Forwarded from Awda Hasab - አውደ ሓሳብ (Ethio Empire)
#DeepSeek-R1 የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል
🙆ዓለምን ያናወጠው ማዕበላዊ አብዮት
~~~~
#የተጠቃለለ
*** በ70 ቢልዮን የአሜሪካን ዶላር የተጀመረው #የOpenAi ChatGPT ወጪ አሁን $300 ቢልዮን አልፏል
*** #የChatGPT Pro (Apiን ጨምሮ) ለመጠቀም በየወሩ $200 USD መክፈል ግድ ይላል
*** #DeepSeek ለ1,000,000 ቃላት $0.20 USD ያስከፍላል (Almost 'ነጻ!')
*** የአሜሪካ ስቶክ ማርኬት በቀናት ውስጥ #ከትሪሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራ አስከትሏል
*** DeepSeek-R1 እንደ ሰው የሚያስብ ሲሆን ያሰበውን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ካስቀመጠ በኋላ በተጠየቀው ቋንቋ በትክክል ይመልሳል (በአማርኛ፣ በትግርኛ እና በኦሮምኛ የጠየቅኩትን በትክክል መልሷል
*** የአብዛኛው ክሪፕቶከረንሲ ዋጋ እስከ 73% አሽቆልቁሏል 💸
*** በApple store እና በGoogle Play ቁጥር 1 ተመራጭ ሆኗል:: ትናንት ሰኞ ብቻ #Apple_store ላይ አንድ ሚሊዮን ሰዎች አፕሊኬሽኑን ጭነዋል::
*** #የOpenAi ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የChatGPT ዋና ፈጣሪ #ሳም አልትማን "አስማታዊ ግኝት" ሲል አድናቆቱን ገልጿል
*** የአሜሪካው ፕረዝዳንት ዶናልድ ትረምፕም "የማንቂያ ደወል ነው" ብለዋል
~~~~~~
#ዝርዝር
እኤአ 2023 ላይ ጥቂት የቻይናውያን ወጣት የሶፍትዌር ባለሙያዎች ተሰባስበው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አቃቁመው ነበር:: ከጥቂት ወራት በፊት ግን ከወጣቶቹ አንዱ "ከስራችን ጎን ለጎን ለምን የAi ሞዴል አንሰራም❓" የሚል ጥያቄ አቀረበላቸው:: ሁሉም ሀሳቡን በደስታ ተቀበሉት:: ይሁንና ቻይና እና ተቋማቶቿ #ለAi ሞዴል ግንባታ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን #የNVidia ዘመን አፈራሽ #GPU (Graphics Processing Unit) እንዳይሸጥላቸው አሜሪካ ማዕቀብ በመጣሏ በዓለም ተወዳዳሪ የሆነ ሞዴል መስራት እንደማይችሉ ያውቁ ነበር:: መግዛት ቢፈቀድላቸውም በጀቱ አልነበራቸውም:: በመሆኑም ጊዜ ሳያጠፉም ገበያ ላይ ብዙም የማይፈለገውን (ጊዜ ያለፈበት) #የNVidia GPU #በ30,000 USD በመግዛት ሥራውን ጀመሩት:: ይሄም ቢሆን ገበያ ላይ የማይገኝ ሲሆን የሥራ ዘርፍ በመቀየሩ ሳይጠቀምበት መጋዘን ካስቀመው አንድ ድርጅት ነበር የገዙት:: ወጣቶቹ ሌት ተቀን በመስራት $5.6 ሚሊዮን USD በማውጣት በሁለት ወራት ውስጥ ሰርተው አጠናቀቁ::
ሥራቸውን ባጋሩት በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ባልጠበቁትና ባልገመቱት ደረጃ ዓለም አቀፍ ማዕበላዊ አብዮት ቀስቅሷል::
በዚህም መሰረት ይህ እንደሰው አስቦ መልስ የሚሰጠው #Ai:-
• እጅግ ውጤታማ መሆኑ
• ነጻ ሊባል በሚችል ደረጃ መቅረቡ
• በአያሌ ቋንቋዎች አስደናቂ የሚባል ችሎታው የዓለም ህዝብን በቅጽበይ ለመሳብና ለማዳረስ ችሏል::
