"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ኤልሮኢ:
​​ በጌቴ ሤማኒ

በጌቴ ሤማኒ በአታክልቱ ቦታ
በጌቴ ሤማኒ በአታክልቱ ቦታ
ለእኛ ሲል ጌታችን በዓለም ተንገላታ
በዓለም ተንገላታ/2/

አዳም እና ሔዋን በአጠፉት ጥፋት
አዳም እና ሔዋን በአጠፉት ጥፋት
እኛም ነበረብን የዘለዓለም ሞት
የዘለዓለም ሞት /2/

መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ
መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ
ይገርፉት ነበረ ሁሉም በየተራ
ሁሉም በየተራ /2/

ድንግል አልቻለችም ዕንባዋን ልትገታ
ድንግል አልቻለችም ዕንባዋን ልትገታ
እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ
ልጇ ሲንገላታ /2/

በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው
በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው
እንዲህ ሲል ጸለየ አባት ሆይ ማራቸው
አባት ሆይ ማራቸው /2/

በረቂቅ ሥልጣኑ ሁሉን የፈጠረ
በረቂቅ ጥበቡ ሁሉን የፈጠረ
በሰው እጅ ተገርፎ ሞቶ ተቀበረ
ሞተ ተቀበረ /2/

ፍቅሩን የገለጸው ተወልዶ በሥጋ
ፍቅሩን የገለጸው ተወልዶ በሥጋ
ኢየሱስ ጌታ ነው አልፋ እና ኦሜጋ
አልፋ እና ኦሜጋ /2/

በመስቀል ተሰቅሎ እንዲያ እየቃተተ
በመስቀል ተሰቅሎ እንዲያ እየቃተተ
ዓለምን ለማዳን የማይሞተው ሞተ
የማይሞተው ሞተ /2/

ከሞት ሊታደገን በመጣልን ፈጥኖ
ከሞት ሊታደገን በመጣልን ፈጥኖ
መስቀል አሸከሙት ውለታው ይኽ ሆኖ
ውለታው ይኽ ሆኖ /2/

መከራውን ሳስብ ሳስታውስ ቀኑን
መከራውን ሳስብ ሳስታውስ ቀኑን
ይቆስላል ይደማል ልቤ በሐዘን
ልቤ በሐዘን /2/

መች ለራሱ ነበር ይኽ ሁሉ መከራ
መች ለራሱ ነበር ይኽ ሁሉ መከራ
መስቀል ተሸክሞ የወጣ ተራራ
የወጣ ተራራ /2/

ሲያጎርሱት የሚናከስ ሰው ክፉ ነውና
ዕውሩን ቢያበራ ጎባጣን ቢያቀና
ጌታዬን ሰቀሉት አይሑድ ጨከኑና
አይሑድ ጨከኑና /2/

ምነው አያሳስብ የአይሑድ ክፋት
ምነው አያሳስብ የአይሑድ ክፋት
የዝናቡን ጌታ ውሐ ሲነፍጉት
ውሐ ሲነፍጉት /2/

በተንኮል በኃጢአት ቀሩ እንደ ሠከሩ
በተንኮል በኃጢአት ቀሩ እንደ ሠከሩ
ሙታን ከመቃብር ተነስተው ሲያስተምሩ
ተነስተው ሲያስተምሩ /2/

እናታችን ሔዋን ወየው በይ አልቅሽ
የአንቺን ሕመም ታሞ ከሞት ሊያድንሽ
የሕያዋን ጌታ ተሰቀለልሽ
ተሰቀለልሽ /2/

አዬ ጉድ አዬ ጉድ ዓለም የኋላሽ
አዬ ጉድ አዬ ጉድ ዓለም የኋላሽ
መድኃኒት ክርስቶስ በግፍ ሞተብሽ
በግፍ ሞተብሽ /2/

በመስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ሲቆርስ
በችንካር ተወግቶ ደሙንም ሲያፈስ
ዋለች በመከራ ድንግል ስታለቅስ
እናት ስታለቅስ /2/

