AL-faruq-tube
6.07K subscribers
255 photos
88 videos
3 files
419 links
Download Telegram
(ፍትህ ለጎንደር ሙስሊሞች )
ዲነል ኢስላም በማንም ሴራ የሚጠፋ እና የሚደናቀፍ አይደለም ሙስሊሞችም የካሀዲያን ሴራ አይበግራቸዉም ሁሌም ዲነል ኢስላም አሸናፊ እና የበላይ ነዉ አሏህ እንዲህ ይላል :-
وَمَكَرُواْ وَمَكَرَ ٱللَّهُ ۖ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ ...

ከሀዲያን ሴራን አሴሩ አሏህም የሴራቸዉን ጀዛ ሰጣቸዉ አድማቸዉን መለሰባቸዉ አሏህም ከሴረኞቹ ሁሉ በላጭ ነዉ .
.اللهم انصر الإسلام والمسلمين وأذل الشرك والمشركين ودمر أعداءك أعداء الدين
ጌታየ ሆይ የጎንደር ሙስለሞችን ፣መሳጂዶችንእና ንብረታቸዉን ለአንተ አደራ ሰጠናል ሁሉም የአንተ ነዉና
ለአማፂያን ጀዛቸዉን በአሳማሚ ሁኔታ አስከፍልልን የካሀዲያን በላእ በራሳቸዉ ላይ ይዝነብልን
አሚን አሚን አሚን 🤲🤲🤲
#ኡስታዝ_ሰኢድ_አህመድ በብዕራቸው ተቃውመዋል!

የወንዶቹ ቁና ያ የዲኑ ማገር
ዑመር የሉም ተብሎ
ኢማም አህመድ ጋዚ አልፈዋል ተብሎ
በጎንደር ሙስሊሞች ስቃይ ቢበረታ
አለላቸው ጀሊል
ፍፁም የማይሞተው የነ ዑመር ጌታ


ታምኖ፣ ችሎ፣ ትቶ፣ ታግሶ ቸልቶ
ገራገሩ ሙስሊም ባለ ልዋል ልደር
መስጂዱ ተቃጥሎ ሰጋጁ ሲገደል
ምን አርጎሽ ነው ብልሽ
መልስ አለሽ ወይ ጎንደር??!!

ይቅር ብሎ አልፎ፣ ሰላምን አንግሶ
ሲነፍጉት ለግሶ፣ ለችግርሽ ደርሶ
የሚኖርን ሙስሊም ሲገደል እያየሽ
በዋዛ አሳለፍሽው ጆሮ ዳባ ብለሽ?!!
እንዴት አይባባስ የኔማ ችግሬ
ሰምታ እንዳልሰማች አይታም እንዳላየች
ሆናብኝ አገሬ።

ሙስሊም የተገፋ የተነካ ለታ
ሚዲያሽ ካለወትሮው
ደንቁሮ ታውሮ
ወሬ ነጋሪሽም አፉ ዱዳ ሆኖ
የመዋሉን ምስጢር አውቃ ዝም አለችኝ
ይህ ነው ወይ ምላሼ አገር እያለችኝ

ያውም በረመዷን
ፆም ውለው ፆም ሟቾች
እጣቸው ያስቀናል እንደ በድር ዘማቾች


አይተሽ እንዳላየሽ ዝም ያልሽው አገሬ
ንገሪው ለዛ ሰው
ከጠጣበት ጉድጓድ አፈር ለመለሰው
የንፁሃንን ደም በግፍ ላፈሰሰው
ያጎረሰውን እጅ ጅሎ ለነከሰው
ንገሪው ለዚያ ሰው
ያን ቀቢፅ ተስፋውን ካፎት ይመልሰው
አለዚያ ሙስሊሙ
ልክ እንደ ቀስት ናቸው ኋሊት ሲሸሽቱ
ሃይ ብለው ተነስተው ከተወነጨፉ
እንኳን የደፈሩት ያሰቡም አይተርፉ
መስጂድ በማቃጠል፣ ሙእሚንን በመግደል
ብትፍረመረሙም ለቀቢፀ_ግዛት
ኢስላም ልማዱ ነው
ሲነቅሉት አፍርቶ ሲቀንሱት መብዛት

ግንስ ያስለቅሳል ከእንባም አልፎ ደም
ያንች አውቆ ዝምታ ለፍትህ መግደርደር
የሰላም ነዋሪን ሰላም ነስቶ ማደር
እንዲያ መጨከኑ በሙስሊሙ መንደር
ምን አርጎ ነው ብልሽ
መልስ አለሽ ወይ ጎንደር
።።።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዒድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን! በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የመተዛዘን የአብሮነት ይሁንልን!

ዒድ ሙባረክ! 🥳

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
كل عام وأنتم بخير
#ሐረር
የሸዋል ኢድን በሐረር ዛሬ ምሽት አንድ ላይ እናከብረዋለን !
#ኸሚስ_ሙባረክ
በጣም ድንቅ ነሺዳ በፉአድ ሸምሱ
#ሀቢበሏህ
የተሰኘ ልዩ ነሺዳ ዛሬ ምሽት 2:00 #በፋአድ_ሸምሱ የYouTube ቻናል ይዞላችሁ ይቀርባል!!

Youtube:
https://youtu.be/ywY_lKMM2G8

ግጥም ኡስታዝ ሰኢድ አህመድ
(ኸሚስ ሙባረክ)😊

የለንበትም

እወቅ ብለናል ሳለህ ሳትሞት
የከጀልክ እንደሁ መራቅ ከሳት

ምህይምና ከሆን ጉዝጓዙ
ወደድክም ጠላህ አይቀርልህም
ውግዙን ፈቅዶ ፍቁድ ማውገዙ

መገን ምክራችን ሰምተህ ከመጣህ
ጥርት ያለውን እውቀት ከጠጣህ
ከስሁት መራቅ ይሆናል እጣህ

ግን ገላምጠኸን ግራ ስትኳትም
አጀልህ ደርሶ ኑሮህ ሲያከትም
ዐዛብ ቢያጣድፍህ ተገኝተህ የትም
የለንበትም!!!

ኡስታዝ ሰኢድ አህመድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አዲስ ድንቅ መንዙማ በሶላሁዲን ሁሴን
ለመጀመርያ ጊዜ በመዲነቱል ሙነወራህ የተሰራ

ልበሎ ዘላለም :- https://youtu.be/DeHUId2EZ5o
አበባማዋ ሌሊት»

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

«አበባማ» የሚል የማዕረግ ቅፅልንና ክቡር ቦታን ያገኘችው ሌሊት፤ የጁሙዐ ሌሊት (ሐሙስ ማታ) ስትሆን
ማለፊያ የሆነ ቅፅልን አውጪው ደግሞ ከአበባም በላይ የፈኩት የኛ ነቢይ ናቸው።

عن عمر بن الخطاب رضي الله عنه قال: قال رسول الله ﷺ أكثروا الصلاة علي في الليلة الزهراء واليوم الأغر فإن صلاتكم تعرض علي فأدعوا لكم وأستغفر

ዑመር ቢን አል ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዓንሁ) እንዳስተላለፉት የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል «በአበባማዋ ሌሊት ( ጁሙዐ ሌሊት) እና በብርሃናማዋ ቀን (በእለተ ጁሙዐ) በኔ ላይ ሶለዋት (ማውረድን) አብዙ፤ ያወረዳችሁት ሶለዋት ለኔ ይቀረባልና፤ እኔም ለእናንተ ዱአ(ጸሎትን) አደርጋለሁ ምህረትንም እለምንላችኋለሁ።»

የሐሙስ ማታው ክፍል በማዕረገ―ቅፅል የተጎናዘለበት ሚስጢር ከአዘቦት ሌሊቶች በተለይቶ «በነብያችን ﷺ ላይ አብዝተን ሶለዋት ማውረድን በመታዘዛችኑ ነው»

እውነትን ባነገሰው የረሱለሏህ ﷺ አንደበት «ጁሙዐ» ቀኑም ሆነ ማታው ከተቀሩት ቀናቶች እና ሌሊቶች በተለይቶ ልዩ ክብር ተሰጥቶታል።

ይህ ማለት «የጁምዐ ቀን» ከሌሎች ቀናቶች፣ ማታው ክፍልም ከሌሎች ማታዎች ይበልጣል ማለት ነው።
በኢስላም ቀንና ሌሊት አሰያየም ረገድ ከኛ ሐበሻዎች በተለይቶ ሌሊቱ ቀኑን ቀድሞት ይሰየማል።

በዚህ መሰረት የጁሙዐ ማታው ክፍል እኛ «ሐሙስ ማታ» ስንል የሰየምነው ነው። እና «የጁሙዐ ቀንና ሌሊት» ከሌሎች ቀናቶች የተለዩ መሆናቸውንና በዚህ የተከበረ ቀንና ሌሊትም ከሌሎች ቀናቶች በተለየ መልኩ በሳቸው ላይ ሶለዋት ማብዛት እንዳለብን ያስተማሩን የአሏህ ነቢይ ﷺ ናቸው።

የአዋቂዎች ሁሉ አዋቂ፣ የብልሆች ሁሉ ብልህ፣ የአዛኞች ሁሉ ቁንጮ፣ የርኅራኄ ጥግ የሆኑት የኛ ነቢይ ﷺ
ሐሙስ ማታን በሶለዋት እንድናስውባት ሲያዙን ለኛ ካላቸው ወደር የለሽ እዝነት ነው።

አንድን ስራ ብቻ የሙጥኝ ብለን በመያዝ (በሰይዳችን ላይ ሶለዋት ማውረድን በማብዛት) ነገር ግን ያ ስራችን

ወንጀልን የሚያስምር፣ ደረጃንና ምንዳን የሚያስጨምር፣ ሪዝቅን (ሲሳይን) የሚያሰፋ፣ ድንገተኛና መጥፎ ችግሮችን የሚያጠፋ፣ በአሏህ የሚያስወድድ፣ የነቢዩን ﷺ ፍቅር የሚጨምር ፣ እሳቸውን በህልም እንድናይ የሚረዳ፣ እሳቸው ዘንድ በመልካም የሚያስወሳን እና እልቆ መሳፍርት የሌላቸው ማለፊያ ሰጤዎችን የሚያስቸረን መሆኑ ነው።

ነብያችን ﷺ እንዳሉት

«አሏህ የፍጥረታትን የስም መዝገብ ዶሴ የሰጠው መላኢካ አለ፤ እኔ በሞትኩ ጊዜ አንድ ሰው በኔ ላይ ሶለዋት ባወረደ ጊዜ መላኢካው ከቀብሬ በመሰየም ሙሐመድ ሆይ! እገሌ የእገሌ ልጅ ባንቱ ላይ ሶለዋትን አውርዷል ይለኛል፤ አሏህም ለዛ ሰው በየ አንዷ (ሶለዋት) ዐስር ምንዳን ሰጥቶ፣ ዐስር ወንጀሉን አፅድቶ፣ ዐስር ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።»

((ሓሪስ ኢብኑ አቢ ኡሳማህ፣ በዛር፣ ጦበራኒይና ሌሎቹም ዘግበውታል))

የተከበረው መላኢካ ስሙን ነቢዩ ዘንድ እንዲያደርስለትና አንዷ ስራው በአሏህ ዘንድ ከአስር እጥፍ ጀምሮ እንዲባዛለት የሚሻ
በትልቁ ሰዋችን፣ ነቢያችን፣ በሰይዳችን፣ በአይነታችን፣ በአዛኛችን፣ በአማላጃችን ሙሐመድ ﷺ ላይ ኒያውን ለጀሊሉ ያጠራ ሆኖ ሶለዋት ማውረድን ያብዛ።

የሶለዋቱ ፍሬ የሚገኘው ሶለዋቱ በጠራና በተስተካከለ መልኩ ሲባል ብቻ በመሆኑ የስራው ልከኛነት ሊያሳስበን ግድ ይላል።

ነቢዩ ﷺ በህልማችን ሃሴት ከሚዘራው ከዚያ አበባማ ፈገግታቸው ጋር መጥተው ያበሽሩን፤