"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ኤልሮኢ
ሞገድ ሲመታኝ

ሞገድ ሲመታኝ ማእበሉ
ማን ያድነዋል ሁሉም ሲሉ
በሰላም አለፍኩ በፀጥታ
ሁሉተችሎ ባንተጌታ

ባንተስ ቁስል ተፈወስኩኝ
ጌታ በፍቅርህ ተማረኩኝ
ሞቴን ሽረኀው ባንተሞት /2/
ይኀው አቆምከኝ በሂወት /2/

ደጅህ ሲጠና ስማፀንክ
መቼ ጨከነጌታ ልብ
እንደቀራጩ አጎነበስኩ
ምህረት ፀጋህን ከጂህ ለበስኩ

ዘውትር እልል ብልብዘምር
ስለገባኝ ነው ያንተፍቅር
ጌታ ምጠራው ስምህን/2/
ለውጠኀው ነው ታሪኬን/2/

አይኖች አያዩ ካንተበቀር
የምትወደድ ምትፈቀር
ዘመድ ወገኔ ሆነህኛል
እኔን የሚችል የት ይገኛል


💚@aleroe💚
ኤልሮኢ፡
✞ ህፃን ንኡስ

ህፃን ንኡስ /3/
ዘይትፈርእ ትዐዛዘ ንጉስ /2/


💚@aleroe❤️
ኤልሮኢ
#ወዳጄ ሆይ!

የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡

አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡ ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@aleroe
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
ኤልሮኢ
"ሌቦች ወርቅና ብር ያለውን እንጂ ድርቆሽና ገለባ እንዲሁም ሰንበሌጥ ያለውን ቤት አይበረብሩም፡፡ ዲያብሎስም የሚያጠቃው (የሚፈትነው) መንፈሳዊ ምግባራትን የሚያበዙትን ሰዎች ነው፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


@aleroe
ኤልሮኢ
ጥር 19/05/11 ዓ.ም.
መዝሙር እሙነ ኮነ ልደቱ

#በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ፡፡

ዲ/ን 2ቆሮ 1÷13_ፍ.ም
ን/ዲ 1ዮሐ 2÷22_ፍ.ም
ን/ካ ግብ፡ሐዋ13÷20_28

#የዕለቱ_ምስባክ

እግዚአብሔር እግዚእ አስተርአየ ለነ
ግበሩ በዓለ በትፍሥሕት በኀበ እለ ያስተሐምምዎ
እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ መዝ ፻፲፯፥፳፯

#ትርጉም
ጌታ እግዚአብሔር ተገለጠን 
በሚያስተነትኑበት በደስታ በዓልን አድርጉ
እስከ መሠዊያው ቀንድ ድረስ

#የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ 2÷42-ፍ.ም
#ቅዳሴ፦ ዘዲዮስቆሮስ


👉 @aleroe
ኤልሮኢ
✞ በማህፀን ቅኔ

በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
በተራራማው ሀገር በኤፈሬምከተማ
ዩሀንስ ይናገር በረሀ ያደገው
ድንግል ስትናገር ምን እንዳዘለለው

የናቱማህፀን የቅኔርስቱነች
ድንግል ያምላክ እናት ፊቱ ስለቆመች
በሀሴት ዘለለ ዘመረ በደስታ
ከድንግል ሲወጣ ታላቁ ሰላምታ

በድንግል ማህፀን ስላየጌታውን
ከመወለድ ቀድሞ ሰማነው መዝሙሩን
ትንቢቱ ሲፈፀም በሆድዋሲነግስ
ሰገደላምላኩ የስድስትወር ፅንስ

ጀመረስብከቱን ገና ሳይወለድ
ተፈጥሮ መችቻለ ነብዩን ለማገድ
አፉ ተከፈተ በታለቅ ምስጋና
በናቱ ማህፀን ድምፅን አሰማና

የዩሀንስ እናት አሰልሳቤት ገረማት
ልጃዋ በማህፀን ቅኔ ሲቀኝባት
ድምፅን ከፍ አረገች ሀገር እንዲሰማ
ሞላት መንፈስ ቅዱስ ለመዝሙር ለዜማ

