"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
እንኳን አደረሳችሁ
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" (Tesfabel)
ኤልሮኢ:(ምክረ አበው)

የአንድ አባት ምክር

በአንድ ወቅት በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ተገኚቼ ነበር፡፡ በዚያ ገዳም የሚኖሩ አባት የነገሩኝ ነገር ለሕይወት መመርያ የሚሆን ነው፡፡ አሁን ከደረስንበት ወቅት ጋር የሚሄድ ነውና ላካፍላችሁ፡፡

በወቅቱ እንደ ዛሬው በቤተ ክርስቲያን ላይ የፈተና ማዕበል ተነሥቶ ነበር፡፡ ያ ወቅት የፖለቲካው ማዕበልም እጅግ ያየለበት ጊዜ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምንሰጠው አገልግሎት ምን ፋይዳ ይኖረዋል? ምንስ ለውጥ ያመጣል? ችግሩ እንደሆነ እየባሰው እንጂ እየተሻለው አልሄደም፤ ታድያ ጊዜያችንን፣ ገንዘባችንን እና ዕውቀታችንን ዝም ብለን እየከሰከስን ይሆን? አሁን የኛ ልፋት የክፉ ሰዎችን ክፋት ለመሸፈን እና በክፋታቸው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ካልሆነ በቀር ችግሩን ይፈታዋል? ወዘተ፣ ወዘተ፣ ጥያቄዎች ይነሡ ነበር::

ያን ጊዜ እኒህ አባት እንዲህ አሉን፡፡

«ብዙ ልጆችን የወለደች የምትወድደው ባሏ የሞተባት አንዲት እናት ነበረች፡፡ ቤተ ዘመዶቿ ምንም ሳይራሩ ያለ ፍላጎቷ ለአንድ ክፉ ባል አጋቧት፡፡ ይህ ባል ግዴለሽ፣ ገንዘብ ወዳድ፣ ጠጥቶ ከመስከር፣ በልቶ ከመጥገብ፣ በስተቀር ሌላ ሞያ የለውም፡፡ ሲወጣ ሲገባ ይደበድባታል፡፡ እንጨት ሽጣ፣ ኩበት ለቅማ፣ እንጀራ ጋግራ፣ ጠላ ጠምቃ ያጠራቀመቻትን ገንዘብ ነጥቆ ይወስድባታል፡፡ ለዘመዶቹም ይበትነዋል፡፡

የት ትሂድ? የሠፈሩ ሕግ፣ ባህሉ እና ልማዱ፣ በሙሉ የእርሷን ሮሮ እና ልመና የሚሰማ አልሆነም፡፡ እርሱን እንደ ሕጋዊ ባልዋ ነው የሚቆጥሩት፡፡ የት ሂዳ መከራዋን ትናገር፡፡ የትስ ሂዳ ከችግሩ ትገላገል?

ይህ ክፉ ባልዋ እርሷን ብቻ ሳይሆን ልጆቿንም ያሰቃያቸው ነበር፡፡ እነርሱም በዚያ ቤት ውስጥ መከራውን እና ስቃዩን፣ ረሃቡን እና ጭቅጭቁን እየሰሙ መኖር መረራቸው፡፡ በዚያ ቤት ሰላም ጠፋ፡፡ ፍቅር ጠፋ፡፡ ምንጊዜም የሚሰማው ክፉ ነገር እና ልብ የሚያደማ ነገር ሆነ፡፡ ሰው ሁሉ ስለዚያ ቤት ያወራል፡፡ መንገድ ላይ ሲያገኛቸው ስለ ቤታቸው ይጠይቃቸዋል፡፡ እነርሱም በሃፍረት ይሸማቀቃሉ፡፡ ስለዚህም እናታቸውን ጥለው ወደ ሌላ ቦታ መሄድና ስለዚያ ቤት ከማያስቡበት እና ከማይሰሙበት ቦታ መድረስ ፈለጉ፡፡ የሚችሉትን ያህል እየሠሩ፣ ለራሳቸው የሚበቃቸውን እየኖሩ፣ መከራውን መገላገል እና እፎይ ብለው መኖር አሰኛቸው፡፡

ታድያ ይህንን ሃሳባቸውን ለአንድ ሽማግሌ ጠቢብ ሰው ነግረው ገንዘብ እና ሃሳብ እንዲሰጣቸው ፈለጉ፡፡ ሄደውም አማከሩት፡፡ ያም ሽማግሌ ሃሳባቸውን ሁሉ ከሰማ በኋላ እንዲህ አላቸው፡፡

«ልጆቼ ልክ ናችሁ ሩቅ ሀገር ሄዳችሁ፣ የምትችሉትን ያህል እየሠራችሁ፣ የራሳችሁን ኑሮ በመኖር ችግሩን ሁሉ መርሳት እና መገላገል ትችላላችሁ፡፡ ምን ያስጨንቃችኋል? ቤት ያለው እዚህ ብቻ ነው እንዴ? ሀገርስ ያለው እዚህ ብቻ ነው እንዴ? ግን አንድ ነገር አስቡ፡፡ እንዲህ ማድረጋችሁ ራሳችሁን ብቻ ከችግሩ ታወጣላችሁ እንጂ ችግሩን አትፈቱትም፤ እናንተ ችግሩን ትረሳላችሁ እንጂ ችግሩን አታስወግዱትም፡፡

«ደግሞም የእንጀራ አባታችሁ እናታችሁን የበደለውን ያህል እናንተም ትበድሏታላችሁ፡፡ እስኪ አስቡት ለዚህች ለእናታችሁ ከእናንተ በቀር የደስታዋ ምንጭ ማን ነው? ሁሉም ነገርዋ የሚያሳዝን እና የሚያስመርር ነው፡፡ እናንተ ግን የደስታዋ ምንጮች ናችሁ፡፡ የእንጀራ አባታችሁ እናታችሁን ያሳዝናታል፤ የእናንተ ጥላችኋት መሄድም ያሳዝናታል፤ እርሱ ብቻዋን እንድትለፋ ትቷታል፤ እናንተ ጥላችኋት ስትሄዱም ያለ አጋዥ ትተዋታላችሁ፤ እርሱ በመስረቅ ዘረፋት፣ እናንተም ባለ መስጠት ዘረፋችኋት፤ ታድያ ከእርሱ በምን ተሻላችሁ?

