"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
+++ ምን ብዬ ልጸልይ? +++
በግሪክ ሀገር ሁለት ሴት ልጆቹን ያሉት አንድ አባት ነበር። በአንድ ዓመት ብቻ የሚበላለጡትን እነዚህን ሕጻናት እንደ አባትም እንደ እናትም ሆኖ ተንከባክቦ ማሳደግ የዚህ ሰው ዋነኛ ሥራው ነበር።
ስለዚህ ወጥቶ በገባ ቁጥር ልጆቹን የሚያስደስት ነገር እየገዛ ፣ የሚጠይቁትን እያሟላ በድሎት ያኖራቸው ነበር። የራሱን ሕይወት ወደ ጎን ትቶ ለልጆቹ መኖሩ ያለ ዋጋ አልቀረም። ሁለቱም ልጆቹ በጤንነት አድገው ዕድሜያቸው ለጋብቻ ደረሰ።
አባት የለፋባቸው ልጆቹን ከመዳሩ በፊት ብዙ መሰብ ነበረበት። አስተዋይ ነበርና ብዙ ሽማግሌ ቢላክበትም ልጆቹን ለመሥጠት የወሰነው ግን በጥንቃቄ ነበር። ስለዚህ ልጆቹ ሁለቱም በአንድ ጊዜ እንዳይቸገሩ በማሰብ የተለያየና የማይነጥፍ መተዳደሪያ ላላቸው ወንዶች ባል እንዲሆኑ ለማድረግ ወሰነ።
እንዲህ ሲልም ያወጣና ያወርድ ጀመር :
"ሰዎች ሁልጊዜም ምግብ ያስፈልጋቸዋል ስለዚህ ገበሬ መቼም ቢሆን እህል ገዢ አያጣም። እንዲሁም ሰዎች ውኃ ለመቅዳት ምግብ ለመሥራት ሸክላ ስለሚፈልጉ ሸክላ ሠሪም ገበያ አያጣም።
ስለዚህ ልጆቼን የምሠጠው ለሸክላ ሠሪና ለገበሬ ነው" አለ። እንዳለውም አንዲቷ ልጁ የገበሬ ሚስት ሌላኛዋ ደግሞ የሸክላ ሠሪ ሚስት እንዲሆኑ ሠጣቸው።
ከብዙ ጊዜ በኋላ በአንድ ሰንበት ይህ ሽማግሌ ዛሬስ ልጆቼን ልጠይቅ ብሎ ተነሣ። በመጀመሪያ ወደ ገበሬው ሚስት ሔዶ ሲጫወት አረፈደ።
ተሰናብቶ ሊወጣ ሲል ልጁ እንዲህ አለችው :
"አባዬ እስካሁን ኑሮአችን ሰላም ነበር። አሁን ግን ችግር ላይ ነን። ላለፉት ሁለት ወራት ዝናም ጨርሶ አልዘነበም። በዚሁ ከቀጠለ የዘራነው አይበቅልም ፣ ተክሎቻችንም ይደርቃሉ።
አባዬ አደራ! በሚመጣው ወር ከባድ ዝናም እንዲጥል ወደ ፈጣሪ ጸልይልን!"
አባት አደራውን ተቀብሎ ተሰናብቶ ወደ ሁለተኛዋ ልጁ ቤት ለመሔድ ጉዞውን ጀመረ።
ከሰዓት በኋላ ወደ ሁለተኛዋ ልጁ ቤት ሲደርስ ከሸክላ ሠሪው ባሏ ጋር በአክብሮት ተቀብለው አስተናገዱት። ከጠዋቱ የበለጠ ደስተኛ ሆኖም አሳለፈ። መሰናበቻው ላይ ግን ልጁ ተነሥታ እንዲህ አለችው:
"አባዬ ለአንተ ለጸሎተኛው አባቴና ለጠንካራው ባለቤቴ ምስጋና ይሁንና ኑሮአችን እስካሁን ጥሩ ነው። እንደምታውቀው ላለፉት ሁለት ወራት ዝናም አልዘነመም። በዚህም ደስተኞች ነን። አሁን የምለምንህ አንድ ነገር ብቻ ነው።
በሜዳ ላይ ተደርድሮ እንደምታየው እጅግ ብዙ ሸክላዎች እየሠራን ነው። በሚመጣው ወር ዝናም ካልዘነመና ደረቅ ከሆነ የሠራናቸው ዕቃዎች ሁሉ ደርቀው ለገበያ ይደርሱልናል። ስለዚህ በሚመጣው ወር ዝናም እንዳይጥል ወደ ፈጣሪህ ጸልይልን"
አባት ተሰናብቶ ሲወጣ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ
"ፈጣሪዬ ሆይ አንዲቱ እንዳይዘንም ጸልይ አለችኝ ፣ ሌላዋ እንዲዘንም ጸልይ አለችኝ ፣ ምን ብዬ ልጸልይ?" አለ።
ይህ አረጋዊ የእኛን ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቢያስቀድስ ኖሮ ግን እንዲህ አይጨነቅም ነበር። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ላይ ዲያቆኑ የሚያነበው ምእመናን በግንባራቸው ተደፍተው የሚሰሙት "በእንተ ቅድሳት" የሚባል ጸሎት ላይ የዚህን ሽማግሌ ልብ የሚያረጋጋ ስለ ዝናም የሚጸለይ አንቀጽ አለ። እንዲህ ይላል:
"በሚሻበት ቦታ እግዚአብሔር ዝናሙን ያዘንም ዘንድ ስለ ዝናም እንማልዳለን"
"በሚሻበት" የሚለው ቃል ላይ "ሻ" ጠብቃ ትነበባለች። "በሚፈለግበት ቦታ እግዚአብሔር ዝናሙን ያዘንም ዘንድ" (ኀበ ዘይትፈቀድ መካን) ማለት ነው። ቀሳውስቱም ስለ ዝናማት በሚጸልዩት መስተብቁዕ ላይ "ወደ ሚሻበት ቦታ ዝናሙን ይልክ ዘንድ" (ከመ ዝናሞ ይፈኑ ውስተ ኀበ ይትፈቀድ መካን) "ወደሚሻበት ቦታ ዝናሞችህን ላክ"(ዝናማቲከ ፈኑ ውስተ ኀበ ይትፈቀድ መካን) ይላሉ።
