Ali medresa 📚 إقرأ
480 subscribers
294 photos
150 videos
7 files
92 links
االهم نفعأ في الأرض، وقبولا في السماء ، ومحبة منك


ሃሳብ አስታየት ለመስጠት @Alijema_bot ይጫኑ።

ቤተሰብ ስለሆንን እናመሰግናለን😍
Download Telegram
ወንድማችንን ለማሳከም ክፖን ተዘጋጅቶዋለ
ባለ 50
ባለ 100
ባላ 200
ያቅማቹን ከኔ ብትገዙኝ ደሞ ምንኛ አማረ

ከኔ ለመግዛት ደውሉልኝ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንግዲ እዚህ ቪዲዮ ላይ የምትመለከቷቸው እናቶች አባቶች እንዱሁም ወጣቶች የአካባቢው ማህበረሰብ ናቸው በርካታ አመታቶችን ከመስጂድ ተገፍተው መስጂዳቸው ላይ ሰግዶ ከመውጣት ውጪ ምንም አይነት ድርሻ የላቹም ተብለው እየተገፍም ችለው ጥጋቸውን ይዘው ይኖሩ የነበሩ ማህበረሰቦች ናቸው ይህ መሆናቸው ደሞ ፀሀይ የሞቀው ሁሉም የሚያቀው ጉዳይ ነው ።

አላህ ጊዜያትን ይቀያይራል እና እስከዛሬ መከታ ያደርጉት የነበረው መጅሊስ መስጂዶች ላይ ሁሉንም ሙስሊም እኩል ተጠቃሚ ሊያደርግ መምጣቱን በማሰብ ለመጅሊስ ጥያቄው ካቀረቡ ሰነባብተዋል።

ይህንን ጥያቄ ያቀረበን ማህበረሰብ ነው እንግዲ አንዴ ወሀብያ ናቸው መስጂዱን ሊወርሱ ነው ፣ ዳዕዋን ሊያስቆሙ ነው ፣መውሊድን ሊያስቆሙ ነው ፣ መድረሳ ሊያዘጉ ነው ፣ከቤተል እና ከአለም ባንክ የመጡ ናቸው ብሎ ውሸትን በማስወራት መጅሊሱንም ማህበረሰቡንም በማናወጥ ላይ ይገኛሉ።

ሌላው ትዝብት ለታክሲ ተራ ልጆች ነው

ከእናንተ ሚጠበቀው ጎራ ለይቶ ለአንዱ ከመቆም ይልቅ እንዴት እርቅ ይፈጠር እንዴት የአካባቢውን ሙስሊም ግጭት ውስጥ ደም መፋሰስ ውስጥ እንዳይገባ እንታደገው ብሎ ማሰብ ነበር። ብዙ ቦታ የተራ ልጆች እስልምና ሲነካ እንደሚያመሩ እናውቃለን በሙስሊሞች መካከል ለተፈጠረ ግጭት አስታራቂ ሆኖ ስርዓት ሲያሲዙም ብዙ አካቢዎች ላይ አይተናል። በሙስሊሞች መሀል በተፈጠረ ነገር ግን ጎራ ይዞ አንዱን ሙስሊም ማህበረሰብ ከመስጂድ አባሮ ሌላኛውን መስጂድ ለማቆይት እንቅስንቃሴ ማድረግ ግን ውርደት ነው ኢስላም ምን እንደሆነም አለመገንዘብ ነው ። ከመሬት ተነስቶ አንዱን ጎራ መስጂድ አትገቡም ብሎ በር ላይ ከመቆም ጠጋ ብሎ ምንድነው ችግሩ ማለት የተሻለ ነው ወይስ እናቶቻችንን ከቤተል እና ከአለም ባንክ የተሰበሰቡ የሚለውለውን ትርክት አምናቹ ተቀብላቹ ነው?
አሰላሙ ዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ

ውድ ወንድም እህቶቼ ይሄን የመሰለ ዕድል አያምልጣችሁ

ከሙስሊሙ በሚሰበሰብ መዋጮ መስጂድ መድረሳ ምናምን እንሰራለን ለሚሉ ሁሉ የሎሚ ሜዳ (ዓሊይ መድረሳ) ልጆች ምርጥዬ ምሳሌ ናቸው። ለግንባታቸው የመሰረት ድንጋይ አልጣሉም ፤ ይልቕዬ ያችን ድንጋይ የመድረሳው አካል አርገው ስራቸውን ጀመሩ። የዛሬ 3 ዓመት ከቑፋሮ አንስቶ እስካሁን ድረስ የሚሰበስቧት ሳንቲ ምን ላይ እንዳረፈች በተግባር ያሳያሉ። የሚሰጡ ሰዎች ብራቸው መሬት ወርዶ ፍሬ እያፈራ እያዩ ስለሚደሰቱም ይመስለኛል እስካሁን ድረስ 3 ዓመት ሙሉ የቴሌግራም ግሩፑ እንቕስቓሴ እንደሞቐ ነው። ሀቂቓ 3 ዓመት መሙላቱን ራሱ ያወኩት ከታች ያያያዝኩትን ፎቶ ለመውሰድ ስሰርች ነውንጂ ዓመትም የሆነው አልመሰለኝም ነበር!

አስባችሁታል በዚህ ወደ አንድ ሺህ ሚጠጉ ልጆችን በነፃ የሚያስተምር ትልቕ ተቛም ላይ አስተዋፅዖ ማድረግ አላህ ዘንድ ሚኖረውን ደረጃ! መቓብሮ ይዘው እሚወርዱትና ያን የጨለማ የብቸኝነት ቤት የሚያበራ ሀብት ነውና አያምልጦ። እስቲ ሌላው ቐርቶ እዚ ገፅ ላይ ቢያንስ 1003 ሰው ብቻ እንኳ ይታጣል 100 አሁኑኑ ትራንስፈር ማድረግ ሚችል?! አጥተን 5ና 11 ብር ራሱ ብንልክ ጌታችን ቸር ነውና እጥፍ ድርብ አርጎ በዱንያ በአኼራ ያስደስተናል። ከአላህ እገዛ በመቐጠል እቺው የተናቐች ብርና የእህቶቻችን ጌጣጌጥ ተሰባስቦ ነው ለዚህ የደረሱት እንጂ ያን ያክል ባለሀብቶች እየረዷቸው ምናምን አይደለምና ትንሽ ናት ብለን ሳንቲያችንን አንናቓት። እንላካት!
ሀባ ማዋጣት ያልቻልን ደሞ ጥሪያቸውን በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን። ማንያውቓል በኛ ሼር ሰበብ አንዱ ልጥጥ ዘጭ ብር አስገብቶ እኛ ቤሳቤስቲን ሳናወጣ አጅር ብናፍስስ

ልዩ አዲስ
ኑር ኢስላሚክ ሴንተር!!!

ኑር ከእህል በረንዳ ሙስሊም ወጣቶች ጀመዐ እስከ ኑር ኢስላሚክ ሴንተር ድረስ 10 አመታትን የተሻገረ ትልቅ ታሪክ ያለው አንጋፋ ተቋም ነው!!!

ኑር አመራሮቹ፣ ኡስታዞቹ ፣ የጊቢው ሰራተኞች ልዩ ናቸው። ኑርን ለመጎብኘት የመጣ ሁሉ በመርከዙ ሳይገረም አይመለስም። ተማሪዎቹ በዲንም ፣ በአካዳሚም፣ በኳስም ጎበዞችና ተወዳዳሪዎች ናቸው።

መድረሳው ከቃዒዳ ጀምሮ እስከ ሂፍዝ ድረስ በካሪኩለም በተገደበ የጊዜ ገደብ ያስተምራል። በኪታብም ደረጃ በአቂዳ፣ በፊቅህ፣በሀዲስ፣ በነህው ፈን ላይ ብቁ ኡስታዞችን መድቦ ያስተምራል!!

መርከዙ ላይ የሚቀሩት ህፃናት ቂርዐት ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም እረፍት ሰዐታቸውን በኑር ጊቢ ማሳለፍ የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ከሆነ ሰነባብቷል!!

ኑር ለአካባቢው ህፃናት ነፃነት ነው። ሰፊ ነፃነት። ከመማር ባሻገር ሙሉ ውሏቸውን የሚያሳልጡበት ሰፊ ነፃነት ። ለቂርዐት ፣ ለጫወታ፣ ለሻወር ፣ለውዱዕ፣ ለሰላት፣ ለሽንትቤት የማይቸገሩበት የሆነ ሰፊ ነፃነት

ኑር መንፈስ ነው፣ የዲን መንፈስ፣ የጀመዐ መንፈስ፣ የሙስሊም መንፈስ።

መድረሳው ትላልቅ ስብዕናዎችን እያፈራ የሚገኝ ፣ ዒልም ፈላጊ ወጣቶችን ያቀማመጠ፣ የተህፊዝ ክፍሉ አስደማሚ ሁፋዞችን ያወጣ ነው።

ብቻ እዚያ ጊቢ ስትገባ ጥሩ ስሜት ይሰማሀል!!

አሁን በዚህ ሰዐትም ጊቢው ላይ ህፃናቱ በቡድን በቡድን ሆነው ኳስ እየተጫወቱ ነው።

mr shemsu Awolia

የኛዋ (አሊ መድረሳስ) ገለፃው ስለማረከኝ
https://vm.tiktok.com/ZM6vEBp1k

ዛሬ ማታ ሶስት ሰዓት : 30
🟢 የሱናን ስርአት ያዘወተረ
አላህ (ሱ.ወ) ቀልቡን በእውቀት
ብርሃን ያበራለታል‥
💚 የውዱን ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ትእዛዛት
ተግባራትና ባህሪን ከመከተል የበለጠ
ክብር ያለው ቦታ የለም ።
[ኢብኑ ዐጣእ (ረ)
መዳሪጁ ሳሊኪን 2/446]
📜 مدرسة علي ابن ابي طالب

📃 ዓሊይ ኢብን አቢ ጧሊብ መድረሰ አልቆ ለሎሚ ሜዳ ብርሃን ሆኖ ማየትን በጣም ናፍቆኛል ኢንሻ አላህ እሩቅም አይሆንም

https://www.facebook.com/100003497284129/posts/pfbid0tunksYv7wTJhWUk9juuGnrPbHyscxakbg9zfyouiiYKZsRRciVJ2Gp8zsbQ4W2JTl/?mibextid=2JQ9oc
" ﺍﻟﺼﺒﺮ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻄﺎﻋﺔ ﺃﺷﺪ ﻣﻦ ﺍﻟﺼﺒﺮ ﻋﻦ ﺍﻟﻤﻌﺼﻴﺔ

ﻭﺑﺎﺏ ﺍﻟﻠﻪ ﻣﻔﺘﻮﺡ ﻟﻚ ﺑﻄﺎﻋﺘﻪ ﺭﻏﻢ ﻣﻌﺼﻴﺘﻚ؛ ﻓﺎﺻﺒﺮ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻄﺎﻋﺔ ﻭﺇﻥ ﻋﺼﻴﺖ

ﻓﺈﻥ ﺃﻭﻫﻤﻚ ﺇﺑﻠﻴﺲ ﺃﻻ ﻗﺒﻮﻝ ﻟﻄﺎﻋﺘﻚ ﻣﻊ المعصيك ففارقت الطاعة؛بقيت على المعصية وخسرت الطاعة؛ فكأنك أغلقت باب الله دونك بيديك ..وأي شئ يبلغ إبليس منك أكثر من أن تغلق باب الله بيديك



💥ታላቅ የሙሀደራ ፕሮግራም
👉በአልይ ኢብን አቢጧሊብ መድረሳ
👉ርዕስ የቀብር ህይወት
👉በኡስታዝ ተውፊቅ ራህመቶ
👉እሁድ የካቲት 10/2016
👉የአስር ሰለት እንደተጠናቀቀ
👉አድራሻ ከመስጂዳችን አሊ ጀርባ

ለሴቶችም በቂ ቦታ አለ!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከልጅነት ትውስታ ረመዳን ላይ ነው እና ቱታ ሱሪ ለብሼ  ከአባቴ አጠገብ ኢሻ  ሰላት ሰግጄ እንደጨረስኩ አንድ ሰው ከኋላዬ ነካ አደረገኝ እና ወደዚህ ዙር አለኝ ዞር ስለ ኡስታዝ ኸይረዲን (ቶክቾው) ነው እግርህ ዘርጋ አለኝ እና መሬት ሲጠርግ የነበረው ሱሪዬን አጠፈልኝ አስከትሎም የነብዩን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ሀዲስ ነግሮ አስጠነቀቀኝ ከዛ ተራዊህ ልሰግድ ስነሳ በሱሪዬ አስተጣጠፍ እየተገረምኩኝ ሲፈታ እራሱ እያጠፍኩት  ሰገድኩኝ  (አልሀምዱሊላህ  ያኔ የታጠፈቿ …) ኢላሂ የመጨረሻዬንም ነገር አደራ

ግርማ ሞገሱ ወንዳ ወንድነቱ ድምፁ ሙሉ እንቅስሴው ሁሉ ይለይ ነበር እኮ ኢሻ ላይ መስጂድ ሲሄድ ካየሁት ዛሬ ዳዕዋ ያደረግ ይሆን የሚል ጉጉት : ዳዕዋው አጭር ናት ግን ትገነባለች  ወኔን ታመጣለች አንድ ታደርጋለች ዘና አድርጋ ባላለቀ እያስባለን ታልቃለች እሱ ለዳዕዋ ከተነሳ ማን ሊነሳ ተገዶ ቁጭ በል ተብሎ ሳይሆን ወዶ ያዳምጣል ጀመዓው ሁሉ በዳዕዋው ተደስቶ አላህ ሀያትህ ያርዝመው አላህ ይጠብቅህ እያለ  ነሸጥ ብሎ ይወጣል ። ይሉኝኝታ የለ ማን ምን  አለ የለ ሀቅ ከሆነ ይነገራል ማን ትንፍሽ ሊል ፣{ አላሁሙ ኢኒ አኡዙ ቢከ አን አዲለ አው ኡደል አን አዚለ አው ኡዘል አን አዝሊመ አው ኡዝለም አን አጅሀለ አው ዩጅሀል አለኝ} እና ሌሎችም የጠዋት እና የማታ ዚክሮችን ተውሂድ እየሰበከባቸው ሰምተን ሀፍዘናቸዋል ገና ረመዳን በገባ በሶስተኛው ቀን ያኸተመ አለ እጁን ያውጣ አሁኑኑ ልሸልመው ከ አስር ቀን ቦሃላ እጠይቃለሁ ይህን ያህል ግዜ ያኸተመ እሸልመዋለሁ ።ረመዳን ላይም ከረመዳን ውጪ ሰው ሳይለይ ጎሮቤት ሳይለይ ይሰድቃል ልጅ አዋቂውን ሰብስቦ አጥግቦ ያበላል ።የሱ ሰደቃ ዘገየ ከተባለ አሰራ ምናም ቀን ወር ከሞላማ አረ ምንድነው ሰደቃ የለም እንዴ ዘገየ ተብሎ ማጉረምረሞች ሁላ ሊከሰቱ ይችላሉ …😁
……የወኔው ትልቀትማ እንዲህ ይል ነበር   …ከዚህ ማለትም ከመስጂዳችን አሊ እስከታች ድረስ እንዲ ዙርያውን መስጂድ አድርገን  እናሰፋውና ኢስላማዊ ዩንቨርስቲ ነው ምንገነባው ይልነበር የመስጂዱ ጎረቤቶች ሊያፈናቅለን ነው እንዴ ብለው ቢደነግጡም ባይደናገጡም እሱ ግን ምኞቱ ነበር  😁😁 

አፉ በሉኝ  ስለሱ ለመፃፍ ሞከርኳ የማልችለውንም አልደፍርም

ብቻ ግን ሰፈሬ እሱን እሱን ትጣራለች  ዳዒ ያስፈላጋታል ጀግና ወንዳ ወንድ የሆነ  ለጎራ ሳይሆን ለ ኢስላም ለአላህ ብቸኛ ተመላኪነት  ለ አርካኑል ኢስላም እና ለአርካኑል ኢማን  የሚታገሉ ኢስላምን ኖረውት ሌሎችም እንዲኖሩት የሚያደርጉ ።

በመጨረሻም ለኸይረዲን አላህ ይዘንለት አጅሩን ደረጃውን ከፍ ያድርግለት ቀብሩን ኑር ያድርግለት ቤተሰቦቹን ባሉበት አላህ ይጠብቃቸው ለኛም  በዲናችን ላይ የተጋረጠብንን አደጋ አላህ ያንሳልን ጥላቻውንም ውዴታውንም  በልኩ ያድርግልን ሌላው ቢቀር በኢስላም ጥላ ይሰብስበን ማንም ይሁን ማን ከመስጂድ አባራሪውን አላህ ቀልብ ይስጠው  እንደ ድሮው ኑ ወደ መስጂድ የሚሉትን  አላህ ያብዛልን

አላሁመሰሊ ወሰሊም ዓላ ነብይና ሙሀመድ 😘
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM



     💥ታላቅ የሙሀደራ ፕሮግራም
👉በአልይ ኢብን አቢጧሊብ መድረሳ
👉ርዕስ የቀብር ህይወት
👉በኡስታዝ ተውፊቅ ራህመቶ
👉እሁድ የካቲት 10/2016
👉የአስር ሰለት እንደተጠናቀቀ
👉አድራሻ ከመስጂዳችን አሊ ጀርባ
       
         ለሴቶችም በቂ ቦታ አለ!!
[ሸይኹ ለተማሪዎቹ ሰሂህ አልቡኻሪን እያስተማሩ አንድ ወጣት ገባና ^ምእራባዊያን ጨረቃ ላይ ደርሰዋል አንተ እዚህ ተቀምጠህ ቡኻሪ ታብራራለህ በማለት
ተናገራቸው

ሸይኹም እንዲህ አሉ ።"ፍጥሮች ፍጡራን ጋር ደረሱ ። እኛ ደግሞ ወደ ፈጣሪያችን መድረስን ፈለግን። ታዲያ ይሄ ምኑ ያስደንቃል።

ነገር ግን በመካከላችን የከሰርከው አንተ መሆንህን ታውቃለህ… ? ወይ ከምዕራባዊያኑ ጋር ወደ ጨረቃ አልወጣህ! ወይ ከኛ ጋር ቁጭ ብለህ ቡኻሪ አልቀራህ ።’አሉት

/አላህ የስገንዝበን /
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር 18 ምርቃት ላይ የተለያዩ ኡስታዞች ተጋብዘው ነበር እና ሁሉም እየተናገረ የሸይኽ ኢልያስ ተራ ደረሰ ተነሱና ተናገሩ በመሃል እንዲህ አሉ ይህ ህንፃው ወሲላ (መዳረሻ or ድልድይ) ነው ጋያው (መድረሻው or ፕሮዳክቱ) ዒልም ነው አሉ

የኡስታዝ ሙሃመድ ዐረቦ ተራ ደረሰና ተነሳ ህንፃውም ዒልሙም ወሲላ (መዳረሻ or ድልድይ) ናቸው ጋያው (መድረሻው or ፕሮዳክቱ) ደግሞ ተቅዋ የአሏህ ፍራቻ ነው ።

(fb) abdu lhafiz mitiku
ታላቅ የሙሐደራ ዝግጅት
==================

⛳️ የፊታችን እሁድ የካቲት 17/06/2016 በእፎይታ (ቁባእ መስጂድ ) 

🧊ከጧቱ 3:00 እሰከ ዙህር

1,በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

🧶የረመዷን ህግጋቶች

2,በኡስታዝ ጂብሪል አክመል

🧶የረመዷን ወር ትሩፋቶች

ሴቶችን ያካተተ የዳዕዋ ፕሮግራም ስለተዘጋጀ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡

ማሳሰቢያ፦
ይህ ፕሮግራም ተደራሽ ይሆን ዘንድ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ የበኩልዎን ይወጡ።
አድራሻ :ኮልፌ አጠና ተራ ቴሌው ጀርባ

  
ረመዷን 21 ቀን ቀረው ከኛ ምን ይጠበቃል በትንሹ


💡٢١ يومًا ثُمّ رمضان💡

🔺 في خواتيم رمضان من كلّ سنة نعاهد أنفسنا أن يكون رمضاننا المقبل خيرًا مما فات، ثم تتكرّر الخيبة كل عام.

الحلّ: هو التدريب والتدريج؛ فإن أخذ النّفْس بالتغيير المفاجئ يرهقها، والنفس كالطفل تحتاج لترويض ومخادعة حتى تستقيم.

يقول علماء النفس: من مارس شيئا ٢١ يومًا يوشك أن يكون له عادة!.
والعرب تقول: الخير عادة؛ فما عودت نفسك عليه استسهلته.

📍حدّد جوانب قصورك في كل رمضان.

⚠️ خذ بعض أمثلة القصور الشائع.
١/ صعوبة الصف الأول في صلاة الظهر..
💡الحل: عوّد نفسك من الآن وألزمها بسنن الرواتب؛ لأن السنن سياج الفرائض، وابدأ بحرب ناعمة على السهر.

٢/ قلة الختمات القرآنية..
💡الحل: زد وردك القرآني من الآن رويدًا رويدًا.

٣/ الإسراف في استعمال الجوال..
💡الحل: ابدأ بتقليل الاستعمال من الآن؛ فالفطام المفاجئ عن العوائد شاق على النفس، وقلّ من يُطيقه.

الاعتياد على الخير نتيجة الصبر والإرادة وجودة التخطيط.

شعبان مزرعة البركة
وكان النبي ﷺ يكثر من الصيام في شعبان.

🔗 استمع لمحاضرة الشيخ حسن بخاري - على اليوتيوب - بعنوان: هدي النبي ﷺ في رمضان ⬇️


📝 سامي هوساوي
٩ شعبان

#السنة_دين_وحياة
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያጀመዓ አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ እንዴት ናቹ 

ስለ ሁሉ ነገር አልሀምዱሊላህ

ይህንን እስቅርዻዽ😘 የሆነ ጀመዓ በምን ቃል ላመስግነው በምን ቃል ላሞካሸው በሚል ግራ መጋባት ውስጥ ሆኜ   ዝምታ ውስጥ ነበርኩኝ { በቃ ትለያላቹ}  አፍ ታሲዛላቹ ።

😍 ስለኛ እና ስለመስጂዳችን ስትጮሁ ስትጨነቁ እላይ ታች ስትሉ  የነበራቹ እናቶቻችን አባቶቻችን እህቶቻችን ወንድሞቻችን ሁሉ በጣም በጣም እናመሰግናቹሀለን በጣም በጣም እንወዳቹሀለን በጣም በጣም ስላስቸገርናቹ አፉ በሉን ።አላህ አጅራቹን ያብዛው ።