"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤልሮኢ:
●▬▬ ሳትሰስቺ ስጪ

ማታ ለመኝታ አልጋ ላይ ሰትወጪ
ሌሊቱ እንዲሰምር ሳትሰስቺ ስጪ

ጠዋት እንደ ነጋ ሳትወርጂ ከአልጋ
ደግመሽ መስጠትሽም እንዳይዘነጋ

ሻወር ቤትም ቢሆን ኩሽና ስትገቢ
ካንጀትሽ ለግሺው ሳትንገበገቢ

ከዋልሽበት ቦታ በሰላም ስትመጪ
በርከክ በይና ጎንበስ ብለሽ ስጪ

ቀናትን ሳትመርጪ ሰኞ አርብ ሳትዪ
ሰባቱንም ቀናት ለሱ አትከልክዪ

ህይወትሽ እንዲያምር ኑሮሽ እንዲቀና
ለአምላክ ምስጋና ይገባዋልና።
ለእሷ ብቻ አይደለም ላንተም ነው በል ንቃ
@aleroe
ኤልሮኢ:

…… እኛ ከየትኛው እንሆን ይሆን

አምስት ዓይነት ክርስቲያኖች

አንደኛው ክርስቲያን
ዘወትር ከቤተ ክርስቲያንየማይለይ በየቀኑ እግሮቹ ወደ ቤተክርስቲያን የሚገሰግሱ ጠዋት ኪዳን ከሰዓት ቅዳሴ ማታ ሰርክ ጉባኤ የማይቀር ዘወትር የሚጸልይ የሚጾምስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ የሚኖር የሰበካ ጉባኤ አባል የሆነ ቤተ ክርስቲያንን በሚችለው የሚያገለግል ቤቱን ካህናት የባረኩትየሚቆርብ አስራቱን በኩራቱን የሚያወጣ ክርስትናን በተግባር የሚገልጠው ነው።
ሁለተኛው ክርስቲያን
በሳምንት አንድ ቀን እሁድ እሁድ ብቻ ቤተ ክርስቲያን የሚሄድ
በሳምንት አንድ ቀን የሚጸልይ
ስድስት ቀን ሙሉ ቤተ ክርስቲያን ትዝ የማይለው በሳምንት አንድ ቀን የሚያስቀድስ ስድስቱን ቀን በግል ስራው የተጠመደ በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ሂዶ እድር እቁብ አለብኝ ወንጌሉ ይጠር ትምህርቱ በዛ መርሃ ግብር ተንዛዛ ቅዳሴው ረዘመ የሚል በሳምንት አንድ ቀን መጥቶ ሥርዓቱ እስኪፈጸም መቆየት ያቃተው ከመንፈሳዊው ይልቅ ለዓለማዊ የሚያዳላው ነው።
ሶስተኛው ክርስቲያን
በወር አንድ ቀን ብቻ ወራዊ በዓላትን ቆጥሮ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሄደው ነው
(የመድኀኔዓም) (የማርያም) (የሚካኤል)ወዘተ
ዛሬ እኮ መድኀኔዓለም ነው ቤተ ክርስቲያን ልሂድ ብሎ ቀን ቆጥሮ የሚሄደው29 ቀን ሙሉ ቤተ ክረስቲያንን የረሳ ኪዳን አድርሶ የማያውቅ ወንጌል ቁጭ ብሎ የማይማር የማያስቀድስበወር አንድ ቀን ብቻ ቤተ ክርስቲያን ደርሶ የሚመለስ ለጸሎት ጊዜ የሌለውበቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የማይሳተፍ የሰበካ ጉባኤ መታወቂያ የሌለው የነፍስ አባቱን ስም እንኳየማያውቅ የነፍስ አባትህ ማነው? ተብሎ ሲጠየቅ እንትና እንትና ማን ነበር ረሳሁት የሚል የነፍስ አባቱን ሲያገባ ሲወልድ ሰው ሲሞትበት ብቻ የሚፈልግ ቤቱን አስባርኮ ጸበል አስረጭቶ የማያውቅ በልምድ ብቻ የሚኖረው ነው።
አራተኛው ክርስቲያን
በዓመት አንድ ቀን በንግሥ ጊዜ ቤተ ክረርስቲያን የሚሄደው ነው
ዛሬ የዓመቱ ገብርኤል ነው
ዛሬ ጥምቀት ነው ብሎ የሚሄደው
364 ቀን ከቤተ ክርስቲያን ቀርቶ በዓመት አንድ ቀን ትዝ የሚለው
የበዓል ሰው የሆነ የነፍስ አባት የሌለው የሰበካ ጉባኤ መታወቂያ የሌለው ጸሎት አድርጎ ኪዳን አድርሶ ቅዳሴ አስቀድሶ ጾም ጹሞ ንስሐ ገብቶ የማያውቅ ኳስ ሲደግፍ ፊልም ሲያይ ቻት ሲያደርግ ካራንቡላ ፑል ሲጫዎት ጊዜውን በማባክን ራሱንበዓለማዊ ነገሮች ቢዚ ያደረገ ቤተ ክርስቲያን እንሂድ ሲሉት ቢዚ ነኝ የሚልሁለት ሰዓት ሙሉ ቁጭ ብሎ ኳስ የሚደግፍ ፊልም የሚያይ ሰላሳ ደቂቃ ወንጌል መማርየሚሰለቸው ዓለም አንቃየያዘቸው በሚያልፍ ነገር የሚታለለው ከመንፈሳዊ ነገር የራቀው ነው።
አምስተኛው ክርስቲያን
በሕይወቱ ቤተክርስቲያንን የማያውቃት ነውክርስትና ሲነሳ እናቱ አዝላ ካመጣችው በሇላ ደግሞ ያልመጣ ለጠናቋይለጣኦት ሲገብር የኖረ በባእድ አምልኮ ተተብትቦ ተይዞ ቆሌ ጨሌ እያለ ኑሮ ሲሞት ለመቅበር ሰዎች ክርስቲያን ነው ብለው አስከሬኑን ወደ ቤተ ክረርስቲያን ያመጡት ስሙ ብቻ ክርስቲያን የተባለ የክርስትና ስራ ሰርቶ የማያውቅ በእሱ ምክንያት ከሰበካ ጉባኤ ጋራ ጭቅጭቅ የሚያስነሳ ሰበካ ጉባኤ ስለማለውቀው ኣይቀበርም የቤተ ክርስቲያን አባል አይደለም ሲል ዘመዶቹ ጎረቤቶቹ ክርስቲያን ነው ይቀበር ብለው የሚከራከሩለት ሰውን ግራ የሚያጋባ ከንቱ የሆነ ሰው ነው ።ክርስቲያኖች ሆይ እኔና እናንተ ከየትኛው ነን ???


