ALL TUTORIAL COLLECTION(ATC)
1.58K subscribers
118 photos
1 video
378 files
271 links
📚 ATC | All Tutorial Collection
Quality notes, entrance exam questions with explanations, and simple tutorials for highschool, Freshman & Remedial students. Learn smarter with proven study techniques and boost your results 100% free! 🚀🎓
Download Telegram
ሰላም ውድ የATC ቤተሰቦች​ ዛሬ ማለትም ሰኔ 23 የ12ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደተጀመረ ይታወቃል ስለሆነም "ፈተናውን በልበ ሙሉነት፣ በሰላም እና በስኬት እንድታጠናቅቁ ከልብ እንመኛለን። ውጤታችሁ ያማረ፣ ድካማችሁም በታላቅ ደስታ የሚተካ ይሁን! መልካም የፈተና ጊዜ!"
​"ጥረታችሁ ፍሬ አፍርቶ፣ ውጤታችሁ ከፍ ብሎ የቤተሰባችሁና የሀገራችሁ ኩራት እንድትሆኑ እንመኛለን።
✨መልካም ፈተና!"✨
❤8👎3🥰1😁1
ትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል።
በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 563 ሺ 960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550 ሺ 210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።

ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 12.8 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ችለዋል።

ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም
ውጤት መቼ ይታያል ?

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሰኞ ጠዋት ወይም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ።

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ከሆነም 5/6 ቀናት ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ የሚሰጣቸው ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም
​🎯 የ 12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና (Entrance) ውጤት ለማየት የሚያስችሉ አማራጮች!

​ውጤት በሚለቀቅበት ወቅት በቀላሉ እና በፍጥነት ለመመልከት የሚከተሉትን ይፋዊ አማራጮች መጠቀም ትችላላችሁ፦

​🌐 በዌብሳይት (Websites):

• https://result.eaes.et
• https://result.neaea.gov.et

​📱 በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):

• @EAESbot (t.me/EAESbot)

​📩 በአጭር የጽሁፍ መልእክት (SMS):

• ወደ 6284 መላክ

​🔥 ለ​ተማሪዎች በሙሉ መልካም እድል እንመኛለን!

​📌 ይቀላቀሉን:
👉 https://t.me/all_tutorial_ATC
❤2
ALL TUTORIAL COLLECTION(ATC) pinned «​🎯 የ 12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና (Entrance) ውጤት ለማየት የሚያስችሉ አማራጮች! ​ውጤት በሚለቀቅበት ወቅት በቀላሉ እና በፍጥነት ለመመልከት የሚከተሉትን ይፋዊ አማራጮች መጠቀም ትችላላችሁ፦ ​🌐 በዌብሳይት (Websites): • https://result.eaes.et • https://result.neaea.gov.et ​📱 በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot): • @EAESbot (t.me/EAESbot)…»
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ አልተደረገም።

የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት መለቀቁን በመግለጽ ተማሪዎችና ወላጀችን የሚያደናግር ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ ይገኛሉ።

እስካሁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣ የፈተናው ውጤት ይፋ ስለመደረጉ በይፋ አላሳወቀም።

ትክክለኛ የተረጋገጡ መረጃዎች ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ብቻ የሚገኙ በመሆኑ ተማሪዎች እና ወላጆች ሀሰተኛ መረጃዎችን ከሚያሰራጩ የተለያዩ አካላትና ገጾች ትጠነቀቁ ዘንድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክት ያስተላልፋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት የፈተናው ውጤት ሰኞ ወይም እስከ ማክሰኞ ከሰዓት ይፋ ይደረጋል ማለታቸው ይታወሳል።

ውጤት ሰኞ ዕለት ይፋ ያልተደረገ ሲሆን እስከ ማክሰኞ ከሰዓት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የፈተናው ውጤት ይፋ ሲደረግ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ብቻ በይፋ የሚያሳውቅ ሲሆን እንዴት ማየት እንደሚቻልም ተቋሙ ገለጻ ያወጣል። እኛም ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
❤2
ሰላም የ ATC family ውጤት እንዲታይላችሁ ምትፈልጉ በዚህ username ላኩልን @mujuman12