መተግበሪያው አሁን ላይ #ከChatGPT፣ #ከGemini እና ከሌሎች ኩባንያዎች Ai በዋጋና በፍጥነት ተመራጭ ሆኗል። በዚህ ምክንያት #ለAi አገልግሎት ውድ ዋጋ ያስከፍሉ የነበሩ አንዳአንድ ኩባንያዎች በፍጥነት እንዲቀንሱ አስገድዷቸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ #DeepSeek በሳምንታት ውስጥ የምዕራባውያን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን (የአክሲዮን ገበያዎቻቸውን) በማሽመድመድ ላይ ይገኛል:: በAi እና በቴክ ኢንደስትሪዎች፣ በቴክኖሎጂ አክሲዮኖች እና በክሪፕቶከረንሲ ዋጋ መካከል ጠንካራ ትስስር በመኖሩ የቴክኖሎጂ አክሲዮኖች መውደቅ ለክሪፕቶከረንሲ ዋጋ ማሽቆልቆል መንስኤ እንደሆነ የዘርፉ ተንታኞች እያመላከቱ ነው። በተለይም ለAi እድገት ተቀዳሚ ድርሻ ባለው #NVidia ትርፍ ለማካበት በስቶክ ማርኬት ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ አፍስሰው የነበሩት ባለሀብቶች በርካሽ ዋጋ #DeepSeek ዓይነት አስደናቂ Ai መስራት ከተቻለ ፈላጊ ሊያጣና ሊያከስረን ይችላል በሚል ስጋት ወደሽያጭ በመግባታቸው ድርጅቱ ትናንት ብቻ $600 ቢሊዮን ኪሳራ አጋጥሞታል።
በተጨማሪም ዋጋ በመተንበይ የCryptocurrency ዘርፉን ገበያ ሊያዛባ (manipulate ሊያደርግ) ይችላል በሚል ስጋት በመፍጠር ገበያ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ እና ውድቀት አስከትሏል። መተማመኛ ያጡ የዘርፉ ኢንቨስተሮች ክሪፕቷቸውን እየሸጡ ከግብይቱ በመውጣታቸው ገበያ እንዲወድቅ ምክንያት ሆኗል።
ያም ሆኖ #የDeepSeek R1 ሞዴልን ካደነቁት መካከል በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ #ተራራው በመባል የሚታወቀው #OpenAi ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳም አልትማን ይገኝበታል:: #የተራራው_ንጉስ በሚል ቅጽል የሚጠራው #ሳም_አልትማን #የOpenAiን ሞዴል የሰራ አሜሪካ ከምትኮራባቸው ምጡቃን አንዱ ነው::
ሳም አልትማን በኦፊሺያል የኤክስ ገጹ ላይ ባጋራው አስተያየት የቻይና ወጣቶች የፈጠሩት Ai “አስደናቂ እና አስማታዊ ግኝት” በማለት አንቆለጳጵሷል:: ለኢንዱስትሪው ጤናማ ፈተና እና ውድድር እንደሚፈጥር በመግለጽ በደስታ እንደተቀበለውም አመልክቷል::
$5.6 ሚሊዮን ዋጋ ባለው የስሌት ግብአቶች የሰለጠነው ይህ የAi ሞዴል የዘርፉን ዋጋ ወጪ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ እንደሚቻል ማሳያ እንደሆነም ጠቁመዋል:: የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሀሙስ በኋይት ሀውስ ይፋ ያደረጉት $500 ቢሊዮን ዶላር የተመደበለት "ስታርጌት" የተሰኘ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ግዙፍ ፕሮጀክት ጥያቄ ላይ ወድቋል::
ፕሮጀክቱ OpenAi፣ Microsoft፣ Meta፣ Oracle፣ የጃፓኑ ሶፍትባንክ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት በጋራ ወጪ የሚያከናውኑት ነው። ፕሬዝዳንት ትረምፕ ፕሮጀክቱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት አሜሪካ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረተ ልማት ዘርፍ ከተፎካካሪ አገሮች ከፍተኛ ብልጫ የሚያቀዳጃት እንደሆነ ገልጸው ነበር።
