AL-faruq-tube
6.13K subscribers
256 photos
88 videos
3 files
437 links
Download Telegram
#ያሸመሰል_ሁዳ

ይህንን ድንቅ መንዙማ #ኡስታዝ_ሰዒድ_አህመድ ምርጥ የተባሉ ቃላቶችን በመገጣጠም አሽረፈል ኸልቅን ያወደሱበት እንዲሁም ሁለቱ ማዲሆች #ሙዓዝ_ሐቢብ እና #ሙሐመዱል_አሚን ( የሚያምረው ) ባማረ ድምፃቸው ይህንን ድንቅ መንዙማ አሸብርቀውታል ።
እንዲሁም:-
#ዓብዱልከሪም_ሙሐመድ በብዙ ስራዎች የምናውቀው ቢሆንም ነገር ግን ከዚህ በፊት በ ሙዓዝ ሐቢብ እና በ ፉአድ ሸምሱ አል-ቡርዳ ሐብሽይ ነኝ የተሰኘው መንዙማ እንዲሳካ በጣም ሲለፋ እንደነበር እና በካሜራ ማንነት እንዲሁም በ ትወና እንደተሳተፈ የማይረሳ ነው ።
አሁን ደግሞ በዚህ ስራ ትልቁን ሚና የሚጫወተው ዓብዱል ከሪም እንደሆነ ማሳወቅ እንወዳለን ።

#ያሸምሰል_ሁዳ መንዙማ የድምፅ ቀረፃው ሙሉ በሙሉ አልቋ የቪዲዮ ቀረፃው ወሎ ሾክይ እንደሚሆን እንዲሁም ለቀረፃ ሙሉ ዝግጅታችንን እንደጨርስን ማብሰር እንወዳለን።

ይህንን ድንቅ መንዙማ በቅርብ ለአድማጭ እና ለተመልካች እናቀርባለን ።
Al- Faruq TUBE አል- ፋሩቅ ቲዩብ

አሰላም ዓለይክ ያሸምሰል ሁዳ
አሰላም ዓለይክ ያሸምሰል ሁዳ
ሙስጦፋ ያ በህረ ነዳ

ዱንያ ሃያቱ፣ አንጡራው ሃብቱ
እንዴው ያላንቱ፣ አንድም አይጠዳ
በኑር መኳያሁ ፣ኩለሁ አስጊጡኝ
በጅሁ አጠጡኝ ፣ሃውዱ ሲቀዳ
።።።።።
ከውከቡል አንፊ፣ ኑሪዩል ወስፊ
ሪቁሁ ሻፊ፣ ላ ለሁ ኒዳ
ፈይዱ ሙሰልሰል፣ የሌለው መሰል
ሚዛቡል ዐሰል፣ ዳኢም ሰርመዳ
።።።
የሩህ ቀለብ ነው፣ ሃልም ቃላቱ
ንጡህ ላበቱ፣ ሚስክ ሚያስቀዳ
ቤቱን ያነጥፋል ፣ ልብሱን ይሰፋል
ይንሰፈሰፋል ለዘመድ ባዳ
።።።።።
የኸሊል ሳቱ፣ ነዶ መጥፋቱ
ነውኮ ባንቱ፣ የዳነው ከእዳ
።።።
ጦይባ የሰከነው፣ የተዘየነው
ሽልማቴ ነው ውዛቴ ቆዳ
አንጎራጉራለሁ፣ላንቱ እቀኛለሁ
እጠራኋለሁ መሸም ማለዳ
።።።።።
ነፍሴ ሰክራለች፣ ተማርካለች
የአለሙን ኑር ሙስጦፋን ወዳ
አርሽ እስከ ሰራ ፣ላንቱ ተሰራ
።።።
አዕዘቡ ሸራብ፣ ጧሒሩል አንሳብ
ኢክሊሉል አንጃብ፣ ታጁል አምጀዳ
አጅመሉል መኽሉቅ፣ ዐዚሙል ኹሉቅ
ሷዲቁል መስዱቅ፣ አውሰዑል መጅዳ
።።።።።።
ሰይዱል አስያድ፣ ሙንተሃል ሙራድ
ሰበቡል ኢስዓድ፣ ናሺሩል ሁዳ
ሷሂቡል መቃም፣ ቲርያቁል አስቃም
ፈቀድ ለሁ ቃም ፣ ሃውደን መውሪዳ
።።።።
ክረምትም በጋ፣ በመሸም ነጋ
ዳኢም ይንጋጋ፣ ሶላት በአህመዳ
በቤተሰቡም በአል በሶህቡ
በሙንተሶቡ ዘመድም ባዳ
።።።።
(ኡስታዝ ሰዒድ አህመድ )