ካሁኑ ሳዓት ጀምራችሁ መላክ ትችላላቹ
ቤተሰብ ውጤት መየት ተጀምሮዋል

ማየት ትላላቹ መልካም እድል


እምቢ ያላቹ ካለቹ

registration number እና first name ላኩ
Network ያስቸገራቹ ቢቻ admission number እና  first name ላኩ
Network ያስቸገራቹ ቢቻ admission number እና  first name ላኩ

ማሳሰቢያ ትክክለኛ admission number እና የራሳቹ ስም መሆን አለበት
Network ያስቸገራቹ ቢቻ admission number እና  first name ላኩ

ማሳሰቢያ ትክክለኛ admission number እና የራሳቹ ስም መሆን አለበት
🚨ሰበር ዜና

የ2018 ሪሜዲያል ውጤት ተለቋል

Link:-https://result.ethernet.edu.et

✍የ/ወ/ዩ/ተ/ህ/ፅ/ቤት

Join us ➦ @wrustudentunion
For any Question ➦ @wrusu_bot
ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባን ለማዘመን ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዘ አዲስ የአሰራር ስርዓት ሊዘረጋ ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር ባደረጉት የምክክር መድረክ እንደገለፁት፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስብጥር ብዝሃነትን ባካተተ፣ መቻቻልንና ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ሊሆን ይገባል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዩኒቨርሲቲዎች ከተማሪዎች ምደባና ዝውውር ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዘ አዲስ የአሰራር ስርዓት በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚዘረጋ ገልፀዋል።

ከበጀት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደበላቸውን በጀት ለታቀደለት ዓላማ ብቻ በቁጠባና በተጠያቂነት መንፈስ መጠቀም እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክንደያ ገብረህይወት (ፕ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርስቲዎቹ በስምምነት ተማሪዎችን ሲያዘዋውሩ ለትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

@tikvahuniversity
በተልዕኮ የተለዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጧቸውን የትምህርት አይነቶች ክለሳ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

ዩኒቨርሲቲዎች ራሳቸውን በተልዕኮ ሲለዩ በአካባቢያቸው ካለው ፀጋ ጋር በማስተሳሰር ትኩረታቸውን ይበልጥ እንዲያጠቡ ወይም በልዩ ሁኔታ እንዲለዩ እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች በሚገኙበት አካባቢ ባሉ ሀብቶች ላይ በመመስረት በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በግብርና እና በመሳሰሉት ዘርፎች ተልዕኳቸውን እንዲለዩ እየተደረገ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት ከሚሰጡ 297 ፕሮግራሞች ውስጥ 111 ያህሉ መከለሳቸውን በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሜጀና (ዶ/ር) ለሸገር ኤፍኤም ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የትምህርት፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የአፕላይድ ሳይንስ፣ የምርምር እና የአጠቃላይ ትምህርት ተብለው የተከፈሉ መሆኑን ያስታወሱት ኃላፊው፣ ተቋማቱ የሚሰጧቸው የትምህርት አይነቶችም በተመደቡበት ተልዕኮ መሰረት እንዲከልሱ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ይህ ክለሳ ተቋማቱ የበለጠ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ብቃት ያለው ተማሪ እንዲያፈሩ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚህ በኋላ ከመረጡት ተልዕኮ ውጪ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡት ትምህርት እንደማይኖር ያስረዱት ኃላፊው፤ ተማሪዎች በአዲሱ የትምህርት ዘመን በሚገባ መረጃ ኖሯቸው እንዲመጡ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲዎች ራሳቸውን በአግባቡ ማስተዋወቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል። #ShegerFM

@tikvahuniversity
የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ያድርጉ!
 
በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሐግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
 
የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ማድረጊያ ጊዜ 👇
ከነሐሴ 28/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 05/2018 ዓ.ም
 
የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ የሚያደርጉበት ሊንክ 👇
https://student.ethernet.edu.et/
 
የሕክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከስድስት ወር በታች ህጻን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል።
 
@tikvahuniversity