🔴አጫጭር ዜናዎች
1፤ በትግራዩ ጦርነት ከፍተኛ ሚና አላቸው በተባሉ 62 ግለሰቦች ላይ የሽብር ክስ መዝገብ መክፈቱን ዓቃቤ ሕግ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። በክሱ የአማጺው ሕወሃት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካዔልን እና ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም የክልሉ ካቢኔ አባላት ግንባር ቀደም ተከሳሾች ሆነዋል። በሕወሃት ትጥቅ ትግል ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው የኢፈርት አመራሮች፣ የግልና መንግሥት ተቋማት፣ የክልሉ ምርጫ ኮሚሽንና በምርጫው የተሳተፉ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የቀድሞ የሕወሃት ከፍተኛ አመራሮች ጭምር በክሱ ተካተዋል። በመዝገቡ የተጠቀሱት ወንጀሎች ሕጋዊውን የክልሉን መንግሥት በሕገወጥ ምርጫ በመለወጥ፣ የፌደራሉን መንግሥት በኃይል ለመለወጥ መሞከር እና በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት የመፈጸም ወንጀሎች ሲሆኑ፣ ተከሳሾቹ ሐምሌ 26 እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ አዟል።
2፤ በትግራይ ክልል በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ልጆች ያሏቸው ወላጆች ዛሬ በአዲስ አበባ በተመድ ጽሕፈት ቤት ፊት ለፊት አቤቱታ ማሰማታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። ተመድ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ወላጆች ድምጻቸውን አሰምተዋል። መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በ10 አውቶብሶች ወደ ትውልድ ቦታቸው መመለስ የሚፈልጉ ተማሪዎችን ከተመድ ታዛቢዎች ጋር ወደ አፋር ክልል ቢያሻግርም፣ የአፋር ክልል ልዩ ኃይሎች አውቶብሶቹን አናሳልፍም ማለታቸውንና ቀሪዎቹን ተማሪዎች በበጀት እጥረት ሳቢያ መቀለብ እንደማይችል ከትናንት ወዲያ መግለጹ ይታወሳል።
3፤ አማጺው ሕወሃት በትግራይ ክልል የማይ ዓይኒ እና አዲ ሐሩሽ የኤርትራዊያን ስደተኛ መጠለያዎችን ለወታደራዊ አገልግሎት እየተጠቀሙባቸው እንደሆነ የስደተኞች እና ስደት ተመላሾች ኤጀንሲ በድረገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የሕወሃት ተዋጊዎች ስደተኛ ጣቢያዎቹን ከያዙ ወዲህ 6 ስደተኞች እንደተገደሉ፣ በመጠለያዎቹ ከባድ መሳሪያ እንደተተከለ፣ የኤጀንሲውና የዓለም ምግብ ፕሮግራም ንብረቶች እንደተዘረፉ፣ ስደተኞች የገንዘብ መዋጮ እንደሚጠየቁ እና ከመጠለያዎቹ መውጣት እንደተከለከሉ ኤጀንሲው አመልክቷል። በስደተኞቹ ደኅንነት ላይ ከባድ አደጋ እንደተደቀነ የተመድ ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነርም የገለጸ ሲሆን፣ ሕወሃት በበኩሉ በስደተኞች ላይ ደርሷል የሚባለው የመብት ጥሰት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ በቀደም ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።
4፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በአዲስ አበባ ከተማ በትግራይ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ነው ያለውን ጅምላ እስር ባስቸኳይ እንዲያስቆሙ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በትዊተር ገጹ ጥሪ ጠይቋል። እስካሁን በጅምላ ታፍሰው እስር ላይ ካሉት ግለሰቦች ላይ መንግሥት በሕጉ መሠረት የወንጀል ክስ የመሠረተባቸው ስለመኖራቸው መረጃ የለኝም- ብሏል አምነስቲ። ፖሊስ መታወቂያ እያየ በብሄሩ ተወላጆች ላይ ይፈጸማል የተባለው የዘፈቀደ እስር እንዲቆም አሁኑኑ ተግባራዊ ርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ አምነስቲ አክሎ አሳስቧል።
5፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 24 የሥራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ውለው የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ የክልሉ መንግሥት ማስታወቁን ዶቸቨለ ከሥፍራው ዘግቧል። ፖሊስ በሥራ ሃላፊዎቹ ላይ ምርመራ የሚያደርገው፣ ሃላፊዎቹ በክልሉ ሰላም እና ጸጥታን ለማስፈን የተጣለባቸውን ሃላፊነት በአግባቡ አልተወጡም በሚል ነው። በክልሉ በሰላማዊው ሕዝብ ላይ የኃይል ጥቃት ሲፈጽሙ የነበሩ ሸማቂዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጧል።
6፤ አፍሪካ ኅብረት የማጓጓዣ ወጭ ለከፈሉ 27 የአፍሪካ ሀገራት ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተባለውን 6 ሚሊዮን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጠብታዎችን ሊያጓጉዝ እንደሆነ መናገሩን ሲኤንኤን ዘግቧል። 18 ሀገራት እስከ ነሐሴ የማጓጓዣ ክፍያ ለመፈጸም ከዓለም ባንክና ሌሎች አበዳሪዎች ጋር ስምምነት ላይ እየደረሱ መሆኑ ተገልጧል። የክትባቱ አቅርቦት የሚጠናቀቀው በቀጣዩ ዓመት መጨረሻ ነው። የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ልዑክ ስትራይቭ ማሲይዋ ግን ለአፍሪካ ዘላቂ መፍትሄ የሚሆነው ክትባቱ በአፍሪካ ምድር ሲመረት ብቻ መሆኑን በመጥቀስ ለዓለማቀፍ ክትባት አምራች ኩባንያዎች ተማጽኖ አቅርበዋል።
7፤ በተመድ ጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ተለዋጭ አባል የሆኑ የአፍሪካ እና ካሪቢያን ሀገሮች በኬንያ ናይሮቢ ስብሰባ እንደተቀመጡ ዴይሊ ኔሽን አሰነብቧል፡፡ በአፍሪካ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ የጋራ አጀንዳ ለመንደፍ እና በምክር ቤቱ የጋራ አቋም ለማንጸባረቅ የተሰበሰቡት፣ ኬንያ፣ ኒጀር፣ ቱኒዝያ፣ ግሪናዳ እና ሴንት ቪንሴንት ናቸው። የጸጥታው ምክር ቤት የሕዳሴ ግድብ ውዝግብን ለአፍሪካ ኅብረት እንዲተወው በተለይ ሦስቱ አፍሪካዊያን የምክር ቤቱ አባላት በቅርቡ የጋራ አቋም ማንጸባረቃቸው ይታወሳል።
#አድስዜና
ዋዜማ ራዲዮ

🔴🔴አጫጭር ዜናዎች
1፤ 324 የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲው ባዘጋጀላቸው አውቶብሶች በአፋር ክልል ዞን ሁለት አብዓላ በተባለ ቦታ በኩል ከአፋር ክልል ዋና ከተማ ሠመራ እንደገቡ ተማሪዎቹ ለዋዜማ ተናግረዋል። ተማሪዎቹ ሠመራ የገቡት በመከላከያ ሠራዊት ታጅበው ነው። ተማሪዎቹ ዛሬ ማምሻውን ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደተሸኙ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ለዋዜማ ተናግረዋል። በተያያዘ 45 የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአውቶብስ ራያ ዞን ቆቦ ከተማ የገቡ ሲሆን፣ ሆኖም በቅርብ ርቀት ሮቢት ከተማ ላይ የተኩስ ልውውጥ በመኖሩ ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ እንዳያልፉ የሕወሃት ተዋጊዎች አግደዋቸው እንደነበር ተማሪዎቹ ለዋዜማ ተናግረዋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም። የአዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ግን እስካሁን ማወቅ አልተቻለም።
2፤ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች ሕወሃት በሀገሪቱ ሕልውና ላይ የከፈተውን ጦርነት ለመመከት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን እንዲቆሙ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ ማድረጋቸውን የከተማዋ ፕሬስ ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። በሕወሃት መሪነት በኢትዮጵያ ላይ የውክልና ጦርነት እንደተከፈተባት የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ፣ እስካሁን መከለከያ ሠራዊቱን ያልተቀላቀሉ ወጣቶች በፍጥነት እንዲቀላቀሉ ጠይቀዋል።
3፤ ወደ ቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያመሩ አውሮፕላኖች በአየር ማረፊያው አከባቢ በተፈጠረ ጭጋጋማ አየር ጠባይ ሳቢያ ማረፍ እንዳልቻሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ለጥንቃቄ ሲባል አውሮፕላኖቹ በአቅራቢያ በሚገኙ አውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ ማድረጉን ገልጧል። አየር ጠባዩ ሲስተካከል ሁኔታው ወደነበረበት እንደሚመለስ የጠቆመው አየር መንገዱ፣ ለጊዜው ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞችን እና አየር መንገዶችን ይቅርታ ጠይቋል። የተጠቀማቸውን አማራጭ አውሮፕላን ማረፊያዎች ግን አየር መንገዱ አልጠቀሰም። ዛሬ በርካታ አውሮፕላኖች ወደ ቦሌ ሲበሩ ውለዋል።
4፤ ማንኛውም በኢትዮጵያ አየር ክልል የሚበሩ አውሮፕላኖች መንግሥት ያወጣውን አዲስ የበረራ መመሪያ እንዲያከብሩ የመንግሥት የወቅታዊ ሁኔታዎች መረጃ ማጣሪያ በትዊተር ገጹ አሳስቧል። የአውሮፕላን አብራሪዎች እና የበረራ ኦፕሬተሮች መንግሥት ያወጣውን አዲስ የበረራ መረጃ ማሳወቂያ መመሪያ የሚጥሱ ከሆነ፣ ለሚደርሰው ጉዳት ሁሉ ሃላፊነት ይወስዳሉ ሲል መረጃ ማጣሪያው አስጠንቅቋል። ወደ ትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ዕርዳታ በረራ ለሚያደርጉ ረድዔት ድርጅቶች መንግሥት ባለፈው ሰኔ 23 አዲስ የበረራ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል።
5፤ በማይጠብሪ፣ በዋግ ኽምራ ልዩ ዞን በአበርገሌ ወረዳ እና በራያ አላማጣ አካባቢ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና ሚሊሻዎች በአማጺው የሕወሃት ተዋጊዎች ላይ በርካታ ድሎችን እየተጎናጸፉ እንደሆነ የአማራ ክልል ኮምንኬሽን ሃላፊ ግዛቸው ሙሉነህን ጠቅሶ የክልሉ መገናኛ ብዙኀን ኮርፖሬሽን ማምሻውን ዘግቧል። መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ሕወሃት ከሚነዛው ፕሮፓጋንዳ የተለየ እንደሆነ ሃላፊው አመልክተዋል። ቀደም ሲል በሕወሃት ተዋጊዎች ተይዘው ሰሞኑን የክልሉ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ በወሰደው መልሶ ማጥቃት ያስለቀቃቸው አካባቢዎች ስለመኖራቸው ግን ዘገባው በስም አልጠቀሰም።
#adszena #አድስዜና

