"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

33ቱ የእመቤታችን በዓላት ሠላሳ ሦስቱ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓላት እነዚህ ናቸው፡-

+ ነሐሴ 7- እመቤታችን የተፀነሰችበት ዕለት፡፡

+ ነሐሴ 16- ሥጋዋ የፈለሰበት/በልጇ ኃይል ከሞት ተለይታ የተነሣችበትና ወደ ሰማይ ያረገችበት ዕለት፡፡

+ ከነሐሴ 17 እስከ ነሐሴ 21 ድረስ ለ5 ቀናት ትንሣኤዋ እንደልጇ ትንሣኤ ይከበራል፡፡ የጌታ ትንሣኤ አንድ እሑድ ቀን መኾኗ የታወቀ ቢሆንም የትንሳኤው መታሰቢያ እስከ 50 ቀናት ማክበራችንን እናስታውስ የእመቤታችንም እንደዚሁ ነው፡፡

+ መስከረም 10- ሥጋን የለበሰች የምትመስለውና ብዙ ተአምራት ታደርግ የነበረችው የእመቤታችን ሥዕል ፄዴንያ ወደተባለ አገር ገብታ የተቀመጠችበትን ዕለት፡፡

+ መስከረም 21 ትከብራለች፡፡ አርዮስን ለማውገዝ በ326 ዓ.ም በኒቅያ የተሰበሰቡት ቅዱሳን ከሚያዝያ እስከ መስከረም 21 ቀን ድረስ በመሆኑ የመስከረም ማርያም (ብዙኃን ማርያም)
ተብሎ በዓሏ ይከበራል፡፡ እንዲሁም ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የክርስቶስን ቅዱስ መስቀል ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ገዳም በመስከረም 21 ቀን ስላስገቡ ምእመናን በዓሉን በግሸን ማርያም ያከብሩታል፡፡

+ ጥቅምት 21- ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡

+ ኅዳር 6- ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል ሀገር ገብታ ያረፈችበት ዕለት፡፡

+ ኅዳር 21- ጽላተ ሙሴ አክሱም ቤተ መቅደስ ተሠርቶላት በክብር ያረፈችበት ዕለት፡፡ ዳግመኛም ካህኑ ዘካርያስ የእመቤታችን ምሳሌ የሆነውን የመቅረዝ ፋና ሲበራ ያየበት ዕለት ነው፡፡

+ ታኅሣሥ 3-በሦስት ዓመቷ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት፡፡

+ ታኅሣሥ 21 ትከብራለች፡፡ የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡

+ ታኅሣሥ 22- ብሥራተ ገብርኤል (ቅዱስ ደቅስዮስ እመቤታችን ጌታን የፀነሰችበትን የመጋቢት 29 ቀንን በዓል በዚህ ዕለት አከበረ)፡፡

+ ታኅሣሥ 28- ጌታችንን የወለደችበት የመታሰቢያ በዓል (በ4 ዓመት አንድ ጊዜወርሃ ጳጉሜን 6 ቀን ስትሆን ልደት በ28 ይውላል)፡፡

+ ታኅሣሥ 29- ጌታችንን በድንግልና የወለደችበት የመታሰቢያ በዓል፡፡

+ ጥር 21- እመቤታችን በ64 ዓመቷ ያረፈችበት ዕለት፡፡

+ የካቲት 16- ከልጇ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበለችበት ዕለት፡፡

+ የካቲት 21 ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡

+ መጋቢት 21 ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡

+ መጋቢት 29 ትከብራለች/ጌታችንን የፀነሰበት ጥንተ በዓል፡፡

+ ሚያዝያ 21 ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡

+ ግንቦት 1- እመቤታችን የተወለደችበት ዕለት፡፡

+ ግንቦት 21- በደብረ ምጥማቅ በገሃድ ተገልጻ ታላቅ ተአምር ያደረገችበት፡፡

+ ግንቦት 22- በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡

+ ግንቦት 23- በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡

+ግንቦት 24- እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በመሰደድ ግብፅ አገር የገባችበት ዕለት፡፡

+ ግንቦት 25- ተወዳጅ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ በተአምራት ያለመለመበት ዕለት፡፡

