✝እንኳን ወደ ኤልሮኢ channel መጡ
ኤልሮኢ ማለት በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት ማለት ነው።✝✝✝✝✝✝
በቻናላችን ✝ ወቅታዊ መዝሙር
✝ ምስባክ
✝ ወንጌል
✝ መንፈሳዊ ምክሮች
ይለቀቃሉ።
👇👇👇👇👇👇
👉 @aleroe 👈
👆👆👆👆👆👆
ኤልሮኢ ማለት በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት ማለት ነው።✝✝✝✝✝✝
በቻናላችን ✝ ወቅታዊ መዝሙር
✝ ምስባክ
✝ ወንጌል
✝ መንፈሳዊ ምክሮች
ይለቀቃሉ።
👇👇👇👇👇👇
👉 @aleroe 👈
👆👆👆👆👆👆
✝✝መዝሙር በእንተ ልደቱ✝✝
✝በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ(×2)
ቤዛ ኩሉ ዓለም(×2) ዮም ተወልደ(×2)
✝እስመ እም ዘርዓ ዳዊት ዘመፃ(×2)
በቤተልሄም ዘይሁዳ በቤተልሄም ዘይ(×2)
✝ውስተ ማህፀነ ድንግል አደረ ማህፀነ ድንግል(×2)
ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ (×2)በጎል ተወልደ(×2)
✝ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እም ቅድስት ድንግል(×2)
ርእይዎ ኖሎት (×2)አእኮትዎ መላእክት(×2)
✝መድኃኒነ ተወልደ ነዋ(×2)
ይእዜኒ ለሠላም ንትልዋ (×2)
@aleroe

#በበረሃው_በሃሩሩ
በበረሃው በሃሩሩ
በሚያስፈራው በባሕሩ
እስራኤልን የታደገው
በክንፎቹ የጋረደው ሚካኤል ነው
ሚካኤል ነው - - - - አፅናኝ ደጋፊዬ
ሚካኤል ነው - - - - በዱር በበረሃ
ሚካኤል ነው - - - - ነፍሴን ያረካልኝ
ሚካኤል ነው - - - - ከአለቱ ውሃ
የፊቴ ፈገግታ የውስጤ ፍስሐ
ከአምላክ የተሰጠኝ በረከት አምሐ
አዝ
ሚካኤል ነው - - - - መብረቅ ያወረደው
ሚካኤል ነው - - - - ጠላት ድል የነሳው
ሚካኤል ነው - - - - የባህራን ወዳጅ
ሚካኤል ነው - - - - ሀዘኑን ያስረሳው
ቤቱን የሰራለት በእግሮቹ ያቆመው
እንደ እናት እንደ አባት ደግሶ የዳረው
አዝ
ሚካኤል ነው - - - - ያሳደገኝ መልአክ
ሚካኤል ነው - - - - በፅድቅ የመራኝ
ሚካኤል ነው - - - - ስደክም ያገዘኝ
ሚካኤል ነው - - - - ስወድቅ ያነሳኝ
በችግሬ ሁሉ የቀደመልኝ
ሚካኤል እርሱ ነው ከጥልቁ ያወጣኝ
አዝ
ሚካኤል ነው - - - - ክሴን ያስቀደደ
ሚካኤል ነው - - - - የበደሌን እዳ
ሚካኤል ነው - - - - በአማላጅነቱ
ሚካኤል ነው - - - - ያዳነኝ ከፍዳ
በመንገዴ ሁሉ እኔን እየረዳ
ፍቅሩን ጽፎት አልፏል በልቤ ሰሌዳ
💚 @aleroe 💚
በበረሃው በሃሩሩ
በሚያስፈራው በባሕሩ
እስራኤልን የታደገው
በክንፎቹ የጋረደው ሚካኤል ነው
ሚካኤል ነው - - - - አፅናኝ ደጋፊዬ
ሚካኤል ነው - - - - በዱር በበረሃ
ሚካኤል ነው - - - - ነፍሴን ያረካልኝ
ሚካኤል ነው - - - - ከአለቱ ውሃ
የፊቴ ፈገግታ የውስጤ ፍስሐ
ከአምላክ የተሰጠኝ በረከት አምሐ
አዝ
ሚካኤል ነው - - - - መብረቅ ያወረደው
ሚካኤል ነው - - - - ጠላት ድል የነሳው
ሚካኤል ነው - - - - የባህራን ወዳጅ
ሚካኤል ነው - - - - ሀዘኑን ያስረሳው
ቤቱን የሰራለት በእግሮቹ ያቆመው
እንደ እናት እንደ አባት ደግሶ የዳረው
አዝ
ሚካኤል ነው - - - - ያሳደገኝ መልአክ
ሚካኤል ነው - - - - በፅድቅ የመራኝ
