"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ኤልሮኢ:(ዝማሬ)
#ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን

ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን /2/
ድንበር የሚጠብቁትን /2/
ጠብቅ እግዚአብሔር ሠራዊቷን /4/

የደም መሬት አትሁን ደም አይፍሰስባት
ካንተ የመነጨ ሰላም ይስፈንባት
አሽናፊ እንድትሆን ለስምህ ተገዝታ
አይንህን ሳትመልስ እያት ጠዋት ማታ

#አዝ

ሰንሰለት ሲፀና ለመከራ ፈርቶ
ኢትዮጲያዊ መልኩን አይቀይርም ከቶ
ድንቁን ብርሃን ያያል ወቶ ከጨለማ
በመንገዱ ሁሉ አዳኝ ቀኝ ቀድማ

#አዝ

እጅግ የፈተናት ተናቅሎላት መርዙ
ከእግሮቿ በታች ጠላቶች ይገዙ
ደጅ ስትጠና እጆቿን ዘርግታ
ጠብቅ ሠራዊቿን ዱሩ እንዳይፈታ

#አዝ

ከራሳቸው ይልቅ ኢትዮጵያን ወደዱ
ደም ከፍለው ሊያቆዮት በዱር ተሰደዱ
በሃሩር በውርጩ የሆኗትን አጥር
በማይፋቅ ቀለም ፃፋቸው ለክብር

ሊቀ-መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ


@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ነሐሴ 19/12/2012 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፵፬፥፱(44፥9)
ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምኢ እዝነኪ

ምስባክ ዘቅዳሴ

በእግዚአብሔር እሴብሕ ቃልየ
በእግዚአብሔር ይከብር ዘነበብኩ
ወበእግዚአብሔር ተወከልኩ ኢይፈርህ ምንት ይሬስያኒ

ቅዳሴ

👉ዘእግዝእትነ አው ግሩም


@aleroe
ኤልሮኢ:(ትርክት ወምክር)

አንተ ግን ሰው ነህ?


አንዱ ወደ አንድ አባት ቀረብ ብሎ "ድንግል ማርያም እኮ እንደ እኛ ሰው ናት" አላቸው። እርሳቸውም "ልክ ነህ እርስዋ
በተፈጥሮዋ ሰው ናት ፣ አንተ ግን ሰው ነህ?" አሉት። ነገሩ ስድብ ይመስላል ፣ አስተውሎ ላየው ግን ሰው ነኝ ለማለትም መሥፈርት እንዳለው ያስታውሳል። "ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ" ነገር ግን ዝናምን በጸሎቱ ያቆመ መሆኑን ስንሰማ ሰው ነን ለማለት እንፈራለን። ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ሰሎሞን "ሰው ሁን" ያለው ሰው መሆን ማለት እንደ ሰው ክብርን አውቆ መኖር ስለሆነ ነው። ክቡር ሆኖ ሳለ ካላወቀና በኃጢአቱ ከጸና እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል። ሰው ለመሆን ብዙ መሥፈርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተቀምጠዋል ፣ የድንግል ማርያምን እናትነት መቀበልም ሰው የመሆን ምልክት
ነው። "ሰው እናታችን ጽዮን ይላል" ተብሎ እንደተጻፈ "ጽዮን እናታችን" ማለት ያልቻለ ምኑ ሰው ይባላል? "የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮን ሆይ ይሉሻል የናቁሽ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ" ተብሎ ለዳዊት ከተማ ተነግሮላት ነበር። ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮትባት ለሚውልባት ለዳዊት ከተማ የሚሰገድ ከሆነ ለንጽሕቲቱ ከተማው ለድንግል ማርያም አይሰገድም እንዴት
ይባላል? ነቢዩ ከጽዮን ጫማ በታች ይሰግዳሉ ብሎ ለዳዊት ከተማ ከተናገረ ከድንግሊቱ ጫማ በታች እንዴት ይሰገድ ይሆን? በእርግጥ የናቅዋት ሁሉ ወደ ጫማዋ ሊሰግዱ ይሆን? በፍጹም
አይሆንም! የድንግልን ጫማዋንማ ለእኛ ለምናከብራትም ማን ባደለን? እኛ አክሱም ጽዮን ቁስቋም ግሸን በረከቷን ሽተን እየተጓዝን የናቋት እንዴት ጫማዋን ያገኛሉ? አባ ጊዮርጊስ "ገሊላዊትዋ ድንግል ጫማን እሸከም ዘንድ ፣
ጥላዋ ያረፈበትን እስም ዘንድ ማን ባደለኝ?" ይል የለምን? ከእግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ ማለት ይዋረዳሉ ነው እንጂ ይህ ክብር ለናቋት የሚገባ አይደለም። "ጽዮንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ" (መዝ 48:12)


