ነብዩሏህ_ኑህ (ዐ.ሰ)

ክፍል 7⃣

አላህ ሱብሀነሁ አተዓላ ከነዝያ ህዝቦች ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራቸው
ዘንድ ኑህ የተባሉ መልዕክተኛን አስነሳ።
ኑህም ህዝባቸውን ሰበሰቡ'ና፦" እኔ ለእናንተ ታማኝ መልዕክተኛ ነኝ፡፡
አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም፡፡
በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ(ክፍያ) አልጠይቃችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ
ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም" ብለው ህዝባቸውን ተጣሩ።
ይህን ሲሰሙ አስተባበሉት ምንም ሊያምኑለት አላቻሉም።እንዲያውም
ያፌዙበት ጀመር። ኑህ ዐ ሰ ያለመሰላቸት ዘወትር ጥሪም ያደርግላቸውም
ነበር።
የህዝቦቹ ማፊዝ እና ማላገጥ በበዛበትም ግዜ፦" ወገኖቼ ሆይ! ምንም
መሳሳት የለብኝም፡፡ ግን እኔ ከዓለማት ጌታ መልእክተኛ ነኝ፡፡
የጌታዬን መልክቶች አደርስላችኋለሁ፡፡ ለእናንተም እመክራችኋለሁ፡፡ ከአላህም
በኩል የማታውቁትን ዐውቃለሁ።" አላቸው።
የኑህን ዐ ሰ ንግግር በሰሙ ግዜ በጣም በመገረም፦" አንተ ኑህ!!! አንተ እኮ
እንደኛው ሰው ነህ እንዴት ነው መልዕክተኛ ነኝ ምትለው? በዛ ላይ ጥቂት
ተከታዮች አሉህ ሁሉም ግን ድሀ እና ኮሳሳ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ
ናቸው።
ደግሞም በሀብትም ሆነ በክብር ከኛ ጋር አትመጣጠኑም" ብለውም
አስተባበሉ።
ያም አላንስ ብሏቸው እርስ በርስ በሚፈፅሙት የሀውልት አምልኮ እንዲፀኑ
ይመካከሩም ጀመር።
ኑህም የህዝቡ ሁኔታ ተስፋ ሲያስቆርጠው በመለማመጥ መልኩ፦አላህን
ልትፈሩና ይታዘንላችሁም ዘንድ ከእናንተው (ጎሳ) በኾነ ሰው ላይ
እንዲያስጠነቅቃችሁ ከጌታችሁ ግሳጼ ቢመጣላችሁ ትደነቃላችሁን" እያለ
ቢያግባባቸውም ክህደታቸው ይበልጥ እየጨመረ እንጂ ምንም አይቀንስም
ነበር።
ምንም እንኳን ኑህ ዐ ሰ የህዝቡ ነገር ተስፋ ቢያስቆርጣቸውም ተልዕኮዋቸውን
በሚገባ በማድረስ ላይ ቀጥለዋል።
እናም ሁሌ ቀን እና ማታ ህዝባቸውን ስለ አላህ ሲያስታውሷቸው ህዝባቸው
የነቢያቸውን ዳዕዋ ከመስማት ጆሮዋቸውን መያዝ ጀመሩ።ጆሮዋቸውን ይዘው
መስማት እንቢ ሲሉ ኑህ ዐ ሰ በምልክት ይነግሯቸው ነበር። ኑህም በምልክት
ሲነግሯቸው ህዥቡ ግን አይኖቻቸውን በልብሶቻቸው ይሸፍኑ ነበር።
ምንም ተስፋ አልቆርጥ ብሎ መቆም መቀመጥ ሲከለክላቸው፦"ድሆች እና
ዝቅተኛ ሰዎች ያንተ ተከታይ ሆነው ሳለ እኛም ከነሱ ጋር እንድንከተልህ
ትሻለህን!!! ይልቁንስ እኛ እንድንከተልህ ከፈለግክ እነዚህን ተራ ሰዎች ከጎንህ
አርቃቸው።" አሉት።
ኑህ'ም ዐ ሰ፦"እነሱ የሚሰሩትን አላህ ነው ሚያውቀው። እኔ ላባርራቸው
አልችልም።
እንዴትስ ረዳቶቼን፣አክባሪዎቼን አባርር ትሉኛላችሁ!!! ቆይ ባባርራቸውስ እኔን
ከአላህ ማን ያተርፈኛል? አታስተውሉምን?" ብሎ ጠንከር አለባቸው።
ኑህ ዐ ሰ መልካም ነብይ ነበሩ። ሀብታም፣ድሀ ደከማ፣ጠንካራ፣ትልቅ፣ትንሽ
ስይሉ ለሁሉም በክብር የተላኩትን ዳዕዋ አደረሱ።
ምንም እንኳም ለ950 አመታት ዳዕዋ ቢያደርጉም ዳዕዋቸውን ከ80 በላይ
ሰው ሊቀበላቸው ባለመቻሉ ሁኔታው ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ለጌታቸው
ስሞታ ለማቅረብ ተገደዱ።
እንዲህም ሲሉ ለአላህ ነገሩት፦"ጌታዬ! ህዝቦቼ እኮ አስተባበሉኝ። በእኔና
በእነርሱም መካከል (ተገቢ) ፍርድን ፍረድ፡፡ አድነኝም፡፡ ከእኔ ጋር ያሉትንም
ምእምናን(አድን)፡፡"
ከዚህ በኋላ የኑህ ዐ ሰ የዳዕዋ ጥሪ ዛቻ አዘል መሆን ጀመረ።እነሱም ለኑህ ዐ
ሰ ዛች ግድ አልነበራቸውም ይልቁኑ፦"የምትዝትብንን አምጣ እውነተኛ
ከሆንክ" እያሉ ሲሳለቁበትም ጀመር።
ኑህም፦"ይህ እኮ በኔ ቁጥጥር ውስጥ አይደለም። ያ የአላህ ስልጣን ነው"
ይላቸዋል።
አሁን ነገሩ መቋጫው ተቃርቧል አላህም አስፈሪ ወህይ እንዲህ ሲል ወደ ኑህ
አወረደ፦" ከሕዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር (ወደፊት ከአሁን በኋላ)
አያምኑም፡፡ ይሠሩትም በነበሩት (ክህደት) አትዘን"
በመቀጠልም አላህ ኑህን ዐ ሰ የዘንባባ ችግኝ እንዲተክል አዘዘው።ያች ዛፍ
ለማፍራት ስትበቃ የአላህ ቅጣትም በነዚያ ህዝቦች ላይ እንደሚፈፀም ቃል
ገባለት።
የአላህ የተለምዶ እዝነቱ ይታወቀ ነው። ትልልቅ ሰዎች ባጠፉት ህፃናትን
አይቀጣም'ና ህፃናት የቅጣቱ ሰለባ እንዳይሆኑ ቅጣቱ ከመፈፀሙ ከ40
አመታት በፊት የሴቶቹ ማህፀን ፅንስ መሸከም እንዳይችል አደረገው።
ለ40 አመት ያህል ምንም አይነት ህፃን ሳይወለድ ቀረ።በዚያ ዘመም ኑህ ዐ ሰ
የታዘዘውን ዛፍ እንክብካቤ ሲያደርግ እነዚህ አመፀኛ ህዝቦች እንዲህ በማለት
ይሳለቁበት ነበር፦"አንተ ኑህ ነቢይ ነኝ እያልክ ዘራፍ ብለህ አላዋጣ ሲልህ
ወደ ግብርና ገባህ እንዴ!!!" ድንጋይም ይወረውሩባቸው ነበር።
የተተከለው ዛፍ 50 አመት ሲሞላው አላህም ለኑህ ዐ ሰ ወህይ በማውረድ
ዛፎችን እንዲቆጣቸው አዘዛቸው።

ክፍል8⃣ ኢንሽአላህ
ይ.......ቀ.......ጥ.......ላ.......ል፡፡

ሌሎች የነብያት ታሪክ'ና የተለያዩ ትምህርታዊ ፅሁፎች ለማግኘት ቻናላችንን(ግሩፓችንን)ይቀላቀሉን፡፡ እርስዎ ጋር እንዲቀመጥ ብቻ አይፍቀዱ፡ለሌሎችም ሸር(#share) አድርጉ፡፡
👇👇👇telegram👇👇👇
👉 https://t.me/alahu_akber1
ሸርብዩሏህ_ኑህ (ዐ,ሰ)