#AL_FARUQ_AUDIO_STUDIO 🎙

AND
..........T........... .........V..........
C O M I N G S O O N



https://www.youtube.com/c/ALFaruqTube
ብስራት አዘል መግለጫ

አሰላሙ ዓለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ

ውድ እና የተከበራችሁ የ "አል- ፋሩቅ" ቲዩብ ቤተሰቦች!
"አል-ፋሩቅ" ቲዩብ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ አሁን ላለበት የከፍታ ማማ ያበቃችሁት እናንተው የዩቲዩቡ ቤተሰቦች (ተከታታዮች) ናችሁና ላቅ ያለ ልባዊ ምስጋናችንን በአሏህ ስም ልናደርሳችሁ እንወዳለን።

በመቀጠል፦ ስለ "አል ፋሩቅ" ቲዩብ ውስን ገለፃን አድርጌ፣ ላሳውቃችሁና ላበስራችሁ ወደ ፈለግኩት አብዩ ጉዳዬ አቀናለሁ።

"አል-ፋሩቅ" ቲዩብ ስራውን "ሀ" ብሎ የጀመረው (2016) ላይ ሲሆን ወደ መንዙማዎች ብቻ የዞረው ግን (2019) ላይ ነበር።

ይህ ቲዩብ አላማው አድርጎ የተነሳው «ዲነል ኢስላምን ለወጣቱ በሚፈልገው መልኩ ማለትም በጥበብ ማስተማር ብሎም የታላላቅ መሻይኾቻችንን ዳና ማስቀጠልን" ነውና፣ አላማውን ከግብ ለማድረስ ሲልም እጅግ ብዙ ወጪዎችን ተቋቁሞ ከሁለት መቶ (200) በላይ የሚሆኑ ቪዲዮ ለተከታዮቹ (ለእናንተው) አድርሷል።

ብዙ ግብአት የፈጁት ክሊፖች ባማረ መልኩ ወደ እናንተ ይደርሱ ዘንድ በሙያና በጉልበት ደፋ ቀና ይሉ የነበሩት የካሜራ ባለ ሙያዎችና ኤዲተሮችም ቢሆኑ የስራውን ኸይራማነት ከማገናዘብ በቀና ልብ "ሊላህ" ሲሉ (ያለ አንዳች ክፍያ) ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በዚህ፦ በባለሙያዎች መልካም ፍቃደኛነትና ልባዊ ትጋት፣ በናንተም ውድ የ ዩቲዩቡ ቤተሰቦች የላቀ አበራታችነት መሰረት "አል―ፋሩቅ" ቲዩብ (ከሰባት ሚሊዬን አራት መቶ ሺህ) በላይ እይታዎችን (views) ሊያገኝም በቅቷል።
ታዲያ የጊዜ፣ የገንዘብና የጉልበት ግብአት ተፈስሶበት፣ እጅጉን ተባትሎበትና ተደክሞበት በዩቲዩባችን መስኮት የምናደርሰውን ውጤታማ ስራ "ተመልክተው" "አብሽሩ" ፣ "ቀጥሉበት" እና መሰል ሞራል አለምላሚ አስተያየታቸውን የሚለግሱን ወዳጆች ስፍር ቁጥር የላቸውም።

