"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አንፈራፁ

አንፈራፁ ሰብዓሰገል /2/
ረኪቦሙ ህፃን /2/ ዘተወልደ ለነ /4/


❤️ @aleroe ❤️
ኤልሮኢ
#የዓለምን_በደል

የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ 
ዘጠና ዘጠኙን መላእክት ትቶ 
ጽድቅን ለመፈጸም በደልን አጥፍቶ 
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ 
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ 
- - - - - - አዝ - - - - - -

የሰማያት ሰማይ የማይችሉት ንጉሥ 
ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ 
ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደ ፈረስ 
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ 
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ 
- - - - - - አዝ - - - - - -
ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ 
ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ 
እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ 
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ 
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ 
- - - - -አዝ - - - - -
ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቀን ሲመሠርት 
መጣ በደመና ሰማያዊው አባት 
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት 
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ 
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ 

💚💛❤️@aleroe💚💛❤️
ኤልሮኢ
#ድንግል_ፈጣሪዋን_ወለደችው

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀቀለለችው
የለምና ስፍራ ለንግዶች ማረፊአ
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደርያ /2/
#አዝ
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ
ወረደ መልአኩ ምስራች ሊያወራ
የህፃኑ ክብር በምድር አበራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
#አዝ
ሰብአ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
ወርቅ እጣን ከርቤዉን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ላለም ተናገሩ ንጉስ መወለዱን
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
#አዝ
የይሁዳ ምድር ምስጋና ተመላ
ንጉስ መቷልና ከናዝሬት ገሊላ
ታምሩን ትናገር ቤተልሄም ታዉራ
ዝማሬ ሲወጣ ከርስቱ ቆጠራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
#አዝ
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ አንደ ሰዉ
በጠባቡ ደረት አዳምን መሰለዉ
ገረማት ጥበቡ ታናሹአን ሙሽራ
ተዋህዳልና ቃል ከ ስጋ ጋራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/

💚 @aleroe 💚
💛 @aleroe 💛
❤️ @aleroe ❤️
ታህሳስ 29/04/2011 ዓ.ም
የበአለ ልደት ምስባክ

#ምስባክ ፦ መዝ 71÷ 10
ነገሥተ ተርሴስ ወደሰያት አምኃ ያበውዑ።
ነገሥተ ሳባ ወዐረብ ጋዳ ያመጽኡ።
ወይሰግዱ ሎቱ ኲሎሙ ነገሥተ ምድር።

💚 @aleroe 💚
💛 @aleroe 💛
❤️ @aleroe ❤️
ኤልሮኢ፡
📚ዳንኤል 📚ክብረት📚

ጊንጥ አና ጊንጠኞች!!

