"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ኤልሮኢ:(ምክር)

#ወዳጄ ሆይ!

የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡

አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡ ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(መዝሙር)

አዝናለሁ አለቅሳለሁ

አዝናለሁ አለቅሳለሁ
ስለ በደሌ ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ
አዝናለሁ አለቅሳለሁ
ስለ ጥፋቴ ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ
ነገር ግን መሐሪ ነህና
እንደምታድነኝ አምናለሁ

ሥጋዬ ለራሱ እያታለለኝ(፪)
ሁሉን በመፈለግ ወሰደና ለጥፋት ሰጠኝ(፪)
አዝ = = = = =
ከመሬት ተገኝታ እስክትገባ
በከንቱ አስቀረችኝ አምላኬ ሆይ ሥጋ ሰገብጋባ(፪)
አዝ = = = = =
ትቻት መምጣቴ ነው አፈር ሥጋዬን
እንድትቀበላት አምላኬ ሆይ አደራ ነፍሴን(፪)

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ትርክት)

"አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ"

ከእለታት አንድ ቀን አንድ ወጣት የንስሀ አባቱን ለማግኘት ተንስቶ ወደ ቤተክርስቲያን ይሄዳል። ፀሎቱን አድርሶ ግቢ ውስጥ ቁጭ እንዳለ አባ ይመጡና በመስቀል ባርከው ደባብሰው ወደ በአታቸው ይዘውት ይገባሉ። ታድያ ልክ እንደ ገባ የክርስቶስን ስነ ስቅለት የእሾሁን አክሊል ያይና በሀሳብ ወደ ቀራንዮ ይሄዳል። አባ ምነው ልጄ እኔን እዚህ ትተህ አንተ ወደ ቀራንዮ ሄድክ ሲሉት ከሀሳቡ ባህር ወጥቶ ቁጭ አለ።

አባ አየህ ልጄ ምን ሆነ መሰለህ ብለው ጨዋታ ጀመሩለት። "በአንድ ሀገር ትልቅ የባቡር መንገድ ነበር ታድያ የባቡሩ መንገድ ታቹ ባህር ነው በጣም ትላልቅ አዞዎች አሉበት። አንድ ቀን ታድያ ይህ መንገድ ኃይለኛ ዝናብ በመጣሉ ምክንያት ይፈርሳል። አንድ ህፃን ልጅ ይህን ሁኔታ አይቶ ኖሯል ባቡሩ እዛ ቦታ ሳይደርስ ለማስቆም ወሰነና የአደጋ ምልክቶችን ፅፎ በተለያየ ርቀት 2 ቦታዎች ላይ አስቀመጠ። ከዚያም 3ኛው ላይ ባንዲራ ይዞ እራሱ ቆመ ባቡሩም መጣ ልክ የመጀመሪያውን የአደጋ ምልክት ሲያይ ይህ የዱርዬዋች ስራ ነው ብሎ ተበሳጭቶ አለፈ። ሁለተኛውንም እንዲሁ አለፈ። በሶስተኛው ህፃኑ ጋር ደረሰ ጥሩንባውን እያጮኸ ዘወር በል አለው ልጁ ግን በጭራሽ ዘወር ሳይል ባቡሩ እዛው ፈጨው የባቡሩ አሽከርካሪ በጣም ደነገጠ ተሳፋሪዎችም ወረዱ ልጁን ሲያዩት የለም ደቋል። ነገር ግን በእጁ የነበረው ወረቀትና ባንዲራ ወድቆ አገኙት አንስተው ሲያነቡት በዝናቡ ምክንያት ድልድዩ መፍረሱን ነበር የሚያሳየው። እውነትም ጠጋ ብለው ሲያዩ ድልድዩ ፈርሶ አዞዎቹ ብቅ ብቅ ብለው መልአከ ሞት የሚጥልላቻውን ነፍስ የሚጠብቁ ነበር የሚመስሉት። ከዛ ሁሉም በጣም አዘኑ አለቀሱ ለእነርሱ መትረፍ ያ ህፃን ልጅ የከፈለውን መስዋዕትነት ተገነዘቡ አንዱ ስለ ሁላቸው ሞቶ እነርሱን አተረፈ። ይህ ሁሉ ስለ ሰዎች ፍቅር ነው።"

