"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ኤልሮኢ:

#አስተውል

☞ ከጎንህ ያለችው ሚስትህ ~ የላጤዎች ሁሉ ምኞት ናት፤
☞ የከዳሀው ልጅህ ~ መውለድ የማይችሉ ሁሉ ምኞት ነው፤
☞ ደሳሳ ጎጆህ ~ ቤት የሌላቸው ሁሉ ምኞት ነች፤
☞ አድካሚ ስራህ ~ ስራ የሌላቸው ሁሉ ምኞት ነው፤
☞ ትንሿ ሀብትህ ~ ምንም ሀብት የሌላቸው ሁሉ ምኞት ነች፤
☞ ውድ የሆነው ጤናህ ~ አልጋ ላይ የሚማቅቁት ሁሉ ምኞት ነች፤
☞ ትንሿ ፈገግታህ ~ የተጨነቁ ያዘኑት ሁሉ ምኞት ነች፤
☞ ሚስትህ የደበቀችልህ ገበና ~ የተጋለጡት እና
የተዋረዱት ሁሉ ምኞት ነች፤
☞ በነፃነት እንደፈለክ የምትንቀሳቀሰው ~ በእስር የሚሰቃዩ መንቀሳቀስ የማይችሉት ሁሉ ምኞት ነች፤
***፦እስኪ መዳፍህን ተመልከት በብዙ ስጦታ በረከት ተሞልቷል፤ ነገር ግን የፈጣሪ ስጦታ በጣምምም በዛና የተሰጠንን ሁሉ ማየት ተሳነን፤
የሚያይ አይን ሳይሆን የሚያስተውል ልቦና ይስጠን
እና እግዚአብሔርን አመስግን ።

@aleroe
ኤልሮኢ:(ስነ ፅሁፍ)

#በምህረቱ መራኝ

ትላንት ነበርኩኝ እያለው የሌለው
እንዳማረ ተክል ፍሬ እንደሌለው
ደስታዬም ነበረ ለሞቴ መንገዱ
ህይወቴም ሚመስሉ አንዳች ያልተጎዱ
እውነታው ባይገባኝ የመኖሬ ምክንያት
እጆቼን ዘረጋው እምባዬም ፈሰሰ
ጉልበቴም ታዘዙ ለዳንስ እንዳልተነሱ
ልሳኔም በቃሉ ይቅርታን ለመነ
የወደቀልኝን እርሱን አገነነ
መውደቄን ተረድቶ የማይለኝ ችላ
አምላከ ብርሃን ህይወቴን አጎላ
በመሃሪነቱ ምህረቱን ሽሮኝ
ለህይወቴ ፍዳ መፍትሄው ሆነኝ



___
👉👉👉@aleroe👈👈👈
ኤልሮኢ:(መዝሙር)

ገብርኤል ነው

ገብርኤል ነው አምላክ የሾመው(፪)
አናንያን አዛርያን ሚሳኤልን ከእሳት ያዳነው

ናቡከደነፆር አንተን በግልፅ አይቶ
ለእግዚአብሔር ሰገደ ያንን ምስል ትቶ
ሐሰትም እነደሆን ይመስክሩ ሦስቱ
ከዚያች ከባቢሎን (፪) የወጡት ከሳእቱ
አዝ = = = = =
ከዓለመ መላእክት ከቅዱሱ ቦታ
የሰውን ልጅ መረጥክ ልትረዳ ጠዋት ማታ
አንጌቤናይቷ ቅድስት ኢየሉጣ
ትመስክር ስላንተ(፪) ከነልጇ ትምጣ
አዝ = = = = =
ልመስክር ስላንተ ነህና ሕይወቴ
ገብርኤል (፪)ሰመረ ስለቴ
የአናብስቱን አፍ የዘጋኸው መላክ
ገብርኤል አንተ ነህ (፪)በእኛ ሁሉ የታመንክ


ቀሲስ ዘበነ ለማ


@aleroe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤልሮኢ:

ለራስህ ነው

አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ! ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡
ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡ ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡ እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ

@aleroe
ኤልሮኢ:

#ነበርኩ_መች_ያድናል


ሀጢያትን ስትሰራ አምላክን እረስተህ
ቅዱሱን ሰውነት በሀጢያት አርክሰህ
ትእዛዝን ሳትፈጽም መልካምን ሳትሰራ
ዘይት ሳታዘጋጅ መብራትህ ሳይበራ
በተጠራህ ጊዜ መላከሞት ሲመጣ
ለማያልፈው አለም ሲወጣልህ እጣ
ለሚዛን ስትቀርብ አገልጋይ ነበርኩኝ እያልክ መናገሩ
መዝሙር ዘምሬያለው ሄጃለው ከበሩ
ብሎ መከራከር ያኔ መች ይጠቅማል
ይዞ መገኘት ነው ነበርኩ መች ያድናል!!!!
____________________

@aleroe
ኤልሮኢ:

​​አድርገህልኛልና በቸርነትህ

አድርገህልኛልና በቸርነትህ
አመሰግንሃለሁ እልል፪
ለዓለመ ዓለም አማኑኤል
እገዛልሃለሁ መድኃኔዓለም፪

ቀኑ ጨልሞብኝ ዙሪያው ገደል ሆኖ
የችግር አረንቋ ፊቴ ተደቅኖ
ረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ
ፍጽሞ አራቅህልኝ የልቤን ትካዜ
አዝ = = = = = =
አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያዬ
ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻዬ
እንደማትተወኝ አሁን አውቄአለሁ
ካለኝ ነገር ይልቅ በአንተ ታምኛለሁ
አዝ = = = = = =
ጥቂቷን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ
የምመልስልህ ባለገኝ ሥጦታ
በቀንም በሌትም ሁሌ ለሚያበራ
መንክር ለባሕርይህ ዕጽብ ለአንተ ሥራ
አዝ = = = = = =
አምላክ ሆይ ምሥጋና ለአንተ ይገባሃል
ለምስኪኗ ጎጆ በረከት ሰጥተሃል
ደሃ ነኝ አልልም ሀብቴ አንተ ነህና
ማሰሮዬ ሞልቷል ላይጎድል እንደገና



<< አድርገህልኛልና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ >>
መዝ፶፪፥፱

@aleroe
ኤልሮኢ፡
አድዋ

………………
ምንሊክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ
በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣሊያን አበሻ እንዳይደርስ
ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ሁዋላ አይገኝ
አባተ በመድፉ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጎጃሙ ንጉሥ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሀን
ዳዊቷን ዘርግታ ሰምዐኒ ስትል
ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል
ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል
እንደ በላዔ ሰብእ እንደመቤታችን
ሲቻለው ይምራል የኛም ጌታችን።

@aleroe
ኤልሮኢ:(መዝሙር)
#ንጹም_ፆመ

ንጹም ፆመ ወናፍቅር ቢጸነ
ወንትፋቀር(፬) ንትፋቀር በበይናቲነ ኧኸ(፫)
#ትርጉም
ፆምን እንጹም ባልንጀራችንን እንውደድ
እርስ በራሳችንም እንፋቀር


@aleroe
ኤልሮኢ:
፨መርሳት፨

በአንድ ወቅት የግብጹ ሊቀ ጳጳስ ብጹኡ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ እያስተማሩ ባሉበት ወቅት በዙ ጥያቄዎች በጹሑፍ ይደርሳቸው ነበር። ታዲያ ከነዛ ጹሑፎች መካከል አንዱ እንዲ ይላል
... አባቴ እኔ ታላቅ የመርሳት ችግር አለብኝ ያደረኩትን የሰማሁትን ነገሮች በሙሉ እረሳቸዋለው እና አባቴ ምን እንደማደርግ ይምከሩኝ ነበር የሚለው። ብጹእነታቸውም ልጄ መምከሩንስ እመክርሃለሁ ምን ማድርግ እንዳለብህ እነግርሃለሁ ግን እንዳትረሳው እፈራለሁ አሉት ይባላል።
ቃለ እግዚአብሔር ስንሰማ በማስተዋል ልቦናችንንም ሰብስበን ሊሆን ይገባል።
በነገሮችም ሁሉ አስተዋዮች ልንሆን ይገባል።በዚህም ማስተዋል እና ጥበብን ወደሚሰጥ አምላክ አጥብቀን ልንማጸን ይገባናል።

@aleroe
ኤልሮኢ:

ሩጫ ✞............🏃🏃🏃🏃

ማልያህን ታጠቅ
ቀበቶህን አጥብቅ
ጫማህን አጠባብቅ
መስመርህን ጠብቅ
አትይ ወደ ኋላ
ተብሎ ተነግሮን
ጀምረን ሩጫ
ለመቀበል ዋንጫ
እኛ ዞርን ስናይ
እነሱ ፈጠኑ
ከሽልማት ጌታ ጽዋም ተቀበሉ።

@aleroe
ኤልሮኢ:(መዝሙር)

አዝናለሁ አለቅሳለሁ

አዝናለሁ አለቅሳለሁ
ስለ በደሌ ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ
አዝናለሁ አለቅሳለሁ
ስለ ጥፋቴ ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ
ነገር ግን መሐሪ ነህና
እንደምታድነኝ አምናለሁ

ሥጋዬ ለራሱ እያታለለኝ(፪)
ሁሉን በመፈለግ ወሰደና ለጥፋት ሰጠኝ(፪)
አዝ = = = = =
ከመሬት ተገኝታ እስክትገባ
በከንቱ አስቀረችኝ አምላኬ ሆይ ሥጋ ሰገብጋባ(፪)
አዝ = = = = =
ትቻት መምጣቴ ነው አፈር ሥጋዬን
እንድትቀበላት አምላኬ ሆይ አደራ ነፍሴን(፪)

@aleroe
ኤልሮኢ:
. #ጸሎት

#ጸሎት ያቆመች ነብስ እየሞተች ያለች ነች።
#ለሊት ተነሥቶ በጸሎት ጠላቱን ያልመታ ጥዋት ቀኑን ሙሉ ሰይጣን ሲመታው (ሲቀጠቅጠው) ይውላል።
#ክርስትያን ተንበርክኮ ማንበርከክ ይችላል። የማይጸልይ ከሆነ ደግሞ ገና ሳይዋጋ ይንበረከካል።
#ሌሊት በጸሎት ያልወረድክበት ሰይጣን። ቀኑን ሙሉ ሲያገሳብህ ይውላል።
#ከእግዚአብሔር ጋር አንዲት ቀን ሳታሳልፍ ከዋልክ፦ ከመልካሙ
ዘመንህ ውስጥ አንዲቷ ቀንህ በከንቱ እንዳባከንካት ቁጠራት።
#እግዚአብሔርን በጸሎት የማይለምን፦ ዘወትር የሰውን ፊት የሚያይ ተለማማጭ ሆኖ ይኖራል።
#ከእግዚአብሔር ጋር መልካም ጊዜን ማሳለፍ፦ገንዘብህን ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኝ ንግድ (ኢንቨስት) ከማድረግ በላይ እጅግ ጠቃሚ ነው።


@aleroe
ኤልሮኢ:
01/07/09

መዝሙር መሐሩነ
#ቅድስት

#በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ፡፡

#የዕለቱ ምስባክ፦ መዝ ፺፭፥፭

እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ
አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ
ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ

#ትርጉም
እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ፈጠረ
እምነትና በጎነት በፊቱ ናቸው
ቅድስና እና የክብር ገናንነት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።

የዕለቱ ወንጌል፦

ማቴ ፮፥፲፯ - ፳፭
ቅዳሴ፦ ዘኤጲፋንዮስ

👉 @aleroe
ኤልሮኢ:
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ዛሬ በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ላጡት ወገኖቻችን እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን። ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እንመኛለን።
💫💫💫💫💫💫💫💫💫
ኤልሮኢ:
#ስጋ_ነው_ምርኩዜ


ስጋዬ ወፍሮ አፌ ክፉ ደፍሮ
ሓሰትን መስክሮ እውነት ቅሉን ሽሮ
እውነት ተሸሸጋ ማን እውነት ሊያወጋ
ስለ ክፉ ስጋ።
ስለ ክፉ ስጋ ነፍሴ ስትወጋ
የአንደበቴ ችቦ የአንደበቴ ሰንጋ
ነፍሴ ስትቃትት የስጋ ጦር ወግቷት
ቀንም ሌሊትም ቁስሉ ሲያሰቃያት
ጭንቅ ጥብብ አለች ቀኑ ጨልሞባት
የምታውቀው ቤቷ ተዘግቶባት
ስጋ ሲበድላት በሐዘን በትካዜ
በሐሰት ባለሟል በስጋ ምርኩዜ
እኔንም ተረድታ በእምነት መደብዘዜ
በህይወት ልታልፍ ልትጓዝ በግዜ
ነፍሴ የተዘጋጀች ልታቀርብ ኑዛዜ።
____________________

@aleroe
ኤልሮኢ:(መዝሙር)

#የሚጠብቀኝ አይተኛም

የሚጠብቀኝ አይተኛም(×2) አያንቀላፋም(×2)
ቤት ባይኖረኝም
በደጅ ባድር
ቀንና ሌሊት ከኔ አይርቅም
ድምፀ አራዊት የሌሊት ግርማ
ወደ እኔ አይገቡም ድምፅህ ሲሰማ
መሰናከልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሀይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ሀይል አያስፈራኝም
ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በፅድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ
የሰማዩን ጥል እታገሳለሁ
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለሁ
ሌሊት በድብቅ ለሚጎበኙ
ለፃድቃኑ ግን አምላክ ይስጥልኝ
እንቅልፌን ባርኮ የሰጠኝ ጌታ
በዓለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የዕለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍፁም
ምስጋና ላቅርብ እስከዘላለም

#ዘማሪ ይልማ

@aleroe
ኤልሮኢ:

……ሰውየው አስር ክፍል ቤት ሠርቶ ብቻውን ሲኖር አንድ
ቀን በሩ ተንኳኳ ሲከፍት ጌታ ነው፡፡ "ውይ አምላኬ
ጌታዬ አንተ እኔ ቤቴ መጣህ?" ብሎ በደስታ
ተቀብሎት አንድ ክፍል ቤት ሰጥቶት መኖር ጀመሩ፡፡
በሌላ ጊዜ በሩ ተንኳኳ፣ ሲከፍት ሰይጣን ነው፡፡
ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ
ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል?" አለው፡፡
ጌታም "ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም " አለው፡፡
ሰውየውም ተሰምቶት ሁለት
ክፍል ቤት ለጌታ ጨምሮለት እርሱ ሰባት ክፍል ይዞ
መኖር ቀጠሉ፡፡ በሩ ተንኳኳ ሲከፈት ሰይጣን ነው፡፡
ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ
ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል? " አለው፡፡
ጌታም " ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም " አለው፡፡
ሰውየውም ተሰምቶት ከጌታ
ጋር እኩል ለእኩል ተካፈለ፡፡
ነገር ግን ቤቱ ከቀድሞ ይልቅ ተንኳኳ ፡፡ አዝኖም
ይዘጋና ጌታ ሆይ አለው፡፡ ጌታም የቀድሞውን መልስ
ሰጠው፡፡
በዚህ ጊዜ ሰውየው ለራሱ አንድ ክፍል ቤት ይዞ
ዘጠኙን ክፍል ቤት ለጌታ ሰጠው፡፡ ነገር ግን
ከቀድሞው ይልቅ በጣም ተንኳኳ፡፡ ቢከፈት ሰይጣን
ነው፡
በሩን ይዘጋና ወደ ጌታ ሄዶ " ጌታ ሆይ ምሥጢሩ
ምንድን ነው? " አለው፡፡ "ጌታ ግን ቤቱ የአንተ እንጂ
የእኔ አይደለም "አለው፡፡
በዚህ ጊዜ ዐሥሩንም ክፍል ለጌታ አስረከበ፡፡ ጌታም
አንድ ክፍል ቤት ለሰውየው ሰጠው፡፡ በሩም ተንኳኳ
፡፡ ጌታም ሊከፍት ተነሣ፡፡ ሲከፍት ሰይጣን ነው፡፡
ሰይጣንም " ይቅርታ የአንተ ቤት መሆኑን አላወቅሁም
" ብሎ ሄደ፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ መንኳኳት ቆመ፡፡
ሁሉንም የሕይወታችንን ክፍል ለጌታ እግዚአብሔር
ካላስረከብነው መንኳኳት አይቆምም፡፡ 1ዐ% ስንሰጥ
ይንኳኳል፡፡ 30% ስንሰጥ ይንኳኳል፡፡ 50% ስንሰጥ
ይንኳኳል፡፡ 99% ስንሰጥ ይበልጥ ይንኳኳል፡፡ 100%
ስንሰጥ መንኳኳት ይቆማል፡፡ እኛ ከከፈትን ሰይጣን
ይገዳደረናል፡፡ ጌታ ሲከፍት ሰይጣን " ይቅርታ የአንተ
ቤት መሆኑን አላወቅሁም " ብሎ ይሄዳል፡፡
ጌታ ሰማይን የደስታ አገር ያደረጋት ሙሉ
በሙሉ የፈጣሪ ፈቃድ የጸናባት በመሆኗ ነው፡፡
ባንተም ሕይወት የሰማይ ደስታ የሚመጣው
የፈጣሪ ፈቃድ በሕይወትህ ሙሉ በሙሉ
ሲፈጸም ነው፡፡ ስለዚህ፡-
· ፈጣሪን እረኛህ አድርገው፡፡
· በፍጹም ልብህ ተከተለው፡፡
· የሚያስፈልጉህ ነገሮችም አንተን ይከተሉሃል፡፡
"ሙሉ ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር እናስረክብ።"

@aleroe
ኤልሮኢ፡
#መፆሙን_ይፆማል

መፆሙን ይፆማል #ሁሉም_የአዳም_ልጅ/2/
የጊዜው መድረሱ #የሚያውቅ_የለም_እንጂ/3/

ይደርሳል ሰዓቱ #ሳስብ_ሌላ_ሌላ/2/
የተሰቀለውን #ስጋውን_ሳልበላ/3/

ድጓ ፆመ ድጓ #ተሰቅሎ_ከቤቴ/2/
አወይ አለማወቅ #ሳልማር_መቅረቴ/3/

ደግሜ ደገሜ #ቀረኝ_አሌፋቱ/2/
አድኅነኒ ሳልል #አትጥራኝ_በከንቱ/3/

እኔስ እሄዳለው #አጣቢ_ፍለጋ/2/
በጣም አድፎብኛል #የለበስኩት_ስጋ/3/

ዳዊት እንዴት ይሙት #ሳልተዋወቀው/2/
የሚመጣው ሁሉ #በገና_የሚያውቀው/3/

ዐርብ ረቡን ገደፍኩ #በሥጋ_አዋዜ/2/
እንዲህ ለሚደርሰው #ለማይቆየው_ጊዜ/3/

ከሥጋው ሳልበላ #ተጠይፌ_ደሙን/2/
ማን ይችለው ይሆን #የላይ_ቤት_ረሃቡን/3/

ከንብረቱ ሁሉ #አልጋዬ_ነው_ሀብቴ/2/
አድርሶኝ ይመጣል #ከዘላለም_ቤቴ/3/

ብልህ ነው ስትለኝ #እዩት_ሞኝነቴን/2/
በራሴ ላይ ሆኖ #አላውቀውም_ሞቴን/3/

መማሩንስ ዳዊት #ተምሬ_ነበረ/2/
ከአምላኪየ ሳልደርስ #ልቤ_ሰንፎ_ቀረ/3/

እንኳን ነአኩተከ #በስመ_አብም_ቸገረኝ/2/
ዳዊት እንዴት ተማርክ #እባክህ_ንገረኝ/3/

👉👉👉@aleroe👈👈👈
👉👉👉@aleroe👈👈👈
👉👉👉@aleroe👈👈👈
ኤልሮኢ:
# እጠበኝ ቆሽሻለው

እጠበኝ ቆሽሻለው አምላኬ በድያለው
ያለናት ያሳደከኝ ያላባት የ ጠበከኝ
ያንሁሉ ዛሬ ረሳው እጠበኝ ቆሽሻለው/2/

ከድንኳንክ ብታስገባኝ ሞገስ ሰተህ
የ አፍኒንን ምግባር ይዤ አስ ቀየምኩህ
ቅባሜሮን ያተምክበት ልጅነቴ
እንዳይጎድፍ ጠብቅልኝ ቸር አባቴ


ሀይል አኑረክ እንደ ሶምሶን በፀጉሬ
ጎልያድን አስጥለኅኝ በጠጠሬ
አቅም ቢያንሰኝ በስጋ ጦር ተሸንፌ
ደጅህ መጣው የንባ መባ ባይኔ አቅፌ

እንዳትረሳኝ በመዳፍህ ቀርፀሀኅኛል
እንዳተወኝ ያለመጠን ወደህኛል
ባሰነዝር ልት ቀጣኝ የሞት በትር
የትግስትክ ሰሌዳነው ለኔክብ

ከከንፈሬ ጥበብ ጽፈህ ቅኔ ቢፈስ
በመታበይ አሳዘንኩት ያንተን መንፈስ
ፍቅር ግተህ በቅፍስር ያሳደከኝ
እባክህን በበደሌ አትቅፀፈኝ


@aleroe
ኤልሮኢ:

……አንድ በምሽት አቅጣጫ የጠፋበት መርከብ ከሩቅ ያየ ሰው ወደ እቤቱ ገብቶ ሻማ ይለኩሳል

ሻማውም ለምን ለኮስከኝ ቢለው ሰውዬው ‹‹አቅጣጫ የጠፋው መርከብ ከሩቅ ያታየኛል
ለሱ በእሳት ልጠቁመው ነው ይለዋል ሻማውም ‹‹ታዲያ እኔ ሻማ ነኝ እንዴት ከሩቅ እታያለሁ›› ቢል ሰውዬውም መለሰ ‹‹ሻማዬ ሆይ አንተ ብቻ የቻልከውን ብራ›› አለውና ይዞት ይወጣና ብዙ ደረቅ እንጨቶችን እንደ ዳመራ ከቆለለ ቦሃላ በሻማው እሳት እንጨቶቹን ለኮሰ ብርሃኑም ብዙ ሆነ
ያኔ መርከቡም ተመልክቶ መጣ

ሰውዬውም ለሻማው እንዲህ አለው ‹‹ሻማዬ ሆይ አየህ አንተ በቻልካት መጠን ስለበራህ ያንተን ብርሀን ተቀብለው የሚያደማምቁ ብዙዎች አሉ›› አለው፡፡


እንግዲህ እንዲህ ነው የኔ ጥረት ትንሽ ናት አትበል፡፡ የቻልከውን ካደረክ ሌሎች ያንተን ብርሃን የሚቀበሉ እልፎች አሉ

‹‹የትም ሁን ማንም ሁን ያቅምህን በጎ ለማድረግ ግን አትስነፍ ደግነት
እንደ ጥሩ ሽቶ ነው ከአንዱ ተነስቶ ወደ አንዱ ይጋባል››

እንግዲህ አንዲህ ነው ለመስጠት የግድ ሃብታም መሆን
አይጠበቅብህም፡፡ ደግሞ ማንም ሰው ልስጥ ካለ የሚሰጠው አያጣም፡፡

@aleroe