እናንተኮ ያሰባችሁት ለእናታችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ነው፡፡ እናታችሁ ስለተቸገረች አይደለም ያዘናችሁት፣ ችግሩ እናንተን ስለነካ ነው፤ እናታችሁ ስለተራበች አይደለም ያዘናችሁት ረሃቡ ስለነካችሁ ነው፡፡ በእናታችሁ ላይ የደረሰው ችግሳይሆን ስለችግሩ ከየሰው አፍ መስማት ነው የሰለቻችሁ፤ ችግሩን ለመቅረፍ አይደለም መሄድ የፈለጋችሁት፤ ችግሩን ላለማየት እና ላለመስማት ነው፡፡

ከዚያ ይልቅ ሥራ ሠርታችሁ ገንዘብ አግኙ እና ለእናታችሁ ምግብ ስጧት፤ የሚያስርባትን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፣ ልብሷን ቀይሩላት፣ የሚያሳርዛትን አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፣ ስትታመም አሳክሟት፣ የሚያሳምማትን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፤ የወግ እቃዎቹን ሰብስቡና አስቀምጡላት፤ዝክረ ታሪኳን ሊያጠፋ የተነሣውን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፤ እርሱ እያረጀ ሲሄድ እናንተ ግን እያደጋችሁ ነው፡፡ ስለዚህም እየበዛችሁ እና እየመላችሁ ሂዱና ይህንን ቀፍድዶ የያዛትን የመንደሩን ሕግ አስተካክሉት፡፡ ምናልባት የእንጀራ አባታችሁ ቢሞት ሌላ የእንጀራ አባት ደግሞ እንዳይተካ፡፡ እንደዚያ ካደረጋችሁ እናንተ የእናታችሁ ልጆች ናችሁ፡፡ ያለ በለዚያ ግን የእንጀራ አባታችሁ ተባባሪዎች ናችሁ፡፡

ሸረሪት ታውቃላችሁ፡፡ ከሰው ቤት ግድግዳ ላይ ድር አድርታ፤ ወልዳ ከብዳ ትኖራለች፡፡ ቤቱ በእሳት ሲያያዝ ግን ከቤቱ ወጥታ ቀድማ የምትሮጥ እርሷ ናት፡፡ ቤቱ የኖርኩበት ነው፡፡ ወግ መዓርግ ያየሁበት ነው፤ እሳቱን በማጥፋት አስተዋጽዖ ማድረግ አለብኝ አትልም፡፡ መሸሽን ብቻ ነው የምትፈልገው፡፡ ለራስዋ ብቻ ነው የምታስበው፡፡ ይህ ከሸረሪትነቷ የመጣ ነው፡፡

እናንተ ግን ሰዎች እንጂ ሸረሪቶች አይደላችሁም፡፡ ሰዎችን እያያችሁ ከሀገራችሁ እና ከቤተ ክርስቲያናችሁ ልትርቁ አትችሉም፡፡ አያገባንም ልትሉ አትችሉም፡፡ እሳቱን ማጥፋት ትታችሁ ከእሳት ለማምለጥ ብቻ ልትሮጡ አትችሉም፡፡ ይህንን ካደረጋችሁ ሸረሪቶች እንጂ ሰዎች አይደላችሁም፡፡» አሏቸው

ይህንን ሰምተው ልጆቹ ወደ እናታቸው ተመለሱ፡፡

እስኪ እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ የዚህች ሀገር እና የዚህች ቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ፍላጎት ምንድን ነው? ይህች ሀገር እና ይህች ቤተ ክርስቲያን ያለ ረዳት እንዲቀሩ ማድረግ አይደለምን?  እናንተም እንተዋት፣ እናቁም፣ እንሽሽ ስትሉ ያለ ረዳት እያስቀራችኋት ነው፡፡ የእነርሱ ፍላጎት ኢትዮጵያን እና ተዋሕዶን ተስፋ ማስቆረጥ አይደለምን? እናንተም ተስፋ ከቆረጣችሁ ተሳካላቸው ማለት ነው፡፡ ልጆቻቸውን እያስመረሩ ማስኮብለል አይደለምን? ከኮበለላችሁ ተሳካላቸው ማለት ነው፡፡ ታሪክን፣ ቅርስን፣ ክብርን፣ ልዕልናን መመዝበር እና ማራከስ አይደለምን? እናንተም ታሪኩን፣ ቅርሱን፣ ባህሉን፣ ክብሩን ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ በራሳችሁ ዓለም ብቻ ስትቀሩ የእናንት ፍላጎት ሳይሆን የእነርሱ ፍላጎት ተሳካ ማለት ነው፡፡