ሚካኤል ነው - - - - ስደክም ያገዘኝ
ሚካኤል ነው - - - - ስወድቅ ያነሳኝ
በችግሬ ሁሉ የቀደመልኝ
ሚካኤል እርሱ ነው ከጥልቁ ያወጣኝ
አዝ
ሚካኤል ነው - - - - ክሴን ያስቀደደ
ሚካኤል ነው - - - - የበደሌን እዳ
ሚካኤል ነው - - - - በአማላጅነቱ
ሚካኤል ነው - - - - ያዳነኝ ከፍዳ
በመንገዴ ሁሉ እኔን እየረዳ
ፍቅሩን ጽፎት አልፏል በልቤ ሰሌዳ
💚 @aleroe 💚
#ባሰማት_ጊዜ
ስሙ ገብርኤል የተባለ
ለድንግል ነገራት መልካም ዜና
እንደምትወልደው ወልድን በድንግልና/2/
ባሰማት ጊዜ ቃሉን
ቅዱስ ገብርኤል በለዛ
ድንግል ቀረበች ወደ እርሱ
ፍጹም ትኅትናን ይዛ
ትፀንሻለሽ ሲላት መልአኩ
ፍጹም በልቧ ሳትመካ
እንደ ቃልህ ይሁን አለችው በቃሉ ተማርካ /2/
#አዝ
የዓለም መድኀኒት ነውና
ከአንቺ የሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ
ትሰይሚዋለሽ ስሙንም ብለሽ ኢየሱስ /2/
#አዝ
ዕፁብ ድንቅ ነው ለሁልጊዜ ለ
ድንግል ማርያም የተሰጣት እድል
የአምላክ እናት ሆኖ መመረጥ
ከሴቶች መካከል /2/
#አዝ
ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ
ይገባሻል ለአንቺ ክብርና ምስጋና
የክብር ባለቤት ሁል ጊዜም
ከአንቺ ጋር ነውና /2/
💚 @aleroe
ስሙ ገብርኤል የተባለ
ለድንግል ነገራት መልካም ዜና
እንደምትወልደው ወልድን በድንግልና/2/
ባሰማት ጊዜ ቃሉን
ቅዱስ ገብርኤል በለዛ
ድንግል ቀረበች ወደ እርሱ
ፍጹም ትኅትናን ይዛ
ትፀንሻለሽ ሲላት መልአኩ
ፍጹም በልቧ ሳትመካ
እንደ ቃልህ ይሁን አለችው በቃሉ ተማርካ /2/
#አዝ
የዓለም መድኀኒት ነውና
ከአንቺ የሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ
ትሰይሚዋለሽ ስሙንም ብለሽ ኢየሱስ /2/
#አዝ
ዕፁብ ድንቅ ነው ለሁልጊዜ ለ
ድንግል ማርያም የተሰጣት እድል
የአምላክ እናት ሆኖ መመረጥ
ከሴቶች መካከል /2/
#አዝ
ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ
ይገባሻል ለአንቺ ክብርና ምስጋና
የክብር ባለቤት ሁል ጊዜም
ከአንቺ ጋር ነውና /2/
💚 @aleroe
ኤልሮኢ
21/04/11 ዓ.ም.
መዝሙር ዘኖላዊ
"ኖላዊ ዘመጽአ"
✝በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ፡፡
ዲ/ን ዕብ 13÷17_ፍ.ም
ን/ዲ 1ጴጥ 2÷21_ፍ.ም
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 11÷22_ፍ.ም
የዕለቱ #ምስባክ፦መዝ 79÷1
ኖላዊሆሙ ለእስራኤል አጽምዕ
ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ
ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርአየ።
#ትርጉም፦
ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ
የእስራኤል ጠባቂ አድምጥ
በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ።
የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ 10፥1 - 22
ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ
👉 @aleroe
21/04/11 ዓ.ም.
መዝሙር ዘኖላዊ
"ኖላዊ ዘመጽአ"
✝በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ፡፡
ዲ/ን ዕብ 13÷17_ፍ.ም
ን/ዲ 1ጴጥ 2÷21_ፍ.ም
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 11÷22_ፍ.ም
የዕለቱ #ምስባክ፦መዝ 79÷1
ኖላዊሆሙ ለእስራኤል አጽምዕ
ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ
ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርአየ።
#ትርጉም፦
ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ
የእስራኤል ጠባቂ አድምጥ
በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ።
የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ 10፥1 - 22
ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ
👉 @aleroe
#ለማርያም
ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም
የተዘጋች ደጅ ለዘለአለም
ሕዝቅኤል ብሏል
ንፅህት ናት በእውነት
በፍፁም ድንግል
አብነት አድርገን
እኛም እርሱን
በፍፅም ፍቅር እንዘምራለን
በፍፁም ፍቅር እንዘምራለን
ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም
የዋህት እርግብ ለዘለአለም
ሰላም አብሳሪ
ለጨለማ ሕይወቴ
ብርሃንን አብሪ
እማፀንሻለሁ
ድንግል ለነፍሴ
አደራ ቅድስት አንቺ ነሽ ዋሴ
አደራ ቅድስት አንቺ ነሽ ዋሴ
ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እጅግ የበዛ ነው ለዘለአለም
ያለኝ ፍቅር
አይወሰንም
አይነገርም
በእርሷ ደስ ይለኛል
ሀሴት አደርጋለሁ
ስሟን እየጠራን እንዘምራለን
ስሟን እየጠራን እንዘምራለን
ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም
ነይ ነይ ስላት ለዘለአለም
ቀንና ሌሊት
አትለየኝም
ለእኔስ ቅርቤ ናት
እፁብ እፁብ ብለው
አመሰገኗት
ክብሯን ሊገልፁ ቢያጥራቸው ቃላት
ክብሯን ሊገልፁ ቢያጥራቸው ቃላት
ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም
💚 @aleroe ❤️
ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም
የተዘጋች ደጅ ለዘለአለም
ሕዝቅኤል ብሏል
ንፅህት ናት በእውነት
በፍፁም ድንግል
አብነት አድርገን
እኛም እርሱን
በፍፅም ፍቅር እንዘምራለን
በፍፁም ፍቅር እንዘምራለን
ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም
የዋህት እርግብ ለዘለአለም
ሰላም አብሳሪ
ለጨለማ ሕይወቴ
ብርሃንን አብሪ
እማፀንሻለሁ
ድንግል ለነፍሴ
አደራ ቅድስት አንቺ ነሽ ዋሴ
አደራ ቅድስት አንቺ ነሽ ዋሴ
ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እጅግ የበዛ ነው ለዘለአለም
ያለኝ ፍቅር
አይወሰንም
አይነገርም
በእርሷ ደስ ይለኛል
ሀሴት አደርጋለሁ
ስሟን እየጠራን እንዘምራለን
ስሟን እየጠራን እንዘምራለን
ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም
ነይ ነይ ስላት ለዘለአለም
ቀንና ሌሊት
አትለየኝም
ለእኔስ ቅርቤ ናት
እፁብ እፁብ ብለው
አመሰገኗት
ክብሯን ሊገልፁ ቢያጥራቸው ቃላት
ክብሯን ሊገልፁ ቢያጥራቸው ቃላት
ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም
💚 @aleroe ❤️
አንድ ወጣት ድምፁን ከፍ አድርጎ ድንግል ማርያም አታማልድም አታማልድም እያለ በአደባባይ ይጮሃል:: ከዛ ድንገት እያለፉ የነበሩ አንድ አባት ድምጽ ይስሙና ወደ ወጣቱ ጠጋ ብለው ልጄ አንዴ ላስቸግርህ ከዛ ፊት ለፊት ካለው ሱቅ 1 ኪሎ ብርትኳን አምጣልኝ አሉት ወጣቱም እሽታውን ገለፀላቸ አባትም ብርትኳኑን አንዳችም ሳያስቀሩ ከበሉ በኃላ ልጄ ብርትኳኑ እንዴት ነው? ይጣፍጣል አይደል ?አሉት ወጣቱም አንዴ ሰውዬ ያምዎታል እንዴ ብርትኳኑን እኮ ብቻወትን ነው የበሉት እና እንዴት ጣሙን ላውቅ እችላለሁ አላቸው በንዴት
አባም አየህ ልጄ ልክ እንደዚህ ብርትኳን የድንግል ማርያም ጣዕሟ አልገባህም ስለዚህ ልጄ ወደ ቤቷ ግባ ጣዕሟንም ቅመሰው ያኔ የድንግል ጣዕም ይገባሃል አሉት ይባላል፡፡
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
እኛስ ተመርጠን ምልጃዋን ተቸርን፣ ረድኤቷን ቀመስን
ክብር ምስጋና ይግባት🙏🙏🙏🙏🙏
አባም አየህ ልጄ ልክ እንደዚህ ብርትኳን የድንግል ማርያም ጣዕሟ አልገባህም ስለዚህ ልጄ ወደ ቤቷ ግባ ጣዕሟንም ቅመሰው ያኔ የድንግል ጣዕም ይገባሃል አሉት ይባላል፡፡
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
እኛስ ተመርጠን ምልጃዋን ተቸርን፣ ረድኤቷን ቀመስን
ክብር ምስጋና ይግባት🙏🙏🙏🙏🙏
#እስከ_መቼ_ነው?
እውነት ቅዱስ ጊዮርጊስን የምንወደው ከሆነ ድምፃችንን እናሰማ እንቃወም፡፡ እስከ መቼ ነው በቅዱሱ አባታችን ስም የሚነገደው? መቼ ነው ታዲያ ስዕሉ የሚከበረው መቼ መቼ? እስከ መቼ ነው ጭፈራ ቤት እና የአህዛብ መቀለጃ ሚያደርጉት፡፡ የቅዱሱ አባታችን ምስል እና ስም ማስነሳት ያቃተን ለምንድነው? ወይስ አንወደውም? ለምን ዝም አልን? መቼስ አያገባኝም አንልም ስለ ዶክተር አብይ እንኳን ስንቱ ነው #ዋ ማንም እንዳይነካዉ እያለ Post የሚያደርገው፡፡ እስቲ ማናችን ነን ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠበቃ የቆምነዉ? እስቲ ማናችን ነን የተከራከርነው? መልሱን እናውቀዋለን፡፡ አሁንም ቢሆን ጊዜው አልረፈደም ሁላችንም FB ላይ post አናድርግ ለሚመለከተው አካል እናድርስ በእርግጥ እኛን ነው የሚመለከተው ነገር ግን መፍትሄ የሚሰጠን አካል ያስፈልገናል። ቅዱስ ስሙ እና ምስሉ ይነሳ ብለን ድምፃችንን እናሰማ መቼም በአባታችን በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ሲነገድ ማየት እሚያስደስተው የለም።
ይህን ያነበበ፣ያየ በሙሉ በተለያዩ ድህረ-ገፅ ላይ POST AND SHARE አድርጉ አደራችሁን።

🔥እሳቱ 🔥
#ሙሐዘ_ጥበባት_ዲያቆን_ዳንኤል_ክብረት
ሰውዬው እሳት እያነደደ የሚኖር ነበረ፡፡
ጌቶቹ ሰፊ ግቢ ነበራቸውና በግቢው መካከል እሳት እያነደደ ቀን ቀን ለምግብ ማብሰያ፣ ማታ ማታ ደግሞ ለመሰባሰቢያ ይጠቅም ነበረ፡፡
ከእሳቱ ጋር ብዙ ጊዜ ስለኖረ ‹እሳቱ› ብለው ይጠሩት ነበር፡፡
እሳቱም ከእሳቱ ጋር የተፈጠረ እስኪመስል ድረስ እሳቱን ተላምዶት ነበር፡፡
ከእርሱ መወለድ በፊት እሳት ምድር ላይ የተፈጠረ አይመስለውም፤ እርሱ ሲሞትም ምድር በብርድ የምታልቅ ይመስለዋል፡፡
አንድ ቀን ከጌቶቹ ጋር ተጣላ፤ አኮረፈ፡፡ ‹ቆይ እሳቱን ማን እንደሚያነድላቸው አያለሁ› አለና ግቢውን ጥሎ ወደ ማዶ ተራራ ወጣ፡፡ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ ጥሎት የሄደውን ግቢ ባሻገር መቃኘት ጀመረ፡፡
ልክ ሲመሽ እሳት በግቢው ውስጥ ቦግ ብሎ ሲነድ ተመለከተ፡፡
ይሄኔ ‹እንዴ! እኔ ሳልኖር እሳቱን ማን አነደደላቸው?› አለ እሳቱ ገርሞት፡፡
እሳቱ እሳት ሲያነድ ያዩት ቤተኞች እንዲያውም ከእርሱ በተሻለ እሳቱን አቀጣጠሉት፡፡
የሚነድ እሳቱ ግን እርሱ ከሌለ እሳት የሚነድ አይመስለው ነበር፡፡
ከእርሱም ሌላ እሳት ማንደድ የሚችል ሰው አለ ብሎ አያምን ነበር፡፡
እርሱ ካዳፈነበት ቦታ በቀር እሳት የሚገኝ አልመሰለውም ነበር፡፡
እርሱ ሳይኖር እሳት ሲነድ ያየው እሳቱ ‹ለካስ ሌላም እሳት አንዳጅ አለ› አለ ይባላል፡፡
***
ከፈጣሪ በታች የማይተካ ማንም የለም፡፡ አንዳንድ ሰው አንድን ነገር ለብዙ ጊዜ ይዞት ሲቆይ የፈጠረውና የሚመግበው እርሱ ብቻ መስሎ ይሰማዋል፡፡ እርሱ ከሌለ ያ ነገር የሚሠራ አይመስለውም፡፡
‹የተዋሱት ዕቃ በእጅ ላይ ሲቆይ የራስ ይመስላል› እንደሚባለው፡፡ ግን ሌላም እሳት አንዳጅ አለ፡፡
አውራ ዶሮ ፀሐይ የምትወጣው እርሱ ሲጮኸ ይመስለዋል፡፡ እርሱ ግን የፀሐይዋን መውጣት ይነግረናል እንጂ ፀሐይዋን አያወጣትም፡፡ ለውጥ መምጣቱን መናገርና ለውጥን ማምጣት የተለያዩ ናቸው፡፡
‹ያለ እኛ አትኖሩም› የሚሉን ነበሩ፡፡ ‹ያለ እኛ ለውጡ አይኖርም› የሚሉን እንዲተኳቸው አንፈልግም፡፡
#በኢትዮጵያ_ውስጥ_የማይተካ_ሚና_ያላት_ራሷ_ኢትዮጵያ_ብቻ_ናት፡፡
👉@aleroe👈

✝✝✝ይነበብ✝✝✝
የነብያት ፆም ወይም የገና ፆም ነብያት 40 ቀን ፆመው ለምን እኛ 44 ቀን እንፆማለን??
አርባው ዕለታት የነቢያት ጾም ሲሆን ከቀሩት ከ4ቱ ሦስቱ ስምዖን ጫማ ሰፊው (አብርሃም ሶሪያዊ) የጾሙትን ጾም ለማሰብ ነው፡፡ በሀገሩ ያሉ አሕዛብ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ‹‹ የሠናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ተነቅለህ ወዲያ ሂድ ብትሉት እንዳላችሁት ይሆንላችኋል ›› ይላል እንግዲያውስ ይህንን በተግባር ያሳዩንና እኛም በእነርሱ እምነት እንመን በማለት ከሀገሩ ንጉሥ ዘንድ በመቅረብ ሊቀ ጳጰሱን አብርሃምን ጠየቁት አባታችንም ሦስት ዕለታትን እንዲሰጡት ነግሯቸው ወደ እመቤታችን ሥዕል ፊት ቀርቦ ይህንን ተአምር ታደርግለት ዘንድ ተማጸናት ተለማኝቱም ይህን ድንቅ ተአምር ይፈጸምልህ ዘንድ ምን ማድረግ እንዳለብህ የሚያስረዳህ ስምዖን የሚባል ሰው አለ ከመንገድ ዳር ተቀምጦ ጫማ ሲሰፋ ታገኘዋለህ አለችው፡፡ አባታችንም ወደ ርሱ ሄዶ የሆነውን ሁሉ ነገረው ቅዱስ ስምዖን ግን ‹‹ እመቤቴ ሆይ እኔነቴን ስለምን ገለጥሽኝ በዚህ መኖሬን አልፈቀድሽውምን እንግዲያውስ ትዕዛዝሽን እፈጽማለሁ በዓቴን ግን ዕለቃለሁ ›› አለ ይህም ቅዱሳን ውዳሴ ከንቱን ስለማይወዱ ክብራቸው በተገለጠበት ቦታ ስለማይኖሩ ነው፡፡ በመቀጠልም ሊቀ ጳጳሱን ሦስት ቀን ያህል እንጹም ሦስተኛውም ቀን በተፈጸመ ጊዜ ህዝቡን ሰብስበህ በተራራው ሥር እግዚኦታ ታደርሳለህ ተአምሩም ይፈጸምልሃል በማለት ነገረው እንደተነገረውም ከሦስት ቀን ጾም በኋላ ሕዝቡን ሰብስቦ እግዚኦታ ሲያደርስ ቅዱስ ስምዖንም ከመሀከላቸው ሆኖ ‹‹ጌታ ሆይ የእነርሱ ክብር እንዲገለጥ ብለው አይደለም የአንተ ክብር እንዲገለጥ አሕዛብም በአንተ ያመልኩ ዘንድ ነውና እባክህን ስማቸው›› እያለ ይማጸንላቸው ጀመር ተራራው ከሥሩ ተነስቶ ክርስቲያኖችን ያስቸግር የነበረውን ባሕር ደፍኖላቸዋል በዚህም አሕዛብ አምነዋል በባህሩ ምክንያት ተለያይተው የነበሩ ክርስቲያኖችም ተገናኝተዋል፡፡ ስለዚህ እንዲህያለ ድንቅ ተአምር የተፈጸመበት ጾም ስለሆነ ከነቢያት ጾም ጋር በአንድነት እንድንጾመው አባቶች አዘዋል፡፡ ቁጥሩም 43 ይሆናል፡፡ 44ተኛ ሆና የምትጾመው ጾመጋድ (ጾመ ገሓድ) ናት፡፡

#የዓለምን_በደል
የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ
ዘጠና ዘጠኙን መላእክት ትቶ
ጽድቅን ለመፈጸም በደልን አጥፍቶ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
- - - - - - አዝ - - - - - -
የሰማያት ሰማይ የማይችሉት ንጉሥ
ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ
ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደ ፈረስ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
- - - - - - አዝ - - - - - -
ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ
ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ
እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
- - - - -አዝ - - - - -
ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቀን ሲመሠርት
መጣ በደመና ሰማያዊው አባት
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
💚💛❤️✝@aleroe✝💚💛❤️
#የዓለምን_በደል
የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ
ዘጠና ዘጠኙን መላእክት ትቶ
ጽድቅን ለመፈጸም በደልን አጥፍቶ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
- - - - - - አዝ - - - - - -
የሰማያት ሰማይ የማይችሉት ንጉሥ
ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ
ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደ ፈረስ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
- - - - - - አዝ - - - - - -
ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ
ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ
እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
- - - - -አዝ - - - - -
ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቀን ሲመሠርት
መጣ በደመና ሰማያዊው አባት
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ
💚💛❤️✝@aleroe✝💚💛❤️
ኤልሮኢ
#ድንግል_ፈጣሪዋን_ወለደችው
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀቀለለችው
የለምና ስፍራ ለንግዶች ማረፊአ
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደርያ /2/
#አዝ
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ
ወረደ መልአኩ ምስራች ሊያወራ
የህፃኑ ክብር በምድር አበራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
#አዝ
ሰብአ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
ወርቅ እጣን ከርቤዉን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ላለም ተናገሩ ንጉስ መወለዱን
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
#አዝ
የይሁዳ ምድር ምስጋና ተመላ
ንጉስ መቷልና ከናዝሬት ገሊላ
ታምሩን ትናገር ቤተልሄም ታዉራ
ዝማሬ ሲወጣ ከርስቱ ቆጠራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
#አዝ
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ አንደ ሰዉ
በጠባቡ ደረት አዳምን መሰለዉ
ገረማት ጥበቡ ታናሹአን ሙሽራ
ተዋህዳልና ቃል ከ ስጋ ጋራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
💚 @aleroe 💚
💛 @aleroe 💛
❤️ @aleroe ❤️
#ድንግል_ፈጣሪዋን_ወለደችው
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀቀለለችው
የለምና ስፍራ ለንግዶች ማረፊአ
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደርያ /2/
#አዝ
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ
ወረደ መልአኩ ምስራች ሊያወራ
የህፃኑ ክብር በምድር አበራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
#አዝ
ሰብአ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
ወርቅ እጣን ከርቤዉን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ላለም ተናገሩ ንጉስ መወለዱን
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
#አዝ
የይሁዳ ምድር ምስጋና ተመላ
ንጉስ መቷልና ከናዝሬት ገሊላ
ታምሩን ትናገር ቤተልሄም ታዉራ
ዝማሬ ሲወጣ ከርስቱ ቆጠራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
#አዝ
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ አንደ ሰዉ
በጠባቡ ደረት አዳምን መሰለዉ
ገረማት ጥበቡ ታናሹአን ሙሽራ
ተዋህዳልና ቃል ከ ስጋ ጋራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
💚 @aleroe 💚
💛 @aleroe 💛
❤️ @aleroe ❤️
ኤልሮኢ፡
📚ዳንኤል 📚ክብረት📚
ጊንጥ አና ጊንጠኞች!!
ብዙ ጊዜ ጊንጥ የሚለውን ቃል ስሰማ ብዙም ትኩረት አልሰጠውም ነበር ዛሬ ግን ጊንጥ አሪፍ ነገር አስተማረኝ፡፡ ይህንን እንድል ያስገደደኝ የዛሬው ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ አጭር ታሪክ ነው ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡
አንድ ሽማግሌ ውሃ ውስጥ ሊሰምጥ ያለ ጊንጥ ያዩና ሊያድኑት ይፈልጋሉ፡፡ ከዚያም ጊንጡን ከውሃው ለማውጣት እጃቸውን ዘርግተው አነሱት በዚህ ጊዜ ጊንጡ ነደፋቸው እሳቸውም ደንግጠው ለቀቁት ጊንጡም ተመልሶ ወደውሃው ገባ፡፡ ሽማግሌው አሁንም የጊንጡን ውሃ ውስጥ መስመጥ ተመልክተው ድጋሚ እጃቸውን ለእርዳታ ዘረጉለት አሁንም በድጋሚ ጊንጡ ነደፋቸው ሲለቁት አሁንም ውሃ ውስጥ ገባ፡፡ ይህንን የሽማግሌውን ትእይንት የሚመለከት አንድ ሰው ወደ ሽማግሌው ጠጋ ይልና ‹‹ይህ እኮ ክፉ ፍጥረት ነው ጊንጥ እሱን ለማዳን ሲሉ እርሶ እየተጎዱ እኮ ነው›› አላቸው።
ሽማግሌውም እንዲህ ሲሉ መለሱ ‹‹የጊንጡ ተፈጥሮ መናደፍ ነው፡ የኔ ተፈጥሮ ደግሞ መርዳትና ማገዝ ነው፡ ስለዚህ ተፈጥሮዬ ክፉ አደለምና ጊንጡን ከመርዳት አላቋርጥም አረዳዴን ግን አስተካክላለሁ›› አሉና ጥቂት አሰብ አድርገው ተነስተው ከዛፉ ላይ አንድ ቅጠል ቀንጥሰው በቅጠሉ ጊንጡን ይዘው አወጡትና ህይወቱን አተረፉለት፡፡
እኛም እንዲህ ነን ሰውን ለመርዳት ስንሄድ ብዙ ጊንጦች ይነድፉናል፡ ደግ ልናደርግ ስንጓዝ ብዙ እንቅፋቶች ይመቱናል፡፡ ነገር ግን ጊንጡ እንዳይነድፈን እናደርጋለን እንጂ እንቅፋቱ እንዳይመታን እንጠነቀቃለን እንጂ እንዴት ደግ ማድረግ እናቆማለን ???
አንተም አንቺም ሁላችንም እዚህ ምድር ላይ ያለን ሰዎች በሙሉ ስንፈጠር ደግና መልካም ነን፡፡ ግን ሰውን ክፉ የሚያደርገው ተፈጥሮው ሳይሆን መጥፎ አጋጣሚ ነው፡፡ ለዛ እኮ ነው በነዚህ ጊንጦች ስለተነደፍን መልካም ለማድረግ ቅስቀሳ በጎ ለመስራት ማጣራት መጠራጠር በሌላ አይን መመልከት ጀመርን፡፡
እስኪ የዛሬዋን አዲስ ቀናችንን እንዲህ ብንውላትስ ሰው ስንረዳ እንደጊንጥ በሚሆኑ ሰዎች ተሸንፈን መልካም ከማድረግ ከምንቆጠብ የምንረዳበትን መንገድ ለይተን ብናውቅስ፡፡ በነገራችን ላይ ለሰው በጎ ማድረግ ሲባል በገንዘብ ብቻ ይመስለናል አይደለም በየቤቱ ገንዘብ ኖሮት ሰው የናፈቀው ህሊና አለ ስለዚህ አንዳንዶች ፈገግታችንን አንዳንዶች እኛነታችንን አንዳንዶች መሰማትን ይፈልጋሉና በየደረስንበት ለመልካም ነገር ጊንጥ ፈርተን እምቢ እንዳንል፡፡
መልካም የምታደርጉ ሁሉ ግን ጊንጡንም ቢሆን ከማዳን አትቦዝኑ።
✝ @aleroe ✝

#እንዘምር
እንዘምር/2/በእልልታ
ለመድሀኔዓለም ለሰራዊት ጌታ
#አዝ
የጠፋውን ሊያድን ወረደ ከላይ
እንዘምር በእልልታ
የበጎች እረኛ አምላክ አዶናይ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
ትንቢት ተናገሩ ነቢያት በሙሉ
እንዘምር በእልልታ
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
ገብርኤል ተልኮ ልደቱን አብሳሪ
እንዘምር በእልልታ
ስጋለብሶ ሲታይ ረቂቅ ፈጣሪ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
ብርሃን ወጣላቸው ለአዳም ልጆች ሁሉ
እንዘምር በእልልታ
የጌታን መወለድ በተስፋ ላመኑ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
በሰማይ በምድር እርቅ ተወጠነ
እንዘምር በእልልታ
ስለተወለደ እግዚአብሄር ምስሌነ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
አምላክ ስጋ ለብሶ እንዴት ተዋረደ
እንዘምር በእልልታ
መጠጊያ ቦታ አጥቶ በጎል ተወለደ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
የሚለብሰው አጥቶ የብርሀናት ጌታ
እንዘምር በእልልታ
ኮባ ቅጠል ለብሶ እጅግ ተንገላታ
እንዘምር በእልልታ
@aleroe
እንዘምር/2/በእልልታ
ለመድሀኔዓለም ለሰራዊት ጌታ
#አዝ
የጠፋውን ሊያድን ወረደ ከላይ
እንዘምር በእልልታ
የበጎች እረኛ አምላክ አዶናይ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
ትንቢት ተናገሩ ነቢያት በሙሉ
እንዘምር በእልልታ
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
ገብርኤል ተልኮ ልደቱን አብሳሪ
እንዘምር በእልልታ
ስጋለብሶ ሲታይ ረቂቅ ፈጣሪ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
ብርሃን ወጣላቸው ለአዳም ልጆች ሁሉ
እንዘምር በእልልታ
የጌታን መወለድ በተስፋ ላመኑ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
በሰማይ በምድር እርቅ ተወጠነ
እንዘምር በእልልታ
ስለተወለደ እግዚአብሄር ምስሌነ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
አምላክ ስጋ ለብሶ እንዴት ተዋረደ
እንዘምር በእልልታ
መጠጊያ ቦታ አጥቶ በጎል ተወለደ
እንዘምር በእልልታ
#አዝ
የሚለብሰው አጥቶ የብርሀናት ጌታ
እንዘምር በእልልታ
ኮባ ቅጠል ለብሶ እጅግ ተንገላታ
እንዘምር በእልልታ
@aleroe