አየህ ልጄ ክርስቶስም ለኛ እንዲህ ነው አሉት ሳያውቁ ሁለቱም በጣም አልቅሰው ነበር በልጁ ታሪክ። "አባቴ እኔ'ኮ ከንቱ ሰው ነኝ እግዚአብሔር እኔን ይቅር ይለኛል?" አላቸው "ልጄ እግዚአብሔር ይቅር ባይ ነው። ግን መጀመሪያ አንተ ቀዶ ጥገና ያልስፈልግሃል" አሉት። "ምን አይነት ቀዶ ጥገና አባቴ?" "ይሄውልህ ልጄ የእስከ አሁኑን ልብህን ልናክመው ይገባል ዳግመኛ ወደ ቀደሞው መጥፎና ኃጢአት የበዛበት ህይወት እንዳትመለስ። ከዚያ ንስሀ የሚባለውን የህይወት መድኃኒት ትወስድና ትድናለህ" አሉት፡፡ ወጣቱም ሁሉን ተናዞ ንስሀ ገብቶ ተፀፅቶ ትላንትን ዳግም ላያየት ከእውነት ጋር ታርቆ ጤናማ ህይውቱን መኖር ጀመረ።


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ምክር)

የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም!!

የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው። ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡
የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደ ወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹሕ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደ ተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ቃላቶችህ የተመጠኑና ጤናማዎች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @aAleroebot
ኤልሮኢ:(ስነፅሁፍ)

🖌……ቅን ከሆንን

ፍቅር ካለ፣
ኅብረት ካለ፣
መደጋገፍ ከታከለ፣
እርስ በእርስ ከተዋደድን፣
ሁላችንም ከተሳሰብን፣
አምላክችን ከእኛ ጋር ነው፣
ምንፈልገው በእጃችን ነው።
ሀዋርያት እንደሰሩት፣
ተደጋግፈው እንደኖሩት ፣
በኛ መሀል ፍቅር ካለ፣
መተሳሰብ ካልጎደለ፣
ማን ተጋፍቶን ማን ደርሶብን፤
መሀላችን ማን ገብቶብን፤
የአምላክን ቃል ከፈፀምን፤
ለሰው ሁሉ ቅን ከሆንን።


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ምክር)


#እውነተኛ ወዳጅ


እውነተኛ ወዳጅ፥ ወዳጅ መኾኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው፡፡ ኹላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሠራለን፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ኾነን ለማለፍ እንጥራለን፡፡ ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን፡፡ ወይም ምንም እንዳላጠፋ ሰው ለመምሰል እንሞክራለን፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል፡፡

አንተ ሆይ! እስኪ ራስህን መርምር፡፡ ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህ? ጓደኛህ ኃጢአት ሠርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ ይቅርታው ያደረገው ይቅርታ ትክክለኛ እንዳልኾነ እንዲያውቅ ታደርጓለህን? እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ምናልባት ጓደኛህ አለአግባብ ሊቈጣህ ይችላል፡፡ ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኃጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትኾነው?

ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊኾን የሚገባውን መኾን አለበት፤ ስንቈጣው እንኳን ቁጣችንን ታግሦ ስናጠፋ የሚያርመን ሊኾን ይገባል፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ጓደኝነት ጥልቀት አይኖረውምና፤ ጓደኞች ነን መባባላችን ጥቅም የለውምና፡፡

ልናውቀው የሚገባን ነገር ግን አለ፡፡ ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው አይገባንም፡፡ ተግሣጻችን ኹልጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ሌላውን መልካምነቱን የሚክድ መኾን የለበትም፡፡ ጥፋቱን ስንነግረው ኹልጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ እንዲኾን ማድረግ አለብን፡፡ ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሣ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልኾነ እንዲያውቅ ማድረግ አለብን፡፡ እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና፡፡


┈┈ • ┈┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈•┈┈┈

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ምክር)

...........የሀጢያት ትንሽ ..............

ዲያብሎስ ልጅነታችንን እናቆሽሽ ዘንድ በእኛ ላይ የሚተናኰለው ተንኰል በጣም ተደጋጋሚና ኃይለኛ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን መንቻካ የዲያብሎስን ደባ ድል እንነሣ ዘንድ ዘወትር ንቁዎችና ጠንቃቆች ልንኾን ይገባናል፡፡ እኛ ይህን ማድረግ ሳንችል ቀርተን እጅግ ጥቂት መግቢያ ቀዳዳ የምንተውለት ከኾነ ግን እርሱ ጥቂቷን ቀዳዳ ሰፊ በር ያደርጋታል፡፡ እንዲህ አድርጎም ኃይሉን ኹሉ ተጠቅሞ ወደ እኛ ይገባል፡፡

ስለዚህ ስለ ድኅነታችን የሚገደን ከኾነ እንደዚህ ጥቂትና ቀልድ በሚመስሉ ነገሮች እንኳን አንዘናጋ፤ እርሱ የሚንቀውና ጥቂት የሚለው ኃጢአት የለምና፡፡ እኛ ጥቃቅን የምንላቸውን ነገሮች መነሻ አድርጎ ልጅነታችንን የምናቆሽሽበትን ታላላቅ ኃጢአቶችን እንድንሠራ አድርጎ እጅግ ይተጋልና፡፡

🖌……ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ስነፅሁፍ)

#መጎዳቴን_አይቶ


መጎዳቴን አይቶ
ሊቀይር ታሪኬን
ካለሁበት መጥቶ
ሊሞላው ጓዳዬን
መዳን ትወዳለህ ?
ብሎ ቢጠይቀኝ
የሰለለ አካሌን
በአይኔ እያማተርኩኝ
እወዳለሁ ! አልኩት
መፈወስን ሽቼ
የመጥምቁ አምላክ
መሆኑን ሰምቼ፡፡
የጫማውን ጠፍር
መፍታት የተሳነው
ዛሬ ሽባ እግሮቼን
መፈወስ ተቻለው፡፡
ዳንኩኝ በጸበሉ
በእጁ ተጠምቄ
ለምስክር በቃው
በምልጃው ደምቄ፡፡

ከረዳኢ ሃዱሽ
___________



@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ: (ትምህርት)

#ዝምታ

#ብፁዕ_አቡነ_ሽኖዳ ......

ዝምታ በመጀመሪያ ደረጃው ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የአንደበት ስህተትን መግታት ማለት ነው፦ " በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።" ምሳ. 10 ፥ 19። ቅዱስ አርሳኔዎስም እንድህ ብሏል ፦ " ብዙ ጊዜ እናገርና እፀፀታለሁ ስለ ዝምታየ ግን ፈጽሞ ተፀፅቼ አላውቅም ።"

በሌላ በኩል ዝምታ ማለት እግዚአብሔር ይሠራ ዘንድ የሰውን ጥረት ማቆም ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አስመልክቶ ሲናገር እንድህ ብሏል፦ .." እግዚአብሔር ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ ። እግዚአብሔር ስለእናንተ ይዋጋል እናንተም ዝም ትላላችሁ .." ዘጸ. 14፥ 13-14።

አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰው ለራሱ የማይበቀልና ክፉን በክፉ የማይቃወም ከሆነ ዝምታ እርጋታ ይሆናል።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም .1ኛ ጴጥ. 2፥23። በአይሁድ ሸንጎ ፣ በሐና ፣ በቀያፍ ወይም በጲላጦስ ፊት ሲከሱት ዝም ነው ያለው።

ዝምታ ውስጥ ግን ኃይል ስለነበረ አገረ ገዥው ጲላጦስ ".. እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኜሁበትም ።" ( ዮሐ . 18 ፥ 38) በማለት ተናግሯል።

ከዚህ በተጨማሪ ዝምታ ለፀሎት ለተመስጦ እድሉን ያደላል።
ብዙ የሚያወራ ሰው ለመፀለይም ሆነ ለውስጣዊ መንፈሳዊ ድርጊት ዕድል አይኖረውም።

አንድ ቅዱስ ሰው".. ብዙ የሚናገር ሰው ውስጡ ባዶ መሆኑን ይገልጣል ።" ብሎ መናገሩ ትክክል ነው። ይህም ማለት ውስጣዊ መንፈሳዊ ሥራ የለውም ማለት ነው።
ቅዱስ አርሳኔዎስ ስለዝምታውና ስለ ምናኔው በተጠየቀ ጊዜ ".. በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋር መሆን አልችልም ።" ብሎ መልሷል።

አንድ ታላቅ መንፈሳዊ አባት የተናገሩት ቃል ምንኛ ድንቅ ነው ፦ " .. ልብህ ይናገር ዘንድ አንደበትህን ዝም አሰኜው እግዚአብሔር ይናገር ዘንድ ልብህን ዝም አሰኜው ።"

የዝምታ አይነቶች ብዙ ቢሆኑም ከነዚህ መካከል ዋና ዋናዎቹ #የአንደበት_ዝምታና_የስሜት_ዝምታ ናቸው። ሰው ስሜቱን ባተሌ እስካላደረገ ድረስ ፀሎቹንና ተመስጦዎቹን ያግዱበት ዘንድ መጥፎ አሳቦችን ያመጡበታል ። ስለሆነም በመንፈሳዊ መንገድ ዝምታውን መጠበቅ የሚወድ ሰው አይኖቹን ፣ ጆሮዎቹንና ስሜቶቹን ሁሉ መጠበቅ አለበት ።

ዝምታ ለሰው መስከንንና እርጋታን አስተምሯል ከጫጫታ፣ ከሁካታ፣ ለመጸለይ አስቸጋሪ ከሚሆኑበትና ሕሊናውን ከሚረብሽበት ብዛት ካላቸው አሳቦች ያርቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ዝምታ የሚሻው ብቼኝነትንና ጥቂት ጓደኞችን ነው።

ምንጭ፦ መንፈሳዊ ቃላትና ጥቅሞቻቸው ፤ #አያሌው_ዘኢየሱስ እንደተረጎመው ።

የብፁ አባታችን ብራኬ ይደርብን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

#ሰሙነ ሕማማት

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።
በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው።
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦

#ሰኞ
መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፦
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

አንጽሖተ ቤተመቅደስ ይባላል፡-
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።

#ማክሰኞ
የጥያቄ ቀን ይባላል፦
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

የትምህርት ቀን ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

#ረቡዕ
ምክረ አይሁድ ይባላል፦
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

የእንባ ቀን ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።

#ሐሙስ
ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

የምስጢር ቀን ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

#ዓርብ
የስቅለት ዓርብ ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

መልካሙ ዓርብ ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

#ቅዳሜ
ቀዳም ስዑር ትባላለች ፦
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።
ለምለም ቅዳሜ ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡-
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ትርክት)

የሕጻን ነገር
-------------------

አንድ መምህር በስብከተ ወንጌሉ መርሐ ግብራቸው ስለመንግስተ ሰማያት ጥሩ አድርገው ይተርኩና ሕዝብ ሁሉ መመሰጡን ሲያዩ "አሁን ከእናንተ መኻል መንግስተ ሰማያት መግባት የማይፈልግ አለ??" ብለው በጅምላ ሲጠይቁ ሁሉም በህብረት "የለም!" ብለው መለሱ።

:በዚህ ያልረኩት መምህር "እስኪ መንግስተ ሰማይምት መግባት የምትፈልጉ እጃችሁን ወደላይ አውጡ" ይላሉ። ሁሉም ያወጣል

:አንድ ሕጻን ግን ትንንሽ እጆቹን በጉንጮቹ ላይ አድርጎ ክርኑን በጉልበቶቹ ላይ ተክሎ በሚያሳዝን አኳኋን ተቀምጦ መምህሩን ብቻ ያያል። የሕጻኑ ሁኔታ የገዛችው መምህር ወደ ሕጻኑ ጠጋ ብለው "ማሙሽዬ አንተ ለምን እጅህን አላውጣህም? መንግስተ ሰማይ መግባት አትፈልግም?" አሉት