#Deepseek በአጭር ጊዜ ውስጥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ከማግኘት ባለፈ የOpenAi እና #የGoogle ኩባንያዎችን ትኩረት መሳቡ የምዕራባውያን የቴክኖሎጂ ምርቶችን እንዳትጠቀም በአሜሪካ ማዕቀብ ለተጣለባት ቻይና መልካም አጋጣሚ ሊፈጥርላት እንደሚችል እየተነገረ ነው። የዘርፉ ምሁራን "በአሜሪካ እና በቻይና መካከል አዲስ የAi ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚያዊ እና ጂኦፖለቲካል ፉክክር ወይም ቅርርብ ሊፈጥር እንደሚችል እየጠቆሙ ነው::
#የDeepSeek R1 Ai ሞዴል የአሜሪካና የቻይና ኢኮኖሚያዊና የጂኦፖለቲክስ ሽኩቻ አካል እንደሚሆን ከወዲሁ አመላካች ሁነቶች እየተስተዋሉ ነው። ፕሬዚዳንት ዶናልድ #ስለDeepSeek ክስተት ገለጻ ከተደረገላቸው በኋላ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በወጪ ቆጣቢ የኮምፒውተር ቴክኒኮች ትኩረት አድርገው ዘርፉ የሚጠይቀውን አሸናፊነት እንዲቀዳጁ አሳስበዋል።
ትረምፕ ዝቅተኛ ዋጋ ያለው AI ሞዴል መለቀቅና ተቀባይነት ማግኘት የአሜሪካ ኢንዱስትሪዎች ፈጠራና ወጪ ቆጣቢነትን ያማከለ ተወዳዳሪነትና አሸናፊነት ግድ እንደሚል በአጽንኦት ገልጸዋል። የቻይናው የAi ግኝት "ለአሜሪካ የማንቂያ ደወል ነው" ያሉት ትረምፕ ለዘርፉ አዎንታዊ እድገት ጠቃሚ እንደሆነ በመግለጽም ይሁንታቸውን ሰጥተዋል።
በአሜሪካ የዘርፉ የኢንዱስትሪ መሪዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች በዘርፉ በፍጥነት እያደጉ ለመጡት አዳዲስ ፈተናዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል ግምገማና ምክረ ሀሳብ እንዲያቀርቡም ትረምፕ አዘዋል።

👍16
#ለማስታወስ (#Tap_Tap ማህበረሰብ)
.
.
.
(#ቀደም ሲል ያልሰበሰባችሁ አይመለከታችሁም።)
.
.
.
ለረጅም ጊዜ ስትጠብቁት የነበረው #Tapswap የሚጠናቀቅበት ከ24 ሰዓታት ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል።
ስለሆነም አቁማችሁ የነበራችሁ (የደከማችሁበት ስለሆነ) በቀረችሁ ጊዜ የምትችሉትን ያህል #የVideo Task ብትወስዱ ትጠቀማላችሁ።
የቪዲዮ Code የምታገኙት #በScreenshot 3-5 በተመለከተው መሰረት ነው። (መጀመሪያ Taskን ነክታችሁ ወደ YouTube መሄድና ማየት ሳይጠበቅባችሁ ከ3-5 ደቂቃ መቆየትን አትዘንጉ)
😤በሚቀጥሉት 7 ቀናት TGE Airdrops ይከፋፈላል😱
እኔ በአንድ አካውንት ከ2.65 Billion በላይ ሰብስቤያለሁ፤ እናንተስ❓🙆

👍8❤2
February 17 – Token claim begins
February 22 – Token claim ends
February 25, 12:00 UTC — Listing
Mark your calendars!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5
Forwarded from Awda Hasab - አውደ ሓሳብ (vvbat)
#ከምኞት ወደ #እውነት - 2018❗
("ሰው ያስባል - ያቅዳል፤ እግዚአብሄር ይፈጽማል")
.
