"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ኤልሮኢ:(ትርክት)

እኩል ነው

አንድ መነኮስ አንድን ትልቅ አባት እንዲህ ሲል ጠየቀው፡- “የምተገብረውና የምኖርበት ምን መልካም ምግባር አለ ?” ሽማግሌውም እንዲህ አለ፡- “መልካም የሆነውን እግዚአብሔር ያውቃል ። ነገር ግን ከአባቶች አንዱ የአባ እንጦንስ ወዳጅ የሆነውን ታላቁን አባት እንዲህ ብሎ እንደ ጠየቀው ሰምቻለሁ፡- ‘እተገብረው ዘንድ ምን መልካም ሥራ አለ ?’ እሱም እንዲህ ሲል መለሰለት፡- ‘ሁሉም ተግባሮች እኩል አይደሉምን ? መጽሐፍም አብርሃም እንግዶችን ይቀበል እንደ ነበረና እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር እንደ ነበረ ፣ ኤልያስም ውስጣዊ ጸጥታንና ሰላምን ይወድ እንደ እንደ ነበረና እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር እንደ ነበረ ፣ ዳዊትም ትሑት እንደ ነበረና እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር እንደ ነበረ ይነገረናል ። ስለዚህ ነፍስህ ለእግዚአብሔር ብላ ማድረግ የምትወደውን ነገር አድርገው ፤ ልብህንም ንቁ አድርግ ።”

የኃጢአት ደረጃ እንደሌለው ሁሉ የመልካም ነገርም ደረጃ የለውም ። ሁሉም ሥራ እንደሆነ ሁሉ የሥራ ደረጃ የለውም ። አናጢነትም ፣ ግንበኛነትም ሁለቱም ሥራ ነው ። አንዱ ከአንዱ አይለይም ። ሁሉም ጸጋ እኩል ነው ። ክብር የሚገኘው በጸጋው ዓይነት ሳይሆን ጸጋውን ለይቶ በትጋት በማገልገል ነው ። የአካል ክፍሎችም ሁሉም እኩል ናቸው ። አንዱ ያለ አንዱ መኖር አይችልም ። እጅ የሌለው እግር መዶሻ ልያዝ ብሎ ሲጨነቅ እናያለን ። ከሁለቱ ዓይንም አንደኛውም በጣም አስፈላጊ አይደለም ፤ ሁለቱም አስፈላጊዎች ናቸው ። ከአሥር ጣቶች አንዱን ይወገድልኝ የሚል የለም ። አሥር ወልዶም አንዱን የሚጥል የለም ። መልካም ነገርም ሁሉም አስፈላጊ እስከ ሆነ ድረስ ሁሉም እኩል ነው ።

እንደ እነ እገሌ መሥራት ስላልቻልን ፣ እንደ እነ እገሌ ማገልገል ስላልቻልን እግዚአብሔርን ያላመለክን ይመስለን ይሆናል ። እንደ ተሰጠን በምግባርና በትሩፋት መገለጥ ይገባናል ። አንዳንድ ሰው ሸክሙ የአእምሮ ታማሚዎችን እየሰበሰበ ገላቸውን ማጠብ ነው ። አንዳንዱም ምኑንም ሳያዩት መቸገራቸው አሳዝኖት ሕፃናት ላይ የሚሠራ ነው ። ሌላውም ሠርተው የተጣሉ የአረጋውያን ነገር ግድ ብሎት እነርሱ ላይ ይሠራል ። አንዳንድ ሰው ቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሥፍራ ስለሆነች ንጹሕ መሆን አለባት ብሎ መጥረጊያ ይዞ ያጸዳል ። ሌላውም የእንግዶችን እግር በማጠብ እባረካለሁ ብሎ በትጋት ያከናውናል ። ሁሉም በእግዚአብሔር የታዘዙ ስለሆኑ የተከበሩና የሚያስፈልጉ ናቸው ። በአሥራ ዘጠኝ ሰባዎቹ ጥር ሥላሴ ዕለት ሕዝብ እያያቸው በአሰቦት ደብረ ወገግ ገዳም ወደ ሰማይ ያረጉ አባት እንደ ነበሩ እናስታውሳለን ። አባ በላይ የሚባሉት እኒህ ሰው በጊዜው የጋዜጣ ዜና ሁነው ነበር ። ተግባራቸው ግን ንጹሕ ዘማ ሳይሉ እግር ማጠብ ነበር ። ለእግዚአብሔር ክብር የማይውል ምንም ነገር የለም ።

ነቢዩ ሙሴ ሚሊየኖችን ነጻ አውጥቶ እየመራ ቀይ ባሕርን ተሻግሯል ፤ እኛ ደግሞ አንድን ሰው ከረሀብ ነጻ ለማውጣት እየሠራን ይሆናል ። ቅዱስ ጴጥሮስ በአንድ ቀን ስብከት ሦስት ሺህ ሰው አሳምኗል ፤ እኛ ደግሞ አንድን ሰው እያገለገልን ይሆናል ። ቅዱስ ጳውሎስ አሥራ አራት መልእክታትን ጽፏል ፤ እኛ ደግሞ የተጻፈውን እያሰራጨን ይሆናል ። ሐዋርያት እስከ ዓለም ጽንፍ ወንጌልን ሰብከዋል ፣ እኛ ደግሞ በዘመናዊ መገናኛዎች ወንጌልን እያዳረስን ይሆናል ። በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ የምናገኘው ባለንበት ስፍራ በትጋት በመንቀሳቀሳችን እንጂ በውጤቱ አይደለም ።

በምን ተግባር እግዚአብሔርን ደስ እንደምናሰኘው የምንጨነቅበት ጊዜ ብዙ ነው ። የአራት ኪሎ መንገድ የጠፋውን ሰው በቅንነት መንገድ ማሳየት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ። ቢሮአችን ውስጥ የሚመጣውን በፈገግታና በፍቅር መቀበል እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ። የአጥራችን መብራት እንዲበራ በማድረግ ሰዎችን ከእንቅፋትና ከሌባ መታደግ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ። ማንም የለኝም የሚለውን ሰው ደውለን እንዴት ነህ ? ማለት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ። ልጆቻቸውን በሞት ያጡ ወላጆችና መበለቶችን መጎብኘት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ። ተስፋ ያዘለ ቃል ለሰዎች መናገርና “አንቺ እህቴ መድረሻሽ ትልቅ ነው” “አንተ ወንድሜ መልካም ነገር አለህና በርታ” ማለት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ። ሰዎችን ስማቸውን እየጠሩ በጸሎት ማሰብ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ።

ጻድቁ አብርሃም እስከ ዛሬ የምናስታውሰው እንግዳ በመቀበሉ ነው ። በመጨረሻም ሥላሴን እቤቱ አስተናግዷል ። በዚህም ሲዘከር ይኖራል ። እንግዳ መቀበል ትንሽ ነገር ይመስላል ፤ ነገር ግን በትልቅ እምነት ካደረግነው አንድ ቀን እግዚአብሔርን እቤታችን ልንቀበለው እንችላለን ። ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ይላል ።1ቆሮ. 10፡31 ። መብልና መጠጥ ለራሳችን የምናደርገው ነገር ነው ። ለራሳችን በምናደርገው ነገርም እግዚአብሔርን ማክበር ይቻላል ። “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ማለት ምን ማለት ነው ? እግዚአብሔር የሚፈልገው ራስ መውደድ አለ ማለት ነው ። መብልና መጠጥ ትንሽ ቢሆንም ለእግዚአብሔር ክብር ሊውል ይችላል ።

ነቢዩ ኤልያስ ጸጥታንና ሰላምን የሚፈልግ ነበር ። በዚህም እግዚአብሔርን ደስ አሰኝቷል ። እንግዳ መቀበል ጸጥታ የለውም ። አብርሃም በእንግዳ መቀበል ፣ ኤልያስ ደግሞ በጸጥታ እግዚአብሐሔርን አክብረዋል ። ጸጥታችንና ጽሞናችን ቃሉን ለማሰላሰል ፣ ለጸሎት እንጂ ሰዎችን ለመግፋት መሆን የለበትም ።

ንጉሥ ዳዊትም ትሑት ነበረ ፣ በዚህም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ ። ንጉሥ ቢሰጥ ሳይሆን ትሑት ቢሆን ይገርማል ። መስጠቱ ዝና ነው ፣ ትሑት መሆኑ ግን መዋረድ ነው ። ትሕትና ወዳጅን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን የሚስብ ገመድ ነው ። እንደ ተሰጠንና እንደምንችለው መልካም ነገርን በንቁ ልብ እንፈጽም ፤ ያን ጊዜ የዚህ ዓለም ክፍተት እየሞላ ይመጣል ።

ለእግዚአብሔር ብለን በምናደርገው መልካም ነገር እግዚአብሔርን ደስ እናሰኘዋለን ። የቱን መልካም ነገር ልሥራ ብለን መጨነቅ የለብንም የከበበን መልካም ሥራ ነው ። ትንሽ የሚመስለውን ስንሠራው ትልቅ ውጤት ያመጣል ።


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(ትርክት)

ለመላቀቅ መልቀቅ!

የስድስት አመት ልጅ ነው፡፡ የሚኖረው ከአባትና ከእናቱ ጋር እንዲሁም ከሁለት ታላላቅ ወንድሞቹ ጋር ነው፡፡ ይህ ልጅ
ከወንድሞቹ ይልቅ ፈጣንና አንዳንዴም ከመስመር ወጣ ያለ ቅልጥፍና ያለው ልጅ ነው፡፡ አንድን ነገር ካየና ከወደደው ያንን ነገር በእጁ የሚያስገባበትን መንገድ በዚህም ሆነ በዚያ ፈልጎ ነገሩን በእጁ ያስገባል፡፡ አንድን ነገር እጁ ለማስገባት ማልቀስ ካለበት ማልቀስን፣ መጣላት ካለበት መጣላትን፣ መስረቅ ካለበት መስረቅን ከመጠቀም የሚመልሰው የለም፡፡ መኝታ ቤቱ ያለው የመጫወቻ ብዛት ይህ ነው አይባልም፡፡ ከየት ለቃቅሞ እንዳመጣው የማይታወቅ ብዙ ነገር ነው ያለው፡፡ አባቱ ይህንን
ባህሪውን ያውቃል፣ ሆኖም በተለያየ መልኩ ሊያስተምረው ከመሞከር ውጪ ምንም ሊያደርገው አልቻለም፡፡
አንድ ቀን ይህ ልጅ የማይረሳውን ትምህርት አገኘ፡፡ ከትምህርት
ቤት ተመልሶ ትንሽ ምግብ ከቀማመሰ በኋላ በረንዳው ላይ ይጫወታል፡፡ የጎረቤታቸውን በረንዳና የእነርሱን በረንዳ
የሚለየው አንድ ከብረት የተሰራ በሰው ቁመት ልክ የሆነ አጥር
ነው፡፡ ይህ ልጅ ቀና ብሎ ሲያይ የጎረቤታቸው ልጅ ሲጫወትባት
የነበረች ትንሽ ሳንቲም የምታክል መጫወቻ ያያል፡፡ በተለያዩ
ቀለማት ስለምታብረቀርቅ ልቡን ሳበችው፡፡ ዘወር ብሎ ዙሪያውን ሲመለከት ማንም ሰው የለም፡፡ ቀና ብሎ ወደ ጎረቤቱ ግቢ ሲያጤን ያ በጣም የሚፈራው ውሻም በአካባቢው የለም፡፡ በቀስታ እጁን በብረት አጥሩ መካከል አሾልኮ ያችን ያጓጓችውን መጫወቻ በእጁ ከጨበጠ በኋላ በቀስታ አጁን ውጣ ቢለው እንዴት ይውጣ! ሁለት ሶስቴ ከሞከረ በኋላ እምቢ ስላለው መደንገጥ ጀመረ፡፡ ከአሁን ከአሁን ውሻው ይመጣብኛል ብሎ ፈራ፡፡ ብዙ ከታገለ በኋላ አልቦታል፤ ከፍርሃትም የተነሳ እንደ ማልቀስ ቃጥቶታል፡፡
በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ነበር አባት የደረሰው፡፡ ዘወር ብሎ አባቱ
መምጣቱን እንዳየ መለስ ሲል ያ ክፉ የጎረቤትም ውሻ ብቅ
አለ፡፡ ልጁ በፍርሃት ማልቀስ ጀመረ፡፡ አባት፣ “ምን ሆነህ ነው?”
ልጅ፣ “እጄ አልወጣ ብሎኝ”፡፡ አባት፣ “እጅህ በሁለቱ የብረት
አጥሮች መካከል እንዴት ገባና ነው አልወጣ ያለህ?” ልጅ፣
“መዳፌን ዘርግቼ ነው ያስገባሁት፡፡” አባት፣ “ታዲያ ለምን
መዳፍህን ዘርግተህ ልክ እንዳስገባኸው አታስወጣውም?”፡፡
ልጅ፣ “መዳፌን ከዘረጋሁት የያዝኩት ነገር ስለሚያመልጠኝ
መልቀቅ አልፈልግም፡፡”
አባት፣ “ካለህበት ሁኔታ መላቀቅ ከፈለግህ የያዝከውን ነገር
መልቀቅ የግድ ነው፡፡ አለዚያ እንደተያዝክ በዚያው መቅረትህ
ነው” ብሎት ጥሎት ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር የውሻው ድምጽ
የተሰማው፡፡ ውሻው እየዘለለ ሲመጣ ያየው ይህ ልጅ ምንም
ምርጫ ስለሌለው የጨበጠውን ነገር በመልቀቅ ከተያዘበት ነገር
ተላቀቀ፡፡ የተያዝክበትና የተጨነክበት ነገር እንዲለቅህ ምናልባት መልቀቅ
ያለብህ ነገር ይኖር ይሆን? በሕይወትህ አልሄድና አልተው ያለህ ችግርህ ምናልባት አንተው መልቀቅና መተው ከሚገባህ ነገር ጋር ይገናኝ ይሆን?
ብዙዎቻችን ጨብጠን ያለቀቅናቸው ብዙ ባዕድ ልማዶች አሉን! እነሱን ሳንተው ከፈጣሪ ዘንድ ልንደርስ አይቻለንም። እናም ክርስቲያኖች መልቀቅ ያለብንን ለቀን መያዝ ያለብን ላይ እናተኩር።


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
teddy (2)
<unknown>
ኤልሮኢ:(ዝማሬ)

አትቁረጡ ተስፋ

አትቁረጡ ተስፋ የእግዚአብሄር ልጆቹ(2)
ከእናንተ አይለዩም የፍቅር ዓይኖቹ(2)
ምድርና መላዋ ናትና የእግዚአብሄር
በሰማያት አለ በቀላይ በባህር

በጥልቁ እንኳን ቢሆን ከእናንተ ጋራ ነው
ወገኖቼ አትስጉ ሰልፉ የእግዚአብሄር ነው
ጌታ አይረሳምና የእጆቹን ስራ
ይኸው በልጆቹ አይተናል ሲሰራ

አትቁረጡ ተስፋ የእግዚአብሄር ልጆቹ(2)
ከእናንተ አይለዩም የፍቅር ዓይኖቹ(2)
ምድርና መላዋ ናትና የእግዚአብሄር
በሰማያት አለ በቀላይ በባህር


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
"ከንስሐ አባትህ ጋር ስትሆን ጥያቄህን እንጂ ውሳኔህን አታቅርብላቸው፤ በልብህ ካሰብከው ጋር እንዲስማሙ ሳይሆን በሀሳብህ ላይ ሀሳባቸውንና ምክራቸውን እንዲሰጡህ አድርግ።"

#ብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሣዊ

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)

ጥቅምት 22/02/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፻፳፩፥፯(121፥7)
ይኵን ሰላም በኃይልከ
ወትፍሥሕት ውስተ ማኅፈደ ክበዲከ
በእንተ አኀውየ ወቢጽየ


ምስባክ ዘቅዳሴ

አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዓ ቃሎሙ
ውስተ ኲሉ መድር ወፅአ ነገሮሙ።
ወእስከ አጽናፈ አለም በጽሐ ነቢቦሙ።


ቅዳሴ

ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ)


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(ትርክት)

…………በአንዲት ትንሽዬ ከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ አይነስውር ሰውዬ ነበር።
ይህ አይነስውር ሰውዬ መሬት ሲጨላልም ወደ ከተማው መውጫ ያለው ወንዝ አከባቢ እየሄደ ንፁህ አየር መውሰድ ያዘወትር ነበር። ታድያ በዛ በጨለማ ሲሄድና ሲመለስ በእ የመብራት ፋኖስ ይዞ ነው። ሁልጊዜ እንዲህ ያደርጋል። ከእለታት በአንዷ ምሽት 3 ወጣቶች እርስ በርስ እየተቀላለዱ
ሲያልፉ አይነስውሩ ሰውዬ ከነፋኑሱ ያገኙታል። "አንተ አይነስውር ነህ፤ እንደሚያይ ሰው ፋኖስ ይዘህ ትዞራለህ
እንዴ" ብለው ተሳለቁበት፣ ሳቁበት።
ሰውዬውም በእርጋታ እንዲህ አላቸው፡-
"ልክ ናቹ፤ እኔስ አላይም ነገር ግን ፋኑሱ ይጠቅመኛል፤ ምክንያቱም ሰዎች በጨለማው ምክንያት ሳያዩኝ ከገፈተሩኝ
በህዋላ ከምናደድባቸው ፋኑሱ ይዤ ባበራላቸው ለሁለታችን ይጠቅማል" ብሏቸው ሄደ። ወጣቶቹም በሰውዬው ቅን
አስተሳሰብ ተደነቁ። "ማየት ያለብን በህሊናችን ነው፤ ለሰዎች የምናደርገው በጎ ነገር ራሱ ተመልሶ በእጥፍ ይከፍለናልና።"

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(ትርክት)

እናት ሰንበት ትምህርት ቤት

………አንዳንድ ጊዜ ‹ትምህርት ቤት› የሚለው ሐረግ ሰንበት ትምህርት ቤትን
አይገልጻት ይሆን ብዬ አስባለሁ፡፡ ‹ሰንበት ትምህርት ቤት› ከምትባል ይልቅ
‹የሰንበት ቤተሰብ ቤት› ብትባል ይሻል ይኾን?
የቤተሰባዊነት ስሜት ለአገልጋዮች እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ሐዋርያት እርስ
በእርሳቸው ‹ወንድሞች› ይባባሉ ነበር፡፡ ወንድሞች መባባላቸው ከአንድ እናትና
አባት ተወልደው አይደለም፤ እንዲሁ አገልግሎት የጋራ እናታቸው ሆናቸው ነው
እንጂ፡፡ የሳቱትን እንኳን ‹ቢፅ ሐሳውያን (ሐሰተኛ ወንድሞች)› ይሉ ነበር፡፡
ይህንን ቤተሰባዊነት ለማጉላት እኔ ባደግኩባት ሰንበት ትምህርት ቤት የቤተሰብ
ጉባኤ የሚባል ጉባኤ አለ፡፡ በዚያ ቀን የሚከወነው እንደ ቤተሰብ ቤተሰባዊና
መንፈሳዊ ወጎችን እንዲሁ ሲጨዋወቱ መዋል ነው፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤቱ
ሰብሳቢ ‹ሰብሳቢ› ሳይሆን ‹አባት› ይባላል፡፡ ኹሉም ‹አባታችን› እያለ
ይጠራዋል፡፡ የቀድሞ ሰብሳቢ ‹አያታችን› ይባላል፡፡ ከእርሱ የቀደመው ‹ቅድመ
አያታችን› ይባላል፡፡ የአመራር አባላት ወንዶቹ ‹አጎቶች› ሴቶቹ ‹አክስቶች›
ይባላሉ፡፡ ሌላው አባል በሙሉ ‹ልጅ› ነው፡፡
ይህ ስሜት ኹሉም ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ አለ፡፡
ሰንበት ተማሪ ዘመደ ብዙ ነው፡፡ አያድርስበትና አንድ ችግር በእርሱ ወይም
በቤተሰቡ ላይ ቢደርስበት የእናት ሰንበት ትምህርት ቤቱ ወንድሞቹና እኅቶቹ
ነቅለው ቤቱ ይሔዳሉ፡፡ ታምሞ ከሆነ ቤቱን ሞልተው ፣ ውዳሴ ማርያምን
አድርሰው ዘምረው ያበረቱታል፡፡ ኃዘን ገጥሞት ከኾነ እስኪጽናና ከቤቱ
አይለዩም፡፡ ዕድርተኛው ‹ጉድ› እስኪል ድረስ ድንኳን የሚተክሉት ፣ ወንበር
የሚደረድሩት ፣ ግቢ የሚያጸዱት ፣ ዕቃ የሚያጥቡት የሰንበት ትምህርት ቤት
እኅትና ወንድሞቹ ናቸው፡፡
ባለቤቱ እንዲደረግ የፈለገውንና የሚያስፈልገውን በማድረግ ልቡን በእርካታ
ይሞሉታል፤ እንደ ልቡ ይሆኑለታል፡፡ የዮናታን ጋሻጃግሬ ለዮናታን እንዳለው
‹‹እንዳንተ ልብ ሁሉ የኔም ልብ እንዲሁ ነው›› ብለው የልባቸውን መሻት
ከወዳጃቸው ልብ መሻት ጋር አንድ ያደርጉታል፡፡ (1ሳሙ.14፡7)፡፡ እርሱ ሲያዝን
የእርሱ አፍ ሳይኾን የራሳቸው ልብ ይነግራቸዋል፤ ‹እንደርሱ ልብ ሁሉ የእነርሱም
ልብ እንዲሁ ነውና›፡፡
ሰርግ ካለበትም የሥጋ ቤተሰቡ አብዝቶ መጨነቅ የለበትም፡፡ በጎደለው ኹሉ
የመንፈስ ቤተሰቦቹ አሉለት፡፡ ምናልባትም ልጅየው ብዙ ጊዜውን ለሰንበት
ትምህርት ቤት በመስጠቱ የሚበሳጭ ቤተሰብ ቢኖረው እንኳን ከእንደዚህ
ዓይነት ገጠመኝ በኋላ ኹሉም ነገር ይለወጣል፡፡ የወንድሞቹና የእኅቶቹ
መተሳሰብ፣ የሚቃወም ልቡናን ኹሉ በፍቅር ሊያነድ የተቀጣጠለ ስንዱ እሳት
ነው - ‹‹ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል›› እንዲል፡፡ (1ጴጥ. 4፡8)፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤት ወንድሞች እውነተኛ ወንድሞች ናቸው - በፍቅር
የተገመደ ትሥሥር ያላቸው፡፡ ወንድማቸው ሲበርደው እነርሱ የሚንቀጠቀጡ ፣
ሲርበው አንጀታቸው የሚላወስ ፣ ሲከፋው አብረው የሚያለቅሱ ውድ ወንድሞች
ናቸው፡፡ ለእኅታቸው ድጋፍን ከመስጠት የማይሰንፉ ፣ ታናሻቸውን በትምህርት
የሚረዱ ፣ ለጥያቄዎቹ የማይሰለቹ ልበ ወርቆች ናቸው፡፡ አብረው መብላት ፣
መጎራረስ ፣ አብረው ማደግ ፣ አብረው መሳቅ ፣ አብረው መጫወት ፣ አብረው
መሔድ ፣ አብረው ማንበብ ፣ አብረው መኖር የሚያጓጓቸው የኁባሬ ስልቻዎች
ናቸው፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤት ወንድሞች በሰንበት ትምህርት ቤት እንጂ
በየትም በሌላ ቦታ አይገኙም፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤት ወንድሞች እንደ ዮናታን ናቸው፡፡ ዳዊት ጎልያድን ገድሎ
በዮናታን አባት በንጉሡ በሳኦል እልፍኝ ከተገኘና የራሱን ማንነት ለንጉሡ ካስረዳ
በኋላ ‹‹የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሠረች፥ ዮናታንም እንደ ነፍሱ
ወደደው›› (1ሳሙ.18፡1)፡፡ ዮናታን ዳዊትን እንደ ነፍሱ ስለ ወደደው አባቱ ሳኦል
በጠላትነት ሲነሣበት እንኳን እንደ ነፍሱ የወደደውን ዳዊትን ከአባቱ በምክሩ
ይደብቀው ነበር፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤት እውነተኛ ወንድሞችም እንዲሁ
ናቸው፡፡ ዳዊት የተባሉ አዳዲስ አባላት ጎልያድ የተባለ ከአገልግሎት መራቅን
ድል ነሥተው ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት ሲመጡ ነፍሳቸው በዳዊቶቹ ነፍሶች
ትታሰራለች፣ እንደ ነፍሳቸውም ይወዷቸዋል፡፡ ምንም ዓይነት ‹ሳኦል› ቢመጣ
ከዳዊቶች ጎን ይቆማሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት ወንድሞች በሰንበት ትምህርት ቤት
ወይም የሰንበት ትምህርት ቤት ልብ ባላቸው ዘንድ እንጂ በየትም በሌላ ቦታ
አይገኙም፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤት እኅቶች ትሕትና የቀበራቸው ፣ ሃይማኖት ያስጌጣቸው ፣
ቅንነት ያቆነጃቸው ፣ የፍቅር ኩራዞች ናቸው - ፀሐዩአ ለጠፋባት የሴትነት ዓለም
ክራቸው እየተቃጠለ ብርሃንን የሚለግሱ ፣ እየጨሱ መቅረዝ የኾኑ፡፡
ወንድሞቻቸውን የሚያከብሩ ፣ ለሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን የሚታመኑ ፣ ካህናትን
ሲያዩ ልባቸው በሚገባ ፍርሐትና አክብሮት የሚርድ የሀገር ኩራቶች ናቸው፡፡
ወንድሞቻቸውን አጥብቀው የሚሹ የቤተሰቡ የወርቅ ምሰሶዎች እነርሱ ናቸው፡፡
በብዙ ትግልና ልፋት ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት ይመጣሉ፤ ሰማይ የሚያክል
ጫናን አገር የሚያክል ጾታዊ ተፅዕኖን ተቋቁመው ያገለግላሉ፡፡ የሰንበት
ትምህርት ቤት እኅቶች በሰንበት ትምህርት ቤት እንጂ በየትም በሌላ ቦታ
አይገኙም፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤት እኅቶች እንደ አቢጊያ ናቸው፡፡ የናባል ሚስት አቢጊያ
ባሏ ንጉሡን እስከ መዳፈር የደፈረ እጅግ አስቸጋሪ ሰው ነበር፡፡ ንጉሥ ዳዊትም
እርሱን ሊገድለው ሲሔድ ብልኋ አቢግያ በመንገድ ጠብቃ ንጉሡ ይቅርታ
ያደርግለት ዘንድ በብዙ ትሕትናና እጅ መንሻ ለመነችው፡፡ ዳዊትም አቢግያን
አደነቀ፤ ‹‹ወደ ደም እንዳልሄድ፥ በእጄም በቀል እንዳላደርግ ዛሬ የከለከለኝ
አእምሮሽ የተመሰገነ ይሁን፥ አንቺም የተመሰገንሽ ሁኚ›› አላት፡፡ (1ሳሙ.25፡
33)፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤት እውነተኛ እኅቶችም እንደ አቢጊያ ናቸው፡፡ ሰውን
ከክፋት በመመለስ ፣ በእርጋት ፣ በትሕትና ፣ በአስተዋይነት አዕምሮአቸው
የተመሰገነ፡፡ ሰውን ጎትተው ወደ ስሕተት የሚከቱ አሰናካይ ሴቶች በበዙበት
በዚህ ዘመን ብልጭልጭን ንቀው የሚስተውን የሚመልሱ የተመሰገኑ ናቸው፡፡
ስለ ወንድሞቻቸውና ስለ እኅቶቻቸው አብዝተው የሚጨነቁና የሚጸልዩ ፣ ጸብን
ለማራቅ ዘወትር በብልኃት የሚመክሩ ፣ ‹ልታይ› ከሚሉት ጀርባ የሚገኙ ባለ
ምስጉን አዕምሮዎች ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነት እኅቶች በሰንበት ትምህርት ቤት
ወይም የሰንበት ትምህርት ቤት ልብ ባላቸው ዘንድ እንጂ በየትም በሌላ ቦታ
አይገኙም፡፡
እኔ በግሌ ልጅ እያለሁ እነዚህ እኅቶችና ወንድሞች ዕቅፍ አድርገው ተቀብለውኝ
ወንድማቸው ባያደርጉኝ ኖሮ አሁን ያለው ማንነቴ አይኖርም ነበር፡፡ ለመጀመሪያ
ጊዜ ሰንበት ትምህርት ቤት ስገባ በፍቅር ሸማ ፣ በመውደድ ብሉኮ ያከናነቡኝን ፣
በጉጉት የተቀበሉኝን ውድ የኆኅተ ብርሃን ቤተሰቦቼን የልጅነት አዕምሮዬ
አይዘነጋቸውም፡፡ እነዚህን ወንድሞችና እኅቶች በሰንበት ትምህርት ቤት እንጂ
በሌላ በየትም ቦታ እስካሁንም አላገኘኋቸውም፡፡
ሰንበት ተማሪ ሌላ ሰንበት ተማሪን በመንገድ ሲያገኝ ወይም በአጋጣሚ
ሲተዋወቅ የጠፋ የእናቱን ልጅ እንዳገኘ ልቡ በፍቅር ስስት ይቃጠላል፡፡ ኹለት
የማይተዋወቁ ሰንበት ተማሪዎች ቢገናኙ ለመግባባት ጊዜ አይወስድባቸውም፤
ልቡናቸው ቀድሞ ይግባባል፡፡ ስማቸውን እንኳን ሳይተዋወቁ ስለ መስቀል ጥናት
፣ ስለ ጥምቀት ፣ስለ ደብረ ታቦር ፣ ስለ ፍልሰታ ፣ ወዘተ… ያወራሉ፡፡ አባባሉስ
ቢሆን ‹‹አንድ ዓይነት ላባ ያላቸው
ወፎች……

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ዝክረ ጥንተ ስቅለት አደረሳችሁ አደረሰን

...." እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።" ዮሐ ፮፡፵፯.....

....."አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ፥ ከጣርም ትጠብቀኛለህ፤ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ።" መዝ ፴፩:፯.....

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)

ጥቅምት 29/02/2013 ዓ.ም

ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፻፱፥፫(109፥3)
ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለተ ኃይል
በብርሃኖሙ ለቅዱሳን
ወለድኩከ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ

ምስባክ ዘቅዳሴ

ወታቀንተኒ ኃይል በጸብዕ
ወአእቀጽኮሙ ለኩሎሙ እለ ቆሙ ላዕሌየ በመትሕቴየ
ወመጠውከኒ ዘባኖሙ ለፀርየ


ቅዳሴ


👉ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም)


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(ዝማሬ)

ሐመረ ኖህ ነሽ
============
ሐመረ ኖህ ነሽ
የምህረት ቃል ኪዳን የተገባልሽ
ትውልድ ይህን አምኖ
ያከብርሻል አልቆ እና አግኖ
አዝ----------------//
በእግዚአብሔር ሀሳብ ነበርሽ በህሊና
ዓለምን ሳይፈጥር አዳምን ሳይሠራ
ሁሉን የናፈቀሽ የወጣብሽ ፀሀይ
ንግሥት ነሽ ድንግል እሙ ለአዶናይ
አዝ----------------//
ያንን የጭንቅ ቀን የጥፋቱን ዘመን
አልፈነዋል ባንቺ በአማናዊት ፅዮን
ምንጭ ነሽ የእርካታ የድህነት መፍለቂያ
የዘለዓለም እረፍት አንባ እና ማረፊያ
አዝ----------------//
የነቢያት ተፈጽሞ አየን
አንቺ ምክንያት ሆነሽ ለመዳናችን
ድምፅሽን ጠላት ይሸበራል
እኛ ግን ሰምተነው በሀሴት ዘለናል
አዝ----------------//
አንዴ በገባልሽ ቃል ኪዳን መሠረት
ትውልዱን ይምራል ይኸው በቸርነት
ስሽ ወለላ ነው ጣፋጭ ለአፋችን
ማርያም ማርያም ብለን ታብሷል እንባችን



@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(ትርክት)

…………………በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ መምህሯ ክፍል ገብታ ስታስተምር ከተማሪዎቹ አንዱ ይነሳና "መምህር እቃ ተሰርቂያለሁ" ይላል ። መምህሯም የተሰረቀው እቃ ምን እንደሆነ ካጣራች ቡኃላ ተማሪዎች ለፍተሻ እንዲዘጋጁ አደረገችና ፍተሻዋን ቀጠለች ።

በፍተሻው ሰአት ታዲያ አንዲት እድሜዋ 10 አመት እማይሞላ ተማሪ ተራዋ ደርሶ ቦርሳዋን እንድትከፍት ስትጠየቅ አሻፈረኝ ትላለች ። መምህሯም በንዴት ጦፋ አንቺ ሌባ አንቺ ነሽ የሰረቅሽው ፓሊስ ነው ምጠራልሽ እያለች ስትጮህ የሰሙት ዳይሬክተሯ ከተፍ ይላሉ ።

ይህን ጊዜ ልጅቷ የባሰ ድንጋጤና ፍርሃት እያንቀጠቀጣት እባክሽ ይቅር በይኝ እኔ ሌባ ኣደለሁም ከፈለግሽ እንኪ ፈትሽኝ ግን እዚህ ተማሪዎች ፊት አደለም እያለች መምህሯ እግር ስር ወድቃ ልመናዋን ቀጠለች ። መምህሯ ግን እየደነፋች ነው ።

በዚህ ጊዜ በእድሜ ጠና ያሉት ሴት ዳይሬክተር ቆይ እስቲ መምህር ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ ብለው ዳይሬክተሯ ወደቢሮ ወሰዷቸው ። ከዛም ልጅቷን በተረጋጋ ሁኔታ እንድትቀመጥ ቢያደርጉም መምህሯ ግን እስካሁን መረጋጋት አልቻለችም ። ዳይሬክተሯ መምህሯን ከገላመጡና ዝም እንድትል ካደረጉ ቡኃላ ልጅቷን እረጋ ብለው "ቦርሳው ውስጥ ምንድነው ያለው" ብለው ጠየቋት ።

ልጅቷም "ቦርሳው ውስጥ ያለው ተማሪዎች በልተው የጣሉት ትርፍራፊ ነው ያለው" አለች በህፍረት እየተሸማቀቀች። ሴትዮዋም በመገርምና ባለማመን ስሜት "እንዴት እንዲህ ይሆናል" ሲሉ ጠየቋት ።

እሷም "ለወንድሞቼ ልወስድላቸው ብየ ነው" አለች አንገቷን ደፍታ በሚያሳዝን ሁኔታ ቅስሟ ተሰብሮ ። ይህን ጊዜ ዳይሬክተሯ ከመቀመጫቸው ተነስተው ተጠጓትና ፀጉሯን እየደባበሱ "አይዞሽ የኔ ልጅ ተረጋግተሽ ስለ አባትሽና ስለ እናትሽ ንገሪኝ ኣሏት ።

ይቺ አንዲት ፍሬ ልጅ እንባዋ እየወረደ እንዲህ አለች" አባቴ በሹፍርና ነበር የሚያስተዳድረን በኋላ ግን በአደጋ ተለይቶናል ። እናቴም ብትሆን ምንም ገቢ ያልነበራት ስትሆን ያባቴን ሞት ስትሰማ እራሷን ስታ ሆስፒታል ገባች ። በዛው የተነሳ ሽባ ሁና ቀረች ። ታዲያ ሁለት ጨቅላ ወንድሞች አሉኝ ቤት ነው ጥያቸው የመጣሁት ዘመድ ስለሌለን ዘወር ብሎ እሚያየን የለም ።

እሚላስ እሚቀመስ የለንም ። ታዲያ ይችን ፍርፋሪ ወስጄ ሂወታቸውን ብታደጋት ብየ ነው ። እባካችሁ ለተማሪዎች እንዳትነግሩብኝ ። ትምህርቴንም ቢሆን አቋርጣለሁ ። ብቻ አትናገሩብኝ እያለች አንጀት በሚያላውስ ሁኔታ ችግሯን ስትናገር ዳይሬክተሯ ልጅቷን አቅፈው አነቡ ። ስለዚህ ከመፀፀት ይልቅ የሰዎችን ሁኔታ በእርጋታ ለመረዳት መሞሞከር ታላቅነት ነው ።

ቴሌግራምን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም ፡፡ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ፡፡ በምድር ላይ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና ፡፡

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ኅዳር 01/03/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፻፮፥፴፮(106፥36)
ሐነጹ አህጉረ ኀበ ይነብሩ
ተከሉ ወይነ ወዘርዑ ገራውሀ
ወገብሩ ማእረረ እክል

ምስባክ ዘቅዳሴ

ወእነግር ስምከ በቅድመ ነገስት ወኢይትኀፈር
ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀረኩ ጥቀ
ወአነሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘአፍቀርኩ


ቅዳሴ


👉ዘቄርሎስ

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(ግጥም)

#የኢትዮጵያን_ነገር…..


አባ አባ ብዬ - በለመንኩህ ለቅሶ - ተሰምቷል ጩሀቴ
በውን ያስጨነቀኝ - ተራራው ፈተና - ተነስቷል ከፊቴ
የተማመንኩበት - የሥምህ ስንቅነት - አንዳች አልጎደለ
ተስፋ ያደረግሁት - የጸሎትህ ሥምረት - በሕይወቴ አለ
የተደገፍኩበት - የደጅህ ዋስ’ነት - ሜዳ አልጣለኝም
እንባ የረጨሁበት - የ’ስማኝ!’ ዋይታዬ - አልወደቀብኝም
ከህጻንነቴ - አንተን ተማምኜ - የሄድኩበት መንገድ
በጥቅጥቁ ጫካ - አንበሳው አልነካኝ - አልሆንኩ አልቦ ዘመድ
ልጅነቴ ሁሌ - ገብረ ሕይወት እያለች -በምልጃህ ተማምና
ትናንት እንዳልተውካት - ዛሬም ስትጣራህ -ለነፍሴ ጭንቅ ና፡፡
Abboo! - Aabboo! ብዬ - ሀገር አሻግሬ - ስምህን እጠራለሁ
ከግብጽ በረሃ - ለምትሻህ ኢትዮጵያ - ቶሎ ና እላለሁ
ታስፈልጋታለህ - እንኳንና ለሰው - ለአናብስት ሁሉ
የጽድቅህን ፍሬ - የቀመሱ ነፍሳት - አባ አባ ይላሉ
የንጽኅናህ ግርማ - ከግብጽ እስከ ኢትዮጵያ - ሀገር እያወደ
አንበሳውም ነብሩም - እያገለገለህ፣- አንተን እያጀበ- ካንተ ጋራ ሄደ፡፡
አቡዬ ና ድረስ- ና ገስግስ ዘንድሮም - ቶሎ ና ለሀገሬ
እረፉ በላቸው - እንዳይናከሱ - ሰውንና ሰውን - ሰውንና አውሬ፡፡
ዛሬም ቁም ዝቋላ - ግባ ከባህሩ - እጆችህን ዘርጋ
ፈልግ ልጆችህን - የጸሎት ፍሬህን - የጠበቅኸውን መንጋ
ከሰሜን ከደቡብ - ከምስራቅ ከምዕራብ - የተጋደልህለት
“ኢትዮጵያን ማርልኝ !” - ብለህ ከአምላክህ ፊት - ብዙ የጸለይክለት
የረገጥከው መሬት - ያረፍክበት ደብር - የነካህ አፈሩ
ዳግም በዛሬው ቀን - ጸሎትህን ይሻል - መላው ሀገሩ
ምድረ ከብድ ድረስ - ተገኝ በዝቋላ - አንሳ እጆችህን
እስከምንጠገን - ተሰብረናልና - እየን ልጆችህን
አታሳፍረንም - ገብረ መንፈስ ቅዱስ - ብለን ስንጠራህ
እንግዲህ አቡዬ - የኢትዮጵያን ነገር - አሁንም አደራህ!!


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
ኅዳር 04/03/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፴፮፥፫(36፥3)
ተወከል በእግዚአብሔር ወግበር ሠናየ
ወየኀድረከ ዲበ ምድር
ወይርእየከ ዲበ ብዕላ

ምስባክ ዘቅዳሴ

እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኩሎ አሚረ
ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሁ
ንቃህ እግዚኦ ለምንት ትነውም

ቅዳሴ

👉ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(ምክር)

አገልግሎትና_መኪና


በአገልግሎት ጋሪ በልኡክ መኪና
ነዳጁ #ፍቅር ነው ፍሬኑ #ትሕትና
መኪና በመንገድ ፍሬን ከሌለው፣
አገልጋይም እንዲሁ ትሕትና ካነሰው፣
መፃኢ ዕጣቸው መጋጨት ብቻ ነው።
ነዳጅና ፍቅርም ይመሳሰላሉ፣
ፍቅር ይኽኛውን ነዳጅም ያኛውን ያንቀሳቅሳሉ።
#ተስፋ መስታወት ነው #ትውፊት ስፖኪዮ፣
#እምነት ደግሞ መሪው የአቅጣጫ መለዮ፤
በእምነት መሪነት በተስፋ መስታወት ወደፊት እያሉ፣
በአዕምሮ ማኅደር በትውፊት 'ሚታዩ ኋላዎችም አሉ።
'ሚንቀሳቀሱበት 'ሚሽከረከሩበት #ትግኃት ይባላል የመኪናው ጎማ፣
#ትግኃት ቅንዓትም ጡሩምባው 'ጲጵ' የሚያደርጉበት ከሃይማኖት መንገድ ዞር እንዲል ጠማማ።
ከእነዚህ ዕቃዎች አንዱ ከጎደለ ወይ ከተጣመመ ወይም ከተበሳ፣
መኪናው አሮጌ ይባላል ከርካሳ።
ጥገናና ሰርቪስ መለዋወጫ ዕቃ ለሚያስፈልገው ሰው፣
መካኒኩ ካህን ፣ ላቫጆው ንስሐ ፣ ጋራጁ መቅደስ ነው።
ሕግ አስከባሪዎች ፖሊሶችስ ካሉ፣
ሥርዐት ቀኖና ተብለው 'ሚጠሩ ትራፊኮች አሉ።
በሃይማኖት መንገድ ሲወጡ ሲወርዱ፣
መጠመቅ ብቻ ነው የመንጃ ፈቃዱ።
መልካም መንገድ!

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(ትርክት)

………“እኛ ግን ጠላቶቻችንንም እንወዳለን”
ቅዱስ ሮማኖስ የተባለ የዘመነ ሰማዕታት ክርስቲያን ሃይማኖትህን ቀይር በማለት ያሰቃየው ለነበረው ዘመን የሰጠው ባለሥልጣን የመለሰለት እንዲህ በማለት ነበር። እናንተስ ክፉ ማድረግን ታውቃላችሁ። እኛ ክርስቲያኖች ግን እግዚአብሔርን በማመን በጎ ማድረግን እናውቃለን። በክርስቶስ ስም አጋንንትን ደዌ ካደረባቸው ሰዎች እናስወጣለን፤ እናስወግዳቸውማለን። እናንተ ለጥቂት ዘመን ሥልጣን አላችሁ ።ያለ መራራትም በሰዎች ላይ ትፈርዳላችሁ። እኛ ግን ጠላቶቻችንንም ሳይቀር እንድንወድ ስለታዘዝን በተግባር እንፈጽመዋለን። ለሚያሳድዱንም እንጸልይላቸዋለን።
እናንተስ ለጥቂት ዘመን ኖረው በሚሞቱ ሰዎች ትተማመናላችሁ። እኛ ግን እግዚአብሔርን በማመን በማይሞቱት በመላእክት ዘንድ እንመሰገናለን። እናንተ ለአጋንንት በመስገድ ሰዎችን ወደ ገሀነም ታቀርቧቸዋላችሁ። እኛ ግን ሰዎችን ከገሀነም እናወጣቸዋለን። እናንተ በምትሀታችሁ ሰዎችን ከዘለዓለም ሕይወት ትለዩዋቸዋላችሁ። እኛ ግን ቅን በሆነች ሥርዓታችን እና በየዋህነታችን ሰዎችን ከሞት እናወጣለቸዋለን።
እናንተ ነገር በማሳመር ሀብት በመሰብሰብ እና በማዳላት በሰው ላይ ሞትን ታመጣላችሁ። እኛ ግን ሰዎች ይድኑ ዘንድ ሥነ ምግባር እናስተማራለቸዋለን። ኃላፊውን ሳይሆን ዘለዓለማዊውን ሕይወት እና ድኅነት እንነግራቸዋለን። እናንተ ኃላፊያን ገዥዎች አሏችሁ። የምትሰግዱላቸውም አምላክ አይደሉም፤ ድንጋይ ናቸው እንጂ።እኛ ግን ዘለዓለማዊውን ንጉሥ እናመልካለን።ለእሱም እንገዛለን፤ እንሰግዳለንም።
እናንተስ የማታገኙትን ትቀበሉ ዘንድ አማልክቶቻችሁን ትለምናላችሁ።ለእኛ ግን አምላካችን በፍጹም እምነት የለመንነውን ይሰጠናል።እኛ ክፉ የሚያደርጉብንን ይቅር እንላቸዋለን። እናንተ ግን ዘለዓለም የምንኖር ስለሚመስላችሁ የሰውን ንብረት ትቀማላችሁ። እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠንንም ስለእግዚአብሔር ብለን ለድሆች እንሰጣቸዋለን። በዚህም ሁሉ እናንተን እንበልጣለን በማለት የክርስቲያኖችን እና የአረማውያንን ሕይወት አነጻጽሮ ይነግረዋል። በዘመነ ሰማዕታት የተፈጸመውን ይህን ጉዳይ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ብናስተያየው ዛሬ የተፈጸመ ያህል ይሰማናል።
ከቅዱሱ በረከት ይክፈለን

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(ትርክት)

ጥበበኛዋ ትል

አንዲት ትል ከአንድ ረጅም ዛፍ ስር ሆና ወደ ላይ ስትመለከት ዛፉ በማፍራት ላይ ያለውን ፍሬዎች በመመልከቷ ከፍሬው ለመመገብ ወደ ዛፉ ላይ የመውጣትን ጉዞ ጀመረች፡፡
በእሷ ፍጥነት (ዝግመት) ዛፉን ወጥታ ያሰበችበት ለመድረስ ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚፈጅ ከተሞክሮ ብታውቀውም በጣም እየጸለየች ወደላይ በወጣች ቁጥር በበለጠ ሁኔታ እየታያት የመጣውን የአካባቢ ገጽታ እያየች በደስታ ዳገቱን ተያያዘችው፡፡
ብዙም ሳትርቅ ከዛፉ ላይ ወደታች የምትወርድ አንዲት ምንነቷ በውል ያልታወቀ እንስሳ ቆም ብላ፣ “ወደየት ነው እንደዚህ በደስታ እየተፍለቀለቅሽ የምትሄጂው አለቻት”፡፡
ትል፣ “ዛፉ ጫፍ ላይ ያለውን ፍሬ ልበላ” አለች፡፡
እንስሳዋም፣ “እኔ ከዚያ ነው የመጣሁት፣ ፍሬዎቹ ገና አልበሰሉምና አትልፊ፡፡ ሲቀጥል ደግሞ አጉል ደስተኛነት አያጥቃሽ ጉዞው ቀላል እንዳይመስልሽ፣ ስለዚህ ብትመለሺ ይሻልሻል” አለቻት፡፡
ትሏም፣ ቆም ብላ እዚያ ለመድረስ የሚፈጅባትን ጊዜ ካሰላች በኋላ፣ “ችግር የለውም፣ እዚያ እስከምደርስ ድረስ ፍሬዎቹ ይበስላሉ” በማለት ጉዞዋን ቀጠለች፡፡
ያሰብከው ከፍታ ለመድረስና የለፋህበትን መንፈሳዊ ፍሬ ለማግኘት . . .
1. ዓላማህን ከጊዜ ጋር አጣጥመህ እቅድ አውጣ
ከሁሉ በፊት ለመድረስ የምትፈልግበትን የዓላማ ከፍታ ወስን፡፡ ከዚያም፣ እዚያ ዓላማህ ጋር ለመድረስ የሚፈጅብህን የጊዜ ሁኔታ አስላና ሁለ-ገብ እቅድ አውጣ፡፡ ሁለ-ገብ እቅድ ማለት፣ እንደ አንተ ሁኔታ ገንዘብን፣ ትምህርትን፣ እድሜን . . . ያካተተ ሊሆን ይችላል፡፡
2. የሰዎችን ሃሳብ አመዛዝን
ሁል ጊዜ ከፍ ያለ እቅድ ስታወጣና መንቀሳቀስ ስትጀምር ተቃራኒውን የሚነግሩህ ሰዎች እንደሚያጋጥሙህ አትርሳ፡፡ አንዳንዶች ለአንተ አስበው በቅንነት፣ ሌሎቹ ደግሞ በአንተ ላይ አስበው በምቀኝነት፡፡ በጭፍንነት ከሰማሃቸው ውጤቱ ያው ስለሆነ ሁለቱንም ቢሆን በጥንቃቄ ማስተናገድ አስፈላጊ ነው፡፡ በዋናነት ደግሞ ዲያቢሎስ በየሄድክበት ሁሉ የእንቅፋት ችግኙን ይተክልብሃል ይህንንም በጸሎት ኃይል ተቃወም ።
3. በጉዞው ተደሰት
ወደ ዓላማህ በአንተ አቅምና ፍጥነት ስትጓዝ ፍጻሜው ላይ የመድረስን ደስታ እስከምታገኝ ተስፋ አትቁረጥ፡፡፡ የመድረስ ደስታ ዓላማህ ላይ እስከምትደርስ ድረስ ያስጠብቅሃል፡፡ የጉዞው ደስታ ደግሞ አሁኑኑ በመደሰት ለጉዞው ጉልበትን ይሰጥሃል፡፡
ያሰብከው ደረጃ መድረስህና ፍሬህን መብላትህ አይቀርምና፣ በፍጹም እንዳትቆም!!!

(ቅዱስ ያሬድንና ያቺን ትል አስብ)

@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክ እና ወንጌል)
ኅዳር 09/03/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፷፪፥፲፩
ንጉሥሰ ይትፌሣሕ በእግዚአብሔር
ወይከብር ኩሉ ዘይምሕል ኪያሁ
እስመ ይትፈጸም አፍ ዘይነብብ ዐመፃ

ምስባክ ዘቅዳሴ

ወነበቡ ዓመፃ ውስተ አርያም
ወአንበሩ ውስተ ሰማይ አፋሆሙ
ወአንሶሰወ ውስተ ምድር ልሳኖሙ

ቅዳሴ


ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም)


@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot