Aleazer Melese
131 subscribers
13 photos
6 files
35 links
የእግዚአብሔርን ቃል መማር
Download Telegram
ሻሎም ቅዱሳን
#ከኢየሱስ__እናት____ከማርያም____ምን__እንማር?
1,በጌታ ሁሉን ቻይነት ማመንን!
2,ሰዎች ለጌታ ኢየሱስ ትዕዛዝ ተገዢ እንድሆኑ ማስተማር!
3,በትጋት ከቅዱሳን ጋር መጸለይ !
አሁን አንደኛውን በጌታ ሁሉን ቻይነት ማመን የሚለውን እንመለከታለን !
ሉቃ 1:26-38
መልአኩ ገብርኤል ወደ ማርያም ተልኮ ኢየሱስን እንደ ምትወልድ በነገራት ጊዜ እሷ #ድንግል ነበረች።
በዚህ ምክንያት ወንድን ስለማታውቅ መልአኩን ወንድን ሳላውቅ እንዴት ዮህ ነገር ልሆን ይችላል ብላ ጠየቀችው ።መልአኩም
->የልዑል መንፈስ ይመጣል የእግዚአብሔር መንፈስ #ይጸልልሻል አላት።ይህን ካላት በኋላ #ለእግዚአብሔር__የሚሳነው__ነገር___የለም አላት ።ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለ የሚታውቀዋ ማርያም #የጌታ___ባርያ___እንደ___ቃልህ____ይሁን___አላችው
ዛሬም እኛ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለ አውቀን ለእግዚአብሔር መታዘዝና በእርሱ መታመን አለብን። ማርያም ያለ ወንድ ልጅ የወለደች #ብቸኛ ሴት መሆኗ ሙስሊሞችም ክርስቲያኖችም ያውቃሉ ። ለዚህ አንዱ ምክንያት የማርያም በእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ማመኗ ነው።
ሉቃስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥
²⁷ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።
²⁸ መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ፦ ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።
²⁹ እርስዋም ባየችው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና፦ ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች።
³⁰ መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።
³¹ እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።
³² እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤
³³ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።
³⁴ ማርያምም መልአኩን፦ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው።
³⁵ መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።
³⁶ እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤
³⁷ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።
³⁸ ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ።

#ይቀጥላል
#share አድርጉ
t.me/aleazermelese
ሻሎም ቅዱሳን

#ኢየሱስ____ጌታ__መሆኑን____ራሱ____አፍ____ተናግሯል_____ወይ?

ይህን የብዙ ሙስልሞች ጥያቄ ከዚህ በመቀጠል ኢየሱስ ጌታ ወይም አምላክ መሆኑን በራሱ አፍ የተናገረውን ከመጽሐፍ ቅዱስ እናያለን!
#ዮሐ 5:17-19
(የዮሐንስ ወንጌል 5 )
------------
17፤ ኢየሱስ ግን። አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው።
18፤ እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ። እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።
19፤ ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና።
#ማት 22:41-42
(የማቴዎስ ወንጌል 22 )
------------
41-42፤ ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ፥ ኢየሱስ። ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው። የዳዊት ልጅ ነው አሉት።
43-44፤ እርሱም። እንኪያስ ዳዊት። ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?
45፤ ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው።
46፤ አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፥ ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።

ቢይንስ ለ10 ሰው #ሼር #አድርጉ
@transformedchristianlife
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ከአምስት አመት በኋላ!

• የዛሬ አምስት አመት የሚኖርህን ጓደኛ የሚወስነው ዛሬ ያዳበርከው አመለካከት ነው፡፡

• የዛሬ አምስት አመት የሚኖርህን የፍቅር ወይም የትዳር ግንኙነት የሚወስነው የዛሬ ወዳጅነት ምርጫህ ነው፡፡

• የዛሬ አምስት አመት የሚኖርህን እውቀት የሚወስነው ዛሬ የምታነባቸው መጻሕፍት ናቸው፡፡

• የዛሬ አምስት አመት የምትገባበትን አዲስ የሕይወት ምእራፍ የሚወስነው ዛሬ ለማድረግ የቆረጥከው ለውጥ ነው፡፡

• የዛሬ አምስት አመት የምትኖረውን የኑሮ ደረጃ የሚወስነው ዛሬ ያዳበርከው ልማድ ነው፡፡

ጥራት ያለው ሕይወት በአንድ ጀንበር አይመጣም፡፡ በአንድ ጀንበር ብቅ ያለ ነገር ካለም በአንድ ጀንበር ጥልቅ ማለቱ ስለማይቀር ጥራትን ዛሬ ጀምረውና በምንም ነገር እንደማይቀለበስ ሆኖ እንዲበቅል ጊዜ ስጠው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
እንደ ነፍስ መዋደድ .3gpp
19.5 MB
From Aleazer Melese

ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉ
@transformedchristianlife
አለባበስ አንዱ የቅድስና ህግ ነዉ
በአምልኮ ሰአት አለባበሳችንን ማስተካከል ይገባናል ወደ ቤተ መንግስት ተጠርተን ከሆነ ከደብዳቤዉ ታች ሲመጡ ሙሉ ሱፍ መልስ እንዳይረሱ ይላል
አምልኮ እግዚአብሄር የንጉስ ግብዣ በመሆኑ የአለባበስ ክብር መጠበቅ ይገባዋል አለባበስ የቅድስና የአምልኮ ድንጋጌ ከሆነ አምልኮ የማያቋርጥ አገልግሎት ነዉናበጸሎት ሰአት ብቻ ሳይሆን በስራችንም በኑሮአችንም አለባበሳችን ክርስቲያናዊ መሆን ይገባል
አንድ ነገር ይገርመኛል በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሁሉም ዋጋዉ ነጠላ ይለብሳሉ አንድ አይነት ነጠላ ደግሞ ዋጋዉ ከሌሎች አንፃር እርካሽ ነዉ ሁሉም ስለሚያደርጉ ማን ሀብታም ማን ደሀ እንደሆነ አያስታዉቅም በእኛ ዘንድ ግን በመጀመሪያ ባለጠጋዉን ከደሀ የምንለየዉ በአለባበስ ነዉ
ለአለባበሳችን የፈጠረን ቢመርጥልን
ለእኛ መልካም ነዉ አዳም በሀጢአቱ ቅጠል ሲለብስ
እግዚአብሄር ግን ቁርበት አደረገለት ቅጠሉ ይጠወልግና ከሰዉነቱ ይጠፍል
ቁርበቱ ግን በተሻለ መልኩ ለረጅም ጊዜ
ይቆያል
አያቹ አንድ እቃ ስትገዙ ከእኛ በተሻለ የሰራዉ የድርጅቱን መመሪያ ብንከተል በተሻለ መልኩ መጠቀም እንችላለን እንዲሁ ለአለባበሳችንም እኛን የፈጠረንን
መመሪያ ብንከተል የተሻለ ይሆንልናል
ተባርካቿል ፀደቀ ነኝ
Channel photo updated
ሻሎም ቅዱሳን
ዛሬ በዚህ ዘመን የእግዚአብሔር ክብር እንዳይገለጥ ምክንያት እየሆኑ ካሉ ነገሮች ጥቂቶቹን እናያለን ።

1,#አለመጸለይ
በዚህ ጊዜ ለብዙዎቻችን ከመጸለይ ይሊቅ መዘመር ከመስማት ይሊቅ መናገር ይቀለናል ።የዚህ ምክንያቱ የግል የጸሎት ጊዜ አለመኖር ነው።
#ጸሎት____መንፈሳዊ____ህይወታችንን_____የሚናሳድግበት____ትልቁ____ትምህር__ቤት______ነው
#ታድያ____ለመጸለይ____ምን____ማድረግ___አለብን ????
አጭርና ግልጽ መልስ #መጸለይ___ነው____ያለብን

2,መጽሐፍ ቅዱስን አለማንበብ
#መጽሐፍ____ቅዱስ____የእግዚአብሔር__ቃል____ነው
ሻሎም ቅዱሳን
#ከማርያም___ምን___እንማር ……
2 ሰዎች ጌታ ኢየሱስ የሚላቸዉን እንድያደርጉ ማስተማር ዮሐ 2፡1-11
በዚህ ሰርግ ኢየሱስ ፣ደቃመዘሙርትና የኢየሱሰ እናት ማርያም ተጠርተዋል ፡፡ነገር ግን በአንድ ጊዜ ለሰርጉ ይተአጋጀዉ የዎይን ጠጅ ስላለቀባቸዉ የኢየሱስ እናት ማርያም ኢየሱ ይህን ችግር እንድፈታላቸዉ ጠየቀቸዉ ፡፡ ኢየሱስም በማክበር አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ ? ጊዜዬ ገና ነዉ ብሎ መለሰላት ፡፡ ከዝያም ማርያም አስተናጋጆቹን የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ ብላ ነገረቻቸዉ ፡፡
እኛም እንደዚህ ዓይነት ፈተና ፣ የበለጠ ችግር ስገጥመን ወይም ለሌሎች ስገጥማቸዉ ጌታን እንድሰሙ መናገር አለብን፡፡ምክንያቱም ኢየሱስ ሁሉን ይችላልና፡፡
ሼር አድርጉ
@transformedchristianlife
| የአይጥ መርዝ ለምን አንጠጣም | || ልብ የሚነካ የመልካም ወጣት ምስክርነት
MARSIL TV WORLDWIDE @marsilchannel
. የአይጥ መርዝ ለምን አንጠጣም
የመልካም ወጣት ምስክርነት
🕑-10:59Min💾-.4.9MB
@marsilchannel
@marsilchannel
△Join Us△
ሻሎም ቅዱሳን በዚህ ቻናል የእግዚአብሔር ቃል እየተማማርን እንገኛለን ። ሌሎችም የበረከቱ ተካፋዮች እንድሆኑ ብትጋብዙአቸው ደስ ይለኛል።
@transformedchristianlife
ሻሎም ቅዱሳን የእግዚአብሔር ልጆች !
#ከማርያም_____ምን___እንማር?

3 #ትጉ__የሆነ__የጸሎት__ሕይወት ሐዋርያ ሥራ 1፡12-24
ኢየሱስ ደቃመዛሙርቱን ሦስት ዓመት ከተኩል አስተምሯቸዉ የምድር አገለግለሎቱን ጨርሶ ወደ አብ ከሄደ በኋላ ደቃመዛሙርት በአንድነት በምጸልዩነት ጊዜ #ማርያም ከኢየሱስ ደቃመዛሙርት ጋር ወደ እግዚአብሔር ትጸልይ ነበር።በዚህ ጊዜ #ማርያም___የኢየሱስ____እናት___መሆኗ በጸሎቱ ጊዜ የፈጠረው #ልዩነት የለም።ስለዚህ እኛም ማርያም እና የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ወደ ጸለዮበት ወደ #እግዚአብሔር___ብቻ___መጸለይ___አለብን

ይህን መልዕክት ለሚታውቋቸው #የኦርቶዶክስ___ተዋህዶ____ቤተክርስቲያን____አማኞች____ካሉ___ሼር____አድርጉላቸው
Share
@transformedchristianlife
ሻሎም ቅዱሳን የጌታ ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን።
#ዛሬ___ስለ___ሰላም__እንማማራለን !

መነሻ ጥቅሳችን

#ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ #ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።ዮሐንስ 14፥27

ኢየሱስ ሰላምን የሚሰጥ ንጉሥ ነው።ሰው በዚህ ዓለም ስኖር ሰላምን ልያገኝ ይችል ይሆናል ።ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ የሚሰጠው ሰላም ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም ።ዓለም ሰላምን የሚሰጠው በወታደሮች ነው።
#ዓለም የውጭ ሰላምን ልሰጥ ይችላል ።
#ኢየሱስ ግን #የውስጥንም ሆነ #የውጭውንም ሰላም ይሰጣል።

ሌላው የሚናየው ጥቅስ
ኤፌሶን 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴-¹⁵ እርሱ #ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥
¹⁶ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር #ያስታርቅ ዘንድ ነው።
¹⁷ መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤
¹⁸ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።

#ኢየሱስ___ሰላም___ሰጪ___ብቻ___ሳይሆን___እርሱ___ራሱ___ሰላማችን___ነው

ሉቃስ 24
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁶ ይህንም ሲነጋገሩ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ፦ #ሰላም___ለእናንተ___ይሁን___አላቸው
³⁷ ነገር ግን ደነገጡና ፈሩ መንፈስም ያዩ መሰላቸው።
³⁸ እርሱም፦ ስለ ምን ትደነግጣላችሁ? ስለ ምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል?

Share

t.me/aleazermelese
https://www.facebook.com/103767338553383/posts/163246635938786/

ይህ ልንክ ተጭነው የፌስቡክ ፔጄን ተቀላቀሉ !
ተባረኩ
👊🤜ጴንጤው ቦክሰኛ🤛👊
———————————————————
የቃል ጥናት ጥቅስ፦ <<ስለ ራሴ ከድካሜ በቀር የምመካበት ነገር የለኝም>> ❪2ኛ ቆሮ. 12፥5❫
———————————————————
| @superchristiantube7 |
| @superchristiantube7 |
| @superchristiantube7 |
| @superchristiantube7 |
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
መጋቢው መልእክታቸውን ለመስማት ለተሰበሰበው ህዝብ እንዲህ እያሉ ማስተማር ጀመሩ። ❮በዚህ ዘመን ያለን ሰዎች ሁሉ የምንመካበት ብዙ ነገሮች አሉን። ለመሆኑ የእነዚህ ነገሮች ሁሉ ምንጭ ማን እንደሆነ አውቃችኋል? #እግዚአብሔር ነው። ስለሆነም ትምክህታችን እርሱ ብቻ ሊሆን ይገባል። ዛሬ እውነቱን ልንገራችሁ፣ ሲመኩበት በሚያስመካው በዘላለሙ ጌታ ላይ ብቻ ትምክህታችንን ካላደረግን ከስረናል። ምናልባት በባንክ ባላችሁ ገንዘብ ብትመኩ ነገ ስለሚረግፍ ወይም ስለሚጠፋ ትምክህታችሁ ከንቱ ነው። ምናልባት በጊዜው ብትመኩ፣ ጊዜው ያልፋልና ከንቱ ነው። ውይም በጉልበታችሁ ብትመኩ፣ ጉልበት የእግዚአብሔር ነውና ከንቱዎች ናችሁ። እንግዲህ ትምክህታችን ምንድን ነው? ትምክህታችን ዛሬ ሲያምኑት ነገ በማይከዳና በማይለወጠው፣ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ላይ ብቻ ሊሆን ይገባል።❯ ለዚህም ዘላለማዊ እውነትነት ላለው ስብከታቸው ቀጣዩን ምሳሌ ተጠቀሙ። ለዚህም
ሰፈሩ ሁሉ የሚፈራው አንድ ሰውነቱ የፈረጠመ ቦክሰኛ ነበረ። ማንም እርሱን ቀና ብሎ አያይም ❪ዝንቡን የሚያባርር የለም❫ ። አለበለዚያ ቀና ብዬ አያለሁ እናገራለሁ ቢል ጡንቻው ከምድር ጋር ነው የሚያደባልቀው። በእንዲህ ሁኔታ ሲኖር ሳለ ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለው እግዚአብሔር በመለኮታዊው ሀይሉ የዚህን ቦክሰኛ ልብ ሰበረና ጌታን ተቀበለ። አማኝ መሆኑን የሰፈሩ ሰዎች ሁሉ ሰሙ። እሰይ እኛም አረፍን አሁን አይመታንም ብለው ተደሰቱ፤ የድሮ ፍርሃታቸውንም አስወግደው በፊቱ በንቀት መመላለስ ጀመሩ። ትንሽ ትልቁ ❮❮ጴጤው ቦክሰኛ❯❯ እያለ ማሾፍ ቀጠለ። አንድ ቀን ጴንጤው ቦክሰኛ #ተበሳጨ የድሮው ነገር ትዝ አለው። አንድ ልጅ እንደተለመደው #ጴንጤው_ቦክሰኛ ብሎት ሲያልፍ ያዘና በቦክስ ሁለት ጊዜ ሲነርተው አማኞች በአከባቢው ደረሱና ገላገሉት። ❮❮ተው፣ ለምን ትማታለህ? አማኝ አይማታም❯❯ ቢሉት፣ ❮❮አይ ጌታ ወንድ ልጅ እንዳለው ላሳያቸው ብዬ ነው❯❯ ብሎ መለሰላቸው።
የእግዚአብሔር ህዝብ ሆይ፣ የጌታ ልጅ መሆናችንን በሥጋችን ሀይል ማሳየት አንችልም፤ አልተፈቀደልንም። በፍቅር እና በእግዚአብሔር ሀይል እንጂ በከንቱ እየተነሣን እንድንመካ የሚያደርገንን የአሮጌውን ሰው ባህርይ እናስወግድ፤ ጌታንም ክርስቶስን ለብሰን በብዙ ትሕትናና አክብሮት እንድንከተለው ራሱ ጌታ ይርዳን። አሜን።
_____________________________
ግጥምጥም፦
በኃይልህ አትመካ ድንገት ይከዳሃል፣
በእግዚአብሔር ተመካ እርሱ ያዋጣሃል።
|2ኛ ቆሮ. 10፥17፤ ገላ. 6፥14|
¯¯¯¯¯¯¯¯­­¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

📱SHARE📲 📱SHARE📲 📱SHARE📲
Shalom የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት ቆያችሁ? ሰላማችሁ ይብዛላችሁ ።

ዛሬ ስለ መንፈሳዊ ሕይወት ዕድገት እንማማራለን ።
አንድ ህጻን ከተወለደ በኋላ ከመወለዱ በፊት በእናቱ ሆድ እያለ ምግብና ሌሎች አስፈላጊ የሚባሉ ነገሮች በእትብት በኩል ያገኛል ።ነገር ግን ህጻኑ ከተወለደ በኋላ የብዙ ጊዜ ባለውለታው እትብት ይቆረጥበታል ። እትብቱ ከተቆረጠለት በኋላ በቀጥታ የእናቱን ጡት መጥባት ይጨምራል ። ከዚያ ከጊዜያት በኋላ ጡት መጥባት ያቆምና ቀላል የምግብ ዓይነቶችን መጠቀም ይጀመራል ,,,,,ዳዴ ይላል ,,,,,ከቆይታ በኋላ ራሱን ችሎ መራመድ ይጀምራል ,,,,ቀላል ምግብ እየተጠቀመ ያለ ልጅ ጥርሱ ስጠነክር ጠንከር የሚል ምግብ መጠቀም ይጀምራል ,,,,,,,እድሜው ከፍ ሲል ሥጋ ወደ መብላት ይደርሳል ።
በተመሳሳይ አንድ ክርሰቲያን ጌታ በተቀበለ ቀን እንደ አዲስ ህጻን ነው። አገልጋዮች ይጸልዩለታል,,,,,ቃል ያስተምሩለታል። ብዙ ድጋፍ ያደርጉለታል ። ከዚያ በኋላ በራሱ ወደ እግዚአብሔር መጸለይና መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ከቻለ ,,,,ይህ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ሕይወት ዕድገት አለ ማለት ነው። በመንፈሳዊ ሕይወቱ እያደገ ሲሄድ ሌሎችም ማስተማርና ለሌሎች ዘደ መጸለይ ሕይወት ይደርሳል ።

#መንፈሳዊ____ሕይወታችን____እንድያድግ

➊መጸለይ
➋የእግዚአብሔርን ቃል መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ
➌መንፈሳዊ ሕብረትን ከቅዱሳን ጋር ማድረግ
➍በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ የተመሰረቱ መንፈሳዊ መጽሐፍትን አለብን ።

share
t.me/aleazermelese
Channel name was changed to «Aleazer Melese»
ሻሎም ቅዱሳን
አዲሱ አመት እንዴት እየሄደላችሁ ነው!?
ዛሬ በገንዘብ ስለ መባረክ እንማራለን እናወራለን
እግዚአብሔር አዳምና ሄዋን ኃጢአት ሰርተው ከገነት ከመባረራቸውም በፊት በገነት ውስጥ በነበሩ ጊዜ ስራ ይሰሩ ነበር። ነገር ግን ከገነት ሳይወጡና ከወጡ በኋላ ያለው የስራ ሁኔታው ወይም መልኩ የተለየ ነበር። እሱም

“አዳምንም አለው፦ የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤”
— ዘፍጥረት 3፥17
1,ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን ።
#ገነት__የተባረከች__ቦታ__ነበረች
2,በሕይወት ዘመን ሁሉ በድካም ከምድር ትበላለህ አለው።

ይህ ኖርማል life ነው።
እግዚአብሔር በገንዘብ እንድባርክልን ከፈለግን
1, አሥራት መስጠት
2,ድሆችን ማገዝ
3,በጽድቅ መስራት!!!!

#ይቀጥላል
t.me/aleazermelese