ክፍል8⃣

የተተከለው ዛፍ 50 አመት ሲሞላው አላህም ለኑህ ዐ ሰ ወህይ በማውረድ
ዛፎችን እንዲቆጣቸው አዘዛቸው።
ኑህም ዐ ሰ ዛፎቹን ከቆረጠ በኋላ አላህም ትልቅ መርከብ እንዲሰራ
አዘዘው።ጂብሪልም መርከብ እንዴት እንደሚሰራ ሊያሳየው ከሰባት ሰማያት
ወረደ።
አላህም እንዲህ ሲል ወህይ አወረደ፦
"የመርከቧ ርዝመት 1200 ክንድ
የጎን ስፋት 800 ክንድ
ከፍታው ደግሞ 80 ክንድ የሆነችን መርከብ ስራ"
በተንጣለለ አሸዋማ እና በረሀማ ቦታ ላይ ኑህ መርከቧን መስራት
ጀመሩ።ህዝቦቹም ከአጠገቡ ሲያልፉ፦"አንተ ኑህ ከነብይነት አናፂነት ይሻላል
ብለህ ነው?" እያሉ ያፌዙበታል።
ከፊሎቹ ደግሞ፦"አንተ ኑህ መርከብ እኮ ለባህር ነው ሚሰራው አንተ እልም
ያለ በረሀ ላይ ትሰራለህ እንዴ!" ይሏቸዋል።
ኑህም ለስለስ ባለ አንደበት፦"ዛሬ በኛ ላይ ብትሳለቁብን ነገ እኛም በእናንተ
ላይ እንሳለቅባችኋለን" ይላቸው ነበር።
የመርከቧ ስራ ከተጠናቀቀ በኋላ አላህ ኑህን ያመኑበትን ሁሉ መርከቧ ላይ
እንዲጭን እና ከእያንዳንዱ እንስሳት እና የዱር አራዊት አንድ ወንድ አንድ ሴት
በመርከቧ እንዲጭን አዘዘ።የምዕመናኑ ቁጥር 80 ብቻ ነበር።
ለኑህም ዐ ሰ ሁለት ሚስቶች ነበሩት አንደኛዋ ሙስሊም ስትሆን ሁለተኛዋ
አመፀኛ ካፊር ናት።እሱም ሙስሊሟን መርከብ ላይ ጫናት።
መርከቧ ውስጥ ሁሉም ቦታውን ከያዘ በኋላ ፀሀይ ብርሀኗን ተነጠቀች ምድር
በአስፈሪ ፅልመት ተዋጠች።
ሰማይም ዶፍ ዝናብን ማንቧቧት ጀመረ...በከርሰ ምድርም ታምቆ የነበረው
ውሀ ምድሪቱን እየሰነጠቀ ለጉድ መፍለቅ ጀመረ።
ከሰማይ የወረደው ውሀ እና ከምድር የወጣው ውሀ ሲገናኝ ምድር ከአቅሟ
በላይ መጥለቅለቅ ጀመረች።ያን ግዜ መርከቧ ቀስ እያለች መንሳፈፍ
ጀመረች።
ውሀው በየሰዐቱ እየጨመረ ነው አጋጣሚ ኑህ ዐ ሰ ሁኔታውን ለማጣራት ወደ
ምድር ሲመለከቱ የአብራካቸው ክፋይ የሆነው ልጃቸው አንዴ ሲወድቅ አንዴ
ሲነሳ ውሀው ሲያንከራትተው ተመለከቱት።
እንዲህም ሲሉ ተጣሩ፦"ልጄ ና ከኛ ጋር ተሳፈር ከካሀዲያን ህዝብም አትሁን"
ልጁ ግን በትዕቢት የተሞላ ነው'ና፦"ከውሀው ይጠብቀኝ ዘንድ ወደ ተራራ
እወጣለሁ" ብሎ መለሰላቸው።
እሳቸውም፦" ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም (እርሱ) ያዘነለት
ካልሆነ በቀር" ብለው ንግግራቸውን ሳይጨርሱ እንደ ትልቅ ተራራ ያለ ማዕበል
መጣና ልጁን ጠራርጎ ወሰደው።
ኑህም ልጄ እያሉ ወደ አላህ ሲጮሁ አላህም፦" ኑሕ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ
አይደለም፤ እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር
አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ" አለው።
ውሀውም ምድርን ለ40 ቀናት ያህል ካጥለቀለቀ በኋላ ምንም አይነት ነፍስ
ያለው ነገር ከምድረ ገፅ ጠፋ።
ያን ግዜ አላህም ምድርን፦"ምድር ሆይ! ውሃሽን ዋጪ፡፡ ሰማይም ሆይ
(ዝናብሽን) ያዢ፡፡" ብሎ ምድርን ከመጥለቅለቅ አስቆመ።
ምድር ትንሽ ጠፈፍ ማለት ስትጀመር ኑህን እና ተከታዮቹን የተሸከመችው
መርከብ በሰላም ጁዲይ በተባለ ተራራ ላይ አረፈች።
አላህም የተቀረውን ውሀ ወደ ውቅያኖስ እንዲፈስ አደረገው።ያን ግዜ ኑህ እና
ተከታዮቹ ከመርከቢቷ ወርደው የያዟቸውንም እንስሳት አውርደው
ለቀቋቸው።በምድርም እንደ አዲስ ግንባታ ጀመሩ።የተለያዩ ዛፎችንና
አዝርዕትን መትከልም ጀመሩ።
ምእመናኑ'ም ምድር ላይም በመበታተን የተለያዩ ከተማዎችን በመመስረት
ብዙ ልጆችን ወልደው ምድርን እንደ አዲስ መሙላት ጀመሩ።
በመጨረሻም አላህ ኑህን ዐ ሰ፦"ኑህ ሆይ! እኔ ፍጥረታትን የፈጠርኩት
እንዲገዙኝ ነው።እኔ ያዘዝኳቸውንም እንዲታዘዙኝ ነው።ነገር ግን አመፁኝ፤ከኔ
ሌላ የሆነንም አካል ጌታ አድርገው ያዙ። ያን ግዜ ቁጣዬም እነሱ ላይ ተፈፃሚ
ሆነ በውሀም አጥለቀለቅኳቸው" ብሎ ወህይ አወረደለት።
አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ የ ኑህን (ዐ ሰ) ህዝብ በውሀ ካጥለቀለቀ በኋላ
በምድር ላይ ከ ኑህ(ዐ ሰ) ጋር አብረው ከዳኑት ምዕመናን ውጭ ምንም
አይነት የሰው ልጅ አልቀረም ነበር።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኑህ ዐ ሰ እና በዘመኑ የነበሩት ሰዎች ከሞቱ በኋላ አንዱ
አንዱን ሲተካ ምድር ዳግም በሰዎች ትሞላ ጀመር።
ያ ዘመን ካለፈ በኋላ የነበሩ ህዝቦችም ማንም አምልኮ ከምያውቀው በላይ
ጣኦትን ማምለክ ተያያዙት።የህዝቡ መለያ ስማቸውም (ዓድ) ይባላል።
በመጀመርያ የዓድን ህዝቦች ላስተዋውቃችሁ...
የዓድ ህዝቦች በዐረቢያ ምድር በየመን ግዛት አህቃፍ በሚባል አካባቢ ኢረም
በተባለች ከተማ የሚኖሩ በጣም ትላልቅ ቁመና ያላቸው ህዝቦች ሲሆኑ፤አላህ
ስፍር ቁጥር የሌለውን የፀጋ አይነት ያትረፈረፈባቸው ህዝቦች ናቸው።
ከፀጋዎቻቸውም የሚኖሩበት ምድር በጣም ለቡቃያ አመቺ እና ለም አፈር
ያለበት አካባቢ ነው።
ሰውነታቸውም በጣም ግዙፎች እና ረጃጅሞችም ነበሩ።
ከሰውነታቸው መግዘፍ የተነሳ አንድን የቴምር ዘንባባ በሁለት ጣታቸው ይነቅሉ
ነበር።(የተምር ዛፎች ምን ያህል ግዙፍ እንደሆኑ ዐረብ ሀገር ያላችሁ ውዶች
ታውቁታላችሁ)
ነገር ግን አላህ ለዋለላቸው እንዲህ አይነት ኒዕማ ምላሻቸው ምስጋና ሳይሆን
ድንበር ያለፈ አመፅ እና መኩራራት ነበር።
የኑህ ህዝቦች ያደርጉት የነበረውን የጣኦት አምልኮ አሟሙቀው ጀመሩት።ያም
አላንስ ብሏቸው ምድርን በተለያዩ የወንጀል አይነቶች ይሞሏትም ጀመር።
ነገር ግን ለቅጣት የማይቸኩለው አላህ በእዝነት አዘል ጥበቡ ከመጥፎ
ከልክሎ ወደ መልካም የሚመራቸውን (ሁድ) የተባለውን መልዕክተኛ
ከመሀከላቸው ላከላቸው።

ክፍል9⃣የ'ሁድ (ዐ,ሰ) ታሪክ በአላህ ፍቃድ👇
ይ.......ቀ.......ጥ.......ላ........ል፡፡

ሌሎች የነብያት ታሪክ'ና የተለያዩ ትምህርታዊ ፅሁፎች ለማግኘት ቻናላችንን(ግሩፓችንን)ይቀላቀሉን፡፡ እርስዎ ጋር እንዲቀመጥ ብቻ አይፍቀዱ፡ለሌሎችም ሼር (#share) አድርጉ፡፡
👇👇👇telegram👇👇👇
👉 https://t.me/alahu_akber1
ሆን
አንዱ ደሞ የንጉስ ጠጅ ጠማቂ ነው።)
ለዩሱፍም እንዲህ ሲል አንደኛው ጠየቀው፦" እኔ በህልሜ የወይን ጠጅን
ስጠምቅ አየሁ" ሁለተኛውም፡-"እኔ በራሴ ላይ ዳቦ ተሸክሜ ከእሱ በራሪ
(አሞራ) ስትበላ አየሁ፡፡ ፍቹን ንገረን፡፡ እኛ ከአሳማሪዎች ሆነህ እናይሃለን'ና"
በማለት ጠየቀው።......

