ኤልሮኢ:
ግንቦት_25 /09/2011
፶፩ እምትንሣኤ እስከ ዕርገት በትንሣኤ እሁድ መዝሙር ይትፌሣሕ፡፡
#ምስባክ
ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም
ወከመ ኀያል ወኅዳገ ወይን
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ፡፡
#ትርጉም
እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደ ሚነቃ ተነሣ
የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኀይለኛም ሰው
ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ፡፡
#መዝ_77:65-66
#ወንጌል
#ማቴዎስ_28:1-ፍጻሜ፡ወሠርክ ሰንበት ለጸቢሖ እሁድ"በሰንበትም ማታ ለእሁድ አጥቢያ ማርያም መግደላዊትና ሁለተኛዋ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ፡፡.............
................................................ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ጻፈው፡፡"
#ማርቆስ_16:1-ፍጻሜ፡ወሐለፈት ሰንበት"ሰንበትም ባለፈች ጊዜ ማርያም መግደላዊት የያዕቆብ እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሥጋዉን ሊቀቡ ሽቱ ገዙ፡፡.......................................................................................ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ በአራት ዓመት ነው፡፡"
#ሉቃስ_24:1-13፡ወበእሑድ ሰንበት"ከሳምንቱም በመጀመሪያዪቱ ቀን ያዘጋጁትን ሽቶ ይዘው እጅግ ማልደው ወደ መቃብሩ ሄዱ ሌሎች ሴቶችም አብረዋቸው ነበሩ፡፡....................
................................................ጴጥሮስም ተነሣ ወደ መቃብርም ፈጥኖ ሄደ ዝቅ ብሎም በተመለከተ ጊዜ በፍታውን ለብቻው ተቀምጦ አየ የሆነውን እያደነቀ ተመለሰ፡፡"
👉 @aleroe

"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
………✍ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ አብረው ይፀልያሉ አንደኛው ፀሎቱ ተመለሰለት አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ። በዚህ ጊዜ ፀሎቱ ያልተመለሰለት ሰው "ጌታ ሆይ ሁለታችንም እኩል ፀልየን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ ከለከልኝ ለምንድ ነው?" አለው። እግዚዘብሔርም "ለእርሱ ባልሰጠው ይጠፋል፣ ላንተ ከሰጠሁህ ደግሞ ትጠፋለህ" አለው ይባላል።
እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችን በመስጠት፣ አንዳችንን በመከልከል ዕድሜያችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሳቱም ሁለቱም በፍቅር ነውና በልመናችን በፀሎታችን የአንተ ፈቃድ ይሁንልን ማለት ተገቢ ነው። ስለሁሉም የመድኃኔዓለም ስም የተመሰገነ ይሁን። አሜን!!
እንኳን ለመድኃኔዓለም ወርሀዊ በዓል
በሰላም አደረሳችሁ!!
@aleroe

ይህን ያውቁ ሮሯል!!!
በተለምዶ ‹‹ አርባ አራቱ ታቦት›› እያልን የምንጠራቸው አብያተ ክርስቲያናት ያሉት በጐንደር ከተማ ሲሆን ስማቸውም የሚከተለው ነው፡፡
1. ፊት ሚካኤል
2. ፊት አቦ
3. አደባባይ ኢየሱስ
4. ግምጃ ቤት ማርያም
5. እልፍኝ ጊዮርጊስ
6. መድኃኔዓለም
7. ቅዱስ ገብርኤል
8. ጠዳ እግዚአብሔር አብ
9. አባ እንጦንዮስ
10. ደብረ ብርሃን ሥላሴ
11. አደባባይ ተክለሃይማኖት
12. ሠለስቱ ምእት
13. ልደታ ለማርያም
14. አጣጣሚ ሚካኤል
15. አቡነ ኤውስጣቴዎስ
16. ቅዱስ ሩፋኤል
17. ደፈጫ ኪዳነ ምሕረት
18. ቁስቋም ደብረ ፀሐይ
19. መጥምቁ ዮሐንስ
20. በኣታ ለማርያም
21. ቅዱስ ቂርቆስ
22. ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
23. አባ ጃሌ ተ/ሃይማኖት
24. ፈንጠር ልደታ
25. ደብረ ምጥማቅ ማርያም
26. አባ ዐቢየ እግዚእ
27. ቅዱስ ፋሲለደስ
28. ሐዋርያት
29. ቀሃ ኢየሱስ
30. አርባዕቱ እንስሳት
31. ጎንደሮች ጊዮርጊስ
32. ጎንደሮች ማርያም
33. አበራ ጊዮርጊስ
34. ብላጅግ ቅዱስ ሚካሌል
35. አባ ሳሙኤል
36. አይራ ሚካኤል
37. ጓራ ዮሐንስ
38. ወረንግቦ ጊዮርጊስ
39. አሮጌ ልደታ
40. አዘዞ ተ/ሃይማኖት
41. ምንዝሮ ተ/ሀይማኖት
42. ሰራራ ማርያም
43. ዳሞት ጊዮርጊስ
44. ጫጭቁና ማርያም
በቃል ያለ ይረሳል በ………………………

02/10/11
#መዝሙር በሰንበት ዐርገ ሐመረ
#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡
ዲ/ን ሮሜ10÷1-ፍ.ም
ን/ዲ 1ጴጥ 3÷15-ፍ.ም
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 1÷1-12
፡#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 45÷5
ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ።
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን።
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።
#ትርጉም፦
እግዚአብሔር በዕልልታ ዐረገ
ጌታችን በመለከት ድምፅ ዐረገ
ዘምሩ ለአምላክችን ዘምሩ።
#ወንጌል
#ሉቃ 24÷45-ፍ ም
#ቅዳሴ
:-ዘዲዮስቆሮስ
@aleroe
02/10/11
#መዝሙር በሰንበት ዐርገ ሐመረ
#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡
ዲ/ን ሮሜ10÷1-ፍ.ም
ን/ዲ 1ጴጥ 3÷15-ፍ.ም
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 1÷1-12
፡#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 45÷5
ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ።
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን።
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ።
#ትርጉም፦
እግዚአብሔር በዕልልታ ዐረገ
ጌታችን በመለከት ድምፅ ዐረገ
ዘምሩ ለአምላክችን ዘምሩ።
#ወንጌል
#ሉቃ 24÷45-ፍ ም
#ቅዳሴ
:-ዘዲዮስቆሮስ
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:(ስነ ፅሁፍ)
ዳግም_ልደት
እሳት ወይስ ውሀ
ሀዘን ወይ ፍስሀ
አንዱን የግድ ምረጥ
ልብህ ባንዱ ይቁረጥ
ወይ ብረድ ወይ ተኩስ ፡በመሀል አትልፋ
ለብ ብለህ ካፉ ላይ፡ ውጭ እንዳትተፋ
ጨለማ ወይ ብርሀን
አንዱን ምረጥ ዝገን
ሞት ወይስ ህይወት
ሀሰት ወይስ እውነት
መዝሙር ወይስ ኮንሰርት
(አንዱን የግድ ምረጥ...)
ጣዖት ወይስ ታቦት
ሲዖል ወይስ ገነት
ይሄኔ አስተውለህ
አስበህ መርምረህ
ካላወክ ጠየቀህ
በውነት በቅንነት ፡ በበጎ ህሊና
አንዱን ምረጥና ፡ በንፁህ ልቦና
ተወለድ ወንድሜ ዳግም እንደገና ፡፡
@aleroe
ዳግም_ልደት
እሳት ወይስ ውሀ
ሀዘን ወይ ፍስሀ
አንዱን የግድ ምረጥ
ልብህ ባንዱ ይቁረጥ
ወይ ብረድ ወይ ተኩስ ፡በመሀል አትልፋ
ለብ ብለህ ካፉ ላይ፡ ውጭ እንዳትተፋ
ጨለማ ወይ ብርሀን
አንዱን ምረጥ ዝገን
ሞት ወይስ ህይወት
ሀሰት ወይስ እውነት
መዝሙር ወይስ ኮንሰርት
(አንዱን የግድ ምረጥ...)
ጣዖት ወይስ ታቦት
ሲዖል ወይስ ገነት
ይሄኔ አስተውለህ
አስበህ መርምረህ
ካላወክ ጠየቀህ
በውነት በቅንነት ፡ በበጎ ህሊና
አንዱን ምረጥና ፡ በንፁህ ልቦና
ተወለድ ወንድሜ ዳግም እንደገና ፡፡
@aleroe
ኤልሮኢ:
ሐመረ ኖህ ነሽ
============
ሐመረ ኖህ ነሽ
የምህረት ቃል ኪዳን የተገባልሽ
ትውልድ ይህን አምኖ
ያከብርሻል አልቆ እና አግኖ
አዝ----------------//
በእግዚአብሔር ሀሳብ ነበርሽ በህሊና
ዓለምን ሳይፈጥር አዳምን ሳይሠራ
ሁሉን የናፈቀሽ የወጣብሽ ፀሀይ
ንግሥት ነሽ ድንግል እሙ ለአዶናይ
አዝ----------------//
ያንን የጭንቅ ቀን የጥፋቱን ዘመን
አልፈነዋል ባንቺ በአማናዊት ፅዮን
ምንጭ ነሽ የእርካታ የድህነት መፍለቂያ
የዘለዓለም እረፍት አንባ እና ማረፊያ
አዝ----------------//
የነቢያት ተፈጽሞ አየን
አንቺ ምክንያት ሆነሽ ለመዳናችን
ድምፅሽን ጠላት ይሸበራል
እኛ ግን ሰምተነው በሀሴት ዘለናል
አዝ----------------//
አንዴ በገባልሽ ቃል ኪዳን መሠረት
ትውልዱን ይምራል ይኸው በቸርነት
ስሽ ወለላ ነው ጣፋጭ ለአፋችን
ማርያም ማርያም ብለን ታብሷል እንባችን
@aleroe
ሐመረ ኖህ ነሽ
============
ሐመረ ኖህ ነሽ
የምህረት ቃል ኪዳን የተገባልሽ
ትውልድ ይህን አምኖ
ያከብርሻል አልቆ እና አግኖ
አዝ----------------//
በእግዚአብሔር ሀሳብ ነበርሽ በህሊና
ዓለምን ሳይፈጥር አዳምን ሳይሠራ
ሁሉን የናፈቀሽ የወጣብሽ ፀሀይ
ንግሥት ነሽ ድንግል እሙ ለአዶናይ
አዝ----------------//
ያንን የጭንቅ ቀን የጥፋቱን ዘመን
አልፈነዋል ባንቺ በአማናዊት ፅዮን
ምንጭ ነሽ የእርካታ የድህነት መፍለቂያ
የዘለዓለም እረፍት አንባ እና ማረፊያ
አዝ----------------//
የነቢያት ተፈጽሞ አየን
አንቺ ምክንያት ሆነሽ ለመዳናችን
ድምፅሽን ጠላት ይሸበራል
እኛ ግን ሰምተነው በሀሴት ዘለናል
አዝ----------------//
አንዴ በገባልሽ ቃል ኪዳን መሠረት
ትውልዱን ይምራል ይኸው በቸርነት
ስሽ ወለላ ነው ጣፋጭ ለአፋችን
ማርያም ማርያም ብለን ታብሷል እንባችን
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
………✍ፈጣሪ ያያል
----------------
አንድ ሰው ወደ እናት አባቱ ቤት አንዲት ሴተኛ አዳሪን ይዞ መጥቶ በእነሡ ፊት ዝሙት ይፈፅማል? ወይስ ማነው ወላጆቹ ፊት የዝሙት ፊልም ከፍቶ ነውር የሚፈፅም? ወላጆቻችን ፊት ጠጥቶ መስከር አያስፈራም? ወይም መስረቅ ወይም ክፉ ስድቦችን ቃላቶችን መናገር እና ሌሎችንም ሀጥያቶች መስራት ይከብዳል አይደል። ደፍሮ ለመፈፀም እጅግ ይከብዳል።
ፈጣሪ የሰማይም የምድርን ንጉሥ ነው!! የምናደርገውን ማንኛውም ድርጊት ይመለከታል። ታዲያ በምድራዊ እናት አባቶቻችን ፊት ከላይ የጠቀስናቸውን ነውሮች ደፍረን የማንፈፅም ከሆነ፥ እንደዚህ ያሉ ተግባራትን በፈጣሪ ፊት ለማከናወን የምንደፍረው ለምንድን ነው?
እግዚአብሔር እኮ ያየናል።
ለምሳሌ ሁላችንም አየርን በአይናችን አይተን አናውቅም አየር መኖሩን ግን አንጠራጠርም። እግዚአብሔርንም በዓይናችን ስላላየነው የለም ማለት አይደለም። እሱ ከኛ ጋር መሆኑን በሱ እይታ ውስጥ መሆናችንን እንዘነጋዋለን። ለመድራዊ ሰዎች የሰጠነውን ክብር እንኳ ለእግዚአብሔር አንሰጠም። ሌላው ይቅርና ሰው ዝሙትን ለመስራት ቢያስብ አንድ ትንሽ ህፃን ቢያየው ያን ተግባር ለማድረግ ያፍራል ይተወዋል። የዝሙት ፊልም የሚያይ ሰውም ትንሽ ህፃን ቢኖር ያፍራል ኡሱ ፊት ነውር አያደርግም። እግዚአብሔርን ግን የዛን ህፃን ያህል አልፈራውም አላከበረውም። በድፍረት ማንም አያየንም እያልን ሀጥያት አንስራ።
ስለዚህ ሰው ሆይ! እያንዳንዷን ድርጊትህ የሚመለከት የሰማይም የምድርም ንጉሥ እንዳለ በፍጹም አትርሳ፡፡ ሁሌም በህይወታችን በምንሰራቸው ነገሮች እግዚአብሔርን ላለማሳዘን በህጉ እና በትእዛዙ እንኑር። በውሎአችን በምንናገረው በምናስበው በምንሰራው ስራ ሁሉ እግዚአብሔር ይህ ነገር ያስደስተዋል ይሆን ወይ ብለን አስቀድመን እራሳችንን ጥይቀን እንደፈቃዱ ልንኖር ይገባል።
"ምን እየሰራቹ ነው ስንባል ለመናገር የምናፍርበትን ድርጊት አንፈፅም"

እንኳን_ደህና_መጣችሁ
እንኳን ደኅና መጣችሁ /2/
ወደ እኔ ወደ እናታችሁ
እጄን ዘርግቼ ስጠብቃችሁ
ወላጆቻችሁን እንድታከብሩ
አምላካችን መናገሩ /2/
እንድትጠብቁ ትእዛዙን
እምቢተኞች ባለመሆን /2/
የዕውቀት ገበያተኞች እንደመሆናችሁ
ምንም ጊዜ ሳይኖራችሁ /2/
እንደዚህ እኮ የምላችሁ
ቤተክርስቲያን ነኝ እናታችሁ /2/
ከሰኞ እስከ ዓርብ እየሠራን
እንጠያየቅ በሰንበት ቀን /2/
@aleroe
እንኳን_ደህና_መጣችሁ
እንኳን ደኅና መጣችሁ /2/
ወደ እኔ ወደ እናታችሁ
እጄን ዘርግቼ ስጠብቃችሁ
ወላጆቻችሁን እንድታከብሩ
አምላካችን መናገሩ /2/
እንድትጠብቁ ትእዛዙን
እምቢተኞች ባለመሆን /2/
የዕውቀት ገበያተኞች እንደመሆናችሁ
ምንም ጊዜ ሳይኖራችሁ /2/
እንደዚህ እኮ የምላችሁ
ቤተክርስቲያን ነኝ እናታችሁ /2/
ከሰኞ እስከ ዓርብ እየሠራን
እንጠያየቅ በሰንበት ቀን /2/
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
"ነገር ሁሉ ለበጎ ነው! "
በአንድ ወቅት አንድ መንፈሳዊ አባት ከነበሩበት ቦታ ወደ በረሃ መሰደድ ግድ ሆነባቸው። ከቅዱስ መጽሐፋቸው ሌላ ሦስት ነገሮች ነበሯቸው።
እነሱም፦ ቅዱስ መጽሐፉን በጨለማ ወቅት ለማንበብ የሚጠቅማቸው ቀንዲል (ኩራዝ)፣ ጎህ ከመቅደዱ በፊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው አንድ አውራ ዶሮ እና ለመጓጓዣነት የሚገለገሉበት አንድ አህያ ነበሩ።
አንድ ቀን ምሽት ከጉዞ የተነሣ በጣም ስለ ደከሙ እኚህ መንፈሳዊ አባት ወደ አንድ መንደር ቀርበው ማደሪያ ቢጠይቁም መንደርተኛው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማንም አልፈቀደላቸውም። ስለዚህም ከመንደሩ አቅራቢያ አንድ ጉድጓድ ያገኙና በዚያ ውስጥ ገብቶ ለማደር በመወሰን ገብተው አደሩ። እንደ ወትሮው ቅዱስ መጽሐፋቸውን ለማንበብ ቀንዲላቸውን ቢለኩሱትም የነበረው ብርቱ ነፋስ አጠፋባቸው።
ስለዚህም ለመተኛት ጋደም እንዳሉ ተኩላ መጥቶ አውራ ዶሮዋቸውን፣ አንበሳም አህያቸውን በሉባቸው። የተደራረበ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሽማግሌው እርዳታን በመሻት ወደዚያ መንደር ቢመለሱ ዘራፊ ሽፍታዎች የመንደሩን ነዋሪዎች በሙሉ ገድለው ንብረት ዘርፈው ዖና መንደር ሆኖ አገኙት።
ሽማግሌው ይህን ሁሉ ባጤኑ ጊዜ እግዚአብሔር ምን ያህል መልካም ነገርን እንዳሰበላቸው አስተዋሉ። በዚያች ምሽት በመንደርተኞቹ በአንዱ ቤት ቢያድሩ ኖሮ የዘራፊዎች ሰለባ ሆነው ሊገደሉ በቻሉ ነበር። ቀንዲላቸውንም ነፋስ ባያጠፋው የብርሃኑ ወጋገን እዚህ ጋር ሰው አለ በማለት ለሽፍታዎቹ ያሳብቅ ነበር። አውራ ዶሮአቸውና አህያቸውም ባይበሉ ኖሮ ከሽፍታዎቹ ተደብቀው ማደር ባልቻሉ ነበር።” እግዚአብሔር ከክፉ ነገሮች ውስጥ መልካም ነገር ማውጣት የሚችል አችግርምላክ ነው።"
ስለዚህ እንዲህ በሉ፦ "የሚደርስብኝ ፤ የሚገጥመኝ ፈተናና መከራ ሁሉ አምላኬ ሆይ ለበጎ ታደርግልኛለህና አመሰግንሐለሁ" አሜን

Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
፨ ተዘጋችተን እኑር፨
ርቀን ከቆምን
ከተዋሕዶ አምባ
ምግባረ ጎዶሎ
እንዳንሆን ገለባ
ለማይበጀን ዓለም
ጭራሽ ለማይረባ
በማይሆነን ሁሉ
ስንል ወጣ ገባ
ያቺ ቀን ሳትመጣ
ሳናውቅ እንደሌባ
ተዘጋጅተን እንኑር
ንስሐም እንግባ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@aleroe
፨ ተዘጋችተን እኑር፨
ርቀን ከቆምን
ከተዋሕዶ አምባ
ምግባረ ጎዶሎ
እንዳንሆን ገለባ
ለማይበጀን ዓለም
ጭራሽ ለማይረባ
በማይሆነን ሁሉ
ስንል ወጣ ገባ
ያቺ ቀን ሳትመጣ
ሳናውቅ እንደሌባ
ተዘጋጅተን እንኑር
ንስሐም እንግባ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
+++ ምን ብዬ ልጸልይ? +++
በግሪክ ሀገር ሁለት ሴት ልጆቹን ያሉት አንድ አባት ነበር። በአንድ ዓመት ብቻ የሚበላለጡትን እነዚህን ሕጻናት እንደ አባትም እንደ እናትም ሆኖ ተንከባክቦ ማሳደግ የዚህ ሰው ዋነኛ ሥራው ነበር።
ስለዚህ ወጥቶ በገባ ቁጥር ልጆቹን የሚያስደስት ነገር እየገዛ ፣ የሚጠይቁትን እያሟላ በድሎት ያኖራቸው ነበር። የራሱን ሕይወት ወደ ጎን ትቶ ለልጆቹ መኖሩ ያለ ዋጋ አልቀረም። ሁለቱም ልጆቹ በጤንነት አድገው ዕድሜያቸው ለጋብቻ ደረሰ።
አባት የለፋባቸው ልጆቹን ከመዳሩ በፊት ብዙ መሰብ ነበረበት። አስተዋይ ነበርና ብዙ ሽማግሌ ቢላክበትም ልጆቹን ለመሥጠት የወሰነው ግን በጥንቃቄ ነበር። ስለዚህ ልጆቹ ሁለቱም በአንድ ጊዜ እንዳይቸገሩ በማሰብ የተለያየና የማይነጥፍ መተዳደሪያ ላላቸው ወንዶች ባል እንዲሆኑ ለማድረግ ወሰነ።
እንዲህ ሲልም ያወጣና ያወርድ ጀመር :
"ሰዎች ሁልጊዜም ምግብ ያስፈልጋቸዋል ስለዚህ ገበሬ መቼም ቢሆን እህል ገዢ አያጣም። እንዲሁም ሰዎች ውኃ ለመቅዳት ምግብ ለመሥራት ሸክላ ስለሚፈልጉ ሸክላ ሠሪም ገበያ አያጣም።
ስለዚህ ልጆቼን የምሠጠው ለሸክላ ሠሪና ለገበሬ ነው" አለ። እንዳለውም አንዲቷ ልጁ የገበሬ ሚስት ሌላኛዋ ደግሞ የሸክላ ሠሪ ሚስት እንዲሆኑ ሠጣቸው።
ከብዙ ጊዜ በኋላ በአንድ ሰንበት ይህ ሽማግሌ ዛሬስ ልጆቼን ልጠይቅ ብሎ ተነሣ። በመጀመሪያ ወደ ገበሬው ሚስት ሔዶ ሲጫወት አረፈደ።
ተሰናብቶ ሊወጣ ሲል ልጁ እንዲህ አለችው :
"አባዬ እስካሁን ኑሮአችን ሰላም ነበር። አሁን ግን ችግር ላይ ነን። ላለፉት ሁለት ወራት ዝናም ጨርሶ አልዘነበም። በዚሁ ከቀጠለ የዘራነው አይበቅልም ፣ ተክሎቻችንም ይደርቃሉ።
አባዬ አደራ! በሚመጣው ወር ከባድ ዝናም እንዲጥል ወደ ፈጣሪ ጸልይልን!"
አባት አደራውን ተቀብሎ ተሰናብቶ ወደ ሁለተኛዋ ልጁ ቤት ለመሔድ ጉዞውን ጀመረ።
ከሰዓት በኋላ ወደ ሁለተኛዋ ልጁ ቤት ሲደርስ ከሸክላ ሠሪው ባሏ ጋር በአክብሮት ተቀብለው አስተናገዱት። ከጠዋቱ የበለጠ ደስተኛ ሆኖም አሳለፈ። መሰናበቻው ላይ ግን ልጁ ተነሥታ እንዲህ አለችው:
"አባዬ ለአንተ ለጸሎተኛው አባቴና ለጠንካራው ባለቤቴ ምስጋና ይሁንና ኑሮአችን እስካሁን ጥሩ ነው። እንደምታውቀው ላለፉት ሁለት ወራት ዝናም አልዘነመም። በዚህም ደስተኞች ነን። አሁን የምለምንህ አንድ ነገር ብቻ ነው።
በሜዳ ላይ ተደርድሮ እንደምታየው እጅግ ብዙ ሸክላዎች እየሠራን ነው። በሚመጣው ወር ዝናም ካልዘነመና ደረቅ ከሆነ የሠራናቸው ዕቃዎች ሁሉ ደርቀው ለገበያ ይደርሱልናል። ስለዚህ በሚመጣው ወር ዝናም እንዳይጥል ወደ ፈጣሪህ ጸልይልን"
አባት ተሰናብቶ ሲወጣ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ
"ፈጣሪዬ ሆይ አንዲቱ እንዳይዘንም ጸልይ አለችኝ ፣ ሌላዋ እንዲዘንም ጸልይ አለችኝ ፣ ምን ብዬ ልጸልይ?" አለ።
ይህ አረጋዊ የእኛን ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቢያስቀድስ ኖሮ ግን እንዲህ አይጨነቅም ነበር። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ላይ ዲያቆኑ የሚያነበው ምእመናን በግንባራቸው ተደፍተው የሚሰሙት "በእንተ ቅድሳት" የሚባል ጸሎት ላይ የዚህን ሽማግሌ ልብ የሚያረጋጋ ስለ ዝናም የሚጸለይ አንቀጽ አለ። እንዲህ ይላል:
"በሚሻበት ቦታ እግዚአብሔር ዝናሙን ያዘንም ዘንድ ስለ ዝናም እንማልዳለን"
"በሚሻበት" የሚለው ቃል ላይ "ሻ" ጠብቃ ትነበባለች። "በሚፈለግበት ቦታ እግዚአብሔር ዝናሙን ያዘንም ዘንድ" (ኀበ ዘይትፈቀድ መካን) ማለት ነው። ቀሳውስቱም ስለ ዝናማት በሚጸልዩት መስተብቁዕ ላይ "ወደ ሚሻበት ቦታ ዝናሙን ይልክ ዘንድ" (ከመ ዝናሞ ይፈኑ ውስተ ኀበ ይትፈቀድ መካን) "ወደሚሻበት ቦታ ዝናሞችህን ላክ"(ዝናማቲከ ፈኑ ውስተ ኀበ ይትፈቀድ መካን) ይላሉ።
ዝናም እንደ ገበሬው ቤት የሚፈለግበት ቦታ እንዳለ ሁሉ እንደ ሸክላ ሠሪው ቤት ደግሞ የማይፈለግበት ቦታ አለና ቤተ ክርስቲያን ከፈጣሪዋ ዝናም ከመለመን አልፋ የሚያዘንምበትን ቦታም እየጠቆመች ትጸልያለች።
"ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ "

የድሆች_መጠጊያ
የድሆች መጠጊያ ቤተክርስቲያን
ለመማር መጥተናል ሰመተን ቃልሽን/2/
ሰላም /2/ የዘላለም ቤቴ
ካንቺ አልለይም እስከለተ ሞቴ
ሰላም ላንቺ ይሁን ቤተ ክርስቲያን
በደሙ ያጸናሽ ኢየሱስ መድህን/2/
ቤተ ክርስቲያን ሆይ የአማንያን እናት
ወዳንቺ ቀርበናል እንድናገኝ ህይወት
ቅረቡ ወጣቶች ባንድነት ሆናችሁ
እጆቻን ዘርግታ ልትቀበላችሁ
ተነስታለችና ቅድስት እናታችሁ
@aleroe
የድሆች_መጠጊያ
የድሆች መጠጊያ ቤተክርስቲያን
ለመማር መጥተናል ሰመተን ቃልሽን/2/
ሰላም /2/ የዘላለም ቤቴ
ካንቺ አልለይም እስከለተ ሞቴ
ሰላም ላንቺ ይሁን ቤተ ክርስቲያን
በደሙ ያጸናሽ ኢየሱስ መድህን/2/
ቤተ ክርስቲያን ሆይ የአማንያን እናት
ወዳንቺ ቀርበናል እንድናገኝ ህይወት
ቅረቡ ወጣቶች ባንድነት ሆናችሁ
እጆቻን ዘርግታ ልትቀበላችሁ
ተነስታለችና ቅድስት እናታችሁ
@aleroe
"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
…………✍መብረር አስተምሪኝ
ዔሊዋ አሞራን ባገኘቻት ቀጥር መብረር አስተምሪኝ እያለች ጭቅጭቅ ታደርጋታለች። አሞራዋም በተገናኙ ቁጥር "ይኽ የተፈጥሯችን ጉዳይ ነው። በመማርና በማስተማር የሚመጣ አይደለም" ትላት ነበር። ኤሊዋ ግን የምቀኝነት ነገር እየመሰላት የአሞራዋን ቃል አልሰማ አለች።
አንድ ቀን አሞራዋ "ምን ላድርግሽ ብትላት?" እንደምንም ብለሽ ወደ ላይ አድርጊኝና ልቀቂኝ ራሴ እበራለሁ አለቻት። በጭቅጭቋ የተማረረችው አሞራ አንድ ባላ ቢጤ አመጣችና ያን በኤሊዋ አፍ አስይዛ ሌላኛውን ጫፍ እሷ ይዛ ሽቅብ ወደ ላይ ከበረረች በኋላ የእንጨቱን ጫፍ ለቃ "ያውልሽ ብረሪ" አለችና ለቀቀቻት። ኤሊዋም ተምዘግዝጋ ወረደችና እንዳልነበረች ሆና ሞተች።
ሰው ሁሉ የተሰጠው የራሱ ጸጋና ሃብት አለው። አንተ ሁልጊዜ አንተ ነህ ሌላውን በአንተ ውስጥ ስትፈልግ ከምትደክም ራስህን በአንተ ውስጥ ፈልግና አግኘው። አዳምና ሄዋን ሰው ናቸው ግን እግዚአብሔርን መሆን ተመኙ እንኳን እግዚአብሔር ሊሆኑ በቅጡ ሰው መሆንንም አጡ። ምላጭ ምንም ያህል ስለታም ቢሆን ዛፍ አይቆርጥም መጥረቢያ የቱንም ያህል ቢጠነክር ጸጉር አይቆርጥም። ልክ እንዲሁ እኛም ለተፈጠርንለት ዓላማ እንኑር
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

፨ገድፍሃል፨
አንደበትህ ክዶህ ሀሰት ከለመደ
መልካሙን ናቅ አርጎ ሴራ ከወደደ
እንደ አምሳል መሰረት ቀረ ሰው መሆንህ
አምላክም አይኖርም ሳይጣን ነው ከጎንህ
በህይዎት እየኖርክ ከሆንክ አሜኬላ
እኔ ሰው ነኝ እያልክ ልብህ ሰው ከጠላ
በእምነቱ ፀንተህ ወስጋ ከደሙ
አልገለጽ ካለህ የህይወት ትረጉሙ
እውነቱን ተቀበል
ጾምህን ገድፍሃል
ለምን! ማለት ጥሩ ለምን ይመስልሃል?
ውሰጥ ተመርዞ
ልብህ ቂም አርግዞ
ላይሰምር ሱባኤ
ልብ ሳይኖር ጉባኤ
ገደብ የለሽ ምኞት
ከአንገት በላይ ፀሎት
በላይኛው አለም ወንዝ አያሻግርም
እዚ እንደለመደከው ማጭበርበር አይኖርም።
@aleroe
፨ገድፍሃል፨
አንደበትህ ክዶህ ሀሰት ከለመደ
መልካሙን ናቅ አርጎ ሴራ ከወደደ
እንደ አምሳል መሰረት ቀረ ሰው መሆንህ
አምላክም አይኖርም ሳይጣን ነው ከጎንህ
በህይዎት እየኖርክ ከሆንክ አሜኬላ
እኔ ሰው ነኝ እያልክ ልብህ ሰው ከጠላ
በእምነቱ ፀንተህ ወስጋ ከደሙ
አልገለጽ ካለህ የህይወት ትረጉሙ
እውነቱን ተቀበል
ጾምህን ገድፍሃል
ለምን! ማለት ጥሩ ለምን ይመስልሃል?
ውሰጥ ተመርዞ
ልብህ ቂም አርግዞ
ላይሰምር ሱባኤ
ልብ ሳይኖር ጉባኤ
ገደብ የለሽ ምኞት
ከአንገት በላይ ፀሎት
በላይኛው አለም ወንዝ አያሻግርም
እዚ እንደለመደከው ማጭበርበር አይኖርም።
@aleroe
ኤልሮኢ:
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን
ኑ በእግዚአብሄር ደስ ይበለን /2/
ለታላቁ ክብር ለዚ ላበቃን
ከሞት ወደ ህይወት ላሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሄር ኑ በድንግል ደስ ይበለን
የሰማዩን መንግሥት እርስቱን ለሰጠን
ከጨለማ አውጥቶ ብርሃንን ላሳየን
ለዚህ ድንቅ ውለታው ምስጋና ያንሰዋል
በእርሱ ደስ ይበለን ክብር ይገባዋል
ከአለት የፈለቀ ውሃ ጠጥተናል
ሰማያዊ መና አምላክ መግቦናል
ፍቅርህ የበዛልህ ምን ልክፈልህ ጌታ
ስምህን ላመስግነው ከጠዋት እስከ ማታ
በቃዴስ በረሀ ምንም በሌለበት
በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት
ለእርሱ መንገድ አለው ከቶ ምን ተስኖት
ልባችሁ አይፍራ በፍፁም እመኑት
በባርነት ሳለን በድቅድቅ ዓለም
ብርሃንን አገኘን በድንግል ማርያም
ያጣነውን ሰላም ዛሬ አገኘን
እጅግ ደስ ይበለን በእመቤታችን
የሐና የኢያቄም የእምነታቸው ፍሬ
በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ
የኢያቄም ስዕለቱ የሐና እምነት
ለምኝልን ለኛ ኪዳነ ምሕረት
@aleroe
ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን
ኑ በእግዚአብሄር ደስ ይበለን /2/
ለታላቁ ክብር ለዚ ላበቃን
ከሞት ወደ ህይወት ላሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሄር ኑ በድንግል ደስ ይበለን
የሰማዩን መንግሥት እርስቱን ለሰጠን
ከጨለማ አውጥቶ ብርሃንን ላሳየን
ለዚህ ድንቅ ውለታው ምስጋና ያንሰዋል
በእርሱ ደስ ይበለን ክብር ይገባዋል
ከአለት የፈለቀ ውሃ ጠጥተናል
ሰማያዊ መና አምላክ መግቦናል
ፍቅርህ የበዛልህ ምን ልክፈልህ ጌታ
ስምህን ላመስግነው ከጠዋት እስከ ማታ
በቃዴስ በረሀ ምንም በሌለበት
በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት
ለእርሱ መንገድ አለው ከቶ ምን ተስኖት
ልባችሁ አይፍራ በፍፁም እመኑት
በባርነት ሳለን በድቅድቅ ዓለም
ብርሃንን አገኘን በድንግል ማርያም
ያጣነውን ሰላም ዛሬ አገኘን
እጅግ ደስ ይበለን በእመቤታችን
የሐና የኢያቄም የእምነታቸው ፍሬ
በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ
የኢያቄም ስዕለቱ የሐና እምነት
ለምኝልን ለኛ ኪዳነ ምሕረት
@aleroe