Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
ምክረ አበው
“ #እምነት-አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡
ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡
ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን #የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡
እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!!
@aleroe

ኤልሮኢ
ማርያም ማርያም
°ማንኛውም የአለም ሰው 5 የስሜት ሕዋሳት አሉት የኢትዮጵያውያን ግን 6 ነው ስድስተኛውም ቅድስት ድንግል ማርያም ናት
+ እርጉዝ ሴት እቤት ስትመጣ የማርያም እንግዳ መጣች
+ ልትወልድ ስትል ማርያም ማርያም
+ ስትወልድ እንኳን ማርያም ማረችሽ
+ እሷ አልጋላይ ሆና ማርያም ታኑርሽ(ህ)
+ ተጠይቆ ሲወጣ ማርያም በሽልም ታውጣሽ
+ ስንጫወት የማርያም መንገድ ስጠኝ(ስጪኝ)
+ ትንሿ ጣታችንን የማርያም ጣት
+ ሰው የጠራን መስሎን ስንደነግጥ የማርያምን ብቅል እየፈጨው ነው
+ ገላችን ላይ ምልክት ስትወጣ ማርያም የሣመችኝ
ኸረ ስንቱ ይነገር እኛ እና እሷ ያለን ወዳጅነት።
መልካም የፆም ጊዜ

🕐 የካቲት 22/06/2012 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
👉 ዲያቆን
📖 1 ቆሮ. 12፥1 ወበእንተሂ ዘመንፈስ ቅዱስ .....
👉 ንፍቅ ዲያቆን
📖 1 ጴጥ. 1፥7 ወባሕቱ አዳጠ ይእዜ ሀለወክሙ ....
👉 ንፍቅ ካህን
📖 ግብረ ሐዋርያት 16÷16 ወእንዘ ነሐውር ለፀሎት ....
👉 ምስባክ
ዘነግህ
1 📖መዝ. 142/143፥1
----------------
እግዚኦ ስምዓኒ ጸሎትየ ወአፅምአኒ ስእለትየ በጽድቅከ ወስምዐኒ በርትዕከ
ዘቅዳሴ
2 📖መዝ. 142/143፥8
----------------
ዘይሰማዕ ግበር ሊተ ምሕረትከ በጽባሕ እስመ ኪያከ ተወከልኩ እግዚኦ ምርሀኒ እግዚኦ ፍኖተ እንተ ባቲ አሐውር
ትርጉም
-------------
1:- አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፤ በእውነትህ ልመናዬን አድምጥ፥ በጽድቅህም መልስልኝ
2:- አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ
📖 ወንጌል
የሉቃስ ወንጌል 13÷ 10 - 17
---------------------
በሰንበትም በአንድ ምኵራብ ያስተምር ነበር ፤ እነሆም፥ ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ የድካም መንፈስ ያደረባት ሴት ነበረች፥ እርስዋም ጐባጣ ነበረች ቀንታም ልትቆም ከቶ አልተቻላትም ፤ ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና። አንቺ ሴት፥ ከድካምሽ ተፈትተሻል አላት፥ እጁንም ጫነባት ፤ ያን ጊዜም ቀጥ አለች፥ እግዚአብሔርንም አመሰገነች ፤ የምኵራብ አለቃ ግን ኢየሱስ በሰንበት ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ መለሰና ሕዝቡን። ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት አይደለም አለ ፤ ጌታም መልሶ። እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በሰንበት በሬውን ወይስ አህያውን ከግርግሙ ፈትቶ ውኃ ሊያጠጣው ይወስደው የለምን? ፤ ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው ፤ ይህንም ሲናገር ሳለ የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ ከእርሱም በተደረገው ድንቅ ሁሉ ሕዝቡ ሁሉ ደስ አላቸው።
📖 ቅዳሴ
ግሩም

አንተ ነህ
አንተ ነህ ×(2)
ከቀድሞ ጀምሮ ታምር የሰራህ
ከቀድሞ ጀምሮ የወጣ ዝናህ
ትላንትናም ዛሬም ዘላለም ያለህ
የእግዚአብሄር ስም ግንብ እያፈረሰ
ቃዴስና በርኔን እያረሰረሰ
ባህር ከፍሎ ህዝብ እያሻገረ
ይኖራል ለትውልድ እየተነገረ
በተዘረጋች እጅ በፀናች ጉልበቱ
በታላቅ ትድግና ይኖራል ፍጥረቱ
እግዚአብሄር ነውና ብርቱና ገናና
ለዘላለም ክብሩ ይነገራል ገና×(2)
ተናገሩ የተጎበኛችሁ
ነቀፌታችሁን ያስወገደላችሁ
ያለፋችሁ ሳይነካቹ ቀስቱ
ከአንበሳ መንጋጋ ተርፋችሁ ከእሳቱ
በተዘረጋች እጅ በፀናች ጉልበት
በታላቅ ትድግና ይኖራል ፍጥረቱ
እግዚአብሄር ነውና ብርቱና ገናና
ለዘላለም ክብሩ ይነገራል ገና×(2)
ከሞት መዳን በእርሱ ነው ማምለጥ
ማንም አይከለክል እግዚአብሄር ሲሰጥ
ከመረጠ ካበቃ ለርስቱ
ሀሌሉያ መዝሙር ይምጣለት ከቤቱ
በተዘረጋች እጅ በፀናች ጉልበቱ
በታላቅ ትድግና ይኖራል ፍጥረቱ
እግዚአብሄር ነውና ብርቱና ገናና
ለዘላለም ክብሩ ይነገራል ገና×(2)
#ዘማሪ ገብረ ዮሀንስ
@aleroe
አንተ ነህ
አንተ ነህ ×(2)
ከቀድሞ ጀምሮ ታምር የሰራህ
ከቀድሞ ጀምሮ የወጣ ዝናህ
ትላንትናም ዛሬም ዘላለም ያለህ
የእግዚአብሄር ስም ግንብ እያፈረሰ
ቃዴስና በርኔን እያረሰረሰ
ባህር ከፍሎ ህዝብ እያሻገረ
ይኖራል ለትውልድ እየተነገረ
በተዘረጋች እጅ በፀናች ጉልበቱ
በታላቅ ትድግና ይኖራል ፍጥረቱ
እግዚአብሄር ነውና ብርቱና ገናና
ለዘላለም ክብሩ ይነገራል ገና×(2)
ተናገሩ የተጎበኛችሁ
ነቀፌታችሁን ያስወገደላችሁ
ያለፋችሁ ሳይነካቹ ቀስቱ
ከአንበሳ መንጋጋ ተርፋችሁ ከእሳቱ
በተዘረጋች እጅ በፀናች ጉልበት
በታላቅ ትድግና ይኖራል ፍጥረቱ
እግዚአብሄር ነውና ብርቱና ገናና
ለዘላለም ክብሩ ይነገራል ገና×(2)
ከሞት መዳን በእርሱ ነው ማምለጥ
ማንም አይከለክል እግዚአብሄር ሲሰጥ
ከመረጠ ካበቃ ለርስቱ
ሀሌሉያ መዝሙር ይምጣለት ከቤቱ
በተዘረጋች እጅ በፀናች ጉልበቱ
በታላቅ ትድግና ይኖራል ፍጥረቱ
እግዚአብሄር ነውና ብርቱና ገናና
ለዘላለም ክብሩ ይነገራል ገና×(2)
#ዘማሪ ገብረ ዮሀንስ
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
#ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ማትያስ_ቀዳማዊ_ፓትርያሪክ_ርእሰ_ሊቃነ_ጳጳሳት_ዘኢትዮጵያ_ሊቀ_ጳጳስ_ዘአክሱም_ወፅጨጌ_ዘመንበረ_ተክለ_ሀይማኖትሞ
💚💛❤️
ዛሬ 7ኛ ዓመት በዓለ ሲመት እየተከበረ ነው። ረጅም እድሜና
ጤና ይስጥልንለአባታችን
#አሜን❤️
💚💛❤️
ዛሬ 7ኛ ዓመት በዓለ ሲመት እየተከበረ ነው። ረጅም እድሜና
ጤና ይስጥልንለአባታችን
#አሜን❤️
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:(ስነፅሁፍ)
በዜሮ ይባዛል!
ፆም×0=0 ስግደት×0=0
ጸሎት ×0=0
ተግቼ ብጸልይ እጆቼን ዘርግቼ
ቤቴ ባዶ ቢቀር ያለኝን መጽውቼ
ቀኑን ሙሉ ብጾም እስኪቆረጥ አንጀቴ
ዘወትር ብሰግድ እስኪዝል ጉልበቴ
በቀድስ ባስቀድስ በመቅደሱ ግርማ
ብዘምር ባወድስ የሚጣፍጥ ዜማ
ወንጌልን ብሰብክ ምስጢር አመስጥሬ
ብናገር ባስተምር ትርጉሙን ዘርዝሬ
ጥልና ክርክር ካሉ በህይወቴ
ሐሜት ክርክር ካልጠፉ ከቤቴ
በዜሮ ይባዛል ፍቅር በማጣቴ።
ስብሐት ለእግዚአብሔር!
ፆም×ፍቅር= 30 ያማር ፍሬ
ጸሎት×ፍቅር= 60ያማር ፍሬ
ስግደት× ትህትና= 100ያማረ ፍሬ
@aleroe
በዜሮ ይባዛል!
ፆም×0=0 ስግደት×0=0
ጸሎት ×0=0
ተግቼ ብጸልይ እጆቼን ዘርግቼ
ቤቴ ባዶ ቢቀር ያለኝን መጽውቼ
ቀኑን ሙሉ ብጾም እስኪቆረጥ አንጀቴ
ዘወትር ብሰግድ እስኪዝል ጉልበቴ
በቀድስ ባስቀድስ በመቅደሱ ግርማ
ብዘምር ባወድስ የሚጣፍጥ ዜማ
ወንጌልን ብሰብክ ምስጢር አመስጥሬ
ብናገር ባስተምር ትርጉሙን ዘርዝሬ
ጥልና ክርክር ካሉ በህይወቴ
ሐሜት ክርክር ካልጠፉ ከቤቴ
በዜሮ ይባዛል ፍቅር በማጣቴ።
ስብሐት ለእግዚአብሔር!
ፆም×ፍቅር= 30 ያማር ፍሬ
ጸሎት×ፍቅር= 60ያማር ፍሬ
ስግደት× ትህትና= 100ያማረ ፍሬ
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
ከዝሙት የዳነችው ብላቴና
ጫማ በመጠገን የሚተዳደር አንድ ሰው ነበር፡፡ ይህም ሰው ደም ግባቷ ያማረ፣ መልከ መልካም፣ የተወደደች፣ የተባረከች መንፈሳዊ ብላቴና ነበረችው፡፡ ውጫዊ ሰውነቷ ፈጽሞ ያማረ እንደሆነ ውስጣዊ ማንነቷም በትሕትና፣ በጸሎትና በጾም ያጌጠ ነው፡፡ ከታላላቁና ከታናናሹ ሁሉ ኃጢአት ርቃ፣ በፍጹም ሐሳቧ በልቧም እመቤታችንን ትወዳት ነበር፡፡ ስሟም ማርያም ይባል ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በእመቤታችን ስዕል ፊት ተቀምጣ “እመቤቴ ሆይ! ይህ ስም ላንቺ ብቻ ነው እንጂ ለእኔ አይገባኝም፡፡ አንቺ የንጹሐን ንጽሕት ነሽና አለች፡፡ በይቅርታሽ ድንግልናዬን ትጠብቂያት ዘንድ፣ የሰይጣንን ተንኮልን ሁሉ በፍቅርሽና በጸሎትሽ ከኔ ታርቂ ዘንድ የምእመናን አለኝታቸው ሆይ! እማጸንሻለሁ” ብላ እመቤታችንን ለመነቻት፡፡
የበጎ ነገር ጠላትና የአዳም ልጆችም ሁሉ ጠላት የሚሆን ሰይጣን ከዓላማዋ ሊያናውጻት ምክንያት አመጣባት፡፡ አንድ ፈረስ ያለው ሰው በመንገድ ሲሄድ ይህቺን ብላቴና አገኛት፡፡ ይህ ባለፈረስ አጅግ ባለ ጸጋና ገንዘቡም የበዛ ነው፡፡ ይህም ሰው ሴት ወዳጅ ስለሆነ ባያት ጊዜ ፈጽሞ ወደዳት፣ በሷም ፍቅር ተነደፈ፡፡
እርሱም ይህን የዝሙት ሐሳቡን እንድታስፈጽምለት አንዲት በጎ ምግባር የሌላትን ባነጋገሯና በሥራዋ የሰውን ልቡና የምታስት፣ ባንደበቷና በልቧ ውስጥ በሚኖር ሰይጣን ማሳትና በሥራዋ የሰውን ነፍስ ወደ ሲኦል የምታወርድ መሠሪት ሴት ወደ ርሷ ላከ፡፡ ያችን ደግ ብላቴና ክፉ በሚሆን ፊቷ ለማታለል ትነጋገራት ዘንድና ታግባባት ዘንድ ጀመረች፡፡ ያችም ደግ ብላቴና ነገሯን በሰማች ጊዜ ሐሳቧንና የውስጧን ተንኮል ዐወቀች፡፡ ፊቷንም ታጠቁር ዘንድ ሥራዋንም ትነቅፍ ዘንድ ጀመረች፡፡ ያችም ክፉ ሴት በብላቴናዋ መልስ እያዘነችና እየተከዘች ትታት ሄደች፡፡ ከዚህ በኋላ ለፈረሰኛው ሰው ሄዳ የኾነውን ነገረችው፡፡ እርሱም በዚች ብላቴና ፍቅር ምክንያት ልቡ እንደእሳት ተቃጥሎ ነበርና፣ እርሷን የሚያገኝበትን መንገድ ሁለተኛ እንድትመክረው ጠየቃት፡፡ ያቺም የሰይጣን የግብር ልጅ የኾነች ሴት እንዲህ አለችው፡፡ “ የዚያች ብላቴና አባት ድሃ ነው፣ አንተ ግን ባለጸጋ ነህና አስጠርተህ ከገንዘብህ ከፍለህ ስጠው፣ ያን ጊዜ ልጁን ፈጥኖ ያመጣልሃል” አለችው፡፡ እርሱም በክፉ ምክሯ ተመርቶ ያለችውን አደረገ፡፡ አባቷም ያለፍቃዷ ልጁን ይዞ እያዘነች እያለቀሰች ወደ ባለጸጋው ወሰዳት፡፡ ብላቴናዋም ሊታደጋት የሚችል ረዳትና ኃይል እንደሌለ ባወቀች ጊዜ አምላክን ወደ ወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደጸናች ክብርት እመቤታችን ጮኻ ለመነች፡፡ “ ሰውን የምትወጂ እመቤቴ ከእኔ አትራቂ” አለቻት፡፡ “የድኾች አለኝታቸው የምትሆኝ የተቸገሩትን የምታድኛቸው፣ ከዚያ ሰው ያንቺ ኃይል ይጸናል፣ ይበልጣል አድኚኝ እያለች ለመነቻት፡፡ ያም ባለጸጋ ብዙ ለቅሶዋንና ኀዘንዋን በሰማ ጊዜ “ለምን እንዲህ አድርገሽ ታዝኛለሽ፣ ታለቅሺያለሽ ኣላት” እኔስ ከሕጻነቴ ጀምሮ ድንግልናዬን ነፍሴን ለእመቤታችን ተስያለሁ አለችው፡፡ አንተም የድንግልናዬን ብጽዓት አፍርሰህ ብትወስደኝ በፈታሔ ጽቅ ልጀዋ ፊት በምትቆምበት በዕለተ ትንሳኤ ጊዜ ይችው ትፈርድብሃለች” አለችው፡፡
ፈረሰኛው ከዚያች ብላቴና አንደበት የእመቤታችን ስም ሲሰማ ፍጹም ፈርቶ እጀግ አዘነ ሰውነቱም ተንቀጠቀጠ፣ ደነገጠ፡፡ ያም ባለጸጋ ባመረ ቃልና በፍጹም ፍርሃት ልትመነኩሺ ትወጃለሽን አላት፡፡ ማገልገሏን የወደድኩ፣ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችንን አገለግላት ዘንድ “ አዎ እወዳለሁ” አለችው፡፡ እኔ ብዙ ገንዘብ ሰጥቼ ወደ መበለታት ገዳም ወስጄ እሰጥሻለሁ፡፡ ዳግመኛም ልብሳቸውንና ምግባቸውን እሰጣቸዋለሁ አላት፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ መበለታት ገዳም ወስዶ ይህችን ብላቴና እንደናንተ ጠብቁዋት፡፡ እኔንም በጸሎታችሁ አትርሱ ብሎ አደራ አስጠበቃቸው፡፡ ዘወትርም ይጎበኛቸው ነበር፡፡ የሚጠብቃቸውንም ያህል ብዙ ገንዘብና ምግባቸውን ይሰጣቸው ነበር፡፡
ተአምረ ማርያም ተአምር ፹፮

የካቲት 27/06/2012 ዓ.ም
በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ
መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ
👉 ዲያቆን
📖 ሮሜ. 6፥5 ወእመሰኬ ተመሰልናሁ በሞቱ .....
👉 ንፍቅ ዲያቆን
📖 1 ጴጥ. 2፥21 ወበእንተ ዝንቱ ተጸዋዕክሙ ....
👉 ንፍቅ ካህን
📖 ግብረ ሐዋርያት 10÷36 ወፈነወ ቃሎ ለደቂቀ እስራኤል ....
👉 ምስባክ
ዘነግህ
1 📖መዝ. 21/22፥16
----------------
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ
ዘቅዳሴ
2 📖መዝ. 55/56፥1
----------------
ተሣሃለኒ እግዚኦ እስመ ኬደኒ ሰብእ ወኵሎ አሚረ አሥርሐኒ ቀትል ወኬዱኒ ፀርየ ኵሎ ዓሚረ በኑኀ ዕለት
ትርጉም
-------------
1:- ብዙ ውሾች ከብበውኛልና፤ የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ
2:- አቤቱ፥ ሰው ረግጦኛልና ማረኝ፤ ሁልጊዜም በሰልፍ አስጨንቆኛል
📖 ወንጌል
የዮሐንስ ወንጌል 19 ÷ 16 - 30
📖 ቅዳሴ
ዮሐንስ አፈወርቅ

ምኩራብ
ምኩራብ የአብይ ጾም ሶስተኛው ሳምንት ነው።
ምኩራብ የአይሁዳውያን ቤተ መቅደስ ሲሆን
ይሄ ሳምንት ምኩራብ የተባለው ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ ለማስተማሩና በምኩራብ የሚሸጡ
የሚለውጡ ነጋዴዎችን ለማስወጣቱ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያ ስለሆነ ነው፡፡
ማቴ ፳፩፥፲፪―፲፬ እንዲህ ይላል«ኢየሱስ ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትና የሚገዙትንም ኹሉ አወጣ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጪዎችን ወንበሮች ገለበጠና ቤቴ የፀሎት ቤት ትባላለች
ተብሎ ተፅፏል እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችውት አላቸው።በመቅደስም እውሮችና አንካሳዎች ወደ ርሱ ቀረቡና ፈወሳቸው።»

ጌታችን አንጽሖተ ቤተ መቅደስን ኹለት ጊዜ መፈጸሙ በወንጌል ተጽፎልናል፡፡ አንደኛው በማቴዎስ 21 ላይ የሚገኝ ታሪክ ሲኾን፡ በሆሣዕና ጊዜ በስፋት የሚነሣ ነው፡፡ ሌላኛው በዮሐንስ 2 ላይ የሚገኘው ነው፡፡ በዚህኛው ክፍል ላይ ጌታችን የፈጸመውን የአንጽሖት ግብር በ3 ዋና ዋና ንዑስ ድርጊቶች ከፍለን መማር እንችላለን፡፡
1ኛ. ጌታችን ‹‹ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ››፡፡(ዮሐ.2፡13-14)፡፡ በመቅደስ የሚነግዱትንም አየ፡፡
2ኛ. ‹‹የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥ ርግብ ሻጪዎችንም። ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።›› (ዮሐ.2፡15-16)፡፡
3ኛ. ይህንን ያዩት አይሁድም በምን ሥልጣኑ ይህን እንደሚያደርግ ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ›› አላቸው፡፡
ልብ በሉ! ማንጻትን የሚያስብ ሰው ኹሉ እነዚህን ሦስት ነገሮች መፈጸም አለበት፡፡ ለአንጽሖት እጅግ አስፈላጊ ነጥቦች ናቸው፡፡
1ኛ. ማየት
የመጀመሪያው፡ ልናነጻው ያሰብነውን ነገር ኼዶ ማየት ነው፡፡ ሳያውቁት፣ ሳይረዱት ማንጻት አይቻልም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሊያነጻ የሚፈልግ ኹሉ፡ ቤተ ክርስቲያንን በደንብ ሊያያት፣ ወደ እርሷ ኼዶ ሊያገኛት፡ ሊያውቃትና ሊረዳት ይገባል፡፡ የዚያን ጊዜ በሬ ሻጮቹ፣ በግ ነጋዴዎቹና ርግብ ሻጮቹ ቁልጭ ብለው ይታዩታል፡፡ ኢትዮጵያንም ሊያነጻ የሚወድ በቅድሚያ ይቅረባት፣ በደንብ ይያት፣ ነጋዴዎቹ የቱጋ እንደ መሸጉ ይለይ፡፡ ራሱንም ሊያነጻ የሚወድ ቢኾን እንኳ፡ ‹‹ካህን›› ወይም ‹‹የንስሐ አባት›› በተባሉ መስታወቶች ራሱን በቅድሚያ በደንብ ማየት አለበት፡፡ ‹‹ራስህን ለካህን አሳይ፥ … ስለ መንጻትህ … መሥዋዕት አቅርብ›› እንዲል፡፡ (ሉቃ.5፡14)፡፡ ካህናት ‹‹አዕይንተ እግዚአብሔር / የእግዚአብሔር ዐይኖች›› ይባላሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ፣ ሀገርም ፣ እኛም በዚህ ዐይን ካልታየን ዕድፋችን አይለይምና መንጻት ከባድ ይኾናል፡፡
2ኛ. ማጽዳት
ጌታችን በመቅደስ ውስጥ የሚሠራውን ካየ በኋላ፡ በቅድሚያ ማጽጃውን ጅራፍ አዘጋጀ፡፡ ከዚያም በሬና በጎችን በጅራፍ አባረረ፤ ጅራፍ የማይችሉትን ርግቦችን ግን ባለቤቶቻቸው እንዲያስወጧቸው አዘዘ፡፡
ለቆሻሻ ኹሉ ማጽጃው አንድ አይደለም፡፡ መጥረጊያ ኹሉን አያጸዳም፡፡ መወልወያም እንዲሁ፡፡ ልብስ በሚታጠብበት የምግብ ዕቃ፣ ዕቃ በሚታጠብበትም ቤት አይታጠብም፡፡ ስለዚህ ለየትኛው ቆሻሻ ምን ዓይነት ማጽጃ እንደሚያስፈልግ በደንብ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ የበሬውን ማጽጃ ለርግብ የሚጠቀም አጽጂ፡ በርግጥም አጽጂ ሊባል አይችልም፡፡ በባሕርይዋ ንጽሕት በኾነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሰዎች ምክንያት ጉድለት ቢገኝ፡ ‹‹ይህ የእነ እገሌ ሥራ ነው፡፡ ጳጳሱ እያሉ፣ መምህሩ እያሉ፣ ቄሱ እያሉ… እኔ ምን ቤት ነኝ›› አይባልም፡፡ ጉድለቱን ሥርዐት በሚፈቅደው መልኩ ለማስወገድ መጣር እንጂ፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ‹‹የአባታችን ቤት›› ናት፡፡ የአባት ቤት ውስጥ ደግሞ ቆሻሻ ታይቶ አይታለፍም፡፡ ስለዚህ የምንወስደው ኹለተኛ ትምህርት አይቶ እንዳላየ ዝም ማለት ሳይኾን ለተግባር መንቀሳቀስን ነው፡፡
ጠያቂዎች ፣ ጌታችን ነጋዴዎቹን ሲያባርር፡ አይሁድ በጠያቂነት ተቃውመው ተነሥተው ነበር፡፡ በምን ሥልጣኑ ይህን እንደሚያደርግ ሲጠይቁት ነበር፡፡ እርሱም የጠየቁትን ምልክት ነገራቸው፡፡ እነርሱ ግን በሌላ ተረዱት፡፡ ‹‹ቤተ መቅደስ›› ሲል እነርሱ ሲሠራ ዓመታትን ስለ ፈጀው ቤተ መቅደስ ያስቡ ነበር፤ ‹‹እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር››፡፡ (ዮሐ.2፡21)፡፡
ማንጻት ስትጀምሩ፣ መልካም ሥራን ‹ሀ› ብላችሁ ስትወጥኑ ጠያቂና አድካሚ ተቃዋሚ አታጡም፡፡ ጠያቂውን ዝም የሚያሰኝ፣ ተቃዋሚውንም የሚቋቋም ዝግጅት ከሌላችሁ የጸዳው ቤት ተመልሶ መቆሸሹ አይቀርም፡፡ ስለዚህ ሥራው እያቆሸሹ መልሶ ማጽዳት እንዳይኾን እንዲህ ዓይነት ዝግጅትም ማድረግ ይገባል፡፡ ለሚጠይቁና ለሚቃወሙ ተገቢውን ምላሽ መስጠት፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ኹኑ›› ያለው ለዚህ ነው፡፡ (1ጴጥ.3፡15)፡፡ ይህ ደግሞ ካለ በቂ ትምህርትና ጸሎት አይኾንም፡፡
የሚገርመው ግን ተቃዋሚዎች ሥራቸው መቃወም ብቻ ስለ ኾነ እንኳን ሳትመልሱ ይቅርና በቂ ምላሽን ብትሰጡም ሊያጣምሙት ይችላሉ፡፡ ስለ ሰውነታችሁ እያወራችሁላቸው ስለ ሕንጻ አወራ ብለው ተቃውሟቸውን ይገፉበታል፡፡ የዚህን ጊዜ ‹‹ውሾች ይጮኻሉ፡ ግመሎቹ ግን ይጓዛሉ›› ብሎ መቀጠል ተገቢ ነው፡፡

ቀኑ መጋቢት 5 ዕለቱ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ሰዓቱ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት
ሆኗል፤ አሁንም ህማሙን እየታገለ እያላበው በድካም ለፍጥረቱ ሁሉ ይለምናል፤
“አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህን ኢትዮጰያንም ባርክ” ይላል። ህመም የጀመረው
መጋቢት 3 ዓርብ ቀን ነው፤ መታመሙን የሰሙ እንደርሱ ቅዱሳን የሆኑት
ዘርአቡሩክ፤ ፍሬ ቅዱስ፤ ያዕቆብ፤ ብንያምና ዮሴፍ እንዲሁም በወቅቱ የኢትዮጰያ
ንጉስ የነበረው እንድርያስ ሊጠይቁት ተሰብስበዋል ወደ አጠገቡ መድረስ ግን
አልተቻላቸውም አባታችን ገብረመንፈስ ቅዱስ የሚጋርደው እንጨት ዛፍ
በሌለበት በርሃ እንደ አንበሳ ተኝቶ አዩት በላዩ ያረፈው የእግዚአብሔር ጸጋ ከፊቱ
የሚወጣው ብርሃን ቀይ መልኩ ረዥም የራስ ጠጉሩ እንደ ነጭ ሐር የሚሆን
ጽሕሙ አስደነቃቸው። ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን ከሰማይ ታላቅ ነጎድጓድ
ድምጽ ተሰማ ጌታችን መላአክትን አስከትሎ ወደ አባታችን ወረደ፤ ከሰማይ ወደ
ምድር ህብሩ አምሳያው ልዩ ልዩ የሆነ እንደ ጸሐይና እንደ ጨረቃ የሚያበራ እንደ
ወንጪፍ ድንጋይ ይወረወር ነበር ከዚያ የነበሩ ሁሉ ፈሩ ወደ ኋላም ሸሹ ምድር
ራደች ተራሮች ኮረብቶች ተናወጡ ብርቱ ጩኸት ንውጽውጽታ ሆነ።“ወዳጄ
ገብረመንፈስ ቅዱስ ሰላም ላንተ ይሁን” እነሆ የማይታበል #ቃል_ኪዳን_እገባልሃለው_ስምህን_የጠራ_መታሰቢያህን_ያደረገውን_እጣን_ቋጥሮ_ግብር
ሰፍሮ መባ ይዞ ቤትህ የመጣውን እምርልሃለው አንተ ከገባህበት ገነት
መንግስተ ሰማያት አገባዋለሁ አለው፤ አባታችንም “#አቤቱ_ጌታ_ሆይ_የኢትዮጰያን
ህዝብ ማርልኝ” አለው፤ እነሆ ምሬልሃለው አስራት በኩራት አድርጌም
ሰጥቼሃለው፤ ከመጋቢት አምስት ቀን ጀምሮ ዝክርህን ያድርጉ በአማላጅነትህም
ይማጸኑ አለው። ከዚህ በኃላ ሰባቱ ሊቃነ መላክት የአባታችንን ነፍስ ሊቀበሉ
ወረዱ በታላቅ ምስጋናም ወደ ሰማይ አሳረጉት ስጋውንም ይዘውት ሄዱ የት
እንደተቀበረ ግን እስካሁን አይታወቅም አንዳንዱ በእየሩሳሌም ነው ይላሉ፤
ሌላው በምድረ ከብድ ነው ይላል ግን እስካሁን ልክ እንደ ሊቀ ነብያት ሙሴ ስጋ
የት እንደ ተቀበረ አይታወቅም። ገድሉ ትሩፋቱ ከሰማይ ከዋክብት ከምድር አሸዋ
ይበዛል ኢትዮጰያን አብዝቶ ይወዳታል፤ ምድራዊ ምግብ አልተመገበም የእናቱን
ጡት እንኳን አልጠባም፤ ልብስ፤ መጠለል አልፈለገም፤ የክረምት ቁር የበጋ
ሐሩር እየተፈራረቀበት በተጋድሎ 562 ዓመት ኖረ፤ በዛሬዋ ቀን መጋቢት 5
ሩጫውን ጨረሰ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ከአባታችን በረከት ያሳትፈን።
(መጽሐፈ ስንክሳር ዘመጋቢት)

........... ሰበር ዜና
የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቅዱስ ፓትሪያሪኩ
አማካይነት #ከዛሬ_እስከ_ትንሳኤ ድረስ የሚቆይ ሰደድ እሳት የሆነውን
ወረርሽኝ በሽታ ፈጣሪ እንዲያቆምልን #ፀሎተ_ምህላ አውጃለች ።

ማር፣ፌጦ፣ጤና አዳም፣ነጭ ሽንኩርት አንድ ላይ ፈጭታቹ አንድ ማንኪያ ዋጡ የሚል መልክት ሰዉን እያሸበረ ይገኛል።
መልክቱ ከአባቶች የተላከ ነው የሚሉት ነገር አለ። ነገር ግን የተኛቹ አባቶች እንደተላከ ግልፅ የወጣ ነገር የለም።
የተባለውን መተግበር ክፋት የለው
ለምን ? ከተባለ የተጠቀሱት ለሰውነታችን ገንቢ እንጂ ጎጂ አይደለም ነገር ግን እኚ መዳኒት ናቸው የተባሉት ንጥረ ነገሮች ከኮሮና ቫይረስ ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም።
#አትሸወዱ #አትሸበሩ
ዛሬ የሀይማኖት አባቶች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በጥሞና ጤና ሚኒስትር የሚለውን ተከታተሉ ማለታቸው ይታወሳል ስለዚህም አባቶቻችን ያሉትን ጤና ሚንስትርን እንከታተል።
ሆኖም ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል #እጅን_መታጠብ አንደኛው እና #ዋነኛው_መንገድ ነው።
#እጃችሁን_ታጠቡ
#ፀልዩ
#ስገዱ

መፃጉዕ
መፃጉዕ የአብይ ፆም አራተኛው ሳምንት ነው። በዚህ ሳምንት ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችንድውያንንስለመፈወሱየሚታሰብበት ሳምንት ነው።በዮሐ ፭፥፪―፲፩ እንዲህ ተፅፎ እናገኛለን«በኢየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቅያ ነበረች አምስት መመላለሻም ነበረባት በእነዚህ ውስጥ የውሀውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኛዎችና እውሮች አንካሳዎችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ህዝብ ይተኙ ነበር።
አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቅያቱ ወርዶ ውሀውን ያናውጥ ነበርና እንግዲህ ከውሀው መናወጥ በኋላ መጀመርያ የገባው ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር በዚያም ከሰላሳ ስምንት አመት ዠምሮ የታመመ አንድ ሰው ነበር።እየሱስ ይህ ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ እስከ አሁንብዙ ዘመን እንዲሁ እንደነበር አውቆ ልትድን ትወዳለህ አለው። ድውዩም ጌታ ሆይ ውሀው በተናወጠ ጊዜ መጠመቅያቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት።እየሱስም ተነስና አልጋህ ተሸከም ሂድ አለው።ያም ቀን ሰንበት ነበር።»
ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።

እኔ መፃጉ ነኝ
ለብዙ ዓመት በአልጋ ላይ የነበርኩ፣
በሥጋ በሽታ በህመም የደከምኩ፣
በአጭር ተቀጭቼ ሳላአብብ የረገፍኩ፣
ፈውሴን የሚናፍቅ ወገን ያልነበረኝ፣
ውሃው ሲነዋወጥ ጠልቆ የሚያወጣኝ፣
ከርታታ ባይተዋር ውዳቂ ነበርኩኝ።
ከለዕታት አንድ ቀን በዚያ ሲያልፍ ጌታዬ፣
ሊፈውሰኝ ወዶ ገብቶ ከጎጆዬ፣
በቃሉ አድኖኝ ቆሜ ሄድኩኝ በዕግሬ፣
አይሁዳዊ እነቴ እንዳይቀር የዘሬ፣
ምስጋና ለማቅረብ ባይታደል ልቤ፣
ተንኮል በኔ ነግሶ ክፋትን ደርቤ፣
ሰንበትን በመሻር የማረኝ ይሄ ነው በማለት፣
ብድሩን ስከፍለው ጥፊን መለስኩለት፣
የወዳጄ ጠላት እኔ መፃጉ ነኝ፣
በሁዳዴ ፆም ውስጥ የምታስታውሱኝ።
@aleroe
እኔ መፃጉ ነኝ
ለብዙ ዓመት በአልጋ ላይ የነበርኩ፣
በሥጋ በሽታ በህመም የደከምኩ፣
በአጭር ተቀጭቼ ሳላአብብ የረገፍኩ፣
ፈውሴን የሚናፍቅ ወገን ያልነበረኝ፣
ውሃው ሲነዋወጥ ጠልቆ የሚያወጣኝ፣
ከርታታ ባይተዋር ውዳቂ ነበርኩኝ።
ከለዕታት አንድ ቀን በዚያ ሲያልፍ ጌታዬ፣
ሊፈውሰኝ ወዶ ገብቶ ከጎጆዬ፣
በቃሉ አድኖኝ ቆሜ ሄድኩኝ በዕግሬ፣
አይሁዳዊ እነቴ እንዳይቀር የዘሬ፣
ምስጋና ለማቅረብ ባይታደል ልቤ፣
ተንኮል በኔ ነግሶ ክፋትን ደርቤ፣
ሰንበትን በመሻር የማረኝ ይሄ ነው በማለት፣
ብድሩን ስከፍለው ጥፊን መለስኩለት፣
የወዳጄ ጠላት እኔ መፃጉ ነኝ፣
በሁዳዴ ፆም ውስጥ የምታስታውሱኝ።
@aleroe
ኤልሮኢ:
መጋቢት 12/07/12
#መዝሙር_ዘደብረ_ዘይት
"እንዘ ይነብር"
#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡
ዲ/ን 1 ተሰሎ 4÷13-ፍ.ም
ን/ዲ 2ጴጥ 3÷7-15
ን/ካ ግብ፡ሐዋ24÷1-22
#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 49÷3
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ
#ትርጒም፦
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል
አምላካችን ዝም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል
#የዕለቱ_ወንጌል፦
ማቴ ፳፬፥፩ -፴፮
ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ
@aleroe
መጋቢት 12/07/12
#መዝሙር_ዘደብረ_ዘይት
"እንዘ ይነብር"
#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡
ዲ/ን 1 ተሰሎ 4÷13-ፍ.ም
ን/ዲ 2ጴጥ 3÷7-15
ን/ካ ግብ፡ሐዋ24÷1-22
#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 49÷3
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ
#ትርጒም፦
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል
አምላካችን ዝም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል
#የዕለቱ_ወንጌል፦
ማቴ ፳፬፥፩ -፴፮
ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ
@aleroe
ኤልሮኢ:
ለጥያቄዬ መልስ ስላጣሁ
ለጥያቄዬ መልስ ስላጣሁ
መጣሁ ከደጅሽ ሱባዔ ገባሁ
ማን አፍሮ ያውቃል በአንቺ ለምኖ
በኪዳንኪ ተማህጸኖ
ለነፍሴ ዕረፍቷ ታዛ መጠጊያ
ካንቺ ተገኝቷል የሞቴ መውጊያ
በሰላምታሽ ድምፅ ተባርኳል ቤቴ
የጌታዬ እናት ለእኔም እናቴ
ማርያም ኵኒ ለሕይወትየ ጸወኖ
እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ
በሥዕልኪ ሥዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ
ቀንን ስናፍቅ በሌሊት ሆኜ
አላተረፍኩም በሰው ታምኜ
ቁልፉ ልጅሽ ነው ለቋጠሮዬ
አሳስሰሽልኝ አልፏል ስቃዬ
ኪዳነምሕረት ኵኒ ለልቡናዬ ብርሃኖ
እስመ ተማህጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ
በሥዕልኪ ሥዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ
ጉልበቴ ዝሎ ቀልዬ ሳለሁ
በኪዳን ጥላሽ ተስፋ አግኝቻለሁ
ደጅሽ መጥቼ ኃይሌ ታደሰ
ያሳዳጆቼ ምክር ፈረሰ
ወላዲተ አምላክ ኵኒ ለእርቃንዬ ክዳኑ
እስመ ተማህጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ
በሥዕልኪ ሥዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ
የዝናቡ ምንጭ ፈጣን ደመና
ከሴቶች ሁሉ ክብርሽ ገናና
አንድያ ልጅሽ ወይን አድርጎኛል
ከትላንት ይልቅ ዛሬ ባርኮኛል
@aleroe
ለጥያቄዬ መልስ ስላጣሁ
ለጥያቄዬ መልስ ስላጣሁ
መጣሁ ከደጅሽ ሱባዔ ገባሁ
ማን አፍሮ ያውቃል በአንቺ ለምኖ
በኪዳንኪ ተማህጸኖ
ለነፍሴ ዕረፍቷ ታዛ መጠጊያ
ካንቺ ተገኝቷል የሞቴ መውጊያ
በሰላምታሽ ድምፅ ተባርኳል ቤቴ
የጌታዬ እናት ለእኔም እናቴ
ማርያም ኵኒ ለሕይወትየ ጸወኖ
እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ
በሥዕልኪ ሥዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ
ቀንን ስናፍቅ በሌሊት ሆኜ
አላተረፍኩም በሰው ታምኜ
ቁልፉ ልጅሽ ነው ለቋጠሮዬ
አሳስሰሽልኝ አልፏል ስቃዬ
ኪዳነምሕረት ኵኒ ለልቡናዬ ብርሃኖ
እስመ ተማህጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ
በሥዕልኪ ሥዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ
ጉልበቴ ዝሎ ቀልዬ ሳለሁ
በኪዳን ጥላሽ ተስፋ አግኝቻለሁ
ደጅሽ መጥቼ ኃይሌ ታደሰ
ያሳዳጆቼ ምክር ፈረሰ
ወላዲተ አምላክ ኵኒ ለእርቃንዬ ክዳኑ
እስመ ተማህጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ
በሥዕልኪ ሥዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ
የዝናቡ ምንጭ ፈጣን ደመና
ከሴቶች ሁሉ ክብርሽ ገናና
አንድያ ልጅሽ ወይን አድርጎኛል
ከትላንት ይልቅ ዛሬ ባርኮኛል
@aleroe
ኤልሮኢ:
መጋቢት 13/07/12
#መዝሙር_ዘደብረ_ዘይት
"እንዘ ይነብር"
በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነብ
መልዕክታት ወንጌልና ምስባክ፡፡
ዲ/ን 1 ተሰሎ 4÷13-ፍ.ም
ን/ዲ 2ጴጥ 3÷7-15
ን/ካ ግብ፡ሐዋ24÷1-22
#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 49÷3
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ
#ትርጒም፦
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል
አምላካችን ዝም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል
#የዕለቱ_ወንጌል፦
ማቴ ፳፬፥፩ -፴፮
ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ
@aleroe
መጋቢት 13/07/12
#መዝሙር_ዘደብረ_ዘይት
"እንዘ ይነብር"
በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነብ
መልዕክታት ወንጌልና ምስባክ፡፡
ዲ/ን 1 ተሰሎ 4÷13-ፍ.ም
ን/ዲ 2ጴጥ 3÷7-15
ን/ካ ግብ፡ሐዋ24÷1-22
#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 49÷3
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ
#ትርጒም፦
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል
አምላካችን ዝም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል
#የዕለቱ_ወንጌል፦
ማቴ ፳፬፥፩ -፴፮
ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ
@aleroe