Forwarded from Awda Hasab - አውደ ሓሳብ (Ethio Empire)
#DeepSeek-R1 የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል
🙆ዓለምን ያናወጠው ማዕበላዊ አብዮት
~~~~
#የተጠቃለለ
*** በ70 ቢልዮን የአሜሪካን ዶላር የተጀመረው #የOpenAi ChatGPT ወጪ አሁን $300 ቢልዮን አልፏል
*** #የChatGPT Pro (Apiን ጨምሮ) ለመጠቀም በየወሩ $200 USD መክፈል ግድ ይላል
*** #DeepSeek ለ1,000,000 ቃላት $0.20 USD ያስከፍላል (Almost 'ነጻ!')
*** የአሜሪካ ስቶክ ማርኬት በቀናት ውስጥ #ከትሪሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራ አስከትሏል
*** DeepSeek-R1 እንደ ሰው የሚያስብ ሲሆን ያሰበውን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ካስቀመጠ በኋላ በተጠየቀው ቋንቋ በትክክል ይመልሳል (በአማርኛ፣ በትግርኛ እና በኦሮምኛ የጠየቅኩትን በትክክል መልሷል
*** የአብዛኛው ክሪፕቶከረንሲ ዋጋ እስከ 73% አሽቆልቁሏል 💸
*** በApple store እና በGoogle Play ቁጥር 1 ተመራጭ ሆኗል:: ትናንት ሰኞ ብቻ #Apple_store ላይ አንድ ሚሊዮን ሰዎች አፕሊኬሽኑን ጭነዋል::
*** #የOpenAi ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የChatGPT ዋና ፈጣሪ #ሳም አልትማን "አስማታዊ ግኝት" ሲል አድናቆቱን ገልጿል
*** የአሜሪካው ፕረዝዳንት ዶናልድ ትረምፕም "የማንቂያ ደወል ነው" ብለዋል
~~~~~~
#ዝርዝር
እኤአ 2023 ላይ ጥቂት የቻይናውያን ወጣት የሶፍትዌር ባለሙያዎች ተሰባስበው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አቃቁመው ነበር:: ከጥቂት ወራት በፊት ግን ከወጣቶቹ አንዱ "ከስራችን ጎን ለጎን ለምን የAi ሞዴል አንሰራም❓" የሚል ጥያቄ አቀረበላቸው:: ሁሉም ሀሳቡን በደስታ ተቀበሉት:: ይሁንና ቻይና እና ተቋማቶቿ #ለAi ሞዴል ግንባታ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን #የNVidia ዘመን አፈራሽ #GPU (Graphics Processing Unit) እንዳይሸጥላቸው አሜሪካ ማዕቀብ በመጣሏ በዓለም ተወዳዳሪ የሆነ ሞዴል መስራት እንደማይችሉ ያውቁ ነበር:: መግዛት ቢፈቀድላቸውም በጀቱ አልነበራቸውም:: በመሆኑም ጊዜ ሳያጠፉም ገበያ ላይ ብዙም የማይፈለገውን (ጊዜ ያለፈበት) #የNVidia GPU #በ30,000 USD በመግዛት ሥራውን ጀመሩት:: ይሄም ቢሆን ገበያ ላይ የማይገኝ ሲሆን የሥራ ዘርፍ በመቀየሩ ሳይጠቀምበት መጋዘን ካስቀመው አንድ ድርጅት ነበር የገዙት:: ወጣቶቹ ሌት ተቀን በመስራት $5.6 ሚሊዮን USD በማውጣት በሁለት ወራት ውስጥ ሰርተው አጠናቀቁ::
ሥራቸውን ባጋሩት በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ባልጠበቁትና ባልገመቱት ደረጃ ዓለም አቀፍ ማዕበላዊ አብዮት ቀስቅሷል::
በዚህም መሰረት ይህ እንደሰው አስቦ መልስ የሚሰጠው #Ai:-
• እጅግ ውጤታማ መሆኑ
• ነጻ ሊባል በሚችል ደረጃ መቅረቡ
