"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ኤልሮኢ:

...........የሀጢያት ትንሽ ..............

ዲያብሎስ ልጅነታችንን እናቆሽሽ ዘንድ በእኛ ላይ የሚተናኰለው ተንኰል በጣም ተደጋጋሚና ኃይለኛ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን መንቻካ የዲያብሎስን ደባ ድል እንነሣ ዘንድ ዘወትር ንቁዎችና ጠንቃቆች ልንኾን ይገባናል፡፡ እኛ ይህን ማድረግ ሳንችል ቀርተን እጅግ ጥቂት መግቢያ ቀዳዳ የምንተውለት ከኾነ ግን እርሱ ጥቂቷን ቀዳዳ ሰፊ በር ያደርጋታል፡፡ እንዲህ አድርጎም ኃይሉን ኹሉ ተጠቅሞ ወደ እኛ ይገባል፡፡

ስለዚህ ስለ ድኅነታችን የሚገደን ከኾነ እንደዚህ ጥቂትና ቀልድ በሚመስሉ ነገሮች እንኳን አንዘናጋ፤ እርሱ የሚንቀውና ጥቂት የሚለው ኃጢአት የለምና፡፡ እኛ ጥቃቅን የምንላቸውን ነገሮች መነሻ አድርጎ ልጅነታችንን የምናቆሽሽበትን ታላላቅ ኃጢአቶችን እንድንሠራ አድርጎ እጅግ ይተጋልና፡፡

🖌……ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@aleroe
ኤልሮኢ:(ስነፅሁፍ)

#መጎዳቴን_አይቶ


መጎዳቴን አይቶ
ሊቀይር ታሪኬን
ካለሁበት መጥቶ
ሊሞላው ጓዳዬን
መዳን ትወዳለህ ?
ብሎ ቢጠይቀኝ
የሰለለ አካሌን
በአይኔ እያማተርኩኝ
እወዳለሁ ! አልኩት
መፈወስን ሽቼ
የመጥምቁ አምላክ
መሆኑን ሰምቼ፡፡
የጫማውን ጠፍር
መፍታት የተሳነው
ዛሬ ሽባ እግሮቼን
መፈወስ ተቻለው፡፡
ዳንኩኝ በጸበሉ
በእጁ ተጠምቄ
ለምስክር በቃው
በምልጃው ደምቄ፡፡

ከረዳኢ ሃዱሽ
_______________



@aleroe
ኤልሮኢ:
#ዝምታ

#ብፁዕ_አቡነ_ሽኖዳ ......

ዝምታ በመጀመሪያ ደረጃው ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የአንደበት ስህተትን መግታት ማለት ነው፦ " በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።" ምሳ. 10 ፥ 19። ቅዱስ አርሳኔዎስም እንድህ ብሏል ፦ " ብዙ ጊዜ እናገርና እፀፀታለሁ ስለ ዝምታየ ግን ፈጽሞ ተፀፅቼ አላውቅም ።"

በሌላ በኩል ዝምታ ማለት እግዚአብሔር ይሠራ ዘንድ የሰውን ጥረት ማቆም ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አስመልክቶ ሲናገር እንድህ ብሏል፦ .." እግዚአብሔር ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ ። እግዚአብሔር ስለእናንተ ይዋጋል እናንተም ዝም ትላላችሁ .." ዘጸ. 14፥ 13-14።

አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰው ለራሱ የማይበቀልና ክፉን በክፉ የማይቃወም ከሆነ ዝምታ እርጋታ ይሆናል።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም .1ኛ ጴጥ. 2፥23። በአይሁድ ሸንጎ ፣ በሐና ፣ በቀያፍ ወይም በጲላጦስ ፊት ሲከሱት ዝም ነው ያለው።

ዝምታ ውስጥ ግን ኃይል ስለነበረ አገረ ገዥው ጲላጦስ ".. እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኜሁበትም ።" ( ዮሐ . 18 ፥ 38) በማለት ተናግሯል።

ከዚህ በተጨማሪ ዝምታ ለፀሎት ለተመስጦ እድሉን ያደላል።
ብዙ የሚያወራ ሰው ለመፀለይም ሆነ ለውስጣዊ መንፈሳዊ ድርጊት ዕድል አይኖረውም።

አንድ ቅዱስ ሰው".. ብዙ የሚናገር ሰው ውስጡ ባዶ መሆኑን ይገልጣል ።" ብሎ መናገሩ ትክክል ነው። ይህም ማለት ውስጣዊ መንፈሳዊ ሥራ የለውም ማለት ነው።
ቅዱስ አርሳኔዎስ ስለዝምታውና ስለ ምናኔው በተጠየቀ ጊዜ ".. በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ከእግዚአብሔርና ከሰዎች ጋር መሆን አልችልም ።" ብሎ መልሷል።

አንድ ታላቅ መንፈሳዊ አባት የተናገሩት ቃል ምንኛ ድንቅ ነው ፦ " .. ልብህ ይናገር ዘንድ አንደበትህን ዝም አሰኜው እግዚአብሔር ይናገር ዘንድ ልብህን ዝም አሰኜው ።"

የዝምታ አይነቶች ብዙ ቢሆኑም ከነዚህ መካከል ዋና ዋናዎቹ #የአንደበት_ዝምታና_የስሜት_ዝምታ ናቸው። ሰው ስሜቱን ባተሌ እስካላደረገ ድረስ ፀሎቹንና ተመስጦዎቹን ያግዱበት ዘንድ መጥፎ አሳቦችን ያመጡበታል ። ስለሆነም በመንፈሳዊ መንገድ ዝምታውን መጠበቅ የሚወድ ሰው አይኖቹን ፣ ጆሮዎቹንና ስሜቶቹን ሁሉ መጠበቅ አለበት ።

ዝምታ ለሰው መስከንንና እርጋታን አስተምሯል ከጫጫታ፣ ከሁካታ፣ ለመጸለይ አስቸጋሪ ከሚሆኑበትና ሕሊናውን ከሚረብሽበት ብዛት ካላቸው አሳቦች ያርቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ዝምታ የሚሻው ብቼኝነትንና ጥቂት ጓደኞችን ነው።

ምንጭ፦ መንፈሳዊ ቃላትና ጥቅሞቻቸው ፤ #አያሌው_ዘኢየሱስ እንደተረጎመው ።

የብፁ አባታችን ብራኬ ይደርብን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።

@aleroe
ኤልሮኢ:(ስነ ፅሁፍ)

#ናፈቀኝ ....