ሰውነትሽ ራደ ሐዘን ከበበሽ
ስቃይ መከራውም ዳግም ጸናብሽ
ተሰቅሎ ስታይ አንድ አምላክ ልጅሽ
አንድ አምላክ ልጅሽ /2/

ቢፈስም ዕንባዬ ሆኖ መንታ መንታ
መች ዋጋ ይሆናል ለአንዲቱ ጠብታ
ለአለቀስሽው ለቅሶ ድንግል የእዛን ዕለታ
እናት የእዛን ዕለታ /2/

በአለቀስሽው ለቅሶ በልጅሽ ሕመም
በአለቀስሽው ለቅሶ በልጅሽ ሕመም
ከሐጢዓት ነፃሁኝ ዳንሁኝ ከገሐነም
ዳንሁኝ ከገሐነም /2/

@aleroe
ኤልሮኢ:
ስለ ሰይጣን ከተተረኩት ለቅምሻ

ሰዎች ርኩስ መንፈስ ያደረበትን ሰው ወደ አንድ ገዳም ይዘው መጡና ያድንላቸው ዘንድ
ለገዳሙ አበምኔት(አለቃ) ሰጡት። የገዳሙ አበምኔትም በተሰጠው ፀጋ ተጠቅሞ በስመ
እግዚአብሔር ሰይጣኑን ውጣ ሲለው ሰይጣኑም «መውጣቱንስ እወጣለሁ ግን አንድ ጥያቄ
ነበረኝ»ይላል።
የገዳሙ አበምኔትም «ምንድነው ጥያቄህ?» ይለዋል። ሰይጣኑም በወንጌል ላይ ፍየሎች
በግራ በጎች በቀኝ ይቆማሉ የሚል ቃል አለ፣ ለመሆኑ በፍየልና በበግ የተመሰሉት እነማን
ናቸው? ይኽንን በምሳሌ አድርገህ ንገረኝ አለው። የሰይጣኑ አመጣጥ የገባው ያ ደግ አባትም እንዲህ መለሰ። «በፍየል የተመሰሉት ኃጥአን፣ በበግ የተመሰሉት ደግሞ ፃድቃን ናቸው። በምሳሌ ንገረኝ ላልከው፣ በፍየል ከተመሰሉት ኃጥአን መካከል ለምሳሌ አንዱ እኔ ነኝ። በበግ የተመሠሉ ፃድቃንን ግን አላውቅም። አሁን ግን ውጣ» አለው። ተንኮሉ
የተነቃበትና ያጠመደው ውዳሴ ከንቱ መረብ ያልያዘለት ሰይጣንም በኃይል ጮኾ ከሰውየው
ወጣ። በሽተኛውም ዳነ፡፡

@aleroe
ኤልሮኢ:
መዝሙር ዘመጻጒዕ
15/07/11 ዓ.ም

#የዕለቱ_ምስባክ፦ 

እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኲሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ መዝ ፵፥፫

ትርጉም፦

እግዚአብሔር በሕማሙ አልጋ ሳለ ይረዳዋል
መኝታውንም ከደዌው የተነሣ ይለውጥለታል
እኔስ አቤቱ ይቅር በለኝ እላለሁ

የዕለቱ ወንጌል፦

ዮሐ ፭፥፩ - ፳፭

ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ
@aleroe
ኤልሮኢ:

፨ ተዘጋችተን እኑር፨

ርቀን ከቆምን
ከተዋሕዶ አምባ
ምግባረ ጎዶሎ
እንዳንሆን ገለባ
ለማይበጀን ዓለም
ጭራሽ ለማይረባ
በማይሆነን ሁሉ
ስንል ወጣ ገባ
ያቺ ቀን ሳትመጣ
ሳናውቅ እንደሌባ
ተዘጋጅተን እንኑር
ንስሐም እንግባ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር


@aleroe
ኤልሮኢ:
​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ
(ውርስ ትርጉም)
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ

“ብላቴና” የሚል፤
ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤
በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤
መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤
ጨቅላ ነው ፤ ትክክል!
ምንም ነፍስ የማያውቅ፤
እሳትና ውሃን መለየት የማይችል።

