"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
Abiye-Tsome-Hudade.pdf
60.6 KB
ትምህርት

ስለ ዐቢይ ፆም

💠.ዐቢይ ለምን ተባለ ?
💠.ስንት ሳምንታት አሉት ?

አጠር ብሎ የተዘጋጀ
ያንብቡ share ያድርጉ

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ዝማሬ)

ሐመረ ኖህ ነሽ
============
ሐመረ ኖህ ነሽ
የምህረት ቃል ኪዳን የተገባልሽ
ትውልድ ይህን አምኖ
ያከብርሻል አልቆ እና አግኖ
አዝ----------------//
በእግዚአብሔር ሀሳብ ነበርሽ በህሊና
ዓለምን ሳይፈጥር አዳምን ሳይሠራ
ሁሉን የናፈቀሽ የወጣብሽ ፀሀይ
ንግሥት ነሽ ድንግል እሙ ለአዶናይ
አዝ----------------//
ያንን የጭንቅ ቀን የጥፋቱን ዘመን
አልፈነዋል ባንቺ በአማናዊት ፅዮን
ምንጭ ነሽ የእርካታ የድህነት መፍለቂያ
የዘለዓለም እረፍት አንባ እና ማረፊያ
አዝ----------------//
የነቢያት ተፈጽሞ አየን
አንቺ ምክንያት ሆነሽ ለመዳናችን
ድምፅሽን ጠላት ይሸበራል
እኛ ግን ሰምተነው በሀሴት ዘለናል
አዝ----------------//
አንዴ በገባልሽ ቃል ኪዳን መሠረት
ትውልዱን ይምራል ይኸው በቸርነት
ስሽ ወለላ ነው ጣፋጭ ለአፋችን
ማርያም ማርያም ብለን ታብሷል እንባችን



@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(ብሂለ አበው)

+ የአባቶች ድንቅ ጥበብ የተሞሉ መልሶች +

ባለ ብዙ ታሪኩ የወሊሶው ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ያጠምቁና ያስተምሩ በነበረበት ሥፍራ አንድ በትዕቢት መንፈስ የሚሰቃይ ወጣት መጣና መፈክርነት ያዘለ ቃል ተናገረ:: ክብር ይግባትና ንግግሩ የድንግል ማርያምን ዘላለማዊ ድንግልና የሚቃወም ነበር::

ወደ አባ ዲዮስቆሮስ ቀርቦ እንዲህ አላቸው :-
ወጣቱ :- "ድንግል ማርያም እኮ ብዙ ልጆች አሉአት"
አቡኑ :- "ባታውቀው ነው እንጂ ለአንተም እኮ እናትህ ናት!"

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

የቦሩ ሜዳው መምህር አካለ ወልድ ከሌሎች ሊቃውንት ጋር ኢየሩሳሌምን ሲሳለሙ ድንገት የሌላ ሀገር መነኮሳት መጥተው በዱላ አጣደፉአቸው:: ነገሩን ሲጠይቁ ለምን በእግዚአብሔር ሦስትነት እንደማያምን ሰባልዮሳዊ
አንድ ጣታችሁን ብቻ ወደላይ ጠቁማችሁ ታማትባላችሁ? ለምን እንደ እኛ ሦስት ጣቶቻችሁን (እንደሚጎርስ ሰው) በአንድ ገጥማችሁአታማትቡም?" አሉና በቁጣ ጮኹ::

መምህር አካለ ወልድ በፈሊጥ እንጂ በፍልጥ የሚሆን ነገር ስለሌለ ቁጭ ብለን እንነጋገር አሉ::

"እኛ በአንድ ጣት ብናማትብም ሦስትነቱን እናምናለን:: አንድዋ ጣትም እኮ ሦስት አንጉዋዎች አሉአት:: አንድ መሆንዋ አንድነቱን ሦስቱ አንጉዋ ሦስትነቱን ያስረዳል::
የታችኛው አንጉዋ መሠረት ነውና የወልድ የመንፈስ ቅዱስ መሠረት ይሆነው የአብ ምሳሌ ነው:: የመካከለኛው በሁለቱ ህልው የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው : የላይኛው ጥፍር የለበሰው ደግሞ ባዕድ ሥጋን የተዋሐደ የወልድ ምሳሌ ነው:: ሀገራችሁ ሔዳችሁ አስተምሩበት" አሉአቸው