@aleroe
ኤልሮኢ:(መዝሙር)

ባለ ዉለታዬ ባለዉለታዬ
ከአመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ
ተመስገን ጌታዬ

በሩን ቢዘጋብኝ ስምዖን ጨክኖ
ዝቅ አድርጎ ቢያየኝ ከአይሁድጋ ሆኖ
እንድቀርብ ወደ እሱ አዘዘ ጌታዬ
እግሩን አጥበዋለሁ ወድቄ በእንባዬ

አዝ

የቀራጭ አለቃ ቢሆንም ስራዬ
እንድወርድ ከዛፉ አዘዘ ጌታዬ
ማረጌን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ
ቤቴ ተባረከ በኢየሱስ ክርስቶስ

አዝ

ድንጋይ የጨበጡ ፈራጆች ከበውኝ
ነውሬን ዘርዝረው ጌታ ፊት አቆሙኝ
ፈረደችባቸው ሀጢያትም በነሱ
በሰላም ሂድ ብሎ ምርኛል ንጉሱ

አዝ

የማምነውን አምላክ አውቀዋለሁ እኔ
በሰራልኝ ስራ በእድሜ በዘመኔ
ፍቅሩን ተሸክሟል የልቤ ትከሻ
ልለየው አልችልም እስከመጨረሻ።

አዝ

የቀራጭ አለቃ ቢሆንም ስራዬ
እንድወርድ ከዛፉ አዘዘ ጌታዬ
ማረጌን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ
ቤቴ ተባረከ በኢየሱስ ክርስቶስ

ባለ ዉለታዬ ባለዉለታዬ
ከአመድ ከያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ
ተመስገን ጌታዬ።

@aleroe
ኤልሮኢ:

…………አንድ ሰውዬ በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ በመዕበል ተመታና መርከቡ ተሰባብራ በባህሩ ሰመጠች ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ ነገር ሰርቶ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል……ምግቡን ዓሳ አያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ። አንድ ቀን ዓሳ ሊያጠምድ ወደ ባህሩ እየሄደ በማሃል እዛች ባህር ላይ ጭስ ሸተተው ዞር ብሎ ሲያይ ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው……
እየሮጠ ቢመለስም ጎጆዋን ሊያድናት አልቻለም ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዷታል አለቀሰ ፈጠሪውን ወቀሰ እንዴት እዚህ ባህር ላይ ብቻዬን ጥለሀኝ
ከቤተሰቦቼ ነጥለሀኝ ስታበቃ በስንት ልፋት የሰራኋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለህ ብሎ አለቀሰ አማረረ……ከደቂቃዎች በኃላ አንድ ድምፅ ሰማ ወደ ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ አየ ተደሰተ……የመርከቡ ሰዎች መጥተው ጭነው ወሰዱት ከዚያም ለመርከቡ ሰዎች ጠየቃቸው! እንዴት አገኛቹኝ እዚህ አካባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት አገኛቹኝ?
አላቸው……መርከበኞቹም እኛማ በዛኛው በኩል ዞረን እየሄድን ነበር ከዚህ በኩል ጭስ አየንና እዚህ ሰዉ ይኖራል ብለን መጣን አንተ አገኘን አሉት። አቤት ጌታዬ ለካ ከዚህ ከስቃዬ ልታውጣኝ ፈልገህ ነው ትንሿ ጎጆዬን ያፍርስከው ወደ ትልቁ ቤት ልትውሰደኝ ነው አለ። አንዳዴ የሆነ ነገር ስናጣና ሲበላሽብን ሰውንም ፈጣሪንም ስናማርር እንኖራለን ግን ካጣነው እና ከጎደለብን ነገር ጀርባ
ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን በችግራችን ጊዜ መጠጋት ያለብንን ፈጣሪያችን እንረሳዋለን ከዚያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪውን እንኮንነዋለን። ያጣነውን እና የሰጠን ፈጣሪ! አእምሮችን ከሚያስበው በላይ
ሊሰጥህን እንደሚችል ማመን አለብን።