ቢለይማ ኖሮ፤
ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ?
......................................................
@aleroe
ኤልሮኢ:
​​አቤቱ ደግሰው

አቤቱ ደግ ሰው /አልቆአልና/(፪)
ከምድርም ፍቅር /ጠፍቷልና/(፪)
እንደቸርነትህ /አድነን/(፪)
በደላችንን /አትቁጠር/(፪)

የረድኤት አምላክ /ፍቅር ስጠን/(፪)
እንደ አህዛቡ/አታድርገን/(፪)
ክርስቲያን ነንና/እንዋደድ/(፪)
እባክህ አንውጣ /ከአንተ መንገድ/(፪)
አዝ = = = = =
አቤቱ ንፁህ ልብ /ፍጠርልን/(፪)
ሰውን የሚያስወድድ/ካለ እንከን/(፪)
አንደበታችንም/እንዲናገር /(፪)
ስለ ሰላም ቋንቋ /ስለ ፍቅር/(፪)
አዝ = = = = =
በእግዚአብሔር ፈቃድ /የሚመራ/(፪)
ትሩፋት ደግነት /የሚሰራ/(፪)
አንደበቱ ሁሉ /የታረመ/(፪)
ለቃለ ወንጌሉ /የደከመ/(፪)
አዝ = = = = =
ምግባርና እውነት/የተሰጠው/(፪)
እባክህን አድለን/ሁነኛ ሰው/(፪)
አንተን የሚመስል/በሕይወቱ/(፪)
ፍቅርና ትሕትና /የግል ሀብቱ/(፪)
አዝ = = = = =
የማስመሰል ፍቅር /እየበዛ/(፪)
ሰው እረክሷልና /እንደዋዛ/(፪)
ፍፁም መዋደድን /ስጠንና/(፪)
አዲስ ሰው እንሁን /እንደገና/(፪)
አዝ = = = = =
ደገኛ ሰው ማግኘት /አስቸግሯል/(፪)
እስከ መጨረሻው /ማን ይፀናል/(፪)
ምግባሩ ትክክል /እውነተኛ/(፪)
ልቡ የሚፀየፍ /ከዳተኛን/(፪)

"አቤቱ አድነኝ ደግ ሰው አልቆአልና
ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና"
መዝ፲፩፥፩

@aleroe
ኤልሮኢ:
ምክረ አበው

#እምነት-አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡
ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡
ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን #የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡
እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!!

@aleroe
ኤልሮኢ:
22/07/11(ዕለተ እሁድ)

#መዝሙር_ዘደብረ_ዘይት
"እንዘ ይነብር"

#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡

ዲ/ን 1 ተሰሎ 4÷13-ፍ.ም
ን/ዲ 2ጴጥ 3÷7-15
ን/ካ ግብ፡ሐዋ24÷1-22

#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 49÷3
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ 
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ

#ትርጒም

እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል
አምላካችን ዝም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል

#የዕለቱ_ወንጌል

ማቴ ፳፬፥፩ -፴፮

ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ

👉 @aleroe
ኤልሮኢ:
  
#ሳልፆም_ሊፈሰክ_ነው አይ የኔ ነገር !


እርግጥ አልበላሁም #ስጋም ሆነ #ቅቤ
አልፆም አለኝ እንጂ #አመፀኛ_ልቤ
ካምናና ካቻምና #የዘንድሮ_ብሶ
መላ ማንነቴ #በሀጢያት_ተለውሶ
#ስዋሽ_ስቀጥፍ
ህግን ስተላለፍ
ስሰድብ ሳደማ
የሰው ስጋ ሳማ
ባይኔ ሳመነዝር
የሰው ሰው ሳማትር
#ገላዬን_ሳራቁት
አዳምን/ሔዋንን ሳሳስት
ስረሳ ስቃይህን
መስቀል ህማምህን
ያን ሁሉ ግርፋት
ነብሴ ሳያስጨንቃት
#አይ_እኔ
በሀሰት ስመሰክር
በሀጢያት ስዳክር
ለማይሞላ ኑሮ
ሳልሻል ዘንድሮ
ፆሙ ተጋመሰ
ጊዜው ተጋመሰ
#ጌታ_ሆይ
አቤቱ አስበኝ
ለንሰሀ አብቃኝ
#እስቲ_የቀረውን ለበረከት በለው
#አመፀኛ_ልቤ ፆምህን ይፁመው
"ከደጀ ሰላሙ ከካህኑ እግር ስር
ንስሀዬን ልውሰድ ስለመስቀል ፍቅር"
🙏

@aleroe
ኤልሮኢ:
# አድኝኝ እናቴ

አድኝኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና
ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አልራቀምና
ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ
አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ(2)

አዝ------

የአማኑኤል እናት የተዋህዶ አክሊል
አትጥፊ ከመሐል እንድ ትሆኝኝ ሃይል
ምንም ቢበዛብን የእኛ ጒስቁልና
ከእኛ ጋራ ከሆንሽ አለን ቅድስና(2)

አዝ------

ተስፋዬ ነሽና እመካብሻለሁ
ግራ ቀኝም አልል ምርኮኛ ሆኛለሁ
ስቅበዘበዝ አይቶ ተስፋ የሰጠኝ
እግዚአበሔር ይመስገን ከአንች ያስጠጋኝ(2)

አዝ-----

በሥጋ ደክሜ በነፍሴ እንዳልጠፋ
እማጸንሻለሁ ድንግል የእኔ ተስፋ
የመንግሥቱ ወራሽ እንድሆን አድርጊኝ
መልካም ሥራን መስራት እኔን አስተምሩኝ(2)

አዝ---

አንች የሌለሽበት ጉባኤው ባዶ ነው
በቁም የደረቀ ሕይወት የተለየው
ከመሃከል ገብተሽ ሙይ የጒደለውን
ሠርጉ ተደግሷል ጕብኝልን ጓዳውን (2)

@aleroe
ኤልሮኢ:
#ለአባ_የትናንቱ

ያለ ማወቅ ጽልመት ሀገሩን ሲወርሰው
ማን ነበር ትውልዱን በወንጌል ያረሰው?

አባ ተክለ ሃይማኖት አባ የትናንቱ
ትዝ አለኝ ተጋድሎው ውል አለኝ ሕይወቱ

በቆላ በደጋ የተንከራተትኸው
የሃይማኖትን ተክል ዞረህ የተከልኸው

የኢትዮጵያ ፀሐይ አባ ተክለ አብ
እስቲ መለስ ብዬ ሥራህን ላስብ

የክህደት ጨለማ በአንተ ሲርቅ
የሃይማኖት ብርሃን ሲያንጸባርቅ

በቀንና ሌሊት ከላይ ታች ዞረህ
ሕዝቡን አደረስከው አስተምረህ መክረህ

ስንት ነበር አባ ‹የጉዞ አበልህ›?
ያረፍህበት ስፍራ የተዘጋጀልህ

የት ነበር መኝታው ጎን ማሳረፊያህ?
ንገረኝ እባክህ ማን ነበር የሸኘህ?
እሳት አባቴ ሆይ እኔ አመድ ልጅህ

በዘመኔ ቋንቋ እስኪ ልጠይቅህ?
#ዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ
@aleroe
ኤልሮኢ:

……ከእለታት አንድ ቀን አንድ አባት ወደ አባታችን አባ መቃርዮስ በኣት ሄደና "አባቴ ሆይ ድኅነትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?" ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው። አባታችንም እንዲህ በማለት አሉት።
"ወደ መቃብር ሂድና ሙታንን ሰድበሃቸው ና" አሉት። ይህ አባትም የተባለውን አድርጎ ተመለሰ። አባታችንም "ምን አሉህ?" ሲሉ ጠየቁት። ሰውየዉም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "አሁን ደግሞ ሂድና ሙታንን አመስግናቸው" አሉት። ሄዶም አመሰገናቸው። "አሁንስ ምን አሉህ" ሲል በድጋሚ ጠየቁት። ሰውዬም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባታችን አባ መቃርዮስም: "ስትሰድባቸው ፤ስታመሰግናቸው እና ስታወድሳቸው ምንም አልመለሱም፤ አንተም ለነፍስህ ድህነትን ከፈለግህ እንደሞተ ሰው ሆነህ ኑር። ሰዎች ክፉ ቢያደርጉብህም፣ ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ" አሉት።
======================
@aleroe
ኤልሮኢ:

ሐጥያት በደሌን ትቼ

ሐጥያት በደሌን ትቼ
በፍቅር ወደርሱ መጥቼ
በእንባዬ እግሮቹን ባጠብኩት
ብቻ ጌታዬን በካስኩት
****
ነፍሴን እያሳደፍኩ በበደል ስኖር
ለካ ሳፈርስ ነበር ሕንፃ እግዚአብሔር
አሁን ግን አንጽድቶኝ በልቤ በገባ
እሰዋለታለሁ የእንባዬን መባ
..... አዝ....
ድካሜን ሳይቆጥር ጌታዬ ከጠራኝ
ወደኋላ አላይም ከእንግዲህ ምን አለኝ
መቅጫዬን ትቼ እከተለዋለሁ
ከእርሱ ጋራ ውዬ ከእርሱ ጋር አድራለሁ
..... አዝ ....
ምሬሀለሁ ብሎ ካበዛልኝ ፀጋ
እለዋለሁ ቅዱስ ሲመሽም ሲነጋ
ፍቅሩ በልቤላይ ስሙ በአንደበቴ
ዘወትር አይጠፋም እርሱ ነው ጉልበቴ
.... አዝ .....
ልጄ ብሎ ጠራኝ እጆቹን ዘርግቶ
እርሱን ማሳዘኔን በደሌን እረስቶ
በፍታን አለበሰኝ ፍሪዳን አረደ
የፈጠረኝ ጌታ መዳኔን ወደደ
.... አዝ .....

#ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
👇
👉👉 @aleroe 👈👈
👉👉 @aleroe👈👈
👉👉 @aleroe👈👈
ኤልሮኢ:
፨ገድፍሃል፨

አንደበትህ ክዶህ ሀሰት ከለመደ
መልካሙን ናቅ አርጎ ሴራ ከወደደ
እንደ አምሳል መሰረት ቀረ ሰው መሆንህ
አምላክም አይኖርም ሳይጣን ነው ከጎንህ
በህይዎት እየኖርክ ከሆንክ አሜኬላ
እኔ ሰው ነኝ እያልክ ልብህ ሰው ከጠላ
በእምነቱ ፀንተህ ወስጋ ከደሙ
አልገለጽ ካለህ የህይወት ትረጉሙ
እውነቱን ተቀበል
ጾምህን ገድፍሃል
ለምን! ማለት ጥሩ ለምን ይመስልሃል?
ውሰጥ ተመርዞ
ልብህ ቂም አርግዞ
ላይሰምር ሱባኤ
ልብ ሳይኖር ጉባኤ
ገደብ የለሽ ምኞት
ከአንገት በላይ ፀሎት
በላይኛው አለም ወንዝ አያሻግርም
እዚ እንደለመደከው ማጭበርበር አይኖርም።



@aleroe
ኤልሮኢ:
ምክረ አበው

እባብ በህይወት እያለ ጉንዳንን ይበላል፡፡ እባብ ሲሞት ጉንዳኖች ይበሉታል፡፡ ጊዜ በማንኛውም ሰዓት ይለወጣል በህይወትህ የማንንም ዋጋ አታሳንስ

ምን አልባት አንተ ሀይለኛ ትሆን ይሆናል ጊዜ ግን ካንተ የበለጠ ጉልበተኛ ነው አስብ አንድ ዛፍ መቶ ሺ ክብሪቶችን ሲሰራ አንድ ክብሪት ግን መቶ ሺ ዛፎችን ታቃጥላለች፡፡

አንድ መጥፎ ስራም ብዙ መልካምነገሮችን ታጠፋለች፡፡ ወናው ነገር በአስተሳሰብ መልካም ሁን ረጋ ብለህ አስብ ለሁሉም ጊዜ አለው አትጨነቅ !