🔴በዛሬው እለት የወጡ አጫጭር ዜናዎች
1፤ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ለተረጅዎች ያስቀመጠው የምግብ ዕርዳታ በቀጣዩ ዐርብ ይሟጠጣል ሲሉ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊ በትዊተር ገጻቸው አስጠንቅቀዋል። ሁሉንም ተረጅዎች ለመመገብ በየቀኑ 100 ዕርዳታ ጫኝ ካሚዮኖች ወደ ክልሉ መግባት እንዳለባቸው የገለጡት ዳይሬክተሩ፣ ባሁኑ ሰዓት ወደ ክልሉ የሚያስገባው መንገድ በመዘጋቱ 170 ዕርዳታ የጫኑ ካሚዮኖች አፋር ክልል ውስጥ ቆመው እንደሚገኙ ገልጠዋል። ሰዎች እየተራቡ ስለሆነ፣ እነዚህ ካሚዮኖቹ አሁኑኑ ወደ ትግራይ እንዲገቡ ሊፈቀድላቸው ይገባል በማለትም ሃላፊው አሳስበዋል።
2፤ መንግሥት በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ዕርዳታ ያወጀው ተኩስ አቁም በሕወሃት ትንኮሳ እየተደናቀፈ መሆኑን የመንግሥት ወቅታዊ ሁኔታዎች መረጃ ማጣሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ሕወሃት በአፋር ክልል በኩል የሚያደርገውን ትንኮሳ እንዲያቆም እና የሰብዓዊ ዕርዳታ መስመሩን እንዲከፍት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ዓለማቀፍ ረድዔት ድርጅቶች ግፊት እንዲያደርጉ መረጃ ማጣሪያው ጠይቋል።
3፤ በደቡብ ምዕራብ ትግራይ በማይዓይኒ እና አዲ ሐሩሽ ስደተኛ መጠለያዎች 24 ሺህ ኤርትራዊያን ስደተኞች በአካባቢው ባለው ውጊያ ሳቢያ፣ ከሰብዓዊ ዕርዳታ ተነጥለው እንደሚገኙ የተመድ ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ላለፉት 2 ሳምንታት መጠለያዎቹ ለኮሚሽኑ ተደራሽ እንዳልሆኑ፣ ንጹህ መጠጥ ውሃ እንዳለቀባቸው፣ ምንም ዓይነት የጤና አገልግሎት እንደማያገኙ እና የምግብ ዕርዳታ ካገኙ አንድ ወር እንዳለፋቸው ኮሚሽኑ ገልጧል። ሰሞኑን ከማይዓይኒ መጠለያ አንድ ስደተኛ በታጣቂዎች እንደተገደለ ተዓማኒ መረጃ ደርሶኛል ያለው ኮሚሽኑ፣ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች የስደተኞችን ዓለማቀፍ መብቶች እንዲያከብሩና የዕርዳታ መስመሮችን እንዲከፍቱ ተማጽኗል። ኮሚሽኑ ለስደተኞች ያዘጋጀው ሰብዓዊ ዕርዳታ ከአንድ ወር በላይ ከአፋር ክልል ሠመራ ከተማ መውጣት አልቻለም።
4፤ በአፋር ክልል በሚገኙ የኤርትራዊያን ስደተኛ መጠለያዎች አቅራቢያ ውጊያ እየተካሄደ ስለመሆኑ መረጃ እንደደረሰው የተመድ ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዛሬ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ግጭቱ እየተካሄደ ያለው፣ ከትግራይ ክልል ውጭ ያሉ 55 ሺህ ኤርትራዊያን ስደተኞች በተጠለሉባቸው መጠለያዎች አቅራቢያ እንደሆነ ኮሚሽኑ ገልጧል። በግጭቱ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የአፋር ክልል ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ኮሚሽኑ አክሎ ገልጧል።
5፤ መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ከአዲስ አበባ ከተማ ለተውጣጡ በጎ ፍቃደኛ ዘማች ወጣቶች እና የሕክምና ባለሙያዎች ዛሬ በመስቀል አደባባይ አሸኛኘት እንደተደረገላቸው የከተማዋ አስተዳደር ፕሬስ ጽሕፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። በሽኝቱ ላይ 3 ሺህ ያህል ወጣቶች የተገኙ ሲሆን፣ ዘማቾቹ ወደየትኛው ማሰልጠኛ እንደሚከቱ ግን አልገለጸም። ከአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና ከሁሉም ክልሎች በጎ ፍቃደኛ ዘማቾች ሕወሃት በሀገሪቱ ሕልውና ላይ የደቀነውን አደጋ ለመመከት ወደተለያዩ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች እየገቡ እንደሆነ የሀገር ውስጥ ዜና ምንጮች በመዘገብ ላይ ናቸው። መንግሥት ለውጊያው ስንት በጎ ፍቃደኛ ዘማቾችን እንደሚፈልግ እስካሁን አልገለጸም።
6፤ ፖሊስ ከኢትዮ ፎረም እና አውሎ ሜዲያ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኀን ያሰርኳቸውን 14 ጋዜጠኞች እና ሠራተኞች በቦታ ጥበት ሳቢያ ወደ አፋር ክልል አዋሽ ሰባት እስር ቤት አዛውራያለሁ ሲል ለፍርድ ቤት መናገሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ፖሊስ ታሳሪዎቹን ባለፈው ሰኔ 19 በክልሉ ፈንታሌ ወረዳ ፍርድ ቤት አቅርቦ እስከ ሐምሌ 26 የምርመራ ጊዜ ማስፈቀዱን የተናገረ ሲሆን፣ ችሎቱ ግን የምርመራ ፍቃድ የተጠየቀበት ሰነድ እንዲቀርብለት ለቀጣዩ ሐሙስ ቀጠሮ ሰጥቷል። ታሳሪዎቹ ብሄረሰቦችን ለማጋጨት፣ ለጦርነት ቅስቀሳ እና ሕገመንግሥቱን በኃይል ለመናድ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ውጭ ሀገር ካሉ ግብረ አበሮቻቸው ጋር ሴራ አሲረዋል በሚል ነው ፖሊስ ጠረጠርኳቸው ያለው።
7፤ ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር እያደረገችው ያለው የወታደራዊ ቴክኒክ ትብብር ከሕዳሴ ግድብ ጋር እንደሚያያዝ ተደርጎ የሚሰራጩ ዘጋባዎችን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኢምባሲ ባሰራጨው መግለጫ አስተባብሏል። የሁለቱ ሀገሮች ወታደራዊ ትብብር በማንም ላይ ስጋት የሚፈጥር እንዳልሆነ የገለጠው የኢምባሲው መግለጫ፣ ሩሲያ ከሱዳን እና ግብጽ ጋር ጭምር ተመሳሳይ የትብብር ስምምነቶች እንዳሏት ገልጧል። የግድቡ ውዝግብ የሚፈታው በሦስትዮሹ የመርሆዎች መግለጫ እና በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ እንደሆነ፣ በኅብረቱ ማዕቀፍ ስር አስማሚ መፍትሄ የመገኘት እድሉም ገና እንዳልተሟጠጠ እና የግድቡን ግንባታ ፖለቲካዊ ገጽታ መስጠት እንደማይጠቅም ኢምባሲው ገልጧል።
8፤ ወደ አውሮፓ በጀልባ በመሻገር ላይ የነበሩ 57 አፍሪካዊያን ፍልሰተኞች በሊቢያ ባሕር ጠረፍ በሜድትራኒያን ባሕር ሰጥመሙ እንደሞቱ ዓለማቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ባሕር ሰጥመው ከሞቱት ፍልሰተኞች መካከል 20ዎቹ ሴቶች ሲሆኑ፣ ሁለቱ ደሞ ሕጻናት ናቸው ተብሏል። ከጥር ወር ወዲህ በሊቢያ በኩል ባሕር ሰጥመው የሞቱት ፍልሰተኞች ብዛት 970 ደርሷል።

🔴 በዚህ ድጅታል ዘመን (Digital World) በየእለቱ ምን እየተከሰተ እንደሆነ ለማወቅ ትክክለኛ አማራጩ ትክክለኛ የመረጃ ምንጮችን መከተል ነው ! ከዚህም አንዱ #አድስዜና ሲሆን፣ በቴሌግራም ቀለል ባለው የፅሁፍ መረጃ ሀላፊነት በተሞላበት ፣ ለማንኛውም ወገን ያላደላ ፣ ትክክለኛ እና ለህዝብ ጠቃሚ ያልናቸውን ወቅታዊ እና አጫጭር መረጃዎች ከተለያዩ ታማኝ ምንጮች በማሰባሰብ ከሀገር ቤት እስከ አለም ዙሪያ ምንአለ የሚለውን በየእለቱ ወደ እናንተ ውድ ተከታታዮቻችን እናደርሳለን! ስለሆነም #አድስዜና ምንም እንኳን ትንሽ ተከታይ ቢኖረውም ጥርት ያለ መረጃ በማድረስ በቀጣይ የአባሎቹን ቁጥር ከፍ እያደረገ እንደሚሄድ ተስፋ እያደረገ ፣ ከዚህም የበለጠ እንዲንሰራና የትልቅ መረጃ ቋት ይሆንም ዘንድ የእናንተ ክቡራን ተከታታዮቻችን ቀና አስተያየት ያበረታናልና ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት
ከታች ባለው #comment መስጫ ላይ አስፍሩልን ለወዳጅ ዘመድም በማጋራት የበለጠ አጠንክሩን!
@adszena ቴሌግራም የቻናላችን ሊንክ ነው!!
ሰላም ለሀገራችን! መልካም ጊዜ ለሁላችን!