+ ሰኔ 8- ተወዳጅ ልጇ ከደረቅ ዓለት ላይ ውኃ ያፈለቀበት፡፡

+ ሰኔ 21- ጌታችን ሰኔ 20 ተገልጦ ሐዋርያቱን ተሰብስቦ በስሟ ቤተ ክርስቲያን ከሠራላት በኋላ በቀጣዩ ቀን ቅዳሴ ቤቷን ያከበረበት ዕለት ነው፡፡

+ሐምሌ 21 ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
​ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መስከረም 05/01/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፴፱፥፭(39፥5)
ብዙኅ ገበርከ እግዚኦ አምላኪየ መንክረከ
ወአልቦ ዘይመስሎ ለሕሊናከ
አይዳዕኩ ወነገርኩ ወበዝኀ እምኁልቍ

ምስባክ ዘቅዳሴ

አዋልደ ንግሥት ለክብርከ
ወትቀወወም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት

ቅዳሴ

ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
​ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መስከረም 07/01/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፭፥፱(5፥9)
ወጸልሐዉ በልሳናቲሆሙ
ኵንኖሙ እግዚኦ ወይደቁ በውዴቶሙ
ወበከመ ብዝኀ ሕብሎሙ ስድዶሙ


ምስባክ ዘቅዳሴ

እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን


ቅዳሴ

ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)

​መስከረም 08/01/2013 ዓ.ም
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፻፲፰፥፷፩(118፥61)
ወእምቃልከ ደንገፀኒ ልብየ
ወበቃልከ ተፈሣሕኩ
ከመ ዘረከበ ምህርካ ብዙኀ

ምስባክ ዘቅዳሴ

ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ
ወጸድቃኒከ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑ
በእንተ ዳዊት ገብርከ


ምስባክ ዘቅዳሴ ተለዋጭ

ይትፌሣሕ ጻድቅ ሶበ ይሬኢ በቀለ
ወይትሐፀብ እዴሁ በደመ ኃጥእ
ወይብል ሰብእ ቦኑ እንጋ ፍሬ ለጻድቅ


ቅዳሴ

ዘኤጲፋንዮስ (ዐቢይ)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ :(መንፈሳዊ ስነፅሁፍ)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ትህትና

ልበ ትሁታን፡ ብፁዕ ናቸውና
እግዚአብሔርን አዩት፡ በንፁህ ህሊና
እስኪ ከቅዱሳን ፡ጉረኛ ማን አለ?
እኔ አውቃለሁ፡ አንተን ወዲያ ያለ!

ለሰው ልጅ ትህትና: በውነት ያስፈልጋል
እንደ አንበሳ ማጉራት :ለትዝብት ይሰጣል

ዲያቢሎስ በትዕቢት :እንዲያ ተወጥሮ
ያልሰራውን ሰራሁ ሲል: ትልቅ ውሸት ፈጥሮ
ከጥልቁ ወደቀ፡ ከዚያ ከጨለማ
ክብር እንዳልነበረው፡ ከኢዮር ራማ

ጥሩ ይመስለዋል፡ አየ ሰው ሞኙ
በጉራ ሲናገር፡ ማይታወቅ ከቶ ማይገኙ

ትህትና አሳይቷል፡ ሰባቱን ሰማያት
መንገድን ይጠርጋል፡በጎውን ለማየት
እድል ያስጥሀል፡ በሰማይ በገነት

ጉራን አውልቃችሁ ፡ትህትናን ልበሱ
ክርስቶስ አሳይቶናል እሱን አስታውሱ፡፡
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
​መስከረም 09/01/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፹፬፥፲፪(84፥12)
እግዚአብሔርኒ ይሁብ ምሕረቶ
ወምድርኒ ትሁብ ፍሬሃ
ጽድቅ የሐውር ቅድሜሁ

ምስባክ ዘቅዳሴ

ደምፁ ወተሐምጉ ማያቲሆሙ
ወአደለቅለቁ አድባር እምኃይሉ
ፈለግ ዘይውኅዝ ያስተፌሥሕ ሀገረ እግዚአብሔር

ቅዳሴ

ያዕቆብ ዘሥሩግ (ተንሥኡ)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
መስከረም 10/01/2013 ዓ.ም
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፩፥፪(1፥2)
ወዘሕጎ ያነብብ መዓልተ ወሌሊተ
ወይከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙኀዘ ማይ
እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ

ምስባክ ዘቅዳሴ

ምድርኒ ወሀበት ፍሬሃ፤
ወይባርከነ እግዚአብሔር አምላክነ፤
ወይባርከነ እግዚአብሔር።

ቅዳሴ

ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
​መስከረም 12/01/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፸፪፥፰(72፥8)
ሐለዩ ወነበቡ ከንቶ
ወነበቡ ዓመፃ ውስተ አርያም
ወአንበሩ ውስተ ሰማይ አፋሆሙ

ምስባክ ዘቅዳሴ

ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ
ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ
ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር

ቅዳሴ

👉ዘቄርሎስ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
መስከረም 13/01/2013 ዓ.ም
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፻፩፥፳፬(101፥24)
ኢትስደኒ በመንፈቀ ዓመትየ
ለትውልደ ትውልድ ዓመቲከ
አንተ እግዚኦ አቅደምከ ሣርሮታ ለምድር

ምስባክ ዘቅዳሴ


ብፁዓን እለ ተኀድገ ሎሙ ኃጢእቶሙ
ወእለ ኢሐሰበ ሎሙ ኩሎ ጌጋዮሙ
ብፁዕ ብእሱ ዘኢኈለቁ ሎቱ እግዚአብሔር ኃጢአቶ

ቅዳሴ

ዘባስልዮስ (እግዚኦ መሐረነ)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መስከረም 14/01/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፺፭፥፲፩(95፥11)
ወትትከወስ ባሕር በምልዓ
ትትኃሠይ ገዳም ወኵሉ ዘውስቴታ
ውእተ አሚረ ይትፌሥሑ ኵሉ ዕፀወ ገዳም

ምስባክ ዘቅዳሴ

ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ
ከመ ያምስጡ እምገጸ ቅሥት
ወይድኀኑ ፍቁራኒከ

ቅዳሴ

ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ :(መንፈሳዊ ስነ ፅሁፍ)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
"አትናቅ"

በዘር በወገንህ: ከመመካት ራቅ
የፈለገ ቢወድቅ: የፈለገ ቢደቅ
ሰው ሆነህ ተፈጥረህ፡ ሰዎችን አትናቅ!
ያደርገዋልና የተዋረዱን: ከፍ የከበሩትን ዝቅ::

ቢኖርህ አትመካ ፡ሙሉ አካል ከጤና
ምን ትሆን ወደፊት ፡ከቶ አታውቅምና፡፡

አለኝ ብለህ አትናቅ: ወርቅ ብር ገንዘብ
ሀላፊ ነው እና: ጌታ እንዳይታዘብ::

የሚመካ ቢኖር፡ ኑ ከዚህ አለ ሀይል
(ትምክህትህ በሌላ አይሁን)
በእግዚአብሔር ማዳን ነው፡ በመከራው መስቀል::

አላዛርም ነዌም ፡ደሀውም ሀብታሙም
ክፉው ዘረኛውም፡ ከቶም ያልፋል ሁሉም
በጎ ስራ ግና፡ ይኖራል ዘላለም፡፡

(በእርሱ ፊት)
ዘርህ አንተ ምነው፡ ቅማንት ወይ አማራ?
ይህን አትጠየቅ! ስምክን አትጠራ!

( ምነው ታዲያ )
ዘሬን እየጠራህ፡ ማለትህ አህያ¡
ምርጥ ነን ማለትህ: ሰውስ ከኛ ወዲያ!
አህያን ብታውቃት፡ ጌታ ሰጧታል ክብር
የከበረ አምላኳ ፡ተቀምጦባት ነበር፡፡

በአንድ አምላክ ተበጅተን፡ከአንድ አዳም ተፈጥረን፡
ከሰዎች ልዩ ነን፡ ማለትህ ምን ይሆን?
(እርሱ ይወቅልህ)

በዘር በወገንህ: ከመመካት ራቅ፣
የፈለገ ቢወድቅ: የፈለገ ቢደቅ፣
ሰው ሆነህ ተፈጥረህ፡ ሰዎችን አትናቅ!
ያደርገዋልና የተዋረዱን: ከፍ የከበሩትን ዝቅ::
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
​መስከረም 15/01/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፻፳፭፥፮(125፥6)
ወጾሩ ዘርዖሙ
ወሶበ የአትዉ መጽኡ እንዘ ይትፌሥሑ
ወፆሩ ከላስስቲሆሙ

ምስባክ ዘቅዳሴ

ብፁዕ ዘኀረይኮ ወዘተወከፍኮ
ወዘኀየርኮ ውስተ አዕፃዲከ
ጸገብነ እግዚአ እምበረከተ ቤትከ

ቅዳሴ

ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
​መስከረም 16/01/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፹፮፥፪(86፥2)
ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን
እምኵሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ
ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር

ምስባክ ዘቅዳሴ

እቤ አዐቅብ አፉየ ከመ ኢይስሐት በልሳንየ
ወአንበርኩ ዐቃቤ ለአፉየ
ሶበ ይትቃወሙኒ ኃጥኣን ቅድሜየ


ምስባክ ዘቅዳሴ ተለዋጭ

አሠንያ እግዚኦ በሥምረትከ ለጽዮን
ወይትሐነፃ አረፋቲሃ ለኢየሩሳሌም
አመ ትሠምር መሥዋዕተ ጽድቅ

ቅዳሴ

👉ዘእግዚእነ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል )
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መስከረም 17/01/2013 ዓ.ም

ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፶፱፥፬(59፥4)
ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ
ከመ ያምስጡ እምገጸ ቅሥት
ወይድኀኑ ፍቁራኒከ

ምስባክ ዘቅዳሴ

ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ
ከመ ያምስጡ እምገጸ ቅሥት
ወይድኀኑ ፍቁራኒከ።

ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፰ ቊ. ፲፮-፲፯ - ፳፰

ምስባክ ዘቅዳሴ ተለዋጭ

ወረከብናሁ ውስተ ዖም ገዳም
ንበውዕ እንከሰ ውስተ አብያቲሁ ለእግዚአብሄር
ወንሰግድ ውስተ መካን ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ


ትርጉም

መዝሙረ ዳዊት ም. ፻፴፪ ቊ. ፮ - ፯

ወንጌል ዘቅዳሴ

የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፱፥፳፭-፳፰

ቅዳሴ

ዘዮሐንስ አፈወርቅ

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
#መጋቢት_10_የጌታችን_መስቀል_የተገኘበት

በደመ ወልደ እግዚአብሔር የከበረ፣ ጌታ ቅዱሳት እጆቹን የዘረጋበት፣ ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት፣ መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስ የተሻረበት፣ ዘላለማዊ ደዌ የጠፋበት፣ የጥል ግድግዳን ያፈረሰበት፣ ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ ድል የተነሣበት የጌታችን መስቀል ከጌታችን ዕርገት በኋላ ሙት እያነሣ፣ ደዉይ እየፈወሰ ለክርስያኖች ታላቅ ክብር በመኾኑ፤ አይሁድ በዚኽ ክፉኛ ይበሳጩ ነበር።

ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵ 3፡18-19 ላይ “ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ፤ መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው” እንዳለ፤ ጒድጓድ ቈፍረው በይሁዳ እና በኢየሩሳሌም ኹሉ ቤቱን የሚጠርግ ጒድፉን አምጥቶ እንዲያፈስስበት በማዘዛቸው ቦታው የቆሻሻ መጣያ ኾኖ ዕሌኒ ንግሥት እስከ መጣችበት ድረስ ለ፫፻ ዓመታት ያኽል ተቀብሮ ኖረ፡፡

የእሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስም በመስቀሉ ኀይል የክርስቲያኖች ጠላት የኾነውን መክስምያኖስን ድል ከነሣ በኋላ በሶል ጴጥሮስ ተጠምቆ ክርስቲያን ኾነ፤ ርሷም ልጄ ክርስቲያን ከኾነ ኢየሩሳሌም ኼጄ የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት አሠራለኊ፤ የጌታዬ መስቀልን ከተቀበረበት አስወጣለኊ ብላ ስዕለት ተስላ ነበርና ያ በመፈጸሙ ደስ ተሰኝታ፤ ለልጇ ነገረችው፤ ርሱም በደስታ ብዙዎች ሰራዊትን ስንቅ አስይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ላካት፤ በደረሰችም ጊዜ ሱባኤን አድርጋ የመስቀሉ ጠላቶችን በጽኑ እስራት አሰረቻቸው፤ በኋላም አሚኖስና ኪራኮስ የሚባሉ በዕድሜ የጠገቡ ሽማግሌዎችን ብትጠይቃቸው ሊነግሯት ፈቃደኛ አልኾኑምና በጽኑ እስራት ብታስጨንቃቸው፤ ታሪኩን ነገሯት፤ ቦታውንም ጠቈሟት፡፡

ከዚያም በጸሎቷ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጾላት በዕጣን ጢስ አማካይነት እንደምታገኘው ተረድታ፤ መስከረም ፲፮ ደመራን አስደምራ በእሳት እንዲቃጠል አድርጋ እጅግ ብዙ ዕጣንን ብታስጨምር ጢሱ ወደ ሰማያት ወጥቶ መስቀሉ ካለበት ቦታ ላይ ተተክሎ ሰገደ፤ “ተተክለ ጢስ ኀበ አንጻረ መስቀል፤ ሰገደ ጢስ ወባረከ” እንዲል ቅዱስ ያሬድ።

ርሷም ፈጣሪዋ እግዚአብሔርን በፍጹም ደስታ አመስግና ቊፏሮውን ከመስከረም 17 ዠምሮ እስከ መጋቢት 10 ድረስ እንዲቈፈር አስደርጋለች፤ በቊፋሮው ወቅትም የፈያታዊ ዘየማንና የፈያታዊ ዘጸጋም መስቀል ቢገኙም ዕውር አላበሩም፣ ሕሙማንን አልፈወሱም፡፡

ከዚያም መጋቢት 10 በ327 ዓ.ም. ክብር ይግባውና ጌታችን ክቡር ደሙን ያፈሰሰበት ቅዱስ መስቀሉ ተገኘ፤ በዚኽ ጊዜ ከሕሙማን ላይ ቢያደርጉት ኹሉንም ፈወሳቸው፣ ዕዉራን በሩ፣ ሙታንም ተነሡ፡፡ ከዚኹም ጋር የተወጋበት ጦሩ፣ የተቸነከረባቸው ቅንዋት ኹሉ ተገኝተዋል፤ ርሷም በፈረሷ ልጓም ላይ የመስቀል ምልክትን አስቀርጻበታለች፡፡

ርሷም ጌታችን ተአምራት በሠራባቸው ቦታዎች አብያተ ክርስቲያናትን በማሠራት፤ በተለይም በጎልጎታ የተሠራው ቤተ ክርስቲያን መስከረም ፲፯ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምእመናን በተገኙበት ቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑ ተከብሯልና፡፡ ርሷም ለድኾችና ለጦም አዳሪዎች ብዙ መልካም ነገርን በማድረግ ግንቦት ፱ በሰላም ዐርፋለች፡፡
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ :(መንፈሳዊ ስነፅሁፍ)


​​​​"አይጣል ነው አይድረስ"


አይጣል ነው፡ አይድረስ
ሰማይ አይታረስ ፡ንጉስ አይከሰስ

የሞት ነገር መቸም ፡ አይሆንልን ዛሬም
ስሙ ሲነሳብን ፡ይቀፈናል ሁሌም፡፡

በዚህ እስካለ፡ ህይወት
ሞትም ፡ከጎኑ ናት፡፡
(ምንም ማድረግ አይቻልም)

"አሁን ብትሞትስ!"ስልህ፡ ምሳሌ ስሰጥህ
ትሰድበኝ ይሆናል፡ "አንት ሟርተኛ"ብለህ
በርግጥም ያስፈራል ፡ወዳላዩት መሄድ
መቸም ቁርጥ ካልሆነ ፡እኔም እንዲዚያ አልወድ፡፡

ምን እናድርግ ?
በተፈጥሮ ህግ!

አይጣል ነው አይድረስ...

ነፍስህ ፡ባንተ አይደለች
በፈጣሪ እጅ ነው፡የተያዘች ያለች
በቤት ውስጥም ሳለህ ፡በመንገድ ጎዳና
በእግርም እየሄድክ፡በአየር መኪና
ልትሞት ትችላለህ ፡አለም ላይ ናትና፡፡


ድንገተኛ አደጋ ፡ምንኛ ሀያል ነው
እዚሁ ከጎናችን ፡በሰፈር ነው ያለው ፡፡
ሀገር ሰላም ብሎ፡ ሰው ከቤቱ ወጦ፣
ከጓደኞቹ ጋ ፡በስርዓት ተቀምጦ፣
የቆመ ግንድ ወድቆ፣
ተባራሪ ጥይት፡ ሌላን ሁሉ ትቶ፣
ሊገድልህ ይችላል ፡አንተኑ ለይቶ፡፡
ምን ይመጣል ብለህ፡ቤትም ብትቀመጥ
ልትሞት ትችላለህ፡በመሬት መንቀጥቀጥ፡፡


(ምን ይታወቃል እያየን ነው)

አይጣል ነው አይድረስ...


ይሄ ሞት የሚሉት ፡ምንም ምርጫ አያውቅም፣
ህፃን ሽማግሌ ፡ሴት ወንድ አይለይም፣
ቀጭኑ ወፍራሙንም፡ ረዥሙ አጭሩን
አያውቅም መሰለኝ፡ በያይነት መኖሩን፡፡

(አይመርጤ አሉ)

ብዙዎች ነጎዱ፡ ሳያውቁ ሳይነቁ
እምነት ምን እንደሆን፡ ቅኔ ሰሙ ወርቁ

ቢደርስም ባይደርስም፡ ሁሌ ተዘጋጁ
ሊመጣ ይችላል፡ ሊወስድ ነፍሱን በጁ፣
ይሄኔ ነቃ በል፡ ነጋሪት ሳይጎሰም ሳይነገር አዋጁ፡፡

እና በል ወዳጄ ፡እችን ያዝ እንግዲህ፣
አንድ ቀን ብለይህ፣
ምንም እንዳይመስልህ፣
አይመርጤ አይመርጥልህ!
እውነቴን ስነግርህ!

በል በል አንተ ወዳጄ፣ ጊዜ አትውሰድብኝ
አንዳንድ ስራ ልስራ፣ ሳይወሰንብኝ
መቸም አይቆጨኝም፣ ዝግጁ ከሆንኩኝ፡፡

አይጣል ነው አይድረስ
ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ።

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
መስከረም 20/01/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፴፱፥፱(39፥9)
ዜኖኩ ጽድቅሰ በማኅበር ዓቢይ
ወናሁ ኢከላዕኩ ከናፍርየ
እግዚኦ ለሊከ ተአምር ጽድቅየ

ምስባክ ዘቅዳሴ

እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን

ቅዳሴ

ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)


@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​መስከረም 21/01/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፳፭፥፲፮(25፥16)
አድኅነኒ እግዚኦ ወተሠሃለኒ
እስመ በርቱዕ ቆማ እገርየ
በማኅበር እባርከከ እግዚኦ

ምስባክ ዘቅዳሴ

ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምኢ እዝነኪ

ቅዳሴ

ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም) አው እግዝእትነ


@aleroe
ኤልሮኢ:(መንፈሳዊ ትርክት)

……ከእለታት አንድ ቀን አንድ አባት ወደ አባታችን አባ መቃርዮስ በኣት ሄደና "አባቴ ሆይ ድኅነትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?" ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው። አባታችንም እንዲህ በማለት አሉት።
"ወደ መቃብር ሂድና ሙታንን ሰድበሃቸው ና" አሉት። ይህ አባትም የተባለውን አድርጎ ተመለሰ። አባታችንም "ምን አሉህ?" ሲሉ ጠየቁት። ሰውየዉም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "አሁን ደግሞ ሂድና ሙታንን አመስግናቸው" አሉት። ሄዶም አመሰገናቸው። "አሁንስ ምን አሉህ" ሲል በድጋሚ ጠየቁት። ሰውዬም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባታችን አባ መቃርዮስም: "ስትሰድባቸው ፤ስታመሰግናቸው እና ስታወድሳቸው ምንም አልመለሱም፤ አንተም ለነፍስህ ድህነትን ከፈለግህ እንደሞተ ሰው ሆነህ ኑር። ሰዎች ክፉ ቢያደርጉብህም፣ ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ" አሉት።
======================
@aleroe