ቁርአንን ስትቀራ እርሱ ከፊቷ ተቀምጦ ያዳምጣታል። ድምጿ ውብ ነው ጆሮውን ሰርስራ ገብታ በጥዑም ዜማዋ የደረቀውን ልቡን ታረሰርሰው ይዛለች።

فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ

ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ ...

የሚለው የቁርአን አንቀፅ ጋር ስትደርስ ድምጿን ዝቅ አደረገች። ፈገግ አለና ወደኋላው ዞሮ ዓይን ዓይኗን እያየ "አንቺ ለኔ ሁሉንም ነሽ" አላት ፍልቅልቅ እያለች ጥዑም የቁርአን ዜማዋን ማነብነቧን ቀጠለች።

ያረብ ለኛም እንዲ ያማረ ትዳር ወፍቀን 🤲🤲🤲
አሚን በሉ 😊

#share
t.me/alahu_akber1
ሚስት ከባሏ ጋ እየተጨቃጨቀች ነበር።
ዝምበይ ቢላት ምን ተደርጎ ነው ዝም የምለው ትለዋለች። ዝም
ካላልሽማ አሳይሻለሁ ይልና ለመምታት ያስባል። ባይሆን ሚስት ብልህ
ነበረችና
((*ሸይኽ ዑሰይሚን ሴትን ልጅ መምታት ወንድነት አይደለም ))ብለዋል
።ሀዲስም ከፈለግክ ነብዩ ፍፁም ሴቶችን አልተማቱም ነበር የሚል
ሶሂህ ሀዲስ አለ ትለዋለች። ያዘጋጀውን መግረፊያ ይጥልላታል።
ከዚያም እሷ ቀስ አድርጋ ሆዱን 👊👊👊በቦክስ ትመታዋለች። መልሶ ይጮሀል።😟😟😟
ሚስት ፈጠን ብላ ሸይኽ ዑሰይሚን ሴትን ልጅ መምታትን ነው
ያወገዙት። ወንድን መምታት ነውር ነው አላሉም። አልወቀሱም ብላ
አስረዳችው።
በፀብ የተሞላው ቤት በሳቅ ተቀየረ።
ሴት ብልህና ተናናሽ ሁና ስትገኝ ቤቱ ሰላም ይሰፍንበታል።

አላህ እንደዚህ አይነት ትዳር ይወፍቀን።
ለበለጠ ኢስላማዊ መረጃ እና ጠቃሚ እዉቀት በዚህ ይከተሉን
👇👇👇
https://t.me/alahu_akber1
🎁〰〰〰እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰🎁
 
የታሪኩ ርዕስ
😢 #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ??❓
      🌀 #Part 1⃣7⃣

✍ ፀሀፊ #አሚር_ሰይድ

............የደሀ ልጅ ፍቅር.............
ምሽት አካባቢ ተጆራ ደረስን ከተማው ጫፍ ላይ ከመኪና ስንወርድ የከተማይቷ ወጣቶች ተደራጅተዉ  መዝረፍ የለመዱት ልክ እንደኮንትሮ ባንድ እቃ ሊሻሙን እየሮጠው መጡ ...... የቻለ እሩጦ ያመልጣል ያልቻለ ያለውን ይዘረፋል

    ሲፈትሹ ደግሞ ብር ይዘዉ ይሆናል ብለዉ ስለሚያስቡ ሹሪ አስወልቀዉ  ፓንት አይቀራቸውም ....ሁላችንም በሩጫ ብትንትናችንን ወጣ ወደ አገኘንበት አቅጣጫ በመሮጥ ግማሹ መስጊድ ግማሹ በተያየ ቦታ ሄደ
   áŠĽáŠ”ም  ከከተማይቷ የሚገኝ አንድ መስጅድ ገብቼ አመለጥኩ ....
መስጊዱ ሁኜ  አንድ ሰዉየ ተባበረኝ ብየ .... ለደላላው አስደወልኩበት ያለሁበትን ቦታ የመስጊዱን ስም ሰዎቹን ጠይቄ ነገርኩት.....
.
     ደላላዉ ክፍያው ስላላለቀ ለልሹ ሲል ሌላ መኪና ተኮናትቶ በያለንበት እየመጣ ሁላችንንም ሰበሰበን፡፡ የመጨረሻ መዳረሻ ወደሆነችው ሃዩ ከተማ ጉዙ ጀመርን ብዙ ከተጓዝን በኋላ ሃዩ ደረስን፡፡
  
      ሀዩ ከተማ ስንወርድ እኛም እናሳዝናለን ግን ከእኛ የባሰባቸው ብዙ ታያለህ ግማሹ ደላላው ብሩን ተቀብሎ ከድቶት ሲያለቅሱ... ግማሹ እዚያ ድረስ በእግሩ እየተጓዘ ደርሰዉ ደክመዉ የተቀመጡ ...ግማሹ ምግብ ስጡኝ እያለ የሚለምን አለ ግማሹ በርሀብ የተነሳ መንቀሳቀስ መራመድ የማይችል ብዙ ነገር አየሁ፡፡ ... ብቻ ስደት አኡዙቢላሂ አስፈሪ ነዉ  የዱኒያ ጀሀነም በስደት ወደ ዉጭ ሀገር ለመሄድ መሞከር ነዉ
   አላህ እንዲህ ይላል  ወላቱልቁ አንፉሰኩም ኢለተህሉካት >>>>>>ራሳችሁን ወደሚጎዳችሁ መጥፎ ነገር ላይ አትጣሉት <<<< ይለናል 
     በስደት ጉዞየ ላይ ተወቃሽ ያደረኩት በባህር ሂደው ውጭ ትንሽ ተቀምጠውና ሰርተው ሲመለሹ እያነጀቡና ስለስደት ጥሩ ጎን ብቻ የሚለፈልፉ ሰወችን ነው፡፡  ስደት በባህር መሄድ በጣም ስቃይ ሞት እንዳለው ለምን ይሸፋፍኑታል??? ስደት ማለት ስድ ነው ያንን ሒወት አይቶ መኖር ለልሹ በጣም አስፈሪ ነዉ፡፡
.

    ....እዚያው ሃዩ ከተማ አደርን በማግስቱ ወደባህሩ ዳርቻ ለመሄድ ከከተማው ወጣ ብለን መኪና መጠበቅ ነበረብንና...... በእግራችን ወጣን
........የሆነ ቦታላይ ደረስን የተሰበሰቡ ሰወች አገኝን ምንድናችሁ ??? ምን ሁናችሁ ነዉ የተሰበሰባችሁት??? አልናቸው
 .....እነሱም  ደላላወቻችን አስቀምጠውን ነው፡፡ አሉን.... ግማሹ ከተቀመጠ ወር ሆኖታል ከዚያም በላይ አለ እንዳይሞቱ የተወሰነ ምግብ ይሰጣቸዋል እንዳይሄዱ መሳሪያ በያዙ ሰወች ይጠበቃሉ ከዚያ መሀል ራቡ አስክሮት የሚጮህ አለ ፡፡ አንዳንዱ እርሀቡን መቆጣጠር አቅቶት የሚንፈራፈር አለ....አንዳንዱ ደግሞ እንግሊዝኛም ይቀላቅላል፡  
   እኔ አረበኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋ አዉቃለሁ ሲያወሩ አሁን ያሉበትን ቦታ ያሳዝናል፡፡ ያለቦታየ መወድቄን አወኩት ተስፋ ተሟጠጠብኝ....   ብቻ ሀበሻ ስንባል በየሔድንበት ችግር መከራ እናሳልፋለን...እናሳዝናለን፡፡
      የኔ ደላላ በሰዉ ነዉ ያገኘሁት ከአሉት ደላላዎች የተሻለ ስለነበረ ወደባህሩ ዳርቻ ሊወስደን መኪና ላይ ጫነን ባህሩ ዳርቻ ለመድረስ ብዙ ሰአት ያስኬዳል ...በመኪና እየሄድኩ  በእግሬ ቢሆን ምን ልሆን ነበር ????እያልኩኝ አልሃምዱሊላህ እላለሁ
.......ደላላው የሆነ ቦታ ላይ ሽንት ለመሽናት አቆመ አብሬ ወረድኩ፡፡ አካባቢው አንዳንድ የበረሀ ዛፍ ቅጠል የሌለው ታያለህ ፡፡ እናም የሆነ ግንድ ላይ ዛፉን ተገድፎ የተቀመጠ ሰው አለ ፡፡ ደላላውን ያ ሰው ምንድነው??? አልኩት
....,,ደላላዉም  ያማ ብር አንሶት  በእግሬ ወደ ባህሩ እደርሳለሁ ብሎ ሲመጣ ረሃብና ውሃ ጥም ገድሎት የሚቀብረዉ አጥቶ ነው አለኝ ፡፡ በጣም አስፈሪ ነበር  እኔም  እንዴት ትተነው እንሄዳለን እንቅበረዉ እንጂ የሞተን ሰዉ ካየህ መቅበር ግዴታ ነዉ እኮ??አልኩት
......... ዳላላዉም አይ አንተ ልጅ  እናንሳው እንቅበረዉ ካልንማ ወደፊት ስንሄድ ብዙ የሞቱ ሰወች እናገኛለን አለኝ..... ያለህ አማራጭ ምን ብታዝን ከንደዚህ አይነት ጭንቀት ራስህን ማውጣት ነው...እነሱን እያየህ ጌታህን እኔን ከዚህ የጠበከኝ እያልክ እያመሰገንክ  ትተህ መሄድ ብቻ ነው አለኝ፡፡  
 
......ምንም አማራጭ የለም እንዳለዉም እየሄድን የብዙ ሰዉ እሬሳ የሚቀብረዉ ጠፍቶ ...ደግሞ ግማሹም አሞራ እየበላዉ  አየሁኝ.....

  በዚህ ባየሁት ሒወት እያዘንኩ የሰዉ ልጅ ያልፍልኛል ብሎ በርሀ ያለቀባሪ መቅረት የቁራ እና የአሞራ ምሳ መሆናችን በጣም አሳዛኝ ነዉ፡፡ እኔ ከሁሉም እንደዚህ ወደ ስደት ሲወጣ እናቱን አባቱን ወንድም እህቱን ልጁን ሚስቱን ጥሎ ያልፍልኛል ብሎ አስቦ እንደወጣ መቅረት አሳዛኝ ነዉ፡፡እናት አባት ወይም የወለደዉ ልጅ ይመጣል ወይም መቼ ነዉ ድምፁን የምሰማዉ እያሉ ሲያለቅሱ መኖር ብቻ ነዉ ....ለምን በስደት ላይ ሙታል እንዴት ብሎ ይመጣል ፡፡ በስደት የወጣ መቼም ሞተ ግን እሱ ብቻዉን አይሞትም እናት እና አባቱ አብረዉ የቁም ሞት ይሞታሉ ..መቼ ነዉ ልጄ የሚደዉልልኝ ???እያሉ መጠበቅ ነዉ የሚሆነዉ.....ሰዉ በስደት እንደ ቅጠል ይረግፋል፡፡
     ደግሞ ሴቶቹ በየቦታዉ በማይታወቅ ሰዉ ይደፈራሉ ፡፡የደላሎች ስሜት ማብረጃ ይሆናሉ፡፡ ሴትነቷን መጠቀሚያ ነዉ የሚያረጓቸዉ መጥፎ ደላሎች ለአንዳንድ ባለሀብቶች ብር እየተቀበሉ እዛ በረሀ ላይ ከምታድሩ እቤት እደሩ ብለዉ ያዘኑ መስለዉ ሳትወድ በግዳ አንድ ወንድ ጋር ታድራለች፡፡ ብታለቅስ ብትጮህ ማንም የሚገላግላት የለም ይሄንን ግፍ ከመቀበል በቀር ...ሒወት ይቀጥላል ሳይሆን ላይቀጥልም ይችላል የሚለዉን ማሰብ አለብን ...ሒወት ከስደት ቡሀላ የሚቀጥል አይመስልም አስፈሪ እንቅልፍ የሚነሳ ነዉ፡፡
   በዚህ እድሚየ ፈጣሪ ስንቱን አሳየኝ፡፡

   ......እንደምንም ብዙ በርሀ ከተጓዝን ቡሀላ ...ባህሩ ዳርቻ ደረስን ፡፡ እዛዉ ሜዳዉ ላይ አደርን......

  ጠዋት ላይ እንደተነሳን እዛዉ ሜዳዉ ላይ ከቀይ ባህር አጠገብ.....ከሀርቡ ከተለያዪ የኢትዮጲያ ሀገር የመጡ ሰዎች ጋር ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍን ...ቁምጣ ለብሰን እበሀሩ ጎን ሁነን በዉሀ ስንቦራጨቅ ዋና የሚችል እዛዉ እየዋኙ... ደስ የሚል ጊዜ ስናሳልፍ ዋልን...ትንሽም ቢሆን ተረጋጋሁ ..ትንሽ ደስታ ትልቅ ሀዘንን ማጥፋት ትችላለች፡፡

    ግን የወጣሁበት አላማ ለካ ለመደሰት ሳይሆን ለማዘንም ነዉ ፡፡ ይሄን ደስታየን ከአንድ ቀን ሳያልፍ....ጀልባው መጣ ፡፡

ሁላችንም ስደተኟች ወደ ሀያ(20) የምንሆን ሰወች በባህሩ ጉዟችንን ልንጀምር ወደ ጀልባዉ እየወጣን ነዉ......
  እኔም ከቀይ ባህር ዳርቻ ቆሜ ፓስፖርቴን እና የሰአዳን ፎቶ የያዘውን ፖርሳየን በፌስታል ውሃ እንዳያበሰብስብኝ ጠቅልየ ጉያየ አስገባሁት
...........ጀልበዋ ወደ የመን መንቀሳቀስ ጀመረች
#Part 1⃣8⃣
ይ.......ቀ......
..............ጥ.......ላ............ል
.........
JOIN   t.me/alahu_akber1
  •════•••🍃🌺🍃•••════
__እዉነተኛ ታሪክ_
😢 #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ??❓
      🌀 #Part 1⃣8⃣

✍ ፀሀፊ #አሚር_ሰይድ

 .   ጀልበዋ  በጣም ትንሽ ነች......ባለጀልባዉም  ከ 12 -15 ሰው በላይ አትይዝም አለዉ ለደላላዉ ...በጀልባ የሚወስደን ሰዉ .....
......ደላላው በዛ በዚህ ብሎ ለብቻዉ ጠርቶ ብር አስጨብጦ  አሳመነው፡፡ ሁላችንም ወደ ጀልባዉ ወጣን.....
     ደላላው ከአሁን ቡሀላ ሀላፊነቴን ተወጥቻለሁ በሰላም ግቡ አላህ ከእናንተ ጋር ይሁን ብሎ ተሰናበተን ........
    ከዚያም  በኋላ ምን እንሆን ይሆን???  ጀልባዋ መንቀሳቀስ ጀመረች ፡፡19 ወንድ ስንሆን አብራን አንዲት ሴት አለች
.............ከድር አለችኝ
...... አቤት አልኩኝ
......,እንካ የጉዞ ኪንን ውሰድ ያስመልሰሀል (ያስታዉከሀል)አለችኝ
 .......ደግሞ ይሄ ውሃ ነዉ ቀጥታ ነዉ የሚሄደው አልወስድም አልኳት
......,ፈገግ አለችና ታያለህ እኔ አሁን ሁለተኛየ የወሰድኩት አለችኝ ፡፡ የበሀር ጉዞ ከአሁን በፊት ሂጄ ነበር  አለችኝ
.....እኔም አልፈልግም አልኳት
.....መሬቱን እየራቅነው ወደባህሩ መሃል ገባን
     ጀልባው  ወደመሀል ስንገባ መለስተኛ ማእበል ተነሳ በዚያ ላይ ጀልባዋ ትንሽ ናት.... ጀልበዋን በተደጋጋሚ ወደላይ ብድግ ያደርጋታል መልሶ ዉሀዉ ላይ ዘጭ ትላለች
      ወላሂ አስታውሳለሁ በአላህ ምየ ነው የምነግራችሁ እዚያ ጀልባ ላይ አላህን እንደለምንኩት ውጭ ሌላ ቀን  ብለምነው ኖሮ ምንም ነገር እምቢ አይለኝም፡፡ ሁላችንም በጀልበዋ ያሉት ሰዎች ጭንቀቱ በረታ፡፡
..... በሁለት እጄ አግዳሚ ጣውላውን ጨብጨ ይዣለሁ ብቻ ብዙ ነገር ሳስታውሰው ይዘገንነኛል ማዉራት ይከብደኛል፡፡
  የመኪና መንገድ  á’áˆľá‰łáˆ˜áŠ•áŒˆá‹ľ  ምናለበት፡፡ መለስተኛ ማዕበል ተነሳ መርከቧን ወደላይ አንስቶ ያፈርጣታል አቤት ጣውላው አለመሰንጠቁ ያች ጀልባ በጉንና ጎኗ ውሃ እየገባ ይሞላታል ውሃውን ዛቁ አውጡ አለቅን ይባባላሉ እኛም ነገሩ ሲጠና እየሄድን  ግማሻችን  ውሃውን እናወጣለን ግማሻችን ያአላህ እያሉ ያለቅሳሉ
    አንዱ የመኔ ጀልባዋን ይሾፍራል ሌላኛው ጓደኛው በኮኮብ አቅጣጫን ከፊት ሆኖ እየተከተለ ይመራል፡፡
.....ልጅቱ መድሀኒቱን ዋጥ ያለችኝ እዉነቷን ነበር.... አንዱ ባንዱ ላያ ያስታውካል እኔ ጣውላውን በእጀ ይዣለሁ ከጎኔ ባለው ሰው አናት ላይ ትውኪያየን ለቀኩበት ፡፡ ማንም ማንንም አይሰማም የጭንቀት ሽንት አለ በአምስት ሊትር ገድበህ የምትሸናው
..... እኔ ውሀው ተቀላቅሎበት ይሁን ሽንቱ በዝቶ አልገባኝም ጎማውን ሞላሁት ከጎኔ ያለው አምጣ እኔም ልሽና አለኝ
....እኔም ቆይ አልጨረስኩም አልኩት አሁን ላይ ሳስበው እንባየ እስከሚመጣ እስቃለሁ
  አንዱ በጭንቀት እንዲህ አለኝ ከድር እየተያየን ከምናልቅ እኔና አንተ ዘለን ውሃው ውስጥ እንግባ አለኝ
....እኔም እሺ አልኩት ሁላችንም በጭንቀት አብደናል ያ ልጅ ብድግ ሲል የመኒው በያዘው ዘንግ ወገቡን ሲለው ቁጭ አለ ብቻ የጭንቀት ሽንት ባህር ላይ ተሸና ፡፡
   በጣም የሚገርመው እኛ በዚያ ጭንቀት ላይ ሆነን  መድሀኒት ዋጥ ያለችኝ ልጅ አብራን የተሳፈረችውን ሴት ጡት ለማሸት ባንድ እጁ እየነዳ ባንድ እጁ ይታገላል፡፡ እሷም ትሸሸዋለች በአማረኛ ተወኝ አላህን ፍራ ትለዋለች
... ከሷ ጎን ያለው ልጅ አብዱ ይባላል ውሃ እየዛቀ ከደር!  ከድር!  በአረበኛ ተናገረው ተው በለው አለኝ
.....እኔም አልሃሪም ሃምላ  አልኩት (ሴቲቷ እርጉዝ ነች)ማለት ነው ድንግጥ ብሎ መተናኮሉን አቆመ.....እኔም ገረመኝ በዛ ጭንቀት እንዴት እንደዛ ስለዉ መተዉ አጀበኝ
 
    እንደምንም ከ 6 ሰአት ጉዞ በኋላ አላህ በሰላም የመን ምድር ደረስን ፡፡.......ደረቁ መሬት áˆ‹á‹­ ጀልባዋ ቆመች..... እኔ ግን እጄ ጣውላውን የጨበጥኩበት እዚያው ላይ ደርቋል ይሄ የጨው ውሃ ሰውነቴን ስለረጨኝ .....ጨው መስያለሁ፡፡
   
     ከባህሩ እንደወረድን  ዳር ላይ የሚቀበሉን የየመን ምሽዋር ቤት ደላላዎች.....እጄን ፈልቅቀው እግርና እጄን ይዘው መኪና ላይ ጫኑኝ ፡፡ ጉዞ ወደ ምሽዋር ቤት በመኪና ተጭነን ሄድን............እዚያ ደረስን ሸዋር አስወሰዱን ምግብ አበሉን ፡፡
.......ለሁለት ቀናት አሳረፉን ገንዘብ የሚላክለትን አስቀርተው ....ሌሎቻችንን ገንዘብ የማይላክልንን የተወሰነ ስንቅ እያስያዙን አሰናበቱን፡፡
    ይህን ያደረጉት ገና አዲስ ምሽዋር ቤት ከፋቾች ጥሩ ሰዎች ስለሆኑ ነዉ እንጂ ብዙዎቹ ጨካኝ ናቸዉ ገላችንን አሳጥበዉ የተወሰነ ስንቅ መስጠታቸዉ የተሻሉ ሁነዉ ነዉ...... ከዚያ ከምሽዋር ወጥቸ በእግሬ አምስት ቀን ተጓዝኩ
 >>>>>>>>>>>>> የምንከተለው ቂብላን ነው... ሲመሽ በርሀ ላይ አድረን አቅጣጫው ከጠፋን ወደኋላም ልንመለስ ስለምንችል በምሽት መጓዙን አልመረጥነዉም...... በየገጠሩ በሚገኙ መንደሮች እያገለልን ምግብ እንጠይቃለን .....የመን የዋህና ገራገር ናቸው ያላቸዉን ይሰጣሉ እንደዚህ እያልን አምስት ቀን ተጓዝን......

   ከ 5 ቀን በኋላ ግን እኔ መጓዝ አልቻልኩም እግሬ አበጠ ዉስጡም ቆሰለ አንድ ጫማ ነዉ ያለኝ  ተገነጠለ.... አብረውኝ የሚጓዙት ሃበሻ ቢሆኑም የሌላ አገር ሰወችም አሉ ፡፡    
    ያገናኝን ይሄ ቀላል መስሎ ከባድ የሆነ መከረኛው ስደት ነው፡፡  ያላቸው አማራጭ እነሱ ለመዳን አብሽር አላህ ይሁንህ ብለዉኝ  እኔን ለአላህ ሰጥተውኝ ወደፊይት መሄድ ብቻ ነው ፡፡ ከዛፍ ሾር አስቀምጠዉኝ ተሰናበቱኝ ...ደላላዉ ጋር ስመጣ እንቀበረዉ እንጂ ከዛፍ ሾር ሙቶ ተቀምጧል ያልኩት ትዝ አለኝ፡፡
......የአላህ ምን ያጋጥመኝ ይሆን እያልኩ 100% ተስፋ ቆርጫለሁ እምባየም ቁጭ ባልኩበት ኩልል እያለ እዛ የበረሀ አፈር ላይ ያርፋል ሞት ብቻ ነዉ የሚጠብቀኝ ...አይታወቅም ከአላህ ተስፋ አልቆርጥም ብየ ዱአ እያረኩ ነዉ ፡፡ 
  
       አንድ በሞተር የሚሄድ የመኒ መጣ....ሞተሩን ከተቀመጥኩበት ጎን አቆመና ብር እንዳለኝ ለመፈተሽ ፖርሳየን አወጣዉ.... ከፈተው ምንም አላገኝም፡፡እኔን  ኬሴን አገላብጦ ፈተሸኝ ባዶ ነኝ ......ሲፈተሽ ግን ሰአዳ የሰጠችኝን ፎቶ መልኳ እስከሚገፍ ድረስ ካየዉ ቡሀላ  መሬት ላይ ጣለዉ፡፡
......ፖርሳውን ፊቴ ላይ ወርውሮ ትቶኝ በሞተሩ ሄደ፡፡  መሬት ላይ የወደቀዉን የሰአዳ ፎቶ አንስቼ መመልከት ጀመርኩ ....ሰአዲ ከኔ ተስፋ ቁረጭ አንገናኝም አንቺን ለማግኘት ላለማጣት ብየ  ብር ለመያዝ በርሀ ላይ ማንም ጠያቂ የሌለበት ምግብ ወሁ ሳይኖረኝ እግሬ ቁስሎልሻል  መሔድ አቅቶኝ ሞቴን እየጠበኩ ነዉ ..ሰአዲ እንገናኝ ይሆን????? ወይንስ እዚሁ የወደኩበት ህይወቴ ያልፍ ይሆን? ረሀቡ አልቻልኩትም የእግሬ መቁሰል መሄድ ስላቃተኝ እዚያ እሰዉ ሀገር ምንም ሰዉ የሌለበት ቁጭ እንዳልኩ ብቻየን አለቅስ ይዣለሁ...
  
   ይቺ ነፍስያ አላስችል አላት አሟሟቴ አስጠላኝ ተስፋ ቆረኩ ላኢለሀኢለሏህ ሙሀመዱ ረሱሉላህ እያልኩ በተደጋጋሚ ሸሀዳ ላይ ነኝ ፡፡
  ጊዜዉም መሸ እኔም እርሀቡ ዉሀ ጥሙ አሸነፈኝ..አልጮህ የሚሰማኝ የለም ደግሞም á‹‰áˆ€ ጥም አፌ ተያይዟል እንኳን ሰዉ እንዲደርስልኝ ቃላት የምናገርበት አቅም የለኝም...አይኔ እያየ መሞት አልቻልኩም..ከተቀመኩበት እንደምንም ለመነሳት ስንገዳገድ አዞሮኝ መሬት ላይ ዝርር ብየ ወደኩ
part 1⃣9⃣ ይቀጥላል👇
 t.me/alahu_akber1
አስለቅሶታል መሰለኝ የነገራት ሰዉ አብሮ ያለቅስ ነበር፡፡ ስደት ማለት ትርፉ ይሄ ነዉ፡፡ ተመልከቱ ሳዉዲ ያለችዉ እህቷ አደራ ምንም እንዳትሆንብኝ እያለች መሞታን ሰማች ያልፍልኛል ብላ እህቴን አገኛለሁ ብላ ለአገሯ አፈር ሳያበቃት እሰዉ ሀገር ሞተች ለዛዉም አሟሟቷ የሚዘገንን ነዉ.....እናት አባት ሲሰሙ ምን ይሉ ይሆን፡፡ መቼም ይሄን እዉነተኛ ታሪክ አንብቦ እምባ የማይወጣዉ ጨካኝ አረመኔ ቢሆን ነዉ፡፡

   ልጅቱን አብሬ አልቅሰን ከቀበርን ቡሀላ ከባድ ሀዘን ተስፋ ተሟጦ  የምሄድበት ግራ ሲገባኝ ከመኪና መንገድ ዳር ላይ ቁሜ ..አንድ  መኪና ሲመጣ እንዲያቆምልኝ በእጄ ምልክት ሰጠሁት....,
.....
ሹፌሩም አቆመልኝ
......,እኔም ወደ ሳውዲ ነኝ ተባበርኝ አልኩት
.......እሽ ውጣ አለኝ 
         መኪናዉ ከላይ ክፍት ነበርና ወጣሁ
  ......ምነው እዚህ መኪና ላይ መዉጣት በቀረብኝ ፡፡ ለካስ የወሰደኝ ሊተባበረኝ ሳይሆን ለምሽዋር ቤት ሊሸጠኝ ነው፡፡ ለምሽዋር ቤቶች ለነዚህ ጨካኞች አስገብቶ 100 ሪያል ሸጠኝ .....
 á‹¨áˆ†áŠ ክፍል ዉስጥ አስገብተዉ ወረወሩኝ እና መልሰዉ በሩን ዘጉት፡፡ ብዙ ሰዉ እንደ በግ የታጎረበት ክፍል ነዉ በጣጣጣጣም  ብዛት አላቸዉ የተለያዩ ሀገር ዜጎች ወንድ ሴት ድብልቅልቅ ያለ ክፍል ነዉ ....
     ቤቱ ግንብ ነው ከላይ ክፍት ነው ዙሪያውን ከግንቡ ላይ መሳሪያ ይዘው የሚጠብቁ አሉ ከዚያ ቦታ ድንበሩን ለማሳለፍ ብቻ 1500 የሳውዲ ሪያል ያስከፍላሉ፡፡  እዚህ ቤት ውስጥ የምትገባው አምነህበት ወደህ ሳይሆን  ተገደህ ነው ....
 .ይሄንን 1500 የሳዉዲ ሪያል ካልከፈልክ መውጣት አይታሰብም ፡፡  ምን ይዉጠኝ የሆን ...አይ የኔ ፈተና ብዛቱ......
 
#part 2⃣0⃣
 á‹­..............ቀ.....
...........ጥ............ላ............ል👇

 .¡¨: ❀ share
           `¡.     t.me/alahu_akber1
#rio
Don’t you ever break someone’s heart, because they only have one. Break their bones, they have 206 of those!
@alahu_akber1
part 1⃣

ከትዳር በፊት እንጠናና...አግባብ ነዉ ወይ??

✍✍ከኒካህ በፊት ስለማንነታችን በደንብ እንተዋወቅ። ለትዳር ሂወታችን ጠቃሚ ስለሆነ እየተጠናና እንቆይ የሚባለው አባባል ከሸሪአ አንፃር እንዴት ይታያል?

💐💐ኢስላም በመሰረቱ ማንኛውም ማህበረሰቡን የሚጎዱ ተግባራትን ቀድሞ እንድንርቃቸው ያዘናል፡፡ በማህበረሰበችን ዘንድ እንኳን ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም ግንኙነት በጥሩ አይን አይታይም፡፡ የሴት ልጅ ክብሯ እና ውበቷ እራሷን የህዝብ ሃብት ከማድረግ መቆጠብ መቻሏ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ሂጃብ ከማደረግ እራሷን ከመሸፈን አንስቶ ከማንኛውም አይነት አጂ ነብይ ወንድ ጋር ከኒካህ በፊት ግንኙነት ሳታደርግ መቆየት መቻሏ ነው፡፡

✅✅ይህን የሃራም ግንኙነት ሁሉም ማለት ይቻላል  ክልክል መሆኑን ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ ወጣቱም፣አዋቂውም፣ጃሂሉም ባጠቃላይ  ማገናዘብ የጀመረ ሙስሊም በሙሉ ከኒካህ በፊት ምንም አይነት ግንኙነት ማድረግ በኢስላም ክልክል መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ይህን የአላህን ክልከላ አውቆ የሚርቀው ግን በጣም ጥቂቱ ነው፡፡

♻️♻️♻️♻️በኢስላም ጋብቻ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው  ሲሆን መልካም የሆኑ ባል እና ሚስቶችን የሚጣመሩበት ይሆን ዘንድ ያዛል፡፡ ባለጌ ባለጌን እንጂ ጨዋን እንድታገባ  በኢስላም አይፈቀደም፡፡ በዝሙት የተጨማለቀ ወንድም የሱ ቢጤውን እንጂ ጥብቅ የሆነችን ሴት እንዲያገባ አይፈቀደም፡፡ ታዲያ ከጋብቻ በፊት ዝሙት እስካልፈፀምን ድረስ ይህ ክልከላ አይመለከተንም ይባል ይሆናል፡፡

መረጃውን እንደሚከተለው እንመልከተው:-

فَانكِحُوهُنَّ بِإِذْنِ أَهْلِهِنَّ وَآتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ مُحْصَنَاتٍ غَيْرَ مُسَافِحَاتٍ وَلَا مُتَّخِذَاتِ أَخْدَانٍ ۚ

ጥብቆች ኾነው ዝሙተኞች ያልኾኑ የስርቆሽ ወዳጆችንም ያልያዙ ሲኾኑ (አግቧቸው)፡(ሱራ አል ኒሳዕ፡25)

✍✍✍ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው ይህን አንቀፅ ኢብኑ አባስ(አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) ሲፈስሩት ጥብቆች የሆኑ ማለቱ ምንም አይነት ዚና ያልፈጸሙ እና የብልግና ተግባር ከማንም ጋር ለመፈፀም እሺ የማይሉ መሆኑን ሲገልፁ  وَلَا مُتَّخِذَاتِ أَخْدَانٍ የሚለው ደግሞ ፍቅረኛ ያልያዙትን ማለት እንደሆነ አስቀምጠዋል፡፡ በዛው ማብራሪያቸው ላይም ሃሰነል በስሪ(አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) የወንድ ጓደኛ ማለት እንደሆነ መናገራቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ተመሳሳይ መልዕክትም  በሱረቱል ማዒዳ ላይ የሚከተለውን እናገኛለን፡-

وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الْمُؤْمِنَاتِ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَافِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِي أَخْدَانٍ

ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)፡፡(አል ማዒዳ፡5)

❤️❤️❤️ይህንንም አንቀፅ አስመልክቶ ኢብኑ ከሲር(አላህ ይዘንላቸው) ሲያብራሩ ጥብቅ የሆነችን ሴት የሚለውን ከዝሙት የራቀች ፣የወንድ እጮኛ ያልየዘች መሆኑን በመግለፅ ይህ ድንጋጌ ወንዱም ጥብቅ፣ዝሙተኛ ያልሆነ፣የሴት እጮኛ ያልያዘ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ማብራሪያቸው ላይ ብዙ እጮኛ ያለውም ሆነ አንዲት እጮኛ ተመሳሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህ ማብራሪያ ላይ ኢማሙ አህመድ(አላህ ይዘንላቸው) ከላይ በተገለፀው አንቀፅ መሰረት ጥብቅ ያልሆነ ወንድ ወይም እጮኛ የያዘ እንደሆነ ጥብቅ የሆነችን ሴት ተውበት አድርጎ ከድርጊቱ ሳይመለስ ማግባት ለሹ የተከለከለ መሆኑን ፡፡ እንዲሁም ጥብቅ ያልሆነች ሴት፣ ወይም ወንድ እጮኛ ይዛ የነበረች ሴት ከድርጊቷ ተውበት አድርጋ እስካልተመለሰች ድረስ ጥብቅ ወይም ጨዋ ወንድን ማግባት ክልክል ነው  ማለታቸውን ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

Part 2⃣
ማታ ይቀጥላል✅✅✅

#Share $ join
👇👇👇
https://t.me/alahu_akber1
part 1⃣

ከትዳር በፊት እንጠናና...አግባብ ነዉ ወይ??

✍✍ከኒካህ በፊት ስለማንነታችን በደንብ እንተዋወቅ። ለትዳር ሂወታችን ጠቃሚ ስለሆነ እየተጠናና እንቆይ የሚባለው አባባል ከሸሪአ አንፃር እንዴት ይታያል?

💐💐ኢስላም በመሰረቱ ማንኛውም ማህበረሰቡን የሚጎዱ ተግባራትን ቀድሞ እንድንርቃቸው ያዘናል፡፡ በማህበረሰበችን ዘንድ እንኳን ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም ግንኙነት በጥሩ አይን አይታይም፡፡ የሴት ልጅ ክብሯ እና ውበቷ እራሷን የህዝብ ሃብት ከማድረግ መቆጠብ መቻሏ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ሂጃብ ከማደረግ እራሷን ከመሸፈን አንስቶ ከማንኛውም አይነት አጂ ነብይ ወንድ ጋር ከኒካህ በፊት ግንኙነት ሳታደርግ መቆየት መቻሏ ነው፡፡

✅✅ይህን የሃራም ግንኙነት ሁሉም ማለት ይቻላል  ክልክል መሆኑን ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ ወጣቱም፣አዋቂውም፣ጃሂሉም ባጠቃላይ  ማገናዘብ የጀመረ ሙስሊም በሙሉ ከኒካህ በፊት ምንም አይነት ግንኙነት ማድረግ በኢስላም ክልክል መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ይህን የአላህን ክልከላ አውቆ የሚርቀው ግን በጣም ጥቂቱ ነው፡፡

♻️♻️♻️♻️በኢስላም ጋብቻ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው  ሲሆን መልካም የሆኑ ባል እና ሚስቶችን የሚጣመሩበት ይሆን ዘንድ ያዛል፡፡ ባለጌ ባለጌን እንጂ ጨዋን እንድታገባ  በኢስላም አይፈቀደም፡፡ በዝሙት የተጨማለቀ ወንድም የሱ ቢጤውን እንጂ ጥብቅ የሆነችን ሴት እንዲያገባ አይፈቀደም፡፡ ታዲያ ከጋብቻ በፊት ዝሙት እስካልፈፀምን ድረስ ይህ ክልከላ አይመለከተንም ይባል ይሆናል፡፡

መረጃውን እንደሚከተለው እንመልከተው:-

فَانكِحُوهُنَّ بِإِذْنِ أَهْلِهِنَّ وَآتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ مُحْصَنَاتٍ غَيْرَ مُسَافِحَاتٍ وَلَا مُتَّخِذَاتِ أَخْدَانٍ ۚ

ጥብቆች ኾነው ዝሙተኞች ያልኾኑ የስርቆሽ ወዳጆችንም ያልያዙ ሲኾኑ (አግቧቸው)፡(ሱራ አል ኒሳዕ፡25)

✍✍✍ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው ይህን አንቀፅ ኢብኑ አባስ(አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) ሲፈስሩት ጥብቆች የሆኑ ማለቱ ምንም አይነት ዚና ያልፈጸሙ እና የብልግና ተግባር ከማንም ጋር ለመፈፀም እሺ የማይሉ መሆኑን ሲገልፁ  وَلَا مُتَّخِذَاتِ أَخْدَانٍ የሚለው ደግሞ ፍቅረኛ ያልያዙትን ማለት እንደሆነ አስቀምጠዋል፡፡ በዛው ማብራሪያቸው ላይም ሃሰነል በስሪ(አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) የወንድ ጓደኛ ማለት እንደሆነ መናገራቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ተመሳሳይ መልዕክትም  በሱረቱል ማዒዳ ላይ የሚከተለውን እናገኛለን፡-

وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الْمُؤْمِنَاتِ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَافِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِي أَخْدَانٍ

ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)፡፡(አል ማዒዳ፡5)

❤️❤️❤️ይህንንም አንቀፅ አስመልክቶ ኢብኑ ከሲር(አላህ ይዘንላቸው) ሲያብራሩ ጥብቅ የሆነችን ሴት የሚለውን ከዝሙት የራቀች ፣የወንድ እጮኛ ያልየዘች መሆኑን በመግለፅ ይህ ድንጋጌ ወንዱም ጥብቅ፣ዝሙተኛ ያልሆነ፣የሴት እጮኛ ያልያዘ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ማብራሪያቸው ላይ ብዙ እጮኛ ያለውም ሆነ አንዲት እጮኛ ተመሳሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህ ማብራሪያ ላይ ኢማሙ አህመድ(አላህ ይዘንላቸው) ከላይ በተገለፀው አንቀፅ መሰረት ጥብቅ ያልሆነ ወንድ ወይም እጮኛ የያዘ እንደሆነ ጥብቅ የሆነችን ሴት ተውበት አድርጎ ከድርጊቱ ሳይመለስ ማግባት ለሹ የተከለከለ መሆኑን ፡፡ እንዲሁም ጥብቅ ያልሆነች ሴት፣ ወይም ወንድ እጮኛ ይዛ የነበረች ሴት ከድርጊቷ ተውበት አድርጋ እስካልተመለሰች ድረስ ጥብቅ ወይም ጨዋ ወንድን ማግባት ክልክል ነው  ማለታቸውን ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

Part 2⃣
ማታ ይቀጥላል✅✅✅

#Share $ join
👇👇👇
https://t.me/alahu_akber1
❤️ፍቅር እና ሞት ሁለት ያልተጋበዙ እንግዶች ናቸው።
ፍቅር ልብን ሲወስድ......
ሞት ደግሞ የልብ ምትን ይወስዳል!!!!😔


Š
.
.
🪴✨🌹🌹✨


      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     âŽ™ă…¤   âŒ˛            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ
#share_join_channel
@alahu_akber1
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
ውድ የ
#rio_islamic_post ቤተሰቦች. የምትፈልጉትን ታሪክ ሊንኩን በመንካት ማግኘት ትችላላችሁ 🥰
📖📖📖📖📖📖📖📖

📌እጣ ፈንታ
https://t.me/alahu_akber1/20


📌የእጁጅ ወመእጁጅ
https://t.me/alahu_akber1/155


📌SCHOOL LIFE(የት/ቤት ሒወት )
https://t.me/alahu_akber1/331


📌መራራ እዉነት
https://t.me/alahu_akber1/576


📌የቅዠት ህልም
https://t.me/alahu_akber1/1906


📌እውነተኛ ፍቅር
https://t.me/alahu_akber1/2382


📌መከረኛዉ ድንች ቤት
https://t.me/alahu_akber1/2716


📌ሳትዋጋ ንገስ (ሳትዋጊ ንገሽ)
https://t.me/alahu_akber1/3717


📌የሕይወት መሰናክል
https://t.me/alahu_akber1/5642


📌ነጫጭ ጥቁረቶች
https://t.me/alahu_akber1/6442


📌የሕይወት ምስቅልቅል
https://t.me/alahu_akber1/6525


📌ፍቅር አንዲህ ነው ወይ ??❓
https://t.me/alahu_akber1/7848


📌ጂኒው ኢፍሪት እና ነጋዴው
https://t.me/alahu_akber1/474

📌አደራዬ
https://t.me/alahu_akber1/15269


📑📑📑📑📑📑📑📑📑📑📑📑
Join እና share በማድረግ አግዙን 🥰
#share
@alahu_akber1
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
ውድ የ
#rio_islamic_post ቤተሰቦች. የምትፈልጉትን ታሪክ ሊንኩን በመንካት ማግኘት ትችላላችሁ 🥰
📖📖📖📖📖📖📖📖

📌እጣ ፈንታ
https://t.me/alahu_akber1/20


📌የእጁጅ ወመእጁጅ
https://t.me/alahu_akber1/155


📌SCHOOL LIFE(የት/ቤት ሒወት )
https://t.me/alahu_akber1/331


📌መራራ እዉነት
https://t.me/alahu_akber1/576


📌የቅዠት ህልም
https://t.me/alahu_akber1/1906


📌እውነተኛ ፍቅር
https://t.me/alahu_akber1/2382


📌መከረኛዉ ድንች ቤት
https://t.me/alahu_akber1/2716


📌ሳትዋጋ ንገስ (ሳትዋጊ ንገሽ)
https://t.me/alahu_akber1/3717


📌የሕይወት መሰናክል
https://t.me/alahu_akber1/5642


📌ነጫጭ ጥቁረቶች
https://t.me/alahu_akber1/6442


📌የሕይወት ምስቅልቅል
https://t.me/alahu_akber1/6525


📌ፍቅር አንዲህ ነው ወይ ??❓
https://t.me/alahu_akber1/7848


📌ጂኒው ኢፍሪት እና ነጋዴው
https://t.me/alahu_akber1/474

📌አደራዬ
https://t.me/alahu_akber1/15269


📑📑📑📑📑📑📑📑📑📑📑📑
Join እና share በማድረግ አግዙን 🥰
#share
@alahu_akber1