• በአያሌ ቋንቋዎች አስደናቂ የሚባል ችሎታው የዓለም ህዝብን በቅጽበይ ለመሳብና ለማዳረስ ችሏል::
መተግበሪያው አሁን ላይ #ከChatGPT፣ #ከGemini እና ከሌሎች ኩባንያዎች Ai በዋጋና በፍጥነት ተመራጭ ሆኗል። በዚህ ምክንያት #ለAi አገልግሎት ውድ ዋጋ ያስከፍሉ የነበሩ አንዳአንድ ኩባንያዎች በፍጥነት እንዲቀንሱ አስገድዷቸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ #DeepSeek በሳምንታት ውስጥ የምዕራባውያን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን (የአክሲዮን ገበያዎቻቸውን) በማሽመድመድ ላይ ይገኛል:: በAi እና በቴክ ኢንደስትሪዎች፣ በቴክኖሎጂ አክሲዮኖች እና በክሪፕቶከረንሲ ዋጋ መካከል ጠንካራ ትስስር በመኖሩ የቴክኖሎጂ አክሲዮኖች መውደቅ ለክሪፕቶከረንሲ ዋጋ ማሽቆልቆል መንስኤ እንደሆነ የዘርፉ ተንታኞች እያመላከቱ ነው። በተለይም ለAi እድገት ተቀዳሚ ድርሻ ባለው #NVidia ትርፍ ለማካበት በስቶክ ማርኬት ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ አፍስሰው የነበሩት ባለሀብቶች በርካሽ ዋጋ #DeepSeek ዓይነት አስደናቂ Ai መስራት ከተቻለ ፈላጊ ሊያጣና ሊያከስረን ይችላል በሚል ስጋት ወደሽያጭ በመግባታቸው ድርጅቱ ትናንት ብቻ $600 ቢሊዮን ኪሳራ አጋጥሞታል።
በተጨማሪም ዋጋ በመተንበይ የCryptocurrency ዘርፉን ገበያ ሊያዛባ (manipulate ሊያደርግ) ይችላል በሚል ስጋት በመፍጠር ገበያ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ እና ውድቀት አስከትሏል። መተማመኛ ያጡ የዘርፉ ኢንቨስተሮች ክሪፕቷቸውን እየሸጡ ከግብይቱ በመውጣታቸው ገበያ እንዲወድቅ ምክንያት ሆኗል።
ያም ሆኖ #የDeepSeek R1 ሞዴልን ካደነቁት መካከል በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ #ተራራው በመባል የሚታወቀው #OpenAi ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳም አልትማን ይገኝበታል:: #የተራራው_ንጉስ በሚል ቅጽል የሚጠራው #ሳም_አልትማን #የOpenAiን ሞዴል የሰራ አሜሪካ ከምትኮራባቸው ምጡቃን አንዱ ነው::
ሳም አልትማን በኦፊሺያል የኤክስ ገጹ ላይ ባጋራው አስተያየት የቻይና ወጣቶች የፈጠሩት Ai “አስደናቂ እና አስማታዊ ግኝት” በማለት አንቆለጳጵሷል:: ለኢንዱስትሪው ጤናማ ፈተና እና ውድድር እንደሚፈጥር በመግለጽ በደስታ እንደተቀበለውም አመልክቷል::
$5.6 ሚሊዮን ዋጋ ባለው የስሌት ግብአቶች የሰለጠነው ይህ የAi ሞዴል የዘርፉን ዋጋ ወጪ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ እንደሚቻል ማሳያ እንደሆነም ጠቁመዋል:: የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሀሙስ በኋይት ሀውስ ይፋ ያደረጉት $500 ቢሊዮን ዶላር የተመደበለት "ስታርጌት" የተሰኘ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ግዙፍ ፕሮጀክት ጥያቄ ላይ ወድቋል::
