትእዛዝ #በAi የተሰራ ነው:: Ai ስትራክቸራል ንድፍ ሳይቀር ወደ ዲዛይን ይቀይራል::
እየተራዳችሁና እየተጠቀማችሁ በሄዳችሁ ቁጥር ትደመማላችሁ፤ በAi ዓለም ምን እየሆነ እንዳለ በቃላት መግለጽ ይከብዳችኋል።
በነገራችን ሁላችሁም እንዲህ አይነትና ሌሎችም አስደናቂ ዲዛይኖችን (ፎቶግራፎችን) መስራት ትችላላችሁ።
እንዴት ለሚለው ጥያቄ መልሱ በቀጣይ #http://xn--horntech-yv7a.com/ በማጋራቸው መረጃዎችና በምሰጠው ስልጠና ታገኙታላችሁ። ለጊዜው ከታች ያሉትን የቴሌግራምና የፌስቡክ አካውንቶች በመቀላቀል ጠብቁኝ። 🙏☺🙋
ዛሬውኑ ተቀላቀሉ:-
#Telegram👇
https://t.me/horntechcom
#የፌስቡክ_ገጽ 👇
https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/
#Horntech #Technology #Innovation #Ethiopia
Horntech.com - የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ምርጫ - በቅርብ ቀን🚀
🔥4
AlltechUp.com
#እንወያይ👌🙋
#እንወያይ👌🙋
ከሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) እና ቴክኖሎጂ ውጭ ህይወትን ማሰብ ዘግናኝ ነው:: ከእነዚህ ዘርፎች ውጭ ፈጣን ለውጥ ዝግ ነው:: የቀጣዩ ዘመን የሀብትና የእውቀት ማዕከል ሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) እና ቴክኖሎጂ ለመሆናቸው መጠራጠር አይገባም::
ለምሳሌ እነዚህ ቁልፍ ዘርፎች:-
1. የፈጠራ እና የእድገት ማነቃቂያ (Catalyst for Innovation and Growth) ናቸው::
👌 በሌላ መንገድ የሳይንስ፣ የህክምና፣ የምህንድስና፣ የምርታማነት እና የሌሎችም ዘርፎች አዳዲስ ግኝቶችን እና ፈጠራዎችን ማሳካት ቀርቶ ማሰብም አይቻልም::
የገበያ ሥርዓቶችና አወቃቀሮች ሳይቀር የሚመሩት በሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) እና ቴክኖሎጂ ይሆነል፤ አሁንም ተጀምሯል። በሂደቱ ተገቢ እውቀትና ክህሎት ጨብጦ አዳዲስ የኢኮኖሚ እድሎችን መፍጠርና ከዘርፉ የድርሻን መጨበጥ ግድ ነው።
2. የእውቀት ተደራሽነት እና ስርጭት (Democratization of Knowledge and Access) ከሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) እና ቴክኖሎጂ ውጭ አይታሰብም።
ለተማሪዎች ሳይቀር የትምህርት ጥራትን በማሻሻል እና ተደራሽነቱን በማስፋት እኩልነትን ማረጋገጥ የሚያስችል መንገድ ነው።
3. የሰው ልጅ ችሎታ የሚሰፋውም (Augmentation of Human Capabilities) በእነዚህ ዘርፎች ነው::
አድካሚ እና ተደጋጋሚ ስራዎችና አሰራሮችን ለማሻሻል፣ ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት እና ለውጤታማነትም ቁልፍ ዘርፎች ናቸው::
ግራፊክስ ዲዛይነሮች፣ ሰዓሊያን፣ ጸሃፊያን፣ ሙዚቀኞች እና ሌሎችም የፈጠራ ባለሙያዎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን ማበልጸግ የሚችሉት በተለይም Ai በመጠቀም ነው።
---
በአጠቃላይ AI እና ቴክኖሎጂ የእውቀትና የክህሎት ቋት፣ የፈጠራና የሀብት ማዕከል፣ የግል እና የህብረተሰብ ችግሮች መፍቻ ቁልፍ፣ የወደፊት ጉዞ መንገድ ናቸው። ለዚህም ነው በአግባቡ መጠቀም እና ማስተዳደር ወሳኝ የሚሆነው። ይሁን እንጂ የሰው ሰራሽ ልህቀት (AI)፣ የቴክኖሎጂ እና ተያያዥ መረጃዎችን፣ እውቀዮችና ክህሎቶችን ከዓለም እኩል ለመቀራመት የቋንቋ እንቅፋቶች ጠንካራ ግንብ ፈጥረዋል። በጋራ ይሄን ግንብ የሚያፈርስ አንዳጅ እርምጃ ካልወሰድን በግልም እንደአገርም ተነጥለን መቅረታችን ነው።
ከዚህ ግንዛቤ በመነሳት (ብዙዎቻችሁም ደጋግማችሁ በጠየቃችሁኝ መሰረት) የመፍትሄ ጠጠር ለመወርወር ዝግጅት እያጠናቀቅኩኝ ነው። በግሌ ለመጀመር እንጂ ከስራው ስፋት አንጻር ብቻዬን የምዘልቀው ስራም አይደለም። ስለሆነም ለጊዜው በአስፈላጊነቱ ላይ የሁላችንም የጋራ መግባባትና መነሳሳት መኖር አለበት። በአማርኛ ጀምረን በሌሎች አገር በቀል ቋንቋዎችም ለመቀጠል ቁርጠኝነቱ የሁላችንም ሊሆን ግድ ይላል።
ለዚህም የመጀመሪያው በጉዳዩ የማመን፣ የመነሳሳትና የቁርጠኝነት መግለጫ ለዚሁ ስራ ሲባል የተከፈቱትን የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገጽ መቀላቀል ነው። ቢያንስ እኔ ጋር ያላችሁት ከ27K በላይ ተከታዮች መቀላቀል ሲጠበቅባችሁ ቴሌግራም 4.8K ፌስቡክ ደግሞ 1.5K አካባቢ ብቻ ናችሁ የተቀላቀላችሁት። በዚህ ሁኔታ እንዴት ነው ያቀድነውን ማሳካት የምንችለው❓ እስቲ እንወያይበት❗🙏🙆
#Telegram👇
https://t.me/horntechcom
#የፌስቡክ_ገጽ 👇
https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/
#Horntech #Technology #Innovation #Ethiopia
Horntech.com - የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ምርጫ - በቅርብ ቀን🚀
Telegram
Horntech.com
Horntech.com የቴክኖሎጂ አለምን ያዳርሳል! 🚀
የቅርብ ጊዜ ፈጠራዎች፣ ጥልቅ ትንታኔዎች፣ ዜናዎች፣ ወርክሾፖች እና ምርጥ የዘርፉ ምርቶችን ይከታተሉን💻📱
ከAI እስከ ፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ ከAi እስከ ጌሚንግ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም መመሪያዎች—ሁሉንም አካትተናል። 💡
የቅርብ ጊዜ ፈጠራዎች፣ ጥልቅ ትንታኔዎች፣ ዜናዎች፣ ወርክሾፖች እና ምርጥ የዘርፉ ምርቶችን ይከታተሉን💻📱
ከAI እስከ ፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ ከAi እስከ ጌሚንግ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም መመሪያዎች—ሁሉንም አካትተናል። 💡
🔥6🥰2❤1👎1