Forwarded from ማህሌት ቲዩብ -Mahelet Tube
Watch "የሰማእቱ የቅዱስ እስቲፋኖስ ታሪክ||Yesemaetu yekedus estifanos tarik" on YouTube
https://youtu.be/lE3ITT3Tdyc
https://youtu.be/lE3ITT3Tdyc
YouTube
የሰማእቱ የቅዱስ እስጢፋኖስ ታሪክ||Yesemaetu yekedus estifanos tarik
on facebook https://cleanuri.com/vm3ng1
on telegram https://t.me/Mahelet_tube
on telegram https://t.me/Mahelet_tube
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
ኤልሮኢ:
# እጠበኝ ቆሽሻለው
እጠበኝ ቆሽሻለው አምላኬ በድያለው
ያለናት ያሳደከኝ ያላባት የ ጠበከኝ
ያንሁሉ ዛሬ ረሳው እጠበኝ ቆሽሻለው/2/
ከድንኳንክ ብታስገባኝ ሞገስ ሰተህ
የ አፍኒንን ምግባር ይዤ አስ ቀየምኩህ
ቅባሜሮን ያተምክበት ልጅነቴ
እንዳይጎድፍ ጠብቅልኝ ቸር አባቴ
ሀይል አኑረክ እንደ ሶምሶን በፀጉሬ
ጎልያድን አስጥለኅኝ በጠጠሬ
አቅም ቢያንሰኝ በስጋ ጦር ተሸንፌ
ደጅህ መጣው የንባ መባ ባይኔ አቅፌ
እንዳትረሳኝ በመዳፍህ ቀርፀሀኅኛል
እንዳተወኝ ያለመጠን ወደህኛል
ባሰነዝር ልት ቀጣኝ የሞት በትር
የትግስትክ ሰሌዳነው ለኔክብ
ከከንፈሬ ጥበብ ጽፈህ ቅኔ ቢፈስ
በመታበይ አሳዘንኩት ያንተን መንፈስ
ፍቅር ግተህ በቅፍስር ያሳደከኝ
እባክህን በበደሌ አትቅፀፈኝ
@aleroe
# እጠበኝ ቆሽሻለው
እጠበኝ ቆሽሻለው አምላኬ በድያለው
ያለናት ያሳደከኝ ያላባት የ ጠበከኝ
ያንሁሉ ዛሬ ረሳው እጠበኝ ቆሽሻለው/2/
ከድንኳንክ ብታስገባኝ ሞገስ ሰተህ
የ አፍኒንን ምግባር ይዤ አስ ቀየምኩህ
ቅባሜሮን ያተምክበት ልጅነቴ
እንዳይጎድፍ ጠብቅልኝ ቸር አባቴ
ሀይል አኑረክ እንደ ሶምሶን በፀጉሬ
ጎልያድን አስጥለኅኝ በጠጠሬ
አቅም ቢያንሰኝ በስጋ ጦር ተሸንፌ
ደጅህ መጣው የንባ መባ ባይኔ አቅፌ
እንዳትረሳኝ በመዳፍህ ቀርፀሀኅኛል
እንዳተወኝ ያለመጠን ወደህኛል
ባሰነዝር ልት ቀጣኝ የሞት በትር
የትግስትክ ሰሌዳነው ለኔክብ
ከከንፈሬ ጥበብ ጽፈህ ቅኔ ቢፈስ
በመታበይ አሳዘንኩት ያንተን መንፈስ
ፍቅር ግተህ በቅፍስር ያሳደከኝ
እባክህን በበደሌ አትቅፀፈኝ
@aleroe
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
……✍ሰውየው አስር ክፍል ቤት ሠርቶ ብቻውን ሲኖር አንድ
ቀን በሩ ተንኳኳ ሲከፍት ጌታ ነው፡፡ "ውይ አምላኬ
ጌታዬ አንተ እኔ ቤቴ መጣህ?" ብሎ በደስታ
ተቀብሎት አንድ ክፍል ቤት ሰጥቶት መኖር ጀመሩ፡፡
በሌላ ጊዜ በሩ ተንኳኳ፣ ሲከፍት ሰይጣን ነው፡፡
ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ
ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል?" አለው፡፡
ጌታም "ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም " አለው፡፡
ሰውየውም ተሰምቶት ሁለት
ክፍል ቤት ለጌታ ጨምሮለት እርሱ ሰባት ክፍል ይዞ
መኖር ቀጠሉ፡፡ በሩ ተንኳኳ ሲከፈት ሰይጣን ነው፡፡
ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ
ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል? " አለው፡፡
ጌታም " ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም " አለው፡፡
ሰውየውም ተሰምቶት ከጌታ
ጋር እኩል ለእኩል ተካፈለ፡፡
ነገር ግን ቤቱ ከቀድሞ ይልቅ ተንኳኳ ፡፡ አዝኖም
ይዘጋና ጌታ ሆይ አለው፡፡ ጌታም የቀድሞውን መልስ
ሰጠው፡፡
በዚህ ጊዜ ሰውየው ለራሱ አንድ ክፍል ቤት ይዞ
ዘጠኙን ክፍል ቤት ለጌታ ሰጠው፡፡ ነገር ግን
ከቀድሞው ይልቅ በጣም ተንኳኳ፡፡ ቢከፈት ሰይጣን
ነው፡
በሩን ይዘጋና ወደ ጌታ ሄዶ " ጌታ ሆይ ምሥጢሩ
ምንድን ነው? " አለው፡፡ "ጌታ ግን ቤቱ የአንተ እንጂ
የእኔ አይደለም "አለው፡፡
በዚህ ጊዜ ዐሥሩንም ክፍል ለጌታ አስረከበ፡፡ ጌታም
አንድ ክፍል ቤት ለሰውየው ሰጠው፡፡ በሩም ተንኳኳ
፡፡ ጌታም ሊከፍት ተነሣ፡፡ ሲከፍት ሰይጣን ነው፡፡
ሰይጣንም " ይቅርታ የአንተ ቤት መሆኑን አላወቅሁም
" ብሎ ሄደ፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ መንኳኳት ቆመ፡፡
ሁሉንም የሕይወታችንን ክፍል ለጌታ እግዚአብሔር
ካላስረከብነው መንኳኳት አይቆምም፡፡ 1ዐ% ስንሰጥ
ይንኳኳል፡፡ 30% ስንሰጥ ይንኳኳል፡፡ 50% ስንሰጥ
ይንኳኳል፡፡ 99% ስንሰጥ ይበልጥ ይንኳኳል፡፡ 100%
ስንሰጥ መንኳኳት ይቆማል፡፡ እኛ ከከፈትን ሰይጣን
ይገዳደረናል፡፡ ጌታ ሲከፍት ሰይጣን " ይቅርታ የአንተ
ቤት መሆኑን አላወቅሁም " ብሎ ይሄዳል፡፡
ጌታ ሰማይን የደስታ አገር ያደረጋት ሙሉ
በሙሉ የፈጣሪ ፈቃድ የጸናባት በመሆኗ ነው፡፡
ባንተም ሕይወት የሰማይ ደስታ የሚመጣው
የፈጣሪ ፈቃድ በሕይወትህ ሙሉ በሙሉ
ሲፈጸም ነው፡፡ ስለዚህ፡-
· ፈጣሪን እረኛህ አድርገው፡፡
· በፍጹም ልብህ ተከተለው፡፡
· የሚያስፈልጉህ ነገሮችም አንተን ይከተሉሃል፡፡
"ሙሉ ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር እናስረክብ።"
@aleroe
……✍ሰውየው አስር ክፍል ቤት ሠርቶ ብቻውን ሲኖር አንድ
ቀን በሩ ተንኳኳ ሲከፍት ጌታ ነው፡፡ "ውይ አምላኬ
ጌታዬ አንተ እኔ ቤቴ መጣህ?" ብሎ በደስታ
ተቀብሎት አንድ ክፍል ቤት ሰጥቶት መኖር ጀመሩ፡፡
በሌላ ጊዜ በሩ ተንኳኳ፣ ሲከፍት ሰይጣን ነው፡፡
ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ
ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል?" አለው፡፡
ጌታም "ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም " አለው፡፡
ሰውየውም ተሰምቶት ሁለት
ክፍል ቤት ለጌታ ጨምሮለት እርሱ ሰባት ክፍል ይዞ
መኖር ቀጠሉ፡፡ በሩ ተንኳኳ ሲከፈት ሰይጣን ነው፡፡
ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ
ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል? " አለው፡፡
ጌታም " ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም " አለው፡፡
ሰውየውም ተሰምቶት ከጌታ
