ጫት የማትቅሙ ሰዎች አትጀምሩ:: የጀመራችሁም እጅግ በጣም ቀንሱ:: አደብ ከሌለው እንኳንስ ጫት ምግብም ሶላትም ያስቀይማሉ:: ሥርዓት የሚያስይዘንና ጸባያችንን የሚያስተካክልልንን ሶላት ስንሰግድ ሥርዓት ካስፈለገ ወትሮም ከሥርዓት የሚያስወጣንን ጫት እንዴት ሊሆን ነው? አቀራርቤ እያወዳደርኩ አይደለም::
ጫት ከመደበኛ የአስተሳሰብ ምሕዋር እንደሚያስወጣ ይታወቃል:: የቻለ አይቅረበው:: የቀረበው ግን ከምንም በላይ ለሥርዓት ይጨነቅ:: ከምሕዋር ይወጣላ! ፈታ ለማለት እየቃምን የምን መጨነቅ ነው ትሉ ይሆናል:: ወንድሜ ሁሌ ፈታ ማለት የለም:: ዱንያ ላይ ጨምደድ የምትልበት ወቅት ይበዛል:: ፈታ ለማለት የምትቅመው ጫት ደግሞ ብዙ ነገርህን ያጨማድድብሃል:: ማጨማደድ ባሕሪው ነው:: ሰተት ብለህ ከገባህለት ይገባልሃል:: አምጣ ባለህ ቁጥር የምትሰጠው አባትህ ወይም እናትህ ወይም ልጅና ሚስትህ አይደለም:: ጫት እኮ አያዝንልህም:: ምን ብትሰጠው አይጠግብም::
የቀድሞ አባቶቻችንን አቃቃም ከደረስክበት:- ቤት ለማሞቅ ይጎዘጉዛሉ:: ጥቂት ነው ቀመስ የሚያደርጉት:: ከሚቃመው ደርቆ የሚጣለው ይበልጣል:: ሲጀመር የሚጣልም ያህል አያመጡም:: እስኪመረቅኑ አይቅሙም:: እኛ አሁን በማኪያቶ ከምንመረቅነው አይዘልም ማለት ይቻላል:: በእርግጥ በዚያው ልክ አጋድመውና ተጋድመው የሚቅሙም ነበሩ::
ሰውነትህን ፕሮግራም ከሰጠኸው ወዲያው ይለምዳል:: ሽንት ባስለመድከው ፕሮግራም ብቻ ይመጣል:: እቤት ውስጥ መፍሳት ከለመድክ የትም ታንዛርጣለህ:: ከተውከውም ይተውሃል:: ምግብ ባስለመድከው ወቅት ብቻ ትበላለህ:: ሰውነታችን ችግር ይለምዳል, ሀብት ይለምዳል, ሀዘን ይለምዳል, መርሳት ይለምዳል, ብርድና ሙቀት ሳይቀር ይለምዳል:: ዋናው ከልብ መቁረጥ ነው::
አንተስ ትቅማለህ ወይ? ካልከኝ አልቅምም ብል ይቀላል:: ከማኪያቶ ሙቀት እንዲዘል አልፈቅድለትም:: ከምቅመው ይልቅ የምጥለው ያስደስተኛል:: አሁን ላይ ባለ 70 የሚሉት ላይ 1/5ኛውን አልፈጅም:: ቤት ያሞቅና እንጥለዋለን:: እርሱም ከዕለታት ባንዱ ቀን:: ለ25 ዓመታት ያቆምኩ ሰው ነኝ:: ከዚያ ለ25 ቀናት ወይም ለ25 ወራት ላልነካ እችላለሁ::
በእስልምና ስም መቃሙን እንኳ ተውት:: እስልምና ንጽሕና ነው:: ለጡሃራ ደግሞ ከውሃም ውስጥ ውሃ ይመረጣል:: ጫትም እስኪያቆሽሽህ ከቃምክ ስተሃል:: ወላሂ!
Hassan injamo
https://t.me/Haseniye
https://t.me/mneyuredulahe