✞ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ✞


@aleroe
ኤልሮኢ:(ስነ ፅሁፍ)
✥ሞት ሆይ ተጠየቅ✥

💐ሞት ሆይ ተጠየቅ ኤልያስን ያስነጠቀውን ሄኖክን ከሞት የሰወረውን ሞትን በሞቱ የገደለውን በትንሣኤው ለትንሳኤያችን በኩር የሆነውን ጌታ የጸነሰችውን ለሞትህ ሞት የሆነውን ጌታ የወለደችውን ድንግል ትቀርባት ዘንድ እንዴት ደፈርክ?
🌹ሞት ሆይ ተጠየቅ ለሕያው እግዚአብሔር መቅደስ የሆነችውን ንጉሡ ከነ ሠራዊቱ(መላእክቱ) የከተመባትን ከተማ በላይ ሳይጎድል በታችም ሳይጨመር የተወለደባትን ቅድስት ትይዛት ዘንድ እንዴት ደፈርክ?
ሞት ሆይ ተጠየቅ ሰማይ ዙፋኑ ምድር መከየደ እግሩ የሆነለትን በሁሉ ያለ ሁሉን የሚወስን የሚወስነው ምንም ነገር የሌለን የተሸከመችን ድንግል ትቀርባት ዘንድ ምን አስቻለህ?
🌷 ሞት ሆይ ተጠየቅ ወለተ ኢያኢሮስን እንቅፍ ከሚመስል ሞት ተነሺ ብሎ ያስነሳትን አልአዛርን ናብሎ ከሞቱ የጠራውን ከመገንዙ ፈቶ ይመላለስ ዘንድ ያስቻለውን የሲኦል ደጆች በቃሉ የሚሩድለት ጌታ የተገኘባት ድንግልን ትቀርብ ዘንድ ምን አጸናህ?
🍀ሞት ሆይ ተጠይቅ? እርሱስ ለእርሱም መልስ የለውምና ከሊቁ ጋር እንዲህ እያልን እናድንቅ ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ ሞትማ ለሚሞት ሰው ይገባል የማርያም ሞት ግን ለሁሉ ይደንቃል!
እንኳን የእመቤታችንን ዕረፍት ለምናስብበት በዓል አደረሳችሁ!

ባሮክ(ኢብሎጊቶስ)

@aleroe
ኤልሮኢ:(ስነ ፅሁፍ)
// አትጥፊ ጨረቃ //
🌙🌑

የዘመኑ ትውልድ ከእንቅልፉ እስኪነቃ
ማዬቱን እስኪያምን የአለምን ጠበቃ
ምስክር ነሽ አንች አትግቢ ጨረቃ
ይዩሽ የማያምኑ ማየት ያልታደሉ
የጨረቃ ግርዶሽ ተከሰተ ላሉ
ከእውነት ተደብቀው ጥምቀትን የጠሉ
ታምር በጨረቃ ይዩልን የት አሉ
አየሽ ጨረቃዬ ማየት ያልታደለ ማሰተዋል ያቃተው
እውነት ግን ታምር ነው? ሲል ማመን ላቃተው
ህሌናውን ጋርዶት ሰው መሆን ለማያምነው
የጥምቀትን ሚስጥር ተረድቶ እስኪነቃ
ምስክር ነሽ እና አንች የኛ ድንቡልቃ
በፈጠረሽ አምላክ አትጥፊ ጨረቃ!!

#ይሄንን ጽሑፍ ሌሎች ክርስቲያን እህት ወንድሞቻጅን እንዲደርስ👉 Share ያድርጉ...

✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@aleroe @aleroe @aleroe
@aleroe @aleroe @aleroe
@aleroe @aleroe @aleroe
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
ኤልሮኢ፡
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን
አስተርእዮ ማርያም
ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኩሉ"
ሞት ለሚሞት ሰው ይገባዋል
የማርያም ሞት ግን በጣም ያስደንቃል
እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕተ ንጹሃን ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ታላቅ አመታዊ በዓል ( ለአስተርእዮ ማርያም) በሰላም በጤና አደረሳችሁ:: አደረሰን!