.
.
". . . ምኞቴማ የትና የት
ሰው ሊያደርገኝ የቃጣበት
የጠወለገው የተስፋ ዕፅ በምኞት ካቆጠቆጠ
የተጣለው መጋረጃ በተስፋ ከተገለጠ
የትና የት! የትና የት!
አካሌ ተወሰነ እንጂ በነባራዊው ሒደት!"
ከበደች ተክለአብ “የት ነው?” /1983/ የግጥም መድብል "የትና የት" በሚል ርዕስ ከጻፈችው ግጥም የተቀነጨበ አንጓ ነው::
በሶማሊያ እስር ቤት የተጻፉት የከበደች ግጥሞች ስሜት ጎርጓሪ፣ አጥንት ሰርሳሪ፣ እውነት አብሳሪ ናቸው:: ማንሳት የፈለግኩት ግን ስለከበደች እና ግጥሞቿ አይደለም፤ ስለራሴው ነው። ምኞቴ እና ሀሳቤማ የት የት . . . ለማለት ነው፤ ገጣሚዋ እንዳለችው "አካሌ ተወሰነ እንጂ በነባራዊው ሒደት!" እቅዴማ፣ ጥረቴማ . . . የትና የት . . . ::
ነገሩ ሁሉ እናንተም "ሰው ያስባል - ያቅዳል፤ እግዚአብሄር ይፈጽማል" እንደምትሉት ሆነ እንጂ በእርግጥም ውስጤ ያለውማ የትና የት . . .
.
.
.
🤗
Forwarded from Awda Hasab - አውደ ሓሳብ (vvbat)
Awda Hasab - አውደ ሓሳብ
#ከምኞት ወደ #እውነት - 2018❗ ("ሰው ያስባል - ያቅዳል፤ እግዚአብሄር ይፈጽማል") . . . ". . . ምኞቴማ የትና የት ሰው ሊያደርገኝ የቃጣበት የጠወለገው የተስፋ ዕፅ በምኞት ካቆጠቆጠ የተጣለው መጋረጃ በተስፋ ከተገለጠ የትና የት! የትና የት! አካሌ ተወሰነ እንጂ በነባራዊው ሒደት!" ከበደች ተክለአብ “የት ነው?” /1983/ የግጥም መድብል "የትና የት" በሚል ርዕስ ከጻፈችው…
#ከምኞት ወደ #እውነት - 2018❗
("ሰው ያስባል - ያቅዳል፤ እግዚአብሄር ይፈጽማል")
.
.
.
በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ቢሆንም ወደዓለም ተጠግቶ ከመራመድ አንጻር ግን እጅግ ሰፊ ክፍተት ነው ያለው።
የችግሩ መሰረታዊ መንስኤ ደግሞ የዘርፉ መረጃዎች የሚገኙት አብዛኛው ህዝባችን አቀላጥፎ በማይችላቸው የውጭ ቋንቋዎች መሆኑ ነው። ብዙዎቻችሁ ደጋግማችሁ የምትገልጹልኝ እና እኔም በተጨባጭ እንደማስተውለው ችግሩ እጅግ ሰፊ እና ጥልቅ ነው:: ይህም ብዙዎች ቴክኖሎጂ ነክ ጉዳዮችን በተሻለ ሁኔታ እንዳይረዱ፣ ክህሎት እንዳይጨብጡና እንዳይጠቀሙ እንቅፋት ሆኖባችኋል።
ስለሆነም በተለያዩ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች መረዳት በሚያስችል ቀላል መንገድ ቢቀርብ ክፍተቱን ከማጥበብ ባለፈ ለቋንቋዎቹ እድገትም ወሳኝ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ገበያን በማጠናከር፣ የፈጠራ ሥራዎችን በማበረታታት እና የዲጂታል ኢትዮጵያ ግብን በማሳካት ረገድም የማይተካ ድርሻ ይኖረዋል።
ከዚህና ከምታቀርቡልኝ ጥያቄዎች/ሀሳቦች በመነሳት ወደ ስራ ለመግባት ቢዝነስ ፕላን ያዘጋጀሁት ከአራት ወራት በፊት ነበር።
በግልጽ ባላሳውቃችሁም ከጉዳዩ ጋር በተያያዛ ጠቋሚ መረጃዎች አጋራችሁ እንደነበርም የሚታወቅ ነው።
ባዘጋጀሁት ቢዝነስ ፕላን መሰረት ቀድሜ ለመጀመር ያቀድኩት #ድረገጽ ነው። ከድረገጹ በመቀጠል በስድስት ወራት ውስጥ #ቲክቲክ እና #ዩቱዩብ የመጀመር መርሃ ግብር ነበረኝ።
#ድረ_ገጽን አማርኛ፣ ኦሮምኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን በቀጥታ (#Auto) እንዲተረጉም ነበር። ነገር ግን ስራው ከተጋመሰ በኋላ በክፍያ #የgoole_Cloud መጠቀም ግድ እንደሆነ ከመታወቁም በላይ ትርጉሙም ቢሆን የተሟላ እንዳልሆነ (Goole translator የሚተረጉመው ዓይነት እኔም ባለሙያቹም አረጋገጥን:: ትክክለኛ ትርጉም የሚሆነው ቋንቋውን ከማወቅ ባለፈ የቴክኖሎጂ ቃላትን መረዳትና መግለጽ የሚችሉ ባለሙያዎች በመጠቀም እንደሆነ ታመነበት::
ከዚህ በመነሳት ከወጪ አንጻር በሂደት ሌሎች ቋንቋዎችን ለማካተት በማሰብ ለጊዜው በአማርኛ ቋንቋ ብቻ ስራው ቀጥሏል::
ይሁንና ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ፣ ስራውን ለማሳደግ፣ ሌሎች ቋንቋዎችንም (ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ አፋርኛ እና ሶማሊኛ) ለማካተት የሚያስችሉ ባለሙያዎችን ለመቅጠር እንዲሁም በቲክቶክ እና በዩቱዩብ ስራዎች የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ሲባል ከነፃ መረጃዎች ባሻገር የክፍያ (Subscription/Premium) ሥርዓት ማካተት አስፈላጊ ሆኗል። የአገር ውስጥ እና የውጭ ድጋፍ (Donation)ን ጨምሮ የማስታወቂያ ክፍያዎችም የተካተቱበትም ይሆናል።