@aleroe
ኤልሮኢ:
# አይሸሸግ እውነቱ

አይሸሸግ እውነቱ ማርያም ብጸት ናት/2
ከእግዚአብሔር ያልተላከ አይችልም ሊያወድሳት (2)

ገብርኤል በከፍታ ከራማ ታላቅ ቤቱ
ገሊላ የተገኘው ወደ ማርያም እህቱ
ከእግዚአብሔር መላኩን ተረዳን በሚስጥር
ለስሟ ክብርንሰቶ ሰምተነዋል ሲየበስር

በዘካርያስ ቤት አቀረብሽ ምስጋና
የባርያውን ውርደት ተመልክቷልና
ፍጥረት ብፅይት ካለሽ ሆኖ ባንድ ቃሉ
ላንቺ ያልዘመረ እንዴት ትውልድ ይባል

ቢያከብርሽ ገብርኤል በታላቅ ትህትና
ልልናሽ በልጦበት ከርሱ ቅድስና
ከልቡ አመንጭቶ መች ሆነ ማክበሩ
እግዚአብሔር ልኮት ነው ለንቺ መዘመሩ

አንዳች አይጎልብኝ አንቺን አወድሼ
ዝማሬን ባበዛው ያለኝንጨርሼ
እንኳን ለማርያም ለአዶናይ እናት
ምስጋናን ሰቷታል ላቤጌያ ዳዊት

@aleroe
ኤልሮኢ: ( ስነ ፅሁፍ)
#ማህሌት

ፈልቀሽ የተገኘሽ ከአፈ መላእክት፣
ያሬድ የተማረሽ ከላይ ከሰማያት፣
እንከን የሌለብሽ አዲሷ ምስጋና።
ምስጢርሽ ሲገለጥ በአስደናቂ ዜማ፣
ከሰማይ መንጭተሽ በምድር ሲሰማ፣
በቃናሽ መስጠሽ ልቡናን በመክፈት፣
ማርከሽ ትወስጃለሽ ነፍስን ወደ ገነት።
የፍቅር መግለጫ የሕይወታችን አርማ፣
ጣእምሽ ልዩ ነው ሲገለጥ በዜማ።
የአድባራቱ ሁሉ ቋንቋና ድምጻቸው፣
የካህናት ቅኔ ሰምና ወርቃቸው፣
ለህዝብ ኢትዮጵያ የነፍስ ምግባቸው፣
ማኅሌት እኮነሽ ጸጋና ሃብታቸው።

____________________
@aleroe
ኤልሮኢ:

……አንድ ካህን ከሰው ተጣልቶ ለታሰረው የነፍስ ልጃቸው ዋስ ለመሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ያመራሉ። ከበር ፈታሹ ጋቢያቸውን አስወልቆ አገላብጦ ከፈተሻቸው በዋላ ያስገባቸዋል። ጊቢ ውስጥ ከገቡ በዋላ ድንገት ዞር ዞር እያሉ ወዴት መሄድ እንዳለባቸው የሚጠቁሟቸውን ሰው ሲፈልጉ አንድ የፖሊስ አባል ፀሀይ እየሞቀ መፅሐፍ ቅዱስ ሲያነብ ያዩታል። ባዩት ነገር የተደሰቱት ቄሱም "ፈጣሪ እና መንግስት ሳይታረቁ አልቀሩም" ብለው እያሰቡ ወደ ፖሊሱ ተጠግተው ሊጠይቁት ወደዱ በዛውም ዕውቀቱንም ለመፈተሽ "ልጄ የአዳምን ልጅ አቤልን የገደለው ማን እንደሆነ ታውቃለህ?" ባሉት ጊዜ ፓሊሱ ለአፍታም ቀና ሳይል "እኔ ምን አውቃለው ሂድና ሳጅን እያሱን ጠይቅ የነፍስ ግድያ መዝገቦችን እሱ ነው የሚመለከተው" አሉ
ቄሱ ግራ ተጋብተው "ገዳዩማ ቃየል ነው" ቢሉት ከተቀመጠበት ተስፈንጥሮ ተነስቶ "ቅደም እንግዲያውስ ምስክር ትሆናለህ" ብሏቸው እርፍፍፍፍ 😂
😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊
ይህን ታሪክ ያመጣሁት ወድጄ አይደለም
ሦስት ነገሮችን ታዝቤ እንጂ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1. ብዙዎቻችን መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ የተራራ ያክል ይከብደናል የተለያዩ ልብወለዶችን ለማንበብ ግን የሚያህለን የለም

2. የምናነበውም ሰዎች ለይስሙላ እናንብ እንጂ ቃሉ በሕይወታችን ውስጥ አይተገበርም

3. ብዙውን ጊዜ የህግ ሰዎች ለካህናት አባቶች የሚሰጡት ቦታ የወረደ ነው (የዋልድባን መመልከት እንችላለን ) እግዚአብሔር ባከበራቸው ልክና በሃይማኖት አባትነታቸው ልናከብራቸው ይገባናል


@aleroe
ኤልሮኢ:


እንደ ግብሬ ሳይሆን እንደ እግሬ ስጠኝ!

ተወዳጆች ሆይ አንዳንዶች ወደ ቤተ ክርስትያን ያለ ልባችን በእግራችን መመላለሳችን ወጋ እንደ ሌለው ይነግሩናል፡፡ እኛም ልባችን እየባከነ፣ሰውነታችን በኃጢአት እያደፈ ቤተ እግዚብሔር መመላለሳችን ዋጋ ቢስ ይመስለናል፡፡

ወዳጆቼ አንድ ሰው ልቡ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ በመጀመርያ እግሩ ሊመላለስ ይገባል፡፡ የእግር መመላለስ ልብን በማስቀደስ እውነተኛውን መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያደርገናል፡፡ የእግር መመላለስ ከንቱነትን የሚሰብኩ አሉ፡፡ ይህ ከእግዚአብሔር ቸርነት አንጻር ተገቢ አይደለም፡፡ እስኪ እኛ ወደ ደጁ ከነ ኃጢአታችን እንመላለስ፤እግዚአብሔር ደግሞ በሂደት በቃሉ መስታወት እራሳችንን ያሳየናል፣በወንጌሉ ብርሃን ልባችንን ያበራል፡፡

ወዳጆቼ በእግዚአብሔር ቤት ከነ ኃጢአታችን እየተመላለስን ስለ ሕይወታችን ቢያንስ እንደ ግብሬ ሳይሆን እንደ እግሬ ስጠኝ ብለን መለመን እንችላለን፡፡ ግብራችን ለልመናችን እቅፋት ቢሆንም እግራችን ግን ወደ እግዚአብሔር በመገስገሱ፣በመመላለሱ እግዚአብሔር እንደ ቸርነቱ ያደርግልናል፡፡

በነገራችን ላይ አብዛኞቻችን ከእግዚአብሔር የሚሰጠን ማናቸውም ነገሮች እንደ ሥራችን ሳይሆን እንደ ቸርነቱ ነው፡፡ በውጭ ለሰው የሚታየው ቅድስናችን፣መልካም ሥራችን ለሰው የተገለጠ ነው ግን የውስጥ ገመናችን፣ኃጢአታችን በእግዚአብሔር ቸርነት ለሰዎች የተሰወረ ነው፡፡ ስለዚህ አብዛኞቻችን እንደ ግብራችን ሳይሆን እንደ እግራችን ነው የሚሠጠን፡፡ በደላችን በሰው ፊት ተሰውሮ፣በእግዚአብሔር ፊት ተነውሮ ግን እግራችን በደጁ በመመላለሱ ነው የሚደረግልንና እየተደረገልን ያለው፡፡

እግዚአብሔርም በባሕርይው እንደ ሥራችን ሳይሆን እንደ ቸርነቱ ስንለምነው ነው የበለጠውን የሚሰጠን፡፡ ሰው በመንፈሳዊው ተጋድሎው፣በቅድስና ሥራው፣በበጎ ምግባሩ ልክ ከለመነው የትኛውም ሥራችን ከእሱ ቸርነት በላይ ስለማይሆን በግብራችን ከሚሰጠን ይልቅ በቸርነቱ የሚሰጠን ይበልጣል፡፡ ልመናችንም በግብራችን ልክ ሳይሆን በቸርነቱ ልክ ሲሆን ነው ተሰሚነት የሚኖረው፡፡

ትዝ ይላችኃል ጌታችን በምሳሌ በሚያሰተምርበት ጊዜ ሁለት ሰዎች ፈሪሳዊና ቀራጭ ወደ መቅደስ መጥተው ፈሪሳዊው እንደ ሌሎች ሰዎች ቀማኛ ዓመጸኛ አመንዝራ እንዳልሆነና በሳምንት ሁለት ጊዜ እንደሚጾም ካገኘው ሁሉ አሥራት እንደሚያወጣና የጽድቅ ሥራውን እየዘረዘረ በምስጋና ያቀርብ ነበር። በዚህም ፈሪሳዊው ፈጣሪ እንደ ግበሩ እንዲሰጠው፣ልመናውን እንዲሰማው ጸለየ፡፡ ቀራጩ ደግሞ በቅን ልቦና፣በትሁት ሰብእና ሆኖ ከርቀት ቆሞ፣ ከአንደበቱ ጸሎት ማፍለቅ ብቻ ሳይሆን ሰማይን ማየት እስኪሳቀቅ ድረስ ኃጢአቱን በማስታወስ "አምልኬ ሆይ እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ" በማለት ደረቱን በመድቃት ይጸልይ ነበር። ሉቃ 18÷13

ከፈሪሳዊው ይልቅ ትህትናን የተላበሰው ቀራጩ በጌታው ዘንድ ጻድቅ ሆኖ ተገኘ። ምክንያቱም ቀራጩ እንደ ግብሩ ሳይሆን እንደ እግሩ ነበር የለመነው፡፡ በኃጢአት መርከሱን ሳይሆን በእግሩ መመላለሱን ፈጣሪ እንዲቆጥርለት ለመነ፡፡ ይህንንም ጌታ እራሱ ‹‹እላችኃለሁ፣ከዚያ ይልቅ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመሰለ›› ብሎ መስክሮለታል፡፡ /ሉቃ 18÷14/

