"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ኤልሮኢ:

#በፀሎት ሰአት ሀሳባችን ለምን ይበተናል?
ቀሲስ ሄኖክ ወ/ማርያም

@aleroe
ኤልሮኢ:(ስነ ፅሁፍ)

#ናፈቀኝ ....

የማለዳ ተመስጦ ... ውዳሴ ማርያም መድገሜ
በልጅነት ልመጣልህ .. ጧት ማታ መፍገምገሜ
ዛሬ ግን ናፍቆት ሆነብኝ .. ተዘረረብኝ አቅሜ
እንቅልፌ ሰላም አጣ .... እባብ ሆነብኝ ሕልሜ ።
.
"እግዚኦ" ሲባል ሰምቼ .. ሳልነሳ ከትራሴ
ድንጋጤ ወረረኝ .. ከእግሬ ጥፍር እስከራሴ
ሰዓታቱን እየሰማሁ ... ተቀሰቀሰ መንፈሴ
ትዝዝ አለኝ ማኅሌቱ ... ስትዋብበት ነፍሴ
የእናቴ ስም ናፈቀኝ ...... የሕርያቆስ ቅዳሴ
.
እራሴንም ስላጣሁት ..... ከቤትህ በመራቄ
እንደ ሎጥ ሚስት መሰልኩኝ ፤ አደባባይ ደርቄ
.
የመዝሙረ-ዳዊት ጸሎት .. አነከተኝ በትዝታ
ነፍሴን ስላስጠማኋት ... አነባችብኝ አብዝታ
እሪሪሪ ብላ አለቀሰች ... በስጋ ወንጭፍ ተገዝታ
.
ናፈቀኝ ትምህርቱ ... የቅዱስ ያሬድ ጸጋ
ቁጥር ዜማ መጮሄ .... አንደበቴ እስኪዘጋ
ዛሬ ላለው ማንነቴ .. ምን ይሆን የ'ኔ ዋጋ ??
.
በከበሮ በጽናጽል ... መዘመሩ ማሸብሸቡ
ጃኖ ለብሶ በመሰለፍ ... ማመርገዱ መወረቡ
የትውስታ ስለት ይዘው ፤ ወደ ልቤ ሰርገው ገቡ
.
አምላኬንም ሳመሰግን .. ወደ ሰማይ አንጋጥጬ
እንዲህ ዛሬ ልቀብረው .. በልቤ ውስጥ ረግጬ
አገልግሎቴ ናፈቀኝ ... ከሁሉ በላይ አስበልጬ
ኮርስ ስማር ትዝ አለኝ ... በዛፉ ስር ተቀምጬ
.
አንገቴ ላይ የታሰረው .. ለምን ነበር ማኅተቤ
ዛሬ ለምን አታለልኩት .. በምክንያት ተንተብትቤ ?
.
ምኑ ነው የሆነብኝ .. ለቤተ መቅደስ እንቅፋት ?
ትዳር ለምን መሰለኝ .. ሜዳ ሆኖ ተዳፋት ?
ልቤ ከብዶ እስከመቼ .. እኖራለሁ በጥፋት ?
ነፍሴንስ ምንበወጣት ... በ'ሳት ጅራፍ ላስገርፋት
.
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ሰው መስዬ ሲመግቡኝ .. ባ'ይኔ ብሌን አይቻለሁ
ታዲያ ግን ምን ዋጋ አለው .. ማንበብ እንደሁ ትቻለሁ
.
እውነት ነው አይካድም .. አውደ ምኅረት መቀመጤ
ወንጌሉንም እየሰማሁ .... ሳላስበው መመሰጤ
ትዝ ይለኛል አጀንዳዬ ... ከንፈሮቼንም መምጠጤ
.
ጽዋ ቢሉ ዝክረ ሰንበት .. እንዳያልፈን ስንጣራ
ዓርብ ጸሎት ስንሰለፍ .. ነጭ ለብሰን በጋራ
ከትንሹም ከትልቁም ... ስለድኅነት ስናወራ
"ጉዞ" ብለን በባዶ እግር .. ሳንደክም በተራራ
ነጭ ለብሰን ጧፍ ይዘን .. እንደ ኮከብ ስናበራ
አዎ! አስታውሳለሁ ... ስልሳ ፍሬ ስናፈራ
.
ጾም ጸሎቱ ትዝ ይለኛል .. በላያችን ስናጌጠው
በስግደት ተሽቀዳድመን ... ሳጥናኤን ስናመልጠው
ብዙ ነበር በንስሐው ... በቁርባኑ የሚገልጠው
.
ጌታ ሆይ!
ተመልሶ ይላክልኝ ... መንፈሳዊ ጀግንነቴ
በመቅደስህ ዋጋ ይክፈል .. የናቡቴ ልጅነቴ
"እሺ" ብሎ እንዳልሰራው .. አይሁንብኝ ማንነቴ
.
ቀራኒዮ አይረሳኝ ... ችንካር ያለው መስቀሉ
በክቡር ደም ተነክሮ .. ቀይ ሆኖ መንቀልቀሉ
.
እመ ብርሐን በልደቷ .. ትመልሰኝ ወደ ጥንቱ
የቅዱሳን ጥበቃቸው .... አይለየኝ በረከቱ
ናፈቀኝ
ሰነፍ ልቤ እየገዛኝ .. በሞት ሰይፍ በጫጨቀኝ
ይቅር በለኝ አምላኬ! ... ከመቅደስህ አታርቀኝ
በግራ መቆም መረረኝ ፤ አሰልፈኝ በልጅህ ቀኝ
አብርሃምን ላክና ... መልስህን ቶሎ አሳውቀኝ
በራሴ አይን ስደናበር.. መታዘብህ አስጨነቀኝ
የምኅረት ቃል አንደበትህ ፤ ፅኑ ፍቅርህ ናፈቀኝ።

#ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
___________
ኤልሮኢ :

አልፋና ዖሜጋ

አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ
በከሀዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ/2/
አዝ---
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሠራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአደም ቤዛ ልትሆን ብዙ ተንገላታህ
አዝ ---
ቅዱሳን እጆችህ የፊጥኝ ታስረው
እንደ በግ ጎተቱህ ልትምራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑህ ለመመጻደቅ
አዝ ---
በዚያ አደባባይ በጲላጦስ ዘንድ
አሳልፈው ሰጡህ አጋልጠው ለፍርድ
ከሐና ቀያፋ ከካህናቱ ደጅ
ከእነ ሄሮድስ ዘንድ አቀረቡህ በአወጅ
አዝ---
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ጸናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር መከራ
አዝ---
አምስቱ ችንካሮች ቅንዋት መስቀል
አይሁዶች አመጡ ገላህን ለማቁሰል
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
አዝ---
ግፈኞቹ አይሁድ በአንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅ ተፉብህ አንተኑ ሊጎዱ
ለእኛ ወገኖች ሀጢያት ላደከመን
የመስቀልህ ጥላ ማረፊያ ይሁነን


@aleroe
Audio
#ውይይት

"እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ። "
(የሐዋርያት ሥራ 2: 36)

ሲል ምን ማለቱ ነው

በዲ/ን ኢዮኤል ዳኛቸው እና
በወንድማችን አቤኔዘር ማሙሸት
Audio
#ውይይት ክፍል ሁለት

"እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ። "
(የሐዋርያት ሥራ 2: 36)

ሲል ምን ማለቱ ነው

በዲ/ን ኢዮኤል ዳኛቸው እና
በወንድማችን አቤኔዘር ማሙሸት
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤልሮኢ:

#የምክር ቃል ከቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ
ለራስህ ነው

አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ! ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡
ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡ ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡ እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡


@aleroe
ኤልሮኢ:
#ሰሙነ_ሕማማት

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።

በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦

#ሰኞ
#መርገመ_በለስ_የተፈጸመበት_ሰኞ_ይባላል
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

#አንጽሖተ_ቤተ_መቅደስ_ይባላል፡-
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።

#ማክሰኞ
#የጥያቄ_ቀን_ይባላል
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

#የትምህርት_ቀን_ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

#ረቡዕ
#ምክረ_አይሁድ_ይባላል
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

#የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

#የእንባ_ቀን_ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።

#ሐሙስ
#ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

#የምስጢር_ቀን_ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

#የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

#ዓርብ
#የስቅለት_ዓርብ_ይባላል
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

#መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

#ቅዳሜ
#ቀዳም_ስዑር_ትባላለች
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።

#ለምለም_ቅዳሜ_ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

#ቅዱስ_ቅዳሜ_ይባላል፡-
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።




ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን

@aleroe
ኤልሮኢ :

አልፋና ዖሜጋ

አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ
በከሀዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ/2/
አዝ---
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሠራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአደም ቤዛ ልትሆን ብዙ ተንገላታህ
አዝ ---
ቅዱሳን እጆችህ የፊጥኝ ታስረው
እንደ በግ ጎተቱህ ልትምራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑህ ለመመጻደቅ
አዝ ---
በዚያ አደባባይ በጲላጦስ ዘንድ
አሳልፈው ሰጡህ አጋልጠው ለፍርድ
ከሐና ቀያፋ ከካህናቱ ደጅ
ከእነ ሄሮድስ ዘንድ አቀረቡህ በአወጅ
አዝ---
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ጸናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር መከራ
አዝ---
አምስቱ ችንካሮች ቅንዋት መስቀል
አይሁዶች አመጡ ገላህን ለማቁሰል
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
አዝ---
ግፈኞቹ አይሁድ በአንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅ ተፉብህ አንተኑ ሊጎዱ
ለእኛ ወገኖች ሀጢያት ላደከመን
የመስቀልህ ጥላ ማረፊያ ይሁነን


@aleroe
ኤልሮኢ:
ቄጠማ(ቀጤማ)

በቀዳም ስዑር ቀሳውቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለ አዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሳኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠ እና ትንሳኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመኑም ለቤተ ክርስቲን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ ቀጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሰሩበትን ድርጊት የሚያስተውስ ነው፡፡ በዚህ እለት ልብስ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲቆናትን ቄጠማ ተሸክመው ቃጭል ሲቃጭሉ መታየታቸው እለተ ትንሳኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ የተወሰደው በኖህ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ ጋር በማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ሆነውእጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውኃ ተጥለቅልቀዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ
ይዞአቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ ትመልሳለች፡፡ ዘፍ.9-1-29፡፡


@aleroe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤልሮኢ:
መዝሙር በእንተ ትንሳኤ

+ ትንሣኤከ ለእለ አመነ /2/
ብርሃነ ከፈኑ ዲቤነ /4/


+ አማን በአማን /4/
ተንሥአ እምነ ሙታን/4/


+ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ/2/
ተሀጺባ በደመ ክርስቶስ /4/

@aleroe
ኤልሮኢ:
ከትንሣኤ እስከ ዳግማይ ትንሣኤ ያሉ ሳምንታት

#ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፥ ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው። በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲዖል ወደ ገነት፣ ከሐሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን።

#ማግሰኞ- ቶማስ ይባላል፦ በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል። ዮሐ. 20፥27-29

#ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፦ በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን። ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤዉን በድል ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን።

#ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፦ በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠውን ተስፋና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን።

#አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፦ በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን/ምእመናንን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል። ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል።

#ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፦ በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል።

#እሑድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፦ በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል።


@aleroe
ኤልሮኢ:

#የምክር ቃል ከብፁዕ_አቡነ_ሽኖዳ

ዝምታ

ዝምታ በመጀመሪያ ደረጃው ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የአንደበት ስህተትን መግታት ማለት ነው፦ " በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።" ምሳ. 10 ፥ 19። ቅዱስ አርሳኔዎስም እንድህ ብሏል ፦ " ብዙ ጊዜ እናገርና እፀፀታለሁ ስለ ዝምታየ ግን ፈጽሞ ተፀፅቼ አላውቅም ።"
በሌላ በኩል ዝምታ ማለት እግዚአብሔር ይሠራ ዘንድ የሰውን ጥረት ማቆም ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አስመልክቶ ሲናገር እንድህ ብሏል፦ .." እግዚአብሔር ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ ። እግዚአብሔር ስለእናንተ ይዋጋል እናንተም ዝም ትላላችሁ .." ዘጸ. 14፥ 13-14።
አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰው ለራሱ የማይበቀልና ክፉን በክፉ የማይቃወም ከሆነ ዝምታ እርጋታ ይሆናል።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም .1ኛ ጴጥ. 2፥23። በአይሁድ ሸንጎ ፣ በሐና ፣ በቀያፍ ወይም በጲላጦስ ፊት ሲከሱት ዝም ነው ያለው።
ዝምታ ውስጥ ግን ኃይል ስለነበረ አገረ ገዥው ጲላጦስ ".. እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኜሁበትም ።" ( ዮሐ . 18 ፥ 38) በማለት ተናግሯል።
ከዚህ በተጨማሪ ዝምታ ለፀሎት ለተመስጦ እድሉን ያደላል።
ብዙ የሚያወራ ሰው ለመፀለይም ሆነ ለውስጣዊ መንፈሳዊ ድርጊት ዕድል አይኖረውም።
አንድ ቅዱስ ሰው".. ብዙ የሚናገር ሰው ውስጡ ባዶ መሆኑን ይገልጣል ።" ብሎ መናገሩ ትክክል ነው። ይህም ማለት ውስጣዊ መንፈሳዊ ሥራ የለውም ማለት ነው።
ቅዱስ አርሳኔዎስ ስለዝምታውና ስለ ምናኔው በተጠየቀ ጊዜ ".. በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋር መሆን አልችልም ።" ብሎ መልሷል።
አንድ ታላቅ መንፈሳዊ አባት የተናገሩት ቃል ምንኛ ድንቅ ነው ፦ " .. ልብህ ይናገር ዘንድ አንደበትህን ዝም አሰኜው እግዚአብሔር ይናገር ዘንድ ልብህን ዝም አሰኜው ።"
የዝምታ አይነቶች ብዙ ቢሆኑም ከነዚህ መካከል ዋና ዋናዎቹ #የአንደበት_ዝምታና_የስሜት_ዝምታ ናቸው። ሰው ስሜቱን ባተሌ እስካላደረገ ድረስ ፀሎቹንና ተመስጦዎቹን ያግዱበት ዘንድ መጥፎ አሳቦችን ያመጡበታል ። ስለሆነም በመንፈሳዊ መንገድ ዝምታውን መጠበቅ የሚወድ ሰው አይኖቹን ፣ ጆሮዎቹንና ስሜቶቹን ሁሉ መጠበቅ አለበት ።
ዝምታ ለሰው መስከንንና እርጋታን አስተምሯል ከጫጫታ፣ ከሁካታ፣ ለመጸለይ አስቸጋሪ ከሚሆኑበትና ሕሊናውን ከሚረብሽበት ብዛት ካላቸው አሳቦች ያርቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ዝምታ የሚሻው ብቼኝነትንና ጥቂት ጓደኞችን ነው።


ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።

@aleroe
ኤልሮኢ:
#ለምን ዳግማዊ ትንሳኤ ተባለ ?

የአምላካችን ትንሣኤው ዕለት ለቅዱሳን ሐዋርያት በዝግ በር ገብቶ በመካከላቸው ተገኝቶ «ሰላም ለሁላችሁ ይሁን» ብሎም ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡

በኋላ ከሔደበት ሲመጣ የጌታችንን መነሣትና እንደተገለጸላቸው በደስታ ሲነግሩት እርሱም "በኋላ እናንተ 'ዐየን' ብላችሁ ልትመሰክሩ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን 'ሰምቼአለሁ' ብዬ ልመሰክር ላስተምር? አይሆንም እኔም ካላየሁ አላምንም" አለ
እነሆ ታሪኩ 👇👇

ዮሐንስ 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
❝²⁴ ነገር ግን ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ ኢየሱስ በመጣ ጊዜ ከእነርሱ ጋር አልነበረም።
²⁵ ሌሎቹም ደቀ መዛሙርቱ፦ ጌታን አይተነዋል አሉት። እርሱ ግን፦ የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ካላየሁ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም አላቸው።

²⁶ ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።
²⁷ ከዚያም በኋላ ቶማስን፦ ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።

²⁸ ቶማስም፦ ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።
²⁹ ኢየሱስም፦ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።❞

እንግዲህ ይህ የትንሣኤው ምስጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት
ዕለት ስለሆነ «ዳግም ትንሣኤ» ተብሎ ሰንበቱ ይጠራበታል፤ ይከበርበታል፡፡

@aleroe
ኤልሮኢ:

👉 መክሊታችንን የሚቀብር ዓይነጥላ
ቀሲስ ሔኖክ ወ/ማርያም እንደጻፈው



@aleroe
ኤልሮኢ:
ምክረ አበው
#1
"ክርስትና የሚጀምረዉ ከተግባር እንጂ ከወሬ አይደለም፡፡ ሕይወታችን በጥቅስ ተገንዞ በጥቅስ የተቀበረ ከሕይወትና ከሥራ የተለየ እንዲሆን አንፍቀድለት፡፡"

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ
#2
‹‹ ዘመን ማለት አንተ ነህ ፡፡ አንተ ሰላማዊ ስትሆን ሰላማዊ ትሆናለች፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ ትከፋለች፡፡››

አንጋረ ፈላስፋ
#3
‹‹ራስህን ለማየት ወደ መስታወት ብትመለከት ዉበትህን ወይም ጉድለትህን ያሳይሀል፡፡ ምንም ነገር እንዳታይ ታደርግ ዘንድ ከመስታወቱ መሰወር አትችልም፡፡ ማንም ሊያመልጥበት በማይችለዉ በፍርድ ቀንም እንዲሁ ይሆናል፡፡››

አንጋረ ፈላስፋ
#4
‹‹ የአንጥረኛ ዕቃ በየቀኑ በተመታ ቁጥር የበለጠ ጽሩይ እየሆነ እንደሚሄደዉ ሁሉ ሰዉነቱን ለማድከም ራሱን የሚያስገዛ ሰዉም እንዲሁ ነዉ፡፡ በየቀኑ እየተማረ፣ እየጠራ እየነጻ ከጠላት ስዉር ወጥመድ እየተጠበቀ ይሄዳል፡፡››

አንጋረ ፈላስፋ
#5
‹‹ ሀብትን ብታከማች ያንተ አይደለም፡፡ ብትመፀዉተዉ ግን ታከማቸዋለህ፡፡››

ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
#6
‹‹ ስለ ወንድሙ መዳን የማይደክም ድኗል ብዬ አላምንም፡፡››

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#7
‹‹ እግዚአብሔር አንድን የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታ ሊሰጥህ ቢወድ ፀጋዉን ልትጠብቀዉ ከምትችለዉ ከትህትና ጋር ይሰጥህ ዘንድ ለምነዉ አለበለዚያ ግን ከአንተ እንዲያርቀዉ ጠይቅ፡፡››

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#8
‹‹ ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እዉነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእዉነት እናገራለሁ፡፡ እዉነተኛ ትህትና ትሩፋትን መሥራት ነዉ፡፡››
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#9
‹‹ ስለ ሌሎች ሰዎች ያለማቋረጥ ፀልዩ፡፡ወደ እግዚአብሔር ይደርሱ ዘንድ የንስሐ እድል አላቸዉና፡፡ ለእነርሱ ነቀፋ እናንተ ምላሻችሁ ፀሎት ይሁን፡፡››

ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥዉ ለአንበሳ


@aleroe
ኤልሮኢ:
የሕያዋን አምላክ


በእኩለ ሌሊት ክርስቶስ ተነሣ /2/
ሙታን ይደለንም ክርስቶስ ተነሣ
ሕያዋን ነን እኛ ክርስቶስ ተነሣ
በመስቀሉ የዳንን ››
ከኃጢአት ቁራኛ ››
የተዋረደውን ››
ሊያከብር ዳግመኛ ››
ሞትን አሽንፎ ››
ተነሣልን ለእኛ ››
አዝ ---
እናንተስ አትፍሩ ክርስቶስ ተነሣ
እነግራችኋላው ››
የተሠቀለውን ››
እንድትሽ አውቃለው ››
ሕያዉን ከሙታን ››
ለምን ፈለጋችሁ ››
እንደተናገረው ››
ተነሥቷል ጌታችሁ ››
አዝ ---
ክርስቶስ ሲነሣ ከርስቶስ ተነሣ
በሰንበት ሌሊት ››
አስቀድሞ ታየ ››
ለመግደላዊት ››
እርሷም ትንሣኤውን ››
ለዓለም አበሠረች ››
ጌታዬን አየሁት ››
ተንስቶአል እያለች ››

@aleroe
ኤልሮኢ:
#የምክር ቃል ከቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ

...........የሀጢያት ትንሽ ..............

ዲያብሎስ ልጅነታችንን እናቆሽሽ ዘንድ በእኛ ላይ የሚተናኰለው ተንኰል በጣም ተደጋጋሚና ኃይለኛ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን መንቻካ የዲያብሎስን ደባ ድል እንነሣ ዘንድ ዘወትር ንቁዎችና ጠንቃቆች ልንኾን ይገባናል፡፡ እኛ ይህን ማድረግ ሳንችል ቀርተን እጅግ ጥቂት መግቢያ ቀዳዳ የምንተውለት ከኾነ ግን እርሱ ጥቂቷን ቀዳዳ ሰፊ በር ያደርጋታል፡፡ እንዲህ አድርጎም ኃይሉን ኹሉ ተጠቅሞ ወደ እኛ ይገባል፡፡

ስለዚህ ስለ ድኅነታችን የሚገደን ከኾነ እንደዚህ ጥቂትና ቀልድ በሚመስሉ ነገሮች እንኳን አንዘናጋ፤ እርሱ የሚንቀውና ጥቂት የሚለው ኃጢአት የለምና፡፡ እኛ ጥቃቅን የምንላቸውን ነገሮች መነሻ አድርጎ ልጅነታችንን የምናቆሽሽበትን ታላላቅ ኃጢአቶችን እንድንሠራ አድርጎ እጅግ ይተጋልና፡፡



@aleroe