AHADU RADIO FM 94.3
19.1K subscribers
2.63K photos
146 videos
1 file
3.12K links
አሐዱ ራድዮ 94.3
Your source for top local and international news and analysis.
"Voice of Ethiopian"
የአሐዱ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ በመሆን ወቅታዊና እውነተኛ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ
Download Telegram
በሱዳኑ ጦርነት ግብፅ በጣልቃ ገብነት እየፈፀመችው ያለው ተግባር በአለም አቀፍ የጦር ወንጀል እንደሚያስጠይቅ ተገለፀ።

የሱዳን ወታደራዊ ሃይል በአለማቀፍ ህግ የሚከለከሉ ወታደራዊ እርምጃዎችን እና ጥቃቶችን እየሰነዘረ ነው። በዚህም ባለፉት ጥቂት ቀናት የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ተደብቆባቸዋል በሚል ሽፋን በካርቱም በሚገኙ የአምስት ሀገራት ኤምባሲዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰንዝሮአል፤ እነዚህ የአየር ድጋፍ የሚያደርጉ አውሮፕላኖች ከግብፅ በድጋፍ መልክ የተሰጡ እና ኦፕሬሽኑን እየደገፉ የሚገኙ የግብጽ አውሮፕላኖች ናቸው ተብሏል።

ግብጽ ይህንን ተግባር እየፈጸመች የምትገኘው ሆን ብላ ከሄሜቲ ጎን ተሰልፈው ድጋፍ ያደርጋሉ በሚል የምትጠረጥራቸውን ሀገራት ለማስጠንቀቅ መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል።

በጉዳዩ ላይ አሀዱ ያነጋገራቸው የህግ ባለሞያው አቶ ፋሲል ስለሺ የትኛውም ሀገር በሌላ ሀገር ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባት እንደማይችል የአለም አቀፉ የጦር ህግ እንደሚደነግግና ገልፀው ተግባሩ አለም አቀፍ ወንጀል መሆኑን ገልፀዋል።

ፋሲል :- ሌላኛው አሀዱ ያነጋገራቸው የህግ ባለሞያ አቶ ካፒታል ክብሬ በበኩላቸው ግብፅ በዚህ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷ በአለም አቀፉ ህግ የሚያስጠይቃት መሆኑን አንስተው ጉዳዩ ትኩረትን የሚሹና ኢትዮጵያን ጨምሮ ሁሉንም ሀገራት የሚመለከት በመሆኑ ወደ ያልተፈለገ አቅጣጫ ሳያመራ በፊት ጥንቃቄን ይሻል ብለዋል።

ካፒታል:- በሱዳን በሁለቱ ወታደራዊ ሀይሎች መካከል በተፈጠረው ግጭት በርካቶች ሲሞቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሀገሪቱን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆነ ይታወቃል።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/aha
ሼዶችን እና አረከበ ሱቆችን የመንጠቅ ስራ እየተሰራ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ ለስራ አጥ ወጣቶች ተላልፈው ረጅም ግዜ በስራ ላይ ከሚገኙት የመስሪያ ቦታዎች በተለምዶ የአርከበ ሱቆች የሚባሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ አርከበ ሱቆች የሚባሉት በ1997 እንዲሁም ከዛ በፊት በሊዝ ለወጣቶች ተላልፎ ሲሰጥ በየ አምስት አመቱ ለአዲስ ሰዎች ይተላለፋል ቢባልም አሁንም ድረስ ሳይሸጋገሩ መቆየታቸውን እንዲሁም ለሶስተኛ ሰው ሸጋገሩ ጭምር መኖራቸውን ተከትሎ አሐዱ ስለጉዳዩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮን አነጋግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የስራ ማስፋፍያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰብሃዲን ሱልጣን ለረጅም ዓመታት በግለሰቦች ተይዘው የነበሩ ሼዶች እና አረከበ ሱቆችን ለሁለተኛ እና ሶስተኛ ወገን አሳልፈው የሸጡትን እንዲሁም ውጤታማ ያለሆኑትን በመንጠቅ ለሌሎች የስራ እድል እየፈጠርንበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከ2 ሺህ በላይ ሼደች እየተነጠቁ ለመንግስት እና ለሚመለከታቸው አካላት እንደተሰጡ ገልጸው በፍርድ ቤት ያሉ ጉዳዮችንም የማጥራት ስራ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡ለሁለተኛ እና ሶስተኛ ወገን የሸጠውን አካል በመንጠቅ ለሚመለከተው አካል የማስተላለፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
የመንግስት ሰራተኞችን እና ጡረተኞችን የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ አስቀድሞ ከሚሰሩባቸው ተቋማት መረጃዎችን የማሰባበ,ሰብ ስራ እጠረሰራ እብ,ንደሆነ ተገለፀ፡፡

በአገራችን የጤና መድህን አገልግሎት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ ትቅም እየሰጠ የሚገኝ ቢሆንም የመንግስት ሰራተኞችን እንዲሁም በጡረታ የተገለሉ ዜጎችን እስካሁን ተጠቃሚ ሳያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ከዚህ አመት መጨረሻ ጀምሮ የጤና መድህን አገልግሎት አባል እዲሆኑ የሚያስችል ምዝገባ እንደሚካሄድ የተገፀ ሲሆን በአገራችን ያለው የመንግስት ሰራተኛ እና በጡረታ የተገለሉ ዜጎች ቀጥር ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ መን አይነት ቅድመ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ሲል አሀዱ የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዘመድኩን አበበን አነጋግሯል፡፡
በምላሻቸውም በሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳደሮች ውስት በሚገኙት ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች በኩል በሁሉም የመንግስት ተቋማት ውስጥ በስራ ላይ ያሉ እንዲሁም በጡረታ የተገለሉ ሰራተኞችን መረጃዎችን የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
ሁሉም የጤና ተቋማት የእናቶች ወሊድ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ ዝግጁ ማድረግ እንደሚያስፍልግ ተገለጸ፡፡

በወሊድ ጊዜ የሚከሰተውን የእናቶች ሞት ለመቀነስ በጤና ተቋማት የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል ምን መደረግ አለበት ሲል አሀዱ በቅዱስ ጳውሎስ በሆስፒታሉ የማህጸን እና ጽንስ እስፔሻሊስት ዶክተር ለሚ በላይን ጠይቋል፡፡
በምላሻቸውም ከእናቶች ወሊድ ጋር በተያያዘ በጤና ተቋማት በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግብዓት እጥረትን ጨምሮ ብዙ ምቹ ያልሆኑ ነገሮች እንዳሉም ተናግረዋል፡፡

ጤና ተቋማት የሚሰጡት አገልግሎቶችና የሚወልዱ እናቶች ቁጥር አለመመጣጠን በዘርፉ ካሉት አንዱ ተግዳሮት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የባለሙያዎች የክህሎት ማነስም እንደ ችግር የሚታይ በመሆኑ ተገቢው ስልጠና ሊሰጣቸው እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡ በዘርፉ ያለውን ችግር ለመቅረፍም ሁሉም የጤና ተቋማት የእናቶችን የወሊድ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ ዝግጁ ማድረግ እንደሚያስፍልግ ተናግረዋል፡፡

አስፈላጊውን የጤና ክትትል ካለማድረግ፤ በቶሎ ወደ ጤና ተቋማት አለመሄድን ጨምሮ እናቶችን እና ህጻነትን ለሞት የሚዳርጉ ምክንያቶች ብዙ እንደመሆናቸው እዛ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረዉ የምግብ እርዳታ ይቀጥል ዘንድ ጥሪ ቀረበ፡፡

ወደ ትግራይ ክልል የሚላከዉን እርዳት በህገ ወጥ ዝርፊያ ምክንያት ለማቋርጥ ተገድጃለሁ በዚህም ምክንያት ከዚህ በሁዋላ ምንም አይነት እርዳት ወደ ክልሉ አይገባም ሲል የአለም ምግብ ፕሮግራም እና የአሜሪካዉ ተራድኦ ድርጅት ማስታወቃቸዉ አይዘነጋም፡፡

ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጉዳዩን ሲያጣራ መቆየቱን በመግለፅ ችግሮቹ ፡ በህገ-ወጥ መንገድ ገበያ ላይ መሸጥ እና ስርቆት መሆናቸዉን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ ነገር ግን የምግብ እርዳታዉ በመቋረጡ ለከፍተኛ ሰብአዊ ቀዉስ የተዳረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ እርዳታዉ መልሶ ይቀጥል ዘንድ ጥሪ ማቅረቡን የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሄኖክ መለሰ ለአሃዱ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ችግሮቹ በህግ አግባብ መታየት አለባቸዉ ያሉ ሲሆን መንግስት እና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስፈላጊዉን ማጣራት እና እርምጃ መዉሰድ እንዳለባቸዉ ተገልጻል፡፡ ለሰብአዊ ቀዉሱ ሃላፊነት ያለባቸዉ የአለም ምግብ ፕሮግራም እና የአሜሪካዉ ተራድኦ ድርጅት ብቻ አይደሉም ነገር ግን የእነርሱ እርዳት መቋረጡ ሰብአዊ ቀዉሱ እንዲጨምር አድርጓል ሰለሆነም በተቻለ መጠን መልሶ የማስጀመር ስራ መሰራት ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ወስጥ በቴክኖሎጂ ክህሎታቸው የላቁ ወጣቶችን ለማፍራት ተኩረት አድረጎ እየሰራ ነው ተባለ፡፡

በሀገር አቀፍ ደራጃ ተግባራዊ በሚሆን የቴክኖሎጂ ክህሎት ማጎልበቻ ማእከል አማካኝነት በዘርፉ የበቁ ወጣቶች እንዲወጡ ለማስቻል አሜሪካ በኢምባሲዋ በኩል ሰፋፊ ስረዎችን በመስራት ላይ እንደምትገኝ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ለሚገኙ ወጣት ተማሪዎች የተለያዩ መሰረታዊ የክህሎት እውቀቶችን እንዲያገኙ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ በአሜሪካን ሀገር ያሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የኢትዮጵያ ተማሪዎችን የትምህርት እድል እንዲያገኙ እና በቴክኖሎጂም እንዲበቁ በማገዝምላይ ናቸው ብለዋል፡፡
በተጨማሪም መንግስት ለሚያክናውናቸው ቴክኖሎጂ ነክ እና ሌሎች አዳዲስ የትምህርትና የስልጠና ፕሮግራሞች ላይ የአሜሪካን መንግስት ድጋፉን እንደሚያስቀጥል ነው የጠቆሙት፡፡›
በተለይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በሌሎች የዲጂታል መሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ላይ በከፍተኛ መጠን እገዛ እየተደረገ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በቴክኖሎጂ መሰረት ላይ እገዛ በማድረግ ሰፋፊ ስራዎች እንዲወጡ በማድረግ ረገድም አሜሪካ ትኩረት አድርጋ እንደምትሰራ አክለዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
የእስራኤል ጦር በፍልስጤም ዌስት ባንክ ባደረሰው ጥቃት ሶስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡

በትላንትናው እለት የእስራኤል ጦር በዌስት ባንክ የሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ላይ በፈጸመው ድንገተኛ ጥቃት ሶስት ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጤም ጤና ሚንስቴር አስታውቋል፡፡
በጥቃቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል ወታደሮች መሳተፋቸው ተነግሯል፡፡

የእስራኤል ሀይሎች የመጠለያ ካፑን መግቢያ በቡልዶዘር መዝጋታቸውና በትንሹ ሰባት ቤቶችን ማፍረሳቸው ታዉቋል፡፡
የእስራኤል ጦር በበኩሉ በትጥቅ እንቅስቃሴና ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የተጠረጠሩ ሶስት ፍልስጤማውያንን ማሰሩን ሲገልጽ ስለግድያው ምንም አይነት አስተያየት አልሰጠም ተብሏል፡፡
የትላንቱ የጥቃት እርምጃ የተወሰደው እንድ የእስራኤል ወታደር ላይ ጉዳት ከደረሰ የተሽከርካሪ ጥቃት በኋላ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ዘገባው፡-የአልጄዚራ ነው፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
ከንግድ ቤቶች ፈረሳ ጋር በተያያዘ አካል ጉዳተኞች ያቀረቡትን ቅሬታ ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገረ መሆኑ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮመሽን አስታውቋል፡፡

ለኢሰመኮ የአካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን መብቶች የስራ ክፍል ዳይሬክተር እሜቴ አቶምሳ ግንቦት 14 ቀን ቁጥራቸው ከ160 በላይ የሚሆኑ አይነ ስውራን እንዲሁም መስማት የተሳናቸው አካል ጉዳተኞች ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት በአካል ተገኝተው ነበር፡፡
ያለአግባብ የንግድ ቤቶቻችን ፈርሰውብናል፣ ንብረታችንም ተወርሶብናል፣ ከዛም በተጨማሪ ቅሬታችንን ለማቅረብ ወደ መንግስት ተቋማት ስንሄድ ማዋከብ እና እንግልት ደርሶብናል ሲሉ ቅሬታ ማቅረባቸውን ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሯ እንደገለጹት ኮሚሽኑ ቅሬታውን እንደተቀበለ ወዲያው ከሚለከታቸው አካላት ጋር መነጋገር ጀምሯል ያሉ ሲሆን አያይዘውም ጉዳዩን በሁለት ከፍለን እያየነው ነው ብለዋል፡፡
በግለሰብ ደረጃ በግል እንግልት ደርሶብናል ያሉትን በግል እያየን ነው ያሉ ሲሆን እንዲሁም ቅሬታቸውን አንድ ላይ ያቀረቡ አካል ጉዳተኞችንም ጉዳያቸው እንዴት ይታያል ፣ ፈረሳው ህጋዊ ነው ወይ፣ ከሆነስ የአካሄድ ሁኔታው ምን ይመስላል በሚል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገርን ነው ሲሉ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
ከምእራብ ትግራይ ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎች ወደቀያቸው እንዲመለሱ አለመደረጉን ተከትሎ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ህዝባዊ ሰልፎች መካሄቸው ተገለጸ፡፡

በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ሲካሄድ የነበረውን ጦርነት ተከትሎ ብዙ ዜጎች ከምእራባዊ ትግራይ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሲሆን በሰላም ስምምነቱ መሰረት በተገቢው እስካሁን ወደ አካባቢያቸው መመለስ አልቻሉም ይህንን ተከትሎም በትላንትናው እለት በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉን የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል አቶ ሀድጉ ገ/ወልድ አስታውቀዋል፡፡

በዋናነት ሰልፉ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ አካባቢያቸው ከመመለስ አኳያ የፌደራሉ መንግስት በሚፈለገው ልክ ትኩረት እንዳልሰጠው አለማቀፍ ተቋማት እንዲያውቁት ለማድረግ ያለመ ሲሆን በተጨማሪም በቅርቡ አለማቀፍ እርዳታ አቅራቢ ተቋማት በክለሉ ያቋረጡትን እርዳታ እንዲቀጥሉ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ ነው ብለዋል፡፡
ከአለማቀፍ ረጂ ተቋማት በኩል ድጋፍ ከቀረበ 6 ወራት እንዳለፉ ገልፀው ይህም አግባብነት እንደሌለው እና የፌደራል መንግስትን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት ክልሉ አሁን ላይ ያለበትን ሁኔታ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠይቋል፡፡

አያይዘወም መቀሌ፣ሽሬ፣አክሱም፣አድዋ ፣ሽራሮ እና ሌሎች የክልሉ ከተሞችላይ ሰልፉ የተካሄደ ሲሆን በአጠቃላይ ከ1 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በሰልፉ ላይእንደተሳተፉ ገልፀዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
በብልሹ አሰራር እና በሙስና ላይ የተሰማሩ 153 ግለስቦች ተጠያቂ መደረጋቸዉ ተገለፀ፡፡

ባለፉት 9 ወራት በተለያዩ ህገወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ 153 ግለስቦችን ተጠያቂ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡
ገንዝብ በመቀበል ያለ መሸኛ እና ያለ ባለቤቱ ፈቃድ በነዋሪዎች ቅፅ ላይ በመመዝገብ የመታወቂያ መስጠት፣ ለውጭ አገር ዜጋ መታወቂያ መስጠት፣ ስደተኞች በውክልና ጋብቻ እንዲፈፅሙ በማድረግ ማስረጃ መስጠት ተጠቃሽ ችግሮች መሆናቸውን የኤጀንሲዉ አማካሪ አቶ መላክ መኮንን ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡
የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋት የማንዋል አሰራርን ሙሉ በሙሉ ለማቆም በቴክኖሎጂ እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን አስታዉቀዋል፡፡
አሁን ላይ በተለያዩ ወረዳዎች ከተቋሙ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው ደላሎች ለተገልጋዩ ህብረተሰብ በክፍያ ሰልፍ የሚይዙ እንዳሉ እንደተደረሰበት ገልፀዋል፡፡
ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከሚረዱ መንገዶች መካከል አንዱ በቴክኖሎጂ አገልግሎትን መሰጠት ሲሆን አስፈላጊ በመሆኑ ቀድመዉ አገልግሎት ከሚሰጡት በተጨማሪ ካሉት 118 ወረዳዎች ዉስጥ በ104ቱ በቴክኖሎጂ ታግዘዉ እየሰጡ መሆናቸዉን አክለዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
ከዘጠኝ መቶ ሺ በላይ ሱዳናዊያን ጦርነቱን ሸሽተው በቻድ መጠለላቸው ተነገረ፡፡

በቻድ የሱዳናዊያን ስደተኞች ቁጥር ከሶስት ቀናት በፊት ሰባ ስድስት ሺ እንደሚደርስ የተገመተ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ዘጠኝ መቶ ሺ መድረሱን በተባበሩት መንግስታት ደርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አሳውቋል፡፡

ከነዚህ በተንቀሳቃሽ መጠለያ ማዕከላት ከተሰበሰቡት ስደተኞች ውስጥ ዘጠና በመቶ የሚሆኑት ሴቶችና ህጻናት ናቸው ተብሏል፡፡
በቅርቡ ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው ክረምትም ለስደተኞቹ እርዳታን ለማቅረብ አዳጋች እንደሚያደርገውም ተዘግቧል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በያዝነው ግንቦት ወር በሱዳን ውስጥ ላሉና ጦርነቱን ሽሽት ለተሰደዱ ዜጎች እርዳታ የሚውል ሶስት ቢሊየን ዶላርም መመደቡ ተጠቁሟል፡፡
ዘገባው፡- የአፍሪካ ኒውስ ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
አሜሪካ የዋግነር ቡድን ለጦር አቅርቦት ዝውውር ማሊን አይኑ ውስጥ እንዳስገባ አሳወቀች፡፡

የዋግነር ሀይል በዩክሬን እየተካሄደ ላለው ጦርነት የሚውል የጦር መሳሪያ ዝውውር ማሊን መሸጋገሪያ ለማድረግ ሙከራ እያደረገ እንደሆነ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንሰቴር አስታውቋል፡፡
ከሩሲያ መደበኛ ጦር ጎን የተሰለፈው የዋግነር ቡድን የሀሰት ሰነዶችን በመጠቀም የጦር መሳሪያ በማሊ በኩል ለማሸጋገር እየሞከረ እንደሆነ የገለጹት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ናቸው ተብሏል፡፡

ቡድኑ ከውጭ ሀገር የመሳሪያ አቅራቢዎች የወታደራዊ መሳሪያዎችን ለመግዛት ሙከራ ሲያደርግ እንደቆየና ማሊን ሶስተኛ ወገን ተዋናይና መሸጋገሪያ እንደሚያደርግ ፍንጮች ደርሰውናል ነው ያሉት፡፡
የመሳሪያ ዝውውሩ ስለመደረጉ እስካሁን ክትትል እያደረግን ነው የዋሽንግተን መንግስትም የዋግነርን ወታደራዊ ዘመቻዎች የደገፈ ማንኛውም አካል በየትኛውም አህጉር ማዕቀብ ይጣልበታል ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡
ዘገባው፡- የአልጄዚራ ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
የሩሲያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሳኡዲ አረብያን ጎብኝተዋል፡፡

በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለባቸው የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትሩ ከሳኡዲ አረብያ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል ነው የተባለው፡፡ ይህም የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ከጎበኙ ከቀናት በኋላ መሆኑ ታውቋል፡፡

የሚንስትሩ ጉብኝት ከዩክሬኑ ጦርነት ባሻገር ሳኡዲ አረብያ እና የገልፍ አረብ ሀገራት ከሞስኮ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ዘላቂ እንዳደረጉ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡
ሁለቱ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትሮች የጸጥታ ጉዳይ ላይ ትብብራቸውን በሚያጠናክሩበት መንገድ እና ሌሎችም የሀገራቱን የጋራ ፍላጎት በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የሳኡዲ አረብያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡
የሩሲያው የሀገር ውስጥ ሚንስትር ሀገራቸው በሶሪያና ዩክሬን የምታደርገውን እንቅስቃሴ ተከትሎ ነበር በፈረንጆች 2018 ጀምሮ አሜሪካ ማዕቀብ የጣለችባቸው ተብሏል፡፡
ዘገባው፡- የአልጄዚራ ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/ 
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
የታጠቁ ሀይሎችም ቢሆኑ መሳሪያቸውን አስቀምጠው ለመወያየት ፍቃደኛ ከሆኑ ዝግጁነት መኖሩን ምክክር ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ለአሐዱ እንደገለፁት በድርድር ሂደት የመሳተፍም ሆነ የፖለቲካ ሽግግርን የማስረፅ ግዴታም ሆነ ሀላፊነት የለዉም ያሉ ሲሆን የትኛዉንም የማህበረሰብ ክፍል የታጠቁ ሀይሎችም ቢሆኑ እንኳን መሳሪያችንን አስቀምጠን እንወያይ ካሉ ግን በምክክር ኮሚሽኑ ስልጣንና ሀላፊነት ልክ የማወያየት ሀሳብ የመቀበልና ወደ መግባባት የማምጣት ዝግጁነት አለ ፤ይህም የኮሚሽኑን ገለልተኝነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡

ነገር ግን አሁንም ድረስ የኮሚሽኑን ተግባርና ሀላፊነት ያልተረዱ አካላት በሚፈጠሩ ችግሮች ሁሉ ጣልቃ እንዲገባ የሚጠይቁ አካላት ቢኖሩም ፤ኮሚሽኑ ተቋቋመበት ዋና አላማ ማወያየት እና ሰላም ማምጣት በመሆኑ የታጠቁ፤ ተቃዋሚ ፤ገዢ ፓርቲ ሳይባል ሁሉንም ለማወያየት ዝግጁ ነት አለ ብለዋል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ባሳለፍነዉ ሳምንት በተለያዩ ክልሎች አጀንዳ ለማሰባሰብ የሚያግዘዉን ስራ ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለፈታኞች ከሚከፍለው ክፍያ ጋር ተያይዞ የህግ ጥሰት እየፈጸመ ነው የሚል ወቀሳ ቀርቦበታል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ አራሬ ሞሲሳ እንደገለጹት በምክር ቤት የጸደቀው በጀት በህግና መመሪያ እየተመራ ካለመሆኑም በላይ የህዝብ ገንዘብ እየባከነ ነው፡፡
በተለይም ከፈታኞች ክፍያ ጋር በተያያዘ የሚከፈላቸው ገንዘብ ከመጠን ያነሰ ወይም ከመጠን ያለፈ እየሆነ ያለው በሚመለከተው አካል ተገቢው ተመን ስላልወጣለት ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢዋ ክፍያዎች በግለሰቦችና በየደረጃው ባሉ አመራሮች ፍቃድና ፍላጎት ላይ ብቻ ተመስርቶ እየተከፈለ በመሆኑ ከፍተኛ የህግ ጥሰት እየተፈጸመ ነው ብለዋል፡፡

መመሪያዎች ተፈጻሚነት ሊኖራቸውና ውሳኔዎችም በግለሰቦች ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ መሆን እንደሌለባቸውም ጠቁመዋል፡፡
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ታደሰ በበኩላቸው መሰል ችግሮች እንዳሉ በማመን በተያዘው በጀት አመት በተለይም ካለፉት 6 ወራት ወዲህ ያሉት እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ማሻሻያና መመሪያ ተኮር እንደሆኑ ገልጸው በዘንድሮው አመት በጀት መዝጊያ ላይ የሚኖረው የኦዲት ግኝት ይህን አመላካች ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24
ዝቅተኛ የደሞዝ ወለልን ለመወሰን መንግስት ጥናት እያስጠና መሆኑ ተገለፀ፡፡

በ2011ዓ.ም በወጣዉ አዋጅ መሰረት ዝቅተኛ የደሞዝ ወለልን የሚወስን ቦርድ እንደሚቋቋም ይገልፃል፡፡
አሐዱም ዝቅተኛ የደሞዝ ወለልን ለመወሰን ምን አይነት ስራዎች እየተሰሩ ነዉ ሲል የስራ እና ክህሎት ሚንስቴር የኢንዱስትሪ ግንኙነት እና የሁነቶች ቁጥጥር ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ተካልኝ አያሌዉ ጠይቁዋል፡፡
ዝቅተኛ የደሞዝ ወለልን ለመወሰን መንግስት ጥናት እያስጠና መሆኑን ገልፀዉ ጉዳዩ ዉስብስብ በመሆኑ ጥናት መሰረት ተደርጎ ችግሩን ለመፍታት እየተሠራ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የባለሙያዎች ቡድንን በማቋቋም ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል የሚወሰንበትን መነሻ ጥናት የሚያጠና ቡድን መቋቋሙን እና በአሰሪዎች እና ሰራተኞች የሚነሱ የሥራ ክርክሮች በማህበራዊ ምክክር እና በሌሎች አማራጮች እልባት እንዲያገኙ ስርአት እየተዘረጋ መሆኑን አስታዉቀዋል፡፡
የቤት ሰራተኞችን በተመለከተ የህግ ሽፋን ለማዉጣት የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸዉን አክለዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24