(ይህ ትርጓሜ በወንጌል አንድምታ ላይ በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን አወጣለሁ የሚለው በተተረጎመበት ሥፍራ ይገኛል)

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

ንቡረ ዕድ ክፍለ ዮሐንስን ደግሞ አንድ ወጣት መጥቶ
"ለእግዚአብሔር የአምልኮ ለቅዱሳን የጸጋ ስግደት እንደሚሰገድ አውቃለሁ:: ግን በቅዱሳን ሥዕል ፊትና በፈጣሪ ፊት ስሰግድ እንዴት ለይቼ የጸጋ የአምልኮ እያልኩ መስገድ እችላለሁ?" አላቸው
ንቡረ ዕድ መለሱ
"አንተ ዝም ብለህ ስገድ እነርሱ የድርሻቸውን ይወስዳሉ!"

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠


አቡነ ሺኖዳ ከሾፌራቸው ጋር ሲሔዱ ሾፌሩ መኪናውን ከመጠን በላይ አበረረው
ፓትርያርኩ እንዲህ አሉ
"ልጄ ስለምንቸኩል ቀስ በል”

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

አንድ ታላቅ የጉባኤ መምህር ተጠየቁ
"ካህናት ዶሮና በግ ወዘተ ማረድ የማይችሉት ለምንድን ነው?"
"የክርስቶስን ሥጋና ደም የሚፈትት ካህን እንደ ኦሪት ካህን የእንስሳ ደም አያፈስስም"
"ካህናቱስ መልካም ሴት ልጅስ ማረድ ለምን ትከለከላለች?"
"ሕይወት የምትሠጥ ሴት ሕይወት አታጠፋም"

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

አለቃ ለማ ልጃቸውን ለምን በጣም እንደሚገርፉት ተጠየቁ
"ልጄን እኔ ካልቀጣሁት እግዚአብሔር ይቀጣብኛል
የእግዚአብሔር ቅጣት ደግሞ ሞት ነው"

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

አንዱ መጥቶ አንድን የመጽሐፍ መምህር
"ጥምቀት ጋድ አለው ወይ?" አላቸው
እርሳቸውም መለሱ
"አምና ነበረው የዘንድሮን እንጃ"

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

አቡነ ዮሐንስ አንድን ሥራ ፈቶ የአብነት ተማሪዎችን
ሲማሩ ከሩቅ የሚያይ ወጣት አዩና
"አንተ አትማርም ወይ?" አሉት
"አይ አባቴ ምን እየበላሁ ልማር ብለው ነው?" አለ እየተቅለሰለሰ
አቡኑ መለሱ
"አሁን ምን እየበላህ ነው የምትደነቁረው?"

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

አቡነ ጎርጎርዮስ በዝዋይ ሳሉ አንድ ወጣት ሰርቆ ሲያመልጥ አባርረው ይዘው ሰዎች አመጡላቸው
ዕቃው ከተመለሰ በኁዋላ ሌባውን ለሕግ አሳልፈው ሊሠጡ ሲቸኩሉ አይሆንም አሉአቸው:: ሰዎቹ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ ወደ ፖሊስ እንውሰደው አሉአቸው
እርሳቸውም መለሱ
"ኦርቶዶክሶች ተሰራርቀው ተካስሰው መጡ ከሚል ስም ውጪ ምንም አናተርፍም"

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

ብፁዕ አቡነ ሰላማን አንዱ ባለ ሥልጣን ጉዳይ ሊያስፈጽሙ በሔዱበት ቢሮው "አንተ" ብሎ በማናገር ሊያቃልላቸው ሞከረ::
እርሳቸው እንዲህ አሉት
"የቤተ ክርስቲያኔን ጉዳይ ፈጽምልኝ እንጂ እንኩዋን አንተ ቀርቶ አንቺም ብለህ ጥራኝ

💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠

የደርግ መንግሥት እንዳሻው ሊዘውራቸው ተስፋ ያደረገባቸው ፓትርያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በመሪው አማካኝነት እንዲህ ሲል ጠየቃቸው
"የቅድስት ሥላሴ ካቴድራልን ወደ ሙዝየምነት የመቀየር ሃሳብ በመንግሥት በኩል ተይዞአል:: ይህንን ለማድረግም የእርስዎን ድጋፍ የግድ ነው"
ፓትርያርኩ መለሱ
"ምን ችግር አለ በቅርቡ የዓመቱ ሥላሴ ክብረ በዓል ስላለ ሕዝቡ ባለበት እናንተም ተገኝታችሁ አብረን ለምን አናወያየውም"
በዚህ ምላሽ ምክንያት እቅዱ ተሠረዘ

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ተግበራዊ ክርስትና.pdf
987.1 KB
ትምህርት

ተግባራዊ ክርስትና
ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ተርጉሞ እንዳዘጋጀው

አውቀው ለማሳወቅ ይትጉ
share ያድርጉ

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

"አስተካክለኝ"

መልካም ነገሮች ከሚባሉት መካከል ተጠቃሽ የሚሆነው አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቆ ሲይዝ እና ሲጠብቅ ነው። እግዚአብሔር ብዙ ቃል ገብቷል እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም
ግልፅና ታማኝ ነው። እናም ቃሉን አያጥፍም። የእርሱን ቃል ይዛችሁ ከእርሱ ጋር ተነጋገሩ። →"ቃል የገባህልንን መች ነው የምትፈፅምልን?" በሉት። →"ቃልህን ይዤ እጠይቅሃለው 'አዲስ ልብን እሰጣችኃለው' ብለሃል። የታለ አዲሱ ልብ? እኔ ራሴን ስመለከተው የድሮ ልቤ እንዳለ ነው። የትናንትናው መጥፎ ጠባይ ልክ እንደ ትናንትናው ነው። የታለ ታዲያ ያ አዲሱ ልብ እሰጥሃለሁ ያልከኝ? እኔ ማወቅ እፈልጋለው ። ከውስጥ እንድትቀይረው እንድትሰማው እፈልጋለው። እኔ አስቸገርኩህ። አንተ አስተካክለኝ፣ ስራብኝ ፥ ደረቅ መሆኔን አስተካክልልኝ።
→ስህተት አለብኝና ስህተቴን አስወግደው።
→ድርቅና አለብኝና ድርቅናዬን አስወግደው ።
→ኃጢያአት አለብኝና ኃጢአቴን አስወግደው።
ጌታ ሆይ እኔ ውስጥ ስራ ። እናም ውስጤን አንጻው። መጋዙን መዶሻውን አንሳው። ሥራብኝ፥ ይህ መጥፎ እንጨት የተባለውን ላንተ ወንበር አርገው ።
''በሕጌ እንድትጓዙ አደርጋችኃለው ቃሌንም ትይዙታላችሁ እናም ትሰሩበታላችሁ ። እኔ ነኝ ይህን እንድታደርጉ የማደርጋችሁ" ብሎናል ። ወንድሞቼና እህቶቼ፥ ቃሉን ቀይሮ መስሏችኃል? አይደለም! እግዚአብሔር ቃሉን አያጥፍም ! ይህ የሚሆነው እኛ ለእግዚአብሔር ልባችንን ስለማንሰጥ ነው ። እንዲሠራበት አንሰጠውም ። ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር አናስረክበውም። ልክ እግዚአብሔር ሊሰራ ሲል ምን እንለዋለን ? "አይ ቆይ ቆይ እራሴን አስተካክዬ ጥሩ ስሆን ወደአንተ እመለሳለሁ" .....ጥሩ ስሆን እመለሳለሁ??? መቼም ጥሩ አትሆንም! ራስህን ጥሩ አድርገህ ወደ እርሱ ከመሄድ ይልቅ ወደ እርሱ ሂድ እርሱ ጥሩ ያደርግሃል ። እኛ ግን በተቃራኒው መንገድ እንሄዳለን። እኛ ምን
እንለዋለን? " እኔ ቤትህ የማልገባበት ምክንያት ጥሩ ሰው ስላልሆንኩ ነው"። አይደለም! ወደ ቤቱ ግባ፥ ከዚያ ጥሩ ሰው ትሆናለህ! "ጌታ ሆይ እኔ መጸለይ አልችልም፥ ምክንያቱም ቆሻሻ
ስለሆንኩ" አይደለም! ጸልይ፥ ከዚያ እርሱ ንጹህ ያደርግሃል። ለምንድን ነው እኛ ብቻችንን መስራት የምንፈልገው?
ከእግዚአብሔር ጋር ሆነህ ተፋለም ፣ ታሸንፋለህ እና ታልፋለህም።
እግዚአብሔርን እንዲ ብለህ ጠይቀው...
→ "ጌታ ሆይ አጋዥ ትባላለህ ፤ አጋዥነትህ የት አለ? ና አግዘኝ።
→አዳኝ ትባላለህ፤ የት አለ ማዳንህ? ና አድነኝ።
→ ምንም ነገር አይሳንህም ትባላለህ... ይቺንም ይዤ እጠይቅሃለው። እኔን ማዳን ከተሳነህ ታዲያ ምንም የማይሳነው የተባልከው ለምንድን ነው ? ጌታ ሆይ፥ እኔ አንድ ችግር ነኝ ። ፊት ለፊትህ ቀርቢያለው መንፈስህን አኑርብኝ። ምንም አይሳንህም እና
እኔን ሥራኝ ። እምነትህ ደካማ ነው ካልከኝ ፥ እሺ ጠንካራ አድርገው ? ልቤ ቆሽሿል እና አፅዳልኝ ። ሙሴ ጸሊምን እና ማርያም መቅደላዊትን እንዳስተካከልካቸው እኔንም አስተካክለኝ። አንተ የምትለው "ወደ እኔ የመጣውን ወደ ውጪ አላስወጣውም " ነው ..ይኸው ወደ አንተ መጥቻለው ባዶ
እጄን አትላከኝ ። ጌታ ሆይ የበጎ ነገር ፈጣሪ ትባላለህ እንዲ ከሆነ በእኔ ውስጥ በጎ ነገርን ስራ ። እየዞርህ በጎ ነገርን ትሰራለህና እንግዲህ በስፍራችን ውስጥ ዙር ፣ ቤታችን ውስጥ ዙር ፣ ክፍሌ ውስጥ ዙር ፣ በነፍሳችን ውስጥ ዙር ፣ በጎ ነገር ሥራብኝ ድሮ እንደምታደርገው አሁንም አድርገው " መኃልየ መኃልየ ዘሰለሞን ምን አለ "ይዤው አልለቀኩትም " እናንተም እንዲ በሉት "ስንት ጊዜ ፀሎት ፀለይኩ ግን አልሰማኸኝም። አሁን ጊዜ ግን አለቅህም ፥ ፀሎቴን ስትሰማ ብቻ ነው የምነሳው።" በሉት። ስለዚህ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ጌታን ከጎናችሁ አድርጉት። ከእግዚአብሔር ጎን ለመሆን ሞክሩ፣ ጸልዩ እርሱ ኃይሉን ይሰጣችኃል ።

[ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ስብከት የተቀነጨበ]


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ :(ዝማሬ)

#እንደ_ቸርነትህ_የንስሐ_ዝማሬ

እንደ ቸርነትህ አቤቱ ማረን/2/
እንደ ምህረትህ ይቅርታን ስጠን/2/

ከሀጥያቴም አንጻኝ ከብዙ በደሌ/2/
ለዛች ክፉ ሀጥያት እንዳልሆናት ሎሌ/2/

እኔስ አበሳዬ በደሌን ሳውቀው/2/
ከቶ የሚያድነኝ ቸርነትህ ነው/2/

አንተን ብቻ በደልኩ ክፉም አደረግሁ/2/
አሁን ይቅር በለን ከፌትህ ወደቅን /2/

ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን ስማጸን አንተን
መውደቄን ተመልከት አምላከ ብርሀን አምላከ ሰላም

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ምክረ አበው)

አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል በመከራ ውስጥ ይመጣል

አንድ ሰው መፍትሔ የሌለው የሚመስል መከራ ሊገጥመው ይችላል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ መከራው የገጠመው ጥቂት ኃጢአቶችን ስለ ፈጸመ መሆኑን ከማስጠንቀቂያ ጋር ይነግረዋል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቃሉ ንስሓ ከገባህ መከራው ፍጻሜ ያገኛል እያለ ውስጡን ሲመክረው ይሰማል። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ንስሓው ሲል ለሰውየው ይራራለታል።

የእግዚአብሔር ድምፅ አንድ ሰው ሲታመም ወይም እርሱ የሚወደው ሌላ ሰው ሲታመም ሊመጣ ይችላል። በዚህ ጊዜ እንዲጸልይ ወይም ስዕለት እንዲሳል የሚመክረውን ድምፅ ከውስጡ ይሰማል ይህ ድምፅ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው።

የዮሴፍ ወንድሞች እህል ሊገዙ ወደ ግብጽ ከወረዱ በኋላ በዚያ ችግር ሲገጥማቸው እርስ በእርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋግረው ነበር “በእውነት ወንድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውና። ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።” ዘፍ. 42፥21። ከዚህ በኋላ ለዮሴፍ እንዲህ ብለውታል “ለጌታዬ ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ...” ዘፍ. 44፥16። ኃጢአታቸውን እንዲያስታውሱ ኀላም እንዲገሰጹ ያደረጋቸው የእግዚአብሔር ድምፅ ነው።

ነቢዩ ዳዊት የጌራ ልጅ በሆነው በሳሚ ሲሰደብ የእግዚአብሔር ድምፅ ውስጡን ስላለፈ ኃጢአቱ እየወቀሰው መሆኑን አዳምጧል። ስለሆነም በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች “እግዚአብሔር ዳዊትን ስደበው ብሎታልና ይርገመኝ።” 2ኛ ሳሙ. 16፥10 በማለት በግልጽ ተናግሯል።

ረሀብና የመሬት መንቀጥቀጥ በዓለም ሲደርስ የእግዚአብሔር ድምፅ በመላው ዓለም ውስጥ ይሰማል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ የሚናገረን “ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ።” ሚል. 3፥7 እያለ ነው። ይህ ድምፅ በረሀቡ ወይም በመሬት መንቀጥቀጡ ጉዳት ለደረሰባቸው ሀገሮች የሚሆን የእርዳታ ጥሪ ለማሰማት ወይም ሌሎቹ ከእነርሱ ትምህርት በመውሰድ ንስሓ እንዲገቡ ለማድረግ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኝት ዝግጅት እንዲያደርጉ ነው።

ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት መከራ ውስጥ ስትገቡ ከውስጣችሁ ያለውን የእግዚአብሔር ድምፅ አድምጡት እርሱ ለእናንተ ሊነግራችሁ የሚወደው ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁና።

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:
#ስጋ_ነው_ምርኩዜ


ስጋዬ ወፍሮ አፌ ክፉ ደፍሮ
ሓሰትን መስክሮ እውነት ቅሉን ሽሮ
እውነት ተሸሸጋ ማን እውነት ሊያወጋ
ስለ ክፉ ስጋ።
ስለ ክፉ ስጋ ነፍሴ ስትወጋ
የአንደበቴ ችቦ የአንደበቴ ሰንጋ
ነፍሴ ስትቃትት የስጋ ጦር ወግቷት
ቀንም ሌሊትም ቁስሉ ሲያሰቃያት
ጭንቅ ጥብብ አለች ቀኑ ጨልሞባት
የምታውቀው ቤቷ ተዘግቶባት
ስጋ ሲበድላት በሐዘን በትካዜ
በሐሰት ባለሟል በስጋ ምርኩዜ
እኔንም ተረድታ በእምነት መደብዘዜ
በህይወት ልታልፍ ልትጓዝ በግዜ
ነፍሴ የተዘጋጀች ልታቀርብ ኑዛዜ።
____________________

@aleroe
ኤልሮኢ:
. #ጸሎት

#ጸሎት ያቆመች ነብስ እየሞተች ያለች ነች።
#ለሊት ተነሥቶ በጸሎት ጠላቱን ያልመታ ጥዋት ቀኑን ሙሉ ሰይጣን ሲመታው (ሲቀጠቅጠው) ይውላል።
#ክርስትያን ተንበርክኮ ማንበርከክ ይችላል። የማይጸልይ ከሆነ ደግሞ ገና ሳይዋጋ ይንበረከካል።
#ሌሊት በጸሎት ያልወረድክበት ሰይጣን። ቀኑን ሙሉ ሲያገሳብህ ይውላል።
#ከእግዚአብሔር ጋር አንዲት ቀን ሳታሳልፍ ከዋልክ፦ ከመልካሙ
ዘመንህ ውስጥ አንዲቷ ቀንህ በከንቱ እንዳባከንካት ቁጠራት።
#እግዚአብሔርን በጸሎት የማይለምን፦ ዘወትር የሰውን ፊት የሚያይ ተለማማጭ ሆኖ ይኖራል።
#ከእግዚአብሔር ጋር መልካም ጊዜን ማሳለፍ፦ገንዘብህን ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኝ ንግድ (ኢንቨስት) ከማድረግ በላይ እጅግ ጠቃሚ ነው።


@aleroe
ኤልሮኢ፡(ስነ ፅሁፍ)

…አንድ አካል

ጳውሎስ እግር ሆኖ በአህዛብ ሀገር፣
ሲሮጥ አይተነዋል ለቃል ሲመሰክር።
እጅ ነበር ጴጥሮስ ሁሉን የሚባርክ፣
ሶስት ሺህ ሰራዊት በአንዴ የሚማርክ።
የዮሀንስ ዓይን ከሩቅ የሚያስተውል፣
ፍጢሙ ላይ ቆሞ ሰማይ የሚያካልል።
ሉቃስም ጣቱ ነው ቃል የሚፃፍበት፣
የፈጣሪው እናት መልኳ የሚሳልበት።
አንደበተ ትሁት ያዕቆብ መምህር፣
ባለፀጋዎቹን ሲወቅስ የማያፍር።
ማቴዎስም መጥቷል ከቀራጭነቱ፣
የፈጣሪ አካል ሆኗል ሰውነቱ።
ቅዱስ ፊሊጶስም እውነተኛ አባት ነህ፣
ታሪክህ ይታወቅ በእኛ በልጆችህ፣
ለህዝበ ኢትዮጵያም ይድረስ በረከትህ።


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ፡(ምክር)

.....ትህትና በአባቶች ሕይወትና ትምህርት ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ ይገኛል። ቅዱስ ያዕቆብ እንዲህ ብሏል ስለ ትህትና ማስተማር እፈልጋለሁ። ደግሞ እፈራለሁ። ስለ እግዚአብሔር ለመናገር እንደሚፈራ ሰው እመስላለሁ። ምክንያቱም ትህትና መለኮት ሰው ሆኖ በምድር ሲገለጥ የተጠቀለለበት መጎናጸፊ ነውና። ሰው ሆኖ በአጭር ደረት በጠባብ ቁመት የመገለጡም ምሥጢር እጅግ አስደናቂ በሆነ በትህትናው ነው። ይሄ ሁኔታው ያስደነቀው ነቢዩ ኢሳይያስ "ያልተጠባበቅነውን የጽድቅ ሥራህን ባደረግህ ጊዜ ወረድህ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ" ኢሳ. 64፥4 ብሏል። ሰይጣን ትሁት ሰው ሲያይ የሚፈራው በትሁት ሰው ውስጥ የፈጠረውንና በትህትና ያሸነፈውን እግዚአብሔር ስለሚያየው ነው።

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(ትርክት)

+++ ልብስህን ማን ወሰደው? +++

በአንድ ወቅት አባ ሰራብዮን ወደ እስክንድርያ ሄደ፡፡ በገበያም ስፍራ አንድ ከልብስ የተራቆተ ነዳይ አገኘ፡፡ ለራሱም ‹ይህ ደሃ ሰው ታርዞ መነኩሴ የተባልኩ እኔ እንዴት ለብሼ እታያለሁ? በእውነት ይህ ‹ታርዤ አልብሳችሁኛልና› ብሎ የተናገረው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? በዚህ ብርድ አየር እየተሰቃየ እኮ ነው!› ብሎ ፈጥኖ የገዛ ልብሱን ከራሱ በማውለቅ ይለብስ ዘንድ ለዚያ ደሃ ሰጠው፡፡ ከዚያም በእጁ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደያዘ እርቃኑን በጎዳናው ላይ ተቀመጠ፡፡ የከተማውም ባለጠጋ ሰው አባ ሰራብዮን ባለበት ሥፍራ ሲያልፍ ተመልክቶት ወደ እርሱ ቀረበና ‹አባ ሰራብዮን ሆይ ልብስህን ማን ወሰደው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ቅዱስም በእጁ ወደ ያዘው መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቆመ ‹ልብሴን የወሰደው ይህ ነው!› አለው፡፡ ያም ባለጠጋ ልብስን ገዝቶ ካለበሰው በኋላ አባ ሰራብዮን ከእርሱ እንደ ተለየ በመንገድ ዕዳውን መክፈል ስላልቻለ እየተንገላታ ወደ ወኅኒ ቤት የሚሄድን አንድ ሰው ተመለከተ፡፡ ቅዱሱም አባት የያዘውን መጽሐፍ ቅዱሱን ሽጦ የዚያን ሰው ዕዳ በመክፈል ነጻ አደረገው፡፡ ይህንም ፈጽሞ ጉዞውን ሲጀምር ሌላ አንድ ነዳይ ሲለምን ተመልክቶ ዳግመኛ የለበሰውን ልብስ አውልቆ ሰጥቶ እርቃኑን ወደ በአቱ ተመለሰ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም እርቃኑን ባዩት ጊዜ ‹መምህር! ልብስህ ወዴት አለ?› ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹መጸወትኩት› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መልሰው ‹እኛን የሚያጽናናን መጽሐፍ ቅዱስህስ አባታችን? › ሲሉ ደግመው ጠየቁት፡፡ አባ ሰራብዮንም ‹መጽሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ ‹ሂድ ያለህን ሽጠህ ለድሆች ስጥ› ይለኛል፤ ስለዚህ እርሱንም ሸጥኩት› አላቸው፡፡

ምንጭ :–Paradise of the monks, P 89

ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደሚናገረው ምጽዋት የፊት መብራት ናት፡፡ አንድ ሰው በጨለማ ሲጓዝ ከኋላው መብራት ቢያበሩለትም እንኳ ከፊቱ የሚቀድመው የገዛ የአካሉ ጥላ እንቅፋት እየሆነበት ይጥለዋል፡፡ ወደ ፊት ያለውን መንገድ አጥርቶ እያየ ያለ ስጋት ለመሄድ እንዲችል የግድ የፊት መብራት ያስፈልገዋል፡፡ ጾም ፣ጸሎት እና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋት እንደ ኋላ መብራት ናቸው፡፡ የፊት መብራት የተሰኘች ምጽዋት ካልታከለችባቸው እነዚህ ብቻቸውን ዋጋን አያሰጡንም፡፡ ከምጽዋት በላይ ታላቅ ነገር እንደሌለ ልንረዳ ይገባል፡፡ ዓለም ሁሉ ከነበረበት የበደል ዕዳ የዳነው ቸር እረኛ በሆነው በመድኃኔ ዓለም በአካሉ ምጽዋትነት (በሥጋው በደሙ መሰጠት) ነውና!!!


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
Forwarded from 666( ኢልሙናቲ ) ሀይማኖት ምዝገባ ማእከል
መፅሀፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች ከነመልሶቻቸው እና ከነ ማስረጃዎቻቸው የምናቀርብበት ፕሮግራማችን በተከታታይ ክፍል ለእናንተ ሲደርስ ቆይቶ አሁን ክፍል 6 ላይ ደርሰናል ሆኖም እስከዛሬ ቪዲዮውን ላላገኛችሁ እንዲሁም ቀጣዩን ክፍል ማግኘት ለምትፈልጉ ከስር ሊንኩን በመንካል ማግኘት ይችላሉ።

https://youtu.be/G4S7uXyscEs
https://youtu.be/G4S7uXyscEs
ኤልሮኢ:(ብሂል)

"ሌቦች ወርቅና ብር ያለውን እንጂ ድርቆሽና ገለባ እንዲሁም ሰንበሌጥ ያለውን ቤት አይበረብሩም፡፡ ዲያብሎስም የሚያጠቃው (የሚፈትነው) መንፈሳዊ ምግባራትን የሚያበዙትን ሰዎች ነው፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ፡(ትርክት)

…… አትማረኝ
--------------
በጣና ገዳማት ውስጥ የአቡነ አሳይ ዋሻ አለ በዚህ ዋሻ አንድ ያልተማረ የቤተክርስቲያንን ትምህርት የማያውቅ ሰው ጸሎት ሲጸልይ አንድ አባት በጀልባ ተሳፍረው ይመጡና ያገኙታል።

ወደ ደሴቷም አረፍ ልበል ብለው ሲገቡ ያ ወጣት ሲጸልይ ይሰሙታል ቀረብ ብለው ቢያደምጡ ይህ ሰው የሚጸልየው "አትማረኝ" እያለ ነው።

እኝህ አባት በጣም ይደነግጡና እንዲህ ያለ ጸሎት አለ ወይ አትማረኝ የሚል ማን ነው ያስተማረህ ሲሉት አንድ መነኩሴ ነው ያስተማሩኝ አላቸው።

እሳቸውም ይህማ ሰይጣን ነው በመነኩሴ ተመስሎ ያስተማረህ እንጂ አትማረኝ ብሎ ጸሎት የለም ብለው "አቡነ ዘበሰማያትን" አስተማሩት። ይኽ ሰው እንደምንም ታግሎ አባታችን ሆይን ከተማረ በኋላ እኝህን አባት ያሰናብታቸዋል።

እሳቸውም በጀልባ ተሳፍረው መንገድ ሲጀምሩ ይኽ ወጣት ወደ ቀደመ በዓቱ ገብቶ መጸለይ ሲጀምር ያን ጸሎት ረሳው። ምን ነበር ያስተማሩኝ ብሎ ቢያስብ ጠፋበት። ከበዓቱም ሮጦ ወጥቶ በጀልባ ተሳፍረው የሚሄዱትን አባት አስቁሞ "ምን ብለው ነው ያስተምሩኝ?" ብሎ ጠየቃቸው እኝህም አባት ሲያዩት ውሃ ላይ ቆሟል፣ በውሃ ላይ ነው ሮጦ የመጣው አትኩረው ቢመለከቱት ውኃው ላይ እንደቆመ ነው።

"በል የእኔ ልጅ እንደቀድሞው አትማረኝ እያልክ ጸልይ" አሉት ይባላል።

ወጣቱ ባለማወቅ በሚጸልየው ጸሎት ውስጥ በቅቶ ነበር። እግዚአብሔር የሰማው ያለውን ሳይሆን የልቦናውን ነው።

የምንጸልየው ጸሎት የተዘበራረቀ ቢሆንም እንኳን እግዚአብሔር እያቃና ይሰማዋል። ስለዚህም ከመጸለይ ወደ ኋላ አንበል እኛ የምንጸልየው ባይገባንም በዙሪያችን ያሉት አጋንንቶች ገብቷቸው ይሸሻሉ።

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ: (ምክረ አበው)
……✍️
አባት ልጁ ከቤት ወጥቶ መኪና እንዳይገጭበት፣ ወድቆ እንዳይሰበርበት፣ ድንገት በአከባቢው የሚያልፉ ከብቶች ገፍተው እንዳይጥሉበት መውጫው በሩን ይዘጋበታል፡፡ ይኼኔ ልጁ በሩ ለምን እንደተዘጋበት አያውቅም፤ ልጅ ነውና፡፡ አባቱ የጠላው መስሎትም ምርር ብሎ ሊያለቅስ
ይችላል፡፡ ማልቀስ ብቻ አይደለም፤ ቂምም ሊይዝበት ይችላል፡፡ አባቱ ግን በሩን የዘጋበት ምክንያት ያውቃል፤ ጠልቶት ሳይሆን ይጐዳበታልና ልጁ ቢያለቅስም አይከፍትለትም፡፡

እውነተኛው አባታችን እግዚአብሔርም አንዳንድ ጊዜ የማይጠቅሙን ይልቁንም ክፉኛ ሊጎዱን የሚችሉ በሮችን ይዘጋብናል፡፡ ከእውቀት ከፍለን የምናውቅ ልጆቹ ነንና አባታችን ለምን እንደዘጋብን ለጊዜው አይታወቀንም፤ ብቻ የከለከለን ይመስለናል፡፡ በመሆኑም ቂም ልንይዝበት ልናማርረውም እንችላለን፡፡ እርሱ ግን ይታገሠናል፤ ለእኛ
የሚያስባት መልካሚቱን በር እርሱ ያውቃታልና ይከፍትልናል፤ በእኛ እይታ መልካም የምትመስለንን ነገር ግን ክፉይቱን በር ይዘጋብናል፡፡

ቅዱስ አባት ሆይ ስለ ከፈትክልን ብቻ ሳይሆን ስለ ዘጋህብንም በር እናመሰግንሃለን ልንለው ይገባል። አሜን!

@aleroe
ኤልሮኢ:(ምክር)

#ወዳጄ ሆይ!

የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡

አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡ ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(መዝሙር)

አዝናለሁ አለቅሳለሁ

አዝናለሁ አለቅሳለሁ
ስለ በደሌ ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ
አዝናለሁ አለቅሳለሁ
ስለ ጥፋቴ ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ
ነገር ግን መሐሪ ነህና
እንደምታድነኝ አምናለሁ

ሥጋዬ ለራሱ እያታለለኝ(፪)
ሁሉን በመፈለግ ወሰደና ለጥፋት ሰጠኝ(፪)
አዝ = = = = =
ከመሬት ተገኝታ እስክትገባ
በከንቱ አስቀረችኝ አምላኬ ሆይ ሥጋ ሰገብጋባ(፪)
አዝ = = = = =
ትቻት መምጣቴ ነው አፈር ሥጋዬን
እንድትቀበላት አምላኬ ሆይ አደራ ነፍሴን(፪)

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot