"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ኤልሮኢ:(ምክረ አበው)

የአንድ አባት ምክር

በአንድ ወቅት በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ተገኚቼ ነበር፡፡ በዚያ ገዳም የሚኖሩ አባት የነገሩኝ ነገር ለሕይወት መመርያ የሚሆን ነው፡፡ አሁን ከደረስንበት ወቅት ጋር የሚሄድ ነውና ላካፍላችሁ፡፡

በወቅቱ እንደ ዛሬው በቤተ ክርስቲያን ላይ የፈተና ማዕበል ተነሥቶ ነበር፡፡ ያ ወቅት የፖለቲካው ማዕበልም እጅግ ያየለበት ጊዜ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምንሰጠው አገልግሎት ምን ፋይዳ ይኖረዋል? ምንስ ለውጥ ያመጣል? ችግሩ እንደሆነ እየባሰው እንጂ እየተሻለው አልሄደም፤ ታድያ ጊዜያችንን፣ ገንዘባችንን እና ዕውቀታችንን ዝም ብለን እየከሰከስን ይሆን? አሁን የኛ ልፋት የክፉ ሰዎችን ክፋት ለመሸፈን እና በክፋታቸው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ካልሆነ በቀር ችግሩን ይፈታዋል? ወዘተ፣ ወዘተ፣ ጥያቄዎች ይነሡ ነበር::

ያን ጊዜ እኒህ አባት እንዲህ አሉን፡፡

«ብዙ ልጆችን የወለደች የምትወድደው ባሏ የሞተባት አንዲት እናት ነበረች፡፡ ቤተ ዘመዶቿ ምንም ሳይራሩ ያለ ፍላጎቷ ለአንድ ክፉ ባል አጋቧት፡፡ ይህ ባል ግዴለሽ፣ ገንዘብ ወዳድ፣ ጠጥቶ ከመስከር፣ በልቶ ከመጥገብ፣ በስተቀር ሌላ ሞያ የለውም፡፡ ሲወጣ ሲገባ ይደበድባታል፡፡ እንጨት ሽጣ፣ ኩበት ለቅማ፣ እንጀራ ጋግራ፣ ጠላ ጠምቃ ያጠራቀመቻትን ገንዘብ ነጥቆ ይወስድባታል፡፡ ለዘመዶቹም ይበትነዋል፡፡

የት ትሂድ? የሠፈሩ ሕግ፣ ባህሉ እና ልማዱ፣ በሙሉ የእርሷን ሮሮ እና ልመና የሚሰማ አልሆነም፡፡ እርሱን እንደ ሕጋዊ ባልዋ ነው የሚቆጥሩት፡፡ የት ሂዳ መከራዋን ትናገር፡፡ የትስ ሂዳ ከችግሩ ትገላገል?

ይህ ክፉ ባልዋ እርሷን ብቻ ሳይሆን ልጆቿንም ያሰቃያቸው ነበር፡፡ እነርሱም በዚያ ቤት ውስጥ መከራውን እና ስቃዩን፣ ረሃቡን እና ጭቅጭቁን እየሰሙ መኖር መረራቸው፡፡ በዚያ ቤት ሰላም ጠፋ፡፡ ፍቅር ጠፋ፡፡ ምንጊዜም የሚሰማው ክፉ ነገር እና ልብ የሚያደማ ነገር ሆነ፡፡ ሰው ሁሉ ስለዚያ ቤት ያወራል፡፡ መንገድ ላይ ሲያገኛቸው ስለ ቤታቸው ይጠይቃቸዋል፡፡ እነርሱም በሃፍረት ይሸማቀቃሉ፡፡ ስለዚህም እናታቸውን ጥለው ወደ ሌላ ቦታ መሄድና ስለዚያ ቤት ከማያስቡበት እና ከማይሰሙበት ቦታ መድረስ ፈለጉ፡፡ የሚችሉትን ያህል እየሠሩ፣ ለራሳቸው የሚበቃቸውን እየኖሩ፣ መከራውን መገላገል እና እፎይ ብለው መኖር አሰኛቸው፡፡

ታድያ ይህንን ሃሳባቸውን ለአንድ ሽማግሌ ጠቢብ ሰው ነግረው ገንዘብ እና ሃሳብ እንዲሰጣቸው ፈለጉ፡፡ ሄደውም አማከሩት፡፡ ያም ሽማግሌ ሃሳባቸውን ሁሉ ከሰማ በኋላ እንዲህ አላቸው፡፡

«ልጆቼ ልክ ናችሁ ሩቅ ሀገር ሄዳችሁ፣ የምትችሉትን ያህል እየሠራችሁ፣ የራሳችሁን ኑሮ በመኖር ችግሩን ሁሉ መርሳት እና መገላገል ትችላላችሁ፡፡ ምን ያስጨንቃችኋል? ቤት ያለው እዚህ ብቻ ነው እንዴ? ሀገርስ ያለው እዚህ ብቻ ነው እንዴ? ግን አንድ ነገር አስቡ፡፡ እንዲህ ማድረጋችሁ ራሳችሁን ብቻ ከችግሩ ታወጣላችሁ እንጂ ችግሩን አትፈቱትም፤ እናንተ ችግሩን ትረሳላችሁ እንጂ ችግሩን አታስወግዱትም፡፡

«ደግሞም የእንጀራ አባታችሁ እናታችሁን የበደለውን ያህል እናንተም ትበድሏታላችሁ፡፡ እስኪ አስቡት ለዚህች ለእናታችሁ ከእናንተ በቀር የደስታዋ ምንጭ ማን ነው? ሁሉም ነገርዋ የሚያሳዝን እና የሚያስመርር ነው፡፡ እናንተ ግን የደስታዋ ምንጮች ናችሁ፡፡ የእንጀራ አባታችሁ እናታችሁን ያሳዝናታል፤ የእናንተ ጥላችኋት መሄድም ያሳዝናታል፤ እርሱ ብቻዋን እንድትለፋ ትቷታል፤ እናንተ ጥላችኋት ስትሄዱም ያለ አጋዥ ትተዋታላችሁ፤ እርሱ በመስረቅ ዘረፋት፣ እናንተም ባለ መስጠት ዘረፋችኋት፤ ታድያ ከእርሱ በምን ተሻላችሁ?

እናንተኮ ያሰባችሁት ለእናታችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ነው፡፡ እናታችሁ ስለተቸገረች አይደለም ያዘናችሁት፣ ችግሩ እናንተን ስለነካ ነው፤ እናታችሁ ስለተራበች አይደለም ያዘናችሁት ረሃቡ ስለነካችሁ ነው፡፡ በእናታችሁ ላይ የደረሰው ችግሳይሆን ስለችግሩ ከየሰው አፍ መስማት ነው የሰለቻችሁ፤ ችግሩን ለመቅረፍ አይደለም መሄድ የፈለጋችሁት፤ ችግሩን ላለማየት እና ላለመስማት ነው፡፡

ከዚያ ይልቅ ሥራ ሠርታችሁ ገንዘብ አግኙ እና ለእናታችሁ ምግብ ስጧት፤ የሚያስርባትን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፣ ልብሷን ቀይሩላት፣ የሚያሳርዛትን አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፣ ስትታመም አሳክሟት፣ የሚያሳምማትን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፤ የወግ እቃዎቹን ሰብስቡና አስቀምጡላት፤ዝክረ ታሪኳን ሊያጠፋ የተነሣውን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፤ እርሱ እያረጀ ሲሄድ እናንተ ግን እያደጋችሁ ነው፡፡ ስለዚህም እየበዛችሁ እና እየመላችሁ ሂዱና ይህንን ቀፍድዶ የያዛትን የመንደሩን ሕግ አስተካክሉት፡፡ ምናልባት የእንጀራ አባታችሁ ቢሞት ሌላ የእንጀራ አባት ደግሞ እንዳይተካ፡፡ እንደዚያ ካደረጋችሁ እናንተ የእናታችሁ ልጆች ናችሁ፡፡ ያለ በለዚያ ግን የእንጀራ አባታችሁ ተባባሪዎች ናችሁ፡፡

ሸረሪት ታውቃላችሁ፡፡ ከሰው ቤት ግድግዳ ላይ ድር አድርታ፤ ወልዳ ከብዳ ትኖራለች፡፡ ቤቱ በእሳት ሲያያዝ ግን ከቤቱ ወጥታ ቀድማ የምትሮጥ እርሷ ናት፡፡ ቤቱ የኖርኩበት ነው፡፡ ወግ መዓርግ ያየሁበት ነው፤ እሳቱን በማጥፋት አስተዋጽዖ ማድረግ አለብኝ አትልም፡፡ መሸሽን ብቻ ነው የምትፈልገው፡፡ ለራስዋ ብቻ ነው የምታስበው፡፡ ይህ ከሸረሪትነቷ የመጣ ነው፡፡

እናንተ ግን ሰዎች እንጂ ሸረሪቶች አይደላችሁም፡፡ ሰዎችን እያያችሁ ከሀገራችሁ እና ከቤተ ክርስቲያናችሁ ልትርቁ አትችሉም፡፡ አያገባንም ልትሉ አትችሉም፡፡ እሳቱን ማጥፋት ትታችሁ ከእሳት ለማምለጥ ብቻ ልትሮጡ አትችሉም፡፡ ይህንን ካደረጋችሁ ሸረሪቶች እንጂ ሰዎች አይደላችሁም፡፡» አሏቸው

ይህንን ሰምተው ልጆቹ ወደ እናታቸው ተመለሱ፡፡

እስኪ እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ የዚህች ሀገር እና የዚህች ቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ፍላጎት ምንድን ነው? ይህች ሀገር እና ይህች ቤተ ክርስቲያን ያለ ረዳት እንዲቀሩ ማድረግ አይደለምን?  እናንተም እንተዋት፣ እናቁም፣ እንሽሽ ስትሉ ያለ ረዳት እያስቀራችኋት ነው፡፡ የእነርሱ ፍላጎት ኢትዮጵያን እና ተዋሕዶን ተስፋ ማስቆረጥ አይደለምን? እናንተም ተስፋ ከቆረጣችሁ ተሳካላቸው ማለት ነው፡፡ ልጆቻቸውን እያስመረሩ ማስኮብለል አይደለምን? ከኮበለላችሁ ተሳካላቸው ማለት ነው፡፡ ታሪክን፣ ቅርስን፣ ክብርን፣ ልዕልናን መመዝበር እና ማራከስ አይደለምን? እናንተም ታሪኩን፣ ቅርሱን፣ ባህሉን፣ ክብሩን ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ በራሳችሁ ዓለም ብቻ ስትቀሩ የእናንት ፍላጎት ሳይሆን የእነርሱ ፍላጎት ተሳካ ማለት ነው፡፡

ታድያ አሁን እናንተ መመለስ ያለባችሁ አንድ ጥያቄ ነው፡፡ የምትፈልጉት የጠላቶቿ ፍላጎት እንዲሳካ ነው ወይስ በመከራ ውስጥ ያለችውና ቀን የጣላት የእናታችሁ ፍላጎት እንዲሳካ ? ምረጡ፡፡

ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ኤልሮኢ:(ግጥም)
ፅዩን ማርያም

ፅዮን ማርያም አማላጅዋ
ግሩም ድንቅ ነው ከለላዋ
ተነግሮ አያልቅ ጥበቃዋ።
ስሟን ስጠራ ተጨንቄ
ፅዮን ማርያም ስላት አጥብቄ
ሰለምናት ለመንገዴ እንድትሆነኝ ስንቄ ፣
ተናግሬ ሳልጨርስ
ከተፍ አለች እኔኑ ልታድስ።
ልትመራኝ ደግፋ ልትሆነኝ ተስፋ
ልትታደገኝ በይፋ።
ምኞትህ መልካም ነው ልጄ፣
አትጥፋ እንግዲ ከደጄ
ብፅዕት ነሽ በለኝ አሁንም ወዳጄ
አስታርቅሃለሁ አማልጄ፤
እያለች ስታፅናናኝ
ፅዮን ማርያም እመቤቴ
መታወቂያ የእኔነቴ
መንገድ መሪዬ መስታወቴ
የኑሮዬ ትርጉም የልማቴ
የድካም ሁሉ ብርታቴ
ምቹ ማረፊያ የስደቴ።
ርቄ ብሄድ ባህር ማዶ
መቼ ሆነ ቤቴ ማዶ
እንባዬ ታብሶልኝ
ፀሎቴ ተሰምቶልኝ
መውደዴ ተቆጥሮልኝ
ፅዮን ማርያም አብራኝ መጣች
ጣፋጭ ቃሏን እያሰማች
ብፅዕት ነሽ በለኝ እያለች።


እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!!!

@aleroe
ኤልሮኢ:(ትርክት)
ፆም እንዴት ነው?

ከእለታት አንድ ቀን አንድ ወጣት ወደ ነፍስ አባቱ ይሄድና ሰላም ካላቸው በኃላ
ልጄ መንፈሳዊ ሂይወት እንዴት ነው?
ወጣቱም መልሶ በጣም ጥሩ ነው አባ።
ደስ ብሏቸው ጎሽ ልጄ በርታ እና ፆሙስ እንዴት ይዞሃል?
ወጣቱም አይ አባቴ ፆም እንኳን እየፆምኩ አይደለም።
ለምን ልጄ ምን ነካህ?
ወጣቱም አይ አባቴ ፆም ከገባ በኋላ ፍርጅ ውስጥ የነበረ ስጋ ወጥ ረሰቸው በላሁት ከዛም ያው አንዴ ሽርያለሁ ብየ አልፆምም።
የነፍስ አባቱም በጣም አዘኑና እህህህ ልጄ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?
ወጣቱም እሺ ይጠይቁኝ
እሳት አየሞክ እያለህ ሳታስበው በድንገት እግርህን ወደ እሳቱ ቢገባና እግርህ ቢቃጠል አንዴ ተቃጥያለው ብለህ ሳታወጣው ዝም ትላለህ ወይስ ታወጣዋለህ?
ወጣቱም በድንጋጤ እንዴ አባቴ ለምን ዝም እላለው ቶሎ ብዬ አውጥቼ በፍጥነት ወደ ህክምና ሄጄ እታከመዋለው።
ጥሩ ብለሃል ልጄ ፆምም አንዴ በልቻለው እያልክ መብላትህ ተገቢ አይደለም። ሃጥያትም ነው ልጄ ልክ ከእሳቱ እግርህን ቶሎ ብለህ አውጥተህ ወደ ህክምና እንደ ሄድክ ነፍስም ከቁስሏ ቶሎ ብለህ ከስህተት ተመልሰህ በፆም በጸሎት ማከም ይገባሃል ልጄ።በስህተት የሻርከውን ንስሐ ይሰጥህና የቀረውን መፆም ነው የሚገባህ ልጄ በስህተት ላይ ስህተት እየጨመርክ መንፈሳዊ ህይወትህ ማጥፋት የለብህም በማለት ቀኖና ሰጥተው ፆሙን እንዲፆም ነግረው አሰናበቱት።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
መልዕክት፦አብዛኞቻችን አንዴ ፆሙን ሽርያለው በሃጢአት ወድቅያለው ገና ወጣት ነኝ ነገ እሳሳታለው እያልን ብዙ ምክንያት እየደረደረን መንፈሳዊ ሂይወታችንን ረስተን በዝሙት በመጠጥ በጭፈራ በተለያዩ ወጥመድ ተይን ወጥተን የጠፋን ስንቶቻችን ነን ቤት ይቁጠረን። ቶሎ ብለን ዲያብሎስን ካልነቃንበት ህይወታችንን በማበላሸት ያጠፋናል።አንዴ ተሳስቻለው ብለን ሁሌም መሳሳት የለብንም በንስሃ ተመልሰን መልካሙን መንፈሳዊ ህይወታችንን እናጠናክር እንዲ እያሉ የሚገስጹ ደግ አባቶቻችንን ያብዛልን።
በንስሐ እንመለስ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

፨ከተስፋ ሚካኤል ሃይለ ማርያም

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)

​ህዳር 27/03/2013 ዓ.ም


ምስባክ

መዝ 2/3፥1
ለምንት አንገለጉ አሕዛብ ወሕዝብኒ ነበቡ ከንቶ ወተንሥኡ ነገሥተ ምድር

ወንጌል
የሉቃስ ወንጌል 10÷1

ቅዳሴ
ግሩም አው ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ

@aleroe
ኤልሮኢ:(ትምህርት)
ይህን ያውቁ ኖሯል?

ለሰባኪያን መቆሚያ ከፍ ያለ ቦታና አትሮንስ በቤተክርስቲያን መጠቀም የተጀመረው ከ386 ዓ.ም አከባቢ ባለው ዩሐንስ አፈወርቅ ነው። ቅዱስ ዩሐንስ አፍወርቅ ቀሚያስተምርበት ጊዜ ሕዝቡ በብዛት ይሰበሰብ ነበር። ነገር ግን የዩሐንስ ቁመት አጭር ነቀረና ከፍ ብሎ ለሕዝብ እንዲታይና ድምፁም እንዲሰማ መቆሚያ ስፍራና ያጽሐፍት ማንበቢያ አትሮንስ ተሰራች። ቤተክርስቲያንም ከዚያ ዘመን ጀምሮ አትሮንስን ትጠቀምበት ጀመር።

ኑዛዜ በቤተክርስቲያን የተጀመረው ሕጋዊና ድንግል ከሆነው የእስክንድርያ 12እኛ ፓትራያርክ ከአባታችን ከቅዱስ ድሜጥሮስ ወዲህ ነው።አባታችን በከንቱ አምተውት የነበሩ ምእመናን በእግዚአብሔር ፋቃድ ክብሩ ቀተገለጠላቸው ጊዜ አባታችን ይቅርበለን ብለው ንስሐ ሲገቡ ይፍትሕ ይኅድግ ብለው ናዝዘዋል። ኑዛዜም ያን ጊዜ ተጀምሯል።

አንገት ላይ ማተብ ማሰር የተጀመረው ቀን5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሶርያ ያስተምር በነበረው በአባታችን በያዕቆብ ዘእልበረዲ ነው። አባታችን እያስተማረ በሚያጠምቅበት ጊዜ ለተጠመቁትና ያልተጠመቁት እየተቀላቀሉ ቢያስቸግሩት ለማየት ይቻል ዘንድ ለተጠመቁት ምዕመናን ማተብ ያስርላቸው ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ማተብ ለተጠመቁ ክርስቲያኖች መለያ ምልክት ሆነ።

@aleroe
ኤልሮኢ:(ግጥም)

ንግስና እንዴት ነበር?

ንግስና እንዲህ ነበር ተኝቶ በራዕይ
እዛሬ ላይ ሁኖ የነገው ንግስና በህልም የሚታይ
በወንድም ተሽጦ በባርነት ኑሮ
ባላደረገው ላይ ፍርድ ሸንጎ ውሎ
የታየው ራዕይ እውን እንደሚሆን ልቡ ስላመነ
መጣል መገፋቱን አምኖ ይሁን አለ
መመረጥስ እንዲህ መሾምስ እንዲህ ነው
ዮሴፍ የነገሰው ምድረ ግብፅ ላይ ነው

ሙሴ እንዴት ነገሰ?
ሙሴ የተሾመው ከማህጸን ነበር
ፈርኦን ነግሶ ህዝቦችን ሲያሸብር
እስራኤልን ገዝቶ በባርነት ቀንበር

እናም
እናም በዛ ጊዜ
ወልዶ መቅበር እንጅ ማቀፍ እኮ የለም
የራሔል እንባ ግን መሬት ፈሶ አልቀረም
እግዜሩም ጠራና ሙሴን እንዲህ አለ
ህዝቦቸን እንዲለቅ መልዕክት ንገር አለ
ቅንና የዋሁ ሙሴም እንዲህ አለ
እንዴት ነጻ ላውጣ ህዝብህን አድኜ
እኔ አፌ ኮልታፋ በምን አንደበቴ ንጉሥ አሳምኜ
ለእስራኤላውያን የነጻነት ቀን ሲመጣ
ሙሴም በእምነት ህዝቡን ይዞ ወጣ
ከጠራው አምላክ ጋር እየተማከረ
ህዝቡን ለማሻገር ባህርን ከፈለ
በምድረ በዳ ላይ መናን ተቀብሎ ዘመን ተሻገረ

ዳዊት እንዴት መጣ?
ከበረት ተወልዶ እረኛ የሆነው የላይኛው ጌታ
ከእረኝነት ጓዳ ዳዊትን መረጠው ጎልያድ እንዲረታ
ሳኦል የነገሰው ህዝቡ ጠይቆ ነው
የሳኦል ንግሰቱ መንገድ መጥረጊያ ነው
የዳዊት ንግስና ከአምላክ ንግስና ጋር ምሳሌው አንድ ነው
እረኛ ነበረ ዳዊት ሳይጠራ
የነገሰ ጊዜ እንደ ልቤ ተብሎ በአምላኩ ተጠራ

የአሁኑስ እንዴት ነው?
ንጉሱ ባሉበት ግብር ይበላሉ?
መሪና ተመሪ ይተዋወቃሉ?
ንግስናው ከየት ነው?
ምንጩስ ከወዴት ነው?
ንጉስ የሆነውስ ለየቱ ወገን ነው?
ለዛኛው ወገንስ ንጉሥ የትኛው ነው?

መሪማ ሙሴ ነው
ህዝቤ ከሚጠፋ እኔ ልጥፋ ያለው
ልጥፋ ያለው ደግሞ ከሕይወት መዝገብ ነው

የአሁኑ ንጉስስ

ምን ብሎልን ይሆን ምንስ ሲል ተሰማ
ምንም አይበልልን ምንም ሲል አንስማ

ይልቅ ይልቅ

አምላካችን ታርቆን ታሪክ በታደሰ
ሙሴያችን በመጣ ዳዊት በነገሰ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

@aleroe
ኤልሮኢ:(የአበው ታሪክ)

#ቅዱስ_ጐርጐርዮስ_ዘአርማንያ

ይህ ቅዱስ አባት ከሰማዕታት: ከጻድቃን: ከሊቃውንትና ከዻዻሳት ዝርዝር ውስጥ ይገኛል:: በቤተ ክርስቲያንም ዓበይት ከሚባሉ አበው አንዱ ነው:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሮማዊ ሲሆን ከክርስቲያን ወላጆቹ የተወለደው በዘመነ ሰማዕታት (በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነው::
አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ የታላቁዋ ሰማዕት #ቅድስት_አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው:: በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት:-
1.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት
2.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት
3.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት:: ቅዱሱ 3ቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ:: ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት:: መከራው በጣም ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ ድረስ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር::
ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው:: በሁዋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኩዋ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ:: በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው:: የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ:: በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ:: በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር:: መከራው ግን አለቀቃቸውም:: ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው:: ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት:: ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው:: አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት::
ወዲያው ደግሞ የቅዱስ ጐርጐርዮስ ማንነቱ በመታወቁ ይዘው አካሉ እስኪያልቅ ገረፉት:: በእሳትም አቃጠሉት:: በብዙ ስቃይም አሰቃዩት::
በመጨረሻ ግን ከነ ሕይወቱ እንዲቀበር ተወሰነበት:: ወደ መጸዳጃ ቤት ወስደውም ከነ ሕይወቱ ቀበሩት:: ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ መተንፈሻ ቀዳዳን ሠራለት:: አንዲት ሽማግሌ ክርስቲያንም በዚያች ቀዳዳ ቂጣ እየጣለችለት ለ15 ዓመታት ተቀብሮ ኖረ:: አካሉና አፈሩ ተጣበቀ:: እርሱ ግን ፈጣሪውን እያመሰገነ ቆየ:: ከነገር ሁሉ በሁዋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው:: የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ:: የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም በዚያች ሽማግሌ መሪነት ቆፍረው አወጡት:: አካሉንም እግዚአብሔር መለሰለት:: ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም:: ለ15 ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው:: ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው:: ወደ ሰውነትም መልሶ መላ አርማንያን ወደ ክርስትና መለሰ:: የንጉሡን እግር ግን የአውሬ አድርጐት ቀርቷል:: በመጨረሻም ቅዱስ ጐርጐርዮስ የአርማንያ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሹሞ ብዙ መጻሕፍትን ደረሰ:: ከ318ቱ ሊቃውንትም አንዱ ሆኖ ተቆጠረ:: ዕረፍቱ ታሕሳስ 15 ቀን ነው።

@aleroe
ኤልሮኢ:(ስነ ፅሁፍ)

አሻግሪኝ

ውሻን አጠጥተሽ በወርቅ ጫማ ውሃ፡
ጠማሽ ሆይ እናቴ ሲና ዱር በረሃ፡
ምስለ ፍቅሩ ወልዳ የብፁኃን ተስፋ፡
ወደ ግብፅ ወረደች ስደት ልጃን ታቅፋ፡
የመለኮት ድንኳን የእሳት መጋረጃ፡
እንዴት ይለብልባት የሐሩር ምድጃ፡
የሰሎሜ ትእግስት የዮሴፍ ትህትና፡
ነይ ነይ ማርያም ባንቺ መንገዴ ይቅና፡
ከምድር ባይገኝ የውበትሽ ደም፡
እንደ ፀኃይ በራሽ ቤዛይት አለም፡
ብሎ ቢከተልሽ ሙት ስጋው ለአዳም፡
ከሰው ፊት ኮብልለሽ ገባሽ ወይ ቁስቋም፡
በእንባሽ ነይ እጠቢኝ እናቴ ማርያም፡
የፅጌ ውዳሴ ምስማከ ነሽ ፅዮን፡
ስምሽን ስጠራው ብዬ እመብርኅን፡
ከጨለማ ኣውጥተሽ አሻግሪኝ በቀን።

@aleroe
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

የሰንበት ት/ቤት

እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ በአርያውና በአምሳሉ ከፈጠረ በኋላ ሰው ከፈጣሪው ጋር በጥብቅ እንዲናገናኝ ልዩ ልዩ የአገልግሎት መንገዶችን አዘጋጀ። እያንዳንዱ በተሰጠው መክሊት ያተርፍና በጸጋው ያገለግል ዘንድ በመጀመርያ ዕድሜው በፈቀደለት ሁሉ መማርና ማገልገል ይኖርበታል። እግዚአብሔር አምላክ መመለክ በአለበት አግባብ ለማምለክ እምነት ያስፈልጋል፤ ከእምነት እንዳንወጣ ደግሞ ስለምናምነው ነገር በቂ ዕውቀት ሊኖረን ይገባል፤ እምነትን፣ ተስፋና ፍቅርን ሰንቆ እስከመጨረሻ ድረስ ለመጽናት መንፈሳዊ ዕውቀት መሠረታዊ ነው።

“ህዝቤ ዕውቀት በማጣት ጠፍቷል” (ሆሴ 4፥6) የተባለው በእኛ ላይ እንዳይፈጸም ዕድሜያችን በሚፈቅድልን ሁሉ ሃይማኖታዊ ዕውቀትን እንድንማር ቤተ ክርስቲያን በቅዱሳን ጸሎት በእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሰንበት ት/ቤትን አቋቋመች። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ልጆቿ ጽድቅን ይማሩ ዘንድ በሰንበት ት/ቤት አሰባስባ ቃለ እግዚአብሔርን አውቀው፣ ባሕርየ እግዚአብሔርን ተረድተው እንዲያመልኩ፣ ሕጉን ጠብቀው፣ በሃይማኖት፣ በምግባርና በትሩፋት ፀንተው አምላካቸውን መስለው እንዲኖሩ የእርሱ የሆነችውን መንግስተ እግዚአብሔርን እንዲወርሱ በብሉይ ከአምላኳ የተቀበለችውን ሕግጋተ እግዚአብሔርን አስተምራ በሐዲስ ኪዳንም በ40 እና በ80 ቀን እያጠመቀች ለምዕመናን እንደ እድሜያቸው እና እንደ አዕምዕሮ ብስለታቸው ቃለ እግዚአብሔርን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ታስተላልፋለች። በስብከት፣ በዝማሬ፣ በቅዳሴ፣ በስዓታት፣ በማሕሌት የቅኔውን ምሥጢር በትርጓሜ እያስተማረች ምዕመናንን በእምነት አንፃ ለመንግስተ ሰማያት እያዘጋጀች ዛሬ ላይ ደርሳለች።

ከስሙ እንደምንረዳው ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት የጾታ ልዩነት ሳይደረግ የቤተ ክርስቲያን ተተኪ ትውልድ ወይም መንፈሳዊ ወጣቶች በዕለተ ሰንበት፣ በዓበይት በዓላትና አመቺ በሆነ ጊዜ ሁሉ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እየተገኙ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ቅኖና፣ሥርዓትና ትውፊት የሚማሩበት እና በእምነት፣በምግባርና በሃይማኖት ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን የሚያጠነክሩበት ትምህርት ቤት ነው:: መንፈሳዊ ወጣቶች የሚባሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓትና ትውፊት በዕድሜ ክልላቸው የሚማሩ የቤተ ክርስቲያን አባላት ናቸው (ቃለ ዓዋዲ ፲፱፻፺፩)።

በመጽሐፍ ቅዱስ ሰንበት ት/ቤት ተብሎ የተፃፈ ቀጥተኛ የሆነ ስም ባይገኝም ዛሬ ላይ በሰንበት ት/ቤት የሚተገበረው መንፈሳዊ አገልግሎት ማለትም ልጆችን በቤተ እግዚአብሔር ማስተማር በብሉይ ኪዳን ዘመንም ይፈጸም እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳናል። የሰንበት ት/ቤት ፅንሰ ሀሳብም ከዚያ የመነጨ ነው። “እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሠሯቸው በዐይኖቻችሁም መካከል እንደ ክታብ ይሁን ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው በቤትህም ስትቀመጥ በመንገድም ስትሄድ ስትተኛም ስትነሣም አጫውቱአቸው” (ዘዳ 11÷18-21 )በማለት እስራኤላውያን ልጆቻቸውን ሕግጋተ እግዚአብሔር እንዲያስተምሯቸው ታዘዋል፡፡ እነርሱም ይህን አምላካዊ ቃል ተግባራዊ ለማድረግ ልጆቻቸውን ወደ ቤተ እግዚአብሔር እየላኩ እና በቤታቸው ውስጥም ተግተው ያስተምሩ ነበር።

በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌ ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ቁም ነገሮች መካከል ሕፃናት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይመጡ ዘንድ ነበር። ልበ ንጹሐንን በሕጻናት መስሎ ያስተማረበት አንቀጽም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተጽፎ ይገኛል። ይህም በዘመናችን ላለችው ቤተ ክርስቲያን የሕፃናት፣ የወጣቶች እና የጎልማሶች ማስተማሪያ ለሆነችው ሰንበት ትምህርት ቤት መነሻ የሆነ እና መሠረቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን ያረጋግጥልናል (ማቴ 18፥3፣ 21፥16፣ ማር 9፥37)፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤት አመሠራረት በኢትዮጵያ ስንመለከት ዘመናዊ ትምህርት ቤት እየተስፋፋ ሲመጣ ወጣቱ ትውልድ ከአምልኮተ እግዚአብሔር እንዳይለይ፤ በተለይ ለዘመናዊ ትምህርት አስተማሪነት በመጡ እራሳቸውን ”ኢየሱሳውያን” ብለው በሚጠሩ የውጭ መምህራን ከመጡበት ዓለማዊ ትምህርት ባሻገር የኑፋቄ ትምህርት ማሰራጨታቸው፣ በተቃራኒው ደግሞ ወደ አብነት ትምህርት ቤት የሚሄደው ወጣት ቁጥር በመቀነሱ ምክንያት በ20ኛው ክፍለ ዘመን ወጣቱን ለመያዝ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮችና የማኅበራት እንቅስቃሴዎች ተጀመሩ። እነዚህ የተጀመሩ መርሐ ግብሮችና ማኅበራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዎቿ ሳይበረዙ ለትውልድ እንዲተላለፉ በተለይ በሕጻናት እና በወጣቶች ላይ ትኩረት ሰጥው እንዲሠሩ ትልቁን ድርሻ ወስደዋል።

በዚህም መሠረት ሰንበት ትምህርት ቤት በማቋቋም ትውልድን በኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖት የማነጽ፣ ዶግማን፣ ቀኖናን እና ትውፊትን ማስተማር ተጀመረ። በ1960 ዓ.ም ይህን የሰንበት ትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴ ለማስተባበር እና ለማጠናከር ይቻል ዘንድ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በስብከተ ወንጌልና ማስታወቂያ መምሪያ ሥር ማእከላዊ ጽ/ቤት በዋናነት ተቋቁሞ ስያሜውም የሰንበት ት/ቤት መምህራን ጽሕፈት ቤት ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ይህ አካሄድ እያደገ ሲመጣ በ1965 ዓ.ም ራሱን ችሎ ወደ ወጣቶች ጉዳይ መምሪያነት እንዲያድግ ተደርጓል፡፡ ዛሬ ላይ የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምርያ የሚል ሰንበት ትምህርት ቤቶችን የሚያደራጅና የሚመራ በተቋም ደረጃ ትልቅ መምርያ ተቋቁሞ አገልግሎቱን እየፈጸመ ይገኛል።

የሰንበት ት/ቤት ጥቅሙና አስፈላጊነቱ የጎላ መሆኑ በተግባር በመረጋገጡ በ1970 ዓ.ም “ሰንበት ት/ቤት” በሚል ስያሜ ሕጋዊ ሆኖ እንዲቀጥል እና በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሰንበት ት/ቤቶች እንዲቋቋሙ የተቋቋሙትም እንዲጠናከሩ ተሻሽሎ በወጣው ቃለ ዓዋዲ እንዲጸድቅ ተደርጓል፡፡ የሰ/ት/ቤት አገልግሎትን የበለጠ ለማጠናከር ሰንበት ት/ቤቶች የሚመሩበትን መተዳደሪያ ደንብ አጽድቆ ሥራ ላይ እንዲውል ያደረገ ሲሆን አሁን አስካለንበት ዘመን ድረስ ሰንበት ት/ቤቶች ይህን መመሪያ ከዋናው ቃለ ዐዋዲ ጋር በማስተባበር እየተመሩበትና ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡

ይህን ወጣቱን ትውልድ በዘመናዊነት ተፅዕኖ ውስጥ ወድቆ ከመንፈሳዊ ሕይወት እንዳይወጣ ልዩ ክትትል በማድረጉ ረገድ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን እኅት አብያተ ክርስቲያናትም ሰንበት ትምህርት ቤትን አቋቁመው አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ብዙ ዓመታትን አስቆጥረዋል። በተለይ ግብፅና ሕንድ በተደራጀ መልኩ እየሠሩበት ይገኛሉ።

የሰንበት ትምህርት ቤት የተቋቋመበት ዋና ዓላማ

የሰንበት ትምህርት ቤት ዓላማ፦

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቅኖና፣ እምነትና ሥርዓት ተጠብቆ ሳይበረዝ ሳይከለስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ

ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ የሆነ ምእመን የሃይማኖቱን ሥርዓት በውል እንዲያውቅና እንዲረዳ ማድረግ

ወጣቶች የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት ተምረው ለሀገርና ለወገን ጠቃሚ፣ መልካምና በሥነ ምግባር የታነፁ ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ

በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ (መክ. ፲፪፡፩) የሚለውን የአምላክ ተእዛዝ ወጣቶች እንዲፈጽሙ ማስቻል

እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን አበይት ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ ጠንካራ ሰንበት ትምህርት ቤት ያስፈልጋል። ወጣቶችን በሰንበት ትምህርት ቤት ለማሳደግ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የበ
ኩላቸውን መወጣት በእጅጉ አስፈላጊ ነው። አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጴጥሮስ ከሰጠው መመርያና ትዕዛዝ መካከል ሕፃናትንና ወጣቶችን በሃይማኖት እያስተማረ ለመንግስተ ሰማያት ማብቃት እንደነበር ቅዱስ ዮሐንስ በመጽሐፍ ቅዱስ ጽፎልናል (ዮሐ 21፥15)። የአምላካችንን ትዕዛዝም ትውልድ ሁሉ ይፈጽመው ዘንድ ሕፃናትን እና ወጣቶችን አስተባብሮ ማስተማር የሚችል ሰንበት ትምህርት ቤት ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም።

ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቱን ትውልድ በአምልኮተ እግዚአብሔርን አፅንቶ በሃይማኖትና በምግባር ከማኖርም ባሻገር ለቤተ ክርስቲያን ቀናኢ የሆኑ አገልጋዮችን አፍርቷል፤ በማፍራት ላይም ይገኛል። ሰንበት ትምህርት ቤት በዕለተ ሰንበትና አበይት በዓላት ወቅት ያሬዳዊ መዝሙራትን ከማቅረብም በላይ ዲያቆናትን፣ ቀሳውስትን፣ ቆሞሳትን፣ ጳጳሳትን፣ መምህራነ ወንጌልን፣ ሰባኪያንን እና በልዩ ልዩ አገልግሎት ላይ የሚፋጠኑ ዘመኑን የዋጁ አገልጋዮችን ለቤተ ክርስቲያናችን አበርክቷል። ይህ አገልግሎት እንዳይቋረጥና ቤተ ክርስቲያን ለትውልድ ሁሉ ከነሙሉ ክብሯ ትተላለፍ ዘንድ በያለንበት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ትምህርት ቤትን ማጠናከር የዘወትር ተግባር ሊሆን ይገባል። በተለይ በዚህ በውጭው ዓለም ልጆቻችንን የምዕራቡ ባህልና እምነትየለሽ ዘመናዊነት እንዳያጠቃቸው በሰንበት ትምህርት ቤት አስመዝግበን ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ እንዲያውቋት ማድረግና በሃይማኖትና በምግባር ተኮትኩተው እንዲያድጉ ማስቻል የወላጅ ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆን አለበት። ምክንያቱም ልጆቻችን ኦርቶዶክሳዊት እምነትን፣ ዶግማን፣ ሥርዓት እና ትውፊትን በሰንበት ት/ቤት ካልተማሩ ሃይማኖታችንን ጠብቀውና አስጠብቀው ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ አይቻላቸውም፡፡

በአጠቃላይ ሰንበት ትምህርት ቤት ትውልድን ለመቅረጽ የሚሰጠው ጠቀሜታ ታላቅ ስለሆነ ወጣቶችና ሕፃናት በሰንበት ትምህርት ቤት የሚሰጠውን መደበኛ ትምህርት መከታተል እንዲችሉ ማድረግና በማነኛውም ጊዜና ቦታ አርያና ምሳሌ ሁነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነትና ሥርዓት አፅንተው ይይዙ ዘንድ ከሁልጊዜውም በተለየ መልኩ የሁላችንም ድጋፍ እንደሚያስፈልግ መረዳትና በመተግበርም እግዚአብሔር አምላክ የሰጠንን ሃይማኖታዊ ተልእኮ መፈጸም ይጠበቅብናል።

@aleroe
እንኳን ወደ ተወዳጁ ወደ ማህሌት ቲዩብ በሰላም መጡ በቻናላችን ከሚያገኟቸው ነገሮቹ መካከል

🔖 የልደት መዝሙሮች
🔖 የጥምቀት መዝሙሮች
🔖 የንስሐ መዝሙሮች
🔖 ገድላት
🔖 ትረካና መነባንብ
🔖 መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ


እነዚህንና ሌሎች መንፈሳዊ ቪዲዮች
የሚያገኙበትን ማህሌት ቲዩብን subscribeበማድረግ አገልሎቱን ይደግፋ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን
🔔Subscribe ማህሌት ቲዩብ🔔
🔔Subscribe ማህሌት ቲዩብ🔔
🔔Subscribe ማህሌት ቲዩብ🔔

የአቡነ ሺኖዳ ትምህርት በጥያቄና መልስ የሚቀርብበት የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ።
📖መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች
📖መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች
📖መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎች


ከትላልቅ መንፈሳዊ መፅሀፍት የተወጣጡ
ጥያቄዎች የሚጠየቁበት እንዲሁም
ተሳትፎ የሚደረግበት መንፈሳዊ ቻናል
ለመቀላቀል ከፈለጉ።👇
||Open Open Open||
||Open Open Open||
teddy (5)
<unknown>
ኤልሮኢ:
የራሴን ፀጉር

የራሴን ፀጉር ቁጥሩን ያውቀዋል
የእጁ ስራ ነኝ መች ይረሳኛል
የልቤ መሻት ዛሬ ባይሞላም
እግዚአብሔር አለ አልጨነቅም (2)


ስለ ምግብና ስለምለብሰው
ብዙ ብጨነቅ ጥቅሙ ምንድን ነው
አበባን ለምድር ምግብን ለወፎች
የሚሰጥ አባት አለኝ ሳይሰለች

አዝ

የማያምኑትን ስሙን ሳያውቁ
የሚያገኙትን ሳይጨነቁ
ስለምን ልድከም በከንቱ መሻት
እያለ ጌታ ያዳነኝ ከሞት

አዝ

የክፉዎች ሰልፉ ቢሰፍር በላዬ
ዝናሩን ታጥቆ ቢዝት ገዳዬ
በሞት ጥላ ዉስጥ ብጓዝ ብሄድም
የሚጠብቀኝ አያንቀላፋም

አዝ

ሀሳቤን ልጣል በእረኛዬ
በሚያሰማራኝ ቸር ጠባቂዬ
ከበረከት ምንጭ አያሳጣኝም
በግ ስለ እራሱ ተጨንቆ አያቅም

አዝ

መንግስቱን ልሻ ልፈልግ ፅድቁን
ስለሚሰጠኝ ጌታ ሌላውን
ስለሚጨነቅ ነገ ለራሱ
ላመስግን ዛሬ ታምኜ በርሱ

@aleroe
ኤልሮኢ:

++ አባቶቻችን እንዲህ አሉ ++

"መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም"
ቅዱስ ባስልዮስ

"በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው" ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ

"ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ

"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው"
ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ

"እግዚአብሔር ለአብርሃም "ከሀገርህ ውጣ ከወገኖችህ"ተለይ ብሎት ነበር። በዚህ ጥሪ እግዚአብሔር ሁላችንንም የተወለድንበት ዘር እንድንተው ይጠራናል። ሰማዕቱ ዮስጦስ (100 AD-165 AD)

"ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ (160 AD - 220 AD)

‹‹ይጸልያል ነገር ግን የሌሎችን ጸሎትም ይሰማል፡፡ ያለቅሳል የሌሎችን ዕንባ ግን ያብሳል፡፡ ሰው ነውና አልዓዛር ወዴት እንደተቀበረ ጠየቀ፡፡ አምላክ ነውና አልዓዛርን ከሞት አስነሣ፡፡ እርሱ በርካሽ ዋጋ ያውም በሠላሳ ብር ብቻ ተሸጠ፡፡ ነገር ግን ዓለምን በውድ ዋጋ በከበረ ደሙ ገዛ፡፡ እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ እርሱ ግን የእስራኤል እረኛ የዓለምም ሁሉ ጠባቂ ነበረ፡፡ እንደ በግ ዝም አለ ነገር ግን እርሱ በምድረ በዳ በሚጮኽ ሰው ድምፅ የተሰበከ ቃል ነበር፡፡ እርሱ የተሰቃየና የቆሰለ ነበር ፤ ሁሉንም በሽታና ቁስል ግን ይፈውስ ነበር›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ

"ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታድርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጽል አይደለም፡፡
የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 26 2011
ጅማ ፣ ኢትዮጵያ

@aleroe
ኤልሮኢ:

ሥራህን ሥራ
(በአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ)

ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል ያንን መስራት የእሱ ፈንታ ነዉ። ቢቻለዉ እሱን ማገድ የዲያብሎስ ሥራ ነዉ። በእርግጥ ሥራዉን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይሞክራል። ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል። በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል የሐሜት ጎርፍ ያስወርድብሃል። ደራሲያን ኦንዲጠይቁህ እጅግ ስመ ጥሩ ሰዎችም በክፋ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል። ጲላጦስ፥ሄሮድስ፥ሀናንያ፥ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ . . . አንተ ግን በፀና ውሳኔ በማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላደርገው የሰጠኽኝን ስራ ፈፀምኩ ሃይማኖቴንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትንም ግብ ተከተል።

አባ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፩፱፫፪፡፩፱፰፪ ዓ.ም.

@aleroe
ኤልሮኢ:(ስነፅሁፍ)
በዜሮ ይባዛል!

ፆም×0=0 ስግደት×0=0
ጸሎት ×0=0


ተግቼ ብጸልይ እጆቼን ዘርግቼ
ቤቴ ባዶ ቢቀር ያለኝን መጽውቼ
ቀኑን ሙሉ ብጾም እስኪቆረጥ አንጀቴ
ዘወትር ብሰግድ እስኪዝል ጉልበቴ
በቀድስ ባስቀድስ በመቅደሱ ግርማ
ብዘምር ባወድስ የሚጣፍጥ ዜማ
ወንጌልን ብሰብክ ምስጢር አመስጥሬ
ብናገር ባስተምር ትርጉሙን ዘርዝሬ
ጥልና ክርክር ካሉ በህይወቴ
ሐሜት ክርክር ካልጠፉ ከቤቴ
በዜሮ ይባዛል ፍቅር በማጣቴ።

ስብሐት ለእግዚአብሔር!

ፆም×ፍቅር= 30 ያማር ፍሬ
ጸሎት×ፍቅር= 60ያማር ፍሬ
ስግደት× ትህትና= 100ያማረ ፍሬ

@aleroe