"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ማር፣ፌጦ፣ጤና አዳም፣ነጭ ሽንኩርት አንድ ላይ ፈጭታቹ አንድ ማንኪያ ዋጡ የሚል መልክት ሰዉን እያሸበረ ይገኛል።

መልክቱ ከአባቶች የተላከ ነው የሚሉት ነገር አለ። ነገር ግን የተኛቹ አባቶች እንደተላከ ግልፅ የወጣ ነገር የለም።

የተባለውን መተግበር ክፋት የለው
ለምን ? ከተባለ የተጠቀሱት ለሰውነታችን ገንቢ እንጂ ጎጂ አይደለም ነገር ግን እኚ መዳኒት ናቸው የተባሉት ንጥረ ነገሮች ከኮሮና ቫይረስ ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም።

#አትሸወዱ #አትሸበሩ

ዛሬ የሀይማኖት አባቶች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በጥሞና ጤና ሚኒስትር የሚለውን ተከታተሉ ማለታቸው ይታወሳል ስለዚህም አባቶቻችን ያሉትን ጤና ሚንስትርን እንከታተል።

ሆኖም ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል #እጅን_መታጠብ አንደኛው እና #ዋነኛው_መንገድ ነው።


#እጃችሁን_ታጠቡ
#ፀልዩ
#ስገዱ

@aleroe
ኤልሮኢ:
መፃጉዕ
መፃጉዕ የአብይ ፆም አራተኛው ሳምንት ነው። በዚህ ሳምንት ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችንድውያንንስለመፈወሱየሚታሰብበት ሳምንት ነው።በዮሐ ፭፥፪―፲፩ እንዲህ ተፅፎ እናገኛለን«በኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቅያ ነበረች አምስት መመላለሻም ነበረባት በእነዚህ ውስጥ የውሀውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኛዎችና እውሮች አንካሳዎችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ህዝብ ይተኙ ነበር።
አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቅያቱ ወርዶ ውሀውን ያናውጥ ነበርና እንግዲህ ከውሀው መናወጥ በኋላ መጀመርያ የገባው ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር በዚያም ከሰላሳ ስምንት አመት ዠምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበር።እየሱስ ይህ ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ እስከ አሁንብዙ ዘመን እንዲሁ እንደነበር አውቆ ልትድን ትወዳለህ አለው። ድውዩም ጌታ ሆይ ውሀው በተናወጠ ጊዜ መጠመቅያቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት።እየሱስም ተነስና አልጋህ ተሸከም ሂድ አለው።ያም ቀን ሰንበት ነበር።»


ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።

@aleroe
ኤልሮኢ:
እኔ መፃጉ ነኝ

ለብዙ ዓመት በአልጋ ላይ የነበርኩ፣
በሥጋ በሽታ በህመም የደከምኩ፣
በአጭር ተቀጭቼ ሳላአብብ የረገፍኩ፣
ፈውሴን የሚናፍቅ ወገን ያልነበረኝ፣
ውሃው ሲነዋወጥ ጠልቆ የሚያወጣኝ፣
ከርታታ ባይተዋር ውዳቂ ነበርኩኝ።
ከለዕታት አንድ ቀን በዚያ ሲያልፍ ጌታዬ፣
ሊፈውሰኝ ወዶ ገብቶ ከጎጆዬ፣
በቃሉ አድኖኝ ቆሜ ሄድኩኝ በዕግሬ፣
አይሁዳዊ እነቴ እንዳይቀር የዘሬ፣
ምስጋና ለማቅረብ ባይታደል ልቤ፣
ተንኮል በኔ ነግሶ ክፋትን ደርቤ፣
ሰንበትን በመሻር የማረኝ ይሄ ነው በማለት፣
ብድሩን ስከፍለው ጥፊን መለስኩለት፣
የወዳጄ ጠላት እኔ መፃጉ ነኝ፣
በሁዳዴ ፆም ውስጥ የምታስታውሱኝ።

@aleroe
ኤልሮኢ:
መጋቢት 12/07/12

#መዝሙር_ዘደብረ_ዘይት
"እንዘ ይነብር"

#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡

ዲ/ን 1 ተሰሎ 4÷13-ፍ.ም
ን/ዲ 2ጴጥ 3÷7-15
ን/ካ ግብ፡ሐዋ24÷1-22

#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 49÷3
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ 
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ

#ትርጒም

እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል
አምላካችን ዝም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል

#የዕለቱ_ወንጌል

ማቴ ፳፬፥፩ -፴፮

ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ

@aleroe
ኤልሮኢ:

ለጥያቄዬ መልስ ስላጣሁ

ለጥያቄዬ መልስ ስላጣሁ
መጣሁ ከደጅሽ ሱባዔ ገባሁ
ማን አፍሮ ያውቃል በአንቺ ለምኖ
በኪዳንኪ ተማህጸኖ

ለነፍሴ ዕረፍቷ ታዛ መጠጊያ
ካንቺ ተገኝቷል የሞቴ መውጊያ
በሰላምታሽ ድምፅ ተባርኳል ቤቴ
የጌታዬ እናት ለእኔም እናቴ

ማርያም ኵኒ ለሕይወትየ ጸወኖ
እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ
በሥዕልኪ ሥዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ

ቀንን ስናፍቅ በሌሊት ሆኜ
አላተረፍኩም በሰው ታምኜ
ቁልፉ ልጅሽ ነው ለቋጠሮዬ
አሳስሰሽልኝ አልፏል ስቃዬ

ኪዳነምሕረት ኵኒ ለልቡናዬ ብርሃኖ
እስመ ተማህጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ
በሥዕልኪ ሥዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ

ጉልበቴ ዝሎ ቀልዬ ሳለሁ
በኪዳን ጥላሽ ተስፋ አግኝቻለሁ
ደጅሽ መጥቼ ኃይሌ ታደሰ
ያሳዳጆቼ ምክር ፈረሰ

ወላዲተ አምላክ ኵኒ ለእርቃንዬ ክዳኑ
እስመ ተማህጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ
በሥዕልኪ ሥዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ

የዝናቡ ምንጭ ፈጣን ደመና
ከሴቶች ሁሉ ክብርሽ ገናና
አንድያ ልጅሽ ወይን አድርጎኛል
ከትላንት ይልቅ ዛሬ ባርኮኛል

@aleroe
ኤልሮኢ:
መጋቢት 13/07/12

#መዝሙር_ዘደብረ_ዘይት
"እንዘ ይነብር"

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነብ
መልዕክታት ወንጌልና ምስባክ፡፡

ዲ/ን 1 ተሰሎ 4÷13-ፍ.ም
ን/ዲ 2ጴጥ 3÷7-15
ን/ካ ግብ፡ሐዋ24÷1-22

#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 49÷3
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ 
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ

#ትርጒም

እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል
አምላካችን ዝም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል

#የዕለቱ_ወንጌል

ማቴ ፳፬፥፩ -፴፮

ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ

@aleroe
ኤልሮኢ:
ደብረ ዘይት
​​ደብረ ዘይት የዐብይ ጾም አምስተኛ ሳምንት
ደብረ ዘይት ማለት ቃሉ “ደብር” ሲል ተራራ ሲሆን “ዘይት” ሲል የወይራ ዛፍን ያመለከታል። ባጠቃላይ ደብረ ዘይት የወይራ ዛፍ (የዘይት ዛፍ) የበዛበት ተራራ ማለት ነው። ቦታው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከጎለጎታ (ቀራንዮ) ተራራ በስተምስራቅ በግምት ፪ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተራራ ነው። በሁለቱ ተራሮች መካከል ጌቴሴማኒ የሚባለው ለምለም ስፍራ ይኸውም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ ይገኛል።
የደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነው። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥ ፩ ከዚሁ ተራራ ላይ ነው ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያረገው። ኋላም በዳግም ምጽአት እዚሁ ተራራ ላይ ነው ለፍርድ የሚመጣው። /ሐዋ ፩፥፲፫/። "
" በዚህ ቀን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ስለመምጣቱ (ዳግም ምፅአቱ ) ይሰበካል። ይህን ዓለምንም አሳልፎ ለመረጣቸውና ላከበራቸው ዘላለማዊ መንግሥትን ሊያወርሳቸው እንደሚመጣ ይነገርበታል። ይህ ቀንም እኩለ ፆም በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህች በተለየች ቀንም ሁሉም እንደ የሥራው ፍርዱን ከአምላክ የሚቀበልበት መሆኑ፤ መልካም ላደረጉ መልካም እንደሚመለስላቸ ክፉም ላደረጉ የክፋታቸውን ዋጋ እንደሚያገኙ ይሰበካል። ጌታም የአባቴ ቡሩካን የተዘጋጀላችሁን የክብር ቦታ ውረሱ በማለት ወዳጆቹን እንደሚጠራ ይነገራል። " እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል " ማቴ.፳፬፡፩-፴፮ ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ። እርሱ ግን መልሶ፦ ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው። እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። "


@aleroe
ኤልሮኢ:
እ .. ረ .. ስ .. ቸ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!!

አንድ ምስኪን ሴት ወደ አንድ መንፈሳዊ አባት ዘንድ ቀርባ "እግዚአብሔር ሁሌም ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ሁኔታ ግራ የተጋቡት እኚህ አባትም በሁኔታው ተበሳጭተው ጥለዋት ይሄዳሉ። ከዚያን ቀን በኋላ እቺ ሴት እየደጋገመች በመምጣት "እግዚአብሔር ማታ ማታ እየመጣ ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ጭቅጭቅ የተሰላቹት እኚህ አባትም እንደለመደችው አንድ ቀን መጥታ ስታናግራቸው እንዲህ አሏት "እውነት አንቺን እለት እለት እየመጣ ፈጣሪ የሚያናግርሽ ከሆነ አምንሽ ዘንድ አንድ የቤት ስራ ልስጥሽ" አሏት ትኩር ብለው እየተመለከቷት! ሴትዬይቱም የሚሏትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባች! እኚህ አባትም ከዚች ሴት ጭቅጭቅ ይገላግለኛል ያሉትን ጥያቄ አቀረቡላት እንዲህ በማለት "እውነት አንቺን እግዚአብሔር የሚያናግርሽ ከሆነ እስቲ ዛሬ ማታ አንድ ጥያቄ ጠይቂልኝ" አሏት። ሴትየዋም በእርጋታ "ምን ልጠይቅልዎ አባቴ?" አለቻቸው። "ለረጅም አመት ልተወው ያልቻልኩት የዛሬ ወር ገደማ ግን ንስሐ ገብቼ የተውኩት አንድ ኃጢአት እሰራ ነበር። ያ በፊት እሰራው የነበረ አሁን ግን ንሰሐ ገብቼ የተውኩት ኃጢአት ምን እንደነበረ ጠይቀሽ ንገሪኝ። እሱን ከነገረሽ እውነትም ላንቺ እግዚአብሔር እንደሚናገር አምናለሁ" አሏት። ሴትዬይቱም ወደቤቷ ሄደች።
ተመልሳ እንደማትመጣ ግን ገምተው ነበር አባ ነገር ግን በበነጋው ያቺ ሴት መጥታ አባን አስጠራቻቸው። አባም ሴትየዬቱን ሲያዩ በጣም ተገርመው ወደሷ በመሄድ በፌዝ መልክ "እህስ ልጄ እግዚአብሔርን ንስሀ ገብቼ ያቆምኩት ሀጢያት ምን እንደነበር ጠየቅሺው?" አሏት ሳቅ እያሉ "አዎን አባ" አለቻቸው ሴትየዋ አንገቷን እንዳቀረቀረች "እህሳ ምን አለሽ?" አሏት አባ በመጓጓት "እረስቸዋለሁ አለኝ" አለቻቸው፡፡ እኚህ መንፈሳዊ አባት ባልገመቱት የእግዚአብሔር ምላሽ ልባቸው ተነክቶ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ወደደረታቸው አስጠግተው አቀፏት!……… ይባላል።

ታዲያ ከዚ ምን እንማር???

የሰው ልጅ ሙሉ ይቅርታ የለውም። ዛሬ ምን ፍሪዳ አርዶ ቢታረቅህ፣ ምን በልቅሶ ታጅበህ እየተንፈራፈርክ ይቅር በለኝ ብትለው "ይቅር ብየሀለሁ" ይልህና የሆነ ቀን ስታስቀይመው ይቅር ያለውን በደልህን እየቆጠረ ሲወቅስህ ይውላል እግዚአብሔር ግን ይቅር ካለህ በቃ ረሳው ፍቅር ነዋ፤ ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሔርን በኛ መጠን መትረን ንስሐ በገባንበት ኃጢአት ዘወትር የምናለቅስ? ስንቶቻችን እንሆን እግዚአብሔር እንደኛ ቂመኛ መስሎን በፍቅር ሂፆጱ ያጠበውን ኃጢአታችንን እያስታወስን ዘወትር በፀፀት እሾህ ራሳችንን የምንገርፍ? ይቅርታ ከመለመን እኮ ይቅር ማለት ይከብዳል! ምሬሀለሁ ከማለት ማረኝ እያሉ እግር ስር መደፋት ቤት በቀለለ! በህይወታችን የገፋንና ያቆሰለንን ሰው በደል ከመርሳትኮ ሺህ ጊዜ ፍሪዳ እያረዱ "እንታረቅ" ማለቱ እጅግ ቀላል ነውኮ ...! ለዚያም ነው መሰል ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሎት አስተምረን ባሉት ጊዜ "እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አንተም ይቅር በለን" ብላችሁ ፀልዩ ያለን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ የይቅርታ ዘመን ያድርግልን የይቅርታ ልብ ይስጠን


@aleroe
#ሰበር_ዜና
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ዛሬ በሰጡት
መግለጫ ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተክርስቲያናት እና ገዳማት በገጠርም በከተማም ካህናተ እግዚአብሔር በየከተማዉ እየዞሩ
በጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያም ቃል ኪዳን መሰረት ሃገራችንን # በማዕጥንት
እንዲያጥኑ በጥብቅ አሳስበዋል።
እግዚአብሔር ሃገራችንን ከኩፉ መከራ ይጠብቅልን።

@aleroe
ኤልሮኢ:
~~~ የጽዋ ማኅበር ~~~


ይህ አይነቱ ትውፊታዊ ሥራዓት አጀማመሩ መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን በሀገራችን በኢትዮጵያ ተጠብቆ የኖረ ምእመናን በየተራ ምግብና መጠጥ አዘጋጅተው ከችግርኞች ጋር የሚሳተፉበት ሥርአት ነው።

በጌታ በእመቤታችን:በቅዱሳን መላእክት : በጻድቃን በሰማእታት ስም በመታሰቢያ እለታቸው ይፈፀማል ።

የፅዋ ማህበር ስህተት አይደለም ይህ ማለት ግን አንድ አንድ ምዕመናን በፅዋ ማህበር ስም የሚያደርጉት ነገር ልክ ነው ማለትም አይደለም ለምሳሌ፦
ስካር፣መሰዳደብ፣በዘፈን መጨፈር ማህበሩን በፃድቃን ስም አዘጋጅቶ አንድ የተቸገረ ሰው ሳይጠሩ ሳያበሉ እርስ በራስ መገባበዝ . . . . ብዙ መጥቀስ እንችላለነን ይህ የቀደምት ሀዋርያቶችን ህብረጥ የሚጥስ ተግባር ነውና ክርስቲያኖች ሆነን እንዲህ የምናደርግ ካለን ከድርጊቱ መቆጠብ አለብን ! ትውፊቱን መጠበቅ አለብን ! እኛ በመሳሳታችን ሌላ ምዕመናንን እያሳሳትን ነውና ከዚህ ድርጊት እንቆጠብ !

የፅዋ ማህበር የመጀመሪያዎቹ ክርስትያኖች ሕይወት የሚያስታውስ ነው።
ይህ አብሮ መብላትና መጠጣት የአንድነት የፍቅር ማእድ አጋፔ (Agape)ከሀዋርያት ዘመን ጀምሮ የነበረ ነው። በዚህም በረከት ይገኝበታል ።

★ምሳ 10:7 የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው የኅጥኣን ስም ግን ይጠፋል።

★ሐዋ 2:44" ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፣ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ ፣ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉ ነበር።

★ዕብ 10:25 በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥መሰብሰባችንን አንተው እርስ በእርሳችን እንመካከር እንጂ፤ይልቁንም ቁኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።"

★ሐዋ 4:32 ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፥ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበር እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደ ሆነ ማንም አልተናገረም።"

★ቆላ 2:5 በስጋ ምንም እኳን ብርቅ በመንፈስ ከናንተ ጋር ነኝና፥ ስርአታችሁንም በክርስቶስም ያለውን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል።"

★ቆላ 4:16 ይህችም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበች በኋላ፥በሎዶቅያ ሰዎች ማህበር ደግሞ እድትነበብ አድርጉ። ከሎዶቅያም የምትገኘውን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።


@aleroe
ኤልሮኢ:
በመንግስትህ አስበኝ

በመንግሥትህ አስበኝ/2/
በበደሌ ብዛት /2/ አይተህ አትጣለኝ/2/
ሳስበው በደሌ ብዙ ነው/2/
በጨለማ ነፍሴን በላት ውድማ/2/
ሆዴ ባባ አፈሳለሁ እንባ/2/
እርቃኔን ቀረሁኝ ተገፈፈ ልብሴ
መድረሻው ጠፋብኝ ተጨነቀች ነፍሴ
የብርሃን ጸዳሌ ከዓይኔ ተገፈፈ
ከፊትህ ለመቆም ጉልበቴ ታጠፈ
አልቻልኩም ደግፈኝ እንድቆም/2/
ለገነት የበቃ ያቀማኛ ሽፍታ
እኔንም ደግፈኝ አውጣኝ የዚያን ለታ/2/

@aleroe
ኤልሮኢ:
🕊መልክአ_ኢትዮጵያ🕊

#የቅድስት_ድንግል_ማርያም_የአሥራት_ሀገር
#የብዙ_ቅዱሳኑ_መጠጊያ
#ሀገረ_እግዚአብሔር_ቅድስት_ኢትዮጵያ
+++
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ኢትዮጵያ !
ሀገሩ ለተክለ ሃይማኖት ሐዋርያ፤
ህዝብኪ ይዜምሩ እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ።
የሃይማኖት ድር የዉበት መለያ፤
ቀደምት ባለ ታሪክ የዓለም አርአያ።
........🕊
ሰላም ለአይንትኪ እለ ርእያ ፈጣሪ፤
ታምረ ኩሉ ገባሪ።
ማዳን ፍቅሩን ላዩ፤
ከጸሎት ላልዘገዩ።
........🕊
ሰላም ለአእዛንኪ እለ ሰምዓ ፈጣሪ፤
በከመ ኮነ እግዚአብሔር መሐሪ፤
ቅዳሴው ሰዓታቱ፤ ላደመጡ ማኅሌቱ።
.......🕊
ሰላም ለአፉኪ ዘነበበ ወንጌሉ፤
እንዘ ይፌጽም ቃሉ፤
ሃሌሉያን ለለመደ፤
አኰቴትን ለወደደ፤
ቅኔ ዜማን ላወረደ።
.......🕊
ሰላም ለገጽኪ ለለብሰ ልምላሜ፤
መልዓ ምሥጢር ወትርጓሜ፤
ለማይሽረው ዘመን እድሜ፤
የመልከኛ ሥያሜ፤
ለሆነው የውበት ፍጻሜ።
......🕊
ሰላም ለሀዳፍኪ እለ ሰፋ ሀበ እግዚአብሔር ህያው፤
ጸሎቱ እና ሙያው፤
ውዳሴ ነውና ግብሩ፤
ጌታሽ ነውና ክብሩ።
.......🕊
ሰላም ለከርስኪ ዘአስረጸ ማዬ፤
ለጸሙ ሰብ ዘአስተዬ፤
ቅዱሱ ጸበል ለፈቀበት፤
የቅዱሳኑ አጽም ላረፈበት፤
ፈዋሹ እምነት ለተገኘበት።
.......🕊
ሰላም ለዘባንኪ እምዘባነ አለም ዘተሌለዬ፤
ጸዊረ ተሰዓቱ ቅዱሳን በሰቢከ ወንጌል ዘአብ፤
እንግዳን መቀበል ላልደከሙ፤
መካናትሽን ለተሸከሙ።
.......🕊
ሰላም ለወልድኪ ያሬድ ማኅሌታይ፤
ወጣእመ ዜማ ቀዳማይ፤
ግዕዝ እዝል ወአራራይ።
ምድርሽን በዝማሬ ላራሰ፤
የአፉን ቅኔ ላፈሰሰ።
......🕊
ሰላም ለወልድኪ አባ ተክለ ሃይማኖት ፤
ዘሖረ በሰናይ ፍኖት፤
እንደ መላእክቱ በክንፍ ለበረረ፤
ባከበረው ንጉስ ለከበረ፤
ጣዖታትን ለሰበረ።
.......🕊
ሰላም ለወልድኪ አባ ዜና ማርቆስ፤
ሐዋርያሁ ለክርስቶስ፤
እምዘመደ ተክለ ሃይማኖት ባህታዊ፤
ጥሪው ሰማያዊ፤
መንገዱ ሰላማዊ።
......🕊
ሰላም ለወለትኪ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ፤
እንበለ መጠን ዘበስዓ እበያ ወክብራ፤
ለተመሰገነች በጽድቅ ሥራ፤
እጅ ላልሰጠች ለዓለም ምርኮ፤
ለጸናች በአምልኮ።
......🕊
ሰላም ለመካንኪ ግሸን ደብረ ከርቤ፤
ለይዜምሩ ካህናት በፍሥሐ ወበይባቤ፤
ፍኖተ ብርሃን ይእቲ፤
መንበረ መስቀሉ ዛቲ፤
መግቢያ በሯ አሐቲ።
........🕊
ሰላም ለመካንኪ መካነ ቅዱሳን ዝቋላ፤
እንተ ጸለዬ በአንቲ ገበረ መንፈስ ቅዱስ በማዕከላ፤
የቅዱሳኑ መፍለቂያ፤
የሰዓታቱ መድመቂያ።
........🕊
ሰላም ለመካንኪ እንተ ተሰይመት ጻድቃኔ፤
በአት ይእቲ ለመናኔ፤
የድውያኑ መፈወሻ፤
የሀዘንተኞች ጭንቅ መርሻ፤
የዲያቢሎስ ድል መንሻ።
.......🕊
ሰላም ለመካንኪ ደብረ ላሊበላ፤
መካነ ትብስእት ወተድላ፤
የጸጋው ዘይት ሲፈላ፤
የተቀባው ልጅሽ፤
ላነጸው መቅደስ በደጅሽ።
........🕊
ሰላም ለመካንኪ መርጦ ለማርያም፤
ደብረ ምሕረት ወሰላም፤
ለማይቋረጥባት እንጣኑ፤
ለሚጸልዩባት ቅዱሳኑ፤
ለፈለቁባት ምሁራኑ።
........🕊
ሰላም ለመካንኪ ደብረ ዮሐንስ ሸንኮራ፤
እምነ ውስቴታ ደናግል ዘይዜምራ፤
ጸበሉ እውራንን የሚያበራ፤
የዮሐንስ ገዳም የመጥምቁ፤
የዘካርያስ ልጅ የጻድቁ።
........ 🕊
ሰላም ለመካንኪ ደብረ ጽዮን አክሱም፤
እንተ ሀለወ ባቲ ታቦተ ጥንታዊት ወቅድም፤
ለጽዮን መኖሪያ ለከበረችው፤
ዳጎንን ለሰበረችው፤
ዳዊትን ካባ ላስጣለችው።
.......🕊
ሰላም ለመካንኪ ዋልድባ ሰላማዊት፤
አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት፤
የአባ ሳሙኤል ገዳማቸው፤
ለሚተረክባት ገድላቸው፤
ላከበራት ጸሎታቸው።
.....🕊
ሰላም ለመካንኪ ደብረ አሰቦት ቅድስት፤
መካነ ቡሩካን ውድስት፤
ጸሎት ላልራቃት ጠዋት ማታ፤
ለቀደሳት ጌታ።
......🕊
ሰላም ለመካንኪ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ፤
እንተ አእረፈ ባቲ ለተክለ ሃይማኖት አጽሙ፤
ቅዱሱ ደብር መታሰቢያ፤
የመናንያን መሰብሰቢያ፤
የባለ ቅኔው ማሸብሸቢያ።
.......🕊
ሰላም ለመካንኪ መካነ ሰላም ደብረ ዳሞ፤
ይጸልዩ ባቲ አበው ቅዱሳን በአርምሞ፤
አረጋዊ በዘንዶ፤
በገደል ላይ ተረማምዶ፤
ለገደማት ጌታ ፈቅዶ።
........🕊
ሰላም ለመካንኪ ምስራቀ ፀሐይ ዘደብረ ዘይት፤
መካነ ሕይዎት አማናዊት፤
ላሳደገችን በውብ ቋንቋ፤
ላስያዘችኝ የዜማ ቃል።
......🕊
ሰላም ለአቡኪ ወልደ ማርያም፤
ንጉሰ ነገስት ስቡህ በአርያም፤
ጠላትሽን ለተዋጋ፤
ለብርታሽ ክንዱን ለዘረጋ፤
ቅጥርሽን በእሳት ለዘጋ።
........🕊
ሰላም ለእምኪ እመ ብዙኃን፤
ዛቲ ይእቲ ተድላ ብዙኃን፤
በአሥራት ለተሰጠሻት፤
በየዘመን ለጠራሻት፤
ስለ ፍቅሯ እናት ላልሻት።

#መልክአ_ኢትዮጵያ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ አስራት ሀገርሽን ኢትዮጵያን
አስቢያት።

+።+።+።+

-ሰለ እናትህ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም:
-ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ
-ስለ ቅዱስ ያሬድ
-ስለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
-ስለ ቅድስት አርሴማ
-ስለ ዜና ማርቆስ
-ስለ አባ ኪሮስ
-ስለ አቡነ ሀብተማርያም
-ስለ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት
-ስለ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ:
-ስለ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
-ስለ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ብለህ ኢትዮጵያን ማራት ይቅር በላት። አሜን


@aleroe
ኤልሮኢ:
#አልችልም_አስችለኝ

እየደነገጠ እየፈራ ልቤ
አንድነት አቅቶት ቅጥልጥል ሃሳቤ
ኮሽ ባለ ቁጥር እየፈራች ነፍሴ
አስጨንቀዋለሁ እራሴን በራሴ
አይኖቼ ተስፋዬን ማየት ተስኖአቸው
እግሮች ጉዞዬን መጓዝ አቅቶአቸው
ይቅበዘበዛሉ መሪ ጠፍቶባቸው
ዝም ባለ ጎጆ ጭጭ ባል ሌሊት
ጩኽት ይሰማኛል ምንም በሌለበት
የሚያሳርፍ ጌታ እንዳለኝ ይወቀው
የሚያስጨንቀኝን አምላኬ አስጨንቀው
አንተ ድረስና የጭንቀቴን ውል ፍታ
አልችልም አስችለኝ እንዳልጠፋ ጌታ

@aleroe
ኤልሮኢ:
እኛን ከወደደበት

እኛን ከወደደበት ከጥልቅ ፍቅሩ የተነሳ
በደላችን ተሻረ ሀዘናችን ተረሳ(2)
ፅድቃችን ሆኖ እንደ መርገም
ነፍሳችን ዝላ በሞት ሸክም
ስለወደደን ጌታ ፈቅዶ
ይኸው አዳነን እንዲ ወዶ
ከጥልቁ ጉድጓድ ተጥለን
ፅኑ መከራ ውስጥ ሳለን
ክርስቶስ በስጋ ተገልጦ
ህይወትን ሰጠን ሞትን ውጦ
ታስሮ ወረደ በፍቅር
መዳፉን ሰጠ ለችንካር
የባዘነውን ሰበሰበ
ርቀን ነበረ አቀረበን
ቁጥር የለውም ለዘመኑ
ድንበር የለውም ለማዳኑ
ይኸው ሞትን አሰናበተ
ሰማይ በደሙ ተከፈተ
#ዘማሪ ገብረ ዮሀንስ
በድምፅ 👇
@aleroe
ኤልሮኢ:

#በፀሎት ሰአት ሀሳባችን ለምን ይበተናል?
ቀሲስ ሄኖክ ወ/ማርያም

@aleroe
ኤልሮኢ:(ስነ ፅሁፍ)

#ናፈቀኝ ....

የማለዳ ተመስጦ ... ውዳሴ ማርያም መድገሜ
በልጅነት ልመጣልህ .. ጧት ማታ መፍገምገሜ
ዛሬ ግን ናፍቆት ሆነብኝ .. ተዘረረብኝ አቅሜ
እንቅልፌ ሰላም አጣ .... እባብ ሆነብኝ ሕልሜ ።
.
"እግዚኦ" ሲባል ሰምቼ .. ሳልነሳ ከትራሴ
ድንጋጤ ወረረኝ .. ከእግሬ ጥፍር እስከራሴ
ሰዓታቱን እየሰማሁ ... ተቀሰቀሰ መንፈሴ
ትዝዝ አለኝ ማኅሌቱ ... ስትዋብበት ነፍሴ
የእናቴ ስም ናፈቀኝ ...... የሕርያቆስ ቅዳሴ
.
እራሴንም ስላጣሁት ..... ከቤትህ በመራቄ
እንደ ሎጥ ሚስት መሰልኩኝ ፤ አደባባይ ደርቄ
.
የመዝሙረ-ዳዊት ጸሎት .. አነከተኝ በትዝታ
ነፍሴን ስላስጠማኋት ... አነባችብኝ አብዝታ
እሪሪሪ ብላ አለቀሰች ... በስጋ ወንጭፍ ተገዝታ
.
ናፈቀኝ ትምህርቱ ... የቅዱስ ያሬድ ጸጋ
ቁጥር ዜማ መጮሄ .... አንደበቴ እስኪዘጋ
ዛሬ ላለው ማንነቴ .. ምን ይሆን የ'ኔ ዋጋ ??
.
በከበሮ በጽናጽል ... መዘመሩ ማሸብሸቡ
ጃኖ ለብሶ በመሰለፍ ... ማመርገዱ መወረቡ
የትውስታ ስለት ይዘው ፤ ወደ ልቤ ሰርገው ገቡ
.
አምላኬንም ሳመሰግን .. ወደ ሰማይ አንጋጥጬ
እንዲህ ዛሬ ልቀብረው .. በልቤ ውስጥ ረግጬ
አገልግሎቴ ናፈቀኝ ... ከሁሉ በላይ አስበልጬ
ኮርስ ስማር ትዝ አለኝ ... በዛፉ ስር ተቀምጬ
.
አንገቴ ላይ የታሰረው .. ለምን ነበር ማኅተቤ
ዛሬ ለምን አታለልኩት .. በምክንያት ተንተብትቤ ?
.
ምኑ ነው የሆነብኝ .. ለቤተ መቅደስ እንቅፋት ?
ትዳር ለምን መሰለኝ .. ሜዳ ሆኖ ተዳፋት ?
ልቤ ከብዶ እስከመቼ .. እኖራለሁ በጥፋት ?
ነፍሴንስ ምንበወጣት ... በ'ሳት ጅራፍ ላስገርፋት
.
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ሰው መስዬ ሲመግቡኝ .. ባ'ይኔ ብሌን አይቻለሁ
ታዲያ ግን ምን ዋጋ አለው .. ማንበብ እንደሁ ትቻለሁ
.
እውነት ነው አይካድም .. አውደ ምኅረት መቀመጤ
ወንጌሉንም እየሰማሁ .... ሳላስበው መመሰጤ
ትዝ ይለኛል አጀንዳዬ ... ከንፈሮቼንም መምጠጤ
.
ጽዋ ቢሉ ዝክረ ሰንበት .. እንዳያልፈን ስንጣራ
ዓርብ ጸሎት ስንሰለፍ .. ነጭ ለብሰን በጋራ
ከትንሹም ከትልቁም ... ስለድኅነት ስናወራ
"ጉዞ" ብለን በባዶ እግር .. ሳንደክም በተራራ
ነጭ ለብሰን ጧፍ ይዘን .. እንደ ኮከብ ስናበራ
አዎ! አስታውሳለሁ ... ስልሳ ፍሬ ስናፈራ
.
ጾም ጸሎቱ ትዝ ይለኛል .. በላያችን ስናጌጠው
በስግደት ተሽቀዳድመን ... ሳጥናኤን ስናመልጠው
ብዙ ነበር በንስሐው ... በቁርባኑ የሚገልጠው
.
ጌታ ሆይ!
ተመልሶ ይላክልኝ ... መንፈሳዊ ጀግንነቴ
በመቅደስህ ዋጋ ይክፈል .. የናቡቴ ልጅነቴ
"እሺ" ብሎ እንዳልሰራው .. አይሁንብኝ ማንነቴ
.
ቀራኒዮ አይረሳኝ ... ችንካር ያለው መስቀሉ
በክቡር ደም ተነክሮ .. ቀይ ሆኖ መንቀልቀሉ
.
እመ ብርሐን በልደቷ .. ትመልሰኝ ወደ ጥንቱ
የቅዱሳን ጥበቃቸው .... አይለየኝ በረከቱ
ናፈቀኝ
ሰነፍ ልቤ እየገዛኝ .. በሞት ሰይፍ በጫጨቀኝ
ይቅር በለኝ አምላኬ! ... ከመቅደስህ አታርቀኝ
በግራ መቆም መረረኝ ፤ አሰልፈኝ በልጅህ ቀኝ
አብርሃምን ላክና ... መልስህን ቶሎ አሳውቀኝ
በራሴ አይን ስደናበር.. መታዘብህ አስጨነቀኝ
የምኅረት ቃል አንደበትህ ፤ ፅኑ ፍቅርህ ናፈቀኝ።

#ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
___________
ኤልሮኢ :

አልፋና ዖሜጋ

አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ
በከሀዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ/2/
አዝ---
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሠራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአደም ቤዛ ልትሆን ብዙ ተንገላታህ
አዝ ---
ቅዱሳን እጆችህ የፊጥኝ ታስረው
እንደ በግ ጎተቱህ ልትምራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑህ ለመመጻደቅ
አዝ ---
በዚያ አደባባይ በጲላጦስ ዘንድ
አሳልፈው ሰጡህ አጋልጠው ለፍርድ
ከሐና ቀያፋ ከካህናቱ ደጅ
ከእነ ሄሮድስ ዘንድ አቀረቡህ በአወጅ
አዝ---
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ጸናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር መከራ
አዝ---
አምስቱ ችንካሮች ቅንዋት መስቀል
አይሁዶች አመጡ ገላህን ለማቁሰል
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
አዝ---
ግፈኞቹ አይሁድ በአንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅ ተፉብህ አንተኑ ሊጎዱ
ለእኛ ወገኖች ሀጢያት ላደከመን
የመስቀልህ ጥላ ማረፊያ ይሁነን


@aleroe
Audio
#ውይይት

"እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ። "
(የሐዋርያት ሥራ 2: 36)

ሲል ምን ማለቱ ነው

በዲ/ን ኢዮኤል ዳኛቸው እና
በወንድማችን አቤኔዘር ማሙሸት
Audio
#ውይይት ክፍል ሁለት

"እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ። "
(የሐዋርያት ሥራ 2: 36)

ሲል ምን ማለቱ ነው

በዲ/ን ኢዮኤል ዳኛቸው እና
በወንድማችን አቤኔዘር ማሙሸት
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM