"ኤልሮኢ ዘተዋህዶ"
1.2K subscribers
26 photos
3 videos
5 files
21 links
ኤልሮኢ
"በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት"
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
ይህ መንፈሳዊ ቻናል
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ:- +ዝማሬ
+ ምክሮች
+ ስነፅሁፎች
+ አጫጭር ትርክቶች እንዲሁም
+ ምስባክና
+ ወንጌል ይለቀቁበታል።

ለበለጠ መረጃ @AleroeBot
ግሩፑን ለማግኘት @alero
Download Telegram
Channel photo updated
እንኳን ወደ ኤልሮኢ channel መጡ
ኤልሮኢ ማለት በእውኑ የሚያየኝን ጌታ አየሁት ማለት ነው።
በቻናላችን ወቅታዊ መዝሙር
ምስባክ
ወንጌል
መንፈሳዊ ምክሮች
ይለቀቃሉ።
👇👇👇👇👇👇
👉 @aleroe 👈
👆👆👆👆👆👆
መዝሙር በእንተ ልደቱ

በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ(×2)
ቤዛ ኩሉ ዓለም(×2) ዮም ተወልደ(×2)

እስመ እም ዘርዓ ዳዊት ዘመፃ(×2)
በቤተልሄም ዘይሁዳ በቤተልሄም ዘይ(×2)

ውስተ ማህፀነ ድንግል አደረ ማህፀነ ድንግል(×2)
ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ (×2)በጎል ተወልደ(×2)

ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እም ቅድስት ድንግል(×2)
ርእይዎ ኖሎት (×2)አእኮትዎ መላእክት(×2)

መድኃኒነ ተወልደ ነዋ(×2)
ይእዜኒ ለሠላም ንትልዋ (×2)

@aleroe
#የልደት_ወረብ

ቤዛ ኲሉ ዓለም ዮም ተወልደ /2/
የዓለም ሁሉ መድኃኒት ዛሬ ተወለደ /2/

💚 @aleroe
​​#በበረሃው_በሃሩሩ

በበረሃው በሃሩሩ
በሚያስፈራው በባሕሩ
እስራኤልን የታደገው
በክንፎቹ የጋረደው ሚካኤል ነው

ሚካኤል ነው - - - - አፅናኝ ደጋፊዬ
ሚካኤል ነው - - - - በዱር በበረሃ
ሚካኤል ነው - - - - ነፍሴን ያረካልኝ
ሚካኤል ነው - - - - ከአለቱ ውሃ
የፊቴ ፈገግታ የውስጤ ፍስሐ
ከአምላክ የተሰጠኝ በረከት አምሐ

አዝ

ሚካኤል ነው - - - - መብረቅ ያወረደው
ሚካኤል ነው - - - - ጠላት ድል የነሳው
ሚካኤል ነው - - - - የባህራን ወዳጅ
ሚካኤል ነው - - - - ሀዘኑን ያስረሳው
ቤቱን የሰራለት በእግሮቹ ያቆመው
እንደ እናት እንደ አባት ደግሶ የዳረው

አዝ

ሚካኤል ነው - - - - ያሳደገኝ መልአክ
ሚካኤል ነው - - - - በፅድቅ የመራኝ
ሚካኤል ነው - - - - ስደክም ያገዘኝ
ሚካኤል ነው - - - - ስወድቅ ያነሳኝ
በችግሬ ሁሉ የቀደመልኝ
ሚካኤል እርሱ ነው ከጥልቁ ያወጣኝ

አዝ

ሚካኤል ነው - - - - ክሴን ያስቀደደ
ሚካኤል ነው - - - - የበደሌን እዳ
ሚካኤል ነው - - - - በአማላጅነቱ
ሚካኤል ነው - - - - ያዳነኝ ከፍዳ
በመንገዴ ሁሉ እኔን እየረዳ
ፍቅሩን ጽፎት አልፏል በልቤ ሰሌዳ

💚 @aleroe 💚
#ባሰማት_ጊዜ

ስሙ ገብርኤል የተባለ
ለድንግል ነገራት መልካም ዜና
እንደምትወልደው ወልድን በድንግልና/2/

ባሰማት ጊዜ ቃሉን
ቅዱስ ገብርኤል በለዛ
ድንግል ቀረበች ወደ እርሱ
ፍጹም ትኅትናን ይዛ

ትፀንሻለሽ ሲላት መልአኩ
ፍጹም በልቧ ሳትመካ
እንደ ቃልህ ይሁን አለችው በቃሉ ተማርካ /2/

#አዝ

የዓለም መድኀኒት ነውና
ከአንቺ የሚወለደው በመንፈስ ቅዱስ
ትሰይሚዋለሽ ስሙንም ብለሽ ኢየሱስ /2/

#አዝ

ዕፁብ ድንቅ ነው ለሁልጊዜ ለ
ድንግል ማርያም የተሰጣት እድል
የአምላክ እናት ሆኖ መመረጥ
ከሴቶች መካከል /2/

#አዝ

ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ
ይገባሻል ለአንቺ ክብርና ምስጋና
የክብር ባለቤት ሁል ጊዜም
ከአንቺ ጋር ነውና /2/

💚 @aleroe
ኤልሮኢ
21/04/11 ዓ.ም.
መዝሙር ዘኖላዊ
"ኖላዊ ዘመጽአ"