በነገራችን ላይ አንድ ሰው Subscribe ሲያደርግ በቀጥታ መለያ #Code ይደርሰውና ሌሎችን ኮዱን እያስገቡ Subscribe እንዲያደርጉ የሚያስችልና ኮሚሽን የሚያገኝበት ነው። በኮዱ Subscribe ከሚያደርጉት ብቻ ሳይሆን የጋበዛቸው ከሚጋብዟቸውም የማይቋረጥ ገንዘብ የሚያገኝበት ይሆናል። እነዚህ ስራዎች ከታቀደው በላይ ጊዜ ጠይቀዋል።
ከዚህ ጎን ለጎንም ህጋዊ የገንዘብ ልውውጥ ስርዓት ውስጥ መግባት ግድ በመሆኑ ፍቃድ የማውጣት፣ ምዝገባዎችን የማድረግ፣ ከቴሌ Api ወስዶ #ቴሌብር የመጠቀም ስራዎች ተጀምረዋል።
#የSubscriptoin ክፍያን በተመለከተ ማንም ሰው መክፈል በሚችለው ደረጃ እጅግ ዝቅ በማድረግ ብዙ ተጠቃሚ የማግኘትና ጉድለቱን ከማስታወቂያ የመሸፈን ስትራቴጂ የሚከተል ይሆናል። እስከአሁን ባለው እቅድ በወር #ከብር 7 (በዓመት 210 ብር) ለማድረግ ነው። በቀጣይም ቢሆን የእናንተን አስተያየት መነሻ በማድረግ ከበዛ የመቀነስ እንጂ የሚጨመር አይኖርም። ምክንያቱም ዋና ግቤ #ብዛት! ነው። (እናንተን ይዤ በሁለት ወራት 100,000 በዓመት አንድ ሚሊዮን #Subscribers መድረስ ነው - ዋና ግቤ። እናንተ ከጎኔ እስካላችሁ ከፈጣሪ ፍቃድ ጋር እንደማሳካው እርግጠኛ ነኝ)
በተጨማሪም በማንኛውም መጠን ማበረታታትና መደገፍ የሚፈልጉ #Donate ማድረግ ስለሚችሉ የሚያንስ አይኖርም።
የሆነው ሆኖ አጠቃላይ ሂደቱን በማጠናቀቅ ቢያንስ በአዲስ ዓመት መባቻ ለሙከራ ማጋራት ባለመቻሌ በጣም ተከፍቻለሁ። ምንምን እንኳን በእያንዳንዱ ምድብ (Category) የሚጋሩ ጽሁፎች አዘጋጅቼ የነበረ ቢሆንም የድረ ገጹ አጠቃላይ ግንባታ ባለመጠናቀቁ "ሀሳቤማ፣ እቅድማ የትና የት . . . " እንድል አስገድዶኛል።
በዚህ አጋጣም የድረገጹ የመረጃ ምድብምድቦች/Categories/ አቢይ ርዕስ (In-depth Analysis)፣ ዜናዎች (News)፣ ወርክሾፕ (Workshop)፣ የቴክኖሎጂ ግምገማ (Product Review)፣ የአጠቃቀም መመሪያዎች (How-to Guides)፣ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ (FinTech)፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ ጨዋታ (Gaming)፣ እና ቅምሻ (Tips) ያካትታል።
👉 የሰው ኃይልና ቁሳቁስ ስለሚጠይቅ ለጊዜው ባይጀመርም በአጭር ጊዜ ውስጥ #ቃለምልልስ (Interview) ይካተትበታል። ይህ ምድብ ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂ ኤክስፐርቶች፣ ስኬታማ ስታርትአፖች፣ የቴክኖሎጂ ተቋማት ስራ አስኪያጆች፣ ምሁራን ስፔሻላይዝ ባደረጉበት ጉዳይ አጠር ያለ ቃለ ምልልስ የሚቀርብበት ይሆናል።
በተጨማሪም በእናንተ እና በባለሙያዎች አስተያየት ላይ በመመስረት የሚደመሩ (አንድ ላይ የሚሆኑ)፣ የሚቀነሱ፣ የሚሻሻሉ፣ ሌሎች የሚጨመሩ ይኖራሉ።
ትልቅ ነገር እንዳልም - በተግባር እንድነሳሳ - ስላደረጋችሁኝ፣ ስለገፋፋችሁኝ፣ አንዳአንዶቻችሁም ስለጨቀጨቃችሁኝ . . . የማመሰግንበት ቃላት የለኝም።
.
.
.
በመጨረሻም 2018 የይቅርታ የመቀራረብ፣ የመተማመን፣ የአንድነት፣ የትጋት፣ የብልፅግና፣ የስኬት እና የፍቅር ዓመት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ። (በዚህ አጋጣሚ በማወቅ ወይም ባለማወቅ ያስቀየምኳችሁ፣ ያስከፋኋችሁ፣ ቅር ያሰኘኋችሁ ሁሉ . . . ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ🙏)
በድጋሚ ከነተወዳጅ ቤተሰቦቻችሁ እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ❗🤗
❤3
AlltechUp.com
"ዓለምን የሚገዛው የ27 ዓመት ታዳጊ ንጉስ"
"ዓለምን የሚገዛው የ27 ዓመት ታዳጊ ንጉስ"
በታሪክ "ቡርዧ" የሚለው ቃል በኢንዱስትሪ አብዮት ወቅት የነበሩትን የካፒታሊዝም ባለሀብቶች፣ የመሬት ከበርቴዎች እና የንግድ ሞኖፖሊስቶች . . . ያመላክታል። በአብዛኛው አያሌ ሰራተኞችን በአነስተኛ ክፍያ ቀጥረው ጉልበትና እውቀት በዝባዦች ተደርገው ይገለጻሉ።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ "ቴክ ቡርዧ" (Tech Bourgeoisie) የሚል አዲስ ቃል ተከስቷል። የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪውን በከፍተኛ ደረጃ የሚቆጣጠሩ፣ የሚያንቀሳቅሱ እና ከፍተኛ ትርፍ የሚያጋብሱ በኃያላን አገራት ሳይቀር (ጂኦግራፊያዊ ድንበሮች የማይገድባቸው) ከፍተኛ ፖለቲካዊ ተፅእኖ የሚፈጥሩ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን ወይም ድርጅቶችን ያካትታል። አንዳአንዶች '#ቴክ_ማፈያ (Tech Mafia)' በማለት የሚጠሯቸው ሲሆን ዋና ዙፋናቸው #ሲሊከን_ቫሊ (Silicon Valley), ካሊፎርኒያ, አሜሪካ ይገኛል።
በዚህ ቦታ ከተከማቹት የዘመናዊው ቴክኖሎጂ ዓለም ገዢዎች መካከል Google (Alphabet Inc.)፣ Apple፣ Meta Platforms (Facebook)፣ Nvidia እና Intel ይገኙበታል።
በዚህ ጽሁፍ Google የሚባለውን የ27 ዓመት እድሜ ያለው የዓለም ገዢ ላስተዋውቃችሁ። ጎግል ላይ ያለው መረጃ እንደሚጠቁመው Google መስከረም 4, 1998 ነው የተመሰረተው። የያዝነው ወር መረጃ እንደሚያመላክተው አጠቃላይ የሀብቱ መጠን $2.84 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ደርሷል።
በቴክኖሎጂው ዓለም ውስጥ አብዮታ ከሳች ተደርጎ የሚቆጠረው ጎግል ዘርፈ ብዙ ንጉስ ነው። ጎግል አሲስታንት (Google Assistant)፣ ጎግል ፎቶስ (Google Photos) እና ጎግል ትራንስሌት (Google Translate) ያካተተው የፍለጋ ኢንጅን (search engine)፣ ቴንሰር ፍሎው (TensorFlow) እና ጀሚኒ (Gemini) የመሳሰሉ የላቁ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎች፣ የAI ቺፖች (TPUs) ወይም የሃርድዌር ልማት፣ የክሎውድ አገልግሎት (Cloud Services)፣ የአልፋቤት (Alphabet Inc.) . . . በመሳሰሉት ታላቅ የገዢነት ዙፋን የተቆናጠጠ ወጣት ንጉስ ነው።
የጎግል የእናት ኩባንያ የሆነው አልፋቤት (Alphabet)፣ ከሴፕቴምበር 2021 እስከ ሰኔ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ 1.5 ቢሊዮን ዶላር በብሎክቼይን ላይ ኢንቨስት አድርጓል። ይህም በምድራችን ከሚገኙ ይፋዊ ኩባንያዎች ትልቁ ኢንቨስትመንት እንደሆነ ተነግሯል።