ዝናም እንደ ገበሬው ቤት የሚፈለግበት ቦታ እንዳለ ሁሉ እንደ ሸክላ ሠሪው ቤት ደግሞ የማይፈለግበት ቦታ አለና ቤተ ክርስቲያን ከፈጣሪዋ ዝናም ከመለመን አልፋ የሚያዘንምበትን ቦታም እየጠቆመች ትጸልያለች።
"ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ "
@aleroe

የድሆች_መጠጊያ
የድሆች መጠጊያ ቤተክርስቲያን
ለመማር መጥተናል ሰመተን ቃልሽን/2/
ሰላም /2/ የዘላለም ቤቴ
ካንቺ አልለይም እስከለተ ሞቴ
ሰላም ላንቺ ይሁን ቤተ ክርስቲያን
በደሙ ያጸናሽ ኢየሱስ መድህን/2/
ቤተ ክርስቲያን ሆይ የአማንያን እናት
ወዳንቺ ቀርበናል እንድናገኝ ህይወት
ቅረቡ ወጣቶች ባንድነት ሆናችሁ
እጆቻን ዘርግታ ልትቀበላችሁ
ተነስታለችና ቅድስት እናታችሁ
@aleroe
የድሆች_መጠጊያ
የድሆች መጠጊያ ቤተክርስቲያን
ለመማር መጥተናል ሰመተን ቃልሽን/2/
ሰላም /2/ የዘላለም ቤቴ
ካንቺ አልለይም እስከለተ ሞቴ
ሰላም ላንቺ ይሁን ቤተ ክርስቲያን
በደሙ ያጸናሽ ኢየሱስ መድህን/2/
ቤተ ክርስቲያን ሆይ የአማንያን እናት
ወዳንቺ ቀርበናል እንድናገኝ ህይወት
ቅረቡ ወጣቶች ባንድነት ሆናችሁ
እጆቻን ዘርግታ ልትቀበላችሁ
ተነስታለችና ቅድስት እናታችሁ
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
…………✍መብረር አስተምሪኝ
ዔሊዋ አሞራን ባገኘቻት ቀጥር መብረር አስተምሪኝ እያለች ጭቅጭቅ ታደርጋታለች። አሞራዋም በተገናኙ ቁጥር "ይኽ የተፈጥሯችን ጉዳይ ነው። በመማርና በማስተማር የሚመጣ አይደለም" ትላት ነበር። ኤሊዋ ግን የምቀኝነት ነገር እየመሰላት የአሞራዋን ቃል አልሰማ አለች።
አንድ ቀን አሞራዋ "ምን ላድርግሽ ብትላት?" እንደምንም ብለሽ ወደ ላይ አድርጊኝና ልቀቂኝ ራሴ እበራለሁ አለቻት። በጭቅጭቋ የተማረረችው አሞራ አንድ ባላ ቢጤ አመጣችና ያን በኤሊዋ አፍ አስይዛ ሌላኛውን ጫፍ እሷ ይዛ ሽቅብ ወደ ላይ ከበረረች በኋላ የእንጨቱን ጫፍ ለቃ "ያውልሽ ብረሪ" አለችና ለቀቀቻት። ኤሊዋም ተምዘግዝጋ ወረደችና እንዳልነበረች ሆና ሞተች።
ሰው ሁሉ የተሰጠው የራሱ ጸጋና ሃብት አለው። አንተ ሁልጊዜ አንተ ነህ ሌላውን በአንተ ውስጥ ስትፈልግ ከምትደክም ራስህን በአንተ ውስጥ ፈልግና አግኘው። አዳምና ሄዋን ሰው ናቸው ግን እግዚአብሔርን መሆን ተመኙ እንኳን እግዚአብሔር ሊሆኑ በቅጡ ሰው መሆንንም አጡ። ምላጭ ምንም ያህል ስለታም ቢሆን ዛፍ አይቆርጥም መጥረቢያ የቱንም ያህል ቢጠነክር ጸጉር አይቆርጥም። ልክ እንዲሁ እኛም ለተፈጠርንለት ዓላማ እንኑር
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
፨ገድፍሃል፨
አንደበትህ ክዶህ ሀሰት ከለመደ
መልካሙን ናቅ አርጎ ሴራ ከወደደ
እንደ አምሳል መሰረት ቀረ ሰው መሆንህ
አምላክም አይኖርም ሳይጣን ነው ከጎንህ
በህይዎት እየኖርክ ከሆንክ አሜኬላ
እኔ ሰው ነኝ እያልክ ልብህ ሰው ከጠላ
በእምነቱ ፀንተህ ወስጋ ከደሙ
አልገለጽ ካለህ የህይወት ትረጉሙ
እውነቱን ተቀበል
ጾምህን ገድፍሃል
ለምን! ማለት ጥሩ ለምን ይመስልሃል?
ውሰጥ ተመርዞ
ልብህ ቂም አርግዞ
ላይሰምር ሱባኤ
ልብ ሳይኖር ጉባኤ
ገደብ የለሽ ምኞት
ከአንገት በላይ ፀሎት
በላይኛው አለም ወንዝ አያሻግርም
እዚ እንደለመደከው ማጭበርበር አይኖርም።
@aleroe
፨ገድፍሃል፨
አንደበትህ ክዶህ ሀሰት ከለመደ
መልካሙን ናቅ አርጎ ሴራ ከወደደ
እንደ አምሳል መሰረት ቀረ ሰው መሆንህ
አምላክም አይኖርም ሳይጣን ነው ከጎንህ
በህይዎት እየኖርክ ከሆንክ አሜኬላ
እኔ ሰው ነኝ እያልክ ልብህ ሰው ከጠላ
በእምነቱ ፀንተህ ወስጋ ከደሙ
አልገለጽ ካለህ የህይወት ትረጉሙ
እውነቱን ተቀበል
ጾምህን ገድፍሃል
ለምን! ማለት ጥሩ ለምን ይመስልሃል?
ውሰጥ ተመርዞ
ልብህ ቂም አርግዞ
ላይሰምር ሱባኤ
ልብ ሳይኖር ጉባኤ
ገደብ የለሽ ምኞት
ከአንገት በላይ ፀሎት
በላይኛው አለም ወንዝ አያሻግርም
እዚ እንደለመደከው ማጭበርበር አይኖርም።
@aleroe
ኤልሮኢ:
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን
ኑ በእግዚአብሄር ደስ ይበለን /2/
ለታላቁ ክብር ለዚ ላበቃን
ከሞት ወደ ህይወት ላሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሄር ኑ በድንግል ደስ ይበለን
የሰማዩን መንግሥት እርስቱን ለሰጠን
ከጨለማ አውጥቶ ብርሃንን ላሳየን
ለዚህ ድንቅ ውለታው ምስጋና ያንሰዋል
በእርሱ ደስ ይበለን ክብር ይገባዋል
ከአለት የፈለቀ ውሃ ጠጥተናል
ሰማያዊ መና አምላክ መግቦናል
ፍቅርህ የበዛልህ ምን ልክፈልህ ጌታ
ስምህን ላመስግነው ከጠዋት እስከ ማታ
በቃዴስ በረሀ ምንም በሌለበት
በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት
ለእርሱ መንገድ አለው ከቶ ምን ተስኖት
ልባችሁ አይፍራ በፍፁም እመኑት
በባርነት ሳለን በድቅድቅ ዓለም
ብርሃንን አገኘን በድንግል ማርያም
ያጣነውን ሰላም ዛሬ አገኘን
እጅግ ደስ ይበለን በእመቤታችን
የሐና የኢያቄም የእምነታቸው ፍሬ
በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ
የኢያቄም ስዕለቱ የሐና እምነት
ለምኝልን ለኛ ኪዳነ ምሕረት
@aleroe
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን
ኑ በእግዚአብሄር ደስ ይበለን /2/
ለታላቁ ክብር ለዚ ላበቃን
ከሞት ወደ ህይወት ላሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሄር ኑ በድንግል ደስ ይበለን
የሰማዩን መንግሥት እርስቱን ለሰጠን
ከጨለማ አውጥቶ ብርሃንን ላሳየን
ለዚህ ድንቅ ውለታው ምስጋና ያንሰዋል
በእርሱ ደስ ይበለን ክብር ይገባዋል
ከአለት የፈለቀ ውሃ ጠጥተናል
ሰማያዊ መና አምላክ መግቦናል
ፍቅርህ የበዛልህ ምን ልክፈልህ ጌታ
ስምህን ላመስግነው ከጠዋት እስከ ማታ
በቃዴስ በረሀ ምንም በሌለበት
በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት
ለእርሱ መንገድ አለው ከቶ ምን ተስኖት
ልባችሁ አይፍራ በፍፁም እመኑት
በባርነት ሳለን በድቅድቅ ዓለም
ብርሃንን አገኘን በድንግል ማርያም
ያጣነውን ሰላም ዛሬ አገኘን
እጅግ ደስ ይበለን በእመቤታችን
የሐና የኢያቄም የእምነታቸው ፍሬ
በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ
የኢያቄም ስዕለቱ የሐና እምነት
ለምኝልን ለኛ ኪዳነ ምሕረት
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
……✍‹‹አንድ ጠርሙስ አረቄ . . . !››
በጠጪነቱ የታወቀ የአንድ መሥሪያ ቤት ሠራተኛ ጧት ሥራ ከመግባቱ በፊት ከቤቱ ጀምሮ ባሉ አንድ አራት መጠጥ ቤቶች ጎራ እያለ ፉት ይላል፡፡ ማታም እንዲሁ አትለፍ የተባለ ይመስል የደንቡን ሳያደርስ ቤቱ አይገባም፡፡
ይህ ልምዱ እንደማያዋጣው በብዙ ሰዎች ከተነገረው በኋላ አንድ ጧት ለራሱ ቃል ገባ፣ ሳይጠጣ ቢሮው ገብቶ ሳይጠጣ ቤቱ ለመመለስ፡፡ እናም፣ ምሎ እና ተገዝቶ እኒያን መጠጥ ቤቶች ጧት ላይ እየገላመጠ እና እየረገማቸው አልፎ መሥሪያ ቤቱ ደረሰ፡፡
በውሳኔው ተደስቶ በሰላም ሲሠራ ከዋለ በኋላ ማታም ወደ ቤቱ ሲመለስ የጧቱኑ ዕርምጃ ወሰደ፡፡
ሳይቀምስ ውሎ ሳይቀምስ በመግባቱ ተደስቶ፣ ‹‹ጀግና ነኝ! ቆራጥ! ለዚህ ጀግንነቴ አንድ ጠርሙስ አረቄ ይገባኛል በማለት ወደ አረቄ ቤት በረረና አረፈዋ!
➴ ይህ ታሪክ የሚያስራዳን ከወሰነ በኃላ ዳግመኛ ወደ ኋላ ወደ ሃጢያት መመለሱን ነው። ታዲያ እኛም እንደዚህ መሆን የለብንም አንዴ በንስሐ ለመመለስ ከወሰን እና ንሰሃም ከገባን በኋላ ዳግመኛ ወደ ረገምነው ሃጢአት መመለስ የለብንም። ካልሆነ ግን በንስሃ ሳሙና ታጥበን ስናበቃ አምላካችን እንደ በረዶ አጥቦን እያለ ዳግመኛ ወደ ረገምነው የሃጢያት እድፍ ጭቃ መዘፈቅ ነው የሚሆነው።

#ከሳሽ_ዕድፉን_ሳያይ
ስታመነዝር አገኘናት፣
ብለው አካልበዋት፣
ከጌታ ፊት እያቻኮሉ፣
ከእግሩ ሥር አምጥተዋት ጣሉ፡፡
ምን ትላለህ ? ስለዚች ሴት፣
ይዘናታል በማመንዘር ኃጢአት፣
ሙሴ እንደው በሕጉ፣
ብሎናል ወግራችሁ ግደሉ፣
አንተስ ምን ትላለህ ?
ይሰማ እስኪ ፍርድህ … ?
ይላሉ ከሳሾች ….
ወንዱን አስመልጠው ፣ ሴቷን አሳዳጆች፤
እውነት አንሻፋፊ ፣ ግማሽ ምስክሮች፤
ኢየሱስ መለሰ ….
ጐንበስ ብሎ ከምድር ፣ አንዳች እየጻፈ፤
ከʻናንተ መካከል ፣ ነውሯ ያላገኘው፤
ድንጋይን ከሯሷ ፣ አሁኑ ይጫነው፤
ብሎ ሳያበቃ ፣ ቀና ሲል ካለበት፤
ከʻርሷ በቀር የለም ፣ ከተከሳሿ ሴት ፤
ለካስ ሁሉም ጥሎ ፣ ከዚያ ሥፍራ የጠፋው፤
ከʻርሷ ጋር ተጋድሞ ፣ ዕድፉን ባያየው ነው፡፡
ያመነች ግን እርሷ ፣ ተከናወነላት ፤
መንገዷን ቀየረች ፣ ከሞት ወደ ሕይወት፡፡
__________________
@aleroe
#ከሳሽ_ዕድፉን_ሳያይ
ስታመነዝር አገኘናት፣
ብለው አካልበዋት፣
ከጌታ ፊት እያቻኮሉ፣
ከእግሩ ሥር አምጥተዋት ጣሉ፡፡
ምን ትላለህ ? ስለዚች ሴት፣
ይዘናታል በማመንዘር ኃጢአት፣
ሙሴ እንደው በሕጉ፣
ብሎናል ወግራችሁ ግደሉ፣
አንተስ ምን ትላለህ ?
ይሰማ እስኪ ፍርድህ … ?
ይላሉ ከሳሾች ….
ወንዱን አስመልጠው ፣ ሴቷን አሳዳጆች፤
እውነት አንሻፋፊ ፣ ግማሽ ምስክሮች፤
ኢየሱስ መለሰ ….
ጐንበስ ብሎ ከምድር ፣ አንዳች እየጻፈ፤
ከʻናንተ መካከል ፣ ነውሯ ያላገኘው፤
ድንጋይን ከሯሷ ፣ አሁኑ ይጫነው፤
ብሎ ሳያበቃ ፣ ቀና ሲል ካለበት፤
ከʻርሷ በቀር የለም ፣ ከተከሳሿ ሴት ፤
ለካስ ሁሉም ጥሎ ፣ ከዚያ ሥፍራ የጠፋው፤
ከʻርሷ ጋር ተጋድሞ ፣ ዕድፉን ባያየው ነው፡፡
ያመነች ግን እርሷ ፣ ተከናወነላት ፤
መንገዷን ቀየረች ፣ ከሞት ወደ ሕይወት፡፡
__________________
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
……✍አንድን ህጻን ልጅ ማሙሽዬ ድንግል ማርያም ላንተ ምንድን ናት
ብዬ ጠየኩት
."ድንግል መርያም ፊደሌ ናት " አለኝ
አንዲት ወጣትንም ድንግል ማርያም ላንቺ ማን ናት ብዬ ጠየኳት
."የደናግል መመኪያ ናት " አለችኝ ።
አንድንም ወጣት ጠየኩት
" ውበት ናት " አለኝ ።
.....
ስደተኛም ሰው አግንቼ ጠየኩ
" እሷ የስደተኞች ስንቅ ናት " አለኝ ።
....
አንዲት እናትንም ጠየኩ
" እሷ የአለም ሁሉ እናት ነች " አሉኝ ።
የቆሎ ተማሪውንም ጠየኩት
" ድንግል ማርያም መመኪያ ናት ስሟን ይዘህ አታፍርም " አለኝ ።
..
ዶክተሩንም ጠየኩት
" የመዳኒት እናት ነች " አለኝ
አናጢውንም ድንግል ማርያም ላንተ ምንድን ነች ብዬ ጠየኩት
.
"የአለም ሁሉ መሰላል ነች " አለኝ
.
አገልጋዩንም ጠየኩት
" የጻድቃን እመቤት ነች" አለኝ
ችግረኛ ድሀውንም ጠየኩት
" የሁሉ ሀብት ነች " አለኝ
.
ባለጸጋውንም ጠየኩት
"ድንግል ማርያም በረከት ነች " አለኝ
ወታደርም አግንቼ ጠየኩ
" ድንግል ማርያም ጋሻ መከታ ናት " አለኝ
.
ያረጁ አዛውንትም አግንቼ ጠየኩ
" ድንግል ማርያም ምርኩዝ ናት " አሉኝ
.........
....
በመጨረሻ ራሴን ጠየኩ
.
አይምሮዬም እንዲህ ብሎ መለሰልኝ
.....
የመስቀል ስር የአደራ ስጦታህ
.
የህይወትህ እንጀራ የተዘጋጀባት መሶብህ
የህይወትህ መጠጥ የተዘጋጀባት ፅዋህ
ከዘላለማዊ ፍዳ ወደ ዘላለማዊ ምህረት የተሻገርክባት መሰላልክ
እንኳን አንተ ቅዱሳን ምሳሌ ያጡላት ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን
እርሷን የሚመስል የሌለ ንግስተ ሰማይ ወምድር ናት።
ድንግል ማርያም የሁሉ መማሪያ ናት" አለኝ
ሁሉ ይማርባታል ፦ ፊደል መጽሀፍ እውቀት ነች ፡
ሁሉ ይማርባታል ፦ ምህረት ታስገኛለች ታማልዳላች ።
እርሷን የሰጠን ይክበር ይመስገን እና፡፡
.
ለናንተስ ድንግል ማርያም ማን ናት ምንድን ናት ??

እግዚአብሄርን ጠራሁት
እግዚአብሔርን ጠራሁት በሐዘኔ ጊዜ
እግዚአብሔርን ጠራሁት በጭንቀቴ ጊዜ አወጣኝ ከጭንቀት ከሐዘን ከትካዜ /2
የልመናዬን ድምጽ እርሱ ሰምቷልና
ጆሮውን ወደ እኔ አዝንብሏልና
በዘመኔ ሁሉ ስጠራው እኖራለሁ
ጎስቋላ ብሆንም ምስጋና አቀርባለሁ/2/
እንደ ቃልህ መሄድ መራመድ አቅቶኝ
የኃጢአቱ መንገድ ማእበሉ ገፍቶኝ
ወደ እርሱ ስማጸን ደግሞም ስጸጸት
አላሳፈረኝም መጣ በምሕረት /2/
በበዛው ምሕረቱ ያለፈውን ትቶ
በፍቅሩ ጎበኘኝ አልተወኝም ከቶ
ሊቀበኝ ወዶ ፊቱን አበራልኝ
ማን ይቃወመኛል እግዚአብሔር ካለልኝ/2/
ኖኅን አንዳዳንከው እኛንም አድነን
ከቀስቱ እንድናመልጥ ምልክትን ስጠን
በትርህ ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑን
አንተ ከእኛ ጋር ነህ አንፈራም ክፉውን/2/

28/11/2010 ዓ.ም
መዝሙር "በሰንበት ቦአ"
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።
ዲያቆን፦ ቲቶ 3÷1-ፍ.ም
ንፍቅ ደያቆን፦1 ጴጥ 4፥6-12
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 28÷1-17
#ምስባክ፦
.. መዝ 134፥7-9
ያዐርግ ደመናት እምአጽናፈ ምድር።
ወገብረ መብረቀ ለጊዜ ዝናም።
ዘያወፅኦሙ ለነፋሳት አመዛግብ ቲሆሙ።
#ትርጉም፦
ከምድር ዳር ደመናትን ያወጣል።
ለዝናብ ጊዜ መብረቅን አደረገ።
ነፋሳትንም ከወንዞች ያወጣል።
#ወንጌል ፦ ማር 6÷47-ፍ.ም
#ቅዳሴ ፦ ዘኤጲፋኒዮስ
@aleroe
28/11/2010 ዓ.ም
መዝሙር "በሰንበት ቦአ"
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።
ዲያቆን፦ ቲቶ 3÷1-ፍ.ም
ንፍቅ ደያቆን፦1 ጴጥ 4፥6-12
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 28÷1-17
#ምስባክ፦
.. መዝ 134፥7-9
ያዐርግ ደመናት እምአጽናፈ ምድር።
ወገብረ መብረቀ ለጊዜ ዝናም።
ዘያወፅኦሙ ለነፋሳት አመዛግብ ቲሆሙ።
#ትርጉም፦
ከምድር ዳር ደመናትን ያወጣል።
ለዝናብ ጊዜ መብረቅን አደረገ።
ነፋሳትንም ከወንዞች ያወጣል።
#ወንጌል ፦ ማር 6÷47-ፍ.ም
#ቅዳሴ ፦ ዘኤጲፋኒዮስ
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
"እግዚአብሔር ባስቀመጥነው ሥፍራ ይቀመጣል።"
በአንድ ወቅት አሜሪካን ሐገር እንዲህ ሆነ። ባል ከቤት ውጭ ከተማ ከጓደኞቹ ጋር ሲዝናና ያመሽና ሚስቱጋ ደውሎ ወደ ጭፈራ ቤት በግሩፕ ከጓደኞቻችን ጋር ስለምንሔድ ለባብሰሽ ተዘጋጅተሽ ጠብቂኝ ይላታል።
ከግማሽ ሰዓት በኋላም ደርሶ ክላክስ እየነፋ እንድትወጣ ይጠራታል። የሚስቱ እናትም ሊሸኙዋት ወደ ደጅ ይወጡና ወደ ተሽከርካሪው ሲያዩ ሁሉም በጣም ጠጥተው እንደሰከሩ ያያሉ። ሁሉምም ከመስከራቸው ብዛት ይጮሁም ነበር። በዚህን ጊዜ ሴትየዋ "እግዚአብሔር በመንገዳችሁ ከእናንተ ጋር ይሁን ጠንቀቅ በሉ።" ይላሉ።
በዚህን ጊዜ አሜን እንደማለት ከግሩፑ አንዱ "እግዚአብሔር የት ይሆናል ቦታ የለንም ቢፈልግ ከኋላ ከእቃው ጋር ይቀመጥ።" ሲል ሁሉም መኪናው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ልክ ነው ብለው አላገጡም ሳቁም ሚስትየዋንም ጭነው በከፍተኛ ፍጥነት መኪናዋን እያሽከረከሩ ሲሄዱም ተሽከርካሪዋ ተገለባብጣ ከፍተኛ አደጋ ይደርስባታል። ሰዎቹም ሁሉም ያልቃሉ።
አንድ ተአምር ግን ይፈጠርና ሁሉንም ያስገርማል። እቃ ማስቀመጫ ላይ የነበሩት እንቁላሎች መኪናው ሶስት ጊዜ ተገለባብጦ ምንም ሳይሰበሩ ይገኛሉ። ምክንያቱ ሰዎቹ ለእግዚአብሔር ቦታ የለንም ከእቃዎቹ ጋር ይቀመጥ ብለው ነበርና እግዚአብሔር ከእቃዎቹ ጋር ተቀምጦ ነበርና እንቁላሎቹ ምንም ሳይሰበሩ ተገኙ። እግዚአብሔር የነጻነት አምላክ እንጂ አስገድዶ የሚገዛ ጌታ አይደለምና ባስቀመጥነው ሥፍራ ይቀመጣል።
እኛስ የት አስቀምጠነው ይሆን ለመሆኑ እግዚአብሔር በትዳራችን፣ በስራ ቦታችን፣ በቤታችን በአጠቃላይ በሕይወታችን ሥፍራ ሰጥተነው ይሆን? ከሰጠነውስ የት ቦታ? ዋናውን ወይስ መጨረሻውን?

#አልችልም_አስችለኝ
እየደነገጠ እየፈራ ልቤ
አንድነት አቅቶት ቅጥልጥል ሃሳቤ
ኮሽ ባለ ቁጥር እየፈራች ነፍሴ
አስጨንቀዋለሁ ራሴን በራሴ
አይኖቼ ተስፋዬን ማየት ተስኗቸው
እግሮቼ ጉዞዬን መጓዝ አቅቷቸው
ይቅበዘበዛሉ መሪ ጠፍቶባቸው
ዝም ባለ ጎጆ ጭጭ ባለ ሌሊት
ጩኸት ይሰማኛል ምንም በሌለበት
የሚያሳርፍ ጌታ እንዳለኝ ይወቀው
የሚያስጨንቀኝን አምላኬ አስጨንቀው
አንተ ድረስና የጭንቄን ውል ፍታ
አልችልም አስችለኝ እንዳልጠፋ ጌታ !
@aleroe
#አልችልም_አስችለኝ
እየደነገጠ እየፈራ ልቤ
አንድነት አቅቶት ቅጥልጥል ሃሳቤ
ኮሽ ባለ ቁጥር እየፈራች ነፍሴ
አስጨንቀዋለሁ ራሴን በራሴ
አይኖቼ ተስፋዬን ማየት ተስኗቸው
እግሮቼ ጉዞዬን መጓዝ አቅቷቸው
ይቅበዘበዛሉ መሪ ጠፍቶባቸው
ዝም ባለ ጎጆ ጭጭ ባለ ሌሊት
ጩኸት ይሰማኛል ምንም በሌለበት
የሚያሳርፍ ጌታ እንዳለኝ ይወቀው
የሚያስጨንቀኝን አምላኬ አስጨንቀው
አንተ ድረስና የጭንቄን ውል ፍታ
አልችልም አስችለኝ እንዳልጠፋ ጌታ !
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
ቤተክርስቲያን ጋር መጣላት ከራስ ጋር መጣላት ነው። ይቅርብህ ወገኔ
ይቅርብሀህ ወዳጄ ይቅርብህ ግዴለም ስማኝ በቤተክርስቲያን ላይ እጅህን
አታንሳ። አጻፋው ይከፋብሃል የሚመጣብህን ቁጣና መቅሰፍት የዲያቢሎስ እራት
ያደርግሀል ወዳጄ ዝቅ ብዩ ልለምነህ ሕይወትህ ትቢያ እንዳይሆን አትጣላ
እንኳን አንተ የሲኦል ደጆች አይችሏትም።
ዝም ስትል ኃይል እንደሌላት አስበህ ከሆነ ተሳስተሀል በደሙ የገዛት ክርስቶስ
በወጋሪዎቹ ፊት ዝም እንዳለ ስለምታውቅ ዝም ትላለች እንጂ። ዝምታዋን
አይተህ አትዳፈር እሳቱን አቀጣጥለህ አትሩጥ ቤኒዚን አታርከፍክፍ ካህን
አትረድ ግዴለህም ስማኝ ።
ካላወቅሀት ወዳጄ ቤተክርስቲያን ማለት:
ካንተ ጋር ካለው ብዙ ኃይልና ጸጋ ያላት
ምድራዊ ሳትሆን አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ናት
ዓለምን የፈጠረው የእግዚአብሔር አካል ነች
በደሙ የተገዛች በደሙ የተዋጀች ውድ አካሉ ናት
ዘወትር የእግዚአብሔር ዓይኖች የሚመለከቷት ናት
የአጋንት መንጋ የማያስደነግጣት ጽኑ እመቤት ናት
የክርስቶስ ስጋና ደም የሚፈተትባት ንጹህ በዓት ናት
የአበው ቅዱሳን ካህናት በዓት
የመንግስተ ሰማያት መንገድ
ያዘኑት የሚጽኑባት የሰላም ሰገነት ናት
ለአመኑት ሁሉ መጠለያ የሆነች ናት ይህን እወቅ
የድሆች መጠጊያ
የምህረት ሰገነት
የጥበብ እመቤት
የታሪክ ባለቤት ናት እንጂ
አንተ እንደምታስበው:-
የአውሮፓ አይደለችም
የአፍሪካ አይደለችም
የአማራ አይደለችም
የትግሬ አይደለችም
የሀረሬ አይደለችም
የኦሮሞ አይደለችም
የአፋር አይደለችም
የወላይታ አይደለችም
የሲዳማ አይደለችም
የጋምቤላ አይደለችም
የጉምዝ አይደለችም
የሀድያ አይደለችም
የጉራጌ አይደለችም
የከንባታ ወ ዘ ተ አይደለችም 100%
# # የእግዚአብሔር ናት##
እና እሷን ስትነካ እግዚአብሔርን እየነካህ ነው። ከፈጣሪህ ጋር ደግሞ አትጣላ
አጻፋና መቅሰፍቱ ይከብዳል ሕይወትህ እርባናቢስ እንዳይሆን ቆም ብለህ
አስብ።
እሷን ያፈረሱ እሷን ያቃጠሉ አፈርበልቷቸዋል
እሷ ግን ዛሬም አለች በክብር
ስታከብራት ትከበራለህ
ካቃጠልካት ትቃጠላለህ
️

የያሬድ ዉብ ዜማ
የያሬድ ዉብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ/ 2/
በምን አንደበቴ እንደምን ባለው ቃል ማርያም ልበልሽ/ 2
ምድርና ሰማዩ ተአምርሺን ይንገሩ
ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ
ድንግል ሆይ እናተ አምሳያም የለሽ
ማርያም ድንግል እረዳቴ
የምትደርሺልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ
ታምርሺን በአይኔ አይቻለሁ
ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ
አዝ - - -
የእግዚአብሄር ጥበቡ በአንቺ ተገለጠ
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ
ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሽ
ነገን ባላውቅ እኔም ቢያስፈራኚ
አንቺ ካለሺኝ በፍጹም አልወድቅም
በፊትሽም እንድቆም ለምስጋና
ማርያም ልበልሽ በትህትና
አዝ - - -
ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም
ባንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም
አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር
ማርያም ማርያም ይበል ተአምርሽን ይናገር
ጨለማው ከፊቴ ተገፈፈ
ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ
ከጎኔ ነይ ስልሽ እጽናናለሁ
እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ
@aleroe
የያሬድ ዉብ ዜማ
የያሬድ ዉብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሽ/ 2/
በምን አንደበቴ እንደምን ባለው ቃል ማርያም ልበልሽ/ 2
ምድርና ሰማዩ ተአምርሺን ይንገሩ
ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ
ድንግል ሆይ እናተ አምሳያም የለሽ
ማርያም ድንግል እረዳቴ
የምትደርሺልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ
ታምርሺን በአይኔ አይቻለሁ
ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ
አዝ - - -
የእግዚአብሄር ጥበቡ በአንቺ ተገለጠ
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ
ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሽ
ነገን ባላውቅ እኔም ቢያስፈራኚ
አንቺ ካለሺኝ በፍጹም አልወድቅም
በፊትሽም እንድቆም ለምስጋና
ማርያም ልበልሽ በትህትና
አዝ - - -
ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም
ባንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም
አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር
ማርያም ማርያም ይበል ተአምርሽን ይናገር
ጨለማው ከፊቴ ተገፈፈ
ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ
ከጎኔ ነይ ስልሽ እጽናናለሁ
እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
ምን ይል ይሆን
ዛፍ ቆራጩ የዛፉን ቅርንጫፍ መልምሎ ሲያበቃ ዛፉ እንደቆመ ራሱን ከዛፉ ጋር አስሮ ከግንዱ ጋር ሊታገል ወደ ላይ ተስቦ ከጫፍ ደርሷል። አሳቡ ቅርንጫፉ ተመልምሎ ያለቀለትን ብቻውን የቆመውን ዛፍ ከላይ ጀምሮ እየቆረጠ ወደ ታች ለመውረድ ነው።
መጥረብያውን ወደ ላይ ሲያነሳ ግን ንፋሱ ወደ ኋላ እያስጎነበሰውና በፍጥነት እያቃና ያንገላታዋል። ይሄኔ በሁለት እጁ ግንዱን አፈፍ ያደርግና ዥዋዥዌ ይጫወታል።
ንፋሱ እንኳንስ ስራ ሊያሰራው ቀርቶ ለህይወቱም አስጊ ሆነ። ይሄኔ ሁሉንም ርግፍ አርጎ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ በማቅናት "ፈጣሪዬ ሆይ ከዚህ በሰላም ካወረድከኝ በኪሴ ያለውም 50 ብር አምጥቼ አስገባለሁ" ሲል ይሳላል
ወድያው ይህን ተናግሮ ሲጨርስ ነፋሱ ይቆምና በሰላም ይወርዳል። ነገር ግን እግሩ መሬት ሲነካ ፍርሃቱ ሁሉ በኖ ስለጠፋ 50 ብሩን ለማስገባት ሳስቶ ምክንያት ይፈልግ ጀመር
"አዎ በርግጥ ከዚህ ዛፍ ላይ ካወረድከኝ ብዬ ተስያለሁ ነገር ግን የወረድኩት እኔ ራሴ ነኝ። ተሸክሞ ያወረደኝ ሳይኖር ለምንድነው 50ብሬን የማወጣው" ብሎ እራሱን በማሳመን ወደ ቤቱ ጉዞ ቀጠለ።
ዳሩ ግን ትንሽ እየተራመደ ትከሻው ቀለለውና ቢዳብሰው መጥረብያው የለም። መጥረብያው ከዛፉ ጫፍ እንደተሰካ ነው። አሁንስ ምን ይል ይሆን።
የሰው ልጅ ፍጡር ነው ሁሌ ከፈጣሪ እጅ አይወጣም እንድያው ይመስለናል እንጂ ያለ እግዚአብሔር መኖር አንችልም። ያለእኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም ይለናል ዮሐ 15፣5

"ምዕመናን በቤተመቅደስ ሊኖራቸው የሚገባ ሥርዓት
፦በቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ገበያ ክልክል ነው። /ማቴ 21፡12 ዮሐ 2፡13-18 ፍትሀነገስት አንቀጽ 1/
፦በቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ግብዣ ማድረግ፣መብላት፣መጠጣት ክልክል ነው። /የሎዶቅያ ሲኖዶስ (ዶቅ) 44 ፍ.ነገ 1/
፦ማንኛውም መብልም ሆነ መጠጥ ከቤተ መቅደስ 40 ክንድ(20 ሜትር) መራቅ አለበት! በመቅደሱ ሕብስቱና ወይኑ ብቻ ይፈተታልና። /ፍ.ነገ 1/
፦በታቦቱ ፊት ለመስገድ ወይም ለመፀለይ ወይም ለማስቀደስ ካልሆነ በቀር ማንም ወደ ቤተመቅደስ ገብቶ እንዲቀመጥ አይፈቀድም
፦ከካህን በስተቀር(ዲያቆናት፣ካህናት፣ቀሳውስት፣ጳጳሳት..) ከምዕመናን ወገን ወደ መቅደስ(ታቦቱ ያለበት) ገብቶ ሥጋ ወደሙን ሊቀበል(ሥጋ ወደሙን የሚያቀብሉ ካህናት ራሳቸው ሁሌም ከማቀበላቸው በፊት በመቅደስ ውስጥ ይቀበላሉ) ታቦቱን ሊጠጋ አይገባም /ፍ.ነገ 1፣ ቀኖና አብሉዲስ ፣ኢያሱ 3፡4/
፦ሴቶች ወደመቅደስ (ታቦቱ ያለበት) እንዲገቡና እንዲፀልዩ አልተፈቀደም። /የሎዶቅያ ሲኖዶስ(ዶቅ) 44፣ ፍ.ነገ 1/
፦ከቤተ ክርስቲያን አንዴ ለአገልግሎት ተመርጦ የገባውንና የተቀደሰውን ንዋየ ቅድሳት እንደገና ወደውጭ አውጥቶ መጠቀም አይገባም። /ፍ.ነገ 1፣ 1ቀለሚንጦስ (ረስጣ) 28/
፦ያላመኑ፣ ያልተጠመቁ፣ ተወግዘው የተለዩ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ ተከልክሏል። /ፍ.ነገ 1፣ ድድስቅሊያ (ድስቅ) 12/
፦ለፀሎትና ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ወደ ቤተክርስቲያን በሚኬድባቸው ዕለታት፣ በጾምና በሰንበት፣ በበዓላት ወቅት ወንድና ሴት ግንኙነት ክልክል ነው። /ዘፀ 19፡15፣ 1ቆሮ 7፡5-7/ (ለባለትዳር ብቻ ነው! ያላገባማ በየትኛውም ጊዜ ከጋብቻ በፊት አይፈቀድም)
፦ነውር ያለበት ወደ ቤተክርስቲያን አይገባም። /ፍ.ነገ 13/
፦ሴት ልጅ ወር አበባዋ ሲመጣ ለ7 ቀን፣ ስትወልድ ወንድ ከወለደች እስከ 40 ቀን፣ ሴት ከወለደች እስከ 80 ቀን ወደ ቤተመቅደስ መግባት አይፈቀድም። (ዘሌ 12፡1__፣ ዘሌ 15፡19-28፣ ፍ.ነገ 6፣ ዘኒቂያ 29)
፦ወንድም ቢሆን ከአፉ ወይም ከአፍንጫው የሚወጣ ፈሳሽ ፣ነስር ሲኖርበት ወደ ቤተ መቅደስ አይገባም! ይህም ቤተመቅደሱን ስለሚያረክስ ወይም ለሌላ #ሳይሆን በቤተ መቅደስ ውስጥ የክርስቶስ ደም ብቻ መፈተት ስላለበት ነው።
፦ወንድ ልጅ ሕልመ ሌሊት ከመታው(ህልመ ዝኔት ካየ(ስጋዊ ህልም ካየ) በዕለቱ ወደ ቤተ መቅደስ አይገባም። (ዘሌ 15፡2)
፦ጠዋትና ማታ ቤተክርስቲያን ለመሳለም መትጋት ያስፈልጋል። (ምሳ 8፡34)
፦ወደ ቤተክርስቲያን ሲገባ በቅፅረ ቤተክርስቲያን በር ላይ ሲደርሱ መሳለም ይገባል (መዝ 28፡2፣ መዝ 95፡9፣ ኤር 26፡2፣ ሕዝ 46፡3)
፦ወደ ቤተክርስቲያን (ቤተመቅደስ) ሲገቡ ጫማን አውልቆ ወገብን ታጥቆ አደግድጎ መግባት ይገባል። (ዘፀ 3፡5-6 ፣ ሐዋ 7፡33፣ ኢያሱ 5፡15፣ ፍ.ነገ 12)
፦በቤተክርስቲያን ውስጥ ተስለው የሚገኙ ቅዱሳን ሥዕላትን እጅ መንሳትና መስገድ ይገባል።
፦በቤተክርስቲያን ውስጥ መሳቅ፣ ስለ ዓለማዊ ነገር መነጋገር ክልክል ነው። /ዮሐንስ አፈወርቅ 19፡32 ፤ 48፤6 አቡሊዲስ 7/
፦አጭር፣ ያደፈ፣ የሰውነት ቅርጽን የሚያሳይ ልብስ ለብሶ ወደ ቤተክርስቲያን መሔድ ፈጽሞ የተከለከለ ነው /ዘፀ 19፡10 ፣ ዮሐ.አፈ 4፡49-72/
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

#ሁሉም_በምክንያት_ነው
ለስራ ሲሄዱ አባት ከልጁ ጋር
ሲደክማቸው አረፉ በአንድ የሾላ ዛፍ ስር
ትንሽም ሳይቆዩ ልጅየው ለማረፍ መሬት ላይ ተንጋሎ
አባቱን አላቸው የሾላውን ፍሬ በደንቡ አስተውሎ
አባቴ ተመልከት አምላክ ግን ሞኝ ነው
እንዴት ባክህ ልጄ ምን እያልከኝ ነው
ይህንን በሚያህል ትልቅ ዛፍ
የጥበቡን ስራ ሲያሳርፍ
እፍኝ የማይሞላ ትንሽዬ ፍሬ እንዲያፈራ ፈጥሮ
ግን ለአቅመ ቢሱ ዱባ ትልቅ ፍሬን ፈጥሮ ታዲያ ሞኝ አይደለም ብሎ ሳይጨርሰው
አባት ጣልቃ ገብቶ ልጁን አቋረጠው
አምላክ አላማ አለው ሲፈጥረው ሁሉንም
በም/ክ ነው እንጂ በአጋጣሚ አይደለም
መቼም እንዳትገባ በፈጣሪ ስራ
ከዛሬ በኋላ እንዲህም አታውራ
ቢሆንም አባቴ አምላክ ልክ አይደለም
ብሎ ተናገረ ሳያስበው ምንም
ትክክል መሆኑን ሊያስረዳ ሲቃጣው
አንዲት ፍሬ ወድቃ ግንባሩን መታችው
አባትም አየና ይናገር ጀመረ
አልሰማም አልክ እንጂ ነግሬህ ነበረ
ልክ አንተ እንዳልከው ይሄ የሾላ ፍሬ ዱባን ቢያክል ኖሮ
ዛሬ ሞተህ ነበር አብቅቶልህ ኑሮ
ስለዚህ አትግባ በሱ ስራ ድንገት
ምክንያቱ ከገባህ ይከተላል ቅጣት

ቀርበን እንስተካከል
አንድ ሰው ጸጉሩን ሊስተካከል ወደ አንድ ጸጉር ቤት ይሄዳል ተራው ደርሶም ጸጉሩን መስተካከል ይጀምራል:: በመካከልም ከፀጉር አስተካካዮ ጋር መጨዋወት ይጀምራሉ ::
ጸጉር አስተካካዮ :- ወንድሜ ግን እግዚአብሔር ያለ ይመስልሃል? ሲል ይጠይቀዋል
ተስተካካዮ :- "አዎና አለ እንጂ በደንብ ነዋ" ሲል ይመልስለታል
ጸጉር አስተካካዮ:- አይ አይ የለም ቢኖርማ ይህ ውሉ ተንኮለኛ ይህ ሁሉ ውሸታም ይህ ሁሉ አመንዝራ ይኖር ነበር? አየኸ የለም ማለት ነው:: ...ብሎ በኩራት ተነፈሰ.....................
ተስተካካዮም ግራ ገብቶት ዝም አለ በመጨረሻም ተስተካክሎ ሲጨርስ ልብሱን አራግፎ ገንዘቡን ከፍሎ ከጸጉር ቤቱ ይወጣ........
በመንገድም ሲሄድ ብዙ ሰዎች ጸጉራቸውን ሳይስተካከሉ ተንጨብርረዘው ሲሄዱ አየና በጣም ተገርሞ በፍጥነት ወደ አስተካካዮ ይመለሳል
ተስተካካዮ:-ወንድሜ በሀገሩ ጸጉር አስተካካይ የለም እንዴ? ...አለው
ጸጉር አስተካካዮ :-አረ ሞልተናል አንተንስ ያስተካከልኩክ እኛ ፀጉር አስተካካዮች ስላለን አይደለም እንዴ?.......... አለው
ተስተካካዮ :- ታድያ እናንተ ጸጉር አስተካካዮች ካላችሁ ለምን ብዙ ሰዎች ተንጨብረው ይዞራሉ ?...... ሲል ይጠይቀዋል
ጸጉር አስተካካዮ:- እሱ እንኳን የኛ ችግር አይደለም ለመስተካከል ወደኛ ካልመጡ ያለ ፍቃዳቸው ቆርጠን ልናስተካክላቸው አንችልም እነርሱ መቆረጥን ጠልተው ተንጨብርገው ስለዞሩ እኛ ጸጉር ቆራጮች የለንም ማለት አይደለም::
በጣም ጥሩ አየህ እግዚአብሔርም ሳይኖር ቀርቶ ሳይሆን እኛ ወደ እርሱ ቀርበን ከክፋታችን ሁሉ አስተካክለን ስላላልነው ነው !!:: ታስታው እንደሆነ መጻዕጉን እንኳን ልትድን ትወዳለህን ብሎ አስፈቅዶ ነው ያዳነው::
ኦኦኦ.........በጣም ልክ ነህ ይቅርታ አድርግልኝ
"ወደ ንሰሐ አባቶቻችን
ቀርበን እንስተካከል"