አድስዜና - adszena
ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ዜናዎችንና የተለያዩ መረጃዎችን በየዕለቱ እናቀርባለን። ምንጊዜም #አድስዜና ከማንም ያልወገኑ፣ ሚዛናዊ፣ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ወደ እናንተ ክቡራን ተከታታዮቻችን ማቅረቡን እንቀጥላል።
አብራችሁን ሁኑ!

Forwarded from አድስ ዜና (MAK story)
በዚህ ድጅታል ዘመን(Digital World) በየእለቱ ምን እየተከሰተ እንደሆነ ለማወቅ ትክክለኛው አማራጩ ትክክለኛ የመረጃ ምንጮችን መከተል ነው ! ከዚህም አንዱ #አድስዜና ቀለል ባለው የፅሁፍ መረጃ ሀላፊነት በተሞላበት ፣ ለማንኛውም ወገን ያላደላ ፣ ትክክለኛ እና ለህዝብ ጠቃሚ ያልናቸውን ወቅታዊ እና አጫጭር መረጃዎችን ከተለያዩ ታማኝ ምንጮች በማሰባሰብ ከሀገር ቤት እስከ አለም ዙሪያ ምን አለ የሚለውን በየእለቱ ወደ እናንተ ውድ ተከታታዮቻችን እናደርሳለን! ስለሆነም አድስዜና ምንም እንኳን ትንሽ ተከታይ ቢኖረውም ጥርት ያለ መረጃ በማድረስ በቀጣይ የአባሎቹን ቁጥር ከፍ እያደረገ እንደሚሄድ ተስፋ አለን ፣ ከዚህም የበለጠ እንዲሰራና ትልቅ የመረጃ ቋት ይሆንም ዘንድ የእናንተ ክቡራን ተከታታዮቻችን ቀና አስተያየት ያበረታናልና ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት
ከታች ባለው #comment መስጫ ላይ አስፍሩልን ለወዳጅ ዘመድም በምጋርት አብሬነታችሁን አሳዩን!
@adszena ቴሌግራም የቻናላችን ሊንክ ነው!!
ሰላም ለሀገራችን! መልካምጊዜ ይሁንላችሁ!

🔴የቅዳሜ ምሽት አጫጭር መረጃዎች
👉የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች የሕወሃት ተዋጊዎችን ከታሪካዊቷ ላሊበላ ከተማ እያስወጡ መሆኑን የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ትናንት ማምሻውን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን በዓለም ታሪካዊ ቅርስነት የመዘገበው ዩኔስኮ በበኩሉ፣ በታሪካዊዎቹ ቅርሶች ላይ ጉዳት ይድረስ አይድረስ የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለው ለዓለማቀፍ ዜና ወኪሎች ተናግሯል። የሕወሃት ወታደራዊ ዕዝ ግን ቅርሶቹ አንዳችም ጉዳት እንደማይደርስባቸው ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ባሰራጨው አጭር መግለጫ ማረጋገጫ ሰጥቷል።
👉አማጺው ሕወሃት ከዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ጋር በቀጥታ ለመገናኘት የሚያስችለውን የውጭ ግንኙነት ቢሮ ማቋቋሙን የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በሚል ስም በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የወጣ መግለጫ አመልክቷል። የውጭ ግንኙነት ቢሮው ለውጭ ሀገራት፣ ለዓለማቀፍ ድርጅቶች እና ዓለማቀፍ መገናኛ ብዙኀን ስለ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስ እና ወታደራዊ ሁኔታዎች ሳምንታዊ መግለጫ እንደሚበትን መግለጫው አመልክቷል። የውጭ ግንኙነት ቢሮው መቀመጫ የት ሀገር እንደሆነ ግን መግለጫው አላብራራም።
👉በመደበኛው የባንኮች ምንዛሪ እና በጥቁር ገበያው መካከል በብር እና በአሜሪካ ዶላር መካከል እየሰፋ የመጣው የምንዛሬ ልዩነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የለውም ሲሉ የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ፍቃዱ ድጋፌ ለመንግሥታዊው ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ልዩነቱ በከፍተኛ መጠን መስፋቱ የኢኮኖሚያዊ አሻጥር ውጤት እንደሆነ የገለጡት ሃላፊው፣ አሻጥር ላሉት ድርጊት ተጠያቂ ያደረጉት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ ሕገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪዎችን ነው። በንግድ ባንኮች እና በጥቁር ገበያው መካከል እስከ 20 ብር የሚደርስ ልዩነት እንዳለ ዋዜማ በሳምንቱ መጀመሪያ ያደረገችውን መጠነኛ ቅኝት መሠረት አድርጋ ከትናንት ወዲያ መዘገቧ ይታወሳል።
👉 የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ሰልፉ የሚካሄደው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች ጸጥታ ኃይሎች ሕዝባዊ ድጋፍን ለመግለጽ እና አማጺው ሕወሃት በሀገሪቱ ሉዓላዊነት ላይ የጋረጠውን ከባድ የህልውና አደጋ ለማውገዝ ነው ተብሏል።
👉በኢትዮጵያ ባሁኑ ወቅት ለሚታዩ ግጭቶች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንደዲረግ እና ግጭቶቹ በሽምግልና እንዲፈቱ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ዛሬ በትዊተር ገጹ ባሰራጨው መግለጫ ጠይቋል። ዓለማቀፉ ኅብረተሰብም የተለያዩ የግጭት ተሳታፊ ወገኖችን ለማሸማገል ቁልፍ ሚና እንዲጫወት ኦብነግ ጥሪ አድርጓል። ሁሉም ብሄረሰቦች እና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ብሄራዊ መድረክ እንዲጠራ እና ሀገሪቱን ለማያባራ ግጭት ሲዳርጓት የኖሩ መዋቅራዊ የፖለቲካ ችግሮችን የሚፈታ አዲስ አስተዳደራዊ ቀመር እንዲበጅ ግንባሩ አክሎ ጠይቋል።
👉 በደቡብ ሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሬክ ማቻር ደጋፊዎች እና በተቀናቃኞቻቸው መካከል ግጭት መቀስቀሱን የተለያዩ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ግጭቱ የተቀሰቀሰው ማቻር የሚመሩት የተቃዋሚ ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ ውስጥ የተወሰኑ ጀኔራሎች ማቻርን ከጦር ሠራዊቱ አዛዥነታቸው እና ከፓርቲው ሊቀመንበርነታቸው በማንሳት ጀኔራል ሲሞን ዱዋልን ሹመናል ማለታቸውን ተከትሎ ነው። ለማቻር የወገኑ ወታደሮች አንጃው የቃጣብንን ጥቃት መክተን ሁለት የአንጃውን ጀኔራሎች ገድለናል ብለዋል። የሀገሪቱ የሽግግር አንድነት መንግሥት አካል የሆነው የማቻር ድርጅት እና ወታደራዊ ክንፉ መከፋፈሉ፣ የሀገሪቱን ሰላም ስምምነት እንዳያኮላሸው ተሰግቷል።
#አድስዜና #ዋዜማሬድዮ