ፕሮጀክቱ OpenAi፣ Microsoft፣ Meta፣ Oracle፣ የጃፓኑ ሶፍትባንክ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት በጋራ ወጪ የሚያከናውኑት ነው። ፕሬዝዳንት ትረምፕ ፕሮጀክቱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት አሜሪካ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረተ ልማት ዘርፍ ከተፎካካሪ አገሮች ከፍተኛ ብልጫ የሚያቀዳጃት እንደሆነ ገልጸው ነበር።
#Deepseek በአጭር ጊዜ ውስጥ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ከማግኘት ባለፈ የOpenAi እና #የGoogle ኩባንያዎችን ትኩረት መሳቡ የምዕራባውያን የቴክኖሎጂ ምርቶችን እንዳትጠቀም በአሜሪካ ማዕቀብ ለተጣለባት ቻይና መልካም አጋጣሚ ሊፈጥርላት እንደሚችል እየተነገረ ነው። የዘርፉ ምሁራን "በአሜሪካ እና በቻይና መካከል አዲስ የAi ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚያዊ እና ጂኦፖለቲካል ፉክክር ወይም ቅርርብ ሊፈጥር እንደሚችል እየጠቆሙ ነው::
#የDeepSeek R1 Ai ሞዴል የአሜሪካና የቻይና ኢኮኖሚያዊና የጂኦፖለቲክስ ሽኩቻ አካል እንደሚሆን ከወዲሁ አመላካች ሁነቶች እየተስተዋሉ ነው። ፕሬዚዳንት ዶናልድ #ስለDeepSeek ክስተት ገለጻ ከተደረገላቸው በኋላ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በወጪ ቆጣቢ የኮምፒውተር ቴክኒኮች ትኩረት አድርገው ዘርፉ የሚጠይቀውን አሸናፊነት እንዲቀዳጁ አሳስበዋል።
ትረምፕ ዝቅተኛ ዋጋ ያለው AI ሞዴል መለቀቅና ተቀባይነት ማግኘት የአሜሪካ ኢንዱስትሪዎች ፈጠራና ወጪ ቆጣቢነትን ያማከለ ተወዳዳሪነትና አሸናፊነት ግድ እንደሚል በአጽንኦት ገልጸዋል። የቻይናው የAi ግኝት "ለአሜሪካ የማንቂያ ደወል ነው" ያሉት ትረምፕ ለዘርፉ አዎንታዊ እድገት ጠቃሚ እንደሆነ በመግለጽም ይሁንታቸውን ሰጥተዋል።
በአሜሪካ የዘርፉ የኢንዱስትሪ መሪዎች እና ፖሊሲ አውጪዎች በዘርፉ በፍጥነት እያደጉ ለመጡት አዳዲስ ፈተናዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል ግምገማና ምክረ ሀሳብ እንዲያቀርቡም ትረምፕ አዘዋል።

👍16
#ለማስታወስ (#Tap_Tap ማህበረሰብ)
.
.
.
(#ቀደም ሲል ያልሰበሰባችሁ አይመለከታችሁም።)
.
.
.
ለረጅም ጊዜ ስትጠብቁት የነበረው #Tapswap የሚጠናቀቅበት ከ24 ሰዓታት ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል።
ስለሆነም አቁማችሁ የነበራችሁ (የደከማችሁበት ስለሆነ) በቀረችሁ ጊዜ የምትችሉትን ያህል #የVideo Task ብትወስዱ ትጠቀማላችሁ።
የቪዲዮ Code የምታገኙት #በScreenshot 3-5 በተመለከተው መሰረት ነው። (መጀመሪያ Taskን ነክታችሁ ወደ YouTube መሄድና ማየት ሳይጠበቅባችሁ ከ3-5 ደቂቃ መቆየትን አትዘንጉ)
😤በሚቀጥሉት 7 ቀናት TGE Airdrops ይከፋፈላል😱
እኔ በአንድ አካውንት ከ2.65 Billion በላይ ሰብስቤያለሁ፤ እናንተስ❓🙆

👍8❤2
February 17 – Token claim begins
February 22 – Token claim ends
February 25, 12:00 UTC — Listing
Mark your calendars!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5