Telegram
Hasen Injamo
Main focus is Value Based Finance ዋነኛ ትኩረቱ እሴት ተኮር ፋይናንስ ነው::
https://telega.io/c/Haseniye
https://telega.io/c/Haseniye
ጫት ስለበላህ ሱፍይ አትባልም። ስላልበላህም ውሃብይ አትባልም። በቀላሉ ከሀገር ውስጥ ሀረር ድሬዳዋ ብትሄድ ከሱፍያው በላይ የሚቅመው ውሃብዩ ነው። አዲስም ውስጥ የምናውቃቸው የሚቅሙ ውሀብዮች አሉ። ድሬ ወይም ሀረር ሄደህ ጫት ሀራም ነው ብትል ውሃብዩ ነው አፈር ድሜ የሚያስበላህ።
ወንድሞች ሲጀመር ጫት አይደለም ከሱፍይነት ከእስልምና ጋር ምንም አያገናኘውም። ስለቃመ ሙስሊም አይባልም። ስላልቃመም ክርስቲያን አይባልም።
ጫት ልክ እንደ ሻይ ማክቶ ቡና ነው። ሌላ ምንም ለውጥ የለውም። ቡና ስለጠጣህ ሱፊ ሰለፊ አትባልም። ሻይም ማክያቶም ጫትም እንደዛው። ጫቱ ለአባቶች እንተወው። ዑለሞቹ ሲቅሙ ኪታብን ያቃራቸው ዘንድ አንድ ሁለት ነው የሚዙት።
✅ አንተ የምትቅመው ቅራ ስንልህ ጊዜ የለኝም ያልከን ስትቅም የሚባክነው ጊዜስ❓ ዑለሞች እኮ ያለ እውቀት የሚሰራ ዒባዳ ባጢል ነው። ተቀባይነት የለውም ብለዋል። እንደውም በፊቅህ በሻፊዕዮች ባፈድልን በሌሎች መዝሀቦችም በባፈድል ደረጃ ያለን ኪታብ ካልቀራ ሰላቱ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።❗️
👌ነገ የመጀመሪያ ሂሳብ የሚደረገው ሰላት ነው። ሰላቱ የተበላሻ ሁሉም ስራው ይበላሻል። ሰላቱ የተስተካከለ ሁሉም ስራው ይስተካከላል። ታድያ ሳትቀራ እንዴት ነው ሰላትህ የሚስተካከለው❓
አንዳንዱ ስለቃመ አረንጓዴ ስለለበሰ ሙስበሃ አንገቱ ላይ ስለደራረበ ወልይ ሱፍይ የሆነ ይመስለዋል። አትሸወድ ሱፍይነት በአጭር አገላለፅ
محاربة النفس لا سلم فيها
{ከነፍስያ ጋር ስምምነት የሌለው ጦርነት መክፈት ነው።}
አንተ ጃሂል ከሆንክ በመቅራት ነፍስያህ ጋር ጦርትነት መጀመር። በቀራሀው ለመስራት መታገል። ውስጥህም ውጭህም ለአላህ አሳልፈህ ለመስጠት የምታደርገው ጦርነት።
ብጣሽ ወረቀት ቀርተህ አፍህን በአላህ ባሮች እየከፈትክ ሱፍይነኝ ስትል አታፍርም❓ተሰውፍነት ወሬ ሳይሆን ስራ ነው። ስራ ደግሞ የሚጀምረው ከዒልም ነው። ሰይዲ ኢማም ማሊክ
من تفقه ولم يتصوف فقد تفسق، ومن تصوف ولم يتفقه فقد تزندق
ዒልም ከስራ ጋር ስናገናኘው ውጤቱ ተሰውፍ ጋር ያደርሰናል። ዒልም እና ዐመል መነጣጠል የሚይችሉ የተሰውፍ መሰረቶች ናቸው።
የፈለገ ይቃም የፈለገ አይቃም መብቱ ነው። ቡናም የፈለገ ይጠጣ የፈለገ አይጠጣ መብቱ ነው። ሻይም ማክያቶም። ነገርግን ስለ ቃምክ ሱፍይ ሱፍይ አይሰራራህ።
https://t.me/ahlusunawelgema