ክፍል 2⃣0⃣ እንሽአሏህ
ይ......ቀ.....ጥ....ላ.....ል፡፡
✍Adem Ahmed

ሌሎች የነብያት፣ የሰሃቦች ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ
እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ
አይፍቀዱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ።

👉 https://t.me/alahu_akber1
#ነብዩሏህ_ዩሱፍ (ዐለይሂ ሰላም)

ክፍል2⃣1⃣

በዚያ መሀል በከንዓን ይኖሩ የነበሩ የዩሱፍ ቤተሰቦችም የድርቁ ሰለባ ነበሩ'ና 10 ወንድሞቹ እህል ፍለጋ የግብፅን ምድር
ረግጠው በማያውቁት ወንድማቸው መጋዘን ለእህል ተሰለፉ።
ድርቁን ተከትሎ ከተለያዩ ሀገራት በድርቅ የተመቱ እህል ሸማቾች ወደ ግብፅ
ምድርም ይተሙ ጀመር።በዚያ መሀል በከንዓን ይኖሩ የነበሩ የዩሱፍ
ቤተሰቦችም የድርቁ ሰለባ ነበሩ'ና 10 ወንድሞቹ እህል ፍለጋ የግብፅን ምድር
ረግጠው በማያውቁት የወንድማቸው መጋዘን ለእህል ተሰለፉ።
በግዜው ከመንግስት መጋዘን ሁሉም እህል ሲሸምት ስሙን እና የመጣበትን
ሀገር እያስመዘገበ ነበር የሚሸምተው።እነዚህም ወንድሞቹ ስማቸውን
እስመዝግበው እህላቸውን ከመረከባቸው በፊት ዩሱፍ የከንዓን ሰዎች
መጥተዋል የሚል ወሬ ሰምቶ ሊያጣራ ሲሄድ ወንድሞቹን ተመለከታቸው።
ምንም እንኳን እሱ ቢያውቃቸውም እነሱ ግን በፍፁም ሊያውቁት
አልቻሉም።ግን ዝም ብለው በግምት፦" ይህ ፊት አዲስ አልሆነብኝም
ይባባላሉ" እርስ በርስ....
ዩሱፍም ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ ቁጥር ስፍር ከሌለው ሰልፈኛ መሀል ለ40
አመት የተለያያቸውን ወንድሞቹን የሰሩበትን ተንኮል ወደ ጎን አድርጎ በናፍቆት
ተሸንፎ ስለማንነቱ ምንም ሳይነግራቸው ወደሚኖርበት ቤተ መንግስት ይዟቸው
ሄድ።
ይህችን ሌሊትም እሱ ጋር አሳልፈው በነጋታው እንደሚሄዱ ካሳመናቸው በኋላ
በጥሩ መስተንግዶ እራት አብልቷቸው ያዕቁብ ስለተባለው ነቢይ መጠየቅ
ጀመረ።በህይወት እንዳለ እና ዩሱፍ በተባለው ልጁ ሀዘን ምክንያት በጣሙን
እንደተጎዳ ነገሩት።ዩሱፍ ይህን ሁሉ ሲሰማ ሆድ እየባሰው ከእንባው ጋር
ትንቅንቅ ቢገጥምም ይህን ሀዘኑን ግን ለወንድሞቹ ግልፅ ሊያደርግ
አልፈለገም።ያውቁኛል ብሎ ሰግቶ.....
በነጋታው ዩሱፍ አገልጋዮቹን ጠርቶ፦"ለእህሉ የከፈሉትን ገንዘብ
በየከረጢታቸው ውስጥ ደብቁትና ሳያውቁ ስጧቸው" ብሎ አዘዘ። ዩሱፍ
ባዘዘውም መልኩ የከፈሉት ገንዘብ ተመልሶ በየከረጢታቸው ተጨመረላቸው።
በመጨረሻም ሲሸኛቻው፦"በሚቀጥለው ዙር ስትመጡ ከንዓን ትታችሁት
የመጣችሁትን ትንሹን ወንድማችሁን ይዛችሁ ኑ። እሱን ካላመጣችሁት ግን
ምንም አይነት እህል አንሰፍርላችሁም" ብሎ ሸኛቸው።
እነሱም እንደሚሞክሩ ቃል ገብተውለት ጉዞ ወደ ከንዓን ጀመሩ።ረጅም
ተጉዘው ከንዓንም ሲደርሱም በግብፅ ከተማ የገጠማቸውን ሁሉ ለአባታቸው
ያዕቁብ ተረኩለት'ና በቀጣይ ዙር ግን ታናሽ ወንድማቸውን ቢንያሚንን
ካላመጡ ምንም አይነት ስፍር እንደማይሰፈርላቸው ነገሩት።
አባታቸው ያዕቁብ ግን ልጆቹ ከዚህ በፊት በልጁ ዩሱፍ የፈፀሙትን በማስታወስ
ዳግም ልጁን ቢንያሚንን ለነሱ አምኖ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም
ነበር።ይሁን እንጂ ያዕቁብ ምንም እንኳን ውድ ልጁን ቢንያሚንን ከአጠገቡ
ማራቅ ቢከብደውም ከፊትለፊቱ የተደቀነው ድርቅ እና ቸነፈር ቢንያሚንን ወደ
ግብፅ ለመላክ አስገድዶታል።
ከመላኩ በፊትም ያዕቁብ ልጆቹን ሰብስቦ፦"ካልተከበባችሁ በስተቀር እርሱን
(ቢንያሚንን) በእርግጥ
የምታመጡልኝ ለመሆናችሁ ከአላህ የሆነን ቃል
ኪዳን መተማመኛ እስከምትሰጡኝ ድረስ ከናንተ
ጋር ፈፅሞ አልልከውም" አላቸው።
መተማመኛቸውንም ቃል ኪዳን በሰጡት ጊዜ ፦"አላህ
በምንለው ሁሉ ላይ ምስክር ነው" አላቸው።
በገቡት ቃል ኪዳን መሰረትም ቢንያሚንን ከአባታቸው እቅፍ አውጥተው
ከከንዓን ምድር ነዋሪዎች ጋር ጉዞ ወደ ግብፅ ከመጀመራቸው በፊትያዕቁብ
ልጆቹን ነጥሎ፦" ልጆቼ ሆይ! ባንድ በር አትግቡ፤ ግን
በተለያየ በሮች ግቡ፤ ከአላህም (ፍርድ)
በምንም አልጠቅማችሁም፤ (አልመልስላችሁም)፤
ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም፤ በርሱ ላይ
ተመካሁ፤ ተመኪዎችም ሁሉ በርሱ ብቻ ይመኩ" ብሎ መከራቸው።
በከንዓን እና በግብፅ መሀከል ያሉትን በረሃማ እና አሸዋማ መንገዶችን
ካቋረጡ በኋላ የዩሱፍን ታናሽ ወንድም ይዘው ቤተ መንግስት ገቡ።ዩሱፍም
ከመጀመርያው በተሻለ መልኩ ካስተናገዳቸው በኋላ ታናሽ ወንድሙን ለግል
አውጥቶ፦"እነሆ እኔ ወንድምህ ነኝ ይሠሩት
በነበሩትም ሁሉ አትቆጭ" ብሎት ነገ እሱን ግብፅ ሊያስቀረው የንጉስ ዋንጫ
በሱ ከረጡት እንደሚሸጉጥበትም ጨምሮ ነግሮት ለአዳር ወንድሞቹ ጋ
አቀላቀለው።
ጠዋትም ለጉዞ በተዘጋጁ ግዜ ዩሱፍ እቃዎቻቸውን አስጭኖላቸው
ሸኛቸው።ብዙም ሳይርቁም ዩሱፍ እና ወታደሮቹ ከአንድ ኮረብታ ላይ ሆነው፦"
እናንተ ባለ ግመሎች ሆይ! እናንተ በርግጥ ሌቦች ናችሁ" በማለት
ተጣሯቸው።
እነሱም ዞረው፦" ምንድነው የጠፋችሁ?" አሉ።
ዩሱፍም፦" ፦ የንጉሡ መስፈሪያ ጠፍቶናል፤ እርሱንም ላመጣ ሰው የግመል
ጭነት ሽልማት አለው፤ እኔም በርሱ ተያዥ
ነኝ" አላቸው።
እነሱም፦" በአላህ እንምላለን በምድር ላይ ለማጥፋት
እንዳልመጣን በእርግጥ ዐውቃችኋል፤ ሌቦችም
አልነበርንም" አሉት።
ዩሱፍም፦" ውሸታሞች ብትሆኑ ቅጣቱ ምንድነው?" አላቸው።
እነሱም፦"ቅጣቱ (በያዕቆብ ሕግ) ዕቃው በጓዙ ውስጥ
የተገኘበት ሰው (ራሱን አገልጋይ አድርጎ መወሰድ) ነው፤ እርሱም
ቅጣቱ ነው። እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን" ብለው መለሱለት።
(ፍተሻውን) ከወንድሙም ዕቃ በፊት
በዕቃዎቻቸው ጀመረ፤ ከዚያም (ዋንጫይቱን)
ከወንድሙ ዕቃ ውስጥ አወጣት።ሁሉም ደነገጡ ሚሉት ጠፋባቸው በዚህ
አጋጣሚ እራሳቸውን ለማዳን፦"እሱ ቢሰርቅ ምንም አይደንቅም አንድ ታላቅ
ወንድሙም እንዲህ ይሰርቅ ነበር" አሉ።
ዩሱፍም በውስጡ፦"እናንተ ሥራችሁ የከፋ
ነው፤ አላህም የምትሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነው" አለ።
ከዚያም እነሱ ራሳቸው በተስማሙት መሰረት እቃውን የሰረቀውን ቢንያሚንን
ዩሱፍ እና ወታደሮቹ ይዘውት ሊሄዱ ሲሉ፦"አንተ የተከበርከው ሆይ! ፦ ለርሱ
(ለቢንያሚን) በእርግጥ ትልቅ
ሽማግሌ አባት አለው፤ ስለዚህ በርሱ ፋንታ
አንደኛችንን ያዝ፤( ይህን ከፈፀምክ) እኛ ከመልካም ሠሪዎች ሆነህ
እናይሃለንና" አሉት።
ዩሱፍም፦"ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ካገኘነው ሰው ሌላን ሰው ከመያዝ በአላህ
እንጠበቃለን፤ እኛ ያን ከፈፀምን በእርግጥ በዳዮች ነን" አለ።
ዩሱፍንም ለምነው ለምነው ተስፋ ሲቆርጡ ወደ ጎን ነጠል ብለው መመካከር
ጀመሩ።በመሀልም ታላቅ ወንድማቸው፦" አባታችሁ በናንተ ላይ
ከአላህ የሆነን መታመኛ ቃል ኪዳን በእርግጥ
የያዘባችሁ መሆኑን ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ
ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ
ለኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለኔ
እስከሚፈርድልኝ ድረስ የግብፅን ምድር
አልለይም፤ እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው።
ወደ አባታችሁ፣ ተመለሱ፤ እንዲህ በሉትም፦ አባታችን
ሆይ! ልጅህ ሰረቀ ባወቅነውም ነገር እንጂ
አልመሰከርንም፤ ሩቁንም ነገር (ምስጢሩን)
ዐዋቂዎች አልነበርንም፤
ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም
በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ፤
እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን በሉ" ብሏቸው እነሱን ትቶ ወደ ከተማይቱ
ገባ።
እነሱም ምንም አማራጭ አልነበራቸውምና የጫኑትን እህል ጭነው ወደ
ከንዓን ተጓዙ።ልክ ከንዓን ሲደርሱ አባታቸው መንገድ ላይ እየጠበቃቸው
ነበር።ሁሉንም ሰላም ብሎ የልጁ ቢንያሚንን መምጣት በጉጉት ሲጠብቅ
ቢንየሚን የውሀ ሽታ ሆነበት።ልጄስ ብሎ ሲጠይቃቸውም የሆነውን ሁሉ
ነገሩት።....
(አባታቸው ቢንያምን ትተው በመምጣታቸው ምን ያደርጋቸው ይመስላችሇል)፡፡