ሆኖም ከዚህ አስደሳች አስተያየት ባሻገር ወደ ብስራት ዜናው ስናልፍ :-
የዩቲዩቡን አቅመ ኃይል፣ የሚተላለፉ ስራዎችን ጥራትና ሸሪዓ-ገጠምነት ( ሁሉም ስራዎች ከመለቀቃቸው በፊት በታላላቅ ሸይኾች ሳንሱር ይደረጋሉና ከሸሪዓችን ጋር አይናቀፉምና ሸርዕ ገጠም ናቸው)፣ እንዲሁም በቲዩቡ ስር ያሉ ባለሙያዎች ጊዚያቸውን፣ እውቀታቸውንና አቅማቸውን ሰውተው ያለ ክፍያ መባተላቸውን ከቁብ በመቁጠር "አል ፋሩቅ" ቲዩቡ ሆነ ያነገበው ቀና አላማ ይበልጡኑ እንዲያድግ እንዲመነደግ፣ እንዲሁም በውስጡ ያሉ አጋዦችም ደግሞ የልፋታቸውን ክፍያ እያገኙ ኑረታቸውን እንዲገፉና እጅጉን ለተሳካለት ስራ እንዲሰነዳዱ የሚያደርግን፣ ማለፊያ የሰናይ ሰናይ ሃሳብ ከነ አድራጎቱ ከአንድ እህታችን ተሰነዘረልን።
ይኸውም «አል ፋሩቅ ቲዩብ ካለው ሙያዊና ሞራላዊ አቅም በተጨማሪ ይበልጥ እንዲሰራና ለውጤታማነት እንዲበቃ በቂ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎለት ወደ ፕሮዳክሽን ቢዘልቅ፣ ከዚያም ይበልጡኑ ወደ ቲቪ ስተንዳርድ ቢያድግ የሚል ሃሳብ ነው።

ይኸንን ማለፊያ ሃሳብ ያቀረበችልን እህታችን "ኢክራም አብዱረህማን" ስትሆን እርሷው ብቻዋንም ሙሉ ወጭውን በመሸፈን በአሏህ ፍቃድ አስፈላጊ መሳሪያዎችን በሙሉ እንድናሰነዳዳ በቅተናል።
እናም ቲዩባችን አስፈላጊው ቁስ ሁሉ ተሟልቶለት ወደ ፕሮዳክሽን ማማ ለመውጣቱ ብቸኛ ቁልፏ እህታችን "ኢክራም" ስትሆን የሌላ ግለሰብም ሆነ የድርጅት "እጅ" የሌለበት መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን!! ከእህታችን ኢክራም ጋር ያለው ውልም ቢሆን በድጋፍ ስም ብቻ ሳይሆን አብረን ተጣምረን እንድንሰራ ያክል መሆኑንም ጨምሬ እበይናለሁ!!

እናም ከስራ ባልደረቦቻችን ጋር በመወያየት በመሻይኾቻችን ምክር በመደገፍም ሸሪዐውን የጠበቀ ፕሮፖዛል ቀርፀን ከባለፉት በላይ የጠሩና ያደጉ ስራዎችን ለናንተው ለማድረስ ጉድ ጉድ እያልን እንገኘለን።

"አል ፋሩቅ" ሊያሟላ የሚገባውን ቅድመ ሁኔታዎች እና ፕሮሶሶችን ሲጨርስ በገዛ ቲቪው መስኮት ብቅ እስኪል ድረስም እንደ ፕሮዳክሽን ከሌሎች ቲቪዎች ጋርም የሚሰራ ይሆናል።
በመጨረሻም የኛ የዩቱዩብ ቻናል ከ 54 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው ሲሆን ሊንኩ ከዚህ ስር ከሚገኘው ውጭ ምንም አይነት የዩቲዩብ ቻናል እንደሌለን እና በኛ ተመሳሳይ ስም የሚለቀቁ ነገራቶች እኛን እንደማይወክሉ ማሳሰብ እንወዳለን።
https://www.youtube.com/c/ALFaruqTube