🔴ወደ ወልዲያ ከባድ መሳሪያዎች እየተተኮሰ መሆኑን እየተገለፀ ነው። የደረሰው ጉዳት እስካሁን አልታወቀም: ሙሉ መረጃው እንደደረሰን የምናደርሳችሁ ይሆናል።
#አድስዜና
#አድስዜና
የአፍሪካ ንግድ ምክር ቤት ኃላፊ ክቡር ገና ፦
"...አንዳንድ ነጋዴዎች በዚህ የፈተና ወቅት መጠቀም አለብን በሚል ባልተገባ መልኩ ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ። በዚህም ለኅብረተሰብ መድረስ ያለበት ምርት በትክክል እንዳይደርስ በማድረግ የሚፈጠር ሳቦታጅ አለ።
በተለይ ጦርነት በሚነሳበት ወቅት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ስለሚከሰት በዚህ ወቅት ለመጠቀም የሚፈልግ ነጋዴ እንደሚኖር ይታመናል።
በኢትዮጵያ የዶላር ምንዛሪ ከፍተኛ እጥረት አለ በሚል ሰበብ እና ወደፊት ይወደዳል በሚል እሳቤ ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎች አሉ ፤ ይህም የዶላር ዋጋ እየጨመረ ስለሚሄድ ሊተካኝ በሚችል መልኩ ዋጋ መሰብሰብ አለብኝ ከሚል እሳቤ የሚመጣ ነው በዚህ ሂደት እቃ የማከማቸት እና ዋጋ የመጨመር አዝማሚያዎች አሉ።
እነዚህ ነጋዴዎች በተለይ ከምግብ ጀምሮ እስከ ኮንስትራክሽን ግብዓት እና ሌሎች ተፈላጊ ምርቶችን ይይዛሉ።
ይህም በኋላ ላይ በተሻለ ዋጋ እሸጣቸዋለሁ ከሚል ፍላጎት የሚመነጭ ነው። ሂደቱ ግን የዋጋ መናርን ያስከትልና ሸማቹ ላይ ጫና ይፈጥራል

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ :
"...ስለህዝብ ያገባናል ፣ እንታገላለን የምትሉ ሁሉ ከሁሉ በላይ #ሰብዓዊነትን አክብሩ፣ ንፁሃንን በፍፁም ኢላማ አታድርጉ፣ ለአንድ ወገን እንታገላለን በማለት የሌላውን ወገን መጉዳት እና ለጥቃት ማጋለጥ፣ የዜጎችን ደህንነት በተለይም የታዳጊ ህፃናትን ተስፋ ማጨለም ፣ ለግዳጅ ማሰማራት ተቀባይነት የሌለውና ተገቢ እንዳልሆነ ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።
በተጨማሪ ለዘመናት ተጠብቀው የኖሩ እንደ ቅዱስ ላሊበላ ፣ አክሱም ፂዮን ፣ አልነጃሺ መስጊድ በመሳሰሉ የሃይማኖት ተቋማት እና የታሪካዊ ቅርሶቻችን ላይ የተቃጣውን ጥቃት በፅኑ እናወግዛለን።
ሁላችሁም አካላት ከግብዝነት ርቃችሁ፣ያነገታችሁትን ጠብመጃ ለሰላም ስትሉ ለማዘቅዘቅ ፣ ህይወት ቀጣፊ እና ንብረት አውዳሚ ከሆነ ተግባር ለመራቅ ልባችሁ ሁሌም የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።"

ዛሬ የተሰሙ ዜናዎች
1፤ የኢትዮጵያ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች በተለያዩ ቁልፍ መሠረተ ልማቶች እና የመረጃ አውታሮች ላይ የበይነ መረብ ጥቃት ለመፈጸም መጠነ ሰፊ ሙከራ እያደረጉ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። እኩይ ዓላማ ያነገቡ አካላት ለዚሁ ተልዕኮ በሀገር ውስጥ የመረጃ አውታሮችንና ተቋማዊ ሥርዓቶችን የሚያስተዳድሩ እና ለሀገራቸው ታማኝ ያልሆኑ ባለሙያዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነ ኤጀንሲው ጠቁሟል። መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ይህንኑ ተረድተው የበይነ መረብ ተቋማዊ መረጃ ሥርዓታቸውን የሚያስተዳድሩና የማኅበራዊ ትስስር ገጾቻቸውን ይለፍ ቁልፍ የሚቆጣጠሩ ባለሙያዎች ትክክለኛ የሙያ ብቃት እና ስነ ምግባር ያላቸው መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ኤጀንሲው አሳስቧል።
2፤ የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ የትግራዩ ግጭት እስከ ጥቅምት መጨረሻ ካልቆመ በሁሉም ተፋላሚ ኃይሎች ላይ ማዕቀብ ሊጥል እንደሚችል በአብላጫ ድምጽ ባጸደቀው የውሳኔ ሃሳብ አስጠንቅቋል። የክልልና ዓለማቀፍ ድንበሮች ለሰብዓዊ ዕርዳታ ክፍት እንዲሆኑ፣ ሕወሃት እና አማራ ክልል በኃይል ከያዟቸው አጎራባች አካባቢዎች ታጣቂዎቻቸውን እንዲያስወጡ፣ ኢትዮጵያ የዓለማቀፉን ወንጀል ፍርድ ቤትን አባል እንድትሆን እና የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ሰላም አስከባሪ ጦር የማሠማራትን ሃሳብ እንዲያጤነው ኅብረቱ ጠይቋል። የኅብረቱ አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ ጦር መሳሪያ እና የስለላ ቁሳቁሶችን እንዳይሸጡ ኅብረቱ ጥሪ አድርጓል።
3፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለኝ መረጃ እና ዕውቀት በየትኞቹም አውሮፕላኖቼ ወደየትኛውም የበረራ መስመር ጦር መሳሪያ አላመላለስኩም ሲል ሲኤንኤን ላወጣው ዘገባ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ምላሽ ሰጥቷል። ሲኤንኤን አገኘሁት ባለው የበረራ ደረሰኝ ላይ የተጓጓዙ "የታሸጉ ምግቦች መሆናቸውን ያሳያል ያለው አየር መንገዱ፣ በዘገባው የተካተቱትን ምስሎች ግን አላውቃቸውም ብሏል። አየር መንገዱ በብሄር ማንነት ለይቶ ከሥራ ያባረራቸው ሠራተኞች እንደሌሉም አክሎ የገለጠ ሲሆን፣ እውነተኛውን መረጃ ከሠራተኛ አስተዳደር ቢሮው ማረጋገጥ እንደሚቻል ጠቁሟል።
4፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ለአጭር ጊዜ ኦፊሴላዊ ፌስቡክ ገጹ ከቁጥጥሩ ውጭ ሆኖበት እንደነበር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። የኩባንያው ፌስቡክ ገጽ ከቁጥጥር ውጭ በቆየበት ጊዜ፣ ከኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ የወጣ በማስመሰል አንድ ሐሰተኛ መልዕክት በገጹ ተሰራጭቶ እንደነበር የጠቀሰው አየር መንገዱ፣ ሆኖም መልዕክቱ ከሥራ አስፈጻሚስም ሆነ ከኩባንያው እንዳልወጣ እና ኩባንያውን እንደማይወክል ገልጧል። ኩባንያው ብዙም ሳይዘገይ ፌስቡክ ገጹን መልሶ ተቆጣጥሯል።
5፤ በጉረቤት ሱማሊያ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሱማሊያዊያን ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱ መሆኑን በኢትዮጵያ የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ኮሚሽኑ ለአዲሶቹ ስደተኞች ቡራሚሮ እና መልካዲዳ በተባሉ ቦታዎች የስደተኛ መጠለያዎችን እንደገነባ አክሎ ገልጧል። በቅርብ ወራት ስንት ሱማሊያዊያን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ግን ኮሚሽኑ አላብራራም።
6፤ ሱማሌላንድ ራስ ገዝ ሰሞኑን ከ1 ሺህ በላይ ሰላማዊ ሱማሊያዊያንን ከግዛቷ ማባረሯን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሐርጌሳ ሱማሊያዊያኑን ከፑንትላንድ ራስ ገዝ ጋር ከምትወዛገብበት "ሱል" አውራጃ ያባረረችው፣ በሕገወጥ መንገድ የሠፈሩ እና ለአካባቢው ኅብረተሰብ የጸጥታ ስጋት የሆኑ ናቸው በማለት ነው። የሞቃዲሾው መንግሥት የሐርጌሳን ርምጃ "አሳፋሪ" በማለት አውግዞታል። ተመድም ድርጊቱን የኮነነ ሲሆን፣ ሐርጌሳ ተጨማሪ ሱማሊያዊያንን ለማባረር ዝግጅት ላይ መሆኗም አሳሳቢ ነው ብሏል።
7፤ ኬንያ ከሱማሊያ ጋር ባላት የሕንድ ውቅያኖስ ወሰን ውዝግብ ላይ ዓለማቀፉ ፍርድ ቤት በመጭው ማክሰኞ የሚሰጠውን ብይን እንደማትቀበለው ከወዲሁ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴሯ በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ኬንያ ለፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስገዳጅነት ዕውቅናዋን መንፈጓንም ገልጻለች። ኬንያ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው፣ የብይን መስጫው ጊዜ እንደገና እንዲራዘምላት በተደጋጋሚ ጠይቃ ውድቅ ስለተደረገባት እና ችሎቱ አድሏዊ ሆኗል በማለት ነው። ኬንያ በተፈጥሮ ጋዝ በበለጸገው የባሕር ግዛት ይገባኛል ጥያቄን በድርድር መፍታት እንደምትፈልግ ግን ጠቁማለች።
at #አድስዜና
via ዋዜማ ራዲዮ

በደሴ ከተማ ላይ በተፈጸመ የመድፍ ጥቃት አንድ ሰው ሲገደል ሦስት ቆሰሉ!
በደቡብ ወሎ ዞን መዲና በደሴ ከተማ ላይ በተተኮሱ የመድፍ አረሮች ምክንያት አንድ ሰው ሲገደል ሦስት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የከተማዋ ከንቲባ ለቢቢሲ ተናገሩ።የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረ መስቀል ለቢቢሲ እንደገለጹት ትናንት ሐሙስ ጥቅምት 18/2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ "የህወሓት ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ላይ በመድፍ በፈጸሙት ጥቃት ነው የሞትና የመቁሰል አደጋ የደረሰው።"እየተካሄደ ስላለው ጦርነት የተረጋገጠ መረጃ ማግኘት አዳጋች ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በደሴ ከተማ አቅራቢያ ባሉ ስፍራዎች በመንግሥት ኃይሎችና በህወሓት ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ እየተዘገበ ነው።
ከንቲባው ለቢቢሲ እንደገለጹት መድፎቹ ወደ ደሴ ከተማ የተተኮሱት ከሰዓት በኋላ በግምት 9፡30 ላይ ሲሆን ሦስት የተለያዩ ቦታዎች የጥቃቱ ኢላማ መሆናቸውን አመልክተዋል።አማጺያኑ በአጠቃላይ አምስት የመድፍ አረሮችን በከተማዋ ላይ የተኮሱ ሲሆን፤ ሁለቱ መናፈሻ በሚባለው የከተማዋ አካባቢ፣ ሁለቱ ዳውዶ በሚባለው ስፋራ እንዲሁም ቀሪው አንድ ደግሞ እርሻ ሰብል ከሚባለው ቦታ ላይ ወደቀዋል ብለዋል።በተለይ እርሻ ሰብል እና መናፈሻ በተባሉት የከተማዋ ስፍራዎች ላይ ያረፉት አረሮች ሰላማዊ ነዋሪዎች በሚገኙባቸው ቦታዎች ላይ እንደሆነና ዳውዶ በተባለው አካባቢ ላይ የተተኮሰው መድፍ በሰው ላይ ጉዳት ሳያደርስ ሜዳ ላይ መውደቁን ከንቲባው አመልክተዋል።
የመድፍ ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ በጦርነቱ ምክንያት ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ ሰዎች የተጠለሉበትና እርዳታ የሚያገኙበት ስፍራ እንደሚገኝበት ከንቲባው ለቢቢሲ ገልጸዋል።ከደሴ ከተማ ውጪ ከሚገኝ ስፍራ በህወሓት ኃይሎች በከተማዋ ላይ ተፈጸመ በተባለው በዚህ የከባድ መሳሪያ ጥቃት የተገደለውና የቆሰሉት ንፁሃን ሰዎች መሆናቸውን አቶ አበበ ገብረ መስቀል ተናግረዋል።
ምንጭ BBC #አድስዜና

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ወደ ቀደመው ኃላፊነታቸው ለመመለስ የሱዳን የፖለቲካ እና ወታደራዊ ኃይሎች ከስምምነት መድረሳቸው ተሰምቷል።
የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሀገሪቱን ከቀውስ ለማውጣት እያካሄዱት ባለው ድርድር ላይ በወታደራዊ ኃይሎች ከስልጣናቸው ተነስተው የነበሩትን አብደላ ሀምዶክ ወደ ቀድሞ ኃላፊነታቸው ለመመለስ ተስማምተዋል።
የሱዳን ሉዓላዊ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃ እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክም በጉዳዩ ላይ ከመግባባት ደርሰዋል ተብሏል።
በስምምነቱ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ ካቢኔያቸውን እንዲያዋቅሩ ከስምምነት ተደርሷል።
በተጨማሪ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞችን ከእስር እንዲለቀቁ ከስምምነት መደረሱን ታውቋል።
(አል ዐይን) #አድስዜና

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ሊሙ ወረዳ አንገር ጉትን ከተማ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ኦነግ ሸኔ ተፈናቃዮች ለቀለብ ብለው ሲያጓጉዙት የነበረውን 400 ኩንታል እህል መቀማቱን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለአዲስ ማለዳ ገለጹ።
አዲስ ማለዳ ከምንጮቿ ያገኘቸው መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ፣ ባሳለፍነው ታኅሳስ 11/2014 አንገር ጉትን መንደር ስድስት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች፣ ለቀለብ የሚሆን እህላቸውን ጭነው ሠላም ወዳለበት የጉትን ከተማ ሲያጓጉዙ የሸኔ ታጣቂ ቡድን እንደቀማቸው ነው መረዳት የተቻለው።
via #addismaleda @#አድስዜና

ዛሬ የወጡ ዋና ዋና ዜናዎች
1፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የለያቸውን 42 ዕጩ ኮሚሽነሮች ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ አድርጓል። ከየ42ቱ ዕጩ ኮሚሽነሮች መካከል፣ ሕዝቅየስ አሠፋ (ፕሮፌሰር)፣ ጥሩሰው ተፈራ (ፕሮፌሰር)፣ በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር)፣ ዘገየ አስፋው፣ አምባሳደር ታደለች ኃይለ ሚካዔል፣ ጥላሁን ተሾመ (ፕሮፌሰር)፣ ባዬ ይማም (ፕሮፌሰር)፣ ሰሚር የሱፍ (ዶ/ር)፣ ሐብታሙ ወንድሙ (ፕሮፌሰር)፣ አብዲሳ ዘርዓይ (ዶ/ር)፣ መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር)፣ አበራ ደሬሳ፣ አምባሳደር ሞሐመድ ድሪር፣ ያዕቆብ አርሳኖ (ፕሮፌሰር)፣ ካሳሁን ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ ሙሉጌታ አረጋዊ (ዶ/ር)፣ ተስፋዬ ሐቢሶ፣ በቀለ ጉተማ (ፕሮፌሰር)፣ አባተ ኪሾ፣ ዘነበወርቅ ታደሠ እና አንዳርጋቸው አሰግድ ይገኙበታል። ምክር ቤቱ 42ቱን ዕጩዎች የለየው ሕዝብ ከጠቆማቸው 632 ዕጩዎች መካከል መሆኑን ገልጾ፣ ሕዝቡ በምክር ቤቱ ድረገጹ በተቀመጠው ቅጽ እስከ የካቲት 1 በዕጩዎቹ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ጋብዟል።
2፤ ጤና ሚንስቴር በአማራ እና አፋር ክልሎች በሰሜኑ ጦርነት ከተጎዱ የጤና ተቋማት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ገና አገልግሎት እንዳልጀመሩ ሚንስትር ሊያ ታደሠ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የ6 ወራት ሪፖርት ማስታወቃቸውን ሪፖርቱን የተከታተለው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። በሁለቱ ክልሎች ከተጎዱት ጤና ተቋማት ውስጥ መሠረታዊ የሕክምና አገልግሎት መስጠት የጀመሩት ከግማሽ በታች መሆናቸውን የጠቀሰው ሚንስቴሩ፣ በሁለቱ ክልሎች በድምሩ 2 ሺህ 924 ጤና ተቋማት በጦርነቱ እንደወደሙ እና እንደተዘረፉ ገልጧል። በሁለቱ ክልሎች ጨርሶ አገልግሎት መጀመር ያልቻሉት አብዛኞቹ ጤና ኬላዎች እንደሆኑ ሚንስትሯ ተናግረዋል።
3፤ የተመድ ስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፌደራሉ መንግሥት ጸጥታ ኃይሎች እና በአማጺ ታጣቂዎች መካከል ባለው ግጭት ከ20 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደተፈናቀሉ ዛሬ በትዊተር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። ከሁለት ሳምንት በፊት ቶንጎ በተባለች ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት 10 ሺህ 300 ስደተኞች የነበሩበት መጠለያ እና በታኅሳስ ጉሬ-ሸምቦላ መጠለያ መውደማቸውን ኮሚሽኑ ጠቅሷል። ከሁለቱ መጠለያዎች የተፈናቀሉ 22 ሺህ ስደተኞች ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ዕርዳታ እንዳላገኙ ኮሚሽኑ የጠቀሰ ሲሆን፣ የክልሉ መንግሥት ለተፈናቀሉት ስደተኞች አዳዲስ መጠለያዎችን ማዘጋጀቱን ገልጧል። ኮሚሽኑ ጨምሮም፣ ከታኅሳስ ወዲህ የክልሉ ጸጥታ ሁኔታ አስጊ ሆኗል ብሏል። በክልሉ 70 ሺህ ሱዳናዊያን እና ደቡብ ሱዳናዊያን ስደተኞች ይገኛሉ።
4፤ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ በኅዳር ወር በምዕራብ ሸዋ ዞን የተገደሉ 14 የከረዩ ኦሮሞ አባገዳ አባላትን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣውን ሪፖርት በበጎ መልኩ እንደሚቀበለው ለመገናኛ ብዙኀን አስታውቋል። ግለሰቦቹ በተገደሉበት ወቅት የክልሉ ፖሊስ ገዳዮቹ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው የሚል መግለጫ እንዳልሰጠ እና ከፖሊስ ኮሚሽኑ መግለጫውን የሰጠ አካል ከነበረ ስህተት እንደሆነ የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን ተናግረዋል። በግድያው እስካሁን 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ተገልጧል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን 14ቱን ሰዎች ያለ ፍርድ የገደሏቸው የክልሉ ፖሊሶች እንደሆኑ አረጋግጫለሁ ማለቱ ይታወሳል።
5፤ ሂውማን ራይትስ ዎች በአዲስ አበባ የሚካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ለሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ትኩረት እንዲሰጥ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ድርጅቱ ጩምሮም፣ አዲሱ የኅብረቱ ሊቀመንበር የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል የአፍሪካ ኅብረት ትኩረቶች በሰላማዊ ሰዎች ደኅንነት፣ በሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ፣ በፍትህ እና ተጠያቂነት ላይ እንዲሆኑ እንዲያደርጉ ጥሪ አድርጓል። የኅብረቱ መሪዎች ነገ እና ከነገ ወዲያ በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ጉባዔ፣ በዋናነት በአሕጉሪቱ የሥርዓተ ምግብ እና የምግብ ዋስትና ይዞታ ላይ ይወያያሉ።
6፤ የሀገር ዓቀፍ ፈተናዎች እና ምዘና ኤጀንሲ ግጭት ውስጥ በከረሙ አካባቢዎች ላለፉት ቀናት ሲሰጥ የቆየውን ሁለተኛ ዙር የ12 ክፍል ሀገር ዓቀፍ ፈተና ማጠናቀቁን ዛሬ ለሀገር ውስጥ ዜና አውታሮች በሰጠው ተናግሯል። የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመጀመሪያው ዙር በግጭቶች ሳቢያ ለፈተናው መቀመጥ ላልቻሉ ተማሪዎች የተሰጠው፣ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋር እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች ነው። የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከወራት በፊት እንደተሰጠ ይታወሳል።
ዘገባው ዋዜማ ራድዮ #አድስዜና

ሊሲቻንስክ ከተማ በሩሲያ ጦር መያዟን ዩክሬን አመነች❗️
➪የሩሲያ ጦር ሊሲቻንስክ ጨምሮ ዶንባስ ክልልን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ከቀናት በፊት መናገሩ የሚታወስ ሲሆን የዩክሬን መከላከያም የሩሲያ ጦር በክልሉ የመጨረሻ ዩክሬን ይዞታ የነበረችውን ሊስቻንስክን ተቆጣጥሯል ብሏል፡፡
➪የዩክሬን ወታደሮች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ያለው የዩክሬን መከላከያ በቀጣይ በሩሲያ ጦር ስር የገቡ ቦታዎችን ሙሉ ለሙሉ ማስለቀቅ የሚያስችሉ ዘመቻዎችን እንጀምራለን ሲልም አስታውቋል።
#የአለምዜና #አድስዜና

ዛሬ ዓለም እያነጋገረ ያለው የሲሪላንካ ጉዳይ ምንድነው ?
• የሲሪላንክ ፕሬዝዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ ደህንነቱ ወደተጠበቀ ስፍራ ተወስደዋል።
• ተቃዋሚዎች የፕሬዜዳንቱ መኖሪያ ቤት ጥሰው ገብተው ሲዋኙ፣ ያሻቸውን ሲበሉ፣ ሲጠጡ ታይተዋል።
ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በሲሪላንካ ዋና ከተማ ኮሎምቦ የሚገኘውን የፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ መኖሪያ ቤት ጥሰው ገብተዋል።
ገብተውም በፕሬዜዳንቱ የመዋኛ ገንዳ ሲዋኙ፣ በመኖሪያ ቤቱ በመግባትም ሲበሉ ፣ ሲጠጡ ፣ አልጋቸው ላይ ሲተኙ፣ መሳቢያዎቸውን እየከፈቱ እቃዎቻቸውን ሲበታትኑ ውለዋል።
ፕሬዜዳንቱ ለጊዜው ደኅንነቱ ወደተጠበቀ ስፍራ መወሰዳቸውንና ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን አንድ ከፍተኛ የጦር ሹም ለኤኤፍፒ ገልጸዋል።
ፖሊስ፣ ወታደር ሀገሪቱ አለኝ የምትለው የፀጥታ ኃይል የዛሬውን ህዝባዊ ተቃውሞ መቆጣጠርም ሆነ መቋቋም አልቻሉም።
ለወራት በዘለቀውና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ችግር በአግባቡ ባለመቆጣጠር በተነሳ ነው ፕሬዚዳንቱ ህዝባዊ ተቃውሞ የገጠማቸው።
ከዚህ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ራኒል ዊክሬሜሲንጌ ስልጣኔ ይቅርብኝ እውርዳለሁ ማለታቸውን ፅ/ቤታቸው አሳውቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉንም ያሳተፈ መንግሥት እንዲመሰረት ለማድረግ ስልጣን ለመልቀቅ ፍቃደኛ እንደሆኑ ነው የገለፁት።
ሲሪላንካ በአሁኑ ወቅት ላይ ከፍተኛ የሆነ ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ውስጥ ናት። ሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ያጋጠማት ሲሆን፤ መድኃኒት፣ ነዳጅ እና ምግብ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት እንደተሳናት ቢቢሲ ፅፏል።
መረጃው ከሲሪላንካ ጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ ከቢቢሲ፣ ኤኤፍፒ የተሰባሰበ ነው።
Video Credit : Anoyme Citoyen, SLTweet, Jamila Husain

ባለፈው ሳምንት " 25 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች " አስክሬን ያለበት የጅምላ መቃብር ምዚምባ በተባለ ግዛት ደን ውስጥ መገኘቱን የማላዊ ፖሊስ ገልጿል።
የአካባቢው ወጣቶች ደኑ ውስጥ የሚያውክ ሽታ እንዳለ መጠቆማቸውን ተከትሎ ነበር አስክሬኖቹ በቁፋሮ የተገኙት።
የጅምላ መቃብሩ ከተገኘ በኋላ በቅርብ ርቀት ሌላ የጅምላ መቃብር ተገኝቶ ተጨማሪ 4 አስክሬኖችን ፖሊስ አውጥቷል።
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ፤ የማላዊ መንግሥት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
የማላዊ የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር ጃን ሴንዴዝ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ የተናገሩት፦
- በጣም የሚያሳዝን ነው። አስከፍቶናል። መንግሥታችን እንዲህ ያለ ድርጊት በጽኑ ያወግዛል። ትክክል አይደለም።
- ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ነው ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ እጃቸው ያለበት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ይውላሉ።
- ኢትዮጵያውያኑ በምን ምክንያት እንደሞቱ ለማወቅ የአስክሬን ምርመራ ይደረጋል።
- የጅምላ መቃብሩ ከተገኘበት ጥበቅ ደን ርቆ በሚገኝ ሌላ ደን ውስጥ 72 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተገኝተው በፖሊስ ተይዘዋል።
- ድንበር አቅራቢያና በአውራ ጎዳናዎች ላይ የሚያደርገው ቁጥጥር ጠብቋል። በሰሜናዊ የማላዊ ግዛት ሰው አዘዋዋሪዎችን ለመያዝ እየተሞከረ ይገኛል።
ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በማዘዋወር የተጠረጠሩ 10 የማላዊ ዜጎች መታሰራቸው የተነገረ ሲሆን እስከሁን ግን ፍ/ቤት አልቀረቡም ተብሏል።
አብዛኞቹ ማላዊ የሚገቡ ስደተኞች ከምሥራቅ አፍሪካ የሚነሱ ናቸው።
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ፤ኢትዮጵያ ከማላዊ መንግሥት ጋር በመተባበር ስለ ክስተቱ ምርመራ እያደረገች ነው ብለዋል። በክስተቱ ሐዘን እንደተሰማቸው ገልፀው የምርመራው ውጤት ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ገልፀዋል።