ታድያ አሁን እናንተ መመለስ ያለባችሁ አንድ ጥያቄ ነው፡፡ የምትፈልጉት የጠላቶቿ ፍላጎት እንዲሳካ ነው ወይስ በመከራ ውስጥ ያለችውና ቀን የጣላት የእናታችሁ ፍላጎት እንዲሳካ ? ምረጡ፡፡

ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ማህሌት መንፈሳዊ የዩቲዩብ ቻናል

"ዛፏ አስተማረችን" መልዕክታዊ መንፈሳዊ ግጥም ይሄንን እና ሌሎች መንፈሳዊ ስነ ፅሁፎችን ለማግኘት ሊንኩን ተጫኑ 👇

https://youtu.be/GxhDSkBEW-M
https://youtu.be/GxhDSkBEW-M
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" (Tesfabel)
ኤልሮኢ:(ምክር)

ዝምተኛው መነኩሴ (#ራስአገዝ)

ከዝምተኛው መነኩሴ አባ ዮስጦስ ፀሎት አንዱ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቅዱሳን በተጓዙበት ጎዳና ምራኝ" ነበር፡፡ የዚህ ጸሎት ትርጉም ቅዱስ አድርገኝ ማለት እንደነበር በህይወታቸው ፍፃሜ በሚገባ ተረድተናል፡፡ ቅዱስ እንደሆኑ ማሰብ እንጂ ቅዱስ ለመሆን ማሰብ ወይም በቅድስና መንገድ ለመጓዝ መሻትና መጸለይ መልካም ነው፤ ምክንያቱም ከፈጣሪያችን ትእዛዛትና ፈቃድ አንዱን ለመፈጸም መመኘት ነውና እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል፡፡ እግዚአብሔር በቃሉ "እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ" እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስም "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ" በማለት የቅድስናን ህይወት እንድንኖር እንደመከረን ስናስተውል ቅዱስ የመሆን ትእዛዝ እንዳለብን እንረዳለን፡፡ ስለቅድስና ሲነሳ እኛ ቅዱሳን ልንሆን ይገባል ማለቱ በራሱ ወደር የማይገኝለት ድፍረት ሆኖ ሳይሰማን አይቀርም፡፡ነገር ግን መሻቱ ሳይሆን የቅድስና ቁምነገር ነኝ አለማለቱ እና በጭራሽም ነኝ ብሎ አለማሰቡ ላይ ነው፡፡ ሰው ቅዱስ የሚሆነውም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ባሻገር በምርጫውና በፍላጎቱ ነውና ይህን የሚያስረዳን ነው።

ዲያቢሎስ ስለመረጠ ከቅድስና ጎድሏል፥ ቅዱሳን መላእክት ደሞ በምርጫቸው ቅዱሳን ሆነዋል ፡፡ሰውም እንዲሁ ነው፡፡ ስለዚህ ለቅድስና መጠራታችንን እና መታዘዛችን እንዲፈጸምልን መጸለይ መሻት መጣር ያስፈልገናል፡፡የጌታችን አማናዊ ቃሉ "ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።"ይለናልና።(ማቴ 7:7)
ስለዚህ ቅዱስ የመሆን ፍላጎት ቅዱስ ነውና በማሰባችን ወይም በመመኘታችን ድፍረት መስሎን መጨነቅ አይደገፍም፡፡ ነገር ግን በትህትና መለመንና ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ቸርነት እንደሚፈጸም ማመን ነው፡፡ ያለ እግዚአብሔር ቸርነት (ሰጪነት) በጥረታችን የምናገኘው ምንም ነገር የለም፡፡ "እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።" (ዮሐ 15:5) እንዳለ ያለእርሱ ቅዱስ መሆን ቀርቶ ቅድስናን ማሰብም እንኳን አይቻልም፤ ከእርሱጋ ግን ሁሉ ይቻላል፡፡ ወደቅድስና ከሚመሩን በርካታ ነገሮች እጅግ ጥቂቶቹ በመቀጠል ቀርበዋል፡፡

✞የእግዚአብሔርን ቸርነት እና ፍቅር ማሰላሰል

✞ህዋሳትን ኃጢአት ከመስራት መጠበቅ

✞ ለሰሩት በደል በቶሎ መፀፀት

✞ከሰው ክብርን አለመፈለግ

✞ምስጋናን አለመሻት

✞ ጥላቻንና ትችትን በፍቅር መቀበል

✞ መጸሐፍቅዱስን አዘውትሮ ማንበብ

✞ ያለማቋረጥ መጸለይ

✞በምስጢራት መካፈል

✞ትእዛዛቱን ለመፈጸም መጣጣር

✞በምክረ ንስሀ መጓዝ

✞ራስን እንደተለየ ነገር አለመቁጠር

✞ራስን መገምገም መመልከት

✞ቃለእግዚአብሔርን ማዳመጥና

✞የምንሰማዉን ቃል መፈጸም

✞ከልብ የሆነ ጾምን መጾምና መጸለይ

✞በጎ አድራጎትን መፈጸም

ማንኛውም የምንሰራው ሥራ እግዚአብሔርን ደስ እንዲያሰኝ ብሎ እንጂ አንዳች ጥቅም አገኝበታለሁ በማለት አይደለም፡፡ መሪ ምክንያቱ ፍቅር እንጂ ጥቅም መሆን የለበትም፡፡ ለቅድስና መጋደል እንጂ ቅዱስ እንደሆኑ ማሰብ መጀመር የውድቀት መጀመሪያው ሳይሆን መጨረሻ መሆኑን ማስመር ይገባል፡፡ እነኚህ በየጥቂቱ ልናድግባቸው የምንችላቸው መንፈሳዊ ተጋድሎ የሚጠይቁ ልምምዶች ናቸው ፡፡

ይቆየን!