ክፍል 2⃣2⃣ ኢንሽአላህ
ይ........ቀ.. ....ጥ......ላ.....ል፡፡
👉 https://t.me/alahu_akber1
🔴 ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ነገ ጀምረዋል

ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ሰላምና እዝነት በታላቁ ነብይ በሙሀመድ በባልደረቦቻቸው እና በቤተሰቦቻቻው ሁሉ ላይ ይሁን፡፡

ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሀጅ ወር ዙልሂጃ ነው። ከቀናት ሁሉ አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው። እንደዉም ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው እነኝህ ቀናት ናቸው። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦

‎عن جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللهِ رَضِيَ الله عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى الله عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّةِ". صحيح الجامع ، رقم 1133

ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል «ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ ቀናት ናቸው። ማለትም አስሩ የዙልሂጃ ቀናት» አልባኒ ሰሂሁል ጃሚዕ 1133 ላይ አስፍረውታል

‎عن ابن ؚباس رضي الله عنهما، عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: "ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله منه في هذه الأيام العشر. قالوا ولا الجهاد في سبيل الله !! قال : ولا الجهاد في سبيل الله، إلا رجل ؎ع؏ بنفسه وماله ولم يرجع من ذلك بشيء" أخرجه البخاري

ከኢብኑ ዓባስ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:‐
«በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች በበለጠ ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤ “በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?” ተባሉ። እርሳቸውም፤ “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም” አሉ።» ቡኻሪ ዘግበውታል

በነዚህ ቀናቶች ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ የዒባዳ አይነቶች መካከል:‐

1. ጾም፦ ጾም ከስራዎች ሁሉ በላጭ ነውና በእነዚህ ቀናት መጾም እጅግ የተወደደ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ዘጠኙን የዙልሂጃ ቀናት ይጾሙ እንደነበር ተዘግቧል። (አስረኛው ቀን ግን ዒድ ስለሆነ አይጾምም)

2. ዚክሮችን ማብዛት፦ አላህን ማመስገን (አልሀምዱሊላህ) ፣ ተክቢር፣ ተስቢህ(ሱብሀነላህ) እና ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢለላህ)፤ ኢባዳዉን ለማስታወስና የአላህን ስም ከፍ ለማድረግ በተለያዩ አጋጣሚዎች ድምጽን ከፍ አድርጎ እነዚህን ዚክሮች ማድረግ ይወደዳል።

‎عن ؚبد الله بن عمر رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم قال : "ما من أيام أعظم عند الله ولا أحب إليه العمل فيهن من هذه الأيام العشر فأك؍عوا فيهن من التهليل والتكبير والتحميد" أخرجه احمد 7/224 وصحّح إسناده أحمد شاكع

ዓብዱላህ ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ እንዲህ ብለዋል፤

«ከነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል አህመድ ሻኪርም ሰሂህነቱን አረጋግጠዋል።

ከተክቢር አደራረግ መካከል፤
‎الله أكبع ، الله أكبع لا إله إلا الله ، والله أكبع ولله الحمد
“አላሁ አክበር፤ አላሁ አክበር፤ ላ ኢላሀ ኢለላህ ወላሁ አክበር ወሊላሂልሀምድ” የሚለው ዋነኛው ሲሆን ሌሎችም ይዘቶች አሉት።

በእነዚህ ቀናት ውስጥ ሊደረግ የሚገባው ይህ ተክቢር ብዙ ሰዎች ስለማይፈጽሙት እየተረሱ ካሉ ሱናዎች መካከል ነው። ሰዎችን ለማስታወስ እና ሱናን ህያው ለማድረግ ድምጽን ከፍ አድርጎ ተክቢር ማድረግ ያስፈልጋል። ዓብዱላህ ኢብኑ ኡመር እና አቡሁረይራህ በነዚህ አስር ቀናት ገበያ ወጥተው ተክቢራ ሲያደርጉ ሰዎችም እያስታወሱ ተክቢራ ያደርጉ እንደነበር ተዘግቧል። ይህም፤ ሁሉም ሰው የራሱን ዚክር ያደርጋል ማለት ነው እንጂ ሰዎች እየተሰባሰቡ በአንድ ድምጽ ተክቢራ ያድርጉ ማለት አይደለም። ይህ መረጃ ያልተገኘለት የተሳሳተ አፈፃፀም ነው።

3. ሐጅና ዑምራ፦ በነዚህ ቀናት ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች መካከል ሐጅ ማድረግ ይገኝበታል፤ በነዚህ አስር ቀናት የሐጅ ዒባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መልኩ ከፈጸመው በአላህ ፍቃድ ከተከታዩ የአላህ መልዕክተኛ ብስራት ድርሻ ይኖረዋል፤

‎عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعته يقول: "الحج المبرور ليس له ؏زاإ إلا الجنة" متفق عليه.
ከአቡ ሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «ከወንጀል የራቀና ተቀባይነት ያለው ሐጅ (አል-ሐጅ አል-መብሩር) ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡»
ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል

4. ኡድሂያ፦ በነዚህ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደአላህ መቃረብ ነው። የሚከተሉት ነጥቦች አጠር ያለ ግንዘቤን ይሰጣሉ፤

- ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ ሱናዎች መካከል ነው። የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረጉ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው።

- ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍራቻ (ተቅዋ) ነው።

- ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል።

- ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት የዒድ ሰላት ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሶስተኛው ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ኡድሂያን ማረድ ይቻላል።

- ግመል፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየል
ለኡድሂያ ይታረዱሉ።

- የአላህ መልዕክተኛ እንከን ያለባቸውን እንስሳት እንዳናርድ ከልክለዋል። አንድ አይኑ የታወረ፣ ስብራት ያለበት፣ የከሳና የደከመ፣ የታመመ እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም።

- ኡድሂያን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን ወይፈን ወይም በሬ መጋርትም ይቻላል።

- አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን በህይወት ለሌሉ ለቤተሰቦቹ አስቦ ሊያርድ ይችላል።

- ኡድሂያውን ለራሱ፣ ለስጦታ እና ለሰደቃ አድርጎ መከፋፈሉ ሱና ነው። ይህ ማለት ግን እንደ አስፈላጊነቱ ለሶስቱም ያውለዋል ማለት እንጂ ሶስት እኩል ቦታዎች ይከፋፍለዋል ማለት አይደለም።

- በዒድ ቀን ኡድሂያን ለማረድ አስቦ የዙልሂጃ ወር ከገባ ጥፍሩንና ጸጉሩን አይቆርጥም። ቆዳውንም አይቀርፍም። ይህ በሀጅ ላይ ያሉ ሰዎችን የሚመሳሰልበት ነብያዊ ትዕዛዝ ነው። ሆኖም ይህ የሚመለከተው የሚያርደዉን ሰው ብቻ ነው። እያወቀ ጥፍሩን ወይም ጸጉሩን የቆረጠ ወንጀል ፈጽሟልና ወደ አላህ በተውበት ሊመለስ ይገባዋል፤ ኡድሂያው ግን አይበላሽም።

የመልካም ስራ በሮች ብዙ ናቸውና የቻልነዉን ሁሉ በመፈጸም ወደ አላህ መቃረብ ይገባል፤ የታሰረን ወይም የታመመን ሰው መጠየቅ፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ሰደቃ ማብዛት፣ ሱና ሰላቶችን ማብዛት፣ ቁርዓን መቅራት፣ ዚክር ማብዛት፣ ዱዓን ማብዛት…ወዘተ ያስፈልጋል።

አላህ በነዚህ ወርቃማ ጊዜያት ከሚጠቀሙና አላህ ዘንድ መልካም ምንዳን ከሚያገኙ ጠንካራና ብልህ የአላህ ባሮች ያድርገን።

#share
https://t.me/alahu_akber1
ቁርአንን ስትቀራ እርሱ ከፊቷ ተቀምጦ ያዳምጣታል። ድምጿ ውብ ነው ጆሮውን ሰርስራ ገብታ በጥዑም ዜማዋ የደረቀውን ልቡን ታረሰርሰው ይዛለች።

فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ

ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ ...

የሚለው የቁርአን አንቀፅ ጋር ስትደርስ ድምጿን ዝቅ አደረገች። ፈገግ አለና ወደኋላው ዞሮ ዓይን ዓይኗን እያየ "አንቺ ለኔ ሁሉንም ነሽ" አላት ፍልቅልቅ እያለች ጥዑም የቁርአን ዜማዋን ማነብነቧን ቀጠለች።

ያረብ ለኛም እንዲ ያማረ ትዳር ወፍቀን 🤲🤲🤲
አሚን በሉ 😊

#share
t.me/alahu_akber1
ሚስት ከባሏ ጋ እየተጨቃጨቀች ነበር።
ዝምበይ ቢላት ምን ተደርጎ ነው ዝም የምለው ትለዋለች። ዝም
ካላልሽማ አሳይሻለሁ ይልና ለመምታት ያስባል። ባይሆን ሚስት ብልህ
ነበረችና
((*ሸይኽ ዑሰይሚን ሴትን ልጅ መምታት ወንድነት አይደለም ))ብለዋል
።ሀዲስም ከፈለግክ ነብዩ ፍፁም ሴቶችን አልተማቱም ነበር የሚል
ሶሂህ ሀዲስ አለ ትለዋለች። ያዘጋጀውን መግረፊያ ይጥልላታል።
ከዚያም እሷ ቀስ አድርጋ ሆዱን 👊👊👊በቦክስ ትመታዋለች። መልሶ ይጮሀል።😟😟😟
ሚስት ፈጠን ብላ ሸይኽ ዑሰይሚን ሴትን ልጅ መምታትን ነው
ያወገዙት። ወንድን መምታት ነውር ነው አላሉም። አልወቀሱም ብላ
አስረዳችው።
በፀብ የተሞላው ቤት በሳቅ ተቀየረ።
ሴት ብልህና ተናናሽ ሁና ስትገኝ ቤቱ ሰላም ይሰፍንበታል።

አላህ እንደዚህ አይነት ትዳር ይወፍቀን።
ለበለጠ ኢስላማዊ መረጃ እና ጠቃሚ እዉቀት በዚህ ይከተሉን
👇👇👇
https://t.me/alahu_akber1
🎁〰〰〰እዉነተኛ ታሪክ〰〰〰🎁
 
የታሪኩ ርዕስ
😢 #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ??❓
      🌀 #Part 1⃣7⃣

✍ ፀሀፊ #አሚር_ሰይድ

............የደሀ ልጅ ፍቅር.............
ምሽት አካባቢ ተጆራ ደረስን ከተማው ጫፍ ላይ ከመኪና ስንወርድ የከተማይቷ ወጣቶች ተደራጅተዉ  መዝረፍ የለመዱት ልክ እንደኮንትሮ ባንድ እቃ ሊሻሙን እየሮጠው መጡ ...... የቻለ እሩጦ ያመልጣል ያልቻለ ያለውን ይዘረፋል

    ሲፈትሹ ደግሞ ብር ይዘዉ ይሆናል ብለዉ ስለሚያስቡ ሹሪ አስወልቀዉ  ፓንት አይቀራቸውም ....ሁላችንም በሩጫ ብትንትናችንን ወጣ ወደ አገኘንበት አቅጣጫ በመሮጥ ግማሹ መስጊድ ግማሹ በተያየ ቦታ ሄደ
   áŠĽáŠ”ም  ከከተማይቷ የሚገኝ አንድ መስጅድ ገብቼ አመለጥኩ ....
መስጊዱ ሁኜ  አንድ ሰዉየ ተባበረኝ ብየ .... ለደላላው አስደወልኩበት ያለሁበትን ቦታ የመስጊዱን ስም ሰዎቹን ጠይቄ ነገርኩት.....
.
     ደላላዉ ክፍያው ስላላለቀ ለልሹ ሲል ሌላ መኪና ተኮናትቶ በያለንበት እየመጣ ሁላችንንም ሰበሰበን፡፡ የመጨረሻ መዳረሻ ወደሆነችው ሃዩ ከተማ ጉዙ ጀመርን ብዙ ከተጓዝን በኋላ ሃዩ ደረስን፡፡
  
      ሀዩ ከተማ ስንወርድ እኛም እናሳዝናለን ግን ከእኛ የባሰባቸው ብዙ ታያለህ ግማሹ ደላላው ብሩን ተቀብሎ ከድቶት ሲያለቅሱ... ግማሹ እዚያ ድረስ በእግሩ እየተጓዘ ደርሰዉ ደክመዉ የተቀመጡ ...ግማሹ ምግብ ስጡኝ እያለ የሚለምን አለ ግማሹ በርሀብ የተነሳ መንቀሳቀስ መራመድ የማይችል ብዙ ነገር አየሁ፡፡ ... ብቻ ስደት አኡዙቢላሂ አስፈሪ ነዉ  የዱኒያ ጀሀነም በስደት ወደ ዉጭ ሀገር ለመሄድ መሞከር ነዉ
   አላህ እንዲህ ይላል  ወላቱልቁ አንፉሰኩም ኢለተህሉካት >>>>>>ራሳችሁን ወደሚጎዳችሁ መጥፎ ነገር ላይ አትጣሉት <<<< ይለናል 
     በስደት ጉዞየ ላይ ተወቃሽ ያደረኩት በባህር ሂደው ውጭ ትንሽ ተቀምጠውና ሰርተው ሲመለሹ እያነጀቡና ስለስደት ጥሩ ጎን ብቻ የሚለፈልፉ ሰወችን ነው፡፡  ስደት በባህር መሄድ በጣም ስቃይ ሞት እንዳለው ለምን ይሸፋፍኑታል??? ስደት ማለት ስድ ነው ያንን ሒወት አይቶ መኖር ለልሹ በጣም አስፈሪ ነዉ፡፡
.

    ....እዚያው ሃዩ ከተማ አደርን በማግስቱ ወደባህሩ ዳርቻ ለመሄድ ከከተማው ወጣ ብለን መኪና መጠበቅ ነበረብንና...... በእግራችን ወጣን
........የሆነ ቦታላይ ደረስን የተሰበሰቡ ሰወች አገኝን ምንድናችሁ ??? ምን ሁናችሁ ነዉ የተሰበሰባችሁት??? አልናቸው
 .....እነሱም  ደላላወቻችን አስቀምጠውን ነው፡፡ አሉን.... ግማሹ ከተቀመጠ ወር ሆኖታል ከዚያም በላይ አለ እንዳይሞቱ የተወሰነ ምግብ ይሰጣቸዋል እንዳይሄዱ መሳሪያ በያዙ ሰወች ይጠበቃሉ ከዚያ መሀል ራቡ አስክሮት የሚጮህ አለ ፡፡ አንዳንዱ እርሀቡን መቆጣጠር አቅቶት የሚንፈራፈር አለ....አንዳንዱ ደግሞ እንግሊዝኛም ይቀላቅላል፡  
   እኔ አረበኛ እና እንግሊዘኛ ቋንቋ አዉቃለሁ ሲያወሩ አሁን ያሉበትን ቦታ ያሳዝናል፡፡ ያለቦታየ መወድቄን አወኩት ተስፋ ተሟጠጠብኝ....   ብቻ ሀበሻ ስንባል በየሔድንበት ችግር መከራ እናሳልፋለን...እናሳዝናለን፡፡
      የኔ ደላላ በሰዉ ነዉ ያገኘሁት ከአሉት ደላላዎች የተሻለ ስለነበረ ወደባህሩ ዳርቻ ሊወስደን መኪና ላይ ጫነን ባህሩ ዳርቻ ለመድረስ ብዙ ሰአት ያስኬዳል ...በመኪና እየሄድኩ  በእግሬ ቢሆን ምን ልሆን ነበር ????እያልኩኝ አልሃምዱሊላህ እላለሁ
.......ደላላው የሆነ ቦታ ላይ ሽንት ለመሽናት አቆመ አብሬ ወረድኩ፡፡ አካባቢው አንዳንድ የበረሀ ዛፍ ቅጠል የሌለው ታያለህ ፡፡ እናም የሆነ ግንድ ላይ ዛፉን ተገድፎ የተቀመጠ ሰው አለ ፡፡ ደላላውን ያ ሰው ምንድነው??? አልኩት
....,,ደላላዉም  ያማ ብር አንሶት  በእግሬ ወደ ባህሩ እደርሳለሁ ብሎ ሲመጣ ረሃብና ውሃ ጥም ገድሎት የሚቀብረዉ አጥቶ ነው አለኝ ፡፡ በጣም አስፈሪ ነበር  እኔም  እንዴት ትተነው እንሄዳለን እንቅበረዉ እንጂ የሞተን ሰዉ ካየህ መቅበር ግዴታ ነዉ እኮ??አልኩት
......... ዳላላዉም አይ አንተ ልጅ  እናንሳው እንቅበረዉ ካልንማ ወደፊት ስንሄድ ብዙ የሞቱ ሰወች እናገኛለን አለኝ..... ያለህ አማራጭ ምን ብታዝን ከንደዚህ አይነት ጭንቀት ራስህን ማውጣት ነው...እነሱን እያየህ ጌታህን እኔን ከዚህ የጠበከኝ እያልክ እያመሰገንክ  ትተህ መሄድ ብቻ ነው አለኝ፡፡  
 
......ምንም አማራጭ የለም እንዳለዉም እየሄድን የብዙ ሰዉ እሬሳ የሚቀብረዉ ጠፍቶ ...ደግሞ ግማሹም አሞራ እየበላዉ  አየሁኝ.....

  በዚህ ባየሁት ሒወት እያዘንኩ የሰዉ ልጅ ያልፍልኛል ብሎ በርሀ ያለቀባሪ መቅረት የቁራ እና የአሞራ ምሳ መሆናችን በጣም አሳዛኝ ነዉ፡፡ እኔ ከሁሉም እንደዚህ ወደ ስደት ሲወጣ እናቱን አባቱን ወንድም እህቱን ልጁን ሚስቱን ጥሎ ያልፍልኛል ብሎ አስቦ እንደወጣ መቅረት አሳዛኝ ነዉ፡፡እናት አባት ወይም የወለደዉ ልጅ ይመጣል ወይም መቼ ነዉ ድምፁን የምሰማዉ እያሉ ሲያለቅሱ መኖር ብቻ ነዉ ....ለምን በስደት ላይ ሙታል እንዴት ብሎ ይመጣል ፡፡ በስደት የወጣ መቼም ሞተ ግን እሱ ብቻዉን አይሞትም እናት እና አባቱ አብረዉ የቁም ሞት ይሞታሉ ..መቼ ነዉ ልጄ የሚደዉልልኝ ???እያሉ መጠበቅ ነዉ የሚሆነዉ.....ሰዉ በስደት እንደ ቅጠል ይረግፋል፡፡
     ደግሞ ሴቶቹ በየቦታዉ በማይታወቅ ሰዉ ይደፈራሉ ፡፡የደላሎች ስሜት ማብረጃ ይሆናሉ፡፡ ሴትነቷን መጠቀሚያ ነዉ የሚያረጓቸዉ መጥፎ ደላሎች ለአንዳንድ ባለሀብቶች ብር እየተቀበሉ እዛ በረሀ ላይ ከምታድሩ እቤት እደሩ ብለዉ ያዘኑ መስለዉ ሳትወድ በግዳ አንድ ወንድ ጋር ታድራለች፡፡ ብታለቅስ ብትጮህ ማንም የሚገላግላት የለም ይሄንን ግፍ ከመቀበል በቀር ...ሒወት ይቀጥላል ሳይሆን ላይቀጥልም ይችላል የሚለዉን ማሰብ አለብን ...ሒወት ከስደት ቡሀላ የሚቀጥል አይመስልም አስፈሪ እንቅልፍ የሚነሳ ነዉ፡፡
   በዚህ እድሚየ ፈጣሪ ስንቱን አሳየኝ፡፡

   ......እንደምንም ብዙ በርሀ ከተጓዝን ቡሀላ ...ባህሩ ዳርቻ ደረስን ፡፡ እዛዉ ሜዳዉ ላይ አደርን......

  ጠዋት ላይ እንደተነሳን እዛዉ ሜዳዉ ላይ ከቀይ ባህር አጠገብ.....ከሀርቡ ከተለያዪ የኢትዮጲያ ሀገር የመጡ ሰዎች ጋር ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍን ...ቁምጣ ለብሰን እበሀሩ ጎን ሁነን በዉሀ ስንቦራጨቅ ዋና የሚችል እዛዉ እየዋኙ... ደስ የሚል ጊዜ ስናሳልፍ ዋልን...ትንሽም ቢሆን ተረጋጋሁ ..ትንሽ ደስታ ትልቅ ሀዘንን ማጥፋት ትችላለች፡፡

    ግን የወጣሁበት አላማ ለካ ለመደሰት ሳይሆን ለማዘንም ነዉ ፡፡ ይሄን ደስታየን ከአንድ ቀን ሳያልፍ....ጀልባው መጣ ፡፡

ሁላችንም ስደተኟች ወደ ሀያ(20) የምንሆን ሰወች በባህሩ ጉዟችንን ልንጀምር ወደ ጀልባዉ እየወጣን ነዉ......
  እኔም ከቀይ ባህር ዳርቻ ቆሜ ፓስፖርቴን እና የሰአዳን ፎቶ የያዘውን ፖርሳየን በፌስታል ውሃ እንዳያበሰብስብኝ ጠቅልየ ጉያየ አስገባሁት
...........ጀልበዋ ወደ የመን መንቀሳቀስ ጀመረች
#Part 1⃣8⃣
ይ.......ቀ......
..............ጥ.......ላ............ል
.........
JOIN   t.me/alahu_akber1
  •════•••🍃🌺🍃•••════
__እዉነተኛ ታሪክ_
😢 #ፍቅር_እንዲህ_ነዉ_ወይ??❓
      🌀 #Part 1⃣8⃣

✍ ፀሀፊ #አሚር_ሰይድ

 .   ጀልበዋ  በጣም ትንሽ ነች......ባለጀልባዉም  ከ 12 -15 ሰው በላይ አትይዝም አለዉ ለደላላዉ ...በጀልባ የሚወስደን ሰዉ .....
......ደላላው በዛ በዚህ ብሎ ለብቻዉ ጠርቶ ብር አስጨብጦ  አሳመነው፡፡ ሁላችንም ወደ ጀልባዉ ወጣን.....
     ደላላው ከአሁን ቡሀላ ሀላፊነቴን ተወጥቻለሁ በሰላም ግቡ አላህ ከእናንተ ጋር ይሁን ብሎ ተሰናበተን ........
    ከዚያም  በኋላ ምን እንሆን ይሆን???  ጀልባዋ መንቀሳቀስ ጀመረች ፡፡19 ወንድ ስንሆን አብራን አንዲት ሴት አለች
.............ከድር አለችኝ
...... አቤት አልኩኝ
......,እንካ የጉዞ ኪንን ውሰድ ያስመልሰሀል (ያስታዉከሀል)አለችኝ
 .......ደግሞ ይሄ ውሃ ነዉ ቀጥታ ነዉ የሚሄደው አልወስድም አልኳት
......,ፈገግ አለችና ታያለህ እኔ አሁን ሁለተኛየ የወሰድኩት አለችኝ ፡፡ የበሀር ጉዞ ከአሁን በፊት ሂጄ ነበር  አለችኝ
.....እኔም አልፈልግም አልኳት
.....መሬቱን እየራቅነው ወደባህሩ መሃል ገባን
     ጀልባው  ወደመሀል ስንገባ መለስተኛ ማእበል ተነሳ በዚያ ላይ ጀልባዋ ትንሽ ናት.... ጀልበዋን በተደጋጋሚ ወደላይ ብድግ ያደርጋታል መልሶ ዉሀዉ ላይ ዘጭ ትላለች
      ወላሂ አስታውሳለሁ በአላህ ምየ ነው የምነግራችሁ እዚያ ጀልባ ላይ አላህን እንደለምንኩት ውጭ ሌላ ቀን  ብለምነው ኖሮ ምንም ነገር እምቢ አይለኝም፡፡ ሁላችንም በጀልበዋ ያሉት ሰዎች ጭንቀቱ በረታ፡፡
..... በሁለት እጄ አግዳሚ ጣውላውን ጨብጨ ይዣለሁ ብቻ ብዙ ነገር ሳስታውሰው ይዘገንነኛል ማዉራት ይከብደኛል፡፡
  የመኪና መንገድ  á’áˆľá‰łáˆ˜áŠ•áŒˆá‹ľ  ምናለበት፡፡ መለስተኛ ማዕበል ተነሳ መርከቧን ወደላይ አንስቶ ያፈርጣታል አቤት ጣውላው አለመሰንጠቁ ያች ጀልባ በጉንና ጎኗ ውሃ እየገባ ይሞላታል ውሃውን ዛቁ አውጡ አለቅን ይባባላሉ እኛም ነገሩ ሲጠና እየሄድን  ግማሻችን  ውሃውን እናወጣለን ግማሻችን ያአላህ እያሉ ያለቅሳሉ
    አንዱ የመኔ ጀልባዋን ይሾፍራል ሌላኛው ጓደኛው በኮኮብ አቅጣጫን ከፊት ሆኖ እየተከተለ ይመራል፡፡
.....ልጅቱ መድሀኒቱን ዋጥ ያለችኝ እዉነቷን ነበር.... አንዱ ባንዱ ላያ ያስታውካል እኔ ጣውላውን በእጀ ይዣለሁ ከጎኔ ባለው ሰው አናት ላይ ትውኪያየን ለቀኩበት ፡፡ ማንም ማንንም አይሰማም የጭንቀት ሽንት አለ በአምስት ሊትር ገድበህ የምትሸናው
..... እኔ ውሀው ተቀላቅሎበት ይሁን ሽንቱ በዝቶ አልገባኝም ጎማውን ሞላሁት ከጎኔ ያለው አምጣ እኔም ልሽና አለኝ
....እኔም ቆይ አልጨረስኩም አልኩት አሁን ላይ ሳስበው እንባየ እስከሚመጣ እስቃለሁ
  አንዱ በጭንቀት እንዲህ አለኝ ከድር እየተያየን ከምናልቅ እኔና አንተ ዘለን ውሃው ውስጥ እንግባ አለኝ
....እኔም እሺ አልኩት ሁላችንም በጭንቀት አብደናል ያ ልጅ ብድግ ሲል የመኒው በያዘው ዘንግ ወገቡን ሲለው ቁጭ አለ ብቻ የጭንቀት ሽንት ባህር ላይ ተሸና ፡፡
   በጣም የሚገርመው እኛ በዚያ ጭንቀት ላይ ሆነን  መድሀኒት ዋጥ ያለችኝ ልጅ አብራን የተሳፈረችውን ሴት ጡት ለማሸት ባንድ እጁ እየነዳ ባንድ እጁ ይታገላል፡፡ እሷም ትሸሸዋለች በአማረኛ ተወኝ አላህን ፍራ ትለዋለች
... ከሷ ጎን ያለው ልጅ አብዱ ይባላል ውሃ እየዛቀ ከደር!  ከድር!  በአረበኛ ተናገረው ተው በለው አለኝ
.....እኔም አልሃሪም ሃምላ  አልኩት (ሴቲቷ እርጉዝ ነች)ማለት ነው ድንግጥ ብሎ መተናኮሉን አቆመ.....እኔም ገረመኝ በዛ ጭንቀት እንዴት እንደዛ ስለዉ መተዉ አጀበኝ
 
    እንደምንም ከ 6 ሰአት ጉዞ በኋላ አላህ በሰላም የመን ምድር ደረስን ፡፡.......ደረቁ መሬት áˆ‹á‹­ ጀልባዋ ቆመች..... እኔ ግን እጄ ጣውላውን የጨበጥኩበት እዚያው ላይ ደርቋል ይሄ የጨው ውሃ ሰውነቴን ስለረጨኝ .....ጨው መስያለሁ፡፡
   
     ከባህሩ እንደወረድን  ዳር ላይ የሚቀበሉን የየመን ምሽዋር ቤት ደላላዎች.....እጄን ፈልቅቀው እግርና እጄን ይዘው መኪና ላይ ጫኑኝ ፡፡ ጉዞ ወደ ምሽዋር ቤት በመኪና ተጭነን ሄድን............እዚያ ደረስን ሸዋር አስወሰዱን ምግብ አበሉን ፡፡
.......ለሁለት ቀናት አሳረፉን ገንዘብ የሚላክለትን አስቀርተው ....ሌሎቻችንን ገንዘብ የማይላክልንን የተወሰነ ስንቅ እያስያዙን አሰናበቱን፡፡
    ይህን ያደረጉት ገና አዲስ ምሽዋር ቤት ከፋቾች ጥሩ ሰዎች ስለሆኑ ነዉ እንጂ ብዙዎቹ ጨካኝ ናቸዉ ገላችንን አሳጥበዉ የተወሰነ ስንቅ መስጠታቸዉ የተሻሉ ሁነዉ ነዉ...... ከዚያ ከምሽዋር ወጥቸ በእግሬ አምስት ቀን ተጓዝኩ
 >>>>>>>>>>>>> የምንከተለው ቂብላን ነው... ሲመሽ በርሀ ላይ አድረን አቅጣጫው ከጠፋን ወደኋላም ልንመለስ ስለምንችል በምሽት መጓዙን አልመረጥነዉም...... በየገጠሩ በሚገኙ መንደሮች እያገለልን ምግብ እንጠይቃለን .....የመን የዋህና ገራገር ናቸው ያላቸዉን ይሰጣሉ እንደዚህ እያልን አምስት ቀን ተጓዝን......

   ከ 5 ቀን በኋላ ግን እኔ መጓዝ አልቻልኩም እግሬ አበጠ ዉስጡም ቆሰለ አንድ ጫማ ነዉ ያለኝ  ተገነጠለ.... አብረውኝ የሚጓዙት ሃበሻ ቢሆኑም የሌላ አገር ሰወችም አሉ ፡፡    
    ያገናኝን ይሄ ቀላል መስሎ ከባድ የሆነ መከረኛው ስደት ነው፡፡  ያላቸው አማራጭ እነሱ ለመዳን አብሽር አላህ ይሁንህ ብለዉኝ  እኔን ለአላህ ሰጥተውኝ ወደፊይት መሄድ ብቻ ነው ፡፡ ከዛፍ ሾር አስቀምጠዉኝ ተሰናበቱኝ ...ደላላዉ ጋር ስመጣ እንቀበረዉ እንጂ ከዛፍ ሾር ሙቶ ተቀምጧል ያልኩት ትዝ አለኝ፡፡
......የአላህ ምን ያጋጥመኝ ይሆን እያልኩ 100% ተስፋ ቆርጫለሁ እምባየም ቁጭ ባልኩበት ኩልል እያለ እዛ የበረሀ አፈር ላይ ያርፋል ሞት ብቻ ነዉ የሚጠብቀኝ ...አይታወቅም ከአላህ ተስፋ አልቆርጥም ብየ ዱአ እያረኩ ነዉ ፡፡ 
  
       አንድ በሞተር የሚሄድ የመኒ መጣ....ሞተሩን ከተቀመጥኩበት ጎን አቆመና ብር እንዳለኝ ለመፈተሽ ፖርሳየን አወጣዉ.... ከፈተው ምንም አላገኝም፡፡እኔን  ኬሴን አገላብጦ ፈተሸኝ ባዶ ነኝ ......ሲፈተሽ ግን ሰአዳ የሰጠችኝን ፎቶ መልኳ እስከሚገፍ ድረስ ካየዉ ቡሀላ  መሬት ላይ ጣለዉ፡፡
......ፖርሳውን ፊቴ ላይ ወርውሮ ትቶኝ በሞተሩ ሄደ፡፡  መሬት ላይ የወደቀዉን የሰአዳ ፎቶ አንስቼ መመልከት ጀመርኩ ....ሰአዲ ከኔ ተስፋ ቁረጭ አንገናኝም አንቺን ለማግኘት ላለማጣት ብየ  ብር ለመያዝ በርሀ ላይ ማንም ጠያቂ የሌለበት ምግብ ወሁ ሳይኖረኝ እግሬ ቁስሎልሻል  መሔድ አቅቶኝ ሞቴን እየጠበኩ ነዉ ..ሰአዲ እንገናኝ ይሆን????? ወይንስ እዚሁ የወደኩበት ህይወቴ ያልፍ ይሆን? ረሀቡ አልቻልኩትም የእግሬ መቁሰል መሄድ ስላቃተኝ እዚያ እሰዉ ሀገር ምንም ሰዉ የሌለበት ቁጭ እንዳልኩ ብቻየን አለቅስ ይዣለሁ...
  
   ይቺ ነፍስያ አላስችል አላት አሟሟቴ አስጠላኝ ተስፋ ቆረኩ ላኢለሀኢለሏህ ሙሀመዱ ረሱሉላህ እያልኩ በተደጋጋሚ ሸሀዳ ላይ ነኝ ፡፡
  ጊዜዉም መሸ እኔም እርሀቡ ዉሀ ጥሙ አሸነፈኝ..አልጮህ የሚሰማኝ የለም ደግሞም á‹‰áˆ€ ጥም አፌ ተያይዟል እንኳን ሰዉ እንዲደርስልኝ ቃላት የምናገርበት አቅም የለኝም...አይኔ እያየ መሞት አልቻልኩም..ከተቀመኩበት እንደምንም ለመነሳት ስንገዳገድ አዞሮኝ መሬት ላይ ዝርር ብየ ወደኩ
part 1⃣9⃣ ይቀጥላል👇
 t.me/alahu_akber1
አስለቅሶታል መሰለኝ የነገራት ሰዉ አብሮ ያለቅስ ነበር፡፡ ስደት ማለት ትርፉ ይሄ ነዉ፡፡ ተመልከቱ ሳዉዲ ያለችዉ እህቷ አደራ ምንም እንዳትሆንብኝ እያለች መሞታን ሰማች ያልፍልኛል ብላ እህቴን አገኛለሁ ብላ ለአገሯ አፈር ሳያበቃት እሰዉ ሀገር ሞተች ለዛዉም አሟሟቷ የሚዘገንን ነዉ.....እናት አባት ሲሰሙ ምን ይሉ ይሆን፡፡ መቼም ይሄን እዉነተኛ ታሪክ አንብቦ እምባ የማይወጣዉ ጨካኝ አረመኔ ቢሆን ነዉ፡፡

   ልጅቱን አብሬ አልቅሰን ከቀበርን ቡሀላ ከባድ ሀዘን ተስፋ ተሟጦ  የምሄድበት ግራ ሲገባኝ ከመኪና መንገድ ዳር ላይ ቁሜ ..አንድ  መኪና ሲመጣ እንዲያቆምልኝ በእጄ ምልክት ሰጠሁት....,
.....
ሹፌሩም አቆመልኝ
......,እኔም ወደ ሳውዲ ነኝ ተባበርኝ አልኩት
.......እሽ ውጣ አለኝ 
         መኪናዉ ከላይ ክፍት ነበርና ወጣሁ
  ......ምነው እዚህ መኪና ላይ መዉጣት በቀረብኝ ፡፡ ለካስ የወሰደኝ ሊተባበረኝ ሳይሆን ለምሽዋር ቤት ሊሸጠኝ ነው፡፡ ለምሽዋር ቤቶች ለነዚህ ጨካኞች አስገብቶ 100 ሪያል ሸጠኝ .....
 á‹¨áˆ†áŠ ክፍል ዉስጥ አስገብተዉ ወረወሩኝ እና መልሰዉ በሩን ዘጉት፡፡ ብዙ ሰዉ እንደ በግ የታጎረበት ክፍል ነዉ በጣጣጣጣም  ብዛት አላቸዉ የተለያዩ ሀገር ዜጎች ወንድ ሴት ድብልቅልቅ ያለ ክፍል ነዉ ....
     ቤቱ ግንብ ነው ከላይ ክፍት ነው ዙሪያውን ከግንቡ ላይ መሳሪያ ይዘው የሚጠብቁ አሉ ከዚያ ቦታ ድንበሩን ለማሳለፍ ብቻ 1500 የሳውዲ ሪያል ያስከፍላሉ፡፡  እዚህ ቤት ውስጥ የምትገባው አምነህበት ወደህ ሳይሆን  ተገደህ ነው ....
 .ይሄንን 1500 የሳዉዲ ሪያል ካልከፈልክ መውጣት አይታሰብም ፡፡  ምን ይዉጠኝ የሆን ...አይ የኔ ፈተና ብዛቱ......
 
#part 2⃣0⃣
 á‹­..............ቀ.....
...........ጥ............ላ............ል👇

 .¡¨: ❀ share
           `¡.     t.me/alahu_akber1
part 1⃣

ከትዳር በፊት እንጠናና...አግባብ ነዉ ወይ??

✍✍ከኒካህ በፊት ስለማንነታችን በደንብ እንተዋወቅ። ለትዳር ሂወታችን ጠቃሚ ስለሆነ እየተጠናና እንቆይ የሚባለው አባባል ከሸሪአ አንፃር እንዴት ይታያል?

💐💐ኢስላም በመሰረቱ ማንኛውም ማህበረሰቡን የሚጎዱ ተግባራትን ቀድሞ እንድንርቃቸው ያዘናል፡፡ በማህበረሰበችን ዘንድ እንኳን ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም ግንኙነት በጥሩ አይን አይታይም፡፡ የሴት ልጅ ክብሯ እና ውበቷ እራሷን የህዝብ ሃብት ከማድረግ መቆጠብ መቻሏ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ሂጃብ ከማደረግ እራሷን ከመሸፈን አንስቶ ከማንኛውም አይነት አጂ ነብይ ወንድ ጋር ከኒካህ በፊት ግንኙነት ሳታደርግ መቆየት መቻሏ ነው፡፡

✅✅ይህን የሃራም ግንኙነት ሁሉም ማለት ይቻላል  ክልክል መሆኑን ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ ወጣቱም፣አዋቂውም፣ጃሂሉም ባጠቃላይ  ማገናዘብ የጀመረ ሙስሊም በሙሉ ከኒካህ በፊት ምንም አይነት ግንኙነት ማድረግ በኢስላም ክልክል መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ይህን የአላህን ክልከላ አውቆ የሚርቀው ግን በጣም ጥቂቱ ነው፡፡

♻️♻️♻️♻️በኢስላም ጋብቻ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው  ሲሆን መልካም የሆኑ ባል እና ሚስቶችን የሚጣመሩበት ይሆን ዘንድ ያዛል፡፡ ባለጌ ባለጌን እንጂ ጨዋን እንድታገባ  በኢስላም አይፈቀደም፡፡ በዝሙት የተጨማለቀ ወንድም የሱ ቢጤውን እንጂ ጥብቅ የሆነችን ሴት እንዲያገባ አይፈቀደም፡፡ ታዲያ ከጋብቻ በፊት ዝሙት እስካልፈፀምን ድረስ ይህ ክልከላ አይመለከተንም ይባል ይሆናል፡፡

መረጃውን እንደሚከተለው እንመልከተው:-

فَانكِحُوهُنَّ بِإِذْنِ أَهْلِهِنَّ وَآتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ مُحْصَنَاتٍ غَيْرَ مُسَافِحَاتٍ وَلَا مُتَّخِذَاتِ أَخْدَانٍ ۚ

ጥብቆች ኾነው ዝሙተኞች ያልኾኑ የስርቆሽ ወዳጆችንም ያልያዙ ሲኾኑ (አግቧቸው)፡(ሱራ አል ኒሳዕ፡25)

✍✍✍ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው ይህን አንቀፅ ኢብኑ አባስ(አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) ሲፈስሩት ጥብቆች የሆኑ ማለቱ ምንም አይነት ዚና ያልፈጸሙ እና የብልግና ተግባር ከማንም ጋር ለመፈፀም እሺ የማይሉ መሆኑን ሲገልፁ  وَلَا مُتَّخِذَاتِ أَخْدَانٍ የሚለው ደግሞ ፍቅረኛ ያልያዙትን ማለት እንደሆነ አስቀምጠዋል፡፡ በዛው ማብራሪያቸው ላይም ሃሰነል በስሪ(አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) የወንድ ጓደኛ ማለት እንደሆነ መናገራቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ተመሳሳይ መልዕክትም  በሱረቱል ማዒዳ ላይ የሚከተለውን እናገኛለን፡-

وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الْمُؤْمِنَاتِ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَافِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِي أَخْدَانٍ

ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)፡፡(አል ማዒዳ፡5)

❤️❤️❤️ይህንንም አንቀፅ አስመልክቶ ኢብኑ ከሲር(አላህ ይዘንላቸው) ሲያብራሩ ጥብቅ የሆነችን ሴት የሚለውን ከዝሙት የራቀች ፣የወንድ እጮኛ ያልየዘች መሆኑን በመግለፅ ይህ ድንጋጌ ወንዱም ጥብቅ፣ዝሙተኛ ያልሆነ፣የሴት እጮኛ ያልያዘ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ማብራሪያቸው ላይ ብዙ እጮኛ ያለውም ሆነ አንዲት እጮኛ ተመሳሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህ ማብራሪያ ላይ ኢማሙ አህመድ(አላህ ይዘንላቸው) ከላይ በተገለፀው አንቀፅ መሰረት ጥብቅ ያልሆነ ወንድ ወይም እጮኛ የያዘ እንደሆነ ጥብቅ የሆነችን ሴት ተውበት አድርጎ ከድርጊቱ ሳይመለስ ማግባት ለሹ የተከለከለ መሆኑን ፡፡ እንዲሁም ጥብቅ ያልሆነች ሴት፣ ወይም ወንድ እጮኛ ይዛ የነበረች ሴት ከድርጊቷ ተውበት አድርጋ እስካልተመለሰች ድረስ ጥብቅ ወይም ጨዋ ወንድን ማግባት ክልክል ነው  ማለታቸውን ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

Part 2⃣
ማታ ይቀጥላል✅✅✅

#Share $ join
👇👇👇
https://t.me/alahu_akber1
part 1⃣

ከትዳር በፊት እንጠናና...አግባብ ነዉ ወይ??

✍✍ከኒካህ በፊት ስለማንነታችን በደንብ እንተዋወቅ። ለትዳር ሂወታችን ጠቃሚ ስለሆነ እየተጠናና እንቆይ የሚባለው አባባል ከሸሪአ አንፃር እንዴት ይታያል?

💐💐ኢስላም በመሰረቱ ማንኛውም ማህበረሰቡን የሚጎዱ ተግባራትን ቀድሞ እንድንርቃቸው ያዘናል፡፡ በማህበረሰበችን ዘንድ እንኳን ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም ግንኙነት በጥሩ አይን አይታይም፡፡ የሴት ልጅ ክብሯ እና ውበቷ እራሷን የህዝብ ሃብት ከማድረግ መቆጠብ መቻሏ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ሂጃብ ከማደረግ እራሷን ከመሸፈን አንስቶ ከማንኛውም አይነት አጂ ነብይ ወንድ ጋር ከኒካህ በፊት ግንኙነት ሳታደርግ መቆየት መቻሏ ነው፡፡

✅✅ይህን የሃራም ግንኙነት ሁሉም ማለት ይቻላል  ክልክል መሆኑን ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ ወጣቱም፣አዋቂውም፣ጃሂሉም ባጠቃላይ  ማገናዘብ የጀመረ ሙስሊም በሙሉ ከኒካህ በፊት ምንም አይነት ግንኙነት ማድረግ በኢስላም ክልክል መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ይህን የአላህን ክልከላ አውቆ የሚርቀው ግን በጣም ጥቂቱ ነው፡፡

♻️♻️♻️♻️በኢስላም ጋብቻ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው  ሲሆን መልካም የሆኑ ባል እና ሚስቶችን የሚጣመሩበት ይሆን ዘንድ ያዛል፡፡ ባለጌ ባለጌን እንጂ ጨዋን እንድታገባ  በኢስላም አይፈቀደም፡፡ በዝሙት የተጨማለቀ ወንድም የሱ ቢጤውን እንጂ ጥብቅ የሆነችን ሴት እንዲያገባ አይፈቀደም፡፡ ታዲያ ከጋብቻ በፊት ዝሙት እስካልፈፀምን ድረስ ይህ ክልከላ አይመለከተንም ይባል ይሆናል፡፡

መረጃውን እንደሚከተለው እንመልከተው:-

فَانكِحُوهُنَّ بِإِذْنِ أَهْلِهِنَّ وَآتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ مُحْصَنَاتٍ غَيْرَ مُسَافِحَاتٍ وَلَا مُتَّخِذَاتِ أَخْدَانٍ ۚ

ጥብቆች ኾነው ዝሙተኞች ያልኾኑ የስርቆሽ ወዳጆችንም ያልያዙ ሲኾኑ (አግቧቸው)፡(ሱራ አል ኒሳዕ፡25)

✍✍✍ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው ይህን አንቀፅ ኢብኑ አባስ(አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) ሲፈስሩት ጥብቆች የሆኑ ማለቱ ምንም አይነት ዚና ያልፈጸሙ እና የብልግና ተግባር ከማንም ጋር ለመፈፀም እሺ የማይሉ መሆኑን ሲገልፁ  وَلَا مُتَّخِذَاتِ أَخْدَانٍ የሚለው ደግሞ ፍቅረኛ ያልያዙትን ማለት እንደሆነ አስቀምጠዋል፡፡ በዛው ማብራሪያቸው ላይም ሃሰነል በስሪ(አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) የወንድ ጓደኛ ማለት እንደሆነ መናገራቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ተመሳሳይ መልዕክትም  በሱረቱል ማዒዳ ላይ የሚከተለውን እናገኛለን፡-

وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الْمُؤْمِنَاتِ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَافِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِي أَخْدَانٍ

ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)፡፡(አል ማዒዳ፡5)

❤️❤️❤️ይህንንም አንቀፅ አስመልክቶ ኢብኑ ከሲር(አላህ ይዘንላቸው) ሲያብራሩ ጥብቅ የሆነችን ሴት የሚለውን ከዝሙት የራቀች ፣የወንድ እጮኛ ያልየዘች መሆኑን በመግለፅ ይህ ድንጋጌ ወንዱም ጥብቅ፣ዝሙተኛ ያልሆነ፣የሴት እጮኛ ያልያዘ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ማብራሪያቸው ላይ ብዙ እጮኛ ያለውም ሆነ አንዲት እጮኛ ተመሳሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህ ማብራሪያ ላይ ኢማሙ አህመድ(አላህ ይዘንላቸው) ከላይ በተገለፀው አንቀፅ መሰረት ጥብቅ ያልሆነ ወንድ ወይም እጮኛ የያዘ እንደሆነ ጥብቅ የሆነችን ሴት ተውበት አድርጎ ከድርጊቱ ሳይመለስ ማግባት ለሹ የተከለከለ መሆኑን ፡፡ እንዲሁም ጥብቅ ያልሆነች ሴት፣ ወይም ወንድ እጮኛ ይዛ የነበረች ሴት ከድርጊቷ ተውበት አድርጋ እስካልተመለሰች ድረስ ጥብቅ ወይም ጨዋ ወንድን ማግባት ክልክል ነው  ማለታቸውን ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

Part 2⃣
ማታ ይቀጥላል✅✅✅

#Share $ join
👇👇👇
https://t.me/alahu_akber1