ይህ ኢንቨስትመንት ለብሎክቼን መሰረተ ልማት ( Block chain infrastructure)፣ ለዲጂታል ንብረት ማከማቻ (digital asset custody) እና ለዌብ3 (Web3) ጨዋታዎች የወጣ እንደሆነ ተነግሯል።
በተጨማሪም የጎግል ክላውድ (Google Cloud) አገልግሎቶችን ለብሎክቼይን ኖዶች (blockchain nodes) ገንቢዎች የEngine አገልግሎት ይሰጣል። በቅርቡም ጎግል ክላውድ አዲስ የብሎክቼይን መድረክ የሆነውን Google Cloud Universal Ledger (GCUL) ስራ አስጀምሯል። ይህም በዋናነት ለፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አቻና ተወዳዳሪ የለውም። በቀጣይነትም ጎግል የክሪፕቶፕስ (cryptos) አጠቃቀምና ደህንነት ለማረጋገጥ፣ የጎግል መለያዎችን በመጠቀም የቢትኮይን (Bitcoin) ቦርሳዎችን (wallets) እንዲያገኙ እና የክሪፕቶ ክፍያዎች ከGmail ወይም Google Pay ጋር በሚመሳሰል ቀላልነት ክፍያዎች እንዲፈፀሙ ለማድረግ ከፍተኛ በጀት መድቦ እየሰራ ነው።
በአጠቃላይ ጎግል የዘመናዊው ዓለምን የስልጣን እና የተፅዕኖ መመዘኛዎች በከፍተኛ ፍጥነት ከመሰረቱ የለዋወጠ ነው።
ጎግል በተለመደው ባህላዊ መንገድ ባይነግስም በዲጂታል ዓለም ባለው እጅግ የላቀ ስልጣን በማያጠራጥር "ንግስናው" የዓለምን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በከፍተኛ ደረጃ እየቀረጸ ይገኛል። ይህም የኃይል ማዕከላዊነት፣ የፖለቲካ ጣልቃገብነት፣ የግላዊነት ስጋቶች እና የሥነ-ምግባር ጥያቄዎች በስፋት የሚያስነሳ ሆኗል።
.
.
.
እንዲህ ዓይነቱ ንጉስን የ27 ዓመት "ጎረምሳ" ብሎ ማጣጣል ግሳፄ ሳይሆን ኩናኔም ሊያስከትል እንደሚችል ለብዙዎቻችን ግልጽ ነው።
❤8
የክሪፕቶ ዘገባዎችን ስናጋራበት የነበረው ይህ ቻናል በቀጣይነትና በዘላቂነት የቴክኖሎጂ እና ተያያዥ ምርጥ መረጃዎችን የምናጋራበት ይሆናል።
❤2
ማይክሮሶፍት በAI የታገዘ ሳይበር ደህንነት ይፋ አደረገ
ማይክሮሶፍት በሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) የታገዘ የደህንነት ስርዓት አስተዋወቀ።
በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ስር ነቀል ለውጥ የተባለለት ይህ የማይክሮሶፍት ሴኪዩሪቲ ኮፓይሎት (Microsoft Security Copilot) የተሰኘ ስርዓት የደህንነት ስጋቶችን በአስተማማኝነት መከላከል የሚያስችል ነው።
በተለይም በራሱ ተነሳሽነት፣ ሊከሰቱ የሚችሉ የደህንነት ጉድለቶችን፣ ስህተቶችን እና የኮምፒዩተር ቫይረሶችን ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት መለየት እና ማጥፋት መቻሉ አስደናቂ አድርጎታል።
በተለይም የማልዌር አይነቶችን በተናጠል የመለየት፣ የመተንተን እና የማጽዳት ልዩ ችሎታው በሳይበር ደህንነት ዘርፍ አዲስ እመርታ ተደርጎ ተቆጥሯል።
ይህ ሥርዓት የሳይበር ደህንነት ብቻ ሳይሆን በኮድ ውስጥ የሚያጋጥሙ የደህንነት ስህተቶችን (bugs) በፍጥነት ለይቶ በማሳወቅ እና በማስተካከል ለሶፍትዌር ፕሮግራመሮች ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ታውቋል።
ምንጭ - #Geekwire