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
አሳስቢ
<unknown>
ኤልሮኢ:(ዝማሬ)

አሳስቢ

አሳስቢ ድንግል ሆይ አሳስቢ
አሳስቢ ስለኛ አሳስቢ
ስለ ምንዱባኑ ዘውትር ስታነቢ(×2)

መወለዱን እና በጨርቅ መጠቅለሉን
በግ እና ላሞቹ ሙቀት የሰጡትን
እርጉም ሔሮድስ ወጥቶ ሊገድለው ቢነሳ
ስለ እኛ ይታሰብ ያየሽው አበሳ

እርጉም ሔሮድስ ወጥቶ ሊገድልሽ ቢነሳ
ስለ እኛ ይታሰብ ያየሽው አበሳ
የግብፅ በረሀ ነባልባል አሳስቢ
ስለ ደሀ አደጎች ዘውትር ስታነቢ

ረሀቡን ጥሙን ችግሩን ሀዘኑን
ከእርሱ ጋር በስደት የደረሰብሽን
ከዓይኖችሽ መውረዱን የመረረ እንባ
የአምላክ ሆነሽ ሳለ ላንቺ ማይገባ

ረሀቡን ጥሙን ችግሩን ሀዘኑን
ከእርሱ ጋር በስደት የደረሰብሽን
ከዓይኖችሽ መውረዱን የመረረ እንባ
የአምላክ እናት ሆነሽ ላንቺ ሳይገባ

ዕጣን ነሽ ማርያም ልጅሽም ዕጣን ነው
የተመረጠ ነው እኛን ያዳነን
ኢየሱስ ክርስቶስ ምዑዝ ነው ልጅሽ
ይታሰብ ይወሳ ስደትሽ መከራሽ

#ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(ምስባክ)

ነሐሴ 7/12/2013 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን :- ዕብራው - 9:1-11
ንፍቅ ዲያቆን :- 1ኛጴጥሮስ - 2:6-18
ንፍቅ ካህን :- የሐዋሥራ - 10:1-30

ምስባክ:- መዝ 93:12
ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ
ወዘመሀርኮ ሕገከ
ከመ ይትገሃሥ እመዋዕለ እኩያት፡፡

ትርጉም
አቤቱ አንተ የገሠጽኸው
ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ምስጉን ነው
እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥልምና፡፡

ወንጌል:- ማቴዎስ16:13-24
ቅዳሴ፡ ዘእግዝእትነ(ጎሥዓ)



@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

#ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ?
#ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል?
#ሙልሙል ለምን ይታደላል?
#ጅራፍ ለምን ይጮሃል ?

#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

#ጅራፍ
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

#ችቦ
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ #በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡

#ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡ ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ….” ይላሉ፡፡
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና
ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡
ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሰወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል ፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ምስባክ
ዝማሬ ዳዊት
ኤልሮኢ:(ምስባክ)

​ነሐሴ 13/12/2013 ዓ.ም
ደብረ ታቦር

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ ዕብ 11÷23-30
ንፍቅ ዲያቆን፦ 2 ጴጥ 1÷15-ፍ.ም
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 7÷44-51

#ምስባክ ፦ መዝ 88፥12-14
ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌስሁ ወይሴብሑ ለስምከ
መዝራዕትከ ምስለ ኀይል

#ትርጉም
ታቦር እና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል
ስምህንም ይመሰግናሉ
ክንድክ ከኃይልክ ጋር ነው

#ወንጌል ፦ ሉቃ 9÷28-38
#ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

​​​​ጳጉሜን

ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ተውሳክ ማለት ሲሆን ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ሌሎች ሀገሮች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ያደርጓታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ እኛ የወርን ቁጠር 30 ስናደርግ እነርሱ 31 ብለው የሚቆጥሩት ወር አላቸው፡፡ ይኹን እንጂ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡

ጳጉሜን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ትመጣለች፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ጳጉሜን ስድስት ቀን ትሆናለች፡፡ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃለች፡፡ ጳጉሜን ስድስት በምትሆንበትም ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈትቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡

በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው። ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዎች ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡

የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡

ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፥2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡

ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡

የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብባትም ወር ነች፡፡ ይህም ጳጉሜን የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና፡፡

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
እንኳን አደረሳችሁ!!!
ሠላም ለእናንተ ይሁን ውድ ኦርቶዶክሳዊያን ቤተሰቦቻችን ሼር በማድረግ ለወንድም እህቶቻችው አድርሱልን ።
ሰላመ እግዚአብሄር አይለየን።
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ጥቅምት ፲፮ (16) ❖

✞✞✞ እንኳን አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ 7ቱ ኪዳናት ወአባ ያቃቱ ሊቀ ዻዻሳት +"+

+"+ 7ቱ ኪዳናት +"+

=>"ተካየደ" ማለት "ተስማማ: ተማማለ" እንደ ማለት
ሲሆን "ኪዳን" በቁሙ "ውል: ስምምነት" እንደ ማለት
ነው:: ይኸውም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር: ሰዎችም
ከሰዎች ጋር የሚያደርጉት ሊሆን ይችላል:: ልዩነቱ
የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቅዱስና የማይለወጥ መሆኑ ነው::