✞ አስተርእዮ ማለት? መታየት መገለጽ ነው
እመቤታችን ጥር ሃያ አንድ ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይቶ በደመና ተነጥቃ ወደ ገነት በመግባት ለጻድቃን ሰዎችና ለመላእክት በሰማይና በምድር ተገልጣ ጸጋና ክብሯ የተገለጸበት እለት በመሆኑ በዓሉ አስተርእዮ ማርያም ይባላል::

✞ ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድ የእመቤታችንን ሞት አስደናቂ መሆኑን እንዲህ ሲል ገልጦታል
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኩሉ"
ሞት ለማናቸወም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል

የእመቤታችን አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁንና እመቤታችን ከእናትና ከአባቷ ዘንድ ሦስት አመት በቤተ መቅደስ አስራ ሁለት አመት ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሰላሣ ሦስት አመት ከሦስት ወር በዮሀንስ ወልደ ነጐድጓድ ዘንድ አስራ አራት አመት ከዘጠኝ ወር በጠቅላላው ስልሣ አራት አመት ሲሆናት ጥር 21 ቀን በ49 ዓመተ ምሕረት ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች::

እመቤታችን ጥር ሃያ አንድ ቀን ዕረፍት በሆነበት ዕለት ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ ለማሳረፍ ወደ ጌቴሰማኒ መካነ ዕረፍት /የመቃብር ቦታ/ ይዘዋት ሲሆዱ አይሁድ በቅንዓት መንፈስ ተነሳስተው ቀድሞ ልጇን በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ አረገ እንደገናም ተመልሶ ይህን ዓለም ለማሳለፍ ይመጣል እያለ በማስተማር ሕዝቡን ፈጽመው ወስደውታል አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷንም እንደ ልጇ ተነሳች አረገች እያሉ በማስተማር ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለም ኑ ተሰብሰቡና በእሳት እናቃጥላት ብለው ተማክረው መጥተው ከመካከላቸው ታውፋኒያ የተባለው ጎበዝ አይሁዳዊ ተመረጦ ሄደ::

የእመቤታችንን ሥጋ የተሸከሙትን አልጋ ያዘ የአልጋውንም ጥራዝ በያዘ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁለት እጁን ሰለቆረጣቸው ከአልጋው ጫፍ ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ ታውፋንያ በፈጸመው ድርጊት ተጸጽቶ ወደ እመቤታችን ስለተማጸነ በኀቡዕ ተአምር የተቆረጡ እጆቹን እንደቀድሞ አድርጋ ፈውሳዋለች::
{ስንክሳር ዘጥር}

✞ ለበቁ ቅዱሳን ተአምሯን የገለጸች እመቤታችን ለእኛም ለልጆቿ ከልጇ ከወዳጇ በአማላጅነቷ ምሕረትን ይቅርታው ታሰጠን::አሜን!
ለተጨነቁ በስደት ላሉ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ የሚሰቃዩ ወገኖቻችን ትፈውስልን የእናታችን የአዛኝቷ ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይሁን አሜን::

@aleroe
ኤልሮኢ:
ሞትማ ለመዋቲ ይገባል

ሞትማ ለመዋቲ ይገባል ይገባል(2)
የድንግል አሟሟት እጅጉን ይደንቃል(2)

ለልጇ ስትነግር ሞት እንደምትፈራ(2)
ወሰዷት በሃሴት መላእክተ ሐራ(2)
ጭንቀቱ ሳይገጥማት ሳታስብ ድንገት(2)
እንደ እንቅልፍ ወሰዳት ያ መልአከ ሞት(2)

አዝ ///

ይገርማል ይደንቃል የድንግል ፍልሰታ(2)
በምስጋና አረገች ከልጇ ተጠርታ
በይባቤ አረገች ከልጇ ተጠርታ
እያሸበሸቡ መላእክተ ሰማይ(2)
ወስደው አቀረቧት ከልጇ መንበር ላይ(2)

