"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ነሐሴ 05/12/2012 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፷፰፥፲፰(68፥18)
ወአንሰ በጸሎትየ ኀበ እግዚአብሔር
ሣህሉ ለእግዚአብሔር በጊዜሁ
እንዘ ብዙኅ ሣህልከ

ምስባክ ዘቅዳሴ

ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ
ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ
ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ


ቅዳሴ

👉ዘእግዝእትነ አው ግሩም

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ነሐሴ 06/12/2012 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፵፯፥፲፩(47፥11)
ይትፌሥሓ አድባረ ጽዮን

ምስባክ ዘቅዳሴ

ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር
ኩሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን


ቅዳሴ

👉ዘእግዝእትነ አው ግሩም


@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ነሐሴ 07/12/2012 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፹፮፥1(86፥1)
መሰረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን።
ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን
እምኩሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ።


ምስባክ ዘቅዳሴ

ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ
መዘመሀርኮ ሕገከ
ከመ ይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት

ቅዳሴ

👉ዘእግዝእትነ

@aleroe
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 4

@aleroe
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 5

@aleroe
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 6

@aleroe
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 7

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ነሐሴ 08/12/2012 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፹፪፥፫(82፥3)
ወተጓኀለውዎሙ ምክረ ለሕዝብከ
ወተማከሩ ዲበ ቅዱሳኒከ
ወይቤሉ ንዑ ንሥርዎሙ እምአሕዛብ

ምስባክ ዘቅዳሴ

ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ
ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ
ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ

ቅዳሴ

👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)


@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ነሐሴ 10/12/2012 ዓ.ም

ምስባክ ዘቅዳሴ

አንሣእኩ አዕይንትየ መንገለ አድባር።
እምአይቴ ይምጻእ ረድኤትየ።
ረድኤትየሰ እምኀበ እግዚአብሔር።

#ወንጌል ፦ ሉቃ 1÷39-46

ቅዳሴ

👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)


@aleroe
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 8

@aleroe
Audio
ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ክፍል 9

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
ነሐሴ 11/12/2012 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፶፱፥፭(59፥5)
አድኅን በየማንከ ወስምዐኒ
እግዚአብሔር ነበበ በመቅደሱ
እትፌሣሕ ወአትካፈል ምህርካ…

ምስባክ ዘቅዳሴ

ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ
ወተሰይሚዮሙ መላእክተ ለኩሉ ምድር
ወይዘክሩ ስመኪ በኩሉ ትውልደ ትውልድ


ቅዳሴ

👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)


@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ነሐሴ 14/12/2012 ዓ.ም

ምስባክ ዘቅዳሴ

ዘአዘዝከ መድኀኒቶ ለያዕቆብ
ብከ ንወግኦሙ ለኩሎሙ ፀርነ
ወበስምከ ናኀስሮሙ ለእለ ቆሙ ላዕሌነ

ወንጌል
ማቴ 17÷14-24

ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ

@aleroe
"እኛ እንዘምራለን"| "Egna Enzemeralen"
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ|@orthodox_mezmurs
ኤልሮኢ:(ዝማሬ)
#እኛ_እንዘምራለን

እኛ እንዘምራለን ጠላት ይጨነቃል
የደስታቸው ምንጩ ከወዴት ነው ይላል
የሰላም መፍሰሻ አንቺ ነሽ ደስታችን
የመስቀል ስር ሰነድ ማርያም እናታችን

#አዝ
በልባችን ደስታ ፊታችን የበራው
ስለት ሰንሰለቱን ልጅሽ ሰብሮልን ነው
ሞት መሻገሪያችን ድልድይ ከመከራ
የምስራቅ ልጅ ፀሃይ የኛ ትንሳኤ ነው

#አዝ
የመድሃኒት መዝገብ ይቁስላችን ጤና
ከርስቱ እንዳንጎድል በተስፋ እንደፀና
ልጅዋን ደስታ ለሚል የደስታምንጭ ሆና
ሀዘን በዕርስዋ እርቋል ስላዘኑት አዝና

#አዝ
የሊቀ ካህናቱ የክርስቶስ እናት
እርሱ ዝናብ ሲሆን እርሷ ደመና ናት
ሲጠብቅ እረኛ ሲርበን በግ ያልነው
አልፋና ኦሜጋ የድንግል ልጅዋ ነው


@aleroe
ኤልሮኢ:(መንፈሳዊ ስነፅሁፍ)
በደብረ ታቦር

መለኮት ተገለጠ በደማቅ ብርሃን አበራ
በተቀደሰው የታቦር ተራራ።
የአብ አባትነት የወልድ ልጅነት
በግልጽ ታወቀ ተነገረ በእውነት
ዮሐንስ ጴጥሮስን ያዕቆብን ጠርቶ
ሙሴን ከመቃብር ከሙታን አንሥቶ
ከብሔረ ሕያዋን ኤልያስን አምጥቶ
በአምላክነቱ ፍጹም አንጸባርቆ
በሕያው መለኮቱ በብርሃን ደምቆ
አብም ተገለጠ በብሩህ ደመና
የምወደው ልጄ ክርስቶስ ነውና።
እርሱን ብቻ ሰሙት እስከ ዘለዓለም
ሕይወት በእርሱ ነው ያለርሱ አትድኑም።
ብሎ ስለልጁ በግለጽ መሰከረ
አምላክነቱንም በተግባር ነገረ።

ከሀብታሙ ገበያው

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
ነሐሴ 15/12/2012 ዓ.ም

ምስባክ ዘቅዳሴ

ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ
ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ፤
ወውስተ ፀሓይ ሤመ ጽላሎቶ።

ወንጌል ዘቅዳሴ

የማቴዎስ ወንጌል ም. ፲ ቊ. ፩ - ፵፪

ቅዳሴ

👉ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ)

@aleroe
ኤልሮኢ:(ዝማሬ)
#ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን

ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን /2/
ድንበር የሚጠብቁትን /2/
ጠብቅ እግዚአብሔር ሠራዊቷን /4/

የደም መሬት አትሁን ደም አይፍሰስባት
ካንተ የመነጨ ሰላም ይስፈንባት
አሽናፊ እንድትሆን ለስምህ ተገዝታ
አይንህን ሳትመልስ እያት ጠዋት ማታ

#አዝ

ሰንሰለት ሲፀና ለመከራ ፈርቶ
ኢትዮጲያዊ መልኩን አይቀይርም ከቶ
ድንቁን ብርሃን ያያል ወቶ ከጨለማ
በመንገዱ ሁሉ አዳኝ ቀኝ ቀድማ

#አዝ

እጅግ የፈተናት ተናቅሎላት መርዙ
ከእግሮቿ በታች ጠላቶች ይገዙ
ደጅ ስትጠና እጆቿን ዘርግታ
ጠብቅ ሠራዊቿን ዱሩ እንዳይፈታ

#አዝ

ከራሳቸው ይልቅ ኢትዮጵያን ወደዱ
ደም ከፍለው ሊያቆዮት በዱር ተሰደዱ
በሃሩር በውርጩ የሆኗትን አጥር
በማይፋቅ ቀለም ፃፋቸው ለክብር

ሊቀ-መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ


@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ነሐሴ 19/12/2012 ዓ.ም


ምስባክ ዘነግህ

መዝ ፵፬፥፱(44፥9)
ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምኢ እዝነኪ

ምስባክ ዘቅዳሴ

በእግዚአብሔር እሴብሕ ቃልየ
በእግዚአብሔር ይከብር ዘነበብኩ
ወበእግዚአብሔር ተወከልኩ ኢይፈርህ ምንት ይሬስያኒ

ቅዳሴ

👉ዘእግዝእትነ አው ግሩም


@aleroe
ኤልሮኢ:(ትርክት ወምክር)

አንተ ግን ሰው ነህ?


አንዱ ወደ አንድ አባት ቀረብ ብሎ "ድንግል ማርያም እኮ እንደ እኛ ሰው ናት" አላቸው። እርሳቸውም "ልክ ነህ እርስዋ
በተፈጥሮዋ ሰው ናት ፣ አንተ ግን ሰው ነህ?" አሉት። ነገሩ ስድብ ይመስላል ፣ አስተውሎ ላየው ግን ሰው ነኝ ለማለትም መሥፈርት እንዳለው ያስታውሳል። "ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ" ነገር ግን ዝናምን በጸሎቱ ያቆመ መሆኑን ስንሰማ ሰው ነን ለማለት እንፈራለን። ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ሰሎሞን "ሰው ሁን" ያለው ሰው መሆን ማለት እንደ ሰው ክብርን አውቆ መኖር ስለሆነ ነው። ክቡር ሆኖ ሳለ ካላወቀና በኃጢአቱ ከጸና እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል። ሰው ለመሆን ብዙ መሥፈርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተቀምጠዋል ፣ የድንግል ማርያምን እናትነት መቀበልም ሰው የመሆን ምልክት
ነው። "ሰው እናታችን ጽዮን ይላል" ተብሎ እንደተጻፈ "ጽዮን እናታችን" ማለት ያልቻለ ምኑ ሰው ይባላል? "የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮን ሆይ ይሉሻል የናቁሽ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ" ተብሎ ለዳዊት ከተማ ተነግሮላት ነበር። ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮትባት ለሚውልባት ለዳዊት ከተማ የሚሰገድ ከሆነ ለንጽሕቲቱ ከተማው ለድንግል ማርያም አይሰገድም እንዴት
ይባላል? ነቢዩ ከጽዮን ጫማ በታች ይሰግዳሉ ብሎ ለዳዊት ከተማ ከተናገረ ከድንግሊቱ ጫማ በታች እንዴት ይሰገድ ይሆን? በእርግጥ የናቅዋት ሁሉ ወደ ጫማዋ ሊሰግዱ ይሆን? በፍጹም
አይሆንም! የድንግልን ጫማዋንማ ለእኛ ለምናከብራትም ማን ባደለን? እኛ አክሱም ጽዮን ቁስቋም ግሸን በረከቷን ሽተን እየተጓዝን የናቋት እንዴት ጫማዋን ያገኛሉ? አባ ጊዮርጊስ "ገሊላዊትዋ ድንግል ጫማን እሸከም ዘንድ ፣
ጥላዋ ያረፈበትን እስም ዘንድ ማን ባደለኝ?" ይል የለምን? ከእግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ ማለት ይዋረዳሉ ነው እንጂ ይህ ክብር ለናቋት የሚገባ አይደለም። "ጽዮንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ" (መዝ 48:12)


@aleroe
ኤልሮኢ:
ማርያም ዐርጋለች

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት (2)
የሰማይ መላእክት እያጀቧት
እርሷም እንደ ልጇ ተነሥታለች
የአባቷ ዳዊትን ትንቢት ልትፈጽም
ወርቁን ተጎናጽፋ በቀኙ ልትቆም
ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት
ዐረገች በእልልታ ድንገል የኛ እናት
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት (2)
የሰማይ መላእክት እያጀቧት
እርሷም እንደ ልጇ ተነሥታለች
ሰማይም ይከፈት ደመናም ይዘርጋ
ዝምታ አይኖርም እመ አምላክ ዐርጋ
አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን
ከዘለዓለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት (2)
የሰማይ መላእክት እያጀቧት
እርሷም እንደ ልጇ ተነሥታለች
የአምላክ ማደርያ ያ ቅዱስ ሥጋሽ
አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ
ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው
ተነሥተዋል በክብር በእምነት አየናቸው
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት (2)
የሰማይ መላእክት እያጀቧት
እርሷም እንደ ልጇ ተነሥታለች
ሐዋርያት አበው እንኳን ደስ ያላችሁ
በክብር ዐረገች ማርያም ሞገሳችሁ
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኗን ይዛችሁ
የድንግል ዕርገቷን ንገሩ ተግታችሁ
ዐርጋለች ማርያም ተነሥታለች

@aleroe
ኤልሮኢ:(የዕለቱ ምስባክና ወንጌል)
​ነሐሴ 24/12/2012 ዓ.ም

ምስባክ፦ 144÷16

ዐይነ ኲሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ
አንተ ትሁቦሙ ሲሳዮሙ በጊዜሁ
ትሰፍሕ የማነከ ወታጸግብ ለኲሉ እንስሳ ዘበሥርዓትከ።


ወንጌል
ዮሐ ፮፥፵፩ - ፍጻሜ

ቅዳሴ
ዘኤጲፋንዮስ


@aleroe