እቅዳችን ይሰምር ዘንድና በቅርቡ በቲቪያችን መስኮት እንድንገናኝ በዱዓ ታግዙን ዘንድ ውድ ተከታዮቻችንን
እንለምናለን፣

"የአል ፋሩቅ ቲዩብ መስራች ወኪል አል- ፋሩቅ
Al- Faruq TUBE አል- ፋሩቅ ቲዩብ
#ሸውቅ
(ናፍቆት)
#ፉአድ_መልካ

አዲስ ሱዳኒክ የነሺዳ ቪዲዮ ክሊፕ በ ሙንሺድ #ፉአድ_መልካ ተዘጋጅቶልናል
ኸሚስ ምሽት ይጠብቁን
#በጣም_ድንቅ_ስራ

የማትቀያየር ቀያያሪ ጌታ
ከፍጡር ማትከጅል
ካቅጣጫም ከቦታ

ከሙአዝ ሀቢብ 👇
በቅርቡ ከ ዋሪዳ ምዕራፍ 2 መድረክ ሌላ ግሩም ስራ ይዤላችሁ ብቅ እላለሁ( እመሰክራለሁ ) የተሰኘው ስለ ፈጣሪያችን አሏሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ሲፋዎች ሀያልነቱን አሸናፊነቱን አዛኝነቱን ጨምሮ የተወሰኑ ሀሳቦችን በ ጥልቀት ይዳስሳል
እነሆ ከ ስንኞቹ 4 መስመር ልጋብዛቹ

የሚሰወር የለም በ ድቅድቅ ጨለማ
የጥቁሯን ቁጫጭ ኮቴ የምትሰማ
ሀያልነትህም ልቅናህ ዘላለም
አንተን ተመክቶ የከሰረ የለም

ግጥሙን ሸይኽ :- ሰዒድ አህመድ ቆንጆ አድርገው ፅፈውታል
ዜማውን :- ሙዓዝ ሀቢብ አበጅቶታል

( ላ ኢላሀ ኢለሏህ ሙሐመዱረሱሉሏህ )
ተ ለ ቀ ቀ

https://youtu.be/2fOntoSZ77Y
https://youtu.be/2fOntoSZ77Y
https://youtu.be/2fOntoSZ77Y