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ፡፡

ዲ/ን ዕብ 13÷17_ፍ.ም
ን/ዲ 1ጴጥ 2÷21_ፍ.ም
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 11÷22_ፍ.ም

የዕለቱ #ምስባክ፦መዝ 79÷1

ኖላዊሆሙ ለእስራኤል አጽምዕ 
ዘይርዕዮሙ ከመ አባግዐ ዮሴፍ
ዘይነብር ላዕለ ኪሩቤል አስተርአየ።

#ትርጉም፦ 
ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ
የእስራኤል ጠባቂ አድምጥ
በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ።

የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ 10፥1 - 22
ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ

👉 @aleroe
#ለማርያም

ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም

የተዘጋች ደጅ ለዘለአለም
ሕዝቅኤል ብሏል
ንፅህት ናት በእውነት
በፍፁም ድንግል
አብነት አድርገን
እኛም እርሱን

በፍፅም ፍቅር እንዘምራለን
በፍፁም ፍቅር እንዘምራለን

ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም

የዋህት እርግብ ለዘለአለም
ሰላም አብሳሪ
ለጨለማ ሕይወቴ
ብርሃንን አብሪ
እማፀንሻለሁ
ድንግል ለነፍሴ

አደራ ቅድስት አንቺ ነሽ ዋሴ
አደራ ቅድስት አንቺ ነሽ ዋሴ

ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም

እጅግ የበዛ ነው ለዘለአለም
ያለኝ ፍቅር
አይወሰንም
አይነገርም
በእርሷ ደስ ይለኛል
ሀሴት አደርጋለሁ

ስሟን እየጠራን እንዘምራለን
ስሟን እየጠራን እንዘምራለን

ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም

ነይ ነይ ስላት ለዘለአለም
ቀንና ሌሊት
አትለየኝም
ለእኔስ ቅርቤ ናት
እፁብ እፁብ ብለው
አመሰገኗት

ክብሯን ሊገልፁ ቢያጥራቸው ቃላት
ክብሯን ሊገልፁ ቢያጥራቸው ቃላት

ለማርያም ለ ማርያም
እንዘምራለን ለዘለአለም
እንዘምራለን ለዘለአለም

💚 @aleroe ❤️
​አንድ ወጣት ድምፁን ከፍ አድርጎ ድንግል ማርያም አታማልድም አታማልድም እያለ በአደባባይ ይጮሃል:: ከዛ ድንገት እያለፉ የነበሩ አንድ አባት ድምጽ ይስሙና ወደ ወጣቱ ጠጋ ብለው ልጄ አንዴ ላስቸግርህ ከዛ ፊት ለፊት ካለው ሱቅ 1 ኪሎ ብርትኳን አምጣልኝ አሉት ወጣቱም እሽታውን ገለፀላቸ አባትም ብርትኳኑን አንዳችም ሳያስቀሩ ከበሉ በኃላ ልጄ ብርትኳኑ እንዴት ነው? ይጣፍጣል አይደል ?አሉት ወጣቱም አንዴ ሰውዬ ያምዎታል እንዴ ብርትኳኑን እኮ ብቻወትን ነው የበሉት እና እንዴት ጣሙን ላውቅ እችላለሁ አላቸው በንዴት
አባም አየህ ልጄ ልክ እንደዚህ ብርትኳን የድንግል ማርያም ጣዕሟ አልገባህም ስለዚህ ልጄ ወደ ቤቷ ግባ ጣዕሟንም ቅመሰው ያኔ የድንግል ጣዕም ይገባሃል አሉት ይባላል፡፡

🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

እኛስ ተመርጠን ምልጃዋን ተቸርን፣ ረድኤቷን ቀመስን

ክብር ምስጋና ይግባት🙏🙏🙏🙏🙏
​​#እስከ_መቼ_ነው?

እውነት ቅዱስ ጊዮርጊስን የምንወደው ከሆነ ድምፃችንን እናሰማ እንቃወም፡፡ እስከ መቼ ነው በቅዱሱ አባታችን ስም የሚነገደው? መቼ ነው ታዲያ ስዕሉ የሚከበረው መቼ መቼ? እስከ መቼ ነው ጭፈራ ቤት እና የአህዛብ መቀለጃ ሚያደርጉት፡፡ የቅዱሱ አባታችን ምስል እና ስም ማስነሳት ያቃተን ለምንድነው? ወይስ አንወደውም? ለምን ዝም አልን? መቼስ አያገባኝም አንልም ስለ ዶክተር አብይ እንኳን ስንቱ ነው #ዋ ማንም እንዳይነካዉ እያለ Post የሚያደርገው፡፡ እስቲ ማናችን ነን ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠበቃ የቆምነዉ? እስቲ ማናችን ነን የተከራከርነው? መልሱን እናውቀዋለን፡፡ አሁንም ቢሆን ጊዜው አልረፈደም ሁላችንም FB ላይ post አናድርግ ለሚመለከተው አካል እናድርስ በእርግጥ እኛን ነው የሚመለከተው ነገር ግን መፍትሄ የሚሰጠን አካል ያስፈልገናል። ቅዱስ ስሙ እና ምስሉ ይነሳ ብለን ድምፃችንን እናሰማ መቼም በአባታችን በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ሲነገድ ማየት እሚያስደስተው የለም።
ይህን ያነበበ፣ያየ በሙሉ በተለያዩ ድህረ-ገፅ ላይ POST AND SHARE አድርጉ አደራችሁን።