አዝ //

ሱባኤ እንደገቡ እንደ ሐዋርያት(2)
እኔም ከቤት ወጣሁ አንቺኑ በመሻት(2)
ትንሳኤሽን በክብር እንዳሳየሻቸው(2)
እኔንም ለዚህ አብቂኝ ብርሃንሽን እንዳየው(2)


💚@aleroe💚
💛@aleroe💛
@aleroe
ኤልሮኢ:
# መልአከ ሰላምነ

መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ኡራኤል/2/
ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለመድኃኔዓለም/2/

ትርጉም ፦
አንተ የሰላም መልአክ ሊቀ መላእክት ዑራኤል (2)
ለምን ስለኛ ፀልይልን አሳርግ ፀሎታችንን በመንበሩ ፊት ለመድሃኒአለም (2)


💚@aleroe
ኤልሮኢ፡

.....ትህትና በአባቶች ሕይወትና ትምህርት ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ ይገኛል። ቅዱስ ያዕቆብ እንዲህ ብሏል ስለ ትህትና ማስተማር እፈልጋለሁ። ደግሞ እፈራለሁ። ስለ እግዚአብሔር ለመናገር እንደሚፈራ ሰው እመስላለሁ። ምክንያቱም ትህትና መለኮት ሰው ሆኖ በምድር ሲገለጥ የተጠቀለለበት መጎናጸፊ ነውና። ሰው ሆኖ በአጭር ደረት በጠባብ ቁመት የመገለጡም ምሥጢር እጅግ አስደናቂ በሆነ በትህትናው ነው። ይሄ ሁኔታው ያስደነቀው ነቢዩ ኢሳይያስ "ያልተጠባበቅነውን የጽድቅ ሥራህን ባደረግህ ጊዜ ወረድህ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ" ኢሳ. 64፥4 ብሏል። ሰይጣን ትሁት ሰው ሲያይ የሚፈራው በትሁት ሰው ውስጥ የፈጠረውንና በትህትና ያሸነፈውን እግዚአብሔር ስለሚያየው ነው።

@aleroe
ኤልሮኢ፡(ስነፅሁፍ)
ምንም አይምሰልህ

የምትሰራው ስራ ሰውን ካልበደለ፣
ክፋትና ተንኮል በልብህ ከሌለ።
ጠንቅቀህ ከፈፀምክ ማድረግ ያለብህን፣
ማንንም ካልጎዳህ ካመንክ አምላክህን።
ላንተ ጥቅም ብለህ ካልገፋህ ሌላውን፣
ይቅርታ ከለመንክ አምነህ ጥፋትህን።
የምታውቀው ታሪክ የምታውቀው ነገር፣
እንዳልሆነ ሆኖ ሲወራ ሲነገር።
የለብህምና ዝም ብሎ መስማት፣
ቀስ ብለህ ብትሞክር ለመስጠት እርማት።
ከእኛ ሌላ አዋቂ ፍፁም የለም ባዮች ፣
የወሬ አንበሳ የተግባር አንካሶች፣
የነገር ሱሰኛ የወሬ ጥመኞች።
ምንም እንደማታውቅ አድርገው ቢቆጡርህ፣
እውቀቱ ካንተ ጋር ታዲያ ምን ቸገረህ፣
አምላክ ካንተ ጋር ነው ምንም አይምሰልህ።

@aleroe
ኤልሮኢ:
✞ የፍቅር እናት

የፍቅር እናት የሰላም /2/
ይናፍቀኛል ስምሽ ሳልጠራው ስቀር ማርያም

በሂወቴ ውስጥ በኑሮዬ
ቅደሚ ከፊት ከሀኅላዬ
ተደላደለ ልቤ
አንቺ አለሽና ካጠገቤ

ምኞቴም ይስመር ትልቅ ህልሜ
ልለፍ ወደፊት ተቋቁሜ
የጌታዬ እናት ነሽ
ሀይልን ያረጋል ፀሎትሽ

እንዴት ቀራለው ከመንገድ
አደራ እናቴ አስቢኝ
ከሚያስጨንቀኝ ጠላት
ለሚያሳድደኝ አትስጪኝ

ትላንትም ዛሬም አመስጋኝ ነኝ
የለም ለነገየሚያስፈራኝ
ሜዳይሆናል ተራራ
ልጅሽ ስላለ ከኔ ጋራ

#ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

💚@aleroe💚
ኤልሮኢ:
ጥር 26/05/11 ዓ.ም.

መዝሙር ተወልደ ኢየሱስ

#በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ፡፡

ዲ/ን ሮሜ 1÷1_12
ን/ዲ 1ጴጥ 1÷13_22
ን/ካ ግብ፡ሐዋ10÷1_11

#የዕለቱ ምስባክ፦ መዝ 47፥8

በከመ ሰማዕነ ከማሁ ርኢነ
በሀገረ እግዚአ ኃያላን በሀገረ አምላክነ
እግዚአብሔር ሣረራ ለዓለም::

#ትርጉም

እንደሰማን እንዲሁ አየን
በሠራዊት ጌታ ከተማ በአምላካችን ሀገር
እግዚአብሔር ለዓለም አጸናት

#የዕለቱ ወንጌል፦ ሉቃ 2፥36 - ፍጻሜ
ቅዳሴ፦ ዘዲዮስቆሮስ

👉 @aleroe
ኤልሮኢ፡

…… አትማረኝ
--------------
በጣና ገዳማት ውስጥ የአቡነ አሳይ ዋሻ አለ በዚህ ዋሻ አንድ ያልተማረ የቤተክርስቲያንን ትምህርት የማያውቅ ሰው ጸሎት ሲጸልይ አንድ አባት በጀልባ ተሳፍረው ይመጡና ያገኙታል።

ወደ ደሴቷም አረፍ ልበል ብለው ሲገቡ ያ ወጣት ሲጸልይ ይሰሙታል ቀረብ ብለው ቢያደምጡ ይህ ሰው የሚጸልየው "አትማረኝ" እያለ ነው።

እኝህ አባት በጣም ይደነግጡና እንዲህ ያለ ጸሎት አለ ወይ አትማረኝ የሚል ማን ነው ያስተማረህ ሲሉት አንድ መነኩሴ ነው ያስተማሩኝ አላቸው።

እሳቸውም ይህማ ሰይጣን ነው በመነኩሴ ተመስሎ ያስተማረህ እንጂ አትማረኝ ብሎ ጸሎት የለም ብለው "አቡነ ዘበሰማያትን" አስተማሩት። ይኽ ሰው እንደምንም ታግሎ አባታችን ሆይን ከተማረ በኋላ እኝህን አባት ያሰናብታቸዋል።

እሳቸውም በጀልባ ተሳፍረው መንገድ ሲጀምሩ ይኽ ወጣት ወደ ቀደመ በዓቱ ገብቶ መጸለይ ሲጀምር ያን ጸሎት ረሳው። ምን ነበር ያስተማሩኝ ብሎ ቢያስብ ጠፋበት። ከበዓቱም ሮጦ ወጥቶ በጀልባ ተሳፍረው የሚሄዱትን አባት አስቁሞ "ምን ብለው ነው ያስተምሩኝ?" ብሎ ጠየቃቸው እኝህም አባት ሲያዩት ውሃ ላይ ቆሟል፣ በውሃ ላይ ነው ሮጦ የመጣው አትኩረው ቢመለከቱት ውኃው ላይ እንደቆመ ነው።

"በል የእኔ ልጅ እንደቀድሞው አትማረኝ እያልክ ጸልይ" አሉት ይባላል።

ወጣቱ ባለማወቅ በሚጸልየው ጸሎት ውስጥ በቅቶ ነበር። እግዚአብሔር የሰማው ያለውን ሳይሆን የልቦናውን ነው።

የምንጸልየው ጸሎት የተዘበራረቀ ቢሆንም እንኳን እግዚአብሔር እያቃና ይሰማዋል። ስለዚህም ከመጸለይ ወደ ኋላ አንበል እኛ የምንጸልየው ባይገባንም በዙሪያችን ያሉት አጋንንቶች ገብቷቸው ይሸሻሉ።

@aleroe
ኤልሮኢ:
……

በዓለም መደሰት ወደ እግዚአብሔር ሊመራችሁ አይችልም ከእርሱ ያርቃችኋል እንጂ። የዓለም ፍቅር ወደ ልባችሁ ከገባም አሳቦቻችሁና አመለካከቶቻችሁ መናጋት ይጀምራሉ ።

በዚህ ጊዜ እናንተ ተስማሚ ነው ብላችሁ ያመናችሁበትን አመለካከት እንዲህ እያላችሁ መጠየቅ ትጀምራላችሁ ፦ ይህንንና ያንን ማድረግ ስሕተቱ ምንድር ነው? እንዲህ ባለው ነገር ብደሰት ኃጢአቱ ወይም ጉዳቱ ምንድር ነው? ከዚህ በኋላ በመመርያዎችና በዋጋቸው የሚደረገው ሰንሰለታማ ክርክር ይጀምራል! ! ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ክርክሮችና ሙግቶች ምክንያት የሚሆነው ለእግዚአብሔር ያላችሁ ፍቅር መቀነስ ነው ።

ስለዚህ ልባችሁን በዓለም ፍላጎቶች ወይም ምኞቶች ውስጥ አታስቀምጡ ደጁ ሰፊ ከሆነ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት አትችሉምና [ማቴ 7÷13]

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

@aleroe
ኤልሮኢ:
እናመስግነው

እናመስግነው በአንድነት
ቸርነቱ ለማያልቅበት/2/
አዝ.............
የሰማዩን አምላክ እናመስግነው
ህይወቱን ለሠጠን እናመስግነው
እናመስግን ጌታን እናመስግነው
በአንድነት ሆነን እናመስግነው
ለኛ ያደረገው እናመስግነው
ከቶ እያልቅምና እናመስግነው
አማኑኤል ቸር ነው እናመስግነው
ይድረሰው ምስጋና እናመስግነው

ድንግል ማርያም ስጦታ ናት
በምልጃዋ ለሚማፀናት/2/
አዝ.........
ስሞን ለሚጠሩ ለሚማፀናት
በፍቅሯ ተስበው ለሚማፀናት
ምህረት ያገኛሉ ለሚማፀናት
ወደሶ ተማፅነው ለሚማፀናት
እሩሩ ናትና ለሚማፀናት
ለሚለምናት ለሚማፀናት

ተክለሀይማኖ ሀዋርያ
ፀለየላት ለኢትዬጽያ/2/
አዝ...........
ኢትዬጽያዊው ብርሀን ተክለሀይማኖት
ታላቁ መምህር ተክለሀይማኖት
ቢነገር አያልቅን ተክለሀይማኖት
የተሰጠህ ክብር ተክለሀይማኖት
የተጋህ በፀሎት ተክለሀይማኖት
በ1 እግርህ ቆመህ ተክለሀይማኖት
አባቴ ተክልዬ ተክለሀይማኖት
ልዩነው ፀጋህ ተክለሀይማኖት

ገብረመንፈስ ቅዱስ አባታችን
በረከትህ ይግባ ቤታችን/2/
አዥ.........
የአምላክ ባለሞል ግባ ቤታችን
በፅድቅ ያበራህ ግባ ቤታችን
ቃልኪዳንህ ፀንቶል ግባ ቤታችን
ለተማፀኑህ ግባ ቤታችን
ህይወትህ አብነት ግባ ቤታችን
ሆኖታል ትውልዱ ግባ ቤታችን
በኪዳንህ ያርፋል ግባ ቤታችን
ያለው በመንገዱ ግባ ቤታችን

የልዳው ሠማእት ጊዮርጊስ
ልትባርከን ና በፈረስ/2/
አዝ..........
የእውነት ተጋዳይ ና በፈረስ
የአምላክ ምስክር ና በፈረስ
3 ጊዜ ሞተህ ና በፈረስ
የተሰጠህ ክብር ና በፈረስ
መከራን የታገስክ ና በፈረስ
ለስጋ ሳትሳሳ ና በፈረስ
አድነን ጊዮርጊስ ና በፈረስ
ከዓለም አበሣ ና በፈረስ
የቤሩቱ ኮከብ ጊዮርጊስ
ልትባርከን ና በፈረስ/2/



💚 @aleroe 💚
ኤልሮኢ:(ምክረ አበው)
……
አባት ልጁ ከቤት ወጥቶ መኪና እንዳይገጭበት፣ ወድቆ እንዳይሰበርበት፣ ድንገት በአከባቢው የሚያልፉ ከብቶች ገፍተው እንዳይጥሉበት መውጫው በሩን ይዘጋበታል፡፡ ይኼኔ ልጁ በሩ ለምን እንደተዘጋበት አያውቅም፤ ልጅ ነውና፡፡ አባቱ የጠላው መስሎትም ምርር ብሎ ሊያለቅስ
ይችላል፡፡ ማልቀስ ብቻ አይደለም፤ ቂምም ሊይዝበት ይችላል፡፡ አባቱ ግን በሩን የዘጋበት ምክንያት ያውቃል፤ ጠልቶት ሳይሆን ይጐዳበታልና ልጁ ቢያለቅስም አይከፍትለትም፡፡

እውነተኛው አባታችን እግዚአብሔርም አንዳንድ ጊዜ የማይጠቅሙን ይልቁንም ክፉኛ ሊጎዱን የሚችሉ በሮችን ይዘጋብናል፡፡ ከእውቀት ከፍለን የምናውቅ ልጆቹ ነንና አባታችን ለምን እንደዘጋብን ለጊዜው አይታወቀንም፤ ብቻ የከለከለን ይመስለናል፡፡ በመሆኑም ቂም ልንይዝበት ልናማርረውም እንችላለን፡፡ እርሱ ግን ይታገሠናል፤ ለእኛ
የሚያስባት መልካሚቱን በር እርሱ ያውቃታልና ይከፍትልናል፤ በእኛ እይታ መልካም የምትመስለንን ነገር ግን ክፉይቱን በር ይዘጋብናል፡፡

ቅዱስ አባት ሆይ ስለ ከፈትክልን ብቻ ሳይሆን ስለ ዘጋህብንም በር እናመሰግንሃለን ልንለው ይገባል። አሜን!

@aleroe
ኤልሮኢ፡(ስነ ፅሁፍ)

…አንድ አካል

ጳውሎስ እግር ሆኖ በአህዛብ ሀገር፣
ሲሮጥ አይተነዋል ለቃል ሲመሰክር።
እጅ ነበር ጴጥሮስ ሁሉን የሚባርክ፣
ሶስት ሺህ ሰራዊት በአንዴ የሚማርክ።
የዮሀንስ ዓይን ከሩቅ የሚያስተውል፣
ፍጢሙ ላይ ቆሞ ሰማይ የሚያካልል።
ሉቃስም ጣቱ ነው ቃል የሚፃፍበት፣
የፈጣሪው እናት መልኳ የሚሳልበት።
አንደበተ ትሁት ያዕቆብ መምህር፣
ባለፀጋዎቹን ሲወቅስ የማያፍር።
ማቴዎስም መጥቷል ከቀራጭነቱ፣
የፈጣሪ አካል ሆኗል ሰውነቱ።
ቅዱስ ፊሊጶስም እውነተኛ አባት ነህ፣
ታሪክህ ይታወቅ በእኛ በልጆችህ፣
ለህዝበ ኢትዮጵያም ይድረስ በረከትህ።


@aleroe
ኤልሮኢ:
"አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ"

ከእለታት አንድ ቀን አንድ ወጣት የንስሀ አባቱን ለማግኘት ተንስቶ ወደ ቤተክርስቲያን ይሄዳል። ፀሎቱን አድርሶ ግቢ ውስጥ ቁጭ እንዳለ አባ ይመጡና በመስቀል ባርከው ደባብሰው ወደ በአታቸው ይዘውት ይገባሉ። ታድያ ልክ እንደ ገባ የክርስቶስን ስነ ስቅለት የእሾሁን አክሊል ያይና በሀሳብ ወደ ቀራንዮ ይሄዳል። አባ ምነው ልጄ እኔን እዚህ ትተህ አንተ ወደ ቀራንዮ ሄድክ ሲሉት ከሀሳቡ ባህር ወጥቶ ቁጭ አለ።

አባ አየህ ልጄ ምን ሆነ መሰለህ ብለው ጨዋታ ጀመሩለት። "በአንድ ሀገር ትልቅ የባቡር መንገድ ነበር ታድያ የባቡሩ መንገድ ታቹ ባህር ነው በጣም ትላልቅ አዞዎች አሉበት። አንድ ቀን ታድያ ይህ መንገድ ኃይለኛ ዝናብ በመጣሉ ምክንያት ይፈርሳል። አንድ ህፃን ልጅ ይህን ሁኔታ አይቶ ኖሯል ባቡሩ እዛ ቦታ ሳይደርስ ለማስቆም ወሰነና የአደጋ ምልክቶችን ፅፎ በተለያየ ርቀት 2 ቦታዎች ላይ አስቀመጠ። ከዚያም 3ኛው ላይ ባንዲራ ይዞ እራሱ ቆመ ባቡሩም መጣ ልክ የመጀመሪያውን የአደጋ ምልክት ሲያይ ይህ የዱርዬዋች ስራ ነው ብሎ ተበሳጭቶ አለፈ። ሁለተኛውንም እንዲሁ አለፈ። በሶስተኛው ህፃኑ ጋር ደረሰ ጥሩንባውን እያጮኸ ዘወር በል አለው ልጁ ግን በጭራሽ ዘወር ሳይል ባቡሩ እዛው ፈጨው የባቡሩ አሽከርካሪ በጣም ደነገጠ ተሳፋሪዎችም ወረዱ ልጁን ሲያዩት የለም ደቋል። ነገር ግን በእጁ የነበረው ወረቀትና ባንዲራ ወድቆ አገኙት አንስተው ሲያነቡት በዝናቡ ምክንያት ድልድዩ መፍረሱን ነበር የሚያሳየው። እውነትም ጠጋ ብለው ሲያዩ ድልድዩ ፈርሶ አዞዎቹ ብቅ ብቅ ብለው መልአከ ሞት የሚጥልላቻውን ነፍስ የሚጠብቁ ነበር የሚመስሉት። ከዛ ሁሉም በጣም አዘኑ አለቀሱ ለእነርሱ መትረፍ ያ ህፃን ልጅ የከፈለውን መስዋዕትነት ተገነዘቡ አንዱ ስለ ሁላቸው ሞቶ እነርሱን አተረፈ። ይህ ሁሉ ስለ ሰዎች ፍቅር ነው።"

አየህ ልጄ ክርስቶስም ለኛ እንዲህ ነው አሉት ሳያውቁ ሁለቱም በጣም አልቅሰው ነበር በልጁ ታሪክ። "አባቴ እኔ'ኮ ከንቱ ሰው ነኝ እግዚአብሔር እኔን ይቅር ይለኛል?" አላቸው "ልጄ እግዚአብሔር ይቅር ባይ ነው። ግን መጀመሪያ አንተ ቀዶ ጥገና ያልስፈልግሃል" አሉት። "ምን አይነት ቀዶ ጥገና አባቴ?" "ይሄውልህ ልጄ የእስከ አሁኑን ልብህን ልናክመው ይገባል ዳግመኛ ወደ ቀደሞው መጥፎና ኃጢአት የበዛበት ህይወት እንዳትመለስ። ከዚያ ንስሀ የሚባለውን የህይወት መድኃኒት ትወስድና ትድናለህ" አሉት፡፡ ወጣቱም ሁሉን ተናዞ ንስሀ ገብቶ ተፀፅቶ ትላንትን ዳግም ላያየት ከእውነት ጋር ታርቆ ጤናማ ህይውቱን መኖር ጀመረ።

✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥
@aleroe