: ሕጻኑም ነቃ ብሎ "መግባትማ እፈልጋለሁ ነገር ግን እናቴ ጉባኤው እንዳለቀ የትም መሔድ የለም ባስቸኳይ እቤት እንድትመጣ ስላለችኝ ነው" አለ ይባላል።

ሕጻኑ የእናቱን ዐደራ ማስታወሱ የሚደነቅ ነው። የሕጻን ነገር ያልነው ግን መንግስተ ሰማይ ላለመግባት ያቀረባትን ምክንያት ለመጥቀስ ነው።
#ዛሬም በየዓውደ ምህረቱ ማዕደ እግዚአብሔር ተዘርግቶ፤ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጸሎት እየደረሰ ልባችን እቤት ሆኖ የተቋጠረ ሲፈታ፤ የተፈታ ሲቋጥር ጊዜውን የምንጨርስ ስንቶች አለን።

#ላለመጸለይ #ላለማስቀደስ #ንስሀ ላለመግባት #ላለመቁረብ ምክንያት መደርደር ከገሃነም እሳት አያድነንም!!!!!!!!!!!!!!!!

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

❖ ሰኞ ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር ማለፍ ማለት ነው በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ከሞት ወደ ሕይወት ከሲኦል ወደ ገነት ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን::

❖ ማክሰኞ ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ ጌታዬና
አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል ዮሐ. 20፡27-29::

❖ ረቡዕ አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን ክርስቶስ የሞትን ስልጣን
የሻረ የሕይወት ራስ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን::

❖ ሐሙስ አዳም ሐሙስ ይባላል፡ በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና
የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን::

❖ አርብ ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን
በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ጥቶ እንዳከበራት ይነገራል ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው ክርስቶስ
ለሕንፃ አልሞተምና::

❖ ቅዳሜ ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና
ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል::

❖ እሁድ ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል::

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ትርክት)

".....ልቡ ግን ከእኔ ርቋል..."


አንድ ባሕታዊ ብዙ ሰዎች ሰብስበው እየሰበኩ ሳለ ጭራቅ ከጫካ ወደ ጉባኤው ይመጣል። ወደ ባሕታዊው ቀረብ ይልና "አባቴ እንግዲህ እንደምታውቁት የእኔ ሕልውና በሰው ሥጋና ደም ላይ የተመረኮዘ ስለሆነ እነኝህን ሰዎች ልበላቸው ነው" አላቸው።

ባሕታዊውም የሰው ሥጋ መብላትህን አውቃለሁ ግና እነዚህ ልጆቼን አትበላሸቸውም የክርስቶስ ናቸውና አትችልም ብለው ገዘቱት።

አቶዬም ግድ የሎትም አባቴ እኔ የክርስቶስ የሆኑትን አልበላም ንክችም አላረግም ሲል ቃል ገባላቸውና ተለያዩ።

ከሄዱበትም ሲመለሱ ጭራቁ ባሕታዊው ያስተማሩትን ሰው ሁሉ በልቶ ከንፈሮቻቸውንና ምላሳቸውን አስቀርቶ ጠበቃቸው ። በጉዳዩም በጣም የተቆጡት ባሕታዊ ምነው የክርስቶስ ናቸው እንዳትበላ አላልኩህም አሉት።

ጭራቁም በሰው ደም የለሰለሰውን ከንፈሮቹን በምላሱ እያበሰ "የክርስቶስ የሆኑትን አሁንም አልበላሁም" ብሎ በኩራት መለስላቸው።

ምን ማለትህ ነው ያስቀረኸው የለም እኮ ቢሉት "አባቴአባቴ የክርስቶስ የሆነው ምላሳቸው ነው። ክርስቶስ ያለው ከንፈሮቻቸውና ምላሳቸው ላይ ብቻ ስለሆነ ሌላውን አካላቸውን በላሁት" አላቸው።
ዛሬም በክስርቶስ ስም ተጠርተን አካላቱ ሆነን ልንመላለስ በሚያስፈልግበት ጊዜ እኛ በእርግጥ ሆነናል ወይስ እንደሰዎቹ ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት ነን።

ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ ርቋል ማቴ ፲፭፣፯ ቃሉን ሰምቶ የማያድርገው ፊቱን በመስታወት እንደሚያይ ሰው ይመስላል። ፊቱን ካየው በኋላ ዞር ሲል ፊቱን ይረሳዋልና።

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ፡(ስነ ፅሁፍ)

……🖌ላዩን ውብ ሆኛለሁ

ላዩን ውብ ሆኛለሁ ውስጤ ግን እረክሷል፣
ንፅህና የለም በኃጥያት ቆሽሿል።
አንደበቴ ሀያል ሁሉን አወቅኩ ባይ ነው፣
የተለሳለሰ ደግ መሳይ መርዝ ነው።
ለተመለከተኝ ላስተዋለኝ ሰው፣
ክንፍ እንጂ ምን ቀረው የማይለኝ ማነው።
በጎ ስነምግባር ትህትና የሌለኝ ፣
መስዬ የምኖር የስም ክርስቲያን ነኝ።
ፍሬ አልባ ወይን ነኝ የማላስደስት፣
አንተ ይቅር በለኝ አምላከ ምህረት።
መወደስ በከንቱ ከእንግዲህ ይብቃኝ፣
እውነተኛ እንድሆን ፈጣሪዬ እርዳኝ።

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(⚜️ስነ ፅሁፍ⚜️)

#በምህረቱ መራኝ

ትላንት ነበርኩኝ እያለው የሌለው
እንዳማረ ተክል ፍሬ እንደሌለው
ደስታዬም ነበረ ለሞቴ መንገዱ
ህይወቴም ሚመስሉ አንዳች ያልተጎዱ
እውነታው ባይገባኝ የመኖሬ ምክንያት
እጆቼን ዘረጋው እምባዬም ፈሰሰ
ጉልበቴም ታዘዙ ለዳንስ እንዳልተነሱ
ልሳኔም በቃሉ ይቅርታን ለመነ
የወደቀልኝን እርሱን አገነነ
መውደቄን ተረድቶ የማይለኝ ችላ
አምላከ ብርሃን ህይወቴን አጎላ
በመሃሪነቱ ምህረቱን ሽሮኝ
ለህይወቴ ፍዳ መፍትሄው ሆነኝ

@aleroe ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
• ቱርክ ኢስታንቡል የሚገኘውን ግዙፉን የሃጊያ ሶፊያን ቤተ መቅደስ ወርሰው ወደ መስጊድነት ቀይረው ስናይ ቱርክ በጣም ሩቅ ይመስለን ነበር።

…ይሄ የምታዩት ለቅሶ ለሸገር ቅርብ እዚሁ እኛ ሃገር አሩሲ ኦሮሚያ ውስጥ የተፈጸመ ነው። የኦሮሚያ የወሐቢይ እስላሞች ወታደር አሰማርተው፣ በጥምቀትና በመስቀል ደመራ የማክበሪያ ሥፍራችን ላይ የነበረን መስቀላችንን ማየት አንፈልግም ነቅላችሁ ውሰዱ ባሉን ጊዜ… ማረድና መውገርም ሲጀምሩ፣ እኛ ከምንነቅለው ነቅላችሁ ውሰዱት ባሉንም ጊዜ አባቶቻችን መክረው "ቀን እስኪያልፍ በትዕግስት እንለፈው" በማለት በምታዩት መልኩ እያለቀሱ መስቀሉን ሲያነሡ ነው የሚታየው ልቅሶና ዋይታ።

…ጊዜ የሰጠው እንዲህ ያደርጋል። ጊዜ የጣለው ደግሞ እንዲህ ይደረጋል። አሁን የመንግሥቱን ሥልጣን፣ ወታደሩም፣ የፍትሕ መሥሪያቤቱም፣ ባንክና ታንኩም የእነሱ ነው። ሁሉን ስትቆጣጠር ደግሞ እንዲህ ያደርግሃል። መንግሥቱን ታዛለህ። እንዳሻህም ትሆናለህ።

… እኛ ደግሞ ለጊዜው መሪም አባቶችም የሉንም። ባለ ሥልጣናትም የሉንም። ስናሳዝን። አሁን ላይ እኛን መግደል፣ ማፈናቀልና ማረድ በሕግ አያስጠይቅም። ነገርግን ሁሌ ደግሞ እንዲህ እንዳለቀስን ባንቀርም እንደሰው ሲታሰብ ግን በጣም ይቆጫል፣ ያሳዝናል፣ ያንገበግባልም።

…ደግሞም ይበሉን። አቤት ኅብረታቸው ግን ሲያስቀና። ከንቲባዋን በፍጥነት ይቅርታ አስጠየቁ። ቤተ ክህነቱን በዳዴ አንበርክከው አስኬዱ። የባሌ ኦሮሞ ነኝ ባዩን አባ ህጻንን በማያገባው አስገብተው በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ይቅርታ አስጠየቁ። "መብት ይወሰዳል እንጂ አይጠየቅም"ብለው እንዲያውም በመንግሥት ወጪ በሁላችንም ብር ያፈጥሩ ዘንድ አስወሰኑ። ችግሩ ከማፍጠሩ አይደለም።አቦ ወንድ ናቸው፣ ሕብረት ይህን ያመጣል! እኛም አስኪ አንድ እንሁን::
#ሁሉም_ይየው

@Gedamat
ኤልሮኢ:(ምክር)

ለራስህ ነው

አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ! ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡
ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡ ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡ እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ስነፅሁፍ)

#ነበርኩ_መች_ያድናል


ሀጢያትን ስትሰራ አምላክን እረስተህ
ቅዱሱን ሰውነት በሀጢያት አርክሰህ
ትእዛዝን ሳትፈጽም መልካምን ሳትሰራ
ዘይት ሳታዘጋጅ መብራትህ ሳይበራ
በተጠራህ ጊዜ መላከሞት ሲመጣ
ለማያልፈው አለም ሲወጣልህ እጣ
ለሚዛን ስትቀርብ አገልጋይ ነበርኩኝ እያልክ መናገሩ
መዝሙር ዘምሬያለው ሄጃለው ከበሩ
ብሎ መከራከር ያኔ መች ይጠቅማል
ይዞ መገኘት ነው ነበርኩ መች ያድናል!!!!
________________

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:ትርክት

መርሳት

በአንድ ወቅት የግብጹ ሊቀ ጳጳስ ብጹኡ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ እያስተማሩ ባሉበት ወቅት በዙ ጥያቄዎች በጹሑፍ ይደርሳቸው ነበር። ታዲያ ከነዛ ጹሑፎች መካከል አንዱ እንዲ ይላል
... አባቴ እኔ ታላቅ የመርሳት ችግር አለብኝ ያደረኩትን የሰማሁትን ነገሮች በሙሉ እረሳቸዋለው እና አባቴ ምን እንደማደርግ ይምከሩኝ ነበር የሚለው። ብጹእነታቸውም ልጄ መምከሩንስ እመክርሃለሁ ምን ማድርግ እንዳለብህ እነግርሃለሁ ግን እንዳትረሳው እፈራለሁ አሉት ይባላል።
ቃለ እግዚአብሔር ስንሰማ በማስተዋል ልቦናችንንም ሰብስበን ሊሆን ይገባል።
በነገሮችም ሁሉ አስተዋዮች ልንሆን ይገባል።በዚህም ማስተዋል እና ጥበብን ወደሚሰጥ አምላክ አጥብቀን ልንማጸን ይገባናል።

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot