"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ኤልሮኢ፡
አድዋ

………………
ምንሊክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ
በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣሊያን አበሻ እንዳይደርስ
ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ሁዋላ አይገኝ
አባተ በመድፉ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጎጃሙ ንጉሥ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሀን
ዳዊቷን ዘርግታ ሰምዐኒ ስትል
ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል
ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል
እንደ በላዔ ሰብእ እንደመቤታችን
ሲቻለው ይምራል የኛም ጌታችን።

@aleroe
ኤልሮኢ:(መዝሙር)
#ንጹም_ፆመ

ንጹም ፆመ ወናፍቅር ቢጸነ
ወንትፋቀር(፬) ንትፋቀር በበይናቲነ ኧኸ(፫)
#ትርጉም
ፆምን እንጹም ባልንጀራችንን እንውደድ
እርስ በራሳችንም እንፋቀር


@aleroe
ኤልሮኢ:
፨መርሳት፨

በአንድ ወቅት የግብጹ ሊቀ ጳጳስ ብጹኡ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ እያስተማሩ ባሉበት ወቅት በዙ ጥያቄዎች በጹሑፍ ይደርሳቸው ነበር። ታዲያ ከነዛ ጹሑፎች መካከል አንዱ እንዲ ይላል
... አባቴ እኔ ታላቅ የመርሳት ችግር አለብኝ ያደረኩትን የሰማሁትን ነገሮች በሙሉ እረሳቸዋለው እና አባቴ ምን እንደማደርግ ይምከሩኝ ነበር የሚለው። ብጹእነታቸውም ልጄ መምከሩንስ እመክርሃለሁ ምን ማድርግ እንዳለብህ እነግርሃለሁ ግን እንዳትረሳው እፈራለሁ አሉት ይባላል።
ቃለ እግዚአብሔር ስንሰማ በማስተዋል ልቦናችንንም ሰብስበን ሊሆን ይገባል።
በነገሮችም ሁሉ አስተዋዮች ልንሆን ይገባል።በዚህም ማስተዋል እና ጥበብን ወደሚሰጥ አምላክ አጥብቀን ልንማጸን ይገባናል።

@aleroe
ኤልሮኢ:

ሩጫ ✞............🏃🏃🏃🏃

ማልያህን ታጠቅ
ቀበቶህን አጥብቅ
ጫማህን አጠባብቅ
መስመርህን ጠብቅ
አትይ ወደ ኋላ
ተብሎ ተነግሮን
ጀምረን ሩጫ
ለመቀበል ዋንጫ
እኛ ዞርን ስናይ
እነሱ ፈጠኑ
ከሽልማት ጌታ ጽዋም ተቀበሉ።

@aleroe
ኤልሮኢ:(መዝሙር)

አዝናለሁ አለቅሳለሁ

አዝናለሁ አለቅሳለሁ
ስለ በደሌ ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ
አዝናለሁ አለቅሳለሁ
ስለ ጥፋቴ ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ
ነገር ግን መሐሪ ነህና
እንደምታድነኝ አምናለሁ

ሥጋዬ ለራሱ እያታለለኝ(፪)
ሁሉን በመፈለግ ወሰደና ለጥፋት ሰጠኝ(፪)
አዝ = = = = =
ከመሬት ተገኝታ እስክትገባ
በከንቱ አስቀረችኝ አምላኬ ሆይ ሥጋ ሰገብጋባ(፪)
አዝ = = = = =
ትቻት መምጣቴ ነው አፈር ሥጋዬን
እንድትቀበላት አምላኬ ሆይ አደራ ነፍሴን(፪)

@aleroe
ኤልሮኢ:
. #ጸሎት

#ጸሎት ያቆመች ነብስ እየሞተች ያለች ነች።
#ለሊት ተነሥቶ በጸሎት ጠላቱን ያልመታ ጥዋት ቀኑን ሙሉ ሰይጣን ሲመታው (ሲቀጠቅጠው) ይውላል።
#ክርስትያን ተንበርክኮ ማንበርከክ ይችላል። የማይጸልይ ከሆነ ደግሞ ገና ሳይዋጋ ይንበረከካል።
#ሌሊት በጸሎት ያልወረድክበት ሰይጣን። ቀኑን ሙሉ ሲያገሳብህ ይውላል።
#ከእግዚአብሔር ጋር አንዲት ቀን ሳታሳልፍ ከዋልክ፦ ከመልካሙ
ዘመንህ ውስጥ አንዲቷ ቀንህ በከንቱ እንዳባከንካት ቁጠራት።
#እግዚአብሔርን በጸሎት የማይለምን፦ ዘወትር የሰውን ፊት የሚያይ ተለማማጭ ሆኖ ይኖራል።
#ከእግዚአብሔር ጋር መልካም ጊዜን ማሳለፍ፦ገንዘብህን ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኝ ንግድ (ኢንቨስት) ከማድረግ በላይ እጅግ ጠቃሚ ነው።


@aleroe
ኤልሮኢ:
01/07/09

መዝሙር መሐሩነ
#ቅድስት

#በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ፡፡

#የዕለቱ ምስባክ፦ መዝ ፺፭፥፭

እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ
አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ
ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ

#ትርጉም
እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ፈጠረ
እምነትና በጎነት በፊቱ ናቸው
ቅድስና እና የክብር ገናንነት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።

የዕለቱ ወንጌል፦

ማቴ ፮፥፲፯ - ፳፭
ቅዳሴ፦ ዘኤጲፋንዮስ

👉 @aleroe
ኤልሮኢ:
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ዛሬ በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ላጡት ወገኖቻችን እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን። ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እንመኛለን።
💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ኤልሮኢ:
#ስጋ_ነው_ምርኩዜ


ስጋዬ ወፍሮ አፌ ክፉ ደፍሮ
ሓሰትን መስክሮ እውነት ቅሉን ሽሮ
እውነት ተሸሸጋ ማን እውነት ሊያወጋ
ስለ ክፉ ስጋ።
ስለ ክፉ ስጋ ነፍሴ ስትወጋ
የአንደበቴ ችቦ የአንደበቴ ሰንጋ
ነፍሴ ስትቃትት የስጋ ጦር ወግቷት
ቀንም ሌሊትም ቁስሉ ሲያሰቃያት
ጭንቅ ጥብብ አለች ቀኑ ጨልሞባት
የምታውቀው ቤቷ ተዘግቶባት
ስጋ ሲበድላት በሐዘን በትካዜ
በሐሰት ባለሟል በስጋ ምርኩዜ
እኔንም ተረድታ በእምነት መደብዘዜ
በህይወት ልታልፍ ልትጓዝ በግዜ
ነፍሴ የተዘጋጀች ልታቀርብ ኑዛዜ።
____________________

@aleroe
ኤልሮኢ:(መዝሙር)

#የሚጠብቀኝ አይተኛም

የሚጠብቀኝ አይተኛም(×2) አያንቀላፋም(×2)
ቤት ባይኖረኝም
በደጅ ባድር
ቀንና ሌሊት ከኔ አይርቅም
ድምፀ አራዊት የሌሊት ግርማ
ወደ እኔ አይገቡም ድምፅህ ሲሰማ
መሰናከልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሀይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም
ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በፅድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ
የሰማዩን ጥል እታገሳለሁ
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለሁ
ሌሊት በድብቅ ለሚጎበኙ
ለፃድቃኑ ግን አምላክ ይስጥልኝ
እንቅልፌን ባርኮ የሰጠኝ ጌታ
በዓለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የዕለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍፁም
ምስጋና ላቅርብ እስከዘላለም

#ዘማሪ ይልማ

@aleroe
ኤልሮኢ:

……ሰውየው አስር ክፍል ቤት ሠርቶ ብቻውን ሲኖር አንድ
ቀን በሩ ተንኳኳ ሲከፍት ጌታ ነው፡፡ "ውይ አምላኬ
ጌታዬ አንተ እኔ ቤቴ መጣህ?" ብሎ በደስታ
ተቀብሎት አንድ ክፍል ቤት ሰጥቶት መኖር ጀመሩ፡፡
በሌላ ጊዜ በሩ ተንኳኳ፣ ሲከፍት ሰይጣን ነው፡፡
ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ
ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል?" አለው፡፡
ጌታም "ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም " አለው፡፡
ሰውየውም ተሰምቶት ሁለት
ክፍል ቤት ለጌታ ጨምሮለት እርሱ ሰባት ክፍል ይዞ
መኖር ቀጠሉ፡፡ በሩ ተንኳኳ ሲከፈት ሰይጣን ነው፡፡
ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ
ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል? " አለው፡፡
ጌታም " ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም " አለው፡፡
ሰውየውም ተሰምቶት ከጌታ
ጋር እኩል ለእኩል ተካፈለ፡፡
ነገር ግን ቤቱ ከቀድሞ ይልቅ ተንኳኳ ፡፡ አዝኖም
ይዘጋና ጌታ ሆይ አለው፡፡ ጌታም የቀድሞውን መልስ
ሰጠው፡፡
በዚህ ጊዜ ሰውየው ለራሱ አንድ ክፍል ቤት ይዞ
ዘጠኙን ክፍል ቤት ለጌታ ሰጠው፡፡ ነገር ግን
ከቀድሞው ይልቅ በጣም ተንኳኳ፡፡ ቢከፈት ሰይጣን
ነው፡
በሩን ይዘጋና ወደ ጌታ ሄዶ " ጌታ ሆይ ምሥጢሩ
ምንድን ነው? " አለው፡፡ "ጌታ ግን ቤቱ የአንተ እንጂ
የእኔ አይደለም "አለው፡፡
በዚህ ጊዜ ዐሥሩንም ክፍል ለጌታ አስረከበ፡፡ ጌታም
አንድ ክፍል ቤት ለሰውየው ሰጠው፡፡ በሩም ተንኳኳ
፡፡ ጌታም ሊከፍት ተነሣ፡፡ ሲከፍት ሰይጣን ነው፡፡
ሰይጣንም " ይቅርታ የአንተ ቤት መሆኑን አላወቅሁም
" ብሎ ሄደ፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ መንኳኳት ቆመ፡፡
ሁሉንም የሕይወታችንን ክፍል ለጌታ እግዚአብሔር
ካላስረከብነው መንኳኳት አይቆምም፡፡ 1ዐ% ስንሰጥ
ይንኳኳል፡፡ 30% ስንሰጥ ይንኳኳል፡፡ 50% ስንሰጥ
ይንኳኳል፡፡ 99% ስንሰጥ ይበልጥ ይንኳኳል፡፡ 100%
ስንሰጥ መንኳኳት ይቆማል፡፡ እኛ ከከፈትን ሰይጣን
ይገዳደረናል፡፡ ጌታ ሲከፍት ሰይጣን " ይቅርታ የአንተ
ቤት መሆኑን አላወቅሁም " ብሎ ይሄዳል፡፡
ጌታ ሰማይን የደስታ አገር ያደረጋት ሙሉ
በሙሉ የፈጣሪ ፈቃድ የጸናባት በመሆኗ ነው፡፡
ባንተም ሕይወት የሰማይ ደስታ የሚመጣው
የፈጣሪ ፈቃድ በሕይወትህ ሙሉ በሙሉ
ሲፈጸም ነው፡፡ ስለዚህ፡-
· ፈጣሪን እረኛህ አድርገው፡፡
· በፍጹም ልብህ ተከተለው፡፡
· የሚያስፈልጉህ ነገሮችም አንተን ይከተሉሃል፡፡
"ሙሉ ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር እናስረክብ።"

@aleroe
ኤልሮኢ፡
#መፆሙን_ይፆማል

መፆሙን ይፆማል #ሁሉም_የአዳም_ልጅ/2/
የጊዜው መድረሱ #የሚያውቅ_የለም_እንጂ/3/

ይደርሳል ሰዓቱ #ሳስብ_ሌላ_ሌላ/2/
የተሰቀለውን #ስጋውን_ሳልበላ/3/

ድጓ ፆመ ድጓ #ተሰቅሎ_ከቤቴ/2/
አወይ አለማወቅ #ሳልማር_መቅረቴ/3/

ደግሜ ደገሜ #ቀረኝ_አሌፋቱ/2/
አድኅነኒ ሳልል #አትጥራኝ_በከንቱ/3/

እኔስ እሄዳለው #አጣቢ_ፍለጋ/2/
በጣም አድፎብኛል #የለበስኩት_ስጋ/3/

ዳዊት እንዴት ይሙት #ሳልተዋወቀው/2/
የሚመጣው ሁሉ #በገና_የሚያውቀው/3/

ዐርብ ረቡን ገደፍኩ #በሥጋ_አዋዜ/2/
እንዲህ ለሚደርሰው #ለማይቆየው_ጊዜ/3/

ከሥጋው ሳልበላ #ተጠይፌ_ደሙን/2/
ማን ይችለው ይሆን #የላይ_ቤት_ረሃቡን/3/

ከንብረቱ ሁሉ #አልጋዬ_ነው_ሀብቴ/2/
አድርሶኝ ይመጣል #ከዘላለም_ቤቴ/3/

ብልህ ነው ስትለኝ #እዩት_ሞኝነቴን/2/
በራሴ ላይ ሆኖ #አላውቀውም_ሞቴን/3/

መማሩንስ ዳዊት #ተምሬ_ነበረ/2/
ከአምላኪየ ሳልደርስ #ልቤ_ሰንፎ_ቀረ/3/

እንኳን ነአኩተከ #በስመ_አብም_ቸገረኝ/2/
ዳዊት እንዴት ተማርክ #እባክህ_ንገረኝ/3/

👉👉👉@aleroe👈👈👈
👉👉👉@aleroe👈👈👈
👉👉👉@aleroe👈👈👈
ኤልሮኢ:
# እጠበኝ ቆሽሻለው

እጠበኝ ቆሽሻለው አምላኬ በድያለው
ያለናት ያሳደከኝ ያላባት የ ጠበከኝ
ያንሁሉ ዛሬ ረሳው እጠበኝ ቆሽሻለው/2/

ከድንኳንክ ብታስገባኝ ሞገስ ሰተህ
የ አፍኒንን ምግባር ይዤ አስ ቀየምኩህ
ቅባሜሮን ያተምክበት ልጅነቴ
እንዳይጎድፍ ጠብቅልኝ ቸር አባቴ


ሀይል አኑረክ እንደ ሶምሶን በፀጉሬ
ጎልያድን አስጥለኅኝ በጠጠሬ
አቅም ቢያንሰኝ በስጋ ጦር ተሸንፌ
ደጅህ መጣው የንባ መባ ባይኔ አቅፌ

እንዳትረሳኝ በመዳፍህ ቀርፀሀኅኛል
እንዳተወኝ ያለመጠን ወደህኛል
ባሰነዝር ልት ቀጣኝ የሞት በትር
የትግስትክ ሰሌዳነው ለኔክብ

ከከንፈሬ ጥበብ ጽፈህ ቅኔ ቢፈስ
በመታበይ አሳዘንኩት ያንተን መንፈስ
ፍቅር ግተህ በቅፍስር ያሳደከኝ
እባክህን በበደሌ አትቅፀፈኝ


@aleroe
ኤልሮኢ:

……አንድ በምሽት አቅጣጫ የጠፋበት መርከብ ከሩቅ ያየ ሰው ወደ እቤቱ ገብቶ ሻማ ይለኩሳል

ሻማውም ለምን ለኮስከኝ ቢለው ሰውዬው ‹‹አቅጣጫ የጠፋው መርከብ ከሩቅ ያታየኛል
ለሱ በእሳት ልጠቁመው ነው ይለዋል ሻማውም ‹‹ታዲያ እኔ ሻማ ነኝ እንዴት ከሩቅ እታያለሁ›› ቢል ሰውዬውም መለሰ ‹‹ሻማዬ ሆይ አንተ ብቻ የቻልከውን ብራ›› አለውና ይዞት ይወጣና ብዙ ደረቅ እንጨቶችን እንደ ዳመራ ከቆለለ ቦሃላ በሻማው እሳት እንጨቶቹን ለኮሰ ብርሃኑም ብዙ ሆነ
ያኔ መርከቡም ተመልክቶ መጣ

ሰውዬውም ለሻማው እንዲህ አለው ‹‹ሻማዬ ሆይ አየህ አንተ በቻልካት መጠን ስለበራህ ያንተን ብርሀን ተቀብለው የሚያደማምቁ ብዙዎች አሉ›› አለው፡፡


እንግዲህ እንዲህ ነው የኔ ጥረት ትንሽ ናት አትበል፡፡ የቻልከውን ካደረክ ሌሎች ያንተን ብርሃን የሚቀበሉ እልፎች አሉ

‹‹የትም ሁን ማንም ሁን ያቅምህን በጎ ለማድረግ ግን አትስነፍ ደግነት
እንደ ጥሩ ሽቶ ነው ከአንዱ ተነስቶ ወደ አንዱ ይጋባል››

እንግዲህ አንዲህ ነው ለመስጠት የግድ ሃብታም መሆን
አይጠበቅብህም፡፡ ደግሞ ማንም ሰው ልስጥ ካለ የሚሰጠው አያጣም፡፡

@aleroe
ኤልሮኢ:(ስነፅሁፍ)
በዜሮ ይባዛል!

ፆም×0=0 ስግደት×0=0
ጸሎት ×0=0


ተግቼ ብጸልይ እጆቼን ዘርግቼ
ቤቴ ባዶ ቢቀር ያለኝን መጽውቼ
ቀኑን ሙሉ ብጾም እስኪቆረጥ አንጀቴ
ዘወትር ብሰግድ እስኪዝል ጉልበቴ
በቀድስ ባስቀድስ በመቅደሱ ግርማ
ብዘምር ባወድስ የሚጣፍጥ ዜማ
ወንጌልን ብሰብክ ምስጢር አመስጥሬ
ብናገር ባስተምር ትርጉሙን ዘርዝሬ
ጥልና ክርክር ካሉ በህይወቴ
ሐሜት ክርክር ካልጠፉ ከቤቴ
በዜሮ ይባዛል ፍቅር በማጣቴ።

ስብሐት ለእግዚአብሔር!

ፆም×ፍቅር= 30 ያማር ፍሬ
ጸሎት×ፍቅር= 60ያማር ፍሬ
ስግደት× ትህትና= 100ያማረ ፍሬ

@aleroe
ኤልሮኢ:
​​ በጌቴ ሤማኒ

በጌቴ ሤማኒ በአታክልቱ ቦታ
በጌቴ ሤማኒ በአታክልቱ ቦታ
ለእኛ ሲል ጌታችን በዓለም ተንገላታ
በዓለም ተንገላታ/2/

አዳም እና ሔዋን በአጠፉት ጥፋት
አዳም እና ሔዋን በአጠፉት ጥፋት
እኛም ነበረብን የዘለዓለም ሞት
የዘለዓለም ሞት /2/

መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ
መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ
ይገርፉት ነበረ ሁሉም በየተራ
ሁሉም በየተራ /2/

ድንግል አልቻለችም ዕንባዋን ልትገታ
ድንግል አልቻለችም ዕንባዋን ልትገታ
እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ
ልጇ ሲንገላታ /2/

በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው
በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው
እንዲህ ሲል ጸለየ አባት ሆይ ማራቸው
አባት ሆይ ማራቸው /2/

በረቂቅ ሥልጣኑ ሁሉን የፈጠረ
በረቂቅ ጥበቡ ሁሉን የፈጠረ
በሰው እጅ ተገርፎ ሞቶ ተቀበረ
ሞተ ተቀበረ /2/

ፍቅሩን የገለጸው ተወልዶ በሥጋ
ፍቅሩን የገለጸው ተወልዶ በሥጋ
ኢየሱስ ጌታ ነው አልፋ እና ኦሜጋ
አልፋ እና ኦሜጋ /2/

በመስቀል ተሰቅሎ እንዲያ እየቃተተ
በመስቀል ተሰቅሎ እንዲያ እየቃተተ
ዓለምን ለማዳን የማይሞተው ሞተ
የማይሞተው ሞተ /2/

ከሞት ሊታደገን በመጣልን ፈጥኖ
ከሞት ሊታደገን በመጣልን ፈጥኖ
መስቀል አሸከሙት ውለታው ይኽ ሆኖ
ውለታው ይኽ ሆኖ /2/

መከራውን ሳስብ ሳስታውስ ቀኑን
መከራውን ሳስብ ሳስታውስ ቀኑን
ይቆስላል ይደማል ልቤ በሐዘን
ልቤ በሐዘን /2/

መች ለራሱ ነበር ይኽ ሁሉ መከራ
መች ለራሱ ነበር ይኽ ሁሉ መከራ
መስቀል ተሸክሞ የወጣ ተራራ
የወጣ ተራራ /2/

ሲያጎርሱት የሚናከስ ሰው ክፉ ነውና
ዕውሩን ቢያበራ ጎባጣን ቢያቀና
ጌታዬን ሰቀሉት አይሑድ ጨከኑና
አይሑድ ጨከኑና /2/

ምነው አያሳስብ የአይሑድ ክፋት
ምነው አያሳስብ የአይሑድ ክፋት
የዝናቡን ጌታ ውሐ ሲነፍጉት
ውሐ ሲነፍጉት /2/

በተንኮል በኃጢአት ቀሩ እንደ ሠከሩ
በተንኮል በኃጢአት ቀሩ እንደ ሠከሩ
ሙታን ከመቃብር ተነስተው ሲያስተምሩ
ተነስተው ሲያስተምሩ /2/

እናታችን ሔዋን ወየው በይ አልቅሽ
የአንቺን ሕመም ታሞ ከሞት ሊያድንሽ
የሕያዋን ጌታ ተሰቀለልሽ
ተሰቀለልሽ /2/

አዬ ጉድ አዬ ጉድ ዓለም የኋላሽ
አዬ ጉድ አዬ ጉድ ዓለም የኋላሽ
መድኃኒት ክርስቶስ በግፍ ሞተብሽ
በግፍ ሞተብሽ /2/

በመስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ሲቆርስ
በችንካር ተወግቶ ደሙንም ሲያፈስ
ዋለች በመከራ ድንግል ስታለቅስ
እናት ስታለቅስ /2/

ሰውነትሽ ራደ ሐዘን ከበበሽ
ስቃይ መከራውም ዳግም ጸናብሽ
ተሰቅሎ ስታይ አንድ አምላክ ልጅሽ
አንድ አምላክ ልጅሽ /2/

ቢፈስም ዕንባዬ ሆኖ መንታ መንታ
መች ዋጋ ይሆናል ለአንዲቱ ጠብታ
ለአለቀስሽው ለቅሶ ድንግል የእዛን ዕለታ
እናት የእዛን ዕለታ /2/

በአለቀስሽው ለቅሶ በልጅሽ ሕመም
በአለቀስሽው ለቅሶ በልጅሽ ሕመም
ከሐጢዓት ነፃሁኝ ዳንሁኝ ከገሐነም
ዳንሁኝ ከገሐነም /2/

@aleroe
ኤልሮኢ:
ስለ ሰይጣን ከተተረኩት ለቅምሻ

ሰዎች ርኩስ መንፈስ ያደረበትን ሰው ወደ አንድ ገዳም ይዘው መጡና ያድንላቸው ዘንድ
ለገዳሙ አበምኔት(አለቃ) ሰጡት። የገዳሙ አበምኔትም በተሰጠው ፀጋ ተጠቅሞ በስመ
እግዚአብሔር ሰይጣኑን ውጣ ሲለው ሰይጣኑም «መውጣቱንስ እወጣለሁ ግን አንድ ጥያቄ
ነበረኝ»ይላል።
የገዳሙ አበምኔትም «ምንድነው ጥያቄህ?» ይለዋል። ሰይጣኑም በወንጌል ላይ ፍየሎች
በግራ በጎች በቀኝ ይቆማሉ የሚል ቃል አለ፣ ለመሆኑ በፍየልና በበግ የተመሰሉት እነማን
ናቸው? ይኽንን በምሳሌ አድርገህ ንገረኝ አለው። የሰይጣኑ አመጣጥ የገባው ያ ደግ አባትም እንዲህ መለሰ። «በፍየል የተመሰሉት ኃጥአን፣ በበግ የተመሰሉት ደግሞ ፃድቃን ናቸው። በምሳሌ ንገረኝ ላልከው፣ በፍየል ከተመሰሉት ኃጥአን መካከል ለምሳሌ አንዱ እኔ ነኝ። በበግ የተመሠሉ ፃድቃንን ግን አላውቅም። አሁን ግን ውጣ» አለው። ተንኮሉ
የተነቃበትና ያጠመደው ውዳሴ ከንቱ መረብ ያልያዘለት ሰይጣንም በኃይል ጮኾ ከሰውየው
ወጣ። በሽተኛውም ዳነ፡፡

@aleroe
ኤልሮኢ:
መዝሙር ዘመጻጒዕ
15/07/11 ዓ.ም

#የዕለቱ_ምስባክ፦ 

እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኲሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ መዝ ፵፥፫

ትርጉም፦

እግዚአብሔር በሕማሙ አልጋ ሳለ ይረዳዋል
መኝታውንም ከደዌው የተነሣ ይለውጥለታል
እኔስ አቤቱ ይቅር በለኝ እላለሁ

የዕለቱ ወንጌል፦

ዮሐ ፭፥፩ - ፳፭

ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ
@aleroe
ኤልሮኢ:

፨ ተዘጋችተን እኑር፨

ርቀን ከቆምን
ከተዋሕዶ አምባ
ምግባረ ጎዶሎ
እንዳንሆን ገለባ
ለማይበጀን ዓለም
ጭራሽ ለማይረባ
በማይሆነን ሁሉ
ስንል ወጣ ገባ
ያቺ ቀን ሳትመጣ
ሳናውቅ እንደሌባ
ተዘጋጅተን እንኑር
ንስሐም እንግባ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር


@aleroe
ኤልሮኢ:
​​​​​​​​#ሕፃን_መፃጕዕ
(ውርስ ትርጉም)
ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ

“ብላቴና” የሚል፤
ከግብሩ የተነሣ የተሰጠው ቅፅል፤
በትርጓሜ ወንጌል የሚነበብ ሰፍሮ፤
መፃጕዕ መፃጕዕ ሕፃነ አእምሮ፤
ጨቅላ ነው ፤ ትክክል!
ምንም ነፍስ የማያውቅ፤
እሳትና ውሃን መለየት የማይችል።

ቢለይማ ኖሮ፤
ከእሳተ መለኮት ፤ እጁን ይልክ ነበር ፤ ለጥፊ ሰንዝሮ ?
......................................................
@aleroe
ኤልሮኢ:
​​አቤቱ ደግሰው

አቤቱ ደግ ሰው /አልቆአልና/(፪)
ከምድርም ፍቅር /ጠፍቷልና/(፪)
እንደቸርነትህ /አድነን/(፪)
በደላችንን /አትቁጠር/(፪)

የረድኤት አምላክ /ፍቅር ስጠን/(፪)
እንደ አህዛቡ/አታድርገን/(፪)
ክርስቲያን ነንና/እንዋደድ/(፪)
እባክህ አንውጣ /ከአንተ መንገድ/(፪)
አዝ = = = = =
አቤቱ ንፁህ ልብ /ፍጠርልን/(፪)
ሰውን የሚያስወድድ/ካለ እንከን/(፪)
አንደበታችንም/እንዲናገር /(፪)
ስለ ሰላም ቋንቋ /ስለ ፍቅር/(፪)
አዝ = = = = =
በእግዚአብሔር ፈቃድ /የሚመራ/(፪)
ትሩፋት ደግነት /የሚሰራ/(፪)
አንደበቱ ሁሉ /የታረመ/(፪)
ለቃለ ወንጌሉ /የደከመ/(፪)
አዝ = = = = =
ምግባርና እውነት/የተሰጠው/(፪)
እባክህን አድለን/ሁነኛ ሰው/(፪)
አንተን የሚመስል/በሕይወቱ/(፪)
ፍቅርና ትሕትና /የግል ሀብቱ/(፪)
አዝ = = = = =
የማስመሰል ፍቅር /እየበዛ/(፪)
ሰው እረክሷልና /እንደዋዛ/(፪)
ፍፁም መዋደድን /ስጠንና/(፪)
አዲስ ሰው እንሁን /እንደገና/(፪)
አዝ = = = = =
ደገኛ ሰው ማግኘት /አስቸግሯል/(፪)
እስከ መጨረሻው /ማን ይፀናል/(፪)
ምግባሩ ትክክል /እውነተኛ/(፪)
ልቡ የሚፀየፍ /ከዳተኛን/(፪)

"አቤቱ አድነኝ ደግ ሰው አልቆአልና
ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና"
መዝ፲፩፥፩

@aleroe