"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
ልሳነ_ግዕዝ ሞክሼ_ፊደላት
ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት አንድ አይነት ድምጽ ያላቸው ነገር ግን በቅርጽ እና በስራቸው የተለያዩ ፊደላት የሆኑ ናቸው።
በድሮ ጊዜ ግን አባቶቻችን ሀን ከ ሐ ፣ ጸን ከ ፀ... ፊደሎችን በድምጽ አወጣጥ ይለዮአቸው ነበር።
እኝህ ፊደላት በቁጥር ፱(9) ሰሆኑ
ሀ ፣ ሐ ፣ ኀ ፣ ሠ ፣ ሰ ፣ አ ፣ ዐ ፣ ጸ ፣ ፀ ናቸው።
ሀ ➺ ሃሌታው "ሀ" ይባላል።
◦ሃሌ ሉያ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ስለሆነ ሃሌታው "ሀ" ተብሏል።
ሐ ➺ ሐመሩ "ሐ" ይባላል።
◦ሐመር ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው በዚህ ፊደል ስለሆነ ነው።
ኀ ➺ ብዙኀኑ "ኀ" ይባላል
◦ብዙህ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው።
አ ➺ አልፋው "አ" ይባላል።
◦አልፋ ኦሜጋ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው።
ዐ ➺ ዓይኑ "ዐ" ይባላል።
◦ዓይኑ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው።
ሠ ➺ ንጉሡ "ሠ" ይባላል።
◦ንጉሥ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለ ሆነ ነው።
ሰ ➺ እሳቱ "ሰ" ይባላል።
◦እሳት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው።
ጸ ➺ ጸሎቱ "ጸ" ይባላል።
◦ጸሎት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለሆነ ነው።
ፀ ➺ ፀሐዩ "ፀ" ይባላል።
◦ፀሐይ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ነው።
✅ እነዚህ ሞክሼ ፊደላት አንዱ በአንዱ ቦታ መግባት የለበትም ምክንያቱም የትርጉም ለውጥ ያመጣሉ።
ለምሳሌ ፦
➺ ሠረቀ = ወጣ
ሰረቀ = ሰረቀ
➺ አመት = አገልጋይ
ዓመት = ዘመን
➺ ሰዐለ = ስዕል ሳለ
ሰአለ = ለመነ
➺ መሀረ = አስተማረ
መሐረ = ይቅር አለ
➺ ኀለየ = አመሰገነ
ሐለየ = አሰበ
➺ ፈጸመ = ጨረሰ
ፈፀመ = ነጨ
➺ ማኅሌት = ማመስገን
ማሕሌት = ማሰብ
@aleroe

Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
#ፍቅር_ማለት
ያን_ሁሉ መስዋእት ያን ሁሉ ግርፋት
ልጅን_ከአባት ጋር አባትን ከልጅ ጋር
አስታርቆ ለማየት ፤
እኔ ያ ሰው ነኝ የከበረ ዋጋ የተከፈለበት
እኔ ያ. ሰው ነኝ በደሙ_ታጥቤ
ነፃ የሆንኩበት ፤
ታድያ ለዚህ ከንቱ አለም ላልወደደው
በትንሽነቱ ሰው ሁሉ ለናቀው ፤
እንዴትስ ተገብቶት ጌታ ሊሞትለት
እንዴትስ ተደርጎ ክብሩን ሊተውለት ፤
ይህ_ፍጡር ማን ቢሆን ነው ከቶ
የሰማዩን_ንጉስ ግዛቱን አስትቶ
በሀጥያቷ ክርፋት ወደ ገማች ምድር
ጠርቶና ጎትቶ ፤
ሞትን_ያቀመሰው የትኛው ፍቅር ነው
የቱ ቅድስና የቱ ማንነቴ የቱ ንፅህና ፤
ንፁህ_የሆነውን ፅድቅ የለበሰውን
ስጋ ያለበሰው ሀጥያት ያደረገው
የቱ እኔነቴ እሱነቱን ትቶ እንዲያ
ሚያዋርደው ? ፤
ያንን_ፍቅርማ ቃላት ተቆፍረው
ያንን_መውደድማ ፊደላት ተጣምረው ፤
ከቶ አይገልፁትም ፍፁም አይደርሱትም
ብርሀን አያደምቀው ጨለማ አይጋርደው
የቀናት መገስገስ የአመታት መንጎድ
ዘመን የማይሽረው ፤
ፍ ቅ ር ማለት ያ ያ ነው
ፍቅር_ውልደቱ ነው ፍቅር መከራው ነው
ፍቅር_መሞቱ_ነው ፍቅር ትንሳኤው ነው ፤
በዘመን ጅማሬ በዘመን ፍፃሜም
የፍቅር ስንኙ የፍቅር ሀረጉ
ኢ የ ሱ ስ ብቻ ነው !
__________________
@aleroe
#ፍቅር_ማለት
ያን_ሁሉ መስዋእት ያን ሁሉ ግርፋት
ልጅን_ከአባት ጋር አባትን ከልጅ ጋር
አስታርቆ ለማየት ፤
እኔ ያ ሰው ነኝ የከበረ ዋጋ የተከፈለበት
እኔ ያ. ሰው ነኝ በደሙ_ታጥቤ
ነፃ የሆንኩበት ፤
ታድያ ለዚህ ከንቱ አለም ላልወደደው
በትንሽነቱ ሰው ሁሉ ለናቀው ፤
እንዴትስ ተገብቶት ጌታ ሊሞትለት
እንዴትስ ተደርጎ ክብሩን ሊተውለት ፤
ይህ_ፍጡር ማን ቢሆን ነው ከቶ
የሰማዩን_ንጉስ ግዛቱን አስትቶ
በሀጥያቷ ክርፋት ወደ ገማች ምድር
ጠርቶና ጎትቶ ፤
ሞትን_ያቀመሰው የትኛው ፍቅር ነው
የቱ ቅድስና የቱ ማንነቴ የቱ ንፅህና ፤
ንፁህ_የሆነውን ፅድቅ የለበሰውን
ስጋ ያለበሰው ሀጥያት ያደረገው
የቱ እኔነቴ እሱነቱን ትቶ እንዲያ
ሚያዋርደው ? ፤
ያንን_ፍቅርማ ቃላት ተቆፍረው
ያንን_መውደድማ ፊደላት ተጣምረው ፤
ከቶ አይገልፁትም ፍፁም አይደርሱትም
ብርሀን አያደምቀው ጨለማ አይጋርደው
የቀናት መገስገስ የአመታት መንጎድ
ዘመን የማይሽረው ፤
ፍ ቅ ር ማለት ያ ያ ነው
ፍቅር_ውልደቱ ነው ፍቅር መከራው ነው
ፍቅር_መሞቱ_ነው ፍቅር ትንሳኤው ነው ፤
በዘመን ጅማሬ በዘመን ፍፃሜም
የፍቅር ስንኙ የፍቅር ሀረጉ
ኢ የ ሱ ስ ብቻ ነው !