ጋር እኩል ለእኩል ተካፈለ፡፡
ነገር ግን ቤቱ ከቀድሞ ይልቅ ተንኳኳ ፡፡ አዝኖም
ይዘጋና ጌታ ሆይ አለው፡፡ ጌታም የቀድሞውን መልስ
ሰጠው፡፡
በዚህ ጊዜ ሰውየው ለራሱ አንድ ክፍል ቤት ይዞ
ዘጠኙን ክፍል ቤት ለጌታ ሰጠው፡፡ ነገር ግን
ከቀድሞው ይልቅ በጣም ተንኳኳ፡፡ ቢከፈት ሰይጣን
ነው፡
በሩን ይዘጋና ወደ ጌታ ሄዶ " ጌታ ሆይ ምሥጢሩ
ምንድን ነው? " አለው፡፡ "ጌታ ግን ቤቱ የአንተ እንጂ
የእኔ አይደለም "አለው፡፡
በዚህ ጊዜ ዐሥሩንም ክፍል ለጌታ አስረከበ፡፡ ጌታም
አንድ ክፍል ቤት ለሰውየው ሰጠው፡፡ በሩም ተንኳኳ
፡፡ ጌታም ሊከፍት ተነሣ፡፡ ሲከፍት ሰይጣን ነው፡፡
ሰይጣንም " ይቅርታ የአንተ ቤት መሆኑን አላወቅሁም
" ብሎ ሄደ፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ መንኳኳት ቆመ፡፡
ሁሉንም የሕይወታችንን ክፍል ለጌታ እግዚአብሔር
ካላስረከብነው መንኳኳት አይቆምም፡፡ 1ዐ% ስንሰጥ
ይንኳኳል፡፡ 30% ስንሰጥ ይንኳኳል፡፡ 50% ስንሰጥ
ይንኳኳል፡፡ 99% ስንሰጥ ይበልጥ ይንኳኳል፡፡ 100%
ስንሰጥ መንኳኳት ይቆማል፡፡ እኛ ከከፈትን ሰይጣን
ይገዳደረናል፡፡ ጌታ ሲከፍት ሰይጣን " ይቅርታ የአንተ
ቤት መሆኑን አላወቅሁም " ብሎ ይሄዳል፡፡
ጌታ ሰማይን የደስታ አገር ያደረጋት ሙሉ
በሙሉ የፈጣሪ ፈቃድ የጸናባት በመሆኗ ነው፡፡
ባንተም ሕይወት የሰማይ ደስታ የሚመጣው
የፈጣሪ ፈቃድ በሕይወትህ ሙሉ በሙሉ
ሲፈጸም ነው፡፡ ስለዚህ፡-
· ፈጣሪን እረኛህ አድርገው፡፡
· በፍጹም ልብህ ተከተለው፡፡
· የሚያስፈልጉህ ነገሮችም አንተን ይከተሉሃል፡፡
"ሙሉ ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር እናስረክብ።"
@aleroe
ኤልሮኢ:(⚜ትምህርት⚜)
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አ
#ጌታችን_ለምን_ተጠመቀ?
1. ምሥጢርን ለመግለጥ፡-
ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ግልፅ ሆኗል፡፡ አብ በደመና “የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው” በማለቱ አብ የወልድ አባት መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወቱ መሆኑን ሲያስረዳ በአምሳለ ርግብ በራሱ ላይ ተቀመጠ ወልድም በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ታየ፡፡ ስለዚህ ምሥጢርን ለመግለጥ ስንል የአንድነት የሦስትነት ምስጢር በጐላ ሁኔታ እንዲታወቅ ተጠመቀ ማለት ነው፡፡ /ማቴ. 3፥16/
2. ትንቢቱን ለመፈፀም፡-
በመዝሙር 46/47/፥16 ላይ “አቤቱ ውሆች አዩህ፣ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ ውሆችም ጮኹ፡፡” ተብሎ በቅዱስ ዳዊት የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም ተጠመቀ፡፡
3. አርአያ ሊሆነን፡-
ተጠምቆ እንድንጠመቅ አደረገን ሥርዓትን ሠራልን ቀድሞ በአርአያውና በአምሳሉ እንደፈጠረን አሁንም አርአያ ምሳሌ ሆነን፡፡ ለዚህም ነው ምሳሌን ከእኔ ተማሩ ያለን፡፡ /ማቴ 11፥29/ ለትምህርት ለአርአያ /ዮሐ. 13፥1-17/
4. የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ፡-
አዳምና ሔዋን ፍዳው በፀናባቸው መከራው በበዛባቸው ጊዜ የሚያቃልልላቸው መስሏቸው ዲያብሎሰ ስመ ግብርናችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ ባላቸው ጊዜ አዳም ገብሩ ለዲያቢሎስ (አዳም የዲያብሎስ የወንድ አገልጋይ) ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ (ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ዲያብሎስም ይህንን ደብዳቤ አንዱን በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ አስቀመጠው፡፡ በዮርዳኖስ ያስቀመጠውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ ደምስሶታል፡፡ ይህንን ጽሕፈት ለመደምሰስ ነው ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተፃፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፡፡” ያለው ቆላ 2፥14
#ጌታችን_መች_ተጠመቀ?
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ5531 ዓመተ ዓለም ዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር፡፡ /ሉቃ. 3፥23/
#ጌታችን_ስለምን_በ30_ዓመት_ተጠመቀ?
በብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ልማድ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር ተልእኮ እና መንፈሳውያን አገልግሎቶች ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር፡፡ እጅግ አስፈላጊ እንኳ ቢሆን ከ20 እና 25 ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ልማድ አልነበረም፡፡ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፣ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው፡፡ /ዘፀ. 4፥3፤1ዜና መዋ. 23፥24፤ 1ጢሞ. 3፥6-10/ ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ30 ዓመቱ ነበር፡፡
ዮሐንስ መጥምቅም የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ30 ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው፡፡ ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40ኛ ቀን ተሰጥቶት ኋላም በኃጢአት ምክንያት ያስወሰደውን ልጅነት ለማስመለስ ነው፡፡
ክርስቶስ የተጠመቀው ክብር ሽቶ ሳይሆን የአብ የባሕርይ ልጅነቱን (የባሕርይ አምላክነቱን) ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር፣ ውኃውን
#የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ያለው የአከባበር ሥርዓት በማንና መቼ ተጀመረ ???????
የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
የጥምቀት በዓል ከሌላው አለም በተለየ መልኩ በሀገራችን በኢትዮጵያ በልዩ ሥርዓት ይከበራል ይህ ደሞ በአንድ ጀምበር የተደረገ ሳይሆን ከዘመን ዘመን በተለያየ ጊዜ በሚነሱ ሊቃውንትና ደጋግ አባቶች በሠሯቸው ሀይማኖታዊ ምስጢሩንም በጠበቀ መልኩ እንዲፈፀሙ ባሳወጇቸው አዋጆች አማካኝነት ነው። ይህ በዓል የሚከበርበት ሰሞን ቤተ ክርስቲያናችን በግእዝ
"አስተርእዮ " በአማርኛም የመታየት የመገለጥ ጊዜ ብላ በሰየመችው ወቅት ነው።ኢትዮጵያ ሀገራችን ስለ ነገረ ጥምቀት የሰማችው ከሌላው ዓለም አስቀድማ ጌታችን ባረገ በጥቂት
ወራት በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አማካኝነት(በ34 ዓ.ም)ነው
(የሐዋ 8፡26-39)፤ይህ በዐል ከዘጠኙ ዐበይት የጌታችን በዐላት
መካከልአንደኛው ሲሆን የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስተምሩን ከሆነ
ጥምቀት በሀገራችን እስከ 6ኛው መ·ከ·ዘ የሚከበረው ታቦታተ ህጉ ከቅፅረ ቤተ ክርስቲያን ሳይውጡ በዑደት ብቻ ነበር። ታዲያ ከ515-529 ዓ.ም ለ14 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በአጼ ገብረ
መስቀል ዘመንና በታላቁ ሊቅ በቅዱስ ያሬድ አማካኝነት የተለያዩ የቤተክርስቲያን በዓላት የአከባበር ሥርዓትን በሚያስተካክሉበት ጊዜ ለጥምቀትም የጌታችንን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ
ማምራት በማሰብ ታቦታቱ ጥር 11 ጠዋት ከመንበረ ክብራቸው
ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ አምርተው አመሻሹ ላይ እንዲመለሱ ሥርዓት ተሠራ፡፡በዚህም አይነት አከባበር በ12ኛው መ,ክ,ዘ ተነስቶ ከ1157-1197 ዓ.ም ድረስ ለ40 ዓመት
ኢትዮጵያን እስከመራው እስከ ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ
ዘመን ድረስ ቀጥሎ ቆየ።ከዚያም እረሱ ደግሞ በአንድ አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስትያናት ታቦታቱ በአንድ ቦታ ላይ እንዲያከብሩ ታላቅ መንፈሳዊ ዐዋጅን አሳውጆ በአንድ አካባቢ፣ወረዳ፣ ያሉ
በአንድ ላይ ማክበር ጀመሩ፤ በርሱ ዘመን የነበሩት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም በአክሱም፣ በጎንደር፣በሸዋ፣ በአንኮበር፣ በመርጡለ ማርያም እየሄዱ ባሕረ ጥምቀቱን ይባርኩ እንደነበር ታሪክ ይናገራል፡፡በመቀጠልም
ከ50 አመታት በኋላ በዐጼ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አሳሳቢነት ታቦታቱ በባሕረ
ጥምቀት ሲውሉ ምእመናን በታላቅ ድምቀት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ
እንዲውሉ መንፈሳዊ ዐዋጅ አሳወጁ፡፡እንደገና ከ200 አመታት በኋላ ተነስተው 1426-1460 ዓ.ም ለ34 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩትና ለቤተክርስቲያናችን መልካም ውለታን በዋሉላት በታላቁ ንጉሥ በዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥትም ንጉሡ ከሊቃውንት ጋር በመወያየት የበዐሉን ታሪክ ተከትሎ ታቦታቱ ጥር 10 ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት እንዲወርዱና ጥር 11 እንዲመለሱ አወጁ።ታቦተ ጽዮን
በሄደችበት ሁሉ በረከትን ትሰጥ እንደነበር፣የዮርዳኖስን ባህር
እንደከፈለች፣የኢያሪኮን ቅጽር እንዳፈረሰች፣ የፍልስጤማውያንን
ጣዖት ዳጎንን ቀጥቅጣ እንዳጠፋች ሁሉ ምድረ ኢትዮጵያ ትባረክ ዘንድ ርኲሳን መናፍስት ይርቁ ዘንድ አካባቢዎች ሁሉ በቃል ኪዳኑ ታቦታት ይቀደሱ ዘንድ ታቦታቱ በመጡበት መንገድ እንዳይመለሱ ታላቅ ዐዋጅ አሳውጁ በዐዋጁም መሠረት ይሄው ዛሬ ድረስ እጅግ በደመቀ መልኩ በዓሉ እየተከበረ ይገኛል፡፡አሁን ባለንበት ጊዜም ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝ· 44፡16 ላይ “በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች
ተወለዱልሽ” በማለት እንደተናገረ ከመቼውም በበለጠ እግዚአብሔር የወጣቱን ልብ በረድኤት ጎብኝቶት ለቃል
ኪዳኑ ታቦታት ክብር አካባቢውን እያስዋበ፣ ታቦታቱ የሚሄዱበትን
መንገድ እየጠረገ፤ ታላላቅ ምንጣፎችን ታቦታቱ በሚሄዱበት ጎዳና ሁሉ እያነጠፈ ለቃል ኪዳኑ ታቦት ከፍተኛ ክብር በመስጠት እግዚአብሔርን እያገለገለ ይገኛል፡፡የወደፊቱን ቀጣይ ጊዜ ደግሞ ከዚህ በበለጠ መልኩ ደምቆና በፍፁም ሰላም እንድናከብር እግዚአብሔር አምላካችን ዘውትር ከእኛ አይለየን።

ኤልሮኢ:(⚜ስነፅሁፍ⚜)
የጠዋቱ ጮራ
ዘመነ ሐዋርያት የጥንቱ
የክርስትና ጎህ የጠዋቱ
ተመልሰህ ና! እንደገና
የጽዋዕው ማኅበር ....
በአንድ ልብ መምከሩ በአንድ ቃል መናገሩ
ከቶ ጠፍቷልና ጨርሶ ከምድሩ
እባክህ ተመለስ ዛሬም እንደገና
መሠረተ እምነት መቅድመ ክርስትና
የሐዋርያት ዘመን የዘለዓለም ፋና
በአንድ መሶብ ዙሪያ ተቋርሶ መብላቱ
በአንድ ጽዋዕ ዋንጫ ቀርቶ መጠጣቱ
የያኔው አሻራ የጠዋቷ
ኧረ ለምን ይሆን ደብዝዞ; ደብዝዞ መቅረቱ
የነደደው እሳት ፍቅር ፍም መጥፋቱ
እንዳይተርፍ ተብሎ ስስት ተጀመረ
በረከት መባሉ ያኔ ድሮ ቀረ
መሶቡ ተነሥቶ በእጅ ሆነ ገበታው
ተድበለበለች ቁርጥ ሆነ እንጀራው
ጸጋው መቆረጡን ማንም አላሰበው
ያኔ! ለጴጥሮስ ሲያስረክብ ርስቱን እየሸጠ
የያኔው ክርስቲያን መች በረኀብ ተዋጠ
መቼ ጎደለበት መቼ ተንገላታ
በፍቅር ኖረ እንጂ አንዴም ሳይፈታ
በረከት በዝቶበት በብዙ ገበታ
እንያ ሐናንያ ሲጳራ ልባቸው የዋለለ
ወደ ገንዘብ ፍቅር ወዲያው ያጋደለ
በሊቀ ሐዋርያት በቅዱስ ጴጥሮስ ቃል
በመንፈስቅዱስ ጅራፍ ተቀጥቅጠዋል
ባለሙት ሁሉም ላይ ሄዶ ቀርቷል
ቀዳሚት ተዋሕዶ የሐዋርያት
የፍቅር ጸጋ በረከት
አትራቂ አትሽሺ አትለይን በእውነት
ከፊት ምሪን እንጂ በመሆን አብነት
ሁሉም እንደወጣ በአንቺ አርነት
ጽዋዕና መሶቡን ዓለም ሲጥለው
በእኛ ዘንድ ተገኘ የጥንት አሻራው
ሸክላ ነህ ስላለህ እንዳይቀር አደራ
እንደ ገዳማቱ እንኑር በጋራ
ብርሀን ነውና የጠዋቱ ጮራ
@aleroe
የጠዋቱ ጮራ
ዘመነ ሐዋርያት የጥንቱ
የክርስትና ጎህ የጠዋቱ
ተመልሰህ ና! እንደገና
የጽዋዕው ማኅበር ....
በአንድ ልብ መምከሩ በአንድ ቃል መናገሩ
ከቶ ጠፍቷልና ጨርሶ ከምድሩ
እባክህ ተመለስ ዛሬም እንደገና
መሠረተ እምነት መቅድመ ክርስትና
የሐዋርያት ዘመን የዘለዓለም ፋና
በአንድ መሶብ ዙሪያ ተቋርሶ መብላቱ
በአንድ ጽዋዕ ዋንጫ ቀርቶ መጠጣቱ
የያኔው አሻራ የጠዋቷ
ኧረ ለምን ይሆን ደብዝዞ; ደብዝዞ መቅረቱ
የነደደው እሳት ፍቅር ፍም መጥፋቱ
እንዳይተርፍ ተብሎ ስስት ተጀመረ
በረከት መባሉ ያኔ ድሮ ቀረ
መሶቡ ተነሥቶ በእጅ ሆነ ገበታው
ተድበለበለች ቁርጥ ሆነ እንጀራው
ጸጋው መቆረጡን ማንም አላሰበው
ያኔ! ለጴጥሮስ ሲያስረክብ ርስቱን እየሸጠ
የያኔው ክርስቲያን መች በረኀብ ተዋጠ
መቼ ጎደለበት መቼ ተንገላታ
በፍቅር ኖረ እንጂ አንዴም ሳይፈታ
በረከት በዝቶበት በብዙ ገበታ
እንያ ሐናንያ ሲጳራ ልባቸው የዋለለ
ወደ ገንዘብ ፍቅር ወዲያው ያጋደለ
በሊቀ ሐዋርያት በቅዱስ ጴጥሮስ ቃል
በመንፈስቅዱስ ጅራፍ ተቀጥቅጠዋል
ባለሙት ሁሉም ላይ ሄዶ ቀርቷል
ቀዳሚት ተዋሕዶ የሐዋርያት
የፍቅር ጸጋ በረከት
አትራቂ አትሽሺ አትለይን በእውነት
ከፊት ምሪን እንጂ በመሆን አብነት
ሁሉም እንደወጣ በአንቺ አርነት
ጽዋዕና መሶቡን ዓለም ሲጥለው
በእኛ ዘንድ ተገኘ የጥንት አሻራው
ሸክላ ነህ ስላለህ እንዳይቀር አደራ
እንደ ገዳማቱ እንኑር በጋራ
ብርሀን ነውና የጠዋቱ ጮራ
@aleroe
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
#ስጋ_ነው_ምርኩዜ
ስጋዬ ወፍሮ አፌ ክፉ ደፍሮ
ሓሰትን መስክሮ እውነት ቅሉን ሽሮ
እውነት ተሸሸጋ ማን እውነት ሊያወጋ
ስለ ክፉ ስጋ።
ስለ ክፉ ስጋ ነፍሴ ስትወጋ
የአንደበቴ ችቦ የአንደበቴ ሰንጋ
ነፍሴ ስትቃትት የስጋ ጦር ወግቷት
ቀንም ሌሊትም ቁስሉ ሲያሰቃያት
ጭንቅ ጥብብ አለች ቀኑ ጨልሞባት
የምታውቀው ቤቷ ተዘግቶባት
ስጋ ሲበድላት በሐዘን በትካዜ
በሐሰት ባለሟል በስጋ ምርኩዜ
እኔንም ተረድታ በእምነት መደብዘዜ
በህይወት ልታልፍ ልትጓዝ በግዜ
ነፍሴ የተዘጋጀች ልታቀርብ ኑዛዜ።
____________________
@aleroe
#ስጋ_ነው_ምርኩዜ
ስጋዬ ወፍሮ አፌ ክፉ ደፍሮ
ሓሰትን መስክሮ እውነት ቅሉን ሽሮ
እውነት ተሸሸጋ ማን እውነት ሊያወጋ
ስለ ክፉ ስጋ።
ስለ ክፉ ስጋ ነፍሴ ስትወጋ
የአንደበቴ ችቦ የአንደበቴ ሰንጋ
ነፍሴ ስትቃትት የስጋ ጦር ወግቷት
ቀንም ሌሊትም ቁስሉ ሲያሰቃያት
ጭንቅ ጥብብ አለች ቀኑ ጨልሞባት
የምታውቀው ቤቷ ተዘግቶባት
ስጋ ሲበድላት በሐዘን በትካዜ
በሐሰት ባለሟል በስጋ ምርኩዜ
እኔንም ተረድታ በእምነት መደብዘዜ
በህይወት ልታልፍ ልትጓዝ በግዜ
ነፍሴ የተዘጋጀች ልታቀርብ ኑዛዜ።
____________________
@aleroe
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
ኤልሮኢ:(መዝሙር)
#የሚጠብቀኝ አይተኛም
የሚጠብቀኝ አይተኛም(×2) አያንቀላፋም(×2)
ቤት ባይኖረኝም
በደጅ ባድር
ቀንና ሌሊት ከኔ አይርቅም
ድምፀ አራዊት የሌሊት ግርማ
ወደ እኔ አይገቡም ድምፅህ ሲሰማ
መሰናከልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሀይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም
ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በፅድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ
የሰማዩን ጥል እታገሳለሁ
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለሁ
ሌሊት በድብቅ ለሚጎበኙ
ለፃድቃኑ ግን አምላክ ይስጥልኝ
እንቅልፌን ባርኮ የሰጠኝ ጌታ
በዓለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የዕለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍፁም
ምስጋና ላቅርብ እስከዘላለም
#ዘማሪ ይልማ
@aleroe
#የሚጠብቀኝ አይተኛም
የሚጠብቀኝ አይተኛም(×2) አያንቀላፋም(×2)
ቤት ባይኖረኝም
በደጅ ባድር
ቀንና ሌሊት ከኔ አይርቅም
ድምፀ አራዊት የሌሊት ግርማ
ወደ እኔ አይገቡም ድምፅህ ሲሰማ
መሰናከልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሀይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም
ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በፅድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ
የሰማዩን ጥል እታገሳለሁ
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለሁ
ሌሊት በድብቅ ለሚጎበኙ
ለፃድቃኑ ግን አምላክ ይስጥልኝ
እንቅልፌን ባርኮ የሰጠኝ ጌታ
በዓለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የዕለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍፁም
ምስጋና ላቅርብ እስከዘላለም
#ዘማሪ ይልማ
@aleroe
Forwarded from "ኤልሮኢ ዘተዋህዶ" via @like
ኤልሮኢ:
……✍አንድ በምሽት አቅጣጫ የጠፋበት መርከብ ከሩቅ ያየ ሰው ወደ እቤቱ ገብቶ ሻማ ይለኩሳል
ሻማውም ለምን ለኮስከኝ ቢለው ሰውዬው ‹‹አቅጣጫ የጠፋው መርከብ ከሩቅ ያታየኛል
ለሱ በእሳት ልጠቁመው ነው ይለዋል ሻማውም ‹‹ታዲያ እኔ ሻማ ነኝ እንዴት ከሩቅ እታያለሁ›› ቢል ሰውዬውም መለሰ ‹‹ሻማዬ ሆይ አንተ ብቻ የቻልከውን ብራ›› አለውና ይዞት ይወጣና ብዙ ደረቅ እንጨቶችን እንደ ዳመራ ከቆለለ ቦሃላ በሻማው እሳት እንጨቶቹን ለኮሰ ብርሃኑም ብዙ ሆነ
ያኔ መርከቡም ተመልክቶ መጣ
ሰውዬውም ለሻማው እንዲህ አለው ‹‹ሻማዬ ሆይ አየህ አንተ በቻልካት መጠን ስለበራህ ያንተን ብርሀን ተቀብለው የሚያደማምቁ ብዙዎች አሉ›› አለው፡፡
እንግዲህ እንዲህ ነው የኔ ጥረት ትንሽ ናት አትበል፡፡ የቻልከውን ካደረክ ሌሎች ያንተን ብርሃን የሚቀበሉ እልፎች አሉ
‹‹የትም ሁን ማንም ሁን ያቅምህን በጎ ለማድረግ ግን አትስነፍ ደግነት
እንደ ጥሩ ሽቶ ነው ከአንዱ ተነስቶ ወደ አንዱ ይጋባል››
እንግዲህ አንዲህ ነው ለመስጠት የግድ ሃብታም መሆን
አይጠበቅብህም፡፡ ደግሞ ማንም ሰው ልስጥ ካለ የሚሰጠው አያጣም፡፡

ኤልሮኢ፡
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን
✝✝አስተርእዮ ማርያም✝✝
ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኩሉ"
ሞት ለሚሞት ሰው ይገባዋል
የማርያም ሞት ግን በጣም ያስደንቃል
እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕተ ንጹሃን ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ታላቅ አመታዊ በዓል ( ለአስተርእዮ ማርያም) በሰላም በጤና አደረሳችሁ:: አደረሰን!
✞ አስተርእዮ ማለት? መታየት መገለጽ ነው
እመቤታችን ጥር ሃያ አንድ ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይቶ በደመና ተነጥቃ ወደ ገነት በመግባት ለጻድቃን ሰዎችና ለመላእክት በሰማይና በምድር ተገልጣ ጸጋና ክብሯ የተገለጸበት እለት በመሆኑ በዓሉ አስተርእዮ ማርያም ይባላል::
✞ ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድ የእመቤታችንን ሞት አስደናቂ መሆኑን እንዲህ ሲል ገልጦታል
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኩሉ"
ሞት ለማናቸወም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል
የእመቤታችን አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁንና እመቤታችን ከእናትና ከአባቷ ዘንድ ሦስት አመት በቤተ መቅደስ አስራ ሁለት አመት ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሰላሣ ሦስት አመት ከሦስት ወር በዮሀንስ ወልደ ነጐድጓድ ዘንድ አስራ አራት አመት ከዘጠኝ ወር በጠቅላላው ስልሣ አራት አመት ሲሆናት ጥር 21 ቀን በ49 ዓመተ ምሕረት ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች::
እመቤታችን ጥር ሃያ አንድ ቀን ዕረፍት በሆነበት ዕለት ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ ለማሳረፍ ወደ ጌቴሰማኒ መካነ ዕረፍት /የመቃብር ቦታ/ ይዘዋት ሲሆዱ አይሁድ በቅንዓት መንፈስ ተነሳስተው ቀድሞ ልጇን በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ አረገ እንደገናም ተመልሶ ይህን ዓለም ለማሳለፍ ይመጣል እያለ በማስተማር ሕዝቡን ፈጽመው ወስደውታል አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷንም እንደ ልጇ ተነሳች አረገች እያሉ በማስተማር ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለም ኑ ተሰብሰቡና በእሳት እናቃጥላት ብለው ተማክረው መጥተው ከመካከላቸው ታውፋኒያ የተባለው ጎበዝ አይሁዳዊ ተመረጦ ሄደ::
የእመቤታችንን ሥጋ የተሸከሙትን አልጋ ያዘ የአልጋውንም ጥራዝ በያዘ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁለት እጁን ሰለቆረጣቸው ከአልጋው ጫፍ ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ ታውፋንያ በፈጸመው ድርጊት ተጸጽቶ ወደ እመቤታችን ስለተማጸነ በኀቡዕ ተአምር የተቆረጡ እጆቹን እንደቀድሞ አድርጋ ፈውሳዋለች::
{ስንክሳር ዘጥር}
✞ ለበቁ ቅዱሳን ተአምሯን የገለጸች እመቤታችን ለእኛም ለልጆቿ ከልጇ ከወዳጇ በአማላጅነቷ ምሕረትን ይቅርታው ታሰጠን::አሜን!
ለተጨነቁ በስደት ላሉ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ የሚሰቃዩ ወገኖቻችን ትፈውስልን የእናታችን የአዛኝቷ ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይሁን አሜን::
➕➕@aleroe➕➕

✍.....ትህትና በአባቶች ሕይወትና ትምህርት ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ ይገኛል። ቅዱስ ያዕቆብ እንዲህ ብሏል ስለ ትህትና ማስተማር እፈልጋለሁ። ደግሞ እፈራለሁ። ስለ እግዚአብሔር ለመናገር እንደሚፈራ ሰው እመስላለሁ። ምክንያቱም ትህትና መለኮት ሰው ሆኖ በምድር ሲገለጥ የተጠቀለለበት መጎናጸፊ ነውና። ሰው ሆኖ በአጭር ደረት በጠባብ ቁመት የመገለጡም ምሥጢር እጅግ አስደናቂ በሆነ በትህትናው ነው። ይሄ ሁኔታው ያስደነቀው ነቢዩ ኢሳይያስ "ያልተጠባበቅነውን የጽድቅ ሥራህን ባደረግህ ጊዜ ወረድህ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ" ኢሳ. 64፥4 ብሏል። ሰይጣን ትሁት ሰው ሲያይ የሚፈራው በትሁት ሰው ውስጥ የፈጠረውንና በትህትና ያሸነፈውን እግዚአብሔር ስለሚያየው ነው።

እርሱ ኃያል ሲሆን የሰው ፍቅር አገብሮት ወደዚች ምድር በትህትና መጣ። የማይታይ ረቂቅ ሲሆን ስለ ፍቅር ሲል ግዘፍ ሥጋን ተዋሐደ ። ባለጸጋ ሲሆን ምንም እንደሌለው በበረት አደረ። እኛን ከፍ ያረገን ዘንድ እርሱ ዝቅ አለ። አምላክ ሲሆን በትህትና በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ። ፍጥረትን ሁሉ የሚመግብ ሲሆን እርሱ ግን 40ቀንና ሌሊት ፆመ ተራበም። የህይወት ውሃ ሲሆን እርሱ ግን ተጠማ። እርሱ የሁሉ ፈራጅ ሲሆን በፈራጅ ፊት ቆሞ ተፈረደበት። የአዳምን ቁስል ይፈውስ ዘንድም ተገርፎ ቆሰለ። የአዳምን የበደል ሸክም ያቀል ዘንድ የእርሱ ጀርባ በጨካኝ ሮማውያን ወታደሮችን ጅራፍ ተገረፈ ። የክብር ባለቤት እርሱ እኛ እንከብር ዘንድ ተዋረደ ምራቅም ተተፋበት። ዘላለማዊን ንጉስ አይሁዳውያን ዘበቱበት። ለሠማዕታት የክብር አክሊልን የሚያቀዳጅ እርሱን ስለ እኛ ፍቅር የእሾህ አክሊልን ተቀዳጀ ። የእኛን ሸክም ያቀል ዘንድ ርጥብ መስቀልን ተሸከመ ከወደቅንበት ያነሳን ዘንድ ወደቀ። የእኛን ፊት በብርሃን ይሞላ ዘንድ የእሱ ፊት በደም ተሸፈነ። እርሱ ቁስላችንን ቆሰለ ህማማችንን ታመመ። እንጀ ቆዳ በእንጨት ላይ ተወጠረ በመስቀል ላይ ተሰቀለ እርሱ ስለ እኛ ራሱን ቤዛ አድርጎ ሠጠን።
ወዳጄ ሆይ እርሱ ለእኛ ራሱን ሰጠ እኛስ ለእርሱ ምን እንሰጠው ይሆን?
በረከት(ወልደ ሰንበት)
የካቲት 6/2013

✝ አዝናለሁ አለቅሳለሁ
አዝናለሁ አለቅሳለሁ
ስለ በደሌ ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ
አዝናለሁ አለቅሳለሁ
ስለ ጥፋቴ ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ
ነገር ግን መሐሪ ነህና
እንደምታድነኝ አምናለሁ
ሥጋዬ ለራሱ እያታለለኝ(፪)
ሁሉን በመፈለግ ወሰደና ለጥፋት ሰጠኝ(፪)
አዝ = = = = =
ከመሬት ተገኝታ እስክትገባ
በከንቱ አስቀረችኝ አምላኬ ሆይ ሥጋ ሰገብጋባ(፪)
አዝ = = = = =
ትቻት መምጣቴ ነው አፈር ሥጋዬን
እንድትቀበላት አምላኬ ሆይ አደራ ነፍሴን(፪)
@aleroe
✝ አዝናለሁ አለቅሳለሁ
አዝናለሁ አለቅሳለሁ
ስለ በደሌ ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ
አዝናለሁ አለቅሳለሁ
ስለ ጥፋቴ ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ
ነገር ግን መሐሪ ነህና
እንደምታድነኝ አምናለሁ
ሥጋዬ ለራሱ እያታለለኝ(፪)
ሁሉን በመፈለግ ወሰደና ለጥፋት ሰጠኝ(፪)
አዝ = = = = =
ከመሬት ተገኝታ እስክትገባ
በከንቱ አስቀረችኝ አምላኬ ሆይ ሥጋ ሰገብጋባ(፪)
አዝ = = = = =
ትቻት መምጣቴ ነው አፈር ሥጋዬን
እንድትቀበላት አምላኬ ሆይ አደራ ነፍሴን(፪)
@aleroe
ኤልሮኢ:(⚜ትምህርት⚜)
ጾመ ሰብአ ነነዌ
በርእሰ ደብር ብርሃኑ አካል
ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሟ የምትጀመርበት ቀን ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡
ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ይረዝማል፡፡ ጾመ ነነዌ በእነዚህ ፴፭ ቀናት ውስጥ ስትመላለስ (ከፍ እና ዝቅ ስትል) ትኖራለች፤ ከተጠቀሱት ዕለታት አትወርድም፤ አትወጣም፡፡ በዚህ ዓመትም የካቲት 15 ቀን ትጀመራለች፡፡
‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሚለው የጽሑፋችን ርእስ እንደሚያስረዳው ይህቺን የሦስት ቀን ጾም የጾሟት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪/ ፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የኾነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶባት ነበር /ዮናስ ፬፥፲፩/፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኀጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው /ሉቃ.፲፩፥፴/፡፡
ዮናስ የስሙ ትርጕም ‹ርግብ› ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናግሯል /፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩/፡፡
ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ኾነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል /፩ኛ ነገ.፲፯፥፲፱/፡፡ መድኀኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ኾድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል /ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪/፡፡
እግዚአብሔር ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡
እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለ ኾነ ንብረታችሁን ሳይኾን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡
እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይኾንም›› አሉ፡፡
ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡
እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መኾኑን አስረድቶታል፡፡
ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ኾኖ ከላይ ታይቶአል፡፡
የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ይመልከቱ/፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡
ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ዅሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች /አስ.፬፥፲፭-፲፮/፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች /ሉቃ.፪፥፵፮/፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መኾኑን ገልጿል /ሉቃ.፲፫፥፴፪/፡፡
ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡
በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡
ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኀጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኀጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ኾነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡
ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡
ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot

ኤልሮኢ:(⚜ትርክት⚜)
ውሻ ይማራልን+(ከልብኑ ይትመሐር?)
(ስሟን ካድልኝ)
እጅግ ገንዘቡ የበዛ የተረፈው አንድ ባለጸጋ ይኖር ነበር። ለአዝማሪ
ለዘዋሪ እየሰጠ አለቀበት አንድም የዚህ ዓለም ገንዘብ ሲሰበሰብ
እንጂ ሲጠፋ አይታወቅምና ከዚኅ በኋላ ከብሬ በኖርሁበት አገር
ተዋርጄ÷ሰጥቼ በኖርሁበት አገር ለምኜ አልኖርም ብሎ አገር ጥሎ
ቁርበት ጠቅሎ ሲሄድ ሰይጣን የጨዋ ልጅ መስሎ ከጎዳና ቆይቶ
ወዴት ትሄዳለህ አለው። ከብሬ በኖርሁበት አገር ተዋርጄ÷ ሰጥቼ
በኖርሁበት አገር ለምኞ አልኖርም ብዬ አገር ጥዬ ቁርበት ጠቅልዬ
መሄዴ ነው አለው።
ዲያቢሎስም ያዘነ መስሎ ድንጊያውን በምትሐት ወርቅ አስመስሎ
ይህን ብሰጥህ አትመለስምን? አለው ይህንንማ ካገኘሁ ለእኔ
ለልጅ ልጄ ይተርፋልና እመለሳለው እንጂ አለው። ከዚህ በኋላ
ሰጠው አንተም ፈቃዴንም ፈጽምልኝ አለው ምን ላድርግልህ
ቢለው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን ካድልኝ መላእክት ጻድቃን
ሰማዕታትን አያማልዱም በል አለው። ካደ አያማልዱም አለ።
ከተለያዩ በኋላ ነገረ ረስቼ ቆየኝ አለው ምእመናን አፍረው
አክብረው ስሟን የሚጠሯት ማርያም የምትባል አለች ወላዲተ
አምላክ መሆንዋን ካድልኝ አለው። የለማኝ ምርጉዜን እንዴት
እክዳለው። ምን ይዞ ይሄዳሉ ጉዞ እንዲሉ እሷንስ አይሆንም
አለው። እንኪያስ አምጣ ብሎ ወርቅ አስመስሎ የሰጠውን ድንጊያ
ተቀብሎ ልብ ራሱን ብሎ ገደለው።
መላእክተ ጽልመት ነፍሱን ከሥጋው ለይተው ወሰዱት። መላእክተ
ብርሃንም የጌታን ቁርጥ ፍርድ ሳያዩ አይለዩምና ከእመቤታችን
ዘንድ ሄደው ምነው ዝም አልሽ ይህች ነፍስ ከሥጋው የተለየች
ባንች ምክንያት አይደለምን አታማልጅም አሏት። እሷም "መሐር
ሊተ ወልድየ ዛተ ነፍስ" አለችው። "ከልብኑ ይትመሐር" አባቴን
እኔን የባሕርይ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱሳን የወዳጆቼ የመላእክት
የጻድቃን የሰማዕታት አማላጅነታቸውን የካደ ይማራልን።አላት
"ዘጸውዕ ስመኪ ወዘገብረ ተዝካረኪ እምሕር ለኪ" ያልኽው ቃልኽ
ይታበላልን አለችው።ያውስ ቢሆን የሕጸጸ ምግባር ነው እንጂ
የሕጸጸ ሃይማኖት ነውን ነገር ግን ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ
ነሥቼ ሰው መሆኔ ፈቃድሽን ላስፈጽምልሽ ነውና ምሬልሻለሁ
አላት። እንኪያስ ከማርክልኝ ነፍሱን ከሥጋው አዋሕደህ አስነሣልኝ
አለችው ነፍሱን ከሥጋው ጋር አዋህዶ አሰነሣላት።
ካድክ አለችው ባጣ አላት ያጣ ይለምናል እንጂ ይክዳልን ብላ
ገሰጸችው። ከልጄ አማልጄህ እንዲህ ካለ ቦታ ምግብህን
አዞልሃለና ሂድ ብላ አሰናበተችው። በሔደበትም ከተማ በዚያች
ቦታ አንድ ባለጸጋ ነበር አንዲት መልከ መልካም ልጅ ነበረችው
ባለጸጋ መጥቶ ልጅህን ስጠኝ ያለው ፉንጋ እንደሆነ ልጄን በመልክ
አትተካከላትም ብሎ ይመልሰዋል። መልከ መልካም መጥቶ
ስጠኛ ያለው እንደሆነ ደግሞ ልጄን በገንዘብ አትተካከላትም ብሎ
ይሸኛዋል። እንዲህ አድርጉ ከፍቅሩ ጽናት የተነሳ ያኖራት ነበር።
በዚያች ቀን ግን እመቤታችን ይህን ባለጸጋ ከቤተክርስቲያን
እንዲሔድ አድረገችው የባለጸጋ ጸሎት አጭር ነውና የሰጠኸኝን
አትንሣኝ ይህችን አንዴት ቅንጣት ልጄን ባርክልኝ ብሎ ተቀመጠ።
ወዲያው ተደሞ መጣበት ያም ሰው ጠፈር ጠፈሩን እያየ ሲዞር
ከሱ አጠገብ ደርሶ ቆመ ልጅህንም ከብትህንም ለዚህ ሰው ስጠው አለችው። ቀና ቢል አየው ከዚህ በኋላ ወስዶ ልጁንም ከብቱንም ሰጥቶ ወዲያው ዐረፈ እሱም ቆርቦ የእመቤታችንን ስሟን ሲጠራ ዝክሯን ሲዘክር የሚኖር ሆኗዋል።
"ወሥሉጥ ስምኪ በኀበ እግዚአብሔር"
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ

Abiye-Tsome-Hudade.pdf
60.6 KB
⚜ትምህርት⚜
ስለ ዐቢይ ፆም
💠.ዐቢይ ለምን ተባለ ?
💠.ስንት ሳምንታት አሉት ?
አጠር ብሎ የተዘጋጀ
ያንብቡ share ያድርጉ
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ስለ ዐቢይ ፆም
💠.ዐቢይ ለምን ተባለ ?
💠.ስንት ሳምንታት አሉት ?
አጠር ብሎ የተዘጋጀ
ያንብቡ share ያድርጉ
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @Aleroebot
ኤልሮኢ:(⚜ዝማሬ⚜)
ሐመረ ኖህ ነሽ
============
ሐመረ ኖህ ነሽ
የምህረት ቃል ኪዳን የተገባልሽ
ትውልድ ይህን አምኖ
ያከብርሻል አልቆ እና አግኖ
አዝ----------------//
በእግዚአብሔር ሀሳብ ነበርሽ በህሊና
ዓለምን ሳይፈጥር አዳምን ሳይሠራ
ሁሉን የናፈቀሽ የወጣብሽ ፀሀይ
ንግሥት ነሽ ድንግል እሙ ለአዶናይ
አዝ----------------//
ያንን የጭንቅ ቀን የጥፋቱን ዘመን
አልፈነዋል ባንቺ በአማናዊት ፅዮን
ምንጭ ነሽ የእርካታ የድህነት መፍለቂያ
የዘለዓለም እረፍት አንባ እና ማረፊያ
አዝ----------------//
የነቢያት ተፈጽሞ አየን
አንቺ ምክንያት ሆነሽ ለመዳናችን
ድምፅሽን ጠላት ይሸበራል
እኛ ግን ሰምተነው በሀሴት ዘለናል
አዝ----------------//
አንዴ በገባልሽ ቃል ኪዳን መሠረት
ትውልዱን ይምራል ይኸው በቸርነት
ስሽ ወለላ ነው ጣፋጭ ለአፋችን
ማርያም ማርያም ብለን ታብሷል እንባችን
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ሐመረ ኖህ ነሽ
============
ሐመረ ኖህ ነሽ
የምህረት ቃል ኪዳን የተገባልሽ
ትውልድ ይህን አምኖ
ያከብርሻል አልቆ እና አግኖ
አዝ----------------//
በእግዚአብሔር ሀሳብ ነበርሽ በህሊና
ዓለምን ሳይፈጥር አዳምን ሳይሠራ
ሁሉን የናፈቀሽ የወጣብሽ ፀሀይ
ንግሥት ነሽ ድንግል እሙ ለአዶናይ
አዝ----------------//
ያንን የጭንቅ ቀን የጥፋቱን ዘመን
አልፈነዋል ባንቺ በአማናዊት ፅዮን
ምንጭ ነሽ የእርካታ የድህነት መፍለቂያ
የዘለዓለም እረፍት አንባ እና ማረፊያ
አዝ----------------//
የነቢያት ተፈጽሞ አየን
አንቺ ምክንያት ሆነሽ ለመዳናችን
ድምፅሽን ጠላት ይሸበራል
እኛ ግን ሰምተነው በሀሴት ዘለናል
አዝ----------------//
አንዴ በገባልሽ ቃል ኪዳን መሠረት
ትውልዱን ይምራል ይኸው በቸርነት
ስሽ ወለላ ነው ጣፋጭ ለአፋችን
ማርያም ማርያም ብለን ታብሷል እንባችን
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(⚜ብሂለ አበው⚜)
+ የአባቶች ድንቅ ጥበብ የተሞሉ መልሶች +
ባለ ብዙ ታሪኩ የወሊሶው ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ያጠምቁና ያስተምሩ በነበረበት ሥፍራ አንድ በትዕቢት መንፈስ የሚሰቃይ ወጣት መጣና መፈክርነት ያዘለ ቃል ተናገረ:: ክብር ይግባትና ንግግሩ የድንግል ማርያምን ዘላለማዊ ድንግልና የሚቃወም ነበር::
ወደ አባ ዲዮስቆሮስ ቀርቦ እንዲህ አላቸው :-
ወጣቱ :- "ድንግል ማርያም እኮ ብዙ ልጆች አሉአት"
አቡኑ :- "ባታውቀው ነው እንጂ ለአንተም እኮ እናትህ ናት!"
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
የቦሩ ሜዳው መምህር አካለ ወልድ ከሌሎች ሊቃውንት ጋር ኢየሩሳሌምን ሲሳለሙ ድንገት የሌላ ሀገር መነኮሳት መጥተው በዱላ አጣደፉአቸው:: ነገሩን ሲጠይቁ ለምን በእግዚአብሔር ሦስትነት እንደማያምን ሰባልዮሳዊ
አንድ ጣታችሁን ብቻ ወደላይ ጠቁማችሁ ታማትባላችሁ? ለምን እንደ እኛ ሦስት ጣቶቻችሁን (እንደሚጎርስ ሰው) በአንድ ገጥማችሁአታማትቡም?" አሉና በቁጣ ጮኹ::
መምህር አካለ ወልድ በፈሊጥ እንጂ በፍልጥ የሚሆን ነገር ስለሌለ ቁጭ ብለን እንነጋገር አሉ::
"እኛ በአንድ ጣት ብናማትብም ሦስትነቱን እናምናለን:: አንድዋ ጣትም እኮ ሦስት አንጉዋዎች አሉአት:: አንድ መሆንዋ አንድነቱን ሦስቱ አንጉዋ ሦስትነቱን ያስረዳል::
የታችኛው አንጉዋ መሠረት ነውና የወልድ የመንፈስ ቅዱስ መሠረት ይሆነው የአብ ምሳሌ ነው:: የመካከለኛው በሁለቱ ህልው የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ነው : የላይኛው ጥፍር የለበሰው ደግሞ ባዕድ ሥጋን የተዋሐደ የወልድ ምሳሌ ነው:: ሀገራችሁ ሔዳችሁ አስተምሩበት" አሉአቸው
(ይህ ትርጓሜ በወንጌል አንድምታ ላይ በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን አወጣለሁ የሚለው በተተረጎመበት ሥፍራ ይገኛል)
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
ንቡረ ዕድ ክፍለ ዮሐንስን ደግሞ አንድ ወጣት መጥቶ
"ለእግዚአብሔር የአምልኮ ለቅዱሳን የጸጋ ስግደት እንደሚሰገድ አውቃለሁ:: ግን በቅዱሳን ሥዕል ፊትና በፈጣሪ ፊት ስሰግድ እንዴት ለይቼ የጸጋ የአምልኮ እያልኩ መስገድ እችላለሁ?" አላቸው
ንቡረ ዕድ መለሱ
"አንተ ዝም ብለህ ስገድ እነርሱ የድርሻቸውን ይወስዳሉ!"
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
አቡነ ሺኖዳ ከሾፌራቸው ጋር ሲሔዱ ሾፌሩ መኪናውን ከመጠን በላይ አበረረው
ፓትርያርኩ እንዲህ አሉ
"ልጄ ስለምንቸኩል ቀስ በል”
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
አንድ ታላቅ የጉባኤ መምህር ተጠየቁ
"ካህናት ዶሮና በግ ወዘተ ማረድ የማይችሉት ለምንድን ነው?"
"የክርስቶስን ሥጋና ደም የሚፈትት ካህን እንደ ኦሪት ካህን የእንስሳ ደም አያፈስስም"
"ካህናቱስ መልካም ሴት ልጅስ ማረድ ለምን ትከለከላለች?"
"ሕይወት የምትሠጥ ሴት ሕይወት አታጠፋም"
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
አለቃ ለማ ልጃቸውን ለምን በጣም እንደሚገርፉት ተጠየቁ
"ልጄን እኔ ካልቀጣሁት እግዚአብሔር ይቀጣብኛል
የእግዚአብሔር ቅጣት ደግሞ ሞት ነው"
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
አንዱ መጥቶ አንድን የመጽሐፍ መምህር
"ጥምቀት ጋድ አለው ወይ?" አላቸው
እርሳቸውም መለሱ
"አምና ነበረው የዘንድሮን እንጃ"
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
አቡነ ዮሐንስ አንድን ሥራ ፈቶ የአብነት ተማሪዎችን
ሲማሩ ከሩቅ የሚያይ ወጣት አዩና
"አንተ አትማርም ወይ?" አሉት
"አይ አባቴ ምን እየበላሁ ልማር ብለው ነው?" አለ እየተቅለሰለሰ
አቡኑ መለሱ
"አሁን ምን እየበላህ ነው የምትደነቁረው?"
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
አቡነ ጎርጎርዮስ በዝዋይ ሳሉ አንድ ወጣት ሰርቆ ሲያመልጥ አባርረው ይዘው ሰዎች አመጡላቸው
ዕቃው ከተመለሰ በኁዋላ ሌባውን ለሕግ አሳልፈው ሊሠጡ ሲቸኩሉ አይሆንም አሉአቸው:: ሰዎቹ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ ወደ ፖሊስ እንውሰደው አሉአቸው
እርሳቸውም መለሱ
"ኦርቶዶክሶች ተሰራርቀው ተካስሰው መጡ ከሚል ስም ውጪ ምንም አናተርፍም"
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
ብፁዕ አቡነ ሰላማን አንዱ ባለ ሥልጣን ጉዳይ ሊያስፈጽሙ በሔዱበት ቢሮው "አንተ" ብሎ በማናገር ሊያቃልላቸው ሞከረ::
እርሳቸው እንዲህ አሉት
"የቤተ ክርስቲያኔን ጉዳይ ፈጽምልኝ እንጂ እንኩዋን አንተ ቀርቶ አንቺም ብለህ ጥራኝ
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
የደርግ መንግሥት እንዳሻው ሊዘውራቸው ተስፋ ያደረገባቸው ፓትርያርክ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በመሪው አማካኝነት እንዲህ ሲል ጠየቃቸው
"የቅድስት ሥላሴ ካቴድራልን ወደ ሙዝየምነት የመቀየር ሃሳብ በመንግሥት በኩል ተይዞአል:: ይህንን ለማድረግም የእርስዎን ድጋፍ የግድ ነው"
ፓትርያርኩ መለሱ
"ምን ችግር አለ በቅርቡ የዓመቱ ሥላሴ ክብረ በዓል ስላለ ሕዝቡ ባለበት እናንተም ተገኝታችሁ አብረን ለምን አናወያየውም"
በዚህ ምላሽ ምክንያት እቅዱ ተሠረዘ

"አስተካክለኝ"
መልካም ነገሮች ከሚባሉት መካከል ተጠቃሽ የሚሆነው አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቆ ሲይዝ እና ሲጠብቅ ነው። እግዚአብሔር ብዙ ቃል ገብቷል እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም
ግልፅና ታማኝ ነው። እናም ቃሉን አያጥፍም። የእርሱን ቃል ይዛችሁ ከእርሱ ጋር ተነጋገሩ። →"ቃል የገባህልንን መች ነው የምትፈፅምልን?" በሉት። →"ቃልህን ይዤ እጠይቅሃለው 'አዲስ ልብን እሰጣችኃለው' ብለሃል። የታለ አዲሱ ልብ? እኔ ራሴን ስመለከተው የድሮ ልቤ እንዳለ ነው። የትናንትናው መጥፎ ጠባይ ልክ እንደ ትናንትናው ነው። የታለ ታዲያ ያ አዲሱ ልብ እሰጥሃለሁ ያልከኝ? እኔ ማወቅ እፈልጋለው ። ከውስጥ እንድትቀይረው እንድትሰማው እፈልጋለው። እኔ አስቸገርኩህ። አንተ አስተካክለኝ፣ ስራብኝ ፥ ደረቅ መሆኔን አስተካክልልኝ።
→ስህተት አለብኝና ስህተቴን አስወግደው።
→ድርቅና አለብኝና ድርቅናዬን አስወግደው ።
→ኃጢያአት አለብኝና ኃጢአቴን አስወግደው።
ጌታ ሆይ እኔ ውስጥ ስራ ። እናም ውስጤን አንጻው። መጋዙን መዶሻውን አንሳው። ሥራብኝ፥ ይህ መጥፎ እንጨት የተባለውን ላንተ ወንበር አርገው ።
''በሕጌ እንድትጓዙ አደርጋችኃለው ቃሌንም ትይዙታላችሁ እናም ትሰሩበታላችሁ ። እኔ ነኝ ይህን እንድታደርጉ የማደርጋችሁ" ብሎናል ። ወንድሞቼና እህቶቼ፥ ቃሉን ቀይሮ መስሏችኃል? አይደለም! እግዚአብሔር ቃሉን አያጥፍም ! ይህ የሚሆነው እኛ ለእግዚአብሔር ልባችንን ስለማንሰጥ ነው ። እንዲሠራበት አንሰጠውም ። ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር አናስረክበውም። ልክ እግዚአብሔር ሊሰራ ሲል ምን እንለዋለን ? "አይ ቆይ ቆይ እራሴን አስተካክዬ ጥሩ ስሆን ወደአንተ እመለሳለሁ" .....ጥሩ ስሆን እመለሳለሁ??? መቼም ጥሩ አትሆንም! ራስህን ጥሩ አድርገህ ወደ እርሱ ከመሄድ ይልቅ ወደ እርሱ ሂድ እርሱ ጥሩ ያደርግሃል ። እኛ ግን በተቃራኒው መንገድ እንሄዳለን። እኛ ምን
እንለዋለን? " እኔ ቤትህ የማልገባበት ምክንያት ጥሩ ሰው ስላልሆንኩ ነው"። አይደለም! ወደ ቤቱ ግባ፥ ከዚያ ጥሩ ሰው ትሆናለህ! "ጌታ ሆይ እኔ መጸለይ አልችልም፥ ምክንያቱም ቆሻሻ
ስለሆንኩ" አይደለም! ጸልይ፥ ከዚያ እርሱ ንጹህ ያደርግሃል። ለምንድን ነው እኛ ብቻችንን መስራት የምንፈልገው?
ከእግዚአብሔር ጋር ሆነህ ተፋለም ፣ ታሸንፋለህ እና ታልፋለህም።
እግዚአብሔርን እንዲ ብለህ ጠይቀው...
→ "ጌታ ሆይ አጋዥ ትባላለህ ፤ አጋዥነትህ የት አለ? ና አግዘኝ።
→አዳኝ ትባላለህ፤ የት አለ ማዳንህ? ና አድነኝ።
→ ምንም ነገር አይሳንህም ትባላለህ... ይቺንም ይዤ እጠይቅሃለው። እኔን ማዳን ከተሳነህ ታዲያ ምንም የማይሳነው የተባልከው ለምንድን ነው ? ጌታ ሆይ፥ እኔ አንድ ችግር ነኝ ። ፊት ለፊትህ ቀርቢያለው መንፈስህን አኑርብኝ። ምንም አይሳንህም እና
እኔን ሥራኝ ። እምነትህ ደካማ ነው ካልከኝ ፥ እሺ ጠንካራ አድርገው ? ልቤ ቆሽሿል እና አፅዳልኝ ። ሙሴ ጸሊምን እና ማርያም መቅደላዊትን እንዳስተካከልካቸው እኔንም አስተካክለኝ። አንተ የምትለው "ወደ እኔ የመጣውን ወደ ውጪ አላስወጣውም " ነው ..ይኸው ወደ አንተ መጥቻለው ባዶ
እጄን አትላከኝ ። ጌታ ሆይ የበጎ ነገር ፈጣሪ ትባላለህ እንዲ ከሆነ በእኔ ውስጥ በጎ ነገርን ስራ ። እየዞርህ በጎ ነገርን ትሰራለህና እንግዲህ በስፍራችን ውስጥ ዙር ፣ ቤታችን ውስጥ ዙር ፣ ክፍሌ ውስጥ ዙር ፣ በነፍሳችን ውስጥ ዙር ፣ በጎ ነገር ሥራብኝ ድሮ እንደምታደርገው አሁንም አድርገው " መኃልየ መኃልየ ዘሰለሞን ምን አለ "ይዤው አልለቀኩትም " እናንተም እንዲ በሉት "ስንት ጊዜ ፀሎት ፀለይኩ ግን አልሰማኸኝም። አሁን ጊዜ ግን አለቅህም ፥ ፀሎቴን ስትሰማ ብቻ ነው የምነሳው።" በሉት። ስለዚህ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ጌታን ከጎናችሁ አድርጉት። ከእግዚአብሔር ጎን ለመሆን ሞክሩ፣ ጸልዩ እርሱ ኃይሉን ይሰጣችኃል ።
[ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ስብከት የተቀነጨበ]