ብዙ ጊዜ ጊንጥ የሚለውን ቃል ስሰማ ብዙም ትኩረት አልሰጠውም ነበር ዛሬ ግን ጊንጥ አሪፍ ነገር አስተማረኝ፡፡ ይህንን እንድል ያስገደደኝ የዛሬው ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ አጭር ታሪክ ነው ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡
አንድ ሽማግሌ ውሃ ውስጥ ሊሰምጥ ያለ ጊንጥ ያዩና ሊያድኑት ይፈልጋሉ፡፡ ከዚያም ጊንጡን ከውሃው ለማውጣት እጃቸውን ዘርግተው አነሱት በዚህ ጊዜ ጊንጡ ነደፋቸው እሳቸውም ደንግጠው ለቀቁት ጊንጡም ተመልሶ ወደውሃው ገባ፡፡ ሽማግሌው አሁንም የጊንጡን ውሃ ውስጥ መስመጥ ተመልክተው ድጋሚ እጃቸውን ለእርዳታ ዘረጉለት አሁንም በድጋሚ ጊንጡ ነደፋቸው ሲለቁት አሁንም ውሃ ውስጥ ገባ፡፡ ይህንን የሽማግሌውን ትእይንት የሚመለከት አንድ ሰው ወደ ሽማግሌው ጠጋ ይልና ‹‹ይህ እኮ ክፉ ፍጥረት ነው ጊንጥ እሱን ለማዳን ሲሉ እርሶ እየተጎዱ እኮ ነው›› አላቸው።
ሽማግሌውም እንዲህ ሲሉ መለሱ ‹‹የጊንጡ ተፈጥሮ መናደፍ ነው፡ የኔ ተፈጥሮ ደግሞ መርዳትና ማገዝ ነው፡ ስለዚህ ተፈጥሮዬ ክፉ አደለምና ጊንጡን ከመርዳት አላቋርጥም አረዳዴን ግን አስተካክላለሁ›› አሉና ጥቂት አሰብ አድርገው ተነስተው ከዛፉ ላይ አንድ ቅጠል ቀንጥሰው በቅጠሉ ጊንጡን ይዘው አወጡትና ህይወቱን አተረፉለት፡፡
እኛም እንዲህ ነን ሰውን ለመርዳት ስንሄድ ብዙ ጊንጦች ይነድፉናል፡ ደግ ልናደርግ ስንጓዝ ብዙ እንቅፋቶች ይመቱናል፡፡ ነገር ግን ጊንጡ እንዳይነድፈን እናደርጋለን እንጂ እንቅፋቱ እንዳይመታን እንጠነቀቃለን እንጂ እንዴት ደግ ማድረግ እናቆማለን ???
አንተም አንቺም ሁላችንም እዚህ ምድር ላይ ያለን ሰዎች በሙሉ ስንፈጠር ደግና መልካም ነን፡፡ ግን ሰውን ክፉ የሚያደርገው ተፈጥሮው ሳይሆን መጥፎ አጋጣሚ ነው፡፡ ለዛ እኮ ነው በነዚህ ጊንጦች ስለተነደፍን መልካም ለማድረግ ቅስቀሳ በጎ ለመስራት ማጣራት መጠራጠር በሌላ አይን መመልከት ጀመርን፡፡
እስኪ የዛሬዋን አዲስ ቀናችንን እንዲህ ብንውላትስ ሰው ስንረዳ እንደጊንጥ በሚሆኑ ሰዎች ተሸንፈን መልካም ከማድረግ ከምንቆጠብ የምንረዳበትን መንገድ ለይተን ብናውቅስ፡፡ በነገራችን ላይ ለሰው በጎ ማድረግ ሲባል በገንዘብ ብቻ ይመስለናል አይደለም በየቤቱ ገንዘብ ኖሮት ሰው የናፈቀው ህሊና አለ ስለዚህ አንዳንዶች ፈገግታችንን አንዳንዶች እኛነታችንን አንዳንዶች መሰማትን ይፈልጋሉና በየደረስንበት ለመልካም ነገር ጊንጥ ፈርተን እምቢ እንዳንል፡፡
መልካም የምታደርጉ ሁሉ ግን ጊንጡንም ቢሆን ከማዳን አትቦዝኑ።
@aleroe
#እንዘምር

እንዘምር/2/በእልልታ
ለመድሀኔዓለም ለሰራዊት ጌታ
#አዝ
የጠፋውን ሊያድን ወረደ ከላይ
እንዘምር በእልልታ
የበጎች እረኛ አምላክ አዶናይ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
ትንቢት ተናገሩ ነቢያት በሙሉ
እንዘምር በእልልታ
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
ገብርኤል ተልኮ ልደቱን አብሳሪ
እንዘምር በእልልታ
ስጋለብሶ ሲታይ ረቂቅ ፈጣሪ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
ብርሃን ወጣላቸው ለአዳም ልጆች ሁሉ
እንዘምር በእልልታ
የጌታን መወለድ በተስፋ ላመኑ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
በሰማይ በምድር እርቅ ተወጠነ
እንዘምር በእልልታ
ስለተወለደ እግዚአብሄር ምስሌነ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
አምላክ ስጋ ለብሶ እንዴት ተዋረደ
እንዘምር በእልልታ
መጠጊያ ቦታ አጥቶ በጎል ተወለደ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
የሚለብሰው አጥቶ የብርሀናት ጌታ
እንዘምር በእልልታ
ኮባ ቅጠል ለብሶ እጅግ ተንገላታ
እንዘምር በእልልታ

@aleroe
ኤልሮኢ
*ብሒለ አበው*
አንድ ሰው አንድ አባት ጋር ቀርቦ አንዳንዶች መላእክት ተገለጡልን ይላሉ ብሎ ጠየቃቸው።
እሳቸውም ከዚህ የበለጠ ደስ የሚያሰኘውስ ሁልጊዜ በኃጢአታቸውን ቢያዩ ቢያስቡ ነበር ሲሉ መለሱለት።
አንድ አባት እንዲህ አሉ ስሕተተኛ በሆናቹ ጊዜ ሁሉ ሌላውን አትወንጅሉ። ይህ የሆነው በራሴ ኃጢአትና ድክመት ምክንያት ነው በሉ። ቅዱሳን አባቶቻችን እንዲህ በማለት ተናግረዋል በርግጥ መላእክት ሊታዩክ ቢችሉ እንኳን አትቀበል ራስህን አዋርድ። እኔ ሃጢአተኛ ነኝና መላእክትን ባይ ምን ይጠቅመኛል በል።
@aleroe
#ዮሐንስኒ

ዮሐንስኒ ያጠምቅ/2/
በሄኖን/4/ በማዕዶተ ዮርዳኖስ

ዮሐንስ ሲያስተምር ያጠምቅ
በጫካ በሜዳ ያጠምቅ
የበግ ፀጉር ለበሶ ያጠምቅ
ሆኖ ምድረ በዳ ያጠምቅ

አምላኩን የሚወድ ያጠምቅ
ብዙ ሰው እያለ ያጠምቅ
ጌታውን ለማጥመቅ ያጠምቅ
ዮሐንስ ታደለ ያጠምቅ

ተራራው ዝቅ ይበል ያጠምቅ
ጎባጣውም ይቅና ያጠምቅ
ብሎ ያስተማረው ያጠምቅ
ዮሐንስ ነውና ያጠምቅ

ከሐጢያት ተለዩ ያጠምቅ
በውሀ ተጠመቁ ያጠምቅ
መንግስተ ሠማያት ያጠምቅ
እንዳለች እወቁ ያጠምቅ


@aleroe
ኤልሮኢ
ጥር 05/05/11 ዓ.ም.
#መዝሙር ይሠርቅ ኮከብ

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ፡፡

ዲ/ን ሮሜ 11÷25_ፍ.ም
ን/ዲ 1 ዮሐ 4÷1_9
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 6÷16_23

#ምስባክ፦ መዝ 88÷27

ወአነሂ በኲርየ እሬስዮ
ወልዑል ውእቱ እምነገሥተ ምድር
ወለዓለም አአቅብ ሎቱ ሣህልየ

#ትርጉም
እኔም በኲሬ አደርገዋለሁ
ከምድር ነገሥታት ይልቅ ከፍ ያለ ነው
ይቅርታዬን ለዘለዓለም እጠብቅለታለሁ

#የዕለቱ ወንጌል፦ ማቴ ፪፥፩ - ፲፫
#ቅዳሴ፦ ዘዲዮስቆሮስ

👉 @aleroe
ኤልሮኢ
#ሖረ_ኢየሱስ

ሖረ ኢየሱስ /4/
ዘገሊላ /3/ ሃበ ዮሐንስ /2/ (ዮርዳኖስ)
#ትርጉም
ሄደ ኢየሱስ ከገሊላ ወደ ዮሐንስ (ወደ ዮርዳኖስ)

💚 @aleroe 💚
ኤልሮኢ
ዮም_ፍስሐ_ኮነ

ዮም /ፍስሐ ኮነ/(2)
በእንተ ልደታ ለማርያም

በባርነት ሳለን ፍስሐ ኮነ
ኃጢአት በአለም ነግሳ ፍስሐ ኮነ
በድንግል መወለድ ፍስሐ ኮነ
ቀረልን አበሳ ፍስሐ ኮነ
እግዚአብሔር መረጠሸ ፍስሐ ኮነ
ልትሆኚው እናቱ ፍስሐ ኮነ
ይኸው ተፈፀመ ፍስሐ ኮነ
የዳዊት ትንቢቱ ፍስሐ ኮነ

አዝ

የሔዋን ተስፋዋ ፍስሐ ኮነ
የአዳም ዘር ህይወት ፍስሐ ኮነ
የኢያቄም የሐና ፍስሐ ኮነ
ፍሬ በረከት ፍስሐ ኮነ
ምክንያተ ድኂን ፍስሐ ኮነ
ኪዳነምህረት ፍስሐ ኮነ
ድንግል ተወለደች ፍስሐ ኮነ
የጌታዬ እናት ፍስሐ ኮነ

አዝ

በሔዋን ምክንያት ፍስሐ ኮነ
ያጣነውን ሰላም ፍስሐ ኮነ
ዛሬ አገኘነው ፍስሐ ኮነ
በድንግል ማርያም ፍስሐ ኮነ
የምስራች እንበል ፍስሐ ኮነ
ሀዘናችን ይጥፋ ፍስሐ ኮነ
ተወልዳለችና ፍስሐ ኮነ
የአለም ሁሉ ተስፋ ፍስሐ ኮነ

💚 aleroe
ኤልሮኢ
# የምስራች

የምስራች ደስ ይበለን (2)
የዓለም መድኃኒት ተወለደልን
ምስራች ደስ ይበለን
አዝ.....

ዐማኑኤል የዓለም ቤዛ(2)
የዓለም ቤዛ (2) ለኛ ተወለደ

አዝ......
ንጉስ ሄዶድስ ይህን ሲሰማ(2)
ፈልጋችሁ አምጡት (በቀን በጨለማ(2)
አዝ.....

ሰብዓ ሰገል እንደ ታዘዙ(2)
በኮከብ ተመርተው (ሕጻኑን አገኝት(2)
አዝ......

ሰገዱለት ከመሬት ወድቀው(2)
ወርቅ እና ዕጣኑን (ከርቤውንም ስጥተው(2)

💚@aleroe
ኤልሮኢ
#ጥምቀተ_ባሕር

ጥምቀተ ባሕር ዮርዳኖስ ነያ /2ጊዜ/
ሀሌ ሉያ /4ጊዜ/
አዝ - - - -
ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለችው
አልችለውም ብላ ወደ ኋላ ሸሸች
ብርሃነ መለኮት በወንዙ ሲሞላ
ዮርዳኖስም ሸሸ ሄደ ወደ ኋላ
አዝ - - - - -
አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ
ለልጁ ምስክር ሊሆን ፈለገና
ቃሉን ተናገረ ሆኖ በደመና
አዝ - - - - - -
ጌታችን ሲጠመቅ በ30 ዓመት
ባሕር ኮበለለች ግዑዟ ፍጥረት
ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀአዳ
ምሥጢረ ሥላሴ ታየ የዛን ለታ
አዝ - - - - - - -
እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት መገኛ
የጽድቅ መሰላል የድኅነታችን መገኛ
ቀላያት አብርህት ብዙዎች እያሉ
እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ


💛 @aleroe 💛
#በእደ_ዮሐንስ

በእደ ዮሐንስ ተጠምቀ
ኢየሱስ ናዝራዊ/2/
ሰማያዊ /5/ ኢየሱስ ናዝራዊ/2/
#ትርጉም
ናዝራዊ ኢየሱስ ክርስቶስ
በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ።

💚 @aleroe 💚
ፆመ ገሀድ

ገሃድ መገለጥ መታየት ነው፡፡ በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት እድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲህ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኃላ በ 30 ዓመት እድሜው በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ይሰቀላል ይሞታል ይነሳል ብለው የተናገሩለት መሲሕ እርሱ መሆኑ ተገልጦአልና፡ አንድም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠለት በመሆኑ ገሃድ ይባላል፡፡ (ማቴ 3፡13-17)
ይህን በማሰብ የምንጾመው ጾም “የገሃድ ጾም” ይባላል፡፡ ቀኑም በዓለ ጥምቀት ከመዋሉ አንድ ቀን ቀድሞ ማለትም ጥር 10 ቀን ለ 11 አጥቢያ ነው፡፡ስለዚህ ጥር 10 ቀን ከ ሰባቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው የገሃድ ጾም ነው ማለት ነው!

❤️@aleroe❤️
ኤልሮኢ
+++ ልብስህን ማን ወሰደው? +++

በአንድ ወቅት አባ ሰራብዮን ወደ እስክንድርያ ሄደ፡፡ በገበያም ስፍራ አንድ ከልብስ የተራቆተ ነዳይ አገኘ፡፡ ለራሱም ‹ይህ ደሃ ሰው ታርዞ መነኩሴ የተባልኩ እኔ እንዴት ለብሼ እታያለሁ? በእውነት ይህ ‹ታርዤ አልብሳችሁኛልና› ብሎ የተናገረው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? በዚህ ብርድ አየር እየተሰቃየ እኮ ነው!› ብሎ ፈጥኖ የገዛ ልብሱን ከራሱ በማውለቅ ይለብስ ዘንድ ለዚያ ደሃ ሰጠው፡፡ ከዚያም በእጁ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደያዘ እርቃኑን በጎዳናው ላይ ተቀመጠ፡፡ የከተማውም ባለጠጋ ሰው አባ ሰራብዮን ባለበት ሥፍራ ሲያልፍ ተመልክቶት ወደ እርሱ ቀረበና ‹አባ ሰራብዮን ሆይ ልብስህን ማን ወሰደው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ቅዱስም በእጁ ወደ ያዘው መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቆመ ‹ልብሴን የወሰደው ይህ ነው!› አለው፡፡ ያም ባለጠጋ ልብስን ገዝቶ ካለበሰው በኋላ አባ ሰራብዮን ከእርሱ እንደ ተለየ በመንገድ ዕዳውን መክፈል ስላልቻለ እየተንገላታ ወደ ወኅኒ ቤት የሚሄድን አንድ ሰው ተመለከተ፡፡ ቅዱሱም አባት የያዘውን መጽሐፍ ቅዱሱን ሽጦ የዚያን ሰው ዕዳ በመክፈል ነጻ አደረገው፡፡ ይህንም ፈጽሞ ጉዞውን ሲጀምር ሌላ አንድ ነዳይ ሲለምን ተመልክቶ ዳግመኛ የለበሰውን ልብስ አውልቆ ሰጥቶ እርቃኑን ወደ በአቱ ተመለሰ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም እርቃኑን ባዩት ጊዜ ‹መምህር! ልብስህ ወዴት አለ?› ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹መጸወትኩት› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መልሰው ‹እኛን የሚያጽናናን መጽሐፍ ቅዱስህስ አባታችን? › ሲሉ ደግመው ጠየቁት፡፡ አባ ሰራብዮንም ‹መጽሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ ‹ሂድ ያለህን ሽጠህ ለድሆች ስጥ› ይለኛል፤ ስለዚህ እርሱንም ሸጥኩት› አላቸው፡፡

ምንጭ :–Paradise of the monks, P 89

ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደሚናገረው ምጽዋት የፊት መብራት ናት፡፡ አንድ ሰው በጨለማ ሲጓዝ ከኋላው መብራት ቢያበሩለትም እንኳ ከፊቱ የሚቀድመው የገዛ የአካሉ ጥላ እንቅፋት እየሆነበት ይጥለዋል፡፡ ወደ ፊት ያለውን መንገድ አጥርቶ እያየ ያለ ስጋት ለመሄድ እንዲችል የግድ የፊት መብራት ያስፈልገዋል፡፡ ጾም ፣ጸሎት እና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋት እንደ ኋላ መብራት ናቸው፡፡ የፊት መብራት የተሰኘች ምጽዋት ካልታከለችባቸው እነዚህ ብቻቸውን ዋጋን አያሰጡንም፡፡ ከምጽዋት በላይ ታላቅ ነገር እንደሌለ ልንረዳ ይገባል፡፡ ዓለም ሁሉ ከነበረበት የበደል ዕዳ የዳነው ቸር እረኛ በሆነው በመድኃኔ ዓለም በአካሉ ምጽዋትነት (በሥጋው በደሙ መሰጠት) ነውና!!!


@aleroe
ኤልሮኢ
ኦ-ክርስቶስ

ኦ ክርስስ ኦ አምላክ ብሩህ ነህ/2/
ልቦናዬን አብራው በጥዑም ቃልህ/2/

አዝ-----

የታቦር ደመና------ክርስቶስ
የሲና ልምላሜ--------ክርስቶስ
ምነው ሙሴን በሆንኩ---ክርስቶስ
እንዳይህ ቀድሜ---- ክርስቶስ
የዮርዳኖስ ውሃ------ክርስቶስ
በላዬ ሲፈላ =ክርስቶስ
የሐንስን በሆንኩ እንዳይህ በተድላ
አዝ--------
ነበልባል ሐመልማል-----ክርስቶስ
ተዋህዶ ሲና------ክርስቶስ
ሙሴ ከሩቅ ሆኖ---ክርስቶስ
ተመልክቷልና-----ክርስቶስ
በቀረበ ጌዜም----ክርስቶስ
ነገሩን ሲረዳ---ክርስቶስ
ለእሥራኤል ሾምከው ሁሉ እንዳይጎዳ
አዝ-----
ሙሴ በበትሩ---ክርስቶስ
ኤርትራን ሲመታ---ክርስቶስ
ተሻገሩ እሥራኤል---ክርስቶስ
በብዙ ደስታ----ክርስቶስ
ያልተደሰቱማ----ክርስቶስ
የፈርኦን ሠራዊት---ክርስቶስ
እየተሰጠሙ ቀሩ ወደ ኀላ
አዝ------
ትንቢቱ ጸደቀ---ክርስቶስ
የኢሳይያስ------ክርስቶስ
ድንግልም ወለደች----ክርስቶስ
በመንፈስ ቅዱስ-----ክርስቶስ
ምነው ባደረገኝ----ክርስቶስ
እንደ ሰሎሜ------ክርስቶስ
ጌታዬ ሲወለድ ለማመስገን ቆሜ
አዝ------
ሐዋርያት ሁሉ-----ክርስቶስ
ዞረው ያስተማሩት---ክርስቶስ
ወንጌልህ ብርሃን ነው----ክርስቶስ
የዓለም መድሃኒት-----ክርስቶስ
ዮሐንስ እንዳለው-----ክርስቶስ
ጥምቀት ለንሰሐ------ክርስቶስ
እጠመቀዋለሁ የጎንህን ውሃ
አዝ------
ሚካኤል በቀኝህ-----ክርስቶስ
ገብርኤል በግራ-----ክርስቶስ
ቅውማን የሆኑት-----ክርስቶስ
ሁሉም በየተራ------ክርስቶስ
ሱራፌል ኪሩቤል----ክርስቶስ
ዐይናቸው የበዛ------ክርስቶስ
ያመሰግኑሃል አንተን የዓለም ቤዛ


💚 @aleroe
ኤልሮኢ
ሞገድ ሲመታኝ

ሞገድ ሲመታኝ ማእበሉ
ማን ያድነዋል ሁሉም ሲሉ
በሰላም አለፍኩ በፀጥታ
ሁሉተችሎ ባንተጌታ

ባንተስ ቁስል ተፈወስኩኝ
ጌታ በፍቅርህ ተማረኩኝ
ሞቴን ሽረኀው ባንተሞት /2/
ይኀው አቆምከኝ በሂወት /2/

ደጅህ ሲጠና ስማፀንክ
መቼ ጨከነጌታ ልብ
እንደቀራጩ አጎነበስኩ
ምህረት ፀጋህን ከጂህ ለበስኩ

ዘውትር እልል ብልብዘምር
ስለገባኝ ነው ያንተፍቅር
ጌታ ምጠራው ስምህን/2/
ለውጠኀው ነው ታሪኬን/2/

አይኖች አያዩ ካንተበቀር
የምትወደድ ምትፈቀር
ዘመድ ወገኔ ሆነህኛል
እኔን የሚችል የት ይገኛል


💚@aleroe💚
ኤልሮኢ፡
✞ ህፃን ንኡስ

ህፃን ንኡስ /3/
ዘይትፈርእ ትዐዛዘ ንጉስ /2/


💚@aleroe❤️
ኤልሮኢ
#ወዳጄ ሆይ!

የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡

አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡ ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@aleroe
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