ناصر الدين(ናሲሩዲን)
[[ وَجَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا ]]
{እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።}
ሼር add በማድረግ የበኩላችን እንወጣ
https://t.me/joinchat/jhrmqQH66YtiOGFk
{እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።}
ሼር add በማድረግ የበኩላችን እንወጣ
https://t.me/joinchat/jhrmqQH66YtiOGFk
📢አስደሳች ዜና ለክረምት ኦን ላይን ደርስ
✍️አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ
ዳሩል ሒጅራተይን ኢስላማዊ ዕውቀት ማዕከል በተለያዩ የኢልም ዘርፎች አጭር የክረምት ኮርስ
መርሀ ግበር ሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭ
ላላቹህ በሙሉ ቁርአንን ማንበብ እና ማወቅ እየፈለጋቹህ እድሉን ላላገኛቹህ በሙሉ ታዳጊዎችን እንዲሁም አዊቂዎችን መሰረታዊ የዲን ዕውቀትን ለማስጨበጥ ዝግጅቱን ጨርሶ የናንተን መምጣት በመጠበቅ ላይ ነው
➜ ልዩ ከሚያረጉን አንዱ ደርስ አሰጣጥ ላይ ሸሪዐውን ባማከለ መልኩ እውቅና ባላቸው ልዪ በሴት ኡስታዛዎች ለሴት ተማሪዎች ደርስ መስጠታችን ሲሆን በተጨማሪም ለወንድ ተማሪዎችም በወንድ ኡስታዞች በልዩ ሁኔታ ደርሶችን የምንሰጥ ይሆናል።ፍላጐታችን ውስን ተማሪ በጥራት ማፍራት ነውና ፈጥነው ይመዝገቡ !!!
📚 በኦን ላይን የክረምት መርሀ ግበር
◦ለልጆች/ ለታዳጊዎች
◦ ለሴቶች
◦ ለወጣቶች እንዲሁም ለአዋቂዎች በሙሉ
🗒 ኮርሱ የሚያካትታቸው ፦
* ቁርዐን
* ተጅዊድ
* ፊቅህ
* አቂዳ
* ሀዲስ እና
* ኢሰላማዊ ስነ- ምግባራት
➥ ምዝባው ፦ከሰኔ 27 - ሀምሌ 09/2014
ይሆናል።
➥ ደርስ የሚጀመርበት ጊዜ ከሀምሌ10 እስከ
መስከረም 05/2015 በአሏህ ፍቃድ
የሚጠናቀቅ ይሆናል።
➥ ለመመዝገብ ፦ 👇👇 http://t.me/Assunnahislamicschool_bot/start
🗞በኮርሱ መጨረሻ ለተማሪዎቻችን
በውጤታቸው መሰረት ሰርተፍኬት የሚሰጣቸው
ይሆናል።
የቻናላችን መገኛ👇👇
https://t.me/DaralHijrataynIslamicSchool

አስተውል.....✍️
ለጉዳይህ ስትል ሶላትህን በጥድፊያ አትስገድ!
ምክንያቱም የቆምከው የቸኮልክለትን ጉዳይህን ጨምሮ ዱኒያን ሁሉ የያወው
ጌታህ ፊት ነውና።
@ahlusunawelgema

⚃ #መልካም_ጎደኛ
"ሁለት ውብ የሂወት ኡደቶችን ይለግሰሀል…"
"አንደኛው አዚህ ዱንያ ላይ ሲሆን"
"ሁለተኛው ደግሞ ጀነት ውስጥ ይሆናል"
# መልካም_ጎደኞች
«ወደ አሏህ መንገድ… ይጠሩሀል…»
«ከጠፋህባቸው… ይፈልጉሀል…»
«ከተዘናጋህ… አስታውሱሀል»
«…በዱአቸው ውስጥ…ያካቱሀል»
«ልክ እንደ ከዋክብቶች…
መርከብህ መንገድ ከሳተች…ይመሩሀል…»
«ነገ ከአሏህ አርሽ ስር…ኢንሸአላህ…ይጠብቁሀል…»
«ጀነት ውስጥ ፈልገውህ ካጡህ…አሏህን ወደነሱ
እንዲቀላቅልህ ይለምኑልሀል»
👌ወንድሜ ዛሬ ላይ ከፊትህ ስቆ ዞር ስትል የሚያማህ ውስጥህ ያለ ጥበብና ችሎታህን ደብቆ ባገኘው አጋጣሚ ጉደለቶችህን የሚያያሳይህ እና የበታችነት እንዲሰማህ ለማድረግ የሚሞክርን ሰው አይደለም ልብህ ጆሮህን አትስጠው።
"አሏህ ሶሊሆቹን አድርጎ ከሶሊሆቹ ያወዳጀን ከሶሊሆቹ
ጎደኞቻችን አይነጥለን በያሉበት ይጠብቅልን "
#አሚን
ለዱንያህ ለቀብርህ ለአኼራህ የሚሆንህን ሰው ምረጥ።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በድሩ ሁሴን የዛኔ በሰላማዊ ጊዜ የተናገረው
ባለቤትህ በፍቅር ቃላት ስታወራህ መንጠባረር ተውና ከሷዋ የበለጠ ፍቅር አሳያት። አንቺም ባልሽ ልቡን ከፍቶ ሲያወራሽ ከአንቺ ሌላ በምድር ሴት የሌለ አይምሰልሽ ተገቢውን ፍቅር ስጩ። ውጪ እኮ በንግግር በአለባበስ በተለያየ መልኩ የሚያማልሉት ብዙ ናቸው።።።።
ደግሞ እቤት ከባልሽ ጋር ስትሆኚ ድሪቶ ትለብሺና ከቤት ስትወጪ ተኳኩለሽ የምትሄጁ ሁለተኛ ለማግባት ነው❓ ባልሽ ወደሌላ እንዲያይ አታድርጊው ተገቢውን ቦታ ስጩ
አብዛኛው ጊዜ ወንዶች ወደውጪ የሚያዩት ከሚስታቸው ተገቢውን ፍቅር ስለማያገኙ ነው። ከተቆጡ መከራ በፍቅር ቃላት ከመጡ መከራ ግራ ሲገባቸው ደጅ ይጠናሉ። ባልሽን አጥበቀሽ ያዢ❗️ አንተም ትዕግስት ይኑርህ እንደ ሸይጣን አትጣደፍ

በወርቅ ቀለም የሚፃፍ ንግግር
አላህ የወደደው ወንጀሉ አይጎዳውም አላህ የጠላው ስራው አይጠቅመውም አሉ።
ሐፊዝ ሙራድ ሙሀመድ ሐፊዘሁላህ

➛➛ከመናገር ማሰብ ይቅደም➛➛
➲ በድሮ ጊዜ አንድ ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል። ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት ምርጫ አቀረቡለት፡፡
አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላት፤
፡
አንድ መቶ ጅራፍ መገረፍ፤
፡
አምስት መቶ ብር መክፈል፡፡
፡
ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቡና የሌለው ነበርና የመጀመርያ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ "ሽንኩርቱን እበላለሁ" አላቸው፡፡
:
አንድ ኪሎ ሽንኩርት ቀረበለት፡፡ ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ታድያ ዓይኑ ማልቀስ ፣ ለሐጩም መዝረብረብ ጀመረ፤ አልቻለም። ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና «መቶ ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል» አላቸው፡፡
፡
ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ እንደደረሰ አልቻለም፡፡ እጁን ወደ ላይ አነሣ፡፡
፡
«እህሳ» አሉት ዳኛው፡፡
፡
«አልቻልኩም» አላቸው፡፡
፡
«ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡
፡
«በቃ አምስት መቶ ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሣ፡፡
፡
«ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት።
✍ብዙዎቻችን ከመናገራችን በፊት ማሰብ ሳንቸል ቀርተን በዘፈቀደ በተናገርነው ቃል እራሳችንን ፣ ቤተሰቦቻችንን ፣ ጎረቤታችንን አልፎም ሀገርን እረብሸናል፤ ጎድተናል፡፡ ሁሌም ከማውራታችን ከመፃፋችን በፊት የምናገረው ፣ የምፅፈው ነገር ሰዎችን ያስከፋል? እውነት ነው ብለን እንጠይቅ፡፡ እውነት እራሱ የብዙሀንን ሰላም ለመጠበቅ ሲባል ካለቦታውና ካለወቅቱ አይገለፅም፡፡
ሼር🙏
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
💖 @ahlusunawelgema 🌷

ما الفضلُ إِلا لأهلِ العلمِ إِنهمُ
على الهُدى لمن استهدى أدلاءُ
وقيمةُ المرءِ ما قد كان يحسِنُهُ
والجـــاهِلونَ لأهل العلمِ أعداءُ
فقمْ بعلمٍ ولا تطلبْ به بدلاً
فالناسُ مَوْتى وأهلُ العلمِ أحياءُ
https://t.me/ahlusunawelgema
على الهُدى لمن استهدى أدلاءُ
وقيمةُ المرءِ ما قد كان يحسِنُهُ
والجـــاهِلونَ لأهل العلمِ أعداءُ
فقمْ بعلمٍ ولا تطلبْ به بدلاً
فالناسُ مَوْتى وأهلُ العلمِ أحياءُ
https://t.me/ahlusunawelgema