ወዳጆቼ ግብርን/ሥራችንን በልመናችን መሃል እንደ ሒሳብ እያወራረድን ከለመንን ልመናችን የፈሪሳዊው ነው። ግብሬን ሳይሆን እግሬን ቁጠርልኝ ካልን ልመናችን የቀራጬ ነውና ቸርነቱ ያደርገናል ቀና። በተለይ አሁን በያዝነው መንፈሳዊ ሕይወት እንደ ልባችን ሳይሆን እንደ እግራችን ነው እየተደረገልን ያለው፡፡ ይህ ማለት የልባችን ክፋት፣የሰውነታችን ኃጢአት ሳይሰፈር፣በእግር መመላለሳችን እየተቆጠረ፣ከቤቱ ባለመጥፋትችን እየታሰበ ነው የሚደረግልን፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር የቃሉ መዶሻ፣የልባችንን ድንጋይ እስኪሰብረው በእግር መመላለሱ ዋጋ ቢስ ስለማያደርገን በእግራችንን ቢሆን መመላለሱን አንተው፡፡
እግዚአብሔር ልባችንን እስኪመልስ፣ኃጢአትን ከሰውነታችን እስኪያፈርስ፣ቢያንስ በቤቱ በእግር እንመላለስ፡፡
↔️↔️↔️↔️↔️↔️↔️↔️↔️↔️
@aleroe
ኤልሮኢ:

"ምዕመናን በቤተመቅደስ ሊኖራቸው የሚገባ ሥርዓት

፦በቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ገበያ ክልክል ነው። /ማቴ 21፡12 ዮሐ 2፡13-18 ፍትሀነገስት አንቀጽ 1/

፦በቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ግብዣ ማድረግ፣መብላት፣መጠጣት ክልክል ነው። /የሎዶቅያ ሲኖዶስ (ዶቅ) 44 ፍ.ነገ 1/

፦ማንኛውም መብልም ሆነ መጠጥ ከቤተ መቅደስ 40 ክንድ(20 ሜትር) መራቅ አለበት! በመቅደሱ ሕብስቱና ወይኑ ብቻ ይፈተታልና። /ፍ.ነገ 1/

፦በታቦቱ ፊት ለመስገድ ወይም ለመፀለይ ወይም ለማስቀደስ ካልሆነ በቀር ማንም ወደ ቤተመቅደስ ገብቶ እንዲቀመጥ አይፈቀድም

፦ከካህን በስተቀር(ዲያቆናት፣ካህናት፣ቀሳውስት፣ጳጳሳት..) ከምዕመናን ወገን ወደ መቅደስ(ታቦቱ ያለበት) ገብቶ ሥጋ ወደሙን ሊቀበል(ሥጋ ወደሙን የሚያቀብሉ ካህናት ራሳቸው ሁሌም ከማቀበላቸው በፊት በመቅደስ ውስጥ ይቀበላሉ) ታቦቱን ሊጠጋ አይገባም /ፍ.ነገ 1፣ ቀኖና አብሉዲስ ፣ኢያሱ 3፡4/

፦ሴቶች ወደመቅደስ (ታቦቱ ያለበት) እንዲገቡና እንዲፀልዩ አልተፈቀደም። /የሎዶቅያ ሲኖዶስ(ዶቅ) 44፣ ፍ.ነገ 1/

፦ከቤተ ክርስቲያን አንዴ ለአገልግሎት ተመርጦ የገባውንና የተቀደሰውን ንዋየ ቅድሳት እንደገና ወደውጭ አውጥቶ መጠቀም አይገባም። /ፍ.ነገ 1፣ 1ቀለሚንጦስ (ረስጣ) 28/

፦ያላመኑ፣ ያልተጠመቁ፣ ተወግዘው የተለዩ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ ተከልክሏል። /ፍ.ነገ 1፣ ድድስቅሊያ (ድስቅ) 12/

፦ለፀሎትና ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ወደ ቤተክርስቲያን በሚኬድባቸው ዕለታት፣ በጾምና በሰንበት፣ በበዓላት ወቅት ወንድና ሴት ግንኙነት ክልክል ነው። /ዘፀ 19፡15፣ 1ቆሮ 7፡5-7/ (ለባለትዳር ብቻ ነው! ያላገባማ በየትኛውም ጊዜ ከጋብቻ በፊት አይፈቀድም)

፦ነውር ያለበት ወደ ቤተክርስቲያን አይገባም። /ፍ.ነገ 13/

፦ሴት ልጅ ወር አበባዋ ሲመጣ ለ7 ቀን፣ ስትወልድ ወንድ ከወለደች እስከ 40 ቀን፣ ሴት ከወለደች እስከ 80 ቀን ወደ ቤተመቅደስ መግባት አይፈቀድም። (ዘሌ 12፡1__፣ ዘሌ 15፡19-28፣ ፍ.ነገ 6፣ ዘኒቂያ 29)

፦ወንድም ቢሆን ከአፉ ወይም ከአፍንጫው የሚወጣ ፈሳሽ ፣ነስር ሲኖርበት ወደ ቤተ መቅደስ አይገባም! ይህም ቤተመቅደሱን ስለሚያረክስ ወይም ለሌላ #ሳይሆን በቤተ መቅደስ ውስጥ የክርስቶስ ደም ብቻ መፈተት ስላለበት ነው።

፦ወንድ ልጅ ሕልመ ሌሊት ከመታው(ህልመ ዝኔት ካየ(ስጋዊ ህልም ካየ) በዕለቱ ወደ ቤተ መቅደስ አይገባም። (ዘሌ 15፡2)

፦ጠዋትና ማታ ቤተክርስቲያን ለመሳለም መትጋት ያስፈልጋል። (ምሳ 8፡34)

፦ወደ ቤተክርስቲያን ሲገባ በቅፅረ ቤተክርስቲያን በር ላይ ሲደርሱ መሳለም ይገባል (መዝ 28፡2፣ መዝ 95፡9፣ ኤር 26፡2፣ ሕዝ 46፡3)

፦ወደ ቤተክርስቲያን (ቤተመቅደስ) ሲገቡ ጫማን አውልቆ ወገብን ታጥቆ አደግድጎ መግባት ይገባል። (ዘፀ 3፡5-6 ፣ ሐዋ 7፡33፣ ኢያሱ 5፡15፣ ፍ.ነገ 12)

፦በቤተክርስቲያን ውስጥ ተስለው የሚገኙ ቅዱሳን ሥዕላትን እጅ መንሳትና መስገድ ይገባል።

፦በቤተክርስቲያን ውስጥ መሳቅ፣ ስለ ዓለማዊ ነገር መነጋገር ክልክል ነው። /ዮሐንስ አፈወርቅ 19፡32 ፤ 48፤6 አቡሊዲስ 7/

፦አጭር፣ ያደፈ፣ የሰውነት ቅርጽን የሚያሳይ ልብስ ለብሶ ወደ ቤተክርስቲያን መሔድ ፈጽሞ የተከለከለ ነው /ዘፀ 19፡10 ፣ ዮሐ.አፈ 4፡49-72/


ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

@aleroe
ኤልሮኢ:

እንዴት ብትወደኝ ነው

እንዴት ብትወደኝ ነው የማትተወኝ (2)
ትዕግስትህን ሳስብ እጅግ ደነቀኝ(2)
እኔን ያዘልክበት ትክሻህ ሰፊ ነው
አእምሮዬም ልቤም አይችልም ሊለካው
ሞት የሚገባውን የስራዬን ብዛት
አይተህ እንዳላየ ተውከው በቸርነት(2)
ድንቅ ስጦታ ነው መልሰህ የሰጠኸኝ
ለኔ የወሰድኩት የማይገባኝ
ፍቅርህ ከሰንሰለት እጅግ ይበረታል
ዓመፀኛው ታዞ ያገለግልሀል(2)
ለበደለ በደል ላጠፋ ጥፋት
ይህን ነበር የማውቀው በዓለም ስርዓት
ያንተ ግን ይደንቃል ገዛኸኝ በምህረት
ፊቴ ትቆማለህ ሁሌ በቸርነት
ያፈቀረን አምላክ ጨክኖ ቢበድል
በፀፀት ይቀጣል በሂሊና ቁስል
ዓላማህ በኔ ላይ ፍቅር ስለሆነ
ህግህ ሊፈርድብኝ አንዴም አልጨከነ

#ሊቀ ዲያቆን ወንደሰን በቀለ

@aleroe
ኤልሮኢ:
11/09/11

#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡

ዲ/ን 1ቆሮ 5÷6-ፍ.ም
ን/ዲ 1ጴጥ 3፥15- ፍ.ም
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 3፥12 ፍ.ም

#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 3÷5-ፍፃ
አንሰ ሰከብኩ ወኖምኩ
ወተንሣይኩ እስመ ዘእግዚአብሔር አንሥአኒ
ኢይፈርህ እምአእላፍ አሕዛብ

#የዕለቱ ወንጌል፦
ማቴ 26፥12- ፍፃ

ቅዳሴ፦ ዘዮሐንስ አፈወርቅ

@aleroe
ኤልሮኢ:

#ከሳሽ_ዕድፉን_ሳያይ

 
ስታመነዝር አገኘናት፣
ብለው አካልበዋት፣
ከጌታ ፊት እያቻኮሉ፣
ከእግሩ ሥር አምጥተዋት ጣሉ፡፡

ምን ትላለህ ? ስለዚች ሴት፣
ይዘናታል በማመንዘር ኃጢአት፣
ሙሴ እንደው በሕጉ፣
ብሎናል ወግራችሁ ግደሉ፣
አንተስ ምን ትላለህ ?
ይሰማ እስኪ ፍርድህ … ?

ይላሉ ከሳሾች ….
ወንዱን አስመልጠው ፣ ሴቷን አሳዳጆች፤
እውነት አንሻፋፊ ፣ ግማሽ ምስክሮች፤

ኢየሱስ መለሰ ….
ጐንበስ ብሎ ከምድር ፣ አንዳች እየጻፈ፤
ከʻናንተ መካከል ፣ ነውሯ ያላገኘው፤
ድንጋይን ከሯሷ ፣ አሁኑ ይጫነው፤
ብሎ ሳያበቃ ፣ ቀና ሲል ካለበት፤
ከʻርሷ በቀር የለም ፣ ከተከሳሿ ሴት ፤
ለካስ ሁሉም ጥሎ ፣ ከዚያ ሥፍራ የጠፋው፤
ከʻርሷ ጋር ተጋድሞ ፣ ዕድፉን ባያየው ነው፡፡

ያመነች ግን እርሷ ፣ ተከናወነላት ፤

መንገዷን ቀየረች ፣ ከሞት ወደ ሕይወት፡፡
__________________

@aleroe
ኤልሮኢ:

………የእርሻ መሬት ወርሰው በጋራ
የሚሰሩ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ አንድኛው ትዳር መስርቶ
ትልቅ ቤተሰብ ሲኖረው ሁለተኛው ግን ብቻውን ነበር የሚኖረው፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ወንድማማቾቹ ከቤተሰባቸው የወረሱትን ሀብትና ንብረት በመከፋፈል በየግላቸው ለመስራት ይስማማሉ፡፡ ያለውንም ሀብት እኩል ተከፋፍለው የየግላቸው ኑሮ ይጀምራሉ፡፡ ወድያውኑ ግን ብቻውን የሚኖረው ወንድሙ ከራሱ ጋር መነጋገር ይጀምራል “ያለውን ሀብትና ትርፍ እኩል መከፋፈላችን አግባብ አልነበረም፡፡ እኔ ብቻየን ነው የምኖረው የሚያስፈልገኝ ነገር በጣም ትንሽ ነው፡፡ እርሱ ግን
ብዙ የቤተሰብ ሀላፊነት አለበት” በማለት ያስባል፡፡ እናም በጎተራው ካለው እህል አንድ ጆንያ የሚሆነውን ሁል ግዜ ማታ
ማታ እየተደበቀ ወንድሙ ጎተራ ውስጥ ማስገባት ይጀምራል፡፡
በተመሳሳይ ግዜ ሚስትና ልጆች ያሉት ወንድምም በተመሳሳይ ሁኔታ ያስባል “ይህንን ሀብት እኩል መካፈል አልነበረብንም፡፡ እኔኮ ትዳር አለኝ፡፡ ሚስቴና ልጆቼ ሁል ግዜ ከጎኔ በመሆናቸው ወደፊት በደንብ ይንከባከቡኛል፡፡ወንድሜ ግን ብቸኛ ነው፡፡ ወደፊት አጠገቡ ሆኖ የሚንከባከበው እንኳ የለውም” ሲል ያስባል፡፡ እርሱም እንደዚያኘው ወንድም በጎተራ ካለው እህል አንድ ጆንያ የሚሆነውን ሁል ግዜ ማታ ማታ እየተደበቀ ወንድሙ ጎተራ ውስጥ ማስገባት ይጀምራል፡፡ ወንድማማቾቹ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ግዜ ኖሩ፡፡ ከብዙ ግዜ ብኋላ ግን ሁለቱንም አንድ ነገር ያስገርማቸው ጀመር፡፡ በጎተራቸው ውስጥ ያለው እህል መጠን እየቀነሰ አለመሄዱ ግራ ያጋባቸዋል፡፡ ሁለቱም የገጠማቸውን ያልተለመደ ነገር ለመመርመር በየግላቸው እየጣሩ ሳለ ከእለታት አንድ ቀን ሌሊት ላይ የተለመደውን ተግባራቸውን ለመፈጸም እህል የተሞላበት ከረጢት እንደተሸከሙ በድንገት ተገናኙ ። ምንም አይነት ቃላት ሳይለዋወጡ ሸክማቸውን መሬት ላይ በመጣል በፍቅር ተቃቅፈው አለቀሱ
*
የመተሳሰብ ፍቅር… በአይምሮህ አስበህ በአንደበትህ የምታወጣው ቃል ሳይሆን፣ በልብህ የሚንፈራገጥ የማይወለድ ፅንስ ነው።
*
የአንድ አገር ልጆች ነን!
የኢትዮጽያ ልጆች!

@aleroe
ኤልሮኢ:

# ትሕትና + ትእግስት + ተስፋ + ፅናት + ፍቅር + እምነት + አምልኮት + ምግባር=>ስኬት!!

~አንዲት ስጋ የምትጠብስ ሴት ስጋውን መጥበሻው ላይ ትጥደውና ስጋውን ታገላብጠዋለች ።ከዛ መብሰል አለመብሰሉን ለማረጋገጥ በሹካ ወጋ ወጋ አድርጋ ታየዋለች። ከበሰለ ታወርድና ለመዓድ ገበታ ላይ ታቀርበዋለች።ልብ በሉ....
~ፈጣሪም እኛን ይለዉጥናል እውቀት ይሰጡናል ያበስሉናል ብሎ ባሰባቸው በተለያዩ ነገሮች ላይ ይጥደንና ጤና ማጣት፣ስራ ማጣት፣ወዳጅ ማጣት፣ የህይወት አጋር ማጣት፣ገንዘብ ማጣት፣ፍትሕ ማጣት፣ተስፋ ማጣት፣ነገሮችን አለመሳካት፣ሰርቶ መና፣መከዳት፣መናቅ፣ወ ... በተባሉ ሹካዎች ወጋ ወጋ አድርጎ መብሰል አለመብሰላችንን ያረጋግጣል።
~ችግር ውስጥ ሆነን ካመሰገንን በስለናል ካማረርን ግን ይቀረናልና፤አንዳንዴ በተለያዩ ችግር ውስጥ ጥዶ ያገላብጠናል።
~አንድ ካሜራ ማን እኛን ፎቶ ከማንሳቱ በፊት ፈገግ በል ቀና በል ትንሽ ወደ ቀኝ ምናምን እያለ አስቀድሞ ያስተካክለናል ከዛ ያነሳናል። ፈጣሪም እኛን በተለያዩ ችግሮች ውስጥ እያስገባ ነው ህይወታችንን ሚያስተካክለው ምክንያትም የደፈረሰ ህይወታችን መጥራት ስላለበትና ጥርት ለማድረግ።
~መከራ ፈጣሪ እኛን ወደሱ የሚጎትትበት ገመድ ነው። ዳይመንድን ውድ ካደረጉት ነገሮች መካከል አንዱ አቆራረጡ ነው።ዳይመንድን የምናውቀውን ቅርፁን ያስያዘውና ከተለያየ አቅጣጫ እንዲያንፀባርቅ ያደረገው አቆራረጡ ነው ይላሉ። እኛንም ዛሬ እየቆረጡንና እያስጨነቁን ያሉ ሳንቋቋማቸው ቀርተን እያማረርንባቸው ያለን ችግሮቻችንን ነገ እኛን ዉድና የሚያበራ ማንነት ባለቤት የሚያደርጉን ናቸው ።
~ማዕበል ሲነሳና ባህሩን ሲያማስለው ሁሉም እንስሶች ይሸሻሉ።ንስር አሞራው ግን በመሀሉ ገብቶ ዓሳ ይዞ ይወጣል።
~ ወዳጄ ሆይ እንደ ንስር አሞራው በችግር ውስጥ ብትሆንም እራስህን አንፅ። ሸክላ የምትሰራ ሴት እንኳን ሸክላዋን ሰርታ ስትጨርስ እንዲጠነክርላት በእሳት ነው ምትጠብሰው።ዛሬ የሚጠብሱህ ችግሮችና የህይወት መሰናክሎች ከፀናህ ማንነትህን ነው የሚያጠነክሩልህ።
~ ስለዚህ ስለሆነው ስለሚሆነው እየሆነ ስላለው ፣ ስለተደረግልህ ስላልተደረገልህ ፣ ስለ ሰጠህ ስለ ነፈገህ ነገር ሁሉ እሱን አመስግነው።
~ # እንዲ_በለው ፦
"ደስታንም ሆነ መከራን ብትሰጠኝ አመሰግንሀለሁ፤ ከኔ ይልቅ አንተ ነህና ለእኔ ምትቀርበው።ስለዚህም ጌታ ሆይ በመንገዴና በህይወቴ ሁሉ ፈቃድህ እንጂ ፈቃዴ አይሁን።"
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

@aleroe
ኤልሮኢ:
በከበረው_ደምህ

በከበረው ደምህ በአማኑኤል ስምህ
ከብሬያለሁና ልሰዋ ምስጋና/2/

በራስ ቅል ላይ ጨርሰኸው የኔን ስራ
ከፍ አደረከኝ ዝቅ ብለህ ሊጦስጥራ
መኖር ጀመርኩ ስትሞትልኝ መድኀኒቴ
ክበርልኝ ለዘለዓለም ቸር አባቴ

ከቀቄዳር ምንጭ እንቁ ከፍለው የማይገዙት
ያንተ መውደድ የተሰጠኝ ከሰማያት
ማን ይጠማል የዘለዓለም ምንጭ እያለ
እያረካኝ የተጠማ አንድ እርሱ ነው

ለብሰህ ቆምክ ቀራንዮ ከለሜዳ
ጨለማዬን ልትገፈው ያንን ፍዳ
ከዚህ በላይ የት ይገኛል የሚያፈቅር
በትህትና የሚሔድ እስከ መቃብር

የቱ ግብሬ ቢማርክህ ብትወደው ነው
የኔን መስቀል ተሸክመህ የደከምከው
ያሸነፈኝ ተሸነፈ በአንተ ችንካር
ተረገጠ የአሳዳጄ የእዳ ጦማር


@aleroe
ኤልሮኢ:
ግንቦት_25 /09/2011

፶፩ እምትንሣኤ እስከ ዕርገት በትንሣኤ እሁድ መዝሙር ይትፌሣሕ፡፡
#ምስባክ
ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም
ወከመ ኀያል ወኅዳገ ወይን
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ፡፡
#ትርጉም
እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደ ሚነቃ ተነሣ
የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኀይለኛም ሰው
ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ፡፡
#መዝ_77:65-66
#ወንጌል
#ማቴዎስ_28:1-ፍጻሜ፡ወሠርክ ሰንበት ለጸቢሖ እሁድ"በሰንበትም ማታ ለእሁድ አጥቢያ ማርያም መግደላዊትና ሁለተኛዋ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ፡፡.............
................................................ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ጻፈው፡፡"
#ማርቆስ_16:1-ፍጻሜ፡ወሐለፈት ሰንበት"ሰንበትም ባለፈች ጊዜ ማርያም መግደላዊት የያዕቆብ እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሥጋዉን ሊቀቡ ሽቱ ገዙ፡፡.......................................................................................ቀላውዴዎስ ቄሣር በነገሠ በአራት ዓመት ነው፡፡"
#ሉቃስ_24:1-13፡ወበእሑድ ሰንበት"ከሳምንቱም በመጀመሪያዪቱ ቀን ያዘጋጁትን ሽቶ ይዘው እጅግ ማልደው ወደ መቃብሩ ሄዱ ሌሎች ሴቶችም አብረዋቸው ነበሩ፡፡....................
................................................ጴጥሮስም ተነሣ ወደ መቃብርም ፈጥኖ ሄደ ዝቅ ብሎም በተመለከተ ጊዜ በፍታውን ለብቻው ተቀምጦ አየ የሆነውን እያደነቀ ተመለሰ፡፡"

👉 @aleroe