@aleroe
ኤልሮኢ:
ማርያም ዐርጋለች

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት (2)
የሰማይ መላእክት እያጀቧት
እርሷም እንደ ልጇ ተነሥታለች
የአባቷ ዳዊትን ትንቢት ልትፈጽም
ወርቁን ተጎናጽፋ በቀኙ ልትቆም
ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት
ዐረገች በእልልታ ድንገል የኛ እናት
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት (2)
የሰማይ መላእክት እያጀቧት
እርሷም እንደ ልጇ ተነሥታለች
ሰማይም ይከፈት ደመናም ይዘርጋ
ዝምታ አይኖርም እመ አምላክ ዐርጋ
አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን
ከዘለዓለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት (2)
የሰማይ መላእክት እያጀቧት
እርሷም እንደ ልጇ ተነሥታለች
የአምላክ ማደርያ ያ ቅዱስ ሥጋሽ
አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ
ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው
ተነሥተዋል በክብር በእምነት አየናቸው
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት (2)
የሰማይ መላእክት እያጀቧት
እርሷም እንደ ልጇ ተነሥታለች
ሐዋርያት አበው እንኳን ደስ ያላችሁ
በክብር ዐረገች ማርያም ሞገሳችሁ
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኗን ይዛችሁ
የድንግል ዕርገቷን ንገሩ ተግታችሁ
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ነሐሴ 24/12/2012 ዓ.ም

ምስባክ፦ 144÷16

ዐይነ ኲሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ
አንተ ትሁቦሙ ሲሳዮሙ በጊዜሁ
ትሰፍሕ የማነከ ወታጸግብ ለኲሉ እንስሳ ዘበሥርዓትከ።


ወንጌል
ዮሐ ፮፥፵፩ - ፍጻሜ

ቅዳሴ
ዘኤጲፋንዮስ


@aleroe
ኤልሮኢ:(ምክር)

እንደማታሸንፉን ንጉሡም ይወቅ!