የማለዳ ተመስጦ ... ውዳሴ ማርያም መድገሜ
በልጅነት ልመጣልህ .. ጧት ማታ መፍገምገሜ
ዛሬ ግን ናፍቆት ሆነብኝ .. ተዘረረብኝ አቅሜ
እንቅልፌ ሰላም አጣ .... እባብ ሆነብኝ ሕልሜ ።
.
"እግዚኦ" ሲባል ሰምቼ .. ሳልነሳ ከትራሴ
ድንጋጤ ወረረኝ .. ከእግሬ ጥፍር እስከራሴ
ሰዓታቱን እየሰማሁ ... ተቀሰቀሰ መንፈሴ
ትዝዝ አለኝ ማኅሌቱ ... ስትዋብበት ነፍሴ
የእናቴ ስም ናፈቀኝ ...... የሕርያቆስ ቅዳሴ
.
እራሴንም ስላጣሁት ..... ከቤትህ በመራቄ
እንደ ሎጥ ሚስት መሰልኩኝ ፤ አደባባይ ደርቄ
.
የመዝሙረ-ዳዊት ጸሎት .. አነከተኝ በትዝታ
ነፍሴን ስላስጠማኋት ... አነባችብኝ አብዝታ
እሪሪሪ ብላ አለቀሰች ... በስጋ ወንጭፍ ተገዝታ
.
ናፈቀኝ ትምህርቱ ... የቅዱስ ያሬድ ጸጋ
ቁጥር ዜማ መጮሄ .... አንደበቴ እስኪዘጋ
ዛሬ ላለው ማንነቴ .. ምን ይሆን የ'ኔ ዋጋ ??
.
በከበሮ በጽናጽል ... መዘመሩ ማሸብሸቡ
ጃኖ ለብሶ በመሰለፍ ... ማመርገዱ መወረቡ
የትውስታ ስለት ይዘው ፤ ወደ ልቤ ሰርገው ገቡ
.
አምላኬንም ሳመሰግን .. ወደ ሰማይ አንጋጥጬ
እንዲህ ዛሬ ልቀብረው .. በልቤ ውስጥ ረግጬ
አገልግሎቴ ናፈቀኝ ... ከሁሉ በላይ አስበልጬ
ኮርስ ስማር ትዝ አለኝ ... በዛፉ ስር ተቀምጬ
.
አንገቴ ላይ የታሰረው .. ለምን ነበር ማኅተቤ
ዛሬ ለምን አታለልኩት .. በምክንያት ተንተብትቤ ?
.
ምኑ ነው የሆነብኝ .. ለቤተ መቅደስ እንቅፋት ?
ትዳር ለምን መሰለኝ .. ሜዳ ሆኖ ተዳፋት ?
ልቤ ከብዶ እስከመቼ .. እኖራለሁ በጥፋት ?
ነፍሴንስ ምንበወጣት ... በ'ሳት ጅራፍ ላስገርፋት
.
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ሰው መስዬ ሲመግቡኝ .. ባ'ይኔ ብሌን አይቻለሁ
ታዲያ ግን ምን ዋጋ አለው .. ማንበብ እንደሁ ትቻለሁ
.
እውነት ነው አይካድም .. አውደ ምኅረት መቀመጤ
ወንጌሉንም እየሰማሁ .... ሳላስበው መመሰጤ
ትዝ ይለኛል አጀንዳዬ ... ከንፈሮቼንም መምጠጤ
.
ጽዋ ቢሉ ዝክረ ሰንበት .. እንዳያልፈን ስንጣራ
ዓርብ ጸሎት ስንሰለፍ .. ነጭ ለብሰን በጋራ
ከትንሹም ከትልቁም ... ስለድኅነት ስናወራ
"ጉዞ" ብለን በባዶ እግር .. ሳንደክም በተራራ
ነጭ ለብሰን ጧፍ ይዘን .. እንደ ኮከብ ስናበራ
አዎ! አስታውሳለሁ ... ስልሳ ፍሬ ስናፈራ
.
ጾም ጸሎቱ ትዝ ይለኛል .. በላያችን ስናጌጠው
በስግደት ተሽቀዳድመን ... ሳጥናኤን ስናመልጠው
ብዙ ነበር በንስሐው ... በቁርባኑ የሚገልጠው
.
ጌታ ሆይ!
ተመልሶ ይላክልኝ ... መንፈሳዊ ጀግንነቴ
በመቅደስህ ዋጋ ይክፈል .. የናቡቴ ልጅነቴ
"እሺ" ብሎ እንዳልሰራው .. አይሁንብኝ ማንነቴ
.
ቀራኒዮ አይረሳኝ ... ችንካር ያለው መስቀሉ
በክቡር ደም ተነክሮ .. ቀይ ሆኖ መንቀልቀሉ
.
እመ ብርሐን በልደቷ .. ትመልሰኝ ወደ ጥንቱ
የቅዱሳን ጥበቃቸው .... አይለየኝ በረከቱ
ናፈቀኝ
ሰነፍ ልቤ እየገዛኝ .. በሞት ሰይፍ በጫጨቀኝ
ይቅር በለኝ አምላኬ! ... ከመቅደስህ አታርቀኝ
በግራ መቆም መረረኝ ፤ አሰልፈኝ በልጅህ ቀኝ
አብርሃምን ላክና ... መልስህን ቶሎ አሳውቀኝ
በራሴ አይን ስደናበር.. መታዘብህ አስጨነቀኝ
የምኅረት ቃል አንደበትህ ፤ ፅኑ ፍቅርህ ናፈቀኝ።

#ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
___________________


@aleroe
ኤልሮኢ:
​​ስምህ በሁሉ

ስምህ በሁሉ ተመሰገነ
ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ
አንተን ማወደስ ያስደስተናል
ስምህን ማክበር ክብራችን ሆኗል(፪)

አምላክ ተመስገን በሰማያት
ስምህ ይወደስ በፍጥረታት
ከህፃናት አፍ ምስጋና ይውጣ
አንተን ማመስገን ይሁን የኛ ዕጣ(፪)
አዝ = = = = = =
በምግብ እጦት ብንሰቃይም
ማህሌትህን አናቋርጥም
የመከራ ዶፍ ቢወርድብንም
እንዘምራለን ለአምላካችን ስም(፪)
አዝ = = = = = =
ሰማዩ ዝናብ ደመና ቢያጣም
ፍቅርህ በእኛ ውስጥ አላቋረጠም
ቸርነትህን እንጠብቃለን
ከአንተ ደጅ ጌታ የት እንሄዳለን(፪)


#ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ



@aleroe
ኤልሮኢ:

አብይ ጾም -የካቲት 25 /06/2011 ሰኞ
ደብረ ዘይት- መጋቢት 22/07/2011 እሁድ
ሆሣዕና- ሚያዚያ 13/08/2011 እሁድ
ስቅለት - ሚያዚያ 18/ 08/2011 አርብ
ትንሳኤ- ሚያዚያ 20/08/2011 አሁድ
እርክበ ካህናት - ግንቦት 14/09/2011 እሮብ
ዕርገት - ግንቦት 29/09/2011 ሀሙስ
ጰራቅሊጦስ - ሰኔ 9/10/2011 እሁድ
ጾመ ሀዋርያት - ሰኔ 10/10/11 ሰኞ
ጾመ ድህነት - ሰኔ 12/10/11እሮብ

@aleroe
ኤልሮኢ:

💚💛❤️ የሕጻን ነገር 💚💛❤️
-------------------

አንድ መምህር በስብከተ ወንጌሉ መርሐ ግብራቸው ስለመንግስተ ሰማያት ጥሩ አድርገው ይተርኩና ሕዝብ ሁሉ መመሰጡን ሲያዩ "አሁን ከእናንተ መኻል መንግስተ ሰማያት መግባት የማይፈልግ አለ??" ብለው በጅምላ ሲጠይቁ ሁሉም በህብረት "የለም!" ብለው መለሱ።

:በዚህ ያልረኩት መምህር "እስኪ መንግስተ ሰማይምት መግባት የምትፈልጉ እጃችሁን ወደላይ አውጡ" ይላሉ። ሁሉም ያወጣል

:አንድ ሕጻን ግን ትንንሽ እጆቹን በጉንጮቹ ላይ አድርጎ ክርኑን በጉልበቶቹ ላይ ተክሎ በሚያሳዝን አኳኋን ተቀምጦ መምህሩን ብቻ ያያል። የሕጻኑ ሁኔታ የገዛችው መምህር ወደ ሕጻኑ ጠጋ ብለው "ማሙሽዬ አንተ ለምን እጅህን አላውጣህም? መንግስተ ሰማይ መግባት አትፈልግም?" አሉት

: ሕጻኑም ነቃ ብሎ "መግባትማ እፈልጋለሁ ነገር ግን እናቴ ጉባኤው እንዳለቀ የትም መሔድ የለም ባስቸኳይ እቤት እንድትመጣ ስላለችኝ ነው" አለ ይባላል።

ሕጻኑ የእናቱን ዐደራ ማስታወሱ የሚደነቅ ነው። የሕጻን ነገር ያልነው ግን መንግስተ ሰማይ ላለመግባት ያቀረባትን ምክንያት ለመጥቀስ ነው።
#ዛሬም በየዓውደ ምህረቱ ማዕደ እግዚአብሔር ተዘርግቶ፤ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጸሎት እየደረሰ ልባችን እቤት ሆኖ የተቋጠረ ሲፈታ፤ የተፈታ ሲቋጥር ጊዜውን የምንጨርስ ስንቶች አለን።

#ላለመጸለይ #ላለማስቀደስ #ንስሀ ላለመግባት #ላለመቁረብ ምክንያት መደርደር ከገሃነም እሳት አያድነንም!!!!!!!!!!!!!!!!

@aleroe
ምን ያህል ወደዱት????
ኤልሮኢ:

".....ልቡ ግን ከእኔ ርቋል..."


አንድ ባሕታዊ ብዙ ሰዎች ሰብስበው እየሰበኩ ሳለ ጭራቅ ከጫካ ወደ ጉባኤው ይመጣል። ወደ ባሕታዊው ቀረብ ይልና "አባቴ እንግዲህ እንደምታውቁት የእኔ ሕልውና በሰው ሥጋና ደም ላይ የተመረኮዘ ስለሆነ እነኝህን ሰዎች ልበላቸው ነው" አላቸው።

ባሕታዊውም የሰው ሥጋ መብላትህን አውቃለሁ ግና እነዚህ ልጆቼን አትበላሸቸውም የክርስቶስ ናቸውና አትችልም ብለው ገዘቱት።

አቶዬም ግድ የሎትም አባቴ እኔ የክርስቶስ የሆኑትን አልበላም ንክችም አላረግም ሲል ቃል ገባላቸውና ተለያዩ።

ከሄዱበትም ሲመለሱ ጭራቁ ባሕታዊው ያስተማሩትን ሰው ሁሉ በልቶ ከንፈሮቻቸውንና ምላሳቸውን አስቀርቶ ጠበቃቸው ። በጉዳዩም በጣም የተቆጡት ባሕታዊ ምነው የክርስቶስ ናቸው እንዳትበላ አላልኩህም አሉት።

ጭራቁም በሰው ደም የለሰለሰውን ከንፈሮቹን በምላሱ እያበሰ "የክርስቶስ የሆኑትን አሁንም አልበላሁም" ብሎ በኩራት መለስላቸው።

ምን ማለትህ ነው ያስቀረኸው የለም እኮ ቢሉት "አባቴአባቴ የክርስቶስ የሆነው ምላሳቸው ነው። ክርስቶስ ያለው ከንፈሮቻቸውና ምላሳቸው ላይ ብቻ ስለሆነ ሌላውን አካላቸውን በላሁት" አላቸው።
ዛሬም በክስርቶስ ስም ተጠርተን አካላቱ ሆነን ልንመላለስ በሚያስፈልግበት ጊዜ እኛ በእርግጥ ሆነናል ወይስ እንደሰዎቹ ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት ነን።

ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ ርቋል ማቴ ፲፭፣፯ ቃሉን ሰምቶ የማያድርገው ፊቱን በመስታወት እንደሚያይ ሰው ይመስላል። ፊቱን ካየው በኋላ ዞር ሲል ፊቱን ይረሳዋልና።
👉@aleroe👈
👉@aleroe👈
👉@aleroe👈
ኤልሮኢ፡(ስነ ፅሁፍ)

……🖌ላዩን ውብ ሆኛለሁ

ላዩን ውብ ሆኛለሁ ውስጤ ግን እረክሷል፣
ንፅህና የለም በኃጥያት ቆሽሿል።
አንደበቴ ሀያል ሁሉን አወቅኩ ባይ ነው፣
የተለሳለሰ ደግ መሳይ መርዝ ነው።
ለተመለከተኝ ላስተዋለኝ ሰው፣
ክንፍ እንጂ ምን ቀረው የማይለኝ ማነው።
በጎ ስነምግባር ትህትና የሌለኝ ፣
መስዬ የምኖር የስም ክርስቲያን ነኝ።
ፍሬ አልባ ወይን ነኝ የማላስደስት፣
አንተ ይቅር በለኝ አምላከ ምህረት።
መወደስ በከንቱ ከእንግዲህ ይብቃኝ፣
እውነተኛ እንድሆን ፈጣሪዬ እርዳኝ።

👉👉👉👉@aleroe👈👈👈👈
ኤልሮኢ:
#ጽኑ_ሰማዕት

ጽኑ ሰማዕት የእምነት አርበኛ
አርሴማ ነይ ነይ ወደኛ
------------------------------
ነይ ነይ ቅዱስ አትናትዮስ
›› ›› በስዕለት ያገኙሽ
›› ›› ብሉይን ከሀዲስ
›› ›› ጠንቅቀሽ የተማርሽ
›› ›› በፍፁም ትህትና
›› ›› በጸሎት የተጋሽ
›› ›› አርሴማ ልዩ ነሽ
›› ›› አምላክ የመረጠሸ
-------------------------------
ነይ ነይ ውበትም ሀሰት ነው
›› ›› ደም ግባትም ከንቱ
›› ›› ንብረት ትዳር ሁሉ
›› ›› አላፊ ውዕቱ
›› ›› ንግስት መባልን
›› ›› በፍጹም ሳትሻ
›› ›› አለምን በመናቅ
›› ›› ገባች ወደዋሻ
-------------------------------------
ነይ ነይ አረመኔው ድርጣድስ
›› ›› ቢያሰቃይሽም
›› ›› ውበቴ ክርስቶስ
›› ›› ነው ብለሽ ሰበክሽ
›› ›› አንገትሽን ለሰይፍ
›› ›› አሳልፈሽ ሰጠሸ
›› ›› ክብርሽም ተገልጾ
›› ›› ለአለም አበራሽ
---------------------------------
ነይ ነይ አርአያ ልትሆኝን
›› ›› ለእኛ ለሁላችን
›› ›› ፈፅመሽ አሳየሽ
›› ›› ታላቅ ተጋድሎሽን
›› ›› ይህን አለም ድል መንሳት
›› ›› አቅቶናል እና
›› ›› አርሴማ አትለይን
›› ›› በእምነት እንድንጸና

@aleroe
ኤልሮኢ:

#አስተውል

☞ ከጎንህ ያለችው ሚስትህ ~ የላጤዎች ሁሉ ምኞት ናት፤
☞ የከዳሀው ልጅህ ~ መውለድ የማይችሉ ሁሉ ምኞት ነው፤
☞ ደሳሳ ጎጆህ ~ ቤት የሌላቸው ሁሉ ምኞት ነች፤
☞ አድካሚ ስራህ ~ ስራ የሌላቸው ሁሉ ምኞት ነው፤
☞ ትንሿ ሀብትህ ~ ምንም ሀብት የሌላቸው ሁሉ ምኞት ነች፤
☞ ውድ የሆነው ጤናህ ~ አልጋ ላይ የሚማቅቁት ሁሉ ምኞት ነች፤
☞ ትንሿ ፈገግታህ ~ የተጨነቁ ያዘኑት ሁሉ ምኞት ነች፤
☞ ሚስትህ የደበቀችልህ ገበና ~ የተጋለጡት እና
የተዋረዱት ሁሉ ምኞት ነች፤
☞ በነፃነት እንደፈለክ የምትንቀሳቀሰው ~ በእስር የሚሰቃዩ መንቀሳቀስ የማይችሉት ሁሉ ምኞት ነች፤
***፦እስኪ መዳፍህን ተመልከት በብዙ ስጦታ በረከት ተሞልቷል፤ ነገር ግን የፈጣሪ ስጦታ በጣምምም በዛና የተሰጠንን ሁሉ ማየት ተሳነን፤
የሚያይ አይን ሳይሆን የሚያስተውል ልቦና ይስጠን
እና እግዚአብሔርን አመስግን ።

@aleroe
ኤልሮኢ:(ስነ ፅሁፍ)

#በምህረቱ መራኝ

ትላንት ነበርኩኝ እያለው የሌለው
እንዳማረ ተክል ፍሬ እንደሌለው
ደስታዬም ነበረ ለሞቴ መንገዱ
ህይወቴም ሚመስሉ አንዳች ያልተጎዱ
እውነታው ባይገባኝ የመኖሬ ምክንያት
እጆቼን ዘረጋው እምባዬም ፈሰሰ
ጉልበቴም ታዘዙ ለዳንስ እንዳልተነሱ
ልሳኔም በቃሉ ይቅርታን ለመነ
የወደቀልኝን እርሱን አገነነ
መውደቄን ተረድቶ የማይለኝ ችላ
አምላከ ብርሃን ህይወቴን አጎላ
በመሃሪነቱ ምህረቱን ሽሮኝ
ለህይወቴ ፍዳ መፍትሄው ሆነኝ



___
👉👉👉@aleroe👈👈👈
ኤልሮኢ:(መዝሙር)

ገብርኤል ነው

ገብርኤል ነው አምላክ የሾመው(፪)
አናንያን አዛርያን ሚሳኤልን ከእሳት ያዳነው

ናቡከደነፆር አንተን በግልፅ አይቶ
ለእግዚአብሔር ሰገደ ያንን ምስል ትቶ
ሐሰትም እነደሆን ይመስክሩ ሦስቱ
ከዚያች ከባቢሎን (፪) የወጡት ከሳእቱ
አዝ = = = = =
ከዓለመ መላእክት ከቅዱሱ ቦታ
የሰውን ልጅ መረጥክ ልትረዳ ጠዋት ማታ
አንጌቤናይቷ ቅድስት ኢየሉጣ
ትመስክር ስላንተ(፪) ከነልጇ ትምጣ
አዝ = = = = =
ልመስክር ስላንተ ነህና ሕይወቴ
ገብርኤል (፪)ሰመረ ስለቴ
የአናብስቱን አፍ የዘጋኸው መላክ
ገብርኤል አንተ ነህ (፪)በእኛ ሁሉ የታመንክ


ቀሲስ ዘበነ ለማ


@aleroe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤልሮኢ:

ለራስህ ነው

አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ! ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡
ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡ ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡ እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ

@aleroe
ኤልሮኢ:

#ነበርኩ_መች_ያድናል


ሀጢያትን ስትሰራ አምላክን እረስተህ
ቅዱሱን ሰውነት በሀጢያት አርክሰህ
ትእዛዝን ሳትፈጽም መልካምን ሳትሰራ
ዘይት ሳታዘጋጅ መብራትህ ሳይበራ
በተጠራህ ጊዜ መላከሞት ሲመጣ
ለማያልፈው አለም ሲወጣልህ እጣ
ለሚዛን ስትቀርብ አገልጋይ ነበርኩኝ እያልክ መናገሩ
መዝሙር ዘምሬያለው ሄጃለው ከበሩ
ብሎ መከራከር ያኔ መች ይጠቅማል
ይዞ መገኘት ነው ነበርኩ መች ያድናል!!!!
____________________

@aleroe
ኤልሮኢ:

​​አድርገህልኛልና በቸርነትህ

አድርገህልኛልና በቸርነትህ
አመሰግንሃለሁ እልል፪
ለዓለመ ዓለም አማኑኤል
እገዛልሃለሁ መድኃኔዓለም፪

ቀኑ ጨልሞብኝ ዙሪያው ገደል ሆኖ
የችግር አረንቋ ፊቴ ተደቅኖ
ረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ
ፍጽሞ አራቅህልኝ የልቤን ትካዜ
አዝ = = = = = =
አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያዬ
ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻዬ
እንደማትተወኝ አሁን አውቄአለሁ
ካለኝ ነገር ይልቅ በአንተ ታምኛለሁ
አዝ = = = = = =
ጥቂቷን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ
የምመልስልህ ባለገኝ ሥጦታ
በቀንም በሌትም ሁሌ ለሚያበራ
መንክር ለባሕርይህ ዕጽብ ለአንተ ሥራ
አዝ = = = = = =
አምላክ ሆይ ምሥጋና ለአንተ ይገባሃል
ለምስኪኗ ጎጆ በረከት ሰጥተሃል
ደሃ ነኝ አልልም ሀብቴ አንተ ነህና
ማሰሮዬ ሞልቷል ላይጎድል እንደገና



<< አድርገህልኛልና ለዘላለም አመሰግንሃለሁ >>
መዝ፶፪፥፱

@aleroe
ኤልሮኢ፡
አድዋ

………………
ምንሊክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ
በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣሊያን አበሻ እንዳይደርስ
ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ሁዋላ አይገኝ
አባተ በመድፉ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጎጃሙ ንጉሥ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሀን
ዳዊቷን ዘርግታ ሰምዐኒ ስትል
ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል
ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል
እንደ በላዔ ሰብእ እንደመቤታችን
ሲቻለው ይምራል የኛም ጌታችን።

@aleroe
ኤልሮኢ:(መዝሙር)
#ንጹም_ፆመ

ንጹም ፆመ ወናፍቅር ቢጸነ
ወንትፋቀር(፬) ንትፋቀር በበይናቲነ ኧኸ(፫)
#ትርጉም
ፆምን እንጹም ባልንጀራችንን እንውደድ
እርስ በራሳችንም እንፋቀር


@aleroe
ኤልሮኢ:
፨መርሳት፨

በአንድ ወቅት የግብጹ ሊቀ ጳጳስ ብጹኡ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ እያስተማሩ ባሉበት ወቅት በዙ ጥያቄዎች በጹሑፍ ይደርሳቸው ነበር። ታዲያ ከነዛ ጹሑፎች መካከል አንዱ እንዲ ይላል
... አባቴ እኔ ታላቅ የመርሳት ችግር አለብኝ ያደረኩትን የሰማሁትን ነገሮች በሙሉ እረሳቸዋለው እና አባቴ ምን እንደማደርግ ይምከሩኝ ነበር የሚለው። ብጹእነታቸውም ልጄ መምከሩንስ እመክርሃለሁ ምን ማድርግ እንዳለብህ እነግርሃለሁ ግን እንዳትረሳው እፈራለሁ አሉት ይባላል።
ቃለ እግዚአብሔር ስንሰማ በማስተዋል ልቦናችንንም ሰብስበን ሊሆን ይገባል።
በነገሮችም ሁሉ አስተዋዮች ልንሆን ይገባል።በዚህም ማስተዋል እና ጥበብን ወደሚሰጥ አምላክ አጥብቀን ልንማጸን ይገባናል።

@aleroe