__________________
@aleroe
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
# ትሕትና + ትእግስት + ተስፋ + ፅናት + ፍቅር + እምነት + አምልኮት + ምግባር=>ስኬት!!
~አንዲት ስጋ የምትጠብስ ሴት ስጋውን መጥበሻው ላይ ትጥደውና ስጋውን ታገላብጠዋለች ።ከዛ መብሰል አለመብሰሉን ለማረጋገጥ በሹካ ወጋ ወጋ አድርጋ ታየዋለች። ከበሰለ ታወርድና ለመዓድ ገበታ ላይ ታቀርበዋለች።ልብ በሉ....
~ፈጣሪም እኛን ይለዉጥናል እውቀት ይሰጡናል ያበስሉናል ብሎ ባሰባቸው በተለያዩ ነገሮች ላይ ይጥደንና ጤና ማጣት፣ስራ ማጣት፣ወዳጅ ማጣት፣ የህይወት አጋር ማጣት፣ገንዘብ ማጣት፣ፍትሕ ማጣት፣ተስፋ ማጣት፣ነገሮችን አለመሳካት፣ሰርቶ መና፣መከዳት፣መናቅ፣ወ ... በተባሉ ሹካዎች ወጋ ወጋ አድርጎ መብሰል አለመብሰላችንን ያረጋግጣል።
~ችግር ውስጥ ሆነን ካመሰገንን በስለናል ካማረርን ግን ይቀረናልና፤አንዳንዴ በተለያዩ ችግር ውስጥ ጥዶ ያገላብጠናል።
~አንድ ካሜራ ማን እኛን ፎቶ ከማንሳቱ በፊት ፈገግ በል ቀና በል ትንሽ ወደ ቀኝ ምናምን እያለ አስቀድሞ ያስተካክለናል ከዛ ያነሳናል። ፈጣሪም እኛን በተለያዩ ችግሮች ውስጥ እያስገባ ነው ህይወታችንን ሚያስተካክለው ምክንያትም የደፈረሰ ህይወታችን መጥራት ስላለበትና ጥርት ለማድረግ።
~መከራ ፈጣሪ እኛን ወደሱ የሚጎትትበት ገመድ ነው። ዳይመንድን ውድ ካደረጉት ነገሮች መካከል አንዱ አቆራረጡ ነው።ዳይመንድን የምናውቀውን ቅርፁን ያስያዘውና ከተለያየ አቅጣጫ እንዲያንፀባርቅ ያደረገው አቆራረጡ ነው ይላሉ። እኛንም ዛሬ እየቆረጡንና እያስጨነቁን ያሉ ሳንቋቋማቸው ቀርተን እያማረርንባቸው ያለን ችግሮቻችንን ነገ እኛን ዉድና የሚያበራ ማንነት ባለቤት የሚያደርጉን ናቸው ።
~ማዕበል ሲነሳና ባህሩን ሲያማስለው ሁሉም እንስሶች ይሸሻሉ።ንስር አሞራው ግን በመሀሉ ገብቶ ዓሳ ይዞ ይወጣል።
~ ወዳጄ ሆይ እንደ ንስር አሞራው በችግር ውስጥ ብትሆንም እራስህን አንፅ። ሸክላ የምትሰራ ሴት እንኳን ሸክላዋን ሰርታ ስትጨርስ እንዲጠነክርላት በእሳት ነው ምትጠብሰው።ዛሬ የሚጠብሱህ ችግሮችና የህይወት መሰናክሎች ከፀናህ ማንነትህን ነው የሚያጠነክሩልህ።
~ ስለዚህ ስለሆነው ስለሚሆነው እየሆነ ስላለው ፣ ስለተደረግልህ ስላልተደረገልህ ፣ ስለ ሰጠህ ስለ ነፈገህ ነገር ሁሉ እሱን አመስግነው።
~ # እንዲ_በለው ፦
"ደስታንም ሆነ መከራን ብትሰጠኝ አመሰግንሀለሁ፤ ከኔ ይልቅ አንተ ነህና ለእኔ ምትቀርበው።ስለዚህም ጌታ ሆይ በመንገዴና በህይወቴ ሁሉ ፈቃድህ እንጂ ፈቃዴ አይሁን።"
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

#ነበርኩ_መች_ያድናል
ሀጢያትን ስትሰራ አምላክን እረስተህ
ቅዱሱን ሰውነት በሀጢያት አርክሰህ
ትእዛዝን ሳትፈጽም መልካምን ሳትሰራ
ዘይት ሳታዘጋጅ መብራትህ ሳይበራ
በተጠራህ ጊዜ መላከሞት ሲመጣ
ለማያልፈው አለም ሲወጣልህ እጣ
ለሚዛን ስትቀርብ አገልጋይ ነበርኩኝ እያልክ መናገሩ
መዝሙር ዘምሬያለው ሄጃለው ከበሩ
ብሎ መከራከር ያኔ መች ይጠቅማል
ይዞ መገኘት ነው ነበርኩ መች ያድናል!!!!
____________________
@aleroe
#ነበርኩ_መች_ያድናል
ሀጢያትን ስትሰራ አምላክን እረስተህ
ቅዱሱን ሰውነት በሀጢያት አርክሰህ
ትእዛዝን ሳትፈጽም መልካምን ሳትሰራ
ዘይት ሳታዘጋጅ መብራትህ ሳይበራ
በተጠራህ ጊዜ መላከሞት ሲመጣ
ለማያልፈው አለም ሲወጣልህ እጣ
ለሚዛን ስትቀርብ አገልጋይ ነበርኩኝ እያልክ መናገሩ
መዝሙር ዘምሬያለው ሄጃለው ከበሩ
ብሎ መከራከር ያኔ መች ይጠቅማል
ይዞ መገኘት ነው ነበርኩ መች ያድናል!!!!
____________________
@aleroe
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
ኤልሮኢ:
✉ ለራስህ ነው ✉
አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ! ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡
ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡ ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡ እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡
✝ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ

ጥር 24/05/2012
✝ የቅዳሴ ምንባባት
፪ ቆሮ ም ፩ ቁ ፲፫-ፍ.ም
፩ ዮሐ ም ፪ ቁ ፳፪-ፍ.ም
ግብ.ሐዋ ም ፲፫ ቁ ፳-፳፰
✝ ምስባክ
እግዚአብሔር እግዚእ አስተርእየ ለነ
ግበሩ በዐለበት ትፍሥሕት በኀበ እለ ያስተሐምምዎ
እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ
🙏 ትርጉም
እግዚአብሔር አምላክ ነው ለእኛም በራልን
እሰከ መሠዊያው ቀንዶች ደረሱ
በዓሉ መሥዋዕት በገመድ እስሩት
መዝ ፻፲፮-፳፮
✝ ወንጌል
ሉቃ 2÷42 ፍ.ም
✝ ቅዳሴ
ዘሐዋርያት አው ዘዲዮስቆሮስ
@aleroe
✝ የቅዳሴ ምንባባት
፪ ቆሮ ም ፩ ቁ ፲፫-ፍ.ም
፩ ዮሐ ም ፪ ቁ ፳፪-ፍ.ም
ግብ.ሐዋ ም ፲፫ ቁ ፳-፳፰
✝ ምስባክ
እግዚአብሔር እግዚእ አስተርእየ ለነ
ግበሩ በዐለበት ትፍሥሕት በኀበ እለ ያስተሐምምዎ
እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ
🙏 ትርጉም
እግዚአብሔር አምላክ ነው ለእኛም በራልን
እሰከ መሠዊያው ቀንዶች ደረሱ
በዓሉ መሥዋዕት በገመድ እስሩት
መዝ ፻፲፮-፳፮
✝ ወንጌል
ሉቃ 2÷42 ፍ.ም
✝ ቅዳሴ
ዘሐዋርያት አው ዘዲዮስቆሮስ
@aleroe
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
ሩጫ ✞............🏃🏃🏃🏃
ማልያህን ታጠቅ
ቀበቶህን አጥብቅ
ጫማህን አጠባብቅ
መስመርህን ጠብቅ
አትይ ወደ ኋላ
ተብሎ ተነግሮን
ጀምረን ሩጫ
ለመቀበል ዋንጫ
እኛ ዞርን ስናይ
እነሱ ፈጠኑ
ከሽልማት ጌታ ጽዋም ተቀበሉ።
@aleroe
ሩጫ ✞............🏃🏃🏃🏃
ማልያህን ታጠቅ
ቀበቶህን አጥብቅ
ጫማህን አጠባብቅ
መስመርህን ጠብቅ
አትይ ወደ ኋላ
ተብሎ ተነግሮን
ጀምረን ሩጫ
ለመቀበል ዋንጫ
እኛ ዞርን ስናይ
እነሱ ፈጠኑ
ከሽልማት ጌታ ጽዋም ተቀበሉ።
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
#ወይ_ማወቅ_ደጉ !
በባህር_በጥልቁ በሰማይ ተማክሮ
ሊወጋው_ምስኪኑን ሃይል አስተባብሮ
ሄደ ከምስኪኑ ሰፈር
ሊያጠፋው መታሰቢያው ሳይቀር
ዉጣ ይለይልህ ኪዳን አለኝ ማለት
ፀሎቱ መዝሙሩ አይደለም ከማጀት
ይህን ሁሉ ፉከራ የሰማው ምስኪን ሰው
ወዬው ጠፋሁ ብሎ ፍርሃት ብርክ ያዘው
የሞት ሞቱን ጨክኖ ብቅ ቢልባቸው
የያዙት_መሳሪያ ወደቀ ከጃቸው
እግሬ_አውጭኝ እግሬ አውጭኝ
እያሉ በሽቅድምድም
ሄዱ ከመጡበት አለም
ይህ ሁሉ የሆነው..ምክንያቱ ምንድነው?
ጋሻ ጦር አልያዝኩኝ....ይሄው ባዶየን ነኝ
ምን አይተው ሮጡ......ሊገሉኝ የመጡ
እያለ ምስኪኑ ግራ እየተጋባ
ግድግዳው ላይ ካለው መስታወት ተጠጋ
ድንገት ቀና ብሎ ፊቱን ቢመለከት
ለካስ_የኢየሱስ ደም በግንባሩ አለበት
አሃ ! ደሙን አይተው ነው የተመለሱት
ወይ ማወቅ ደጉ!
#ለካስ_መፍትሄው ግንባርን ማሳየት
#ያኔ_ይመለሳል ሰይጣን ከመጣበት ።
@aleroe
#ወይ_ማወቅ_ደጉ !
በባህር_በጥልቁ በሰማይ ተማክሮ
ሊወጋው_ምስኪኑን ሃይል አስተባብሮ
ሄደ ከምስኪኑ ሰፈር
ሊያጠፋው መታሰቢያው ሳይቀር
ዉጣ ይለይልህ ኪዳን አለኝ ማለት
ፀሎቱ መዝሙሩ አይደለም ከማጀት
ይህን ሁሉ ፉከራ የሰማው ምስኪን ሰው
ወዬው ጠፋሁ ብሎ ፍርሃት ብርክ ያዘው
የሞት ሞቱን ጨክኖ ብቅ ቢልባቸው
የያዙት_መሳሪያ ወደቀ ከጃቸው
እግሬ_አውጭኝ እግሬ አውጭኝ
እያሉ በሽቅድምድም
ሄዱ ከመጡበት አለም
ይህ ሁሉ የሆነው..ምክንያቱ ምንድነው?
ጋሻ ጦር አልያዝኩኝ....ይሄው ባዶየን ነኝ
ምን አይተው ሮጡ......ሊገሉኝ የመጡ
እያለ ምስኪኑ ግራ እየተጋባ
ግድግዳው ላይ ካለው መስታወት ተጠጋ
ድንገት ቀና ብሎ ፊቱን ቢመለከት
ለካስ_የኢየሱስ ደም በግንባሩ አለበት
አሃ ! ደሙን አይተው ነው የተመለሱት
ወይ ማወቅ ደጉ!
#ለካስ_መፍትሄው ግንባርን ማሳየት
#ያኔ_ይመለሳል ሰይጣን ከመጣበት ።
@aleroe
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
ኤልሮኢ:(መዝሙር)
#የሚጠብቀኝ አይተኛም
የሚጠብቀኝ አይተኛም(×2) አያንቀላፋም(×2)
ቤት ባይኖረኝም
በደጅ ባድር
ቀንና ሌሊት ከኔ አይርቅም
ድምፀ አራዊት የሌሊት ግርማ
ወደ እኔ አይገቡም ድምፅህ ሲሰማ
መሰናከልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሀይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም
ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በፅድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ
የሰማዩን ጥል እታገሳለሁ
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለሁ
ሌሊት በድብቅ ለሚጎበኙ
ለፃድቃኑ ግን አምላክ ይስጥልኝ
እንቅልፌን ባርኮ የሰጠኝ ጌታ
በዓለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የዕለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍፁም
ምስጋና ላቅርብ እስከዘላለም
#ዘማሪ ይልማ
@aleroe
#የሚጠብቀኝ አይተኛም
የሚጠብቀኝ አይተኛም(×2) አያንቀላፋም(×2)
ቤት ባይኖረኝም
በደጅ ባድር
ቀንና ሌሊት ከኔ አይርቅም
ድምፀ አራዊት የሌሊት ግርማ
ወደ እኔ አይገቡም ድምፅህ ሲሰማ
መሰናከልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሀይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም
ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በፅድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ
የሰማዩን ጥል እታገሳለሁ
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለሁ
ሌሊት በድብቅ ለሚጎበኙ
ለፃድቃኑ ግን አምላክ ይስጥልኝ
እንቅልፌን ባርኮ የሰጠኝ ጌታ
በዓለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የዕለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍፁም
ምስጋና ላቅርብ እስከዘላለም
#ዘማሪ ይልማ
@aleroe
ኤልሮኢ:
ዘፈን' #ለምን_ተከለከለ?
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ለምን ዘፈንን አወገዘች???
#1. ዘፈን የአጋንንት ሥራ ነው:: አጋንንት ይዘፍናሉና:: ለዚህ ምንም ማስተባበያ አያስፈልገውም:: መጽሐፍ ቅዱስ "በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ" በማለት ስለ አጋንንት ዘፋኝነት ይናገራል::(ኢሳ.13:21) አትዝፈኑ ማለት የአጋንንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን እንረዳ:: ይህን በተመለከተ መጽሐፈ መቃብያን ደግሞ እንዲህ ይላል:- "....እየዘፈኑም ከአጋንንት ጋር ይጫወቱ ነበር:: አጋንንትም ጫወታቸውንና ዘፈናቸውንም ሁሉ ያደንቁላቸው ነበር::" (1ኛ.መቃ.36፥27-28) በዚህ ስፍራ አገላለጥ ደግሞ ለየት የሚለው አጋንንት ዘፋኞች ብቻ ሳይሆኑ ከዘፈን አድናቂዎች ጐራ መሰለፋቸው ነው::
#2. ፍትሐ ነገሥት መንፈሳዊ ሥራን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል:- "ስለ ተግባረ ዕድ ግን በዓለም ከሚሠሩ ሥራዎች መንፈሳዊ ሕግን ከሚቃወም ሥራ በቀር ሁሉንም ሊሠሩ ይገባል:: ... እንደ ዘፋኝነት፥ እንደ መጥፎ ጫወታ፥
በእግር እንደ ማሸብሸብ(ዳንስና ጭፈራ) ካልሆነ በቀር ነው::" (ፍት.ነገ.መን.አን. 23:820) ይህ የአበው ቃል ዘፋኝነት በመንፈሳዊ እይታ እንደ ሥራ መቆጠር እንደሌለበት ያስረዳል::
#3. ዘፋኝነት "የሥጋ ሥራ" በመሆኑ ኃጢአት ነው::
(ገላ.5:21):: "በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ፤" ተብሏልና:: (ገላ.5:16)::
#4. ዘፈን በመንፈሳውያን መጻሕፍት ተወግዟል:: ሐዋርያት በዲድስቅልያ "ኢትኩኑ ዘፈንያነ" ፥ "ዘፋኞች አትሁኑ" ብለዋል:: (ዲድስቅልያ፤ አንቀጽ 7) ቅዱስ ጳውሎስ "በቀን እንደምንሆን በአግባብ እንመላለስ:: በዘፈንና በስካር አይሁን" ብሏል:: (ሮሜ.13፥13) ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ "በስካርና በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል::" ይለናል:: (1ኛ.ጴጥ.4:3):: መጽሐፈ ሐዊ ደግሞ "ከሰይጣን የተገኘ ነውና ዘፈንንና ዳንስን ከኛ ማራቅ ይገባናል::" ይለናል:: (መጽ.ሐዊ አን. 50):: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ደግሞ ከማዘዝ አልፎ ዘፈንን እንተው ዘንድ "ዘፈንን ትተዉ ዘንድ እማልዳችሗለሁ፤" በማለት ይማጸናል:: (ተግ.ዘዮሐ.አፈ.28) ዘፈንን አንተውም
ላሉ ደግሞ መጽሐፈ ሐዊ "በዘፈን ጸንተው የሚኖሩ ይፈረድባቸዋል" በማለት ሲያስጠነቅቅ እናገኛለን:: (መጽ.ሐዊ.አን. 12)

እኅቴን ላኩልኝ
#በዲ/ን ሕሊና በለጠ
√
ምነው ጨላለመች - የሀገሬ ፀሐይ
የሴት ልጅ ደም ፈሶ - ሥርየት አለ ወይ?
√
ዓርቡ የረዘመ - እሑዱ የራቀው
ምን የሚሉት ጾም ነው - ባ'ገሬ የገባው?
√
ምን ክፋት ቢኖርህ - ምንም ያ'ል ብታቄም
ምን ጀብደኛ ብትኾን - ብታደራጅ አቅም
ሴት አሥሮ 'ሚሟገት - ጀግናስ እኔ አላውቅም።
√
መጥቀው እንዲያመጥቁን - ብንሰድ እንዲማሩ
በዕውቀት ተራቀው - ተሠወሩ አሉ።
√
"ከማጀት ላውላት" - ብዬ ነበር ያኔ
"ግድ የሎትም ትማር" - ብለው ወትውተውኝ - ነጥለው ከጎኔ
ትም' ርቱ አልበቃ ቢል - ለጦር ላኳት አሉ - ወዮ ኧረ ወይኔ!
√
እኅትነት ቅኔ - መውደዷም ነው ዕንቁ
ደግሞ ሠወር ስትል - እንኳንስ ሕይወቷ - ድምጿም መናፈቁ።
√
ያገሬ መጋኛ - ጥፊው አያጠፋም
ያገሬ ሰላቢ - ምትሐቱ ዕቃን እንጂ - ሰውን አይሠውርም።
አፍኖ የዋጠሽ - ሲያኝክ ማያሰማ
የየት አገሩ ይኾን - የበላሽ እቴዋ!?
√
ምግቡም ጣዕም የለው - አልበላ አለኝ
አጣፍጣ ታጉርሰኝ - እኅቴን ላኩልኝ።

የቫላንታይን ቀን በዓል - ድብቅ እውነታ
======================
(ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ)
ስንቶቻችን ይሆን የቫለንታይን ቀን(የፍቅረኞች ቀን ብለን የምናከብረው) የሚከበርበት ምክንያትና መነሻው የምናውቀው? ወይስ ሰው ስለ አከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው? ክርስቶስ ከመወለዱ ከብዙ ክፍለ ዘመናት በፊት አረማዊ ሮማውያንየካቲት 14 ማታና የካቲት 15 "የተኩላ አዳኙ"ለሚሉት ሉፐርኩስ(Lupercus) ክብር በማለት በጣኦት አምልኮ ያከብሩት ነበር።ሮማውያን ይህ በዓል ሉፐርካልያ
(Lupercalia) ይሉታል።ንጉሥ ቆንጠንጢኖስ ክርስትና የሮማውያን ይፋዊ ሃይማኖት መሆኑ በማወጁ ማነኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር ቢያስጠነቅቅም የተወስኑ ሮማውያን
ሰዎች ግን በዓሉን ማክበር አልተዉም።ይህንን አረማዊ በዓል
ማለትም ሉፐርካልያ የሮማው ጳጳስ ገላስዮስ ክርስትያናዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር አደረጉ።ጳጳስ ገላስዮስ ለካቲት 15 ሲከበር የነበረው በዓል የቅዱስ ቫለንታይን ቀን በሚል አዲስ ስያሜ የካቲት 14 እንዲከበር አደረጉ።
እንዴት ይህ አረማዊ በዓል የቅዱስ ቫለንታይን ቀን የሚል ስያሜ ተሰጠው?
ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው።ቫላንታይን ጥንታዊው ታዋቂው ሉፐርኩስ ነው።ሉፐርኩስ በግሪካውያን ፓን(pan) ተብሎ ይጠራል።በጥንታውያን አይሁድ
ደግሞ ይህ ፓን ባል(Baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል።ባል በመጽሓፍ ቅዱስ ዘፍጥረት 10-9 ላይ ታላቁ አዳኝ ተብሎ
ለተገለጸው ኒምሮድ ሌላኛው መጠርያው ነው።ኒምሮድ የሮማውያን የተኩላ አዳኙ ሉፐርኩስ ነበር።በዚህ መሠረትም
የቅዱስ ቫለንታይን ቀን የአረማውያን ለኒምሮድ ክብር የሚያከብሩት የጣኦት አምልኮ ነው። ቫለንታይን የሚል ቃል ቫለንቲኑስ(valentinus) ቫለንስ ከሚል
የላቲን ቃል የመጣ ነው።ቀጥተኛ ትርጉሙ ጠንካራ፣ሃይለኛ
ታላቅ ማለት ነው።ዘፍጥረት10-9 ላይ እንደምናነበው " እርሱም
በእግዚአብሔር ፊት አዳኝ ነበረ ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር
ፊት ሃያል አዳኝ እንደ ኒምሮድ ተባለ።" ኒምሮድ የሮማውያን
ጀግና ሃይለኛ ሰው ቫለንታይን ነበር።
ሌላኛው የኒምሮድ ስም ሳንክቱስ(Sancutus) ወይ ሳንታ
(santa) ነው ሳይንት(saint) የሚል የእግሊዝኛ ትርጉምአለው
ማለትም ቅዱስ።የሮማውያን ሉፐርካልያ በመጨረሻ ቅዱስ
ቫለንታይን የሚል ስያሜያዘ ማለት ነው።
ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን በቀዱት አረማዊ የልብ
(heart) ምልክት ይጠቀማሉ።በባቢሎናውያን ባል(bal) ልብ የሚል ፍቺ ነው ያለው።በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት
ለቫለንታይን ቀን(የፍቅረኛሞች ቀንየምንለው) መገለጫ እንጠቀምበታለን።ባል የባቢሎናውያን የጣኦት ጌታ ነበር።በሌላ መንገድም ኒምሮድ ወይም ቅዱስ ቫለንታይን ሳተርን ተብሎ ይጠራል።ሳተርን የሮማ-ባቢሎን ከአባራሮዎቹ ለመሸሽ በምስጥራዊ ቦታ የሚደበቅ ጣኦት ነው።ሳተርን የሚል የላቲን ቃል ሴመቲክ(አይሁድ) ቋንቋ ከሚናገሩ ባቢሎናውያን የተገኝ ነው።መደበቅ፣ራስን መደበቅ የሚል ፍቺ አለው። በጥንታዊ እምነትም ኒምሮድ(ሳተርን) ከአባራሮዎቹ በመሸሽ ወደ ጣልያን እንደተጓዘይነገራል።የአፐኒን ተራራ ስያሜው ወደ ኔምብሮድ ወይም ኒምሮድ ተቀየረ።ይህ ተራራ ኒምሮድ በጣልያን የተሸሸገበት ቦታ ነበር።ሮማም በዚ ተራራ ላይ እንደ ተመሰረተች ይታወቃል።ሮም ፈርሳ እንደገና ከመሰራትዋ 753ዓ/ዓ በፊት ሳቹርንያ (ሳተርን፡ኒምሮድ የተደበቀባት ቦታ) የሚል ስያሜ ነበራት።ኒምሮድ በዚህ ቦታ ተይዞበፈጸመው ወንጀል ተገደለ።በንጉሥ ቆስጠንጦኖስ ጊዜም ክርስትያናዊ ሰማዕት የሚል የውሸት ክብር ተሰጥቶት በሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን
መዘከር ጀመረ።ኒምሮድ፣ባል፣ቫለንታይን፣ታላቁ አዳኝ፣ፋውኑስና ሉፐርክስ 31ኛ፣32ኛና 33ኛና ደረጃ (ዲግሪ) ላይ ያሉ ፍሪማሶኖሪዎች ከሚያመልኩትባፎሜት(የሜንደዝ ፍየል) ጋር የሚስተካከል ነው። እንግዲህ በሰላቢ እጆች (ኢሊሙናቲ) ሴራ ዘመናዊነት ተላብሶ ድብቅ ጣኦት የሚመለክበት የቅዱስ ቫለንታይን ቀን እኛ ደግሞ የፍቅረኛሞች ቀን በማለት እያከበርን ማለትም እያመለክን ነው።አንድ በአል የሚከበርበትን ምክንያትና አስፈላጊነት ሊኖረው ግድ ነው።ሆኖም የምናከብረውን በአል የምናከብርበትን ምክንያትና አስፈላጊነት ሳናውቅ ከሴሮኞች ድብቅ አላማ ማስፈጸምያ ከመሆን መቆጠብ ይበጃል።

#እንኳን ለዐብይ ፆም በሰላም አደረሰን
☞ፆም ማለት ምን ማለት ነው?
☞የአብይ ስያሜዎች ስንት ናቸው?
☞የአብይ ፆም ለምን ታላቁ ጾም ተበለ?
☞የአብይ ጾም ስንት ክፍሎች አሉት?
☞የአብይ ጾም ለስንት ሳምንት ይፆማል
☞ስለ ዘወረደ ምን ያውቃሉ?
1ኛ. ፆም ማለት ምን ማለት ነው?
ፆመ ፦ ተወ " ታቀበ"ታረመ ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው።
ፍቹም ምግብን መተው ' መከልከል' መጠበቅ ማለት ነው።
ፆም ማለት ሰውነት ከሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል መወሰን ማለት
ነው። ወይም ለሰውነት የሚያምረውን የሚያስጎመጀውን ነገር መተው ማለት
ነው ።
ፆም ከሃይማኖት ጋር ዝምድና ስላለው ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ፆም አለ።
ፆም በብሉይ እና ኪዳን ከፍተኛ ቦታ አለው ።
ነብያት ከእግዚአብሄር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውሃ በአፋቸው አይገባም
ነበር።//ዘፀ ፴፬÷፳፰//34*28//
በሐፂያት ብዛት የታዘዘውን የእግዚአብሔርን መዓት የሚመልሰው ሕዝቡ በፆም
ሲለምኑት ሲማልዱት ነበር። //ዮሐ ፪÷፯_፲// 2*7-20//
በሐዲስ ኪዳንም ፆም ሰው ሰራሽ ህግ ሳይሆን እራሱ መድኃኒታችን በመዋዕለ
ስጋዌው የስራ መጀመሪያ አድርጎ የሰራው ህግ ነው።//፬÷፪// 4*2//
ይህ ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ እርኩስ ሰይጣን እንኳን
በፆም እሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል።// ማቴ ፲፯÷፳፩//
17*21/ሐ
ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የታዘዙ ሐዋሪያትም ከመንፈስ ቅዱስ በየጊዜው
ትዕዛዝ እሚቀበሉበት በፆም እና በፆለት ላይ እንዳሉ ነበር።// የሐዋ
፲፫÷፪//13*2//
ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናት ቀሳውስት የሚሾሙት በፆምና
በፆለት ነበር።//የሐዋ፲፫÷፫//13*3//
ፆምስ በታወቀው እለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ መከልከል ነው።
ፆም ማለት፦ጥለላት ማባልዕትን ፈፅሞ መተው ሰውነትን ከመብልና ከመጠጥ
ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ መጠበቅ ፣መገዛት፣ መቆጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ
በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ይቅር በለኝ በማለት ቅድመ
እግዚአብሔር በመንበርከክ ምህረት በአምላክ ለመቀበል መዘጋጀት ነው።
ፆም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፣ሀይለ ፍትወትን የምታደክም የበጎ ምግባር
ሁሉ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ፀጋን የምትሰጥ ፣የወንጌል ስራ መጀመሪያ፣
የፅሙዳን ክብራቸው፣ የደናግል እና የንፅህና ጌጣቸው
፣የንፅህና መገለጫ፣ የጸሎት ምክንያት እናት፣ የእንባ መገናኛ መፍለቂያ፣
አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ስራ ሁሉ የምትነቃቃ፣ ሰውነትን
በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትህትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ
መድኃኒት ነፍስ ናት።
ከህገ ልቦና ከነበሩ አበው አንስቶ በዘመነ ኦሪት እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ
በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ ቀደምት አበው ነቢያት፣ ነገስታት፣ካህናት በፆምና
በጸሎት ፅሙድ ሁነው እግዚአብሔር አምላካቸው ከክፉ ነገር እንዲሰውራቸው
በይቅርታ እንዲጎበኛቸው ሀይልንም እንዲያጎናፅፋቸው ተማፅነው ሀሳባቸውን
ፈፅሞላቸዋል።
በሀድስ ኪዳን ፆም ስለ ፅድቅ ተብሎ መከናወን ያለበት አብይ ተግባር ነው። //
ማቴ፭÷፮// 5*6//
ስጋዊ ጥቅምን ለማግኘት ተድላ ስጋን በመሻት ሳይሆን ዘላለማዊ መንግስት
ለመውረስ ስለ ፅድቅ ተብሎ የሚፈፀም ነው።
ፆም እንደምን ነው ቢሉ የስጋ ምግባር ነው።
ምፅዋት የገንዘብ ግብር እንደሆነች:አንድም ምፅዋት ስጋን መገበር ነው።
ምፅዋት ገንዘብ መገበር እንደሆነች። ~~~ስለዚህ የሚፆም ሰው በፈቃደ
ስጋው ላይ ድልን ይቀዳጃል።
በእምነት ሁኖ የለመነውን እግዚአብሔር ይሰጠዋል። ሰማያዊ የሆነውን
ምስጢር ለማየት ከአለማዊ ነገሮች ተለይቶ ይነጠቃል።
በአለም እየኖረ ከአለሙ ይለያል። ከአለም አይደለምና//
ዮሐ፲፭÷፲፱//15*19 //
2ኛ.
ዐቢይ ጾምም ቤተክርስቲያናችን እንድንጾም ካወጀችልን ጾም አንዱ ነው፡፡
ዐቢይ ጾምየተለያዩ ስሞች አሉት፡፡ አንደኛ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም በመሆኑ እንዲሁም ዐቢይ
እግዚአብሔር ወዓቢይ ኀይሉ ዓቢይ እግዚአብሔር ወብዙኃ አኰቴቱ የተባለ
ጌታ የጾመው ስለሆነ፣ /መዝ.47፥1፣ መዝ.146፥5/፡፡ ሁለተኛ ሁዳዴ ጾም
ይባላል፡፡ ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት
ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲሆን ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ
አምላካችን ስለጾመው ነው፡፡፣ /አሞ.7፥1/፡፡ ሦስተኛ በዓተ ጾም ይባላል፡፡
የጾም መግቢያ፣ መባቻ ወይም ጾሙ የሚሰፍርበት በዓት ማለት ነው፡፡ አራተኛ
ጾመ አርባ ይባላል፡፡ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው 40 /ዓርባ/ ቀን
ስለሆነ፣ /ማቴ.4፥1/ አምስተኛ ጾመ ኢየሱስይባላል፡፡ ጾሞ፣ ጹሙ ብሎ
ስላዘዘን፣ ስድስተኛ ጾመ ሙሴ ይባላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ሰኞ ዕዝል
ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም፣ ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት እያለ በጾመ
ድጓ ስለ ዘመረ ነው፡፡
ዐቢይ ጾምጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ማቴ.4፥1
ምእመናን ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል፡፡ ዐቢይ ጾም
ስምንት ሳምንታት /55 ቀኖች/ አሉት፡፡ ሰባት ቅዳሜ ስምንት እሑድ ይገኛሉ፡፡
አሥራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጦሙ
የጦሙ ወራት አርባ ቀን ብቻ ይሆናል፡፡
3ኛ.
የአቢይ ጾም ሦስቱ ክፍሎች
1. ዘወረደ (ጾመ ሕርቃል)፤ ይህም ጾሙ ከሚገባበት
ሰኞ ጀምሮ እስከ እሑድ ያረስ ያለው 7 ቀን ነው።
2. የጌታ ጾም፤ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና
ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው 40 ቀን ነው።
3. ሕማማት፤ ይህም ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ
ከተቀመጠበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር
ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት
ነው።
ይህም 7+40+8 = 55 ቀን ማለት ነው።
4ኛ.
የአብይ ጾም ሳምንታት 8 ናቸው፤
ዘወረደ
ቅድስት
ምኩራብ
መጻጉዕ
ደብረዘይት
ገብርሔር
ኒቆዲሞስ
ሆሣዕ
ሰለ ተትርጉማቸው ከታች ከተለጠፈው ሰንጠረዥ ተመልከት
5ኛ. ለምን አብይ / ታላቅ
ተባለ
አብይ ፆም መባሉ ትልቅና ታላቅ ፆም መሆኑን
ለማሳወቅ ነው። ይህ ፆም ታላቅ
መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መፆሙና
ከሌሎቹ አፅዋማት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር
መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ
ቆሮንቶስ መፆም ሳይገባው ለእኛ አርአያና
ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የፆመው ፆምም
በመሆኑ ነው
6ኛኛ.
የመጀመሪያ የአቢይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም
ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ስያሜውም፤ በ 614 ዓ . ም ኪርዮስ የተባለ
የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60 ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ 14 ዓመት በኋላ በ 628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡

የካቲት 15/06/2012
✝ምስባክ
+ ዘነግህ
1 📖መዝ. 101/102፥21
----------------
ከመ ይንግሩ በጽዮን ስመ እግዚአብሔር ወስብሐቲሁኒ በኢየሩሳሌም ሶበ ተጋብኡ አሕዛብ ኅቡረ
+ ዘቅዳሴ
2 📖መዝ. 146/147፥፡1
----------------
ተሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን እስመ አጽንዐ መናሥግተ ኆኃትኪ
✝ትርጉም
1:- የእግዚአብሔርን ስም በጽዮን ምስጋናውንም በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ
2:- እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ መዝሙር መልካም ነውና። ለአምላካችን ምስጋና ያማረ ነው ፤ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይሠራል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል

#እያለፈ_ነው_ዘመኔ
እያለፈ ነው ዘመኔ ትእዛዙን ሳልፈጽም
ወየው ለእኔ/2/
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ
ና ብሎ ወደእኔ/2/
በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ
ብዙ አዝመራ/2/
ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ
ልኑር ከአንተ ጋራ/2/
የማስብበት በየለእቱ ንጹሕ ልብን
ስጠኝ አቤቱ /2/
ከትእዛዝህ ውጪ በመሆን
እዳልቀር በከንቱ /2/
እንደየሥራው ለመስጠት
በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ/2/
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ
ፊተናን የወጣ/2/
እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ
እየተማራችሁ ከቃሉ/2/
ይመጣሉና በእርሱ ስም
አምላክ ነን የሚሉ/2/
ትእግሥትን በመያዝ ሁላችሁ
እስከመጨረሻው ጠንክሩ/2/
ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ
የማዳን ተግባሩ/2/
@aleroe
#እያለፈ_ነው_ዘመኔ
እያለፈ ነው ዘመኔ ትእዛዙን ሳልፈጽም
ወየው ለእኔ/2/
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ
ና ብሎ ወደእኔ/2/
በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ
ብዙ አዝመራ/2/
ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ
ልኑር ከአንተ ጋራ/2/
የማስብበት በየለእቱ ንጹሕ ልብን
ስጠኝ አቤቱ /2/
ከትእዛዝህ ውጪ በመሆን
እዳልቀር በከንቱ /2/
እንደየሥራው ለመስጠት
በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ/2/
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ
ፊተናን የወጣ/2/
እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ
እየተማራችሁ ከቃሉ/2/
ይመጣሉና በእርሱ ስም
አምላክ ነን የሚሉ/2/
ትእግሥትን በመያዝ ሁላችሁ
እስከመጨረሻው ጠንክሩ/2/
ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ
የማዳን ተግባሩ/2/
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
፨ጊዜዬን ባርክልኝ፨
በዝናብ አብቅለህ በፀሐይ አብስለህ
የምትመግብ ጌታ ሁሉን አዘጋጅተህ
ነጻነቱን ሰጥተህ ጥበቡን አድለህ
እዚህ ላደረስከኝ ምስጋና ይድረስህ
ሁሌም ጠብቀኸኝ በምሕረት ጥላ
ጊዜን ባርክልኝ ሰርቼ እንድበላ
ከፍጥረታት ሁሉ አልቀህ ፈጥረኸኝ
የጸጋን ገዢነት በፍቅርህ አድለኸኝ
ከቤትህ እንድኖር ርስትአውረሰኸኝ
ለዚህ ያበቃህኝ ከቶ እኔ ማነኝ
ያለኝ ምስጋና ነው አምላክ ክበርልኝ
እኔ ስበድልህ አንተ ስትምረኝ
በምሕረት ታግለህ ፈጥነህ ሳታጠፋኝ
ንስሐ እንድገባ ጊዜን ባርክልኝ።
@aleroe
፨ጊዜዬን ባርክልኝ፨
በዝናብ አብቅለህ በፀሐይ አብስለህ
የምትመግብ ጌታ ሁሉን አዘጋጅተህ
ነጻነቱን ሰጥተህ ጥበቡን አድለህ
እዚህ ላደረስከኝ ምስጋና ይድረስህ
ሁሌም ጠብቀኸኝ በምሕረት ጥላ
ጊዜን ባርክልኝ ሰርቼ እንድበላ
ከፍጥረታት ሁሉ አልቀህ ፈጥረኸኝ
የጸጋን ገዢነት በፍቅርህ አድለኸኝ
ከቤትህ እንድኖር ርስትአውረሰኸኝ
ለዚህ ያበቃህኝ ከቶ እኔ ማነኝ
ያለኝ ምስጋና ነው አምላክ ክበርልኝ
እኔ ስበድልህ አንተ ስትምረኝ
በምሕረት ታግለህ ፈጥነህ ሳታጠፋኝ
ንስሐ እንድገባ ጊዜን ባርክልኝ።
@aleroe
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
……✍ከእለታት አንድ ቀን አንድ አባት ወደ አባታችን አባ መቃርዮስ በኣት ሄደና "አባቴ ሆይ ድኅነትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?" ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው። አባታችንም እንዲህ በማለት አሉት።
"ወደ መቃብር ሂድና ሙታንን ሰድበሃቸው ና" አሉት። ይህ አባትም የተባለውን አድርጎ ተመለሰ። አባታችንም "ምን አሉህ?" ሲሉ ጠየቁት። ሰውየዉም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "አሁን ደግሞ ሂድና ሙታንን አመስግናቸው" አሉት። ሄዶም አመሰገናቸው። "አሁንስ ምን አሉህ" ሲል በድጋሚ ጠየቁት። ሰውዬም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባታችን አባ መቃርዮስም: "ስትሰድባቸው ፤ስታመሰግናቸው እና ስታወድሳቸው ምንም አልመለሱም፤ አንተም ለነፍስህ ድህነትን ከፈለግህ እንደሞተ ሰው ሆነህ ኑር። ሰዎች ክፉ ቢያደርጉብህም፣ ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ" አሉት።

ምክረ አበው
“ #እምነት-አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡
ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡
ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን #የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡
እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!!

ኤልሮኢ
ማርያም ማርያም
°ማንኛውም የአለም ሰው 5 የስሜት ሕዋሳት አሉት የኢትዮጵያውያን ግን 6 ነው ስድስተኛውም ቅድስት ድንግል ማርያም ናት
+ እርጉዝ ሴት እቤት ስትመጣ የማርያም እንግዳ መጣች
+ ልትወልድ ስትል ማርያም ማርያም
+ ስትወልድ እንኳን ማርያም ማረችሽ
+ እሷ አልጋላይ ሆና ማርያም ታኑርሽ(ህ)
+ ተጠይቆ ሲወጣ ማርያም በሽልም ታውጣሽ
+ ስንጫወት የማርያም መንገድ ስጠኝ(ስጪኝ)
+ ትንሿ ጣታችንን የማርያም ጣት
+ ሰው የጠራን መስሎን ስንደነግጥ የማርያምን ብቅል እየፈጨው ነው
+ ገላችን ላይ ምልክት ስትወጣ ማርያም የሣመችኝ
ኸረ ስንቱ ይነገር እኛ እና እሷ ያለን ወዳጅነት።
መልካም የፆም ጊዜ

🕐 የካቲት 22/06/2012 ዓ.ም🕖
✨✨በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ✨✨
✨✨መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ✨✨
👉 ዲያቆን
📖 1 ቆሮ. 12፥1 ወበእንተሂ ዘመንፈስ ቅዱስ .....
👉 ንፍቅ ዲያቆን
📖 1 ጴጥ. 1፥7 ወባሕቱ አዳጠ ይእዜ ሀለወክሙ ....
👉 ንፍቅ ካህን
📖 ግብረ ሐዋርያት 16÷16 ወእንዘ ነሐውር ለፀሎት ....
👉 ምስባክ
ዘነግህ
1 📖መዝ. 142/143፥1
----------------
እግዚኦ ስምዓኒ ጸሎትየ ወአፅምአኒ ስእለትየ በጽድቅከ ወስምዐኒ በርትዕከ
ዘቅዳሴ
2 📖መዝ. 142/143፥8
----------------
ዘይሰማዕ ግበር ሊተ ምሕረትከ በጽባሕ እስመ ኪያከ ተወከልኩ እግዚኦ ምርሀኒ እግዚኦ ፍኖተ እንተ ባቲ አሐውር
ትርጉም
-------------
1:- አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፤ በእውነትህ ልመናዬን አድምጥ፥ በጽድቅህም መልስልኝ
2:- አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ
📖 ወንጌል
የሉቃስ ወንጌል 13÷ 10 - 17
---------------------
በሰንበትም በአንድ ምኵራብ ያስተምር ነበር ፤ እነሆም፥ ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ የድካም መንፈስ ያደረባት ሴት ነበረች፥ እርስዋም ጐባጣ ነበረች ቀንታም ልትቆም ከቶ አልተቻላትም ፤ ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና። አንቺ ሴት፥ ከድካምሽ ተፈትተሻል አላት፥ እጁንም ጫነባት ፤ ያን ጊዜም ቀጥ አለች፥ እግዚአብሔርንም አመሰገነች ፤ የምኵራብ አለቃ ግን ኢየሱስ በሰንበት ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ መለሰና ሕዝቡን። ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት አይደለም አለ ፤ ጌታም መልሶ። እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በሰንበት በሬውን ወይስ አህያውን ከግርግሙ ፈትቶ ውኃ ሊያጠጣው ይወስደው የለምን? ፤ ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው ፤ ይህንም ሲናገር ሳለ የተቃወሙት ሁሉ አፈሩ፤ ከእርሱም በተደረገው ድንቅ ሁሉ ሕዝቡ ሁሉ ደስ አላቸው።
📖 ቅዳሴ
ግሩም