ክርስትናን ከሐዋርያት ተቀብለው ያቆዩልን አበው፡ በነገሥታትና በባለሥልጣናት እጅግ ብዙ መከራን ተቀብለዋል፡፡ ይደርስባቸው ከነበረው የመከራ ብዛትና አስከፊነት የተነሣ ብዙዎች ቢንገላቱና ቢሞቱም ግና፡ የሰማዕታቱ ደም ለክርስትና ስፋት ዘር፣ የአበው ጽናትም ለደቂቀ አበው መኸር (ብርታት) ኾነው ክርስትና
ይበልጥ ስታብብ ኖራለች፡፡ ከእነዚህ አበው አንዱ ከአባቱና ከሴት አያቱ ይማር የነበረውና በታላቅ እኅቱ በቅድስት ማቅሪና መሪነት ከታናሽ ወንድሙ ከቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ጋር በብርታት የጎለበተው የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ የልብ ወዳጅ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ነው፡፡ ባስልዮስ በጥብዓታቸው ከሚታወቁት አበው አንዱ ነው፡፡ በአንድ ወቅት በጊዜው የነበረው ንጉሥ ቫለንስ፡
አገረ ገዢውን (እንደራሴውን) ልኮ የአሪዮስን ክሕደት መደገፍ እንዳለበት ቢያሳስበውም፡ ቅዱሱ ግን በአስደናቂ ጥብዓት ሳይፈራ ይመልስለት ነበር፡፡
የቅዱስ ባስልዮስን ጽንዓት ያስተዋለው አገረ ገዢው፡ ሀብቱን ኹሉ እንደሚወርስበት ፣ እንደሚያሰቃየውና
በግዞት እንደሚሰደው ዛተበት፡፡ በዚኽ ጊዜ ቅዱሱም ሀብቱን በተመለከተ ካባውና ጥቂት መጻሕፍቱ እንጂ ይወረስብኛል ብሎ የሚሠጋበት ምድራዊ ሀብት እንደሌለው፣ በግዞት መሰደድን በተመለከተ በምድር ላይ የትም ቦታ ቤቱ እንደ ኾነና እንደማያሠጋው፣ ስቃይን በተመለከተም አካሉ የመጀመሪያውን ሞት ለመሞት እንደሚሽቀዳደምና፣ ቢገለው እርሱን ወደ አምላኩ በቶሎ በመላክ ውለታ እንደሚውልለት ቅንጣት ሳይፈራ
በጥብዓት መለሰለት፡- ‹‹የምኖረው ለእርሱ፣ (አመሰግነው ዘንድ) የምጣደፈውና የተፈጠርኩትም ለእርሱ ነውና ወደ እግዚአብሔር ይበልጥ ስለሚያቀርበኝ ሞት ለእኔ ችሮታ ነው፡፡››
በዚህ ምላሹ የተገረመው አገረ ገዥም ‹‹ማንም ሰው ከዚህ በፊት በእንዲኽ ዓይነት ድፍረት አናግሮኝ አያውቅም›› ቢለው፡ ቅዱስ ባስልዮስም፡-
‹‹ምናልባት ክርስቲያን የኾነ አባትን አግኝተህ አታውቅ ይኾናል፡፡ እሳት፣ ሰይፎች ፣ አውሬዎች እና የሰውነት
አካልን የሚቆራጡባቸው መሣሪያዎች ለእኛ አስደንጋጭ ሳይኾኑ በደስታ የምንቀበላቸው ናቸው፡፡ አጥቁን ፣
አሠቃዩን፣ አስፈራሩን፣ የምትችሉትን ኹሉ አድርጉ፣ በጉልበታችሁ ተመኩብን…. ነገር ግን እጅግ በከፋ ጭካኔ ብታስፈራሩንም እንኳን እውነትን ትሸፍኑ ዘንድ በምንም ዓይነት መንገድ እንደማታሸንፉን ንጉሡም
ይወቅ፡፡›› ሲል መለሰለት፡፡ ከዚህ በኋላ ንጉሡ ቅዱስ ባስልዮስን መቃወምን አቆመ፡፡ ንጉሡም ኾነ አገረ ገዢው ግን እጅግ ተደንቀውበት ነበር፡፡ በሌላ ጊዜ የጶንጠስ አገረ ገዢ ባስልዮስን ያስፈራራው ጀመር፡፡ ቅዱሱ ግን ፈጽሞ አልፈራለትም፡፡ አገረ ገዢው ወደ ፍርድ አቅርቦት ‹‹ጉበትህን ነው ቆርጬ የማወጣልህ›› ሲለው ባስልዮስም ‹‹እባክህ አድርገው፤ እንዲያውም ውስጥ ኾኖ እያስቸገረኝ ነው›› ብሎ መልሶለታል፡፡ የቅዱስ ባስልዮስ በረከት ይደርብን፡፡ አሜን፡፡

በዲ/ን ሕሊና በለጠ

@aleroe
ኤልሮኢ:(ፀሎተ አበው)

አቤቱ ሆይ ነፍሴን ውደዳት ደንዳና ያልሆነ ኀሊናንም አድለኝ። በአንተም ጋሻ ሰውረኝ። አንተ ከወደድከኝ ማን ይጠላኛል? ጠላቶቼ ይፈሩኛል። ባለጋራዎቼም አይችሉኝም፤ አጋንንት ከእኔ ይርቃሉ፤ መላእክትም ይቀርቡኛል። ፀሐይ ያመሠግነኛል። ጨረቃም ይባርከኛል።ከዋክብትም ያወድሱኛል። አቤቱ አንተ ካልወደድከኝ ማን ይወደኛል? ጓደኞቼ ይጠሉኛል የሚቀርቡኝም ከእኔ ይርቃሉ መላእክትም ይሸሹኛል አጋንትም በፊቴ ይሣለቃሉ እግሮቻቸው እንደላም እግር ነው። ራሣቸውም የተከፈተ ነው። ጦራቸውም የተገተረ ነው።

ፀሐይ ይከሰኛል ጨረቃም ታጣላኛለች። ኮከቦችም ይዘልፋኛል። አንተ ካልወደድከኝ ስድቤ ምን ያህል ይበዛ? ከወደድከኝም ክብሬ ምን ያህል ይበዛ? አንተ የባረከውን ሁሉም ያመሠግነዋልና። የሌላ /የጠላት/ እጅም አይቆርጠውም፤የሰይጣን ክንድም አያንገላታውም። የጸጋህ ባዕለጸጋነት ይራራለታልና። አቤቱ ፈጽሜ በደልሁበደልሁ፤ በፊትህም የማይገባኝን አደረግሁ። እኔ ባስቆጣህም ወደ እናትህ ምልጃ ተመልከት። በማድረግም ቢሆን በመናገርም ቢሆን እኔ ዝሙት ባደርግ ሊተረጉሙት ወደማይቻል ወደ እናትህ ድንግልናዊ ንጽሕና ተመልከት። በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ብዋሽ ስለ እኔ በመማለድ ወደምትጮህ ወደ ተሸከመችህ ወደ እመቤታችን ምልጃና ጸሎት ተመልከት፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ኆኀተ ብርሃን ምዕራፍ 1 ቁጥር 22-23


@aleroe
"ነሐሴ 26፦ ይህች ዕለት የታላቁ ቅዱስ አቡነ ሀብተማርያም በዓለ ፅንሰታቸው ናት” በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ታላቁ ጻድቅ አቡነ ሀብተማርያም የተወለዱት በመንዝ አውራጃ ልዩ ስሙ የራዊ በተባለ ቦታ ሲሆን የአባታቸው ስም ፍሬ ብሩክ የእናታቸው ስም ዮስቴና ይባላል፡፡ ከታላቁ የተጋድሎ አርበኛ ፃድቅ አባታችን ቅዱስ ሀብተማርያምና በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ሌሎች ቅዱሳንና ሰማዕታትም ቃልኪዳን ፣ ረድኤት ፣ በረከት ያሳትፈን! አሜን!

@aleroe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

ዝሙት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ጫት መቃም . . . ወዘተ የሚከለክለው ጥቅሱ የቱ ጋር ነው?


@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ነሐሴ 29/12/2012 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፻፲፥፫(110፥3)
ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለተ ኃይል
በብርሃኖሙ ለቅዱሳን
ወለድኩከ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ


ምስባክ ዘቅዳሴ

እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንጹሐ
ማዕዜ ትመጽእ ኀቤየ
ወአሐውር በየዋሃተ ልብየ ማዕከለ ቤትየ


ቅዳሴ

ዘእግዚእነ (ነአኩተከ)

@aleroe
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

፨ በመንፈስ ጀምሮ በሥጋ መጨረስ ፨
ጌታችን በውኃ ላይ እየተራመደ ወደ ሐዋርያት ሲመጣ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ተመልክቶ በእምነት " ጌታ ሆይ
በውኃ ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ" አለው። ጌታም እምነቱን ተመልክቶ "ና" አለው። ቅዱስ ጴጥሮስ ከታንኳይቱ ወርዶ ወንድሞቹ ሐዋርያት እስኪደነቁ ውኃውን
እንደ የብስ በመቁጠር በባህር ላይ እየተራመደ ወደ ጌታ ሄደ። ልክ ጌታችን ጋር ሊደርስ ሲል የንፋሱ ኃይል ሲያናውጠው ባህሩ የሚያሰጥመው ስለመሰለው እምነቱ ጎደለ። አጠገቡ በባህሩ ላይ የቆመውን ና ያለውን ጌታ ማሰብ ትቶ በሥጋ ፈርቶ "እሰጥም ይሆን" አለ። በባህሩ ላይ ያስኬደው፣ያቆመው እምነቱ ሲከዳው፣ ባህሩ አሰጠመው።
ጴጥሮስም በመንፈስ ጀምሮ በሥጋ ጨረሰ። አንተም በእምነት ጀምረህ እምነትህ ልክ ጌታህ ጋር ሊያደርስ ሲል በሥጋ ፍላጎት መናወጥ ከጀመርክ
በኃጢአት ባህር ትሰጥማህ። ብዙዎች መንፈሳዊነትን በጽኑ እምነት ጀምረው፣ልክ ጌታ ጋር ሊደርሱ ሲሉ፤የሰይጣን የፈተና ንፋስ እያንገዳገዳቸው፣ትዕግስት እያሳጣቸው ከመጽናት፤ በኃጢአት ባህር ሰጥመው መዋኘት ይጀምራሉ።
ቅዱስ ጴጥሮስ በእምነት የጀመረውን በሥጋ ቢጨርስም በባህሩ ሰጥሞ እንዳይቀር ጌታውን "ጌታ ሆይ አድነኝ"
ብሎ ጮኸ። ጌታችንም ቅዱስ ጴጥሮስን "አንተ እምነት የጎደለህ፣ስለምን ተጠራጠርህ?" ብሎ ወቅሶት እጁን፣ዘርግቶለት ከባህሩ አውጥቶታል።
አንተም ምንም በኃጢአት ባህር ብትሰጥምም፣ እምነት ቢጎድልህም ጌታህን "አድነኝ" ብለህ ብትጮህ ለጴጥሮስ የተዘረጋ እጁም ላንተ ይዘረጋል፣ከሰጠምክበትም ያወጣኃል። ብቻ አድነኝ ብለህ ጮህ። ማቴ 14÷25


@aleroe
ኤልሮኢ፡(ስነፅሁፍ)

ምንም አይምሰልህ

የምትሰራው ስራ ሰውን ካልበደለ፣
ክፋትና ተንኮል በልብህ ከሌለ።
ጠንቅቀህ ከፈፀምክ ማድረግ ያለብህን፣
ማንንም ካልጎዳህ ካመንክ አምላክህን።
ላንተ ጥቅም ብለህ ካልገፋህ ሌላውን፣
ይቅርታ ከለመንክ አምነህ ጥፋትህን።
የምታውቀው ታሪክ የምታውቀው ነገር፣
እንዳልሆነ ሆኖ ሲወራ ሲነገር።
የለብህምና ዝም ብሎ መስማት፣
ቀስ ብለህ ብትሞክር ለመስጠት እርማት።
ከእኛ ሌላ አዋቂ ፍፁም የለም ባዮች ፣
የወሬ አንበሳ የተግባር አንካሶች፣
የነገር ሱሰኛ የወሬ ጥመኞች።
ምንም እንደማታውቅ አድርገው ቢቆጡርህ፣
እውቀቱ ካንተ ጋር ታዲያ ምን ቸገረህ፣
አምላክ ካንተ ጋር ነው ምንም አይምሰልህ።

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ጳጉሜን 01/13/2012 ዓ.ም

ምስባክ

እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ 
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ መዝ ፵፱፥፫

ትርጒም

እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል
አምላካችን ዝም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል


የዕለቱ ወንጌል፦

ሉቃ ፲፯፥፳፪ - ፍጻሜ

ቅዳሴ
ዘዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ኀቤከ)


@aleroe
ኤልሮኢ:(መንፈሳዊ ትርክት)

+++ ልብስህን ማን ወሰደው? +++

በአንድ ወቅት አባ ሰራብዮን ወደ እስክንድርያ ሄደ፡፡ በገበያም ስፍራ አንድ ከልብስ የተራቆተ ነዳይ አገኘ፡፡ ለራሱም ‹ይህ ደሃ ሰው ታርዞ መነኩሴ የተባልኩ እኔ እንዴት ለብሼ እታያለሁ? በእውነት ይህ ‹ታርዤ አልብሳችሁኛልና› ብሎ የተናገረው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? በዚህ ብርድ አየር እየተሰቃየ እኮ ነው!› ብሎ ፈጥኖ የገዛ ልብሱን ከራሱ በማውለቅ ይለብስ ዘንድ ለዚያ ደሃ ሰጠው፡፡ ከዚያም በእጁ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደያዘ እርቃኑን በጎዳናው ላይ ተቀመጠ፡፡ የከተማውም ባለጠጋ ሰው አባ ሰራብዮን ባለበት ሥፍራ ሲያልፍ ተመልክቶት ወደ እርሱ ቀረበና ‹አባ ሰራብዮን ሆይ ልብስህን ማን ወሰደው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ቅዱስም በእጁ ወደ ያዘው መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቆመ ‹ልብሴን የወሰደው ይህ ነው!› አለው፡፡ ያም ባለጠጋ ልብስን ገዝቶ ካለበሰው በኋላ አባ ሰራብዮን ከእርሱ እንደ ተለየ በመንገድ ዕዳውን መክፈል ስላልቻለ እየተንገላታ ወደ ወኅኒ ቤት የሚሄድን አንድ ሰው ተመለከተ፡፡ ቅዱሱም አባት የያዘውን መጽሐፍ ቅዱሱን ሽጦ የዚያን ሰው ዕዳ በመክፈል ነጻ አደረገው፡፡ ይህንም ፈጽሞ ጉዞውን ሲጀምር ሌላ አንድ ነዳይ ሲለምን ተመልክቶ ዳግመኛ የለበሰውን ልብስ አውልቆ ሰጥቶ እርቃኑን ወደ በአቱ ተመለሰ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም እርቃኑን ባዩት ጊዜ ‹መምህር! ልብስህ ወዴት አለ?› ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹መጸወትኩት› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መልሰው ‹እኛን የሚያጽናናን መጽሐፍ ቅዱስህስ አባታችን? › ሲሉ ደግመው ጠየቁት፡፡ አባ ሰራብዮንም ‹መጽሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ ‹ሂድ ያለህን ሽጠህ ለድሆች ስጥ› ይለኛል፤ ስለዚህ እርሱንም ሸጥኩት› አላቸው፡፡

ምንጭ :–Paradise of the monks,

ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደሚናገረው ምጽዋት የፊት መብራት ናት፡፡ አንድ ሰው በጨለማ ሲጓዝ ከኋላው መብራት ቢያበሩለትም እንኳ ከፊቱ የሚቀድመው የገዛ የአካሉ ጥላ እንቅፋት እየሆነበት ይጥለዋል፡፡ ወደ ፊት ያለውን መንገድ አጥርቶ እያየ ያለ ስጋት ለመሄድ እንዲችል የግድ የፊት መብራት ያስፈልገዋል፡፡ ጾም ፣ጸሎት እና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋት እንደ ኋላ መብራት ናቸው፡፡ የፊት መብራት የተሰኘች ምጽዋት ካልታከለችባቸው እነዚህ ብቻቸውን ዋጋን አያሰጡንም፡፡ ከምጽዋት በላይ ታላቅ ነገር እንደሌለ ልንረዳ ይገባል፡፡ ዓለም ሁሉ ከነበረበት የበደል ዕዳ የዳነው ቸር እረኛ በሆነው በመድኃኔ ዓለም በአካሉ ምጽዋትነት (በሥጋው በደሙ መሰጠት) ነውና!!!


@aleroe
ኤልሮኢ:(ምክረ አበው)

#ወዳጄ ሆይ!

የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡

አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡ ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@aleroe
ኤልሮኢ:(ዝማሬ)

እንዴት ብትወደኝ ነው

እንዴት ብትወደኝ ነው የማትተወኝ (2)
ትዕግስትህን ሳስብ እጅግ ደነቀኝ(2)
እኔን ያዘልክበት ትክሻህ ሰፊ ነው
አእምሮዬም ልቤም አይችልም ሊለካው
ሞት የሚገባውን የስራዬን ብዛት
አይተህ እንዳላየ ተውከው በቸርነት(2)
ድንቅ ስጦታ ነው መልሰህ የሰጠኸኝ
ለኔ የወሰድኩት የማይገባኝ
ፍቅርህ ከሰንሰለት እጅግ ይበረታል
ዓመፀኛው ታዞ ያገለግልሀል(2)
ለበደለ በደል ላጠፋ ጥፋት
ይህን ነበር የማውቀው በዓለም ስርዓት
ያንተ ግን ይደንቃል ገዛኸኝ በምህረት
ፊቴ ትቆማለህ ሁሌ በቸርነት
ያፈቀረን አምላክ ጨክኖ ቢበድል
በፀፀት ይቀጣል በሂሊና ቁስል
ዓላማህ በኔ ላይ ፍቅር ስለሆነ
ህግህ ሊፈርድብኝ አንዴም አልጨከነ

#ሊቀ ዲያቆን ወንደሰን በቀለ

@aleroe
ኤልሮኢ :(ብሒለ አበው)

አንድ ሰው አንድ አባት ጋር ቀርቦ አንዳንዶች መላእክት ተገለጡልን ይላሉ ብሎ ጠየቃቸው።
እሳቸውም ከዚህ የበለጠ ደስ የሚያሰኘውስ ሁልጊዜ በኃጢአታቸውን ቢያዩ ቢያስቡ ነበር ሲሉ መለሱለት።
አንድ አባት እንዲህ አሉ ስሕተተኛ በሆናቹ ጊዜ ሁሉ ሌላውን አትወንጅሉ። ይህ የሆነው በራሴ ኃጢአትና ድክመት ምክንያት ነው በሉ። ቅዱሳን አባቶቻችን እንዲህ በማለት ተናግረዋል በርግጥ መላእክት ሊታዩክ ቢችሉ እንኳን አትቀበል ራስህን አዋርድ። እኔ ሃጢአተኛ ነኝና መላእክትን ባይ ምን ይጠቅመኛል በል።

@aleroe
ኤልሮኢ:(ምክረ አበው)

++ አባቶቻችን እንዲህ አሉ ++

"መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም"
ቅዱስ ባስልዮስ

"በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው" ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ

"ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ

"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው"
ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ

"እግዚአብሔር ለአብርሃም "ከሀገርህ ውጣ ከወገኖችህ"ተለይ ብሎት ነበር። በዚህ ጥሪ እግዚአብሔር ሁላችንንም የተወለድንበት ዘር እንድንተው ይጠራናል። ሰማዕቱ ዮስጦስ (100 AD-165 AD)

"ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ (160 AD - 220 AD)

‹‹ይጸልያል ነገር ግን የሌሎችን ጸሎትም ይሰማል፡፡ ያለቅሳል የሌሎችን ዕንባ ግን ያብሳል፡፡ ሰው ነውና አልዓዛር ወዴት እንደተቀበረ ጠየቀ፡፡ አምላክ ነውና አልዓዛርን ከሞት አስነሣ፡፡ እርሱ በርካሽ ዋጋ ያውም በሠላሳ ብር ብቻ ተሸጠ፡፡ ነገር ግን ዓለምን በውድ ዋጋ በከበረ ደሙ ገዛ፡፡ እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ እርሱ ግን የእስራኤል እረኛ የዓለምም ሁሉ ጠባቂ ነበረ፡፡ እንደ በግ ዝም አለ ነገር ግን እርሱ በምድረ በዳ በሚጮኽ ሰው ድምፅ የተሰበከ ቃል ነበር፡፡ እርሱ የተሰቃየና የቆሰለ ነበር ፤ ሁሉንም በሽታና ቁስል ግን ይፈውስ ነበር›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ

"ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታድርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጽል አይደለም፡፡
የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 26 2011
ጅማ ፣ ኢትዮጵያ

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
​መስከረም 01/01/2013 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፷፬፥፲፩(64፥11)
ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ
ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም
ወይረውዩ አድባረ በድው


ምስባክ ዘቅዳሴ

አድኅነኒ እምእለ ሮዱኒ እስመ ይኄይሉኒ
ወአውጽኣ እምቅሕ ለነፍስየ
ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ

ቅዳሴ

👉ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

@aleroe
ኤልሮኢ:(ትምህርት)

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
# ዘመን መለወጫ ምንድነው.?
# እንቁጣጣሽ ምንድነው..?
# አዲሱ ዓመት ለምን ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል...?

ኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፡፡ ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

# ዘመን__መለወጫ
ዘመን መለወጫ መስከረም ወር የሆነበት ምክንያት “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር ይተካከላል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ቢቆጥሩ 366 ቀናት ይሆናል፡፡ “ሌሊቱም ከቀኑ ጋራ ይተካከላል፡፡ ዓመቱም ጠንቅቆ ቢቆጥሩት ሦስት መቶ ስልሳ አራት ቀን ይሆናል፡፡ /ሄኖክ.26፥44/ “ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድሱ” /ሰ.ኤር.5፥21/ከቆየ እንዲል፡፡ በዘመነ ኖኅ ዓለምን ንፍር ውኃ አጥለቅልቆት በኋላ ዳግመኛ ውኃው የጎደለበት በመሆኑ /ኩፋሌ 7፥1/ “በመጀመሪያው ወር መባቻም ምድር ታየች” እንዲል፡፡

# ዕንቁጣጣሽ
ዕንቁጣጣሽ የተባለበት ምክንያት አንደኛ “ዕንቁ - ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባውን አህጉራትን መፈንዳት ያመለክታል፡፡ ሁለተኛ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ በእጣ ሲያካፍላቸው አፍሪካ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪካ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ
ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኀ
መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡ ሦስተኛው /1ነገ.10፥1-10/ ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሣባ /መንሻ አዜብ የንጉሡን ጥበብ ከመስማት ማየትን መርጣ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ከብዙ ሠራዊቶቿ ጋር የእጅ በመያዝ ሄደች፡፡ ንጉሡም በደስታ ተቀብሎ እርሱም “እንቁ ለጣትሽ ወርኀ ጌጥ ይሁንሽ” በማለት አራት አይነት ቀለም የሚታይበት በቀንና በሌሊት የምታበራ ቀለበት ሰጥቷታል፡፡ ወሩም መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ወጥቷል፡፡

# ቅዱስ_ዮሐንስ
ሦስተኛው የአዲስ ዘመን ስያሜ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፡፡ የመጥምቁ ዮሐንስ
ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት
መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር አባቶች ወስነዋል፡፡ /ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ
ገጽ 1-3/ መጽሐፈ ስንክሳር “የመስከረም ወር የተባረከ ነው፡፡ እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው፡፡ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጎደለ ይሄዳል” እንዲል፡፡

በአጠቃላይ ዘመን መለወጫ ከላይ ባየናቸው የተለያየ ስያሜ ይጠራ እንጂ ዘመኑ አዲስ እየተባለ ቢጠራም አዲስ መሆን ያለበት ወርና ወቅቱ ብቻ ሳይሆን የእኛ የክርስቲያኖች ሥርዓት ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ሰውነታችሁን አታርክሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና እያለ በመዋዕለ ሥጋዌው ያስተምር ነበር፡፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በኀጥያት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ፣ በቅዱስ ቊርባን፣ በመልካም ተግባር አዲስ ልናደርገው ይገባናል፡፡

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
አሜን!!!

@aleroe
ኤልሮኢ:(ዝማሬ)

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
የእለት የዓመት

ከዚህ ዕለት ከዚህ ዓመት ላደረሰን ሁላችንን /2/
የሰው ልጆች እድሜ ጥንቱንም ሲጀመር
ምን ቢወጣ ቢወርድ ቢበዛ ቢደመር
አንድ ቀን አይሞላም እንደአንተ አቆጣጠር /2/

አዝ . . .

ስለዚህ አምላክ ሆይ ክቡር ነው ቅዱስ ነው
ወደአንተ እንዲመለስ ቀን የሰጠኸው ሰው
ደካማ ነውና ሰው እድሜ ከራበው /2/

አዝ . . .

እጅግ አደንቃለሁ የአምላክን ጥበብ
ምድርን በአበባ ሰማይን በኮከብ
እንዳሸበረቃት አስተውዬ ሳስብ /2/

አዝ . . .

ከንቱ ካሳለፍኩት ጊዜዬን በዋዛ
ምን ያደርግልኛል ዘመኔ ቢበዛ
ደግሞም በጠቅላላ ዓለምን ብገዛ /2/

አዝ . . .

በከንቱ ጊዜያችን ፈጽሞ እንዳይጠፋ
በርትተን ከሠራን ያለአንዳች ነቀፋ
አምላክ የሚሰጠን አለን ፍጹም ተስፋ /2/

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

@aleroe