ኤልሮኢ:(⚜ወቅታዊ ትምህርት⚜)
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
እንኳን ለፆመ ፍልሰታ በሰላም አደረሰን አደረሳቹ
አምላካችን ፆሙን የረድኤት በረከት ያድርግልን አሜን!!!
#ጾመ ፍልሰታ ማለት
ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጉም ስናነሣ ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ /
የተገኘ/ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ ከምድር ከመቃብር መለየት፣ ማረግ፤ ወደ ላይ
መውጣት የሚለውን ትርጉም ያመለክታል፡፡ በዚህ መሰረት ጾመ ፍልሰታ
በአጠቃላይ የእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋዋን ከመቃብር መለየትና
ወደ ገነት ማረጉን የሚያመለክት ሲሆን ቅድስት ቤተክርስቲያን ምዕመናን
እንዲጾሙት ከምታዘው አጽዋም አንዱና ለዓመቱ ደግሞ የመጨረሻው ጾም
ነው፡፡ ይህ ጾመ ፍልሰታ በሌላ አጠራሩ ጾመ ማርያምም በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ወቅት በብዛት የሚወሳው /የሚነገረው/ቃለ እግዚአብሔር በአብዛኛው ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የተያያዘ በመሆኑና የእርስዋ የሥጋዋ ፍልሰት መታሰቢያ በመሆኑ ጾመ ማርያም ተባለ፡፡
#ነገር ከስሩ ውኃ ከጥሩ እንዲሉ አበው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ይህንን
የእመቤታችንን ጾም ለምን እንደምታከብር ለመዘርዘር እንወዳለን፡፡
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህች የሰው ልጆች መኖሪያ በሆነችዋ
ምድር ከእናትና ከአባቷ ማህፀንና አብራክ ተከፍላ ከተወለደችበት ግዜ አንስቶ እስከ መጨረሻዋ የዕረፍት ዘመን በምድር ላይ ስልሳ አራት ዓመታትን ማለትም ከእናት ከአባቷ ቤት ሦስት ዓመት ከሰባት ወር፣ በቤተመቅደስ 12 ዓመት፣ በቤተ ዮሴፍ 34 ዓመት ከሦስት ወር፣ ከጌታ እርገት በኋላ ከወንጌላዊው
ዮሐንስ ጋር 14ዓመት ኖራለች፡፡ ከዚህ በኋላ እርሷም የአዳም ዘር ናትና ጥር
21ቀን ዐርፋለች፡፡ አበው"ሞትኪሰ ማርያም ይመስል ከብካበ"እንዳሉት
የእመቤታችን እረፍት እንባ መራጨት፣ ጠጉር መንጨት፣ ደረት መድቃት
እንዳለበት የሰው ሞት አልነበረም፡፡ ይልቁንም አንደ ሠርግ ቤት መላዕክት
በውዳሴ፤ በማህሌት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና ወደ ሰማይ ሸኟት፡፡ እንጂ ቅዱስ ያሬድም"ተለዐለት እምድር ወበህየ ነበረት ዘምስለ ወልዳ በየማነ አብ
ወመንፈስ ቅዱስ" እመቤታችን ድንግል ማርያም ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ
አለች፡፡ በዚያም ከልጇ ጋር በአብና በመንፈስ ቅዱስ ቀኝ ተቀመጠች
በማለትም ዘምሯል፡፡ የእመቤታችን ሥጋዋ ከጌቴሴማኔ ወደ ገነት መፍለሱን
አስቀድሞ አባቷ ቅዱስ ዳዊት በትንቢት ሲናገር "ተንስእ እግዚኦ ውስተ
እረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ" አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና
የመቅደስህ ታቦት በማለት ተንብየዋል፡፡ መዝ. 131፡8 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍት ጥር 21 ሲሆን እረፍቷና ዕርገቷ ብዙ መንፈሳዊ ተአምራትና አስደናቂ ምስጢር የተገለጠበት በመሆኑ ሞት
በጥር በነሐሴ መቃብር የተባለበትም ምክንያት ከዚህ በመነሣት ነው፡፡
#የእመቤታችን እረፍት በሆነበት እለት አይሁድ በአስከሬኗ ጥፋት ለማድረስ ብዙ ጥረዋል፡፡ እነ ታውፋንያም እጁን በመቆረጥ ተአምር ተደርጎበታል፡፡ በዚህ ጊዜ ብዙ ንውጽውጽታ ስለነበር ሐዋርያትም በሀዘን ከጌቴሰማኔ ተመለሱ፡፡ በዚህ ሀዘንም እያሉ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ሲመጣ እመቤታችንን መላዕክት ሲያሳርጓት አየ፡፡ ሰገደላት፣ አመሰገናትም እርሷም ባርካው ተለያዩ፡፡
ለሐዋርያው ቶማስም የእመቤታችንን መቀበር ደቀ መዛሙርት አስረዱት፡፡
ቶማስም ሥጋዋን አስከማይ አላምንም አላቸው፡፡ ሥጋዋን ያሣዩት ዘንድ ወደ
መቃብርዋ በአደረሱት ጊዜ በመቃብር ውስጥ ሥጋዋን አላገኙም ደንግጠውም
አደነቁ ያን ጊዜ ከመላእክት ጋር ወደ ሰማይ ስታርግ እመቤታችንን እንዳገኛት
ቶማስ ነገራቸው፡፡ በዚህም ሥጋዋ ሲያርግ ባለማየታቸው አንድ ቀን እንደሚያሳያቸው ጌታችን ተገልጦ ቃል ገባላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ከሚያስተምርበት ሀገረ እስያ ወደ ሰማይ ተነጥቆ የእመቤታችን ሥጋ ያለበትን ስፍራ አየ፡፡ ሐዋርያትም ይህን በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ፡፡ ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆይተው ነሐሴ በገባ በመጀመሪያው ቀን በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ፡፡ ነሐሴ14 ቀን ሁለት ሱባዔ ሲጨርሱ ሥጋዋን አምጥቶ ሰጣቸው በጥር ወር የእረፍት ጊዜ ተወስኖ በነበረው ቦታ በጌቴሰማኔ ቀበሯት፡፡ ነሐሴ 16 ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው፡፡ በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋህዳ ተነሥታ እመቤታችንን አዩዋት፡፡ እጆችዋንም ዘርግታ ሐዋርያትንም ባረከቻቸው በእልልታ በደስታ ወደ ሰማይ አረገች፡፡ ሐዋርያትም በልባቸው ደስ አላቸው፡፡
#ጾመ ፍልሰታ እንደወንዝ ፈሳሽ እንደ እንግዳ ደራሽ የሆነ ታሪክ ሳይሆን ልብን የሚነካ መንፈሳዊ ታሪክ ነው፡፡ ለዚህም ነው ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት "አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦት" ያለው፡፡ አንተ ያለው ጌታችንን ሲሆን የመቅደስህ ታቦት ያለው ጌታ ለዘለዓለም አድሮባት የኖረባትን እናቱ ድንግል ማርያምን ነው፡፡ ጌታ በገዛ ፈቃዱ ሞትን ድል አድርጎ በሦስተኛው ቀን እንደተነሣ እርሷም በልጅዋ ቸርነት ከሦስት ቀን በኋላ ከሞት ተነሳች፡፡
ስለዚህም ነው ምዕመናን ነሐሴ አንድ ቀን የምትገባዋን ጾመ ማርያም ሱባዔ
ለመያዝ ህጻናቱ ተማሪው የክረምት እረፍት በመሆኑ፣ ሰራተኛው የዓመት
ፈቃዱን ወስዶ ሌሊት በሰዓታት፣ ቀን በትርጓሜና በቅዳሴ የሚያሳልፈው፡፡
እግዚአብሔር አብርሃምን "የሚባርኩህን እባርካለሁ፣ የሚረግሙህን
እረግማለሁ"እንዳለው፡፡ ዘፍ.12፡3የአብርሃም ዘር የሆነች ድንግል ማርያምን የሚያመሰግን ትውልድ ይባረካል፡፡ ለዚህም ነው እመቤታችንም "ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል" በማለት የተናገረችው፡፡ ይህ የሱባዔ ወቅትም እመቤታችንን እንደ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ደስ ይበልሽ ብለን አመስግነን፣ እንደ ቅዱሳን አባቶች ሰአሊነነ ቅድስት በማለት ለምነን በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ
የምናገኝበት ልዩ ወቅት ነው፡፡
በብዙዎቻችን ዘንድ የዚህ ሱባዔ ወቅት የማይረሳ ልዩ ትዝታም አለው፡፡
ስለሆነም በተለይ በአሁኑ ጊዜ በቤተክርስቲያን የሚታየውን ፈተና ለመቋቋም በርትተን "ጸልዮ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን" እንዲል ስለቤተክርስቲያን ሰላም መፀለይ ይገባናል፡፡ ክፉ የተባሉ ቀናት አይቻልም የሚባሉ ችግሮች በጸሎት
ኃይል እንደሚሸነፉ የመጽሐፍ ቅዱሳን ምስክርነት ማየት ይበቃል፡፡ ሐዋ. 12÷5
#የጾመ ፍልሰታ ልዩ ገጽታ
ቅድስት ቤተክርስቲያን ሰባት ያህል አጽዋማትን በአዋጅ ታጾማለች፡፡ ነገር ግን
የጾመ ፍልሰታ ልዩ ገጽታን ለማየት ያህል፤
1. ከዚህ በፊት በተለየ መልኩ ሙሉ ጊዜ /ቀንም ሆነ ሌሊት/ያልተቋረጠ
የቤተክርስቲያን አገልግሎት ማለትም የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የሰዓታት
ድርሰት፣ የቅዱስ ያሬድ ዜማ፣ የቅዱስ ኤፍሬም የውዳሴ ማርያም ትርጓሜ፣
የአባ ህርያቆስ ቅዳሴ ማርያም በስፋትና በጥልቀት የሚሰማበት መሆኑ
ከፍተኛ የመንፈስ እርካታን ይሰጣል፡፡
2. በትምህርት ጊዜ ሲባዝኑ የነበሩ ህጻናትና ተማሪዎች፣ ወጣት፣ አረጋውያኑ
ለመቁረብ ነጠላ ለብሰው በጊዜ ቤተክርስቲያን ገብተው ሲያስቀድሱ ማየትየህብረት የተሰጥኦ ዜማቸውን መስማት አንዱ ልዩ ገጽታ ነው፤
3. ጊዜው ሁለት ሱባዔ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በፍቅር የምትጾም መሆኗም
ከሌሎቹ የአጽዋማት ጊዜ ልዩ የጾመ ማርያም ገጽታ ነው፡፡
🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆
@aleroe

ኤልሮኢ:(⚜የዕለቱ ምስባክና ወንጌል⚜)
ነሐሴ 01/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፰፯፥፳፭(67፥25)
በጽሑ መላእክት
ምስባክ ዘቅዳሴ
ወእነግር ስምከ በቅድመ ነገስት ወኢይትኀፈር
ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀረኩ ጥቀ
ወአነሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘአፍቀርኩ
ቅዳሴ
👉ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ አው ዘእግዝእትነ
@aleroe
ነሐሴ 01/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፰፯፥፳፭(67፥25)
በጽሑ መላእክት
ምስባክ ዘቅዳሴ
ወእነግር ስምከ በቅድመ ነገስት ወኢይትኀፈር
ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀረኩ ጥቀ
ወአነሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘአፍቀርኩ
ቅዳሴ
👉ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ አው ዘእግዝእትነ
@aleroe
ባላገሩ ቴሌቪዥን የፆመ ፍልሰታ ለማርያምን ከመንበረ ፓትርያርክ ቅ/ቅ ማርያም ገዳም እስከ ፆሙ ማብቂያ ድረስ በቀጥታ ስርጭት ያስተላልፋል።
ወረርሽኙ በአሳሳቢ ሁኔታ በመስፋፋት ላይ በመሆኑ የህዝቡን ጤንነት ለመጠበቅና የህዝቡን ፍላጎት ለማሟላት በሚደረገው ርብርብ ሁሉ ባላገሩ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል እንደሚሰራ ስንገልፅ በደስታ ነው።
ጤና ይስጥልን!
ባላገሩ ቴሌቪዥን

ኤልሮኢ:(⚜ምክረ አበው⚜)
. #ጸሎት
#ጸሎት ያቆመች ነብስ እየሞተች ያለች ነች።
#ለሊት ተነሥቶ በጸሎት ጠላቱን ያልመታ ጥዋት ቀኑን ሙሉ ሰይጣን ሲመታው (ሲቀጠቅጠው) ይውላል።
#ክርስትያን ተንበርክኮ ማንበርከክ ይችላል። የማይጸልይ ከሆነ ደግሞ ገና ሳይዋጋ ይንበረከካል።
#ሌሊት በጸሎት ያልወረድክበት ሰይጣን። ቀኑን ሙሉ ሲያገሳብህ ይውላል።
#ከእግዚአብሔር ጋር አንዲት ቀን ሳታሳልፍ ከዋልክ፦ ከመልካሙ
ዘመንህ ውስጥ አንዲቷ ቀንህ በከንቱ እንዳባከንካት ቁጠራት።
#እግዚአብሔርን በጸሎት የማይለምን፦ ዘወትር የሰውን ፊት የሚያይ ተለማማጭ ሆኖ ይኖራል።
#ከእግዚአብሔር ጋር መልካም ጊዜን ማሳለፍ፦ገንዘብህን ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኝ ንግድ (ኢንቨስት) ከማድረግ በላይ እጅግ ጠቃሚ ነው።

ነሐሴ 02/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፻፪፥፩(102፥1)
እምአይቴ ይምጻእ ረድኤትየ
ረድኤትየሰ እምኀበ እግዚአብሔር
ዘገብረ ሰማየ ወምድረ
ምስባክ ዘቅዳሴ
ወይወስዱ ለንጉሥ ደናግለ ድኅሬሃ
ወቢጻሂ ይወስዱ ለከ
ወይወስድዎን በትፍሥሕት ወበሐሤት
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
@aleroe
ነሐሴ 02/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፻፪፥፩(102፥1)
እምአይቴ ይምጻእ ረድኤትየ
ረድኤትየሰ እምኀበ እግዚአብሔር
ዘገብረ ሰማየ ወምድረ
ምስባክ ዘቅዳሴ
ወይወስዱ ለንጉሥ ደናግለ ድኅሬሃ
ወቢጻሂ ይወስዱ ለከ
ወይወስድዎን በትፍሥሕት ወበሐሤት
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
@aleroe
ኤልሮኢ:(⚜መንፈሳዊ ትርክት⚜)
፨መርሳት፨
በአንድ ወቅት የግብጹ ሊቀ ጳጳስ ብጹኡ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ እያስተማሩ ባሉበት ወቅት በዙ ጥያቄዎች በጹሑፍ ይደርሳቸው ነበር። ታዲያ ከነዛ ጹሑፎች መካከል አንዱ እንዲ ይላል
... አባቴ እኔ ታላቅ የመርሳት ችግር አለብኝ ያደረኩትን የሰማሁትን ነገሮች በሙሉ እረሳቸዋለው እና አባቴ ምን እንደማደርግ ይምከሩኝ ነበር የሚለው። ብጹእነታቸውም ልጄ መምከሩንስ እመክርሃለሁ ምን ማድርግ እንዳለብህ እነግርሃለሁ ግን እንዳትረሳው እፈራለሁ አሉት ይባላል።
ቃለ እግዚአብሔር ስንሰማ በማስተዋል ልቦናችንንም ሰብስበን ሊሆን ይገባል።
በነገሮችም ሁሉ አስተዋዮች ልንሆን ይገባል።በዚህም ማስተዋል እና ጥበብን ወደሚሰጥ አምላክ አጥብቀን ልንማጸን ይገባናል።

ነሐሴ 03/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘቅዳሴ
ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ
ብዑላነ ምድር
ኩሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን
ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ም. ፲፰ ቊ. ፱ - ፲፰
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
@aleroe
ነሐሴ 03/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘቅዳሴ
ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ
ብዑላነ ምድር
ኩሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን
ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ም. ፲፰ ቊ. ፱ - ፲፰
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
@aleroe
ኤልሮኢ:(⚜መንፈሳዊ ትምህርት⚜)
✍ …… እኛ ከየትኛው እንሆን ይሆን
አምስት ዓይነት ክርስቲያኖች
✝ አንደኛው ክርስቲያን
ዘወትር ከቤተ ክርስቲያንየማይለይ በየቀኑ እግሮቹ ወደ ቤተክርስቲያን የሚገሰግሱ ጠዋት ኪዳን ከሰዓት ቅዳሴ ማታ ሰርክ ጉባኤ የማይቀር ዘወትር የሚጸልይ የሚጾምስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ የሚኖር የሰበካ ጉባኤ አባል የሆነ ቤተ ክርስቲያንን በሚችለው የሚያገለግል ቤቱን ካህናት የባረኩትየሚቆርብ አስራቱን በኩራቱን የሚያወጣ ክርስትናን በተግባር የሚገልጠው ነው።
✝ ሁለተኛው ክርስቲያን
በሳምንት አንድ ቀን እሁድ እሁድ ብቻ ቤተ ክርስቲያን የሚሄድ
በሳምንት አንድ ቀን የሚጸልይ
ስድስት ቀን ሙሉ ቤተ ክርስቲያን ትዝ የማይለው በሳምንት አንድ ቀን የሚያስቀድስ ስድስቱን ቀን በግል ስራው የተጠመደ በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ሂዶ እድር እቁብ አለብኝ ወንጌሉ ይጠር ትምህርቱ በዛ መርሃ ግብር ተንዛዛ ቅዳሴው ረዘመ የሚል በሳምንት አንድ ቀን መጥቶ ሥርዓቱ እስኪፈጸም መቆየት ያቃተው ከመንፈሳዊው ይልቅ ለዓለማዊ የሚያዳላው ነው።
✝ ሶስተኛው ክርስቲያን
በወር አንድ ቀን ብቻ ወራዊ በዓላትን ቆጥሮ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሄደው ነው
(የመድኀኔዓም) (የማርያም) (የሚካኤል)ወዘተ
ዛሬ እኮ መድኀኔዓለም ነው ቤተ ክርስቲያን ልሂድ ብሎ ቀን ቆጥሮ የሚሄደው29 ቀን ሙሉ ቤተ ክረስቲያንን የረሳ ኪዳን አድርሶ የማያውቅ ወንጌል ቁጭ ብሎ የማይማር የማያስቀድስበወር አንድ ቀን ብቻ ቤተ ክርስቲያን ደርሶ የሚመለስ ለጸሎት ጊዜ የሌለውበቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የማይሳተፍ የሰበካ ጉባኤ መታወቂያ የሌለው የነፍስ አባቱን ስም እንኳየማያውቅ የነፍስ አባትህ ማነው? ተብሎ ሲጠየቅ እንትና እንትና ማን ነበር ረሳሁት የሚል የነፍስ አባቱን ሲያገባ ሲወልድ ሰው ሲሞትበት ብቻ የሚፈልግ ቤቱን አስባርኮ ጸበል አስረጭቶ የማያውቅ በልምድ ብቻ የሚኖረው ነው።
✝ አራተኛው ክርስቲያን
በዓመት አንድ ቀን በንግሥ ጊዜ ቤተ ክረርስቲያን የሚሄደው ነው
ዛሬ የዓመቱ ገብርኤል ነው
ዛሬ ጥምቀት ነው ብሎ የሚሄደው
364 ቀን ከቤተ ክርስቲያን ቀርቶ በዓመት አንድ ቀን ትዝ የሚለው
የበዓል ሰው የሆነ የነፍስ አባት የሌለው የሰበካ ጉባኤ መታወቂያ የሌለው ጸሎት አድርጎ ኪዳን አድርሶ ቅዳሴ አስቀድሶ ጾም ጹሞ ንስሐ ገብቶ የማያውቅ ኳስ ሲደግፍ ፊልም ሲያይ ቻት ሲያደርግ ካራንቡላ ፑል ሲጫዎት ጊዜውን በማባክን ራሱንበዓለማዊ ነገሮች ቢዚ ያደረገ ቤተ ክርስቲያን እንሂድ ሲሉት ቢዚ ነኝ የሚልሁለት ሰዓት ሙሉ ቁጭ ብሎ ኳስ የሚደግፍ ፊልም የሚያይ ሰላሳ ደቂቃ ወንጌል መማርየሚሰለቸው ዓለም አንቃየያዘቸው በሚያልፍ ነገር የሚታለለው ከመንፈሳዊ ነገር የራቀው ነው።
✝ አምስተኛው ክርስቲያን
በሕይወቱ ቤተክርስቲያንን የማያውቃት ነውክርስትና ሲነሳ እናቱ አዝላ ካመጣችው በሇላ ደግሞ ያልመጣ ለጠናቋይለጣኦት ሲገብር የኖረ በባእድ አምልኮ ተተብትቦ ተይዞ ቆሌ ጨሌ እያለ ኑሮ ሲሞት ለመቅበር ሰዎች ክርስቲያን ነው ብለው አስከሬኑን ወደ ቤተ ክረርስቲያን ያመጡት ስሙ ብቻ ክርስቲያን የተባለ የክርስትና ስራ ሰርቶ የማያውቅ በእሱ ምክንያት ከሰበካ ጉባኤ ጋራ ጭቅጭቅ የሚያስነሳ ሰበካ ጉባኤ ስለማለውቀው ኣይቀበርም የቤተ ክርስቲያን አባል አይደለም ሲል ዘመዶቹ ጎረቤቶቹ ክርስቲያን ነው ይቀበር ብለው የሚከራከሩለት ሰውን ግራ የሚያጋባ ከንቱ የሆነ ሰው ነው ።ክርስቲያኖች ሆይ እኔና እናንተ ከየትኛው ነን ???

ነሐሴ 04/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፲፱፥፩(19፥1)
ይስማዕከ እግዚአብሔር በዕለተ ምንዳቤከ
ወይቁም ለከ ስሙ ለአምላከ ያዕቆብ
ወይፈኑ ለከ ረድኤተ እመቅደሱ…
ምስባክ ዘቅዳሴ
እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ
ወቡዙኃ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ
ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ አው ዘቄርሎስ
@aleroe
ነሐሴ 04/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፲፱፥፩(19፥1)
ይስማዕከ እግዚአብሔር በዕለተ ምንዳቤከ
ወይቁም ለከ ስሙ ለአምላከ ያዕቆብ
ወይፈኑ ለከ ረድኤተ እመቅደሱ…
ምስባክ ዘቅዳሴ
እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ
ወቡዙኃ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ
ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ አው ዘቄርሎስ
@aleroe
ኤልሮኢ:(⚜የዕለቱ ምስባክና ወንጌል⚜)
ነሐሴ 05/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፷፰፥፲፰(68፥18)
ወአንሰ በጸሎትየ ኀበ እግዚአብሔር
ሣህሉ ለእግዚአብሔር በጊዜሁ
እንዘ ብዙኅ ሣህልከ
ምስባክ ዘቅዳሴ
ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ
ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ
ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ አው ግሩም
@aleroe
ነሐሴ 05/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፷፰፥፲፰(68፥18)
ወአንሰ በጸሎትየ ኀበ እግዚአብሔር
ሣህሉ ለእግዚአብሔር በጊዜሁ
እንዘ ብዙኅ ሣህልከ
ምስባክ ዘቅዳሴ
ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ
ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ
ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ አው ግሩም
@aleroe
ኤልሮኢ:(⚜የዕለቱ ምስባክና ወንጌል⚜)
ነሐሴ 06/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፵፯፥፲፩(47፥11)
ይትፌሥሓ አድባረ ጽዮን
ምስባክ ዘቅዳሴ
ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር
ኩሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ አው ግሩም
@aleroe
ነሐሴ 06/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፵፯፥፲፩(47፥11)
ይትፌሥሓ አድባረ ጽዮን
ምስባክ ዘቅዳሴ
ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር
ኩሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ አው ግሩም
@aleroe
ኤልሮኢ:(⚜የዕለቱ ምስባክና ወንጌል⚜)
ነሐሴ 07/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፹፮፥1(86፥1)
መሰረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን።
ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን
እምኩሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ።
ምስባክ ዘቅዳሴ
ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ
መዘመሀርኮ ሕገከ
ከመ ይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ
@aleroe
ነሐሴ 07/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፹፮፥1(86፥1)
መሰረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን።
ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን
እምኩሉ ተዐይኒሁ ለያዕቆብ።
ምስባክ ዘቅዳሴ
ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ
መዘመሀርኮ ሕገከ
ከመ ይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ
@aleroe
ኤልሮኢ:(⚜የዕለቱ ምስባክና ወንጌል⚜)
ነሐሴ 08/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፹፪፥፫(82፥3)
ወተጓኀለውዎሙ ምክረ ለሕዝብከ
ወተማከሩ ዲበ ቅዱሳኒከ
ወይቤሉ ንዑ ንሥርዎሙ እምአሕዛብ
ምስባክ ዘቅዳሴ
ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ
ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ
ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
@aleroe
ነሐሴ 08/12/2012 ዓ.ም
ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፹፪፥፫(82፥3)
ወተጓኀለውዎሙ ምክረ ለሕዝብከ
ወተማከሩ ዲበ ቅዱሳኒከ
ወይቤሉ ንዑ ንሥርዎሙ እምአሕዛብ
ምስባክ ዘቅዳሴ
ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ
ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ
ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ
ቅዳሴ
👉ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)
@aleroe