+እግዚአብሔር አምላክ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ በየጊዜው
ከብዙ ወዳጆቹ ጋር ኪዳንን አድርጉዋል:: ቅድስት ቤተ
ክርስቲያንም እነዚህን ኪዳናት ጥቅልል አድርጋ 7 እንደ
ሆኑ ታስተምራለች:: ስለዚህም ዛሬ ፈጣሪ ቢረዳን
እነዚሁን 7 ኪዳናት በጥቂቱ እንመለከታለን::
"ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ"
"ከመረጥኩዋቸው ጋር ቃል ኪዳንን አደረግሁ" (መዝ. 88:3)

(1) +"+ ኪዳነ አዳም +"+

=>አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት:
የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው::
እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ
አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን አባታችን
በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: (ዘፍ. 3:1)

+አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን
ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን
ተቀበሉ:: (ቀሌምንጦስ: ገላ. 4:4)

(2) +"+ ኪዳነ ኖኅ +"+

=>ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ባሉት 10 ትውልድ ዓለም
በዓመፃ ተሞላች:: ቅዱስ ኖኅ በደግነቱ መርከብ ሠርቶ
ቤተሰቡን ሲያተርፍ ዓለም በማየ ሥራዌ ጠፋች::
ከመርከቡ ከወጣ በሁዋላ ኖኅና እግዚአብሔር በቀስተ
ደመና ምልክትነት ቃል ኪዳን ተጋቡ:: "ኢያማስና
ለምድር ዳግመ በማየ አይኅ" እንዲል:: (ዘፍ. 9:12)

(3) +"+ ኪዳነ መልከ ጼዴቅ +"+

=>መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ: የክርስቶስም
ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉሥ ነው:: በ15 ዓመቱ
መንኖ: አጽመ አዳምን ይዞ: በቀራንዮ በሕብስትና በወይን
ያስታኩት ነበር::

+እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን
ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ አድርጐ
በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ
ሞትን እስካሁን አልቀመሰም:: ይህም ካህኑ መልከ
ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: (ዘፍ. 14:17, ዕብ. 7:1)

(4) +"+ ኪዳነ አብርሃም +"+

=>ቅዱስ አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት: ሥርወ
ሃይማኖት: የጽድቅም አበጋዝ ነው:: ስለ ፍቅረ
እግዚአብሔር ሲል ከርስቱና ከወገኖቹ ተለይቶ በቅድስና
ኑሯልና እግዚአብሔር "በዘርሕ አሕዛብ ይባረካሉ"
አለው:: (ዘፍ. 12:1) የቃል ኪዳን ምልክትም ይሆነው
ዘንድ ግዝረትን ሰጠው:: (ዘፍ. 17:1-14)

(5) +"+ ኪዳነ ሙሴ +"+

=>ቅዱስ ሙሴ የነቢያት አለቃ: የእሥራኤል እረኛ:
የእግዚአብሔር ሰው እና ፍጹም ትሑት (የዋህ) ሰው
ነው:: በፈጣሪው ትዕዛዝ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት
አውጥቶ ለ40 ዘመናት በበርሃ ሲመራቸው
ከእግዚአብሔር የኪዳንን ጽላትና አሠርቱን ትዕዛዛት
ተቀብሏል:: (ዘጸ. 20:1, 31:18)

(6) +"+ ኪዳነ ዳዊት +"+

=>ቅዱስ ዳዊት ሥርወ ነገሥት: ጻድቅ: የዋህና ቡሩክ
የሆነ አባት ነው:: እግዚአብሔር ከእረኝነት ጠርቶ ንጉሥ
አድርጐ ሹሞት "ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ
አኖራለሁ" (መዝ. 131:11) ሲል ምሎለታል:: አክሎም
ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቶ "አልዋሰሽህም" ብሎ ሲምልለት
እንመለከታለን:: (መዝ. 88:35)

(7) +"+ ኪዳነ ምሕረት +"+

=>በብሉይ ኪዳን የነበሩ 6ቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና
ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል
ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን
ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም
ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል
ማርያም ማሕጸን አደረ::

+በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ:
ተጠምቆ: አስተምሮ: ሙቶ: ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ
ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው:: ኪዳነ ምሕረት
(የምሕረት ኪዳን) የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው::

+የጌታችን መጸነሱ: መወለዱ: መሰደዱ: መጠመቁ:
ማስተማሩ: ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ: መሰቀሉ:
መሞቱና መነሳቱ: ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ
በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል:: ታዲያ ይህ ሁሉ
የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት::

+የእርሷ ኪዳን የ6ቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ
"የኪዳናት ማሕተም" ይባላል:: የድንግል ማርያም ኪዳኗ
ከሲዖልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና::
መድኃኒታችን ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን
ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ ጐልጐታ ላይ ነው::

+እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ
ሆይ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን
እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና:: ይሔው በእመ
ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና
ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ 2ሺ ዓመታት ሆኑ::
ዛሬም እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን
በጥላዋ ሥር እንኖራለን::

*" ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ: ኃጢአተነ: ወጌጋየነ፡፡
ማርያም እሙ ለእግዚእነ፡፡
በኪዳንኪ: ወበስደትኪ ድንግል ተማሕጸነ:: "*

"ድንግል ሆይ! ኃጢአታችን: አበሳችንና በደላችንን
አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ ተማጽነናል::"

=>ቸሩ ልጇ ከበረከተ ኪዳኗ አይለየን::

+"+ አባ ያቃቱ ሊቀ ዻዻሳት +"+

=>በምድረ ግብጽ ከተነሱና ለመንጋው ከራሩ አበው
ዻዻሳት አንዱ አባ ያቃቱ ናቸው:: አባ ያቃቱ መጻሕፍትን
የተማሩ: በገዳምም የኖሩ በመሆናቸው እንደ
ቀደምቶቻቸው ቤተ ክርስቲያኗን በቅን መርተዋል::

+ፓትርያርክ ሆነው ከተሾሙ በሁዋላ ብዙ ጭንቅ ያሳለፉ
ሲሆን እግዚአብሔር አቅሎላቸዋል:: ከማረፋቸው
በፊትም ከእርሳቸው ቀጥለው የሚሾሙትን በጸጋ
ተናግረዋል:: አባ ያቃቱ ለግብጽ 49ኛ ሊቀ ዻዻሳት
ናቸው::

=>በረከታቸው ይደርብን::

=>ጥቅምት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.አባ ያቃቱ ሊቀ ዻዻሳት
2.ጻድቃን እለ ድርቂ
3.አባ ዻውሊ ገዳማዊ
4.አባ ማርቆስ መስተጋድል
5.አባ አሮን መስተጋድል

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (የቅ/ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዳንኤል ጻድቅ
7.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ (ወንጌሉ ዘወርቅ)

=>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ::
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው::
ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው::
በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . .
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ::
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ::
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ.
44:12-17)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

ዝክረ ቅዱሳን ማኀበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" (Tesfabel)
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

እርሱ ኃያል ሲሆን የሰው ፍቅር አገብሮት ወደዚች ምድር በትህትና መጣ። የማይታይ ረቂቅ ሲሆን ስለ ፍቅር ሲል ግዘፍ ሥጋን ተዋሐደ ። ባለጸጋ ሲሆን ምንም እንደሌለው በበረት አደረ። እኛን ከፍ ያረገን ዘንድ እርሱ ዝቅ አለ። አምላክ ሲሆን በትህትና በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ። ፍጥረትን ሁሉ የሚመግብ ሲሆን እርሱ ግን 40ቀንና ሌሊት ፆመ ተራበም። የህይወት ውሃ ሲሆን እርሱ ግን ተጠማ። እርሱ የሁሉ ፈራጅ ሲሆን በፈራጅ ፊት ቆሞ ተፈረደበት። የአዳምን ቁስል ይፈውስ ዘንድም ተገርፎ ቆሰለ። የአዳምን የበደል ሸክም ያቀል ዘንድ የእርሱ ጀርባ በጨካኝ ሮማውያን ወታደሮችን ጅራፍ ተገረፈ ። የክብር ባለቤት እርሱ እኛ እንከብር ዘንድ ተዋረደ ምራቅም ተተፋበት። ዘላለማዊን ንጉስ አይሁዳውያን ዘበቱበት። ለሠማዕታት የክብር አክሊልን የሚያቀዳጅ እርሱን ስለ እኛ ፍቅር የእሾህ አክሊልን ተቀዳጀ ። የእኛን ሸክም ያቀል ዘንድ ርጥብ መስቀልን ተሸከመ ከወደቅንበት ያነሳን ዘንድ ወደቀ። የእኛን ፊት በብርሃን ይሞላ ዘንድ የእሱ ፊት በደም ተሸፈነ። እርሱ ቁስላችንን ቆሰለ ህማማችንን ታመመ። እንጀ ቆዳ በእንጨት ላይ ተወጠረ በመስቀል ላይ ተሰቀለ እርሱ ስለ እኛ ራሱን ቤዛ አድርጎ ሠጠን።

ወዳጄ ሆይ እርሱ ለእኛ ራሱን ሰጠ እኛስ ለእርሱ ምን እንሰጠው ይሆን?

በረከት(ወልደ ሰንበት)
የካቲት 6/2013

@aleroe
ኤልሮኢ፡

.....ትህትና በአባቶች ሕይወትና ትምህርት ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ ይገኛል። ቅዱስ ያዕቆብ እንዲህ ብሏል ስለ ትህትና ማስተማር እፈልጋለሁ። ደግሞ እፈራለሁ። ስለ እግዚአብሔር ለመናገር እንደሚፈራ ሰው እመስላለሁ። ምክንያቱም ትህትና መለኮት ሰው ሆኖ በምድር ሲገለጥ የተጠቀለለበት መጎናጸፊ ነውና። ሰው ሆኖ በአጭር ደረት በጠባብ ቁመት የመገለጡም ምሥጢር እጅግ አስደናቂ በሆነ በትህትናው ነው። ይሄ ሁኔታው ያስደነቀው ነቢዩ ኢሳይያስ "ያልተጠባበቅነውን የጽድቅ ሥራህን ባደረግህ ጊዜ ወረድህ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ" ኢሳ. 64፥4 ብሏል። ሰይጣን ትሁት ሰው ሲያይ የሚፈራው በትሁት ሰው ውስጥ የፈጠረውንና በትህትና ያሸነፈውን እግዚአብሔር ስለሚያየው ነው።

@aleroe
#የልደት_ወረብ

ቤዛ ኲሉ ዓለም ዮም ተወልደ /2/
የዓለም ሁሉ መድኃኒት ዛሬ ተወለደ /2/

💚 @aleroe
#ባሰማት_ጊዜ

ስሙ ገብርኤል የተባለ
ለድንግል ነገራት መልካም ዜና
እንደምትወልደው ወልድን በድንግልና/2/

ባሰማት ጊዜ ቃሉን
ቅዱስ ገብርኤል በለዛ
ድንግል ቀረበች ወደ እርሱ
ፍጹም ትኅትናን ይዛ

ትፀንሻለሽ ሲላት መልአኩ
ፍጹም በልቧ ሳትመካ
እንደ ቃልህ ይሁን አለችው በቃሉ ተማርካ /2/

#አዝ

የዓለም መድኀኒት ነውና
ከአንቺ የሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ
ትሰይሚዋለሽ ስሙንም ብለሽ ኢየሱስ /2/