ያ ሸምሰል ሁዳ
።።።።
ለግሶት መውላይ ውበት ከጠባይ
ታጣለት መሳይ ከውቦች ጓዳ
እስክሽር በልሜ መዳፉን ስሜ
ሆኗል ቀለሜ የርሱ ባለእዳ
።።።።።
ቅንድቦች መሃል በድር ይታይሃል
ሲባል ሰምተሃል ከጫሎች ዘንዳ
ጥርሱ ንጣቱ ኮከብ ማጥፋቱ
ደግሞ ፍንጭቱ ኑር ሚያፈነዳ
።።።።
መልኩ ተጀንበር ያበራ ነበር
ጥንቱን ሲደበር በውበት ማርዳ
ስንቱን ማረከው ቅንድብሁ ረቆ
ጉንጭሁ ፈንድቆ ከፅጌረዳ
።።።።።።።
ያ ኸይረል በሸር ባንቱ ልበሸር
ልገመሻሸር በሃድራው ሜዳ
ካሪፎች ይዤ ልምጣ ተጉዤ
ቀልቤን ገርዤ ከወንጀል ልፅዳ
።።።
በኔው ላይ አሁን ጥለሁ ጥላሁን
ልየው ስፍራሁን አልሁን እንግዳ
አንቱ የኔ እጣ ፣ የሎት ባላንጣ
የመጣው ይምጣ ካየሆት ወዲያ
።።።
ያ ታጀል አርሳል፣ ፍቅርሁ ያነግሳል
ሙሂብ ያወርሳል፣ ዙላል ከምንዳ
ይገመድላል ፣ፈይዱን ያድላል
ያሞናድላል ያላንዳች እዳ
።።።።
የፍቅርሁ ሃለት በጅግ ይገርማል
ይዝገመገማል ሌትም ማለዳ
የተወጋው ሰው ነው ሚላወሰው
ሚወሰወሰው ወዳንቱ ዘንዳ
።።።።።
ሲሻው ነው ሃኪም ሲሻውም ህመም
ሲሻውም ለምለም ጥንቅሽ አጋዳ
ይሆናል መሪ፣ ሲለውም ፈሪ
ልብን ጠፋሪ ማያስከነዳ
።።።።
እምቢን አያውቁ ከተጠየቁ
ውሃ ሚያፈልቁ ከጃቸው ሜዳ
ማሂ ቅረቡኝ ፣ ወዳንቱው ሳቡኝ
ከፍተሁ አስገቡኝ ፣ከርስዎ ጓዳ
።።።።
ሾንክዩ ውዱ፣ ያሏህ ዛሂዱ
አንቱን ቢወዱ፣ ተብለዋል ቅዳ
ቀልቡ ነው ዋና ፣ስጋው መንማና
የሾንኬ ማዕና፣ ዱረተል በይዷ
።።።
በሃያት ካሉት ፣ዱንያን ከጠሉት
ከሚያዳድሉት፣ ኢልሙን በማዳ
ከሱናው ኮቴ ካሏህ ከበርቴ
ከነ ሸይኽ ዛቴ፣ ይፈሳል ሁዳ
።።።
ገትዩን ማውሳት፣ አለው ልግሳት
አይጠብስም እሳት፣ መቃሙ ዘንዳ
እንዲያው ነው ወጉ ፣ ትልቅ ሲጠጉ
አይፈሩ አይሰጉ፣ ከዚያማ ወዲያ
።።።።።
ኢሽቁ ገረፈኝ አዝለፈለፈኝ
አክለፈለፈኝ የሸውቁ ናዳ
ነቢየ ሃብቴ ፣ ፈንታየ ቤቴ
እናት አባቴ ፣ይሁኖት ፊዳ
።።።።።።
እንከን የላቸው ውበት ከጠባይ
አይደል ቃል አባይ ፣ ወዳጅ ሚከዳ
የርሱ በረካው ስንቱን አፈካው
ኡመር ቢነካው ጨለጠ ሁዳ

።።።
በለዘብታ ነው ፣ ወግም ካወጉ
እግር አይዘረጉ፣ በሰዎች ዘንዳ
ያለን ሚቸሩ፣ ማያሳድሩ
ብለው ነገሩ አኢሻም ሰውዳ
።።
ሰውን አይንቁ፣ ጮኸው አይስቁ
ፈገግታው እንቁ፣ ሚያናግር ዲዳ
ጎራው ቢናድም፣ ሰማይ ቢወርድም
እናት አትወልድም እንደ አህመዳ
።።።
።።
ገራገር ሸጋ በመሸም ነጋ
አንቱን ፍለጋ፣ ሰልማን ገባ እዳ
ሙዐዝዋየ፣ ይላል እየየ
አንቱን ካላየ፣ እንጃለት ወዲያ
።።።
ያናብስት አዛዥ የጀግና አለቃ
የፍልሚያው ሳንቃ፣ በርሱ ሚነዳ
ቅዋው ያርባ ሰው፣ የለም ሚደርሰው
አንከላበሰው፣ የጀህልን ናዳ
።።።።
ኢብራሂም ውዲ፣ ስራቸው ሃዲ
ሶስት ይሁን አንዲ፣ አልዋሹም ወዲያ
ነበሩ መሪ ፣ሐቅ አስተማሪ
ካሏህ ከባሪ፣ ትዛዝ ሚቀዳ
።።።
ሙላው ነቢያት፣ በማማር ግባት
ሆነዋል ነባት፣ የምርጦች ፃዳ
ያዩብ አካሉ አልተላም አሉ
ከፀያፍ ሁሉ ፣ ጅስሙ የጠዳ
አህመደል ሃዲ ፣ያንቱ ሙሂቡ
ጦሽ አለ ልቡ፣ ከረውዷው ዘንዳ
ግንባርሁ ጣለው በድር የመሰለው
ሸሪካ የለው ፣ የርሱ ሲያዳ
።።።
ዩሱፉ ሲያልፉ እጅ የከተፉ
ማርኳቸው ወስፉ፣ የመልኩ ፃዳ
አምሮ የገነነው የተዘየነው
ተቆንጥሮ ነው ከኛው አህመዳ
።።።
ሚሳልም የለው ጠባይ አካሉ
ከውሰር ጠለለው፣ በጁድ ማኢዳ
አንቱን ነውንጂ ሌላን አላልኩም
ከቶ አላረፍኩም ይዤም መከዳ
።።።።
ተስመንምናለች፣ ናፍሴ ናፍቃለች
ልትበር ደርሳለች ነፍሴ አንቱን ወዳ
ዱንያ ሃያቱ፣ አንጡራው ሃብቱ
እንዴው ያላንቱ፣ አንድም አይጠዳ
ዱንያ ሃያቱ፣ አንጡራው ሃብቱ
እንዴው ያላንቱ፣ አንድም አይጠዳ
በኑር መኳያሁ ፣ኩለሁ አስጊጡኝ
በጅሁ አጠጡኝ ፣ሃውዱ ሲቀዳ
።።።።።
ከውከቡል አንፊ፣ ኑሪዩል ወስፊ
ሪቁሁ ሻፊ፣ ላ ለሁ ኒዳ
ፈይዱ ሙሰልሰል፣ የሌለው መሰል
ሚዛቡል ዐሰል፣ ዳኢም ሰርመዳ
።።።
የሩህ ቀለብ ነው፣ ሃልም ቃላቱ
ንጡህ ላበቱ፣ ሚስክ ሚያስቀዳ
ቤቱን ያነጥፋል ፣ ልብሱን ይሰፋል
ይንሰፈሰፋል ለዘመድ ባዳ
።።።።።
የኸሊል ሳቱ፣ ነዶ መጥፋቱ
ነውኮ ባንቱ፣ የዳነው ከእዳ
።።።
ጦይባ የሰከነው፣ የተዘየነው
ሽልማቴ ነው ውዛቴ ቆዳ
አንጎራጉራለሁ፣ላንቱ እቀኛለሁ
እጠራኋለሁ መሸም ማለዳ
።።።።።
ነፍሴ ሰክራለች፣ ተማርካለች
የአለሙን ኑር ሙስጦፋን ወዳ
አርሽ እስከ ሰራ ፣ላንቱ ተሰራ
።።።
አዕዘቡ ሸራብ፣ ጧሒሩል አንሳብ
ኢክሊሉል አንጃብ፣ ታጁል አምጀዳ
አጅመሉል መኽሉቅ፣ ዐዚሙል ኹሉቅ
ሷዲቁል መስዱቅ፣ አውሰዑል መጅዳ
።።።።።።
ሰይዱል አስያድ፣ ሙንተሃል ሙራድ
ሰበቡል ኢስዓድ፣ ናሺሩል ሁዳ
ሷሂቡል መቃም፣ ቲርያቁል አስቃም
ፈቀድ ለሁ ቃም ፣ ሃውደን መውሪዳ
።።።።
ክረምትም በጋ፣ በመሸም ነጋ
ዳኢም ይንጋጋ፣ ሶላት በአህመዳ
በቤተሰቡም በአል በሶህቡ
በሙንተሶቡ ዘመድም ባዳ
ግጥም
ኡስታዝ ሰኢድ አህመድ