@aleroe
ኤልሮኢ:
06/08/11

#መዝሙር_ዘኒቆዲሞስ
" ሖረ ኀቤሁ "

#በዕለቱ_ቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበ_መልዕክታት_ወንጌልና_ምስባክ፡፡

ዲ/ን ሮሜ 7÷1-12
ን/ዲ 1ዮሐ 4÷18-ፍ ም
ን/ካ ግብ፡ሐዋ5÷34-ፍ ም

#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 16÷3
ሐወፅከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ
አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ
ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው::

#ትርጒም

በሌሊት ጎበኘኸኝ ልቤንም ፈተንኸው
ፈተንኸኝ ዓመፅ አልተገኘብኝም
የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር

#የዕለቱ_ወንጌል

ዮሐ 3÷1-12

ቅዳሴ: ዘእግዝእትነ

👉 @aleroe
ኤልሮኢ:

………"የዛሬ 2000 ዓመት ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ እጅመንሻ ይዛ ለተገኘች፡ ኢየሱስ ክርስቶስን በሕፃንነቱ ሲሰደድ ለተቀበለች፡ ኢየሱስ ባረገ በዓመቱ በጃንደረባዋ በኩል በስሙ ለተጠመቀች፡ ከማንም በፊት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላትን እምነት በንጉሥዋ በኢዛና በኩል በይፋ ለገለጠች፡ በዓለም ጥንታዊዉን በእጅ የተጻፈ የኢየሱስ ወንጌል በአባ ገሪማ ገዳም ለያዘች፡ በዓመት ከ1825 ጊዜ በላይ የኢየሱስ ወንጌል እንዲነበብ ሥርዓት ለሠራች ኢትዮጵያ፡- "ኢየሱስ ጌታ ነው" የሚለው ሰበር ዜናዋ ሊሆን አይችልም፡፡ ደንቆሮ የሰማ ዕለት ያብዳል ሆኖ ነው እንጅ፡፡"

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
@aleroe
ኤልሮኢ:

#ቢፈልግባትም_መልካሙ_ገበሬ

ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ
አልተገኘባትም ከበለስዋ ፍሬ፤

ለስልሶላት ነበር ሀይማኖት መሬቱ፤
ተቀጥሮላት ነበር አጥር ስርዓቱ፤
ተነቅሎላት ነበር ድንጋይ ፈተናዋ፤
ፍሬ ግን ታጣባት በመጨረሻዋ፤

ፍሬ የሌለባት ቅጠል ስለሆነች፤
ተካይዋን በምግባር ስላላስደሰተች፤
መልካሙን ገበሬ ሊቆርጣት ተነሳ፤
ሌሎች እንዳይጠፉ በእርሷ የተነሳ፤

ለንስሐ የሚሆን እድሜ እንዲሰጣት፤
ጠባቂ መልዐኳ ተማጸነላት፤
ምክር እና ተግሳጽ ይጨመርላት፤
ታፈራ እንደሆነ ለዓመት እንያት፤

ልመናውን ሰምቶ ጌታውም ፈቀደ፤
ጥቂት እድሜ ሊሰጥ ሊታገስ ወደደ፤
ዳግመኛ ሲመጣ ፍሬ ካላፈራች፤
ተቆርጣ ወደ ቶን እሳት ትጣላለች፤


👇👇👇👇👇
👉 @aleroe 👈
👉 @aleroe👈
👉 @aleroe👈
👆 👆👆👆👆
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤልሮኢ:

++ ንጉሥ በአህያ ላይ ++
(ሽራፊ ሃሳብ ከሆሳዕና ምንባብ)

"አህያ" ስምዋ ስድብ ከሆነ የቆየች እንስሳ ናት። የዚህች በዓለም ሁሉ የምትገኝ እንስሳ የሕይወት ታሪክዋ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው። በሚበዙት ሀገራት አህያ ከባድ ሸክም ስትሸከም ትውላለች ፣ ደክሟት ለማረፍ ብትፈልግና ሸብረክ ብትል እንኳን በዱላ የሚመታት እንጂ "እስቲ አረፍ በይ" የሚላት የለም። ጀርባዋ በሸክም ብዛት የቆሰለ ፣ እግርዋ በጭነት ብዛት የተብረከረከ ፣ ዱላ ያስመረራት ፣ ዕረፍት የናፈቃት እንስሳ ናት።
ይህችን የተዋረደች እንስሳ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊው ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ አደረጋት። ዱላ በለመደችው ፣ ዕረፍት በናፈቃት በዚህች ምስኪን ላይ "ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜ ቀሊል ነው" ያለው ንጉሥ ተቀመጠባት።

ኃያላን ነገሥታት ባማረ ሠረገላ ላይ ሆነው ፣ በሠራዊት ታጅበው ፣ ነጋሪት እያስመቱ ፣ መለከት እያስነፉ ፣ ሰይፍ በታጠቁ ጦረኞች እየተፎከረላቸው ወደሚገቡባት ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአህያ ላይ ተጭኖ ፣ በዓሣ አጥማጆች ተከብቦ ፣ በሕፃናት ዝማሬና በዘንባባ ዝንጣፊ ታጅቦ ገባ።

ፈርተውት ሳይሆን ወደውት የሚዘምሩለት ንጉሥ ፣ ልብስ ገፍፎ የሚረግጥ ሳይሆን ልብሳቸውን አውልቀው ረግጠህ እለፍ የሚሉት ንጉሥ ፣ በቅንጦት ሠረገላ የሚሣፈር ሳይሆን "በአህያ ላይ ከተቀመጥኩ ይበቃኛል" የሚል ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።

"የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል" የተባለላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? "የዋህና ትሑት ንጉሥ" ያላት ሀገር ፣ ከተማይቱን እያየ የሚያለቅስላት ንጉሥ ፣ መልካምነቱን ለመሸፈን የሚፈልጉ ሰዎች ስለ እሱ አትናገሩ ቢሉ እንኳን የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው የሚመሰከሩለት ንጉሥ ያላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? የታሰሩትን አስታውሶ "ያስፈልጉኛል ፣ ፈትታችሁ አምጡልኝ" የሚል ንጉሥ የነገሠባት ፣ ዘንባባ ተይዞ ስለ ሰላም የተዘመረባት ፣ "ሰላምሽ ዛሬ ነው" የተባለላት ያቺ ከተማ ምንኛ የታደለች ናት?

ወደ አህያይቱ ነገር እንመለስ ያቺን "ሸክም ያቆሰላትን ፣ ዕረፍት የናፈቃትን አህያ ክርስቶስ ፈትታችሁ አምጡልኝ ብሎ ዙፋኑ አደረጋት" የሚለው ታሪክ ለአህያ ብቻ ክብር የተሠጠበት ቀን መሆኑን የሚያሳይ ከመሰለን የዋሆች ነን። አህዮች አንብበው የማይጽናኑበት ወንጌል ላይ ይህ ክስተት የተጻፈው ለእኛ እንጂ ለምንም አይደለም።

እንደ አህያ ዕቃ ባንሸከምም ፣ ጀርባችን ባይቆስልም የልባችን ጀርባ በኃጢአት ሸክም የጎበጠ ፣ በበደል ብዛት የቆሰለብን ብዙዎች ነን። "መቼ ነው ይህንን የኃጢአት ሸክም አራግፌ ዕርፍ የምለው?" እያልን የምንሠቃይ ሞልተናል። መድኃኔ ዓለም ያኔ የላካቸውን ካህናት ዛሬም ወደ እኛ ልኮ "ፈትታችሁ አምጡልኝ" ብሎ እኛንም ቢያስፈታን ምናለ? ለነገሩ የእኛ የኃጢአት ማሠሪያ እጅግ ትብትብ ያለ ስለሆነ ካህናቱም "ከኃጢአት ማሠሪያ እግዚአብሔር ይፍታ" ሲሉ እንሰማቸዋለን።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

@aleroe