#አዝ

ዕፁብ ድንቅ ነው ለሁልጊዜ ለ
ድንግል ማርያም የተሰጣት እድል
የአምላክ እናት ሆኖ መመረጥ
ከሴቶች መካከል /2/

#አዝ

ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ
ይገባሻል ለአንቺ ክብርና ምስጋና
የክብር ባለቤት ሁል ጊዜም
ከአንቺ ጋር ነውና /2/

💚 @aleroe
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" (Tesfabel)
Abiye-Tsome-Hudade.pdf
60.6 KB
ትምህርት

ስለ ዐቢይ ፆም

💠.ዐቢይ ለምን ተባለ ?
💠.ስንት ሳምንታት አሉት ?

አጠር ብሎ የተዘጋጀ
ያንብቡ share ያድርጉ

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:

#እንኳን ለዐብይ ፆም በሰላም አደረሰን
☞ፆም ማለት ምን ማለት ነው?
☞የአብይ ስያሜዎች ስንት ናቸው?
☞የአብይ ፆም ለምን ታላቁ ጾም ተበለ?
☞የአብይ ጾም ስንት ክፍሎች አሉት?
☞የአብይ ጾም ለስንት ሳምንት ይፆማል
☞ስለ ዘወረደ ምን ያውቃሉ?

1ኛ. ፆም ማለት ምን ማለት ነው?
ፆመ ፦ ተወ " ታቀበ"ታረመ ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው።
ፍቹም ምግብን መተው ' መከልከል' መጠበቅ ማለት ነው።
ፆም ማለት ሰውነት ከሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል መወሰን ማለት
ነው። ወይም ለሰውነት የሚያምረውን የሚያስጎመጀውን ነገር መተው ማለት
ነው ።
ፆም ከሃይማኖት ጋር ዝምድና ስላለው ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ፆም አለ።
ፆም በብሉይ እና ኪዳን ከፍተኛ ቦታ አለው ።
ነብያት ከእግዚአብሄር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውሃ በአፋቸው አይገባም
ነበር።//ዘፀ ፴፬÷፳፰//34*28//
በሐፂያት ብዛት የታዘዘውን የእግዚአብሔርን መዓት የሚመልሰው ሕዝቡ በፆም
ሲለምኑት ሲማልዱት ነበር። //ዮሐ ፪÷፯_፲// 2*7-20//
በሐዲስ ኪዳንም ፆም ሰው ሰራሽ ህግ ሳይሆን እራሱ መድኃኒታችን በመዋዕለ
ስጋዌው የስራ መጀመሪያ አድርጎ የሰራው ህግ ነው።//፬÷፪// 4*2//
ይህ ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ እርኩስ ሰይጣን እንኳን
በፆም እሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል።// ማቴ ፲፯÷፳፩//
17*21/ሐ
ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የታዘዙ ሐዋሪያትም ከመንፈስ ቅዱስ በየጊዜው
ትዕዛዝ እሚቀበሉበት በፆም እና በፆለት ላይ እንዳሉ ነበር።// የሐዋ
፲፫÷፪//13*2//
ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናት ቀሳውስት የሚሾሙት በፆምና
በፆለት ነበር።//የሐዋ፲፫÷፫//13*3//
ፆምስ በታወቀው እለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ መከልከል ነው።
ፆም ማለት፦ጥለላት ማባልዕትን ፈፅሞ መተው ሰውነትን ከመብልና ከመጠጥ
ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ መጠበቅ ፣መገዛት፣ መቆጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ
በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ይቅር በለኝ በማለት ቅድመ
እግዚአብሔር በመንበርከክ ምህረት በአምላክ ለመቀበል መዘጋጀት ነው።
ፆም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፣ሀይለ ፍትወትን የምታደክም የበጎ ምግባር
ሁሉ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ፀጋን የምትሰጥ ፣የወንጌል ስራ መጀመሪያ፣
የፅሙዳን ክብራቸው፣ የደናግል እና የንፅህና ጌጣቸው
፣የንፅህና መገለጫ፣ የጸሎት ምክንያት እናት፣ የእንባ መገናኛ መፍለቂያ፣
አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ስራ ሁሉ የምትነቃቃ፣ ሰውነትን
በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትህትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ
መድኃኒት ነፍስ ናት።
ከህገ ልቦና ከነበሩ አበው አንስቶ በዘመነ ኦሪት እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ
በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ ቀደምት አበው ነቢያት፣ ነገስታት፣ካህናት በፆምና
በጸሎት ፅሙድ ሁነው እግዚአብሔር አምላካቸው ከክፉ ነገር እንዲሰውራቸው
በይቅርታ እንዲጎበኛቸው ሀይልንም እንዲያጎናፅፋቸው ተማፅነው ሀሳባቸውን
ፈፅሞላቸዋል።
በሀድስ ኪዳን ፆም ስለ ፅድቅ ተብሎ መከናወን ያለበት አብይ ተግባር ነው። //
ማቴ፭÷፮// 5*6//
ስጋዊ ጥቅምን ለማግኘት ተድላ ስጋን በመሻት ሳይሆን ዘላለማዊ መንግስት
ለመውረስ ስለ ፅድቅ ተብሎ የሚፈፀም ነው።
ፆም እንደምን ነው ቢሉ የስጋ ምግባር ነው።
ምፅዋት የገንዘብ ግብር እንደሆነች:አንድም ምፅዋት ስጋን መገበር ነው።
ምፅዋት ገንዘብ መገበር እንደሆነች። ~~~ስለዚህ የሚፆም ሰው በፈቃደ
ስጋው ላይ ድልን ይቀዳጃል።
በእምነት ሁኖ የለመነውን እግዚአብሔር ይሰጠዋል። ሰማያዊ የሆነውን
ምስጢር ለማየት ከአለማዊ ነገሮች ተለይቶ ይነጠቃል።
በአለም እየኖረ ከአለሙ ይለያል። ከአለም አይደለምና//
ዮሐ፲፭÷፲፱//15*19 //

2ኛ.
ዐቢይ ጾምም ቤተክርስቲያናችን እንድንጾም ካወጀችልን ጾም አንዱ ነው፡፡
ዐቢይ ጾምየተለያዩ ስሞች አሉት፡፡ አንደኛ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም በመሆኑ እንዲሁም ዐቢይ
እግዚአብሔር ወዓቢይ ኀይሉ ዓቢይ እግዚአብሔር ወብዙኃ አኰቴቱ የተባለ
ጌታ የጾመው ስለሆነ፣ /መዝ.47፥1፣ መዝ.146፥5/፡፡ ሁለተኛ ሁዳዴ ጾም
ይባላል፡፡ ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት
ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲሆን ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ
አምላካችን ስለጾመው ነው፡፡፣ /አሞ.7፥1/፡፡ ሦስተኛ በዓተ ጾም ይባላል፡፡
የጾም መግቢያ፣ መባቻ ወይም ጾሙ የሚሰፍርበት በዓት ማለት ነው፡፡ አራተኛ
ጾመ አርባ ይባላል፡፡ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው 40 /ዓርባ/ ቀን
ስለሆነ፣ /ማቴ.4፥1/ አምስተኛ ጾመ ኢየሱስይባላል፡፡ ጾሞ፣ ጹሙ ብሎ
ስላዘዘን፣ ስድስተኛ ጾመ ሙሴ ይባላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ሰኞ ዕዝል
ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም፣ ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት እያለ በጾመ
ድጓ ስለ ዘመረ ነው፡፡
ዐቢይ ጾምጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ማቴ.4፥1
ምእመናን ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል፡፡ ዐቢይ ጾም
ስምንት ሳምንታት /55 ቀኖች/ አሉት፡፡ ሰባት ቅዳሜ ስምንት እሑድ ይገኛሉ፡፡
አሥራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጦሙ
የጦሙ ወራት አርባ ቀን ብቻ ይሆናል፡፡

3ኛ.
የአቢይ ጾም ሦስቱ ክፍሎች
1. ዘወረደ (ጾመ ሕርቃል)፤ ይህም ጾሙ ከሚገባበት
ሰኞ ጀምሮ እስከ እሑድ ያረስ ያለው 7 ቀን ነው።
2. የጌታ ጾም፤ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና
ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው 40 ቀን ነው።
3. ሕማማት፤ ይህም ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ
ከተቀመጠበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር
ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት
ነው።
ይህም 7+40+8 = 55 ቀን ማለት ነው።

4ኛ.
የአብይ ጾም ሳምንታት 8 ናቸው፤
ዘወረደ
ቅድስት
ምኩራብ
መጻጉዕ
ደብረዘይት
ገብርሔር
ኒቆዲሞስ
ሆሣዕ

ሰለ ተትርጉማቸው ከታች ከተለጠፈው ሰንጠረዥ ተመልከት

5ኛ. ለምን አብይ / ታላቅ
ተባለ
አብይ ፆም መባሉ ትልቅና ታላቅ ፆም መሆኑን
ለማሳወቅ ነው። ይህ ፆም ታላቅ
መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መፆሙና
ከሌሎቹ አፅዋማት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር
መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ
ቆሮንቶስ መፆም ሳይገባው ለእኛ አርአያና
ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የፆመው ፆምም
በመሆኑ ነው

6ኛኛ.
የመጀመሪያ የአቢይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም
ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ስያሜውም፤ በ 614 ዓ . ም ኪርዮስ የተባለ
የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60 ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ 14 ዓመት በኋላ በ 628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡

@aleroe
#ዜና_ዕረፍት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ።

ሃሌ ሉያ ግሩማን መላእክት ሱራፌል ወኪሩቤል እለ አክናፊሆሙ ነበልባል ወረዱ ዮም ይተቀበሉከ በብሒል አማን መርቆሬዮስ

#በዕለተ_መርቆሬዎስ_መርቆሬዎስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም በትናንተናዎ ዕለት ከለሊቱ 6 ሰዓት ዐርፈዋል።

አቡነ መርቆርዮስ ከብፁዓን ጳጳሳት ጋር ከሀያ ስድስት ዓመት ስደት በኃላ ሐምሌ 25/2010 ዓ.ም አስራ ዘጠኝ ሊቃነ ጳጳሳት እና አገልጋይ ካህናት ጋር ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል።

#ከስደት_ወደ_ሃገራቸው_የተመለሱትም_ያረፉትም_በዕለተ_መርቆሬዎስ_ነው

በረከታቸው አትለየን።
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

@FENOTESELAM27
❖◈❖◈❖◈❖◈❖◈❖◈❖◈❖◈❖◈
|የቡራዩ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት