ኤልሮኢ:(⚜መንፈሳዊ ትርክት⚜)
………✍የእርሻ መሬት ወርሰው በጋራ
የሚሰሩ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ አንድኛው ትዳር መስርቶ
ትልቅ ቤተሰብ ሲኖረው ሁለተኛው ግን ብቻውን ነበር የሚኖረው፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ወንድማማቾቹ ከቤተሰባቸው የወረሱትን ሀብትና ንብረት በመከፋፈል በየግላቸው ለመስራት ይስማማሉ፡፡ ያለውንም ሀብት እኩል ተከፋፍለው የየግላቸው ኑሮ ይጀምራሉ፡፡ ወድያውኑ ግን ብቻውን የሚኖረው ወንድሙ ከራሱ ጋር መነጋገር ይጀምራል “ያለውን ሀብትና ትርፍ እኩል መከፋፈላችን አግባብ አልነበረም፡፡ እኔ ብቻየን ነው የምኖረው የሚያስፈልገኝ ነገር በጣም ትንሽ ነው፡፡ እርሱ ግን
ብዙ የቤተሰብ ሀላፊነት አለበት” በማለት ያስባል፡፡ እናም በጎተራው ካለው እህል አንድ ጆንያ የሚሆነውን ሁል ግዜ ማታ
ማታ እየተደበቀ ወንድሙ ጎተራ ውስጥ ማስገባት ይጀምራል፡፡
በተመሳሳይ ግዜ ሚስትና ልጆች ያሉት ወንድምም በተመሳሳይ ሁኔታ ያስባል “ይህንን ሀብት እኩል መካፈል አልነበረብንም፡፡ እኔኮ ትዳር አለኝ፡፡ ሚስቴና ልጆቼ ሁል ግዜ ከጎኔ በመሆናቸው ወደፊት በደንብ ይንከባከቡኛል፡፡ወንድሜ ግን ብቸኛ ነው፡፡ ወደፊት አጠገቡ ሆኖ የሚንከባከበው እንኳ የለውም” ሲል ያስባል፡፡ እርሱም እንደዚያኘው ወንድም በጎተራ ካለው እህል አንድ ጆንያ የሚሆነውን ሁል ግዜ ማታ ማታ እየተደበቀ ወንድሙ ጎተራ ውስጥ ማስገባት ይጀምራል፡፡ ወንድማማቾቹ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ግዜ ኖሩ፡፡ ከብዙ ግዜ ብኋላ ግን ሁለቱንም አንድ ነገር ያስገርማቸው ጀመር፡፡ በጎተራቸው ውስጥ ያለው እህል መጠን እየቀነሰ አለመሄዱ ግራ ያጋባቸዋል፡፡ ሁለቱም የገጠማቸውን ያልተለመደ ነገር ለመመርመር በየግላቸው እየጣሩ ሳለ ከእለታት አንድ ቀን ሌሊት ላይ የተለመደውን ተግባራቸውን ለመፈጸም እህል የተሞላበት ከረጢት እንደተሸከሙ በድንገት ተገናኙ ። ምንም አይነት ቃላት ሳይለዋወጡ ሸክማቸውን መሬት ላይ በመጣል በፍቅር ተቃቅፈው አለቀሱ
*
የመተሳሰብ ፍቅር… በአይምሮህ አስበህ በአንደበትህ የምታወጣው ቃል ሳይሆን፣ በልብህ የሚንፈራገጥ የማይወለድ ፅንስ ነው።
*
የአንድ አገር ልጆች ነን!
የኢትዮጽያ ልጆች!
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot

ኤልሮኢ:(⚜የዕለቱ ምስባክና ወንጌል⚜)
ጥቅምት 06/02/2013 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፺፱፥፫(99፥3)
ንሕነሰ ሕዝቡ ወአባግዐ መርዔቱ
ባኡ ውስተ አናቅጺሁ በተጋንዮ
ወውስተ አዕጻዲሁ በስብሐት እመንዎ
ምስባክ ዘቅዳሴ
እበውእ ቤተከ ምስለ መባዕየ
ወእሁብ ብፅዐትየ ዘነበብኩ በአፉየ
ዘእቤ በከናፍርየ አመ ምንዳቤየ
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ጥቅምት 06/02/2013 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፺፱፥፫(99፥3)
ንሕነሰ ሕዝቡ ወአባግዐ መርዔቱ
ባኡ ውስተ አናቅጺሁ በተጋንዮ
ወውስተ አዕጻዲሁ በስብሐት እመንዎ
ምስባክ ዘቅዳሴ
እበውእ ቤተከ ምስለ መባዕየ
ወእሁብ ብፅዐትየ ዘነበብኩ በአፉየ
ዘእቤ በከናፍርየ አመ ምንዳቤየ
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(⚜መንፈሳዊ ትርክት⚜)
#ኀጢአቷን_የምትጽፈው1ሴት
አንዲት ሴት ነበረች ኀጢአቷን የምትጽፍ
ልቧ በኀጢአት የሰከረ ለኀጢአትም ተገዚ የሆነች ይቸ ሴት የተለያየ ኀጢአት የምሰራ ነት ትዘሙታለች፣ ትዋሻለች፣ ታማለች፣ ትሰርቃለች፣ ትገድላለች
በአል ትሽራለች፣ ትሰክራለች፣ በትእቢት የተሞላች ሴት ናት ለብሷ ኀጢአት ነበር። ነገር ግን የምሰረውን ኀጢአቷን ሁሉ አየጻፈች ታስቀምጥ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን የጻፈችው ኀጢአትቷን ብታየው ስንክሳር አክሎ ተመለከተችው
ስንክሳር ማለት በ365 ቀኖች የሚውሉ የቅዱሳን ታሪክ ሰብስቦ የያዘ ትልቅ መጽሐፍ ነው። የዚች ሴትም ኀጢአትም ይህን አክሎ ነበር እንዳየችው ደነገጠችና ኀጢአቷን ተሸክማ አባት ወደ ለበት ወደ አንጾኪያ ሄደች አባ ባስልዮስን አገኘችው አባቴ በዚህ ያለው ኀጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችው አባ ባስልዮስም ይፋቅልሽ አላት ገልጣ ብታየው ሁሉ ተፍቆ አንዲት ኀጢአቷ ብቻ ቀርታ አየቻት። በጣም ከባድ ኀጢአት ነበረች ሊሰሩአት የምትከብድ ሊነግሯት የምታሳፍር ነበረች
አባቴ ይችሳ አለችው አባ ባስልዮስም ይችን ኀጢአትሽንስ ማስተስረይ የሚችል ልጄ ቅዱስ ኤፍሬም ነው ሂደሽ ለእርሱ ንገሪው አላት።አባ ባስልዮስ ይሄን ያላት ኀጢአቷን መፋቅ አቅቶት አይደለም የራሱ ክብር ከሚገለጥ የቅዱስ ኤፍሬም ክብር እንዲገለጥ ፈልጎ ነው።ደግሞም ስትመላለስ ንስሐ እንዲሆናት ጭምር ነው። እሷም አባ ባሰስልዮስ እንዳላት ቅዱስ ኤፍሬም ወዳለበት ወደ ሶርያ ሄደች በባዶ እግሯ እንቅፋቱ እየመታት እሾሁ እየወጋት እግሯ ሲደማ ልብሷን ቀዳ እየጠመጠመች ተጉዛ ከቅዱ ኤፍሬም ደረሰች። አባቴ በዚህ ያለው ኀጢአትሽ ይፋቅልሽ በለኝ አለችው ቅዱስ ኤፍሬም ግን ይሄ ለኔ አይቻለኝም ለአባቴ ለአባ ባስለዮስ እንጂ አላት ቅዱስ ኤፍሬም ኀጢአቷን መደምሰስ አቅቶት አይደለም በፈሊጥ ቀኖና ሲሰጣት እንጅ ስትመላለስ ኀጢአቷ እንዲቀልላትም ነው። ሂደሽ ለአባ ባስለዮስ ንገሪው እሱ ይደመስስልሻል አላት እሷም አግኝቸው እኮ አይሆንልኝም ብሎ ወደ አንተ ልኮኛል ሳትል እሽ ብላ መንገድ ስትጀምር እንደ ቀድሞው በህይወት አታገኝውም ሙቶ ካህናት ሊቀብሩት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይዘውት ሲሄዱ ታገኝዋለሽ ሳትጠራሪ የተጻፈው ኀጢአትሽን ከአስከሬኑ ላይ ጣይው አላት እርሷም እሽ ብላ ሄደች የቀኑ ሙቀት የሌሊቱ ብርድ እያሰቀያት ደረሰች ሙቶ ካህናት ፍትሀት እየፈቱት አየች።
የእግዚአብሔር አገልጋይ ባስልዮስ ሆይ የባሪያህን ኀጢአት ደምስስልኝ ብላ ከአስከሬኑ ላይ ጣለችው አስከሬኑም ድምጽ ወጥቶ ኀጢአትሽ ተደምስሶልሻል አላት ገልጣ ብታይ ተደምስሶላታል። አምላኳን አመሰገነች በደስታ ዘመረች
ከዚህ በኋላ ዓለምን ንቃ ገዳም ገብታ መኖር ጀመረች። እንደ ዚች ሴት ኀጢአቱን የሚያስታውስ ማን ነው? ወደ ካህን ሂዶ ንስሐ የገባስ ስንቱ ነው? ስለኀጢአቱ በረሃ የተንከራተተ ማን ይሆን? የዚችን ሴት መጨረሻ ያሳመረ የሁላችንም ጨረሻ ያሳምርልን ኀጢአቷን የደመሰሰ የሁላችንም ኀጢአት ይደምስስልን አምላኬ ሆይ ያለ ንስሐ አትጥራኝ!
#ለንሰሐ_የሚሆን_ፍሬ_አድርጉ!

ኤልሮኢ:(⚜ትርክት⚜)
……✍ከእለታት ባንዱ ቀን አንድ ታዳጊ አባቱን “የህይወት ዋጋው ስንት ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡ አባትም መልስ በመስጠት ፈንታ ልጁን እንዲህ ሲል አዘዘው፡፡ “እንካ ይህንን የድንጋይ ቁራጭ...ወደ ገበያ ውሰደው፡፡ ሰዎችም ዋጋውን ከጠየቁህ በጣቶችህ ሁለት ቁጥርን ብቻ አሳያቸው እንጂ ምንም አትናገር” አለው፡፡ ልጁም ድንጋዩን ወሰደ፡፡ ወጥቶም በገበያ መሃል ቆመ፡፡ አንዲት ሴትም መጣች፡፡ “ይህ ድንጋይ ዋጋው ስንት ነው? ብትሸጥልኝ ወስጄ ግቢዬ ውስጥ አስቀምጠዋለሁ” አለችው፡፡ ልጁም እንደታዘዘው ምንም ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳያት፡፡ እሷም አለች “ሁለት ብር?
እወስደዋለሁ!!”
ልጁም ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ በገበያ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡
አባትየውም አለው “አሁን ደግሞ ድንጋዩን ይዘህ ወደ ሙዚየም ሂድ፡፡ ዋጋውን ሲጠይቁህም ሁለት ጣቶችህን አሳይ”፡፡ ልጁም ወደ ሙዚየም ወጣ፡፡ ገዢም መጥቶ ዋጋ በጠየቀው ጊዜ ሁለት ጣቶቹን አሳየው፡፡ ገዢውም “ሁለት መቶ ብር? እወስደዋለሁ!” አለው፡፡ ልጁም በድንጋጤ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡
አባትየውም ተናገረ፡፡ “አሁን ደግሞ በመጨረሻ ድንጋዩን ይዘህ ወደ የከበሩ ማዕድናት መሸጫ ሂድ ለባለቤቱም አሳየው”
አለው፡፡ ልጁም ሄደ፡፡ ለሱቁም ባለቤት አሳየው፡፡ የሱቁ ባለቤት በመገረም “ይህ እኮ አለም ላይ እጅግ ውድ ከሆኑ የከበሩ ድንጋዮች አንዱ ነው” አለ፡፡ “ከየት አገኘኸው? ስንትስ ትሸጠዋለህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም ምንም ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳየ፡፡
የሱቁም ባለቤት አለ.... “ይህንን ድንጋይ በሁለት መቶ ሺህ ብር እወስደዋለሁ፡፡”
ልጁም በመገረም እየሮጠ ወደ ቤቱ ተመልሶ ያጋጠመውን ለአባቱ ነገረው፡፡
አባትየውም “ልጄ አሁን የህይወትህ ዋጋ ተገልጦልሃል” አለው፡፡
አየህ የመጣህበት ቦታ፣ ዘርህ፣ ሃይማኖትህ፣ የቤተሰቦችህ ሃብት፣ የተወለድክበት ቦታ ልዩነት አይፈጥርም፡፡ ዋናው ራስህን የምታስቀምጥበት ቦታ፣ ራስህን የምታገኝበት የሰዎች ስብስብ ነው፡፡ ልዩነቱ ያለው ራስህን ለመሸከም በምትመርጥበት መንገድ ነው፡፡ ህይወትህን ሙሉ የሁለት ብር ድንጋይ ዋጋ ስትሰጠው ኖረህ ይሆናል፡፡ ህይወትህን ሙሉ የኖርከው ዋጋህ ሁለት ብር ብቻ እንደሆነ በሚያስቡ ሰዎች ተከበህ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ውድ የሆነ የከበረ ድንጋይ በውስጡ ይዟል፡፡ ልዩነቱም ያለው ውስጣችን
ያለውን የከበረ ድንጋይ አይተው ዋጋ በሚሰጡን ሰዎች መሃል መገኘትን ስንመርጥ ነው፡፡ ራሳችንን በገበያ ወይም በከበሩ ማዕድናት ሱቅ የማስቀመጥ ምርጫው አለን፡፡ በሌሎች ሰዎች ውስጥ ያለውንም ውድ ዋጋ ለማየት ምርጫው የኛው ነው፡፡ ሌሎች ሰዎችም የከበረ ዋጋቸውን እንዲረዱ ማድረግ
እንችላለን፡፡ አብረህ የምትውላቸውን ሰዎች በጥንቃቄ ምረጥ፡፡ ይህ በህይወትህ ልዩነትን ይፈጥራልና፡፡

አሳስቢ
<unknown>
ኤልሮኢ:(⚜ዝማሬ⚜)
አሳስቢ
አሳስቢ ድንግል ሆይ አሳስቢ
አሳስቢ ስለኛ አሳስቢ
ስለ ምንዱባኑ ዘውትር ስታነቢ(×2)
መወለዱን እና በጨርቅ መጠቅለሉን
በግ እና ላሞቹ ሙቀት የሰጡትን
እርጉም ሔሮድስ ወጥቶ ሊገድለው ቢነሳ
ስለ እኛ ይታሰብ ያየሽው አበሳ
እርጉም ሔሮድስ ወጥቶ ሊገድልሽ ቢነሳ
ስለ እኛ ይታሰብ ያየሽው አበሳ
የግብፅ በረሀ ነባልባል አሳስቢ
ስለ ደሀ አደጎች ዘውትር ስታነቢ
ረሀቡን ጥሙን ችግሩን ሀዘኑን
ከእርሱ ጋር በስደት የደረሰብሽን
ከዓይኖችሽ መውረዱን የመረረ እንባ
የአምላክ ሆነሽ ሳለ ላንቺ ማይገባ
ረሀቡን ጥሙን ችግሩን ሀዘኑን
ከእርሱ ጋር በስደት የደረሰብሽን
ከዓይኖችሽ መውረዱን የመረረ እንባ
የአምላክ እናት ሆነሽ ላንቺ ሳይገባ
ዕጣን ነሽ ማርያም ልጅሽም ዕጣን ነው
የተመረጠ ነው እኛን ያዳነን
ኢየሱስ ክርስቶስ ምዑዝ ነው ልጅሽ
ይታሰብ ይወሳ ስደትሽ መከራሽ
#ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
አሳስቢ
አሳስቢ ድንግል ሆይ አሳስቢ
አሳስቢ ስለኛ አሳስቢ
ስለ ምንዱባኑ ዘውትር ስታነቢ(×2)
መወለዱን እና በጨርቅ መጠቅለሉን
በግ እና ላሞቹ ሙቀት የሰጡትን
እርጉም ሔሮድስ ወጥቶ ሊገድለው ቢነሳ
ስለ እኛ ይታሰብ ያየሽው አበሳ
እርጉም ሔሮድስ ወጥቶ ሊገድልሽ ቢነሳ
ስለ እኛ ይታሰብ ያየሽው አበሳ
የግብፅ በረሀ ነባልባል አሳስቢ
ስለ ደሀ አደጎች ዘውትር ስታነቢ
ረሀቡን ጥሙን ችግሩን ሀዘኑን
ከእርሱ ጋር በስደት የደረሰብሽን
ከዓይኖችሽ መውረዱን የመረረ እንባ
የአምላክ ሆነሽ ሳለ ላንቺ ማይገባ
ረሀቡን ጥሙን ችግሩን ሀዘኑን
ከእርሱ ጋር በስደት የደረሰብሽን
ከዓይኖችሽ መውረዱን የመረረ እንባ
የአምላክ እናት ሆነሽ ላንቺ ሳይገባ
ዕጣን ነሽ ማርያም ልጅሽም ዕጣን ነው
የተመረጠ ነው እኛን ያዳነን
ኢየሱስ ክርስቶስ ምዑዝ ነው ልጅሽ
ይታሰብ ይወሳ ስደትሽ መከራሽ
#ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(⚜ምክር⚜)
ዝምተኛው መነኩሴ (#ራስአገዝ)
ከዝምተኛው መነኩሴ አባ ዮስጦስ ፀሎት አንዱ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቅዱሳን በተጓዙበት ጎዳና ምራኝ" ነበር፡፡ የዚህ ጸሎት ትርጉም ቅዱስ አድርገኝ ማለት እንደነበር በህይወታቸው ፍፃሜ በሚገባ ተረድተናል፡፡ ቅዱስ እንደሆኑ ማሰብ እንጂ ቅዱስ ለመሆን ማሰብ ወይም በቅድስና መንገድ ለመጓዝ መሻትና መጸለይ መልካም ነው፤ ምክንያቱም ከፈጣሪያችን ትእዛዛትና ፈቃድ አንዱን ለመፈጸም መመኘት ነውና እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል፡፡ እግዚአብሔር በቃሉ "እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ" እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስም "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ" በማለት የቅድስናን ህይወት እንድንኖር እንደመከረን ስናስተውል ቅዱስ የመሆን ትእዛዝ እንዳለብን እንረዳለን፡፡ ስለቅድስና ሲነሳ እኛ ቅዱሳን ልንሆን ይገባል ማለቱ በራሱ ወደር የማይገኝለት ድፍረት ሆኖ ሳይሰማን አይቀርም፡፡ነገር ግን መሻቱ ሳይሆን የቅድስና ቁምነገር ነኝ አለማለቱ እና በጭራሽም ነኝ ብሎ አለማሰቡ ላይ ነው፡፡ ሰው ቅዱስ የሚሆነውም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ባሻገር በምርጫውና በፍላጎቱ ነውና ይህን የሚያስረዳን ነው።
ዲያቢሎስ ስለመረጠ ከቅድስና ጎድሏል፥ ቅዱሳን መላእክት ደሞ በምርጫቸው ቅዱሳን ሆነዋል ፡፡ሰውም እንዲሁ ነው፡፡ ስለዚህ ለቅድስና መጠራታችንን እና መታዘዛችን እንዲፈጸምልን መጸለይ መሻት መጣር ያስፈልገናል፡፡የጌታችን አማናዊ ቃሉ "ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።"ይለናልና።(ማቴ 7:7)
ስለዚህ ቅዱስ የመሆን ፍላጎት ቅዱስ ነውና በማሰባችን ወይም በመመኘታችን ድፍረት መስሎን መጨነቅ አይደገፍም፡፡ ነገር ግን በትህትና መለመንና ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ቸርነት እንደሚፈጸም ማመን ነው፡፡ ያለ እግዚአብሔር ቸርነት (ሰጪነት) በጥረታችን የምናገኘው ምንም ነገር የለም፡፡ "እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።" (ዮሐ 15:5) እንዳለ ያለእርሱ ቅዱስ መሆን ቀርቶ ቅድስናን ማሰብም እንኳን አይቻልም፤ ከእርሱጋ ግን ሁሉ ይቻላል፡፡ ወደቅድስና ከሚመሩን በርካታ ነገሮች እጅግ ጥቂቶቹ በመቀጠል ቀርበዋል፡፡
✞የእግዚአብሔርን ቸርነት እና ፍቅር ማሰላሰል
✞ህዋሳትን ኃጢአት ከመስራት መጠበቅ
✞ ለሰሩት በደል በቶሎ መፀፀት
✞ከሰው ክብርን አለመፈለግ
✞ምስጋናን አለመሻት
✞ ጥላቻንና ትችትን በፍቅር መቀበል
✞ መጸሐፍቅዱስን አዘውትሮ ማንበብ
✞ ያለማቋረጥ መጸለይ
✞በምስጢራት መካፈል
✞ትእዛዛቱን ለመፈጸም መጣጣር
✞በምክረ ንስሀ መጓዝ
✞ራስን እንደተለየ ነገር አለመቁጠር
✞ራስን መገምገም መመልከት
✞ቃለእግዚአብሔርን ማዳመጥና
✞የምንሰማዉን ቃል መፈጸም
✞ከልብ የሆነ ጾምን መጾምና መጸለይ
✞በጎ አድራጎትን መፈጸም
ማንኛውም የምንሰራው ሥራ እግዚአብሔርን ደስ እንዲያሰኝ ብሎ እንጂ አንዳች ጥቅም አገኝበታለሁ በማለት አይደለም፡፡ መሪ ምክንያቱ ፍቅር እንጂ ጥቅም መሆን የለበትም፡፡ ለቅድስና መጋደል እንጂ ቅዱስ እንደሆኑ ማሰብ መጀመር የውድቀት መጀመሪያው ሳይሆን መጨረሻ መሆኑን ማስመር ይገባል፡፡ እነኚህ በየጥቂቱ ልናድግባቸው የምንችላቸው መንፈሳዊ ተጋድሎ የሚጠይቁ ልምምዶች ናቸው ፡፡
ይቆየን!

ኤልሮኢ:(⚜ምክረ አበው⚜)
የአንድ አባት ምክር
በአንድ ወቅት በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ተገኚቼ ነበር፡፡ በዚያ ገዳም የሚኖሩ አባት የነገሩኝ ነገር ለሕይወት መመርያ የሚሆን ነው፡፡ አሁን ከደረስንበት ወቅት ጋር የሚሄድ ነውና ላካፍላችሁ፡፡
በወቅቱ እንደ ዛሬው በቤተ ክርስቲያን ላይ የፈተና ማዕበል ተነሥቶ ነበር፡፡ ያ ወቅት የፖለቲካው ማዕበልም እጅግ ያየለበት ጊዜ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምንሰጠው አገልግሎት ምን ፋይዳ ይኖረዋል? ምንስ ለውጥ ያመጣል? ችግሩ እንደሆነ እየባሰው እንጂ እየተሻለው አልሄደም፤ ታድያ ጊዜያችንን፣ ገንዘባችንን እና ዕውቀታችንን ዝም ብለን እየከሰከስን ይሆን? አሁን የኛ ልፋት የክፉ ሰዎችን ክፋት ለመሸፈን እና በክፋታቸው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ካልሆነ በቀር ችግሩን ይፈታዋል? ወዘተ፣ ወዘተ፣ ጥያቄዎች ይነሡ ነበር::
ያን ጊዜ እኒህ አባት እንዲህ አሉን፡፡
«ብዙ ልጆችን የወለደች የምትወድደው ባሏ የሞተባት አንዲት እናት ነበረች፡፡ ቤተ ዘመዶቿ ምንም ሳይራሩ ያለ ፍላጎቷ ለአንድ ክፉ ባል አጋቧት፡፡ ይህ ባል ግዴለሽ፣ ገንዘብ ወዳድ፣ ጠጥቶ ከመስከር፣ በልቶ ከመጥገብ፣ በስተቀር ሌላ ሞያ የለውም፡፡ ሲወጣ ሲገባ ይደበድባታል፡፡ እንጨት ሽጣ፣ ኩበት ለቅማ፣ እንጀራ ጋግራ፣ ጠላ ጠምቃ ያጠራቀመቻትን ገንዘብ ነጥቆ ይወስድባታል፡፡ ለዘመዶቹም ይበትነዋል፡፡
የት ትሂድ? የሠፈሩ ሕግ፣ ባህሉ እና ልማዱ፣ በሙሉ የእርሷን ሮሮ እና ልመና የሚሰማ አልሆነም፡፡ እርሱን እንደ ሕጋዊ ባልዋ ነው የሚቆጥሩት፡፡ የት ሂዳ መከራዋን ትናገር፡፡ የትስ ሂዳ ከችግሩ ትገላገል?
ይህ ክፉ ባልዋ እርሷን ብቻ ሳይሆን ልጆቿንም ያሰቃያቸው ነበር፡፡ እነርሱም በዚያ ቤት ውስጥ መከራውን እና ስቃዩን፣ ረሃቡን እና ጭቅጭቁን እየሰሙ መኖር መረራቸው፡፡ በዚያ ቤት ሰላም ጠፋ፡፡ ፍቅር ጠፋ፡፡ ምንጊዜም የሚሰማው ክፉ ነገር እና ልብ የሚያደማ ነገር ሆነ፡፡ ሰው ሁሉ ስለዚያ ቤት ያወራል፡፡ መንገድ ላይ ሲያገኛቸው ስለ ቤታቸው ይጠይቃቸዋል፡፡ እነርሱም በሃፍረት ይሸማቀቃሉ፡፡ ስለዚህም እናታቸውን ጥለው ወደ ሌላ ቦታ መሄድና ስለዚያ ቤት ከማያስቡበት እና ከማይሰሙበት ቦታ መድረስ ፈለጉ፡፡ የሚችሉትን ያህል እየሠሩ፣ ለራሳቸው የሚበቃቸውን እየኖሩ፣ መከራውን መገላገል እና እፎይ ብለው መኖር አሰኛቸው፡፡
ታድያ ይህንን ሃሳባቸውን ለአንድ ሽማግሌ ጠቢብ ሰው ነግረው ገንዘብ እና ሃሳብ እንዲሰጣቸው ፈለጉ፡፡ ሄደውም አማከሩት፡፡ ያም ሽማግሌ ሃሳባቸውን ሁሉ ከሰማ በኋላ እንዲህ አላቸው፡፡
«ልጆቼ ልክ ናችሁ ሩቅ ሀገር ሄዳችሁ፣ የምትችሉትን ያህል እየሠራችሁ፣ የራሳችሁን ኑሮ በመኖር ችግሩን ሁሉ መርሳት እና መገላገል ትችላላችሁ፡፡ ምን ያስጨንቃችኋል? ቤት ያለው እዚህ ብቻ ነው እንዴ? ሀገርስ ያለው እዚህ ብቻ ነው እንዴ? ግን አንድ ነገር አስቡ፡፡ እንዲህ ማድረጋችሁ ራሳችሁን ብቻ ከችግሩ ታወጣላችሁ እንጂ ችግሩን አትፈቱትም፤ እናንተ ችግሩን ትረሳላችሁ እንጂ ችግሩን አታስወግዱትም፡፡
«ደግሞም የእንጀራ አባታችሁ እናታችሁን የበደለውን ያህል እናንተም ትበድሏታላችሁ፡፡ እስኪ አስቡት ለዚህች ለእናታችሁ ከእናንተ በቀር የደስታዋ ምንጭ ማን ነው? ሁሉም ነገርዋ የሚያሳዝን እና የሚያስመርር ነው፡፡ እናንተ ግን የደስታዋ ምንጮች ናችሁ፡፡ የእንጀራ አባታችሁ እናታችሁን ያሳዝናታል፤ የእናንተ ጥላችኋት መሄድም ያሳዝናታል፤ እርሱ ብቻዋን እንድትለፋ ትቷታል፤ እናንተ ጥላችኋት ስትሄዱም ያለ አጋዥ ትተዋታላችሁ፤ እርሱ በመስረቅ ዘረፋት፣ እናንተም ባለ መስጠት ዘረፋችኋት፤ ታድያ ከእርሱ በምን ተሻላችሁ?
እናንተኮ ያሰባችሁት ለእናታችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ነው፡፡ እናታችሁ ስለተቸገረች አይደለም ያዘናችሁት፣ ችግሩ እናንተን ስለነካ ነው፤ እናታችሁ ስለተራበች አይደለም ያዘናችሁት ረሃቡ ስለነካችሁ ነው፡፡ በእናታችሁ ላይ የደረሰው ችግሳይሆን ስለችግሩ ከየሰው አፍ መስማት ነው የሰለቻችሁ፤ ችግሩን ለመቅረፍ አይደለም መሄድ የፈለጋችሁት፤ ችግሩን ላለማየት እና ላለመስማት ነው፡፡
ከዚያ ይልቅ ሥራ ሠርታችሁ ገንዘብ አግኙ እና ለእናታችሁ ምግብ ስጧት፤ የሚያስርባትን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፣ ልብሷን ቀይሩላት፣ የሚያሳርዛትን አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፣ ስትታመም አሳክሟት፣ የሚያሳምማትን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፤ የወግ እቃዎቹን ሰብስቡና አስቀምጡላት፤ዝክረ ታሪኳን ሊያጠፋ የተነሣውን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፤ እርሱ እያረጀ ሲሄድ እናንተ ግን እያደጋችሁ ነው፡፡ ስለዚህም እየበዛችሁ እና እየመላችሁ ሂዱና ይህንን ቀፍድዶ የያዛትን የመንደሩን ሕግ አስተካክሉት፡፡ ምናልባት የእንጀራ አባታችሁ ቢሞት ሌላ የእንጀራ አባት ደግሞ እንዳይተካ፡፡ እንደዚያ ካደረጋችሁ እናንተ የእናታችሁ ልጆች ናችሁ፡፡ ያለ በለዚያ ግን የእንጀራ አባታችሁ ተባባሪዎች ናችሁ፡፡
ሸረሪት ታውቃላችሁ፡፡ ከሰው ቤት ግድግዳ ላይ ድር አድርታ፤ ወልዳ ከብዳ ትኖራለች፡፡ ቤቱ በእሳት ሲያያዝ ግን ከቤቱ ወጥታ ቀድማ የምትሮጥ እርሷ ናት፡፡ ቤቱ የኖርኩበት ነው፡፡ ወግ መዓርግ ያየሁበት ነው፤ እሳቱን በማጥፋት አስተዋጽዖ ማድረግ አለብኝ አትልም፡፡ መሸሽን ብቻ ነው የምትፈልገው፡፡ ለራስዋ ብቻ ነው የምታስበው፡፡ ይህ ከሸረሪትነቷ የመጣ ነው፡፡
እናንተ ግን ሰዎች እንጂ ሸረሪቶች አይደላችሁም፡፡ ሰዎችን እያያችሁ ከሀገራችሁ እና ከቤተ ክርስቲያናችሁ ልትርቁ አትችሉም፡፡ አያገባንም ልትሉ አትችሉም፡፡ እሳቱን ማጥፋት ትታችሁ ከእሳት ለማምለጥ ብቻ ልትሮጡ አትችሉም፡፡ ይህንን ካደረጋችሁ ሸረሪቶች እንጂ ሰዎች አይደላችሁም፡፡» አሏቸው
ይህንን ሰምተው ልጆቹ ወደ እናታቸው ተመለሱ፡፡
እስኪ እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ የዚህች ሀገር እና የዚህች ቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ፍላጎት ምንድን ነው? ይህች ሀገር እና ይህች ቤተ ክርስቲያን ያለ ረዳት እንዲቀሩ ማድረግ አይደለምን? እናንተም እንተዋት፣ እናቁም፣ እንሽሽ ስትሉ ያለ ረዳት እያስቀራችኋት ነው፡፡ የእነርሱ ፍላጎት ኢትዮጵያን እና ተዋሕዶን ተስፋ ማስቆረጥ አይደለምን? እናንተም ተስፋ ከቆረጣችሁ ተሳካላቸው ማለት ነው፡፡ ልጆቻቸውን እያስመረሩ ማስኮብለል አይደለምን? ከኮበለላችሁ ተሳካላቸው ማለት ነው፡፡ ታሪክን፣ ቅርስን፣ ክብርን፣ ልዕልናን መመዝበር እና ማራከስ አይደለምን? እናንተም ታሪኩን፣ ቅርሱን፣ ባህሉን፣ ክብሩን ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ በራሳችሁ ዓለም ብቻ ስትቀሩ የእናንት ፍላጎት ሳይሆን የእነርሱ ፍላጎት ተሳካ ማለት ነው፡፡
ታድያ አሁን እናንተ መመለስ ያለባችሁ አንድ ጥያቄ ነው፡፡ የምትፈልጉት የጠላቶቿ ፍላጎት እንዲሳካ ነው ወይስ በመከራ ውስጥ ያለችውና ቀን የጣላት የእናታችሁ ፍላጎት እንዲሳካ ? ምረጡ፡፡
እነሆ ይህ ጥያቄ ሁሌም ይመጣብኛል፡፡
✍ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

እኩል ነው
አንድ መነኮስ አንድን ትልቅ አባት እንዲህ ሲል ጠየቀው፡- “የምተገብረውና የምኖርበት ምን መልካም ምግባር አለ ?” ሽማግሌውም እንዲህ አለ፡- “መልካም የሆነውን እግዚአብሔር ያውቃል ። ነገር ግን ከአባቶች አንዱ የአባ እንጦንስ ወዳጅ የሆነውን ታላቁን አባት እንዲህ ብሎ እንደ ጠየቀው ሰምቻለሁ፡- ‘እተገብረው ዘንድ ምን መልካም ሥራ አለ ?’ እሱም እንዲህ ሲል መለሰለት፡- ‘ሁሉም ተግባሮች እኩል አይደሉምን ? መጽሐፍም አብርሃም እንግዶችን ይቀበል እንደ ነበረና እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር እንደ ነበረ ፣ ኤልያስም ውስጣዊ ጸጥታንና ሰላምን ይወድ እንደ እንደ ነበረና እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር እንደ ነበረ ፣ ዳዊትም ትሑት እንደ ነበረና እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር እንደ ነበረ ይነገረናል ። ስለዚህ ነፍስህ ለእግዚአብሔር ብላ ማድረግ የምትወደውን ነገር አድርገው ፤ ልብህንም ንቁ አድርግ ።”
የኃጢአት ደረጃ እንደሌለው ሁሉ የመልካም ነገርም ደረጃ የለውም ። ሁሉም ሥራ እንደሆነ ሁሉ የሥራ ደረጃ የለውም ። አናጢነትም ፣ ግንበኛነትም ሁለቱም ሥራ ነው ። አንዱ ከአንዱ አይለይም ። ሁሉም ጸጋ እኩል ነው ። ክብር የሚገኘው በጸጋው ዓይነት ሳይሆን ጸጋውን ለይቶ በትጋት በማገልገል ነው ። የአካል ክፍሎችም ሁሉም እኩል ናቸው ። አንዱ ያለ አንዱ መኖር አይችልም ። እጅ የሌለው እግር መዶሻ ልያዝ ብሎ ሲጨነቅ እናያለን ። ከሁለቱ ዓይንም አንደኛውም በጣም አስፈላጊ አይደለም ፤ ሁለቱም አስፈላጊዎች ናቸው ። ከአሥር ጣቶች አንዱን ይወገድልኝ የሚል የለም ። አሥር ወልዶም አንዱን የሚጥል የለም ። መልካም ነገርም ሁሉም አስፈላጊ እስከ ሆነ ድረስ ሁሉም እኩል ነው ።
✝እንደ እነ እገሌ መሥራት ስላልቻልን ፣ እንደ እነ እገሌ ማገልገል ስላልቻልን እግዚአብሔርን ያላመለክን ይመስለን ይሆናል ። እንደ ተሰጠን በምግባርና በትሩፋት መገለጥ ይገባናል ። አንዳንድ ሰው ሸክሙ የአእምሮ ታማሚዎችን እየሰበሰበ ገላቸውን ማጠብ ነው ። አንዳንዱም ምኑንም ሳያዩት መቸገራቸው አሳዝኖት ሕፃናት ላይ የሚሠራ ነው ። ሌላውም ሠርተው የተጣሉ የአረጋውያን ነገር ግድ ብሎት እነርሱ ላይ ይሠራል ። አንዳንድ ሰው ቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሥፍራ ስለሆነች ንጹሕ መሆን አለባት ብሎ መጥረጊያ ይዞ ያጸዳል ። ሌላውም የእንግዶችን እግር በማጠብ እባረካለሁ ብሎ በትጋት ያከናውናል ። ሁሉም በእግዚአብሔር የታዘዙ ስለሆኑ የተከበሩና የሚያስፈልጉ ናቸው ። በአሥራ ዘጠኝ ሰባዎቹ ጥር ሥላሴ ዕለት ሕዝብ እያያቸው በአሰቦት ደብረ ወገግ ገዳም ወደ ሰማይ ያረጉ አባት እንደ ነበሩ እናስታውሳለን ። አባ በላይ የሚባሉት እኒህ ሰው በጊዜው የጋዜጣ ዜና ሁነው ነበር ። ተግባራቸው ግን ንጹሕ ዘማ ሳይሉ እግር ማጠብ ነበር ። ለእግዚአብሔር ክብር የማይውል ምንም ነገር የለም ።
✝ነቢዩ ሙሴ ሚሊየኖችን ነጻ አውጥቶ እየመራ ቀይ ባሕርን ተሻግሯል ፤ እኛ ደግሞ አንድን ሰው ከረሀብ ነጻ ለማውጣት እየሠራን ይሆናል ። ቅዱስ ጴጥሮስ በአንድ ቀን ስብከት ሦስት ሺህ ሰው አሳምኗል ፤ እኛ ደግሞ አንድን ሰው እያገለገልን ይሆናል ። ቅዱስ ጳውሎስ አሥራ አራት መልእክታትን ጽፏል ፤ እኛ ደግሞ የተጻፈውን እያሰራጨን ይሆናል ። ሐዋርያት እስከ ዓለም ጽንፍ ወንጌልን ሰብከዋል ፣ እኛ ደግሞ በዘመናዊ መገናኛዎች ወንጌልን እያዳረስን ይሆናል ። በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ የምናገኘው ባለንበት ስፍራ በትጋት በመንቀሳቀሳችን እንጂ በውጤቱ አይደለም ።
በምን ተግባር እግዚአብሔርን ደስ እንደምናሰኘው የምንጨነቅበት ጊዜ ብዙ ነው ። የአራት ኪሎ መንገድ የጠፋውን ሰው በቅንነት መንገድ ማሳየት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ። ቢሮአችን ውስጥ የሚመጣውን በፈገግታና በፍቅር መቀበል እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ። የአጥራችን መብራት እንዲበራ በማድረግ ሰዎችን ከእንቅፋትና ከሌባ መታደግ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ። ማንም የለኝም የሚለውን ሰው ደውለን እንዴት ነህ ? ማለት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ። ልጆቻቸውን በሞት ያጡ ወላጆችና መበለቶችን መጎብኘት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ። ተስፋ ያዘለ ቃል ለሰዎች መናገርና “አንቺ እህቴ መድረሻሽ ትልቅ ነው” “አንተ ወንድሜ መልካም ነገር አለህና በርታ” ማለት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ። ሰዎችን ስማቸውን እየጠሩ በጸሎት ማሰብ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል ።
✝ጻድቁ አብርሃም እስከ ዛሬ የምናስታውሰው እንግዳ በመቀበሉ ነው ። በመጨረሻም ሥላሴን እቤቱ አስተናግዷል ። በዚህም ሲዘከር ይኖራል ። እንግዳ መቀበል ትንሽ ነገር ይመስላል ፤ ነገር ግን በትልቅ እምነት ካደረግነው አንድ ቀን እግዚአብሔርን እቤታችን ልንቀበለው እንችላለን ። ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ይላል ።1ቆሮ. 10፡31 ። መብልና መጠጥ ለራሳችን የምናደርገው ነገር ነው ። ለራሳችን በምናደርገው ነገርም እግዚአብሔርን ማክበር ይቻላል ። “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ማለት ምን ማለት ነው ? እግዚአብሔር የሚፈልገው ራስ መውደድ አለ ማለት ነው ። መብልና መጠጥ ትንሽ ቢሆንም ለእግዚአብሔር ክብር ሊውል ይችላል ።
✝ነቢዩ ኤልያስ ጸጥታንና ሰላምን የሚፈልግ ነበር ። በዚህም እግዚአብሔርን ደስ አሰኝቷል ። እንግዳ መቀበል ጸጥታ የለውም ። አብርሃም በእንግዳ መቀበል ፣ ኤልያስ ደግሞ በጸጥታ እግዚአብሐሔርን አክብረዋል ። ጸጥታችንና ጽሞናችን ቃሉን ለማሰላሰል ፣ ለጸሎት እንጂ ሰዎችን ለመግፋት መሆን የለበትም ።
✝ንጉሥ ዳዊትም ትሑት ነበረ ፣ በዚህም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ ። ንጉሥ ቢሰጥ ሳይሆን ትሑት ቢሆን ይገርማል ። መስጠቱ ዝና ነው ፣ ትሑት መሆኑ ግን መዋረድ ነው ። ትሕትና ወዳጅን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን የሚስብ ገመድ ነው ። እንደ ተሰጠንና እንደምንችለው መልካም ነገርን በንቁ ልብ እንፈጽም ፤ ያን ጊዜ የዚህ ዓለም ክፍተት እየሞላ ይመጣል ።
ለእግዚአብሔር ብለን በምናደርገው መልካም ነገር እግዚአብሔርን ደስ እናሰኘዋለን ። የቱን መልካም ነገር ልሥራ ብለን መጨነቅ የለብንም የከበበን መልካም ሥራ ነው ። ትንሽ የሚመስለውን ስንሠራው ትልቅ ውጤት ያመጣል ።

ለመላቀቅ መልቀቅ!
የስድስት አመት ልጅ ነው፡፡ የሚኖረው ከአባትና ከእናቱ ጋር እንዲሁም ከሁለት ታላላቅ ወንድሞቹ ጋር ነው፡፡ ይህ ልጅ
ከወንድሞቹ ይልቅ ፈጣንና አንዳንዴም ከመስመር ወጣ ያለ ቅልጥፍና ያለው ልጅ ነው፡፡ አንድን ነገር ካየና ከወደደው ያንን ነገር በእጁ የሚያስገባበትን መንገድ በዚህም ሆነ በዚያ ፈልጎ ነገሩን በእጁ ያስገባል፡፡ አንድን ነገር እጁ ለማስገባት ማልቀስ ካለበት ማልቀስን፣ መጣላት ካለበት መጣላትን፣ መስረቅ ካለበት መስረቅን ከመጠቀም የሚመልሰው የለም፡፡ መኝታ ቤቱ ያለው የመጫወቻ ብዛት ይህ ነው አይባልም፡፡ ከየት ለቃቅሞ እንዳመጣው የማይታወቅ ብዙ ነገር ነው ያለው፡፡ አባቱ ይህንን
ባህሪውን ያውቃል፣ ሆኖም በተለያየ መልኩ ሊያስተምረው ከመሞከር ውጪ ምንም ሊያደርገው አልቻለም፡፡
አንድ ቀን ይህ ልጅ የማይረሳውን ትምህርት አገኘ፡፡ ከትምህርት
ቤት ተመልሶ ትንሽ ምግብ ከቀማመሰ በኋላ በረንዳው ላይ ይጫወታል፡፡ የጎረቤታቸውን በረንዳና የእነርሱን በረንዳ
የሚለየው አንድ ከብረት የተሰራ በሰው ቁመት ልክ የሆነ አጥር
ነው፡፡ ይህ ልጅ ቀና ብሎ ሲያይ የጎረቤታቸው ልጅ ሲጫወትባት
የነበረች ትንሽ ሳንቲም የምታክል መጫወቻ ያያል፡፡ በተለያዩ
ቀለማት ስለምታብረቀርቅ ልቡን ሳበችው፡፡ ዘወር ብሎ ዙሪያውን ሲመለከት ማንም ሰው የለም፡፡ ቀና ብሎ ወደ ጎረቤቱ ግቢ ሲያጤን ያ በጣም የሚፈራው ውሻም በአካባቢው የለም፡፡ በቀስታ እጁን በብረት አጥሩ መካከል አሾልኮ ያችን ያጓጓችውን መጫወቻ በእጁ ከጨበጠ በኋላ በቀስታ አጁን ውጣ ቢለው እንዴት ይውጣ! ሁለት ሶስቴ ከሞከረ በኋላ እምቢ ስላለው መደንገጥ ጀመረ፡፡ ከአሁን ከአሁን ውሻው ይመጣብኛል ብሎ ፈራ፡፡ ብዙ ከታገለ በኋላ አልቦታል፤ ከፍርሃትም የተነሳ እንደ ማልቀስ ቃጥቶታል፡፡
በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ነበር አባት የደረሰው፡፡ ዘወር ብሎ አባቱ
መምጣቱን እንዳየ መለስ ሲል ያ ክፉ የጎረቤትም ውሻ ብቅ
አለ፡፡ ልጁ በፍርሃት ማልቀስ ጀመረ፡፡ አባት፣ “ምን ሆነህ ነው?”
ልጅ፣ “እጄ አልወጣ ብሎኝ”፡፡ አባት፣ “እጅህ በሁለቱ የብረት
አጥሮች መካከል እንዴት ገባና ነው አልወጣ ያለህ?” ልጅ፣
“መዳፌን ዘርግቼ ነው ያስገባሁት፡፡” አባት፣ “ታዲያ ለምን
መዳፍህን ዘርግተህ ልክ እንዳስገባኸው አታስወጣውም?”፡፡
ልጅ፣ “መዳፌን ከዘረጋሁት የያዝኩት ነገር ስለሚያመልጠኝ
መልቀቅ አልፈልግም፡፡”
አባት፣ “ካለህበት ሁኔታ መላቀቅ ከፈለግህ የያዝከውን ነገር
መልቀቅ የግድ ነው፡፡ አለዚያ እንደተያዝክ በዚያው መቅረትህ
ነው” ብሎት ጥሎት ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር የውሻው ድምጽ
የተሰማው፡፡ ውሻው እየዘለለ ሲመጣ ያየው ይህ ልጅ ምንም
ምርጫ ስለሌለው የጨበጠውን ነገር በመልቀቅ ከተያዘበት ነገር
ተላቀቀ፡፡ የተያዝክበትና የተጨነክበት ነገር እንዲለቅህ ምናልባት መልቀቅ
ያለብህ ነገር ይኖር ይሆን? በሕይወትህ አልሄድና አልተው ያለህ ችግርህ ምናልባት አንተው መልቀቅና መተው ከሚገባህ ነገር ጋር ይገናኝ ይሆን?
ብዙዎቻችን ጨብጠን ያለቀቅናቸው ብዙ ባዕድ ልማዶች አሉን! እነሱን ሳንተው ከፈጣሪ ዘንድ ልንደርስ አይቻለንም። እናም ክርስቲያኖች መልቀቅ ያለብንን ለቀን መያዝ ያለብን ላይ እናተኩር።

teddy (2)
<unknown>
ኤልሮኢ:(⚜ዝማሬ⚜)
አትቁረጡ ተስፋ
አትቁረጡ ተስፋ የእግዚአብሄር ልጆቹ(2)
ከእናንተ አይለዩም የፍቅር ዓይኖቹ(2)
ምድርና መላዋ ናትና የእግዚአብሄር
በሰማያት አለ በቀላይ በባህር
በጥልቁ እንኳን ቢሆን ከእናንተ ጋራ ነው
ወገኖቼ አትስጉ ሰልፉ የእግዚአብሄር ነው
ጌታ አይረሳምና የእጆቹን ስራ
ይኸው በልጆቹ አይተናል ሲሰራ
አትቁረጡ ተስፋ የእግዚአብሄር ልጆቹ(2)
ከእናንተ አይለዩም የፍቅር ዓይኖቹ(2)
ምድርና መላዋ ናትና የእግዚአብሄር
በሰማያት አለ በቀላይ በባህር
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
አትቁረጡ ተስፋ
አትቁረጡ ተስፋ የእግዚአብሄር ልጆቹ(2)
ከእናንተ አይለዩም የፍቅር ዓይኖቹ(2)
ምድርና መላዋ ናትና የእግዚአብሄር
በሰማያት አለ በቀላይ በባህር
በጥልቁ እንኳን ቢሆን ከእናንተ ጋራ ነው
ወገኖቼ አትስጉ ሰልፉ የእግዚአብሄር ነው
ጌታ አይረሳምና የእጆቹን ስራ
ይኸው በልጆቹ አይተናል ሲሰራ
አትቁረጡ ተስፋ የእግዚአብሄር ልጆቹ(2)
ከእናንተ አይለዩም የፍቅር ዓይኖቹ(2)
ምድርና መላዋ ናትና የእግዚአብሄር
በሰማያት አለ በቀላይ በባህር
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
"ከንስሐ አባትህ ጋር ስትሆን ጥያቄህን እንጂ ውሳኔህን አታቅርብላቸው፤ በልብህ ካሰብከው ጋር እንዲስማሙ ሳይሆን በሀሳብህ ላይ ሀሳባቸውንና ምክራቸውን እንዲሰጡህ አድርግ።"
#ብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሣዊ
@aleroe
#ብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሣዊ
@aleroe
ኤልሮኢ:(⚜የዕለቱ ምስባክና ወንጌል⚜)
ጥቅምት 22/02/2013 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፻፳፩፥፯(121፥7)
ይኵን ሰላም በኃይልከ
ወትፍሥሕት ውስተ ማኅፈደ ክበዲከ
በእንተ አኀውየ ወቢጽየ
ምስባክ ዘቅዳሴ
አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዓ ቃሎሙ
ውስተ ኲሉ መድር ወፅአ ነገሮሙ።
ወእስከ አጽናፈ አለም በጽሐ ነቢቦሙ።
ቅዳሴ
ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ)
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ጥቅምት 22/02/2013 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፻፳፩፥፯(121፥7)
ይኵን ሰላም በኃይልከ
ወትፍሥሕት ውስተ ማኅፈደ ክበዲከ
በእንተ አኀውየ ወቢጽየ
ምስባክ ዘቅዳሴ
አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዓ ቃሎሙ
ውስተ ኲሉ መድር ወፅአ ነገሮሙ።
ወእስከ አጽናፈ አለም በጽሐ ነቢቦሙ።
ቅዳሴ
ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ)
@aleroe
ለሀሳብ አስተያየት @AleroeBot
ኤልሮኢ:(⚜ትርክት⚜)
…………✍በአንዲት ትንሽዬ ከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ አይነስውር ሰውዬ ነበር።
ይህ አይነስውር ሰውዬ መሬት ሲጨላልም ወደ ከተማው መውጫ ያለው ወንዝ አከባቢ እየሄደ ንፁህ አየር መውሰድ ያዘወትር ነበር። ታድያ በዛ በጨለማ ሲሄድና ሲመለስ በእ የመብራት ፋኖስ ይዞ ነው። ሁልጊዜ እንዲህ ያደርጋል። ከእለታት በአንዷ ምሽት 3 ወጣቶች እርስ በርስ እየተቀላለዱ
ሲያልፉ አይነስውሩ ሰውዬ ከነፋኑሱ ያገኙታል። "አንተ አይነስውር ነህ፤ እንደሚያይ ሰው ፋኖስ ይዘህ ትዞራለህ
እንዴ" ብለው ተሳለቁበት፣ ሳቁበት።
ሰውዬውም በእርጋታ እንዲህ አላቸው፡-
"ልክ ናቹ፤ እኔስ አላይም ነገር ግን ፋኑሱ ይጠቅመኛል፤ ምክንያቱም ሰዎች በጨለማው ምክንያት ሳያዩኝ ከገፈተሩኝ
በህዋላ ከምናደድባቸው ፋኑሱ ይዤ ባበራላቸው ለሁለታችን ይጠቅማል" ብሏቸው ሄደ። ወጣቶቹም በሰውዬው ቅን
አስተሳሰብ ተደነቁ። "ማየት ያለብን በህሊናችን ነው፤ ለሰዎች የምናደርገው በጎ ነገር ራሱ ተመልሶ በእጥፍ ይከፍለናልና።"

እናት ሰንበት ትምህርት ቤት
………አንዳንድ ጊዜ ‹ትምህርት ቤት› የሚለው ሐረግ ሰንበት ትምህርት ቤትን
አይገልጻት ይሆን ብዬ አስባለሁ፡፡ ‹ሰንበት ትምህርት ቤት› ከምትባል ይልቅ
‹የሰንበት ቤተሰብ ቤት› ብትባል ይሻል ይኾን?
የቤተሰባዊነት ስሜት ለአገልጋዮች እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ሐዋርያት እርስ
በእርሳቸው ‹ወንድሞች› ይባባሉ ነበር፡፡ ወንድሞች መባባላቸው ከአንድ እናትና
አባት ተወልደው አይደለም፤ እንዲሁ አገልግሎት የጋራ እናታቸው ሆናቸው ነው
እንጂ፡፡ የሳቱትን እንኳን ‹ቢፅ ሐሳውያን (ሐሰተኛ ወንድሞች)› ይሉ ነበር፡፡
ይህንን ቤተሰባዊነት ለማጉላት እኔ ባደግኩባት ሰንበት ትምህርት ቤት የቤተሰብ
ጉባኤ የሚባል ጉባኤ አለ፡፡ በዚያ ቀን የሚከወነው እንደ ቤተሰብ ቤተሰባዊና
መንፈሳዊ ወጎችን እንዲሁ ሲጨዋወቱ መዋል ነው፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤቱ
ሰብሳቢ ‹ሰብሳቢ› ሳይሆን ‹አባት› ይባላል፡፡ ኹሉም ‹አባታችን› እያለ
ይጠራዋል፡፡ የቀድሞ ሰብሳቢ ‹አያታችን› ይባላል፡፡ ከእርሱ የቀደመው ‹ቅድመ
አያታችን› ይባላል፡፡ የአመራር አባላት ወንዶቹ ‹አጎቶች› ሴቶቹ ‹አክስቶች›
ይባላሉ፡፡ ሌላው አባል በሙሉ ‹ልጅ› ነው፡፡
ይህ ስሜት ኹሉም ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ አለ፡፡
ሰንበት ተማሪ ዘመደ ብዙ ነው፡፡ አያድርስበትና አንድ ችግር በእርሱ ወይም
በቤተሰቡ ላይ ቢደርስበት የእናት ሰንበት ትምህርት ቤቱ ወንድሞቹና እኅቶቹ
ነቅለው ቤቱ ይሔዳሉ፡፡ ታምሞ ከሆነ ቤቱን ሞልተው ፣ ውዳሴ ማርያምን
አድርሰው ዘምረው ያበረቱታል፡፡ ኃዘን ገጥሞት ከኾነ እስኪጽናና ከቤቱ
አይለዩም፡፡ ዕድርተኛው ‹ጉድ› እስኪል ድረስ ድንኳን የሚተክሉት ፣ ወንበር
የሚደረድሩት ፣ ግቢ የሚያጸዱት ፣ ዕቃ የሚያጥቡት የሰንበት ትምህርት ቤት
እኅትና ወንድሞቹ ናቸው፡፡
ባለቤቱ እንዲደረግ የፈለገውንና የሚያስፈልገውን በማድረግ ልቡን በእርካታ
ይሞሉታል፤ እንደ ልቡ ይሆኑለታል፡፡ የዮናታን ጋሻጃግሬ ለዮናታን እንዳለው
‹‹እንዳንተ ልብ ሁሉ የኔም ልብ እንዲሁ ነው›› ብለው የልባቸውን መሻት
ከወዳጃቸው ልብ መሻት ጋር አንድ ያደርጉታል፡፡ (1ሳሙ.14፡7)፡፡ እርሱ ሲያዝን
የእርሱ አፍ ሳይኾን የራሳቸው ልብ ይነግራቸዋል፤ ‹እንደርሱ ልብ ሁሉ የእነርሱም
ልብ እንዲሁ ነውና›፡፡
ሰርግ ካለበትም የሥጋ ቤተሰቡ አብዝቶ መጨነቅ የለበትም፡፡ በጎደለው ኹሉ
የመንፈስ ቤተሰቦቹ አሉለት፡፡ ምናልባትም ልጅየው ብዙ ጊዜውን ለሰንበት
ትምህርት ቤት በመስጠቱ የሚበሳጭ ቤተሰብ ቢኖረው እንኳን ከእንደዚህ
ዓይነት ገጠመኝ በኋላ ኹሉም ነገር ይለወጣል፡፡ የወንድሞቹና የእኅቶቹ
መተሳሰብ፣ የሚቃወም ልቡናን ኹሉ በፍቅር ሊያነድ የተቀጣጠለ ስንዱ እሳት
ነው - ‹‹ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል›› እንዲል፡፡ (1ጴጥ. 4፡8)፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤት ወንድሞች እውነተኛ ወንድሞች ናቸው - በፍቅር
የተገመደ ትሥሥር ያላቸው፡፡ ወንድማቸው ሲበርደው እነርሱ የሚንቀጠቀጡ ፣
ሲርበው አንጀታቸው የሚላወስ ፣ ሲከፋው አብረው የሚያለቅሱ ውድ ወንድሞች
ናቸው፡፡ ለእኅታቸው ድጋፍን ከመስጠት የማይሰንፉ ፣ ታናሻቸውን በትምህርት
የሚረዱ ፣ ለጥያቄዎቹ የማይሰለቹ ልበ ወርቆች ናቸው፡፡ አብረው መብላት ፣
መጎራረስ ፣ አብረው ማደግ ፣ አብረው መሳቅ ፣ አብረው መጫወት ፣ አብረው
መሔድ ፣ አብረው ማንበብ ፣ አብረው መኖር የሚያጓጓቸው የኁባሬ ስልቻዎች
ናቸው፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤት ወንድሞች በሰንበት ትምህርት ቤት እንጂ
በየትም በሌላ ቦታ አይገኙም፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤት ወንድሞች እንደ ዮናታን ናቸው፡፡ ዳዊት ጎልያድን ገድሎ
በዮናታን አባት በንጉሡ በሳኦል እልፍኝ ከተገኘና የራሱን ማንነት ለንጉሡ ካስረዳ
በኋላ ‹‹የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሠረች፥ ዮናታንም እንደ ነፍሱ
ወደደው›› (1ሳሙ.18፡1)፡፡ ዮናታን ዳዊትን እንደ ነፍሱ ስለ ወደደው አባቱ ሳኦል
በጠላትነት ሲነሣበት እንኳን እንደ ነፍሱ የወደደውን ዳዊትን ከአባቱ በምክሩ
ይደብቀው ነበር፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤት እውነተኛ ወንድሞችም እንዲሁ
ናቸው፡፡ ዳዊት የተባሉ አዳዲስ አባላት ጎልያድ የተባለ ከአገልግሎት መራቅን
ድል ነሥተው ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት ሲመጡ ነፍሳቸው በዳዊቶቹ ነፍሶች
ትታሰራለች፣ እንደ ነፍሳቸውም ይወዷቸዋል፡፡ ምንም ዓይነት ‹ሳኦል› ቢመጣ
ከዳዊቶች ጎን ይቆማሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት ወንድሞች በሰንበት ትምህርት ቤት
ወይም የሰንበት ትምህርት ቤት ልብ ባላቸው ዘንድ እንጂ በየትም በሌላ ቦታ
አይገኙም፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤት እኅቶች ትሕትና የቀበራቸው ፣ ሃይማኖት ያስጌጣቸው ፣
ቅንነት ያቆነጃቸው ፣ የፍቅር ኩራዞች ናቸው - ፀሐዩአ ለጠፋባት የሴትነት ዓለም
ክራቸው እየተቃጠለ ብርሃንን የሚለግሱ ፣ እየጨሱ መቅረዝ የኾኑ፡፡
ወንድሞቻቸውን የሚያከብሩ ፣ ለሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን የሚታመኑ ፣ ካህናትን
ሲያዩ ልባቸው በሚገባ ፍርሐትና አክብሮት የሚርድ የሀገር ኩራቶች ናቸው፡፡
ወንድሞቻቸውን አጥብቀው የሚሹ የቤተሰቡ የወርቅ ምሰሶዎች እነርሱ ናቸው፡፡
በብዙ ትግልና ልፋት ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት ይመጣሉ፤ ሰማይ የሚያክል
ጫናን አገር የሚያክል ጾታዊ ተፅዕኖን ተቋቁመው ያገለግላሉ፡፡ የሰንበት
ትምህርት ቤት እኅቶች በሰንበት ትምህርት ቤት እንጂ በየትም በሌላ ቦታ
አይገኙም፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤት እኅቶች እንደ አቢጊያ ናቸው፡፡ የናባል ሚስት አቢጊያ
ባሏ ንጉሡን እስከ መዳፈር የደፈረ እጅግ አስቸጋሪ ሰው ነበር፡፡ ንጉሥ ዳዊትም
እርሱን ሊገድለው ሲሔድ ብልኋ አቢግያ በመንገድ ጠብቃ ንጉሡ ይቅርታ
ያደርግለት ዘንድ በብዙ ትሕትናና እጅ መንሻ ለመነችው፡፡ ዳዊትም አቢግያን
አደነቀ፤ ‹‹ወደ ደም እንዳልሄድ፥ በእጄም በቀል እንዳላደርግ ዛሬ የከለከለኝ
አእምሮሽ የተመሰገነ ይሁን፥ አንቺም የተመሰገንሽ ሁኚ›› አላት፡፡ (1ሳሙ.25፡
33)፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤት እውነተኛ እኅቶችም እንደ አቢጊያ ናቸው፡፡ ሰውን
ከክፋት በመመለስ ፣ በእርጋት ፣ በትሕትና ፣ በአስተዋይነት አዕምሮአቸው
የተመሰገነ፡፡ ሰውን ጎትተው ወደ ስሕተት የሚከቱ አሰናካይ ሴቶች በበዙበት
በዚህ ዘመን ብልጭልጭን ንቀው የሚስተውን የሚመልሱ የተመሰገኑ ናቸው፡፡
ስለ ወንድሞቻቸውና ስለ እኅቶቻቸው አብዝተው የሚጨነቁና የሚጸልዩ ፣ ጸብን
ለማራቅ ዘወትር በብልኃት የሚመክሩ ፣ ‹ልታይ› ከሚሉት ጀርባ የሚገኙ ባለ
ምስጉን አዕምሮዎች ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነት እኅቶች በሰንበት ትምህርት ቤት

እኔ በግሌ ልጅ እያለሁ እነዚህ እኅቶችና ወንድሞች ዕቅፍ አድርገው ተቀብለውኝ
ወንድማቸው ባያደርጉኝ ኖሮ አሁን ያለው ማንነቴ አይኖርም ነበር፡፡ ለመጀመሪያ
ጊዜ ሰንበት ትምህርት ቤት ስገባ በፍቅር ሸማ ፣ በመውደድ ብሉኮ ያከናነቡኝን ፣
በጉጉት የተቀበሉኝን ውድ የኆኅተ ብርሃን ቤተሰቦቼን የልጅነት አዕምሮዬ
አይዘነጋቸውም፡፡ እነዚህን ወንድሞችና እኅቶች በሰንበት ትምህርት ቤት እንጂ
በሌላ በየትም ቦታ እስካሁንም አላገኘኋቸውም፡፡
ሰንበት ተማሪ ሌላ ሰንበት ተማሪን በመንገድ ሲያገኝ ወይም በአጋጣሚ
ሲተዋወቅ የጠፋ የእናቱን ልጅ እንዳገኘ ልቡ በፍቅር ስስት ይቃጠላል፡፡ ኹለት
የማይተዋወቁ ሰንበት ተማሪዎች ቢገናኙ ለመግባባት ጊዜ አይወስድባቸውም፤
ልቡናቸው ቀድሞ ይግባባል፡፡ ስማቸውን እንኳን ሳይተዋወቁ ስለ መስቀል ጥናት
፣ ስለ ጥምቀት ፣ስለ ደብረ ታቦር ፣ ስለ ፍልሰታ ፣ ወዘተ… ያወራሉ፡፡ አባባሉስ
ቢሆን ‹‹አንድ ዓይነት ላባ ያላቸው

⚜እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ዝክረ ጥንተ ስቅለት አደረሳችሁ አደረሰን⚜
...." እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።" ዮሐ ፮፡፵፯.....
....."አንተ ለእኔ መሸሸጊያዬ ነህ፥ ከጣርም ትጠብቀኛለህ፤ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ።" መዝ ፴፩:፯.....