ግጥምና ታሪኮች
1.11K subscribers
88 photos
5 videos
3 files
115 links
በዚ Channel ★የራሴን የግጥም ስራዎችና በሌሎች ገጣሚያን የተሠሩ አሪፍ አሪፍ የግጥም ስራዎች★ እንዲሁም ተከታታይ መሳጭ ታሪኮችየምታገኙ ይሆናል አብራቹኝ ሁኑ @darkniha ላይ አውሩን

★ Anything አስተያየት እና ሀሳብ ካለዎት💛 for any comment
@darkniha
@dark_niha_bot
@Hanan_Akmel
Download Telegram
ውሾች 250 የሚሆኑ ቃላቶችን መረዳት ይችላሉ፡፡ @achacher
👉በጥያቄያችሁ መሰረት ስለ ናዚ እና ስለ አዶልፍ ሂትለር ትንሽ እንበል ...👈

👉1.የናዚዎች የዘረኝነት ጭፍጨፋ ሆሎካስት ተብሎ ይጠራል፡፡

👉2.ሆሎካስት የተጀመረው በ 1933 ልክ አዶልፍ ሂትለር ስልጣን ሲይዝ ሲሆን ያበቃው ደሞ በ 1945 ናዚ ሲሸነፍ ነው፡፡

👉3.በሰአቱ በአውሮፓ 9 ሚሊየን ጂዊሾች ይኖሩ የነበረ ሲሆን ሂትለር ከ 5-6 ሚልን የሚሆኑትን አስገድሏል፡፡

👉4.ጅዊሾችን ማግባት ወይም ከነሱ ጋ ግንኙነት መፈፀም የተከለከለ ነበር፡፡

👉5.ጅዊሽ የሆነ ማንኛውም ህፃን( እርጉዝ እናቶች ሳይቀሩ ) አይታለፉም፡፡ይገደላሉ፡፡

👉6,,,3.4 ሚልየን የናዚ ወታደሮች ጦርነቱ ካለቀ በዋላ በአሜሪካ በራሺያና በእንግሊዝ ተባባሪነት ተቀጥተዋል፡፡

👉7.የናዚ አመራሮች ፕላናቸውን ሆሎካስት ብለው አይጠሩትም፡፡ Final solution እንጂ፡፡ወይም ባጭሩ የኮድ ቋንቋቸው Final solution ይባላል፡፡

👉8.ናዚ የሚለው ቃል NAZI (“Nationalsozialistishe Deutsche
Arbeiterpartei” (“National Socialist German
Worker’s Party”).የሚለውን ይወክላል፡፡

👉9.ሂትለር 6 ትላልቅ የመግደያ ካምፖችን አሰረቷል፡፡ 1.Chelmno, 2.Belzec, 3.Sobibor, 4.Treblinka,
5.Auschwitz, and Majdanek.(5አና 6 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገደሉባቸው ካምፓች ናቸው፡፡

👉10. አምስተኛው ካምፕ ተልቁና ብዙ ሰው (1.1 ሚልየን ሰው) የተገደለበት ካምፕ ነው፡፡ ይህካምፕ አሁንም ድረስ ያለ ሲሆን በአመት በ 500,000 ሰዎች ይጎበኛል፡፡

👉11. ሰዎች ወደካምፖቹ የሚገቡት ለሻወር ነው ተብለው ተታለው ነበር፡፡

👉12.ከሞታቸው በፊት አንዳንዶቹ ሰዎች ላይ ልክ እንደ አይጥ medical experiment test ይደረግባቸው ነበር፡፡

👉13.አንድ ቀን ሂትለር የአጎቱን ልጅ አፓርታማ በስህተት አፈንድቷል፡፡

👉14. አዶልፍ ሂትለር በአጠቃላይ 11 ሚሊየን ሰዎችን አስገድሏል፡፡

👉15. ከዚህ ሁሉ ሞት በዋላ ሂትለር በ 56 አመቱ April 30 1945 አ.ም መሸነፉን ሲያውቅ እራሱን በገዛ ሽጉጡ ገደሏል፡፡

@achacher
በተፈጥሮ ወንዶች ከሴቶች በበለጠ ተናንሽ ፅሁፎችን ማንበብ ሲችሉ ሴቶች ደሞ ከወንዶች የበለጠ መስማት ይችላሉ፡፡ @achacher
​​​​#ወዳጄ__ሳቅ !😁😁😁


😁ሳቅ ማንነትን ደብቆ ከሰው ጋር መኖር
ያስችላል ፣ እድሜ ይጨምራል

😁ሳቅ ትካዜን ቀይሮ ደስተኛ ያረጋል
ፊትን ያጠራል

😁ሳቅ ኩርፊያን አስጥሎ ህሊናን ያድሳል የፊት መጨማተርን ያስወግዳል

😁ሳቅ~የቁጣን ሀይል ወደ ፈገግታ ይቀይራል ለሰው መጥፎ እንዳናስብ ያደርጋል

😁ሳቅ የውስጥን ጨለማ በፈገግታ ያደምቃል

😁ሳቅ~የልብን ስብራት በጥርስ ይደብቃል

😁ሳቅ የደስታን ስሜት በነብስ ውስጥ ያኖራል::

👌የህይወት ውጣ ውረድ ብዙ እና አድካሚ ቢሆንም ባገኛችሁት አጋጣሚ ሁሉ #ለመሳቅ ሞክሩ😁

😁ለሳቅ ለጨዋታ የምታባክኑት ጊዜ አይፀፅታችሁ ይቺ አለም እንደ ኪራይ ቤት ናት!!

😁😁ስለዚህ ስቀህ እለፋት!!😁😁

✔️""ሳቅ የደስታ ምንጭ ነው ""✔️
@achacher
1
በትክክለኛው መንገድ ወደ ትክክለኛ ቦታ እየተጋስክ ከሆነ ስለ መርዘሙ አትጨነቅ
ሀሳብና አስተያየተረዎን 👇
@Niyabot ያድርሱን
ሰላም የ ጠቃሚ app አባላት


እያንዳንዳቹ በ ቀላሉ ለ 5 ሰዎች ሼር ብታረጉ 3500 እንሆናለን፡፡
በ ቅንነት ሼር ስለምታረጉ አመሰግናለው፡፡

ሰላም የዚህ ቻናልተከታታዮች
ዛሬ ለየት ያለ ቻናል ይዜ
መጥቻለው ስሙ ጠቃሚ app
ይባላል ልክ እንደ ስሙ ጠቃሚ ነው።
🔻በውስጡ🔻
🔹አዳዲስ apps&softwars
🔹የ ሚሸጡ appኦች በነፃ
ያገኛሉ።
🔹አዳዲስ ጌሞች
🔸በ ስልክ እናcomputer
የሚሰሩ online ስራዎች💲
🔹በwesternunion,payonner
የሚከፍሉ ትክክለኛ ስራዎች።
🔸በ ካርድ የሚከፍሉ
🔹ብሩን ወደ Ethiopia እንዴት
እንደምንልክ
🔹ከነ ብር መቀበያ አማራጮች
🔹የhackingtutorials&tricks
With videos
🔹programing ለምሳሌ፡–
html,c++,java etc
🔹አንዳንዴ ሽልማት ያላቸው
ጥያቄዎችነው
🔷 ከናንተ የሚጠበቀው JOIN
ማድረግ ብቻ
🔰JOIN ያረጋቹ አለፈላቹ
📱⌚️📱⌚️📱⌚️📱⌚️
join ለማድረግ ከፈለጉ
https ብሎ የሚጀምረውን ይንኩ፡፡
https://telegram.me/usefullapplication
https://telegram.me/usefullapplication

@usefullapplication
@usefullapplication

❗️❗️ሼር ለ 5 ሰው ❗️❗️❗️
#fb_lite ላይ እንዴት በተለያዩ ቀለማት ያማሩ ፅሁፎችን መፃፍ እንችላለን?

🖲ለኮሜንት እንዲሁም ለተለያዩ ፖስቶች
የከለር ኮዶች እነሆ
=======================

<fg=b0ffd700> golden
<fg=b0000000> black
<fg=b0ff7f00> orange
<fg=b0ffff00> yellow
<fg=b0ff00ff> light pink
<fg=b0ff007f> dark pink
<fg=b0ff0000> redish pink
<fg=b0800000> brown
<fg=b0ffc0cb> light purple
<fg=b06f00ff> dark blue
<fg=b0c0c0c0> grey
<fg=80ffffff> sky blue
<fg=b000ffff> light blue
<fg=b0bf00ff> purple
<fg=b08f00ff> dark purple
<fg=b0808000> mehandi green
<fg=b0ba55d3> light purple
<fg=b0f000f0> majenta
<fg=b00000ff> blue
<fg=b0b08080> steel grey
<fg=b0000080> movve
<fg=b0964b00> light brown
<fg=f0f00f0f> red
<fg=b000ff00> green






⛔️መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት የቻናላችንን link ሼር በማድረግ ተባበሩን።

👇👇
@achacher share
# ልብ___በል ………………!
የሆነ ሰዉ መልእክት ልከህለት ካልመለሰልህ ለምን አልመለሰልኝም ብለህ ሌላ
አተካራ ዉስጥ አትግባ፡፡ በግድ የሆነ ጓደኝነትና የፍቅር ግንኙነት የትም አይደርስም።
ለነገሮች ትንተና አትስጥ፡፡ አስፈላጊ ሆኖ የተገኘ ሰአት ብቻ እንጂ ስለእያንዳንዱ ነገር
ገለፃ የምታደርግ ከሆነ እራስህን ታደክማለህ
ሰዎችን መቼም ቢሆን ለመለወጥ አትነሳ፡፡ ማንም ቢሆን ላንተ ብሎ እራሱን
አይቀይርም፡፡ ሲጋራ የሚያጨስን ሰዉ 'አታጭስ' ስላልከዉ ማጨሱን አያቆምም ይልቅስ
ለምን ማጨስ እንደማያስፈልገዉ የሚረዳበትን ፍንጭ አሳየዉ...እምቢ ካለ አፈግፍግ
ከራስህና ከሚቀርቡህ ሰዎች ምረጥ ብትባል እራስህን ምረጥ፡፡ ይሄ እራስ ወዳድ
መሆን ሳይሆን በከባዱ የህይወትህ ሰአት የራስ ማንነትህ ከሌሎቹ በተለየ መንገድ እንዴት
እንዳሳለፈ ያዉቀዋል
አንተ ጋር ብቻ ያለ ፍቅር ከምትወደዉ ሰዉ ዉስጥ ከሌለ እራስህን እያጎሳቆልክ ነዉና
አሁኑኑ አቁም
የመጥፎ ባህሪ ድግግሞሽ የህይወት መርዝ ነዉ
ለማንም ቢሆን እራስህን ግልጥልጥ አድርገህ አታሳይ ምክንያቱም 90 ፐርሰንት
የሚሆነዉ ሰዉ ማንነትህን እስከጥጉ ካወቀ በደካማዉ ጎንህ መጫወት ይጀምራል
ሰዎች እንደሚወዱህ ቢነግሩህና ጥሩ ለመሆን ብትሞክርም አንተ ላይ መፍረዳቸዉን
አያቆሙም
ተጨማሪ አጫጭር ምክሮች ከፈለጉ
⚂ፔጁን join ያድርጉ⚂
@achacher share
ውድ አንባቢዎቼ በቅርቡ የሂባዋን ናርዶስ የሚለውን ልቦለድ ይዤላቹ ከች እላለው እስከዚያው መልካም ጊዜ 😊
የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል አንድ
(ፉአድ ሙና)
.
ህይወት ሰንሰለት ናት። ከአንዱ ወደ አንዱ ክስተት በሽግግር የተሞላች፣ ሞት የሚባል መቀስ ብቻ ከሽግግር የሚገታት፣ ህይወት በፍርግርጓ የተሳለች ፣ በመልካም በመጥፎ የተኳለች ፤ አድካሚ ሰንሰለት ናት። ይኸው ትናንት ልጅ ነበሩ። ከሱቅ ደስታ ከረሜላ እኩል የሚገዛላቸው ፣ አላፊ አግዳሚው በየተራ እያነሳ ከንፈሩን እያሞጠሞጠ የሚያጫውታቸው ፣ ለአንዳቸው ብቻ የተደረገ ለሌላቸው አለመደረጉ ነውር የሚመስላቸው ፣ ባለ ንፁህ ልብ ህፃናት ነበሩ።
የህይወት ሰንሰለት ከጨቅላነት ወደ ታዳጊነት ሲያዛውራቸው ፣ የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው ትምህርት ቤቶችን ሲያምሱ ፣ በቀለም ዳብረው ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሲገቡ እና ለዛሬዋ የምርቃት ቀናቸው ሲበቁ የሁለቱ ሰንሰለት አብሮ የተገመደ ነበር።
የአብሮነታቸው ብርታት ያስቀናው የጣሊያን ሰፈር ሰው ሁሉ ‹‹አንድ ወንድ ለሁለት እንዳያፈቅሩ ብቻ!›› እያለ የህብረታቸውን ስር መስደድ ሲመሰክር ፣ ‹‹ምን የባረካቸው ናቸው?›› እያለ ሲቀድሳቸው ይኸው ዛሬም አሉ። ከመልካቸው ውጪ የሚለያዩት በሀይማኖታቸው ብቻ ሳይሆን አይቀርም። ድሮ ድሮ ልጅነት ነገሮችን በመለየት የወጣትነት ቀለም መልኩ ሳይደበዝዝ በፊት ሂባ ከእናቷ ጋር ለጁምዓ ስግደት ወደ መስጂድ ስትሄድ ናርዶስ አብሬ ካልሄድኩ ብላ አልቅሳለች። ናርዶስ የጥምቀት ዕለት ከላይ እስከ ታች በነጠላ እና በሀበሻ ቀሚስ ተውባ ታቦት ለመሸኘት ከእናቷ ጋር ስትሄድ አብሮ ለመሄድ የምትቋምጠው ሂባ በእናቷ ስትከለከል ያነባችውን መቼም አትረሳውም። የሂባ ኡስታዝ የሰፈሩን ሙስሊም ህፃናት ሰብስበው እነሂባ ቤት ቁርዓን ሲያስተምሩ ናርዶስም አብሮ የመማሩን እድል አግኝታለች። መከልከል የደከማቸው ቤተሰቦቿ አረብኛ ቋንቋ እንድታውቅ ይረዳታል ብለው በመልካም ሰበብ ልባቸውን አሳርፈውት ነበርና የአረብኛ ፊደላትና ቁጥሮችን ከማወቅ አልፋ ከቁርዓን አጫጭሮቹ ምዕራፎች ውስጥ ከስድስት ምዕራፍ በላይ ተምራለች።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመግባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ሲሞሉ የሁለቱም ወረቀት ከግል መረጃቸው በቀር የተለያየ አልነበረም። ፈጣሪ ጥምረታቸውን ይወደዋል መሰል ከአዲስ አበባ 278 ኪሜ ርቃ ወደምትገኘው ሀዋሳ በአንድነት ተመደቡ። የኢንጅነሪንግ ተማሪ ሊባሉ ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አቀኑ። የኋላ የኋላ ምንም እንኳ የትምህርት ክፍላቸው ቢለያይም አብሮነታቸውን የማቆርፈድ አቅም ግን አልተቸረውም። የተገሩበት ዘዬ ተመሳስሎ የበረታ ነውና ስነ–ምግባራቸው እጅጉን የተዋደደ ነበር። እምነታቸው ላይ ያላቸው እውቀት ለተመሳስሎው እጅጉን አስተዋፅኦ አበርክቷል። ዛሬ ሊመረቁ ነው። ለአምስት አመታት የተማሩበትን ግቢ ለቀው ወደ አዲስ አበባ ሊመለሱ የዛሬውን ስነ ስርዓት መታደምና የትምህርት ማስረጃቸውን መቀበል ብቻ ቀርቷቸዋል።
.
የመኝታ ክፍላቸው የተለያየ ቢሆንም ሂባ ክፍል ባዶ አልጋ ስላለ ሰሞኑን አብረው ነበር የሚያድሩት። የንጋት ስግደት መድረሱን የሂባ ስልክ አላርም ሲያበስር ሁለቱም ከእንቅልፋቸው ባነኑ። ሂባ የመኝታ ቱታዋን እንደለበሰች መስኮቱ ጋር ቻርጅ ተሰክቶ የተቀመጠውን ስልኳን አደብ ልታስይዝ ሄደች። ‹‹ሂቡ እስኪ ስልኬን አቀብዪኝ›› ናርዶስ እንቅልፍ ጎሮሮዋ ላይ እንደተኛ አወራች።
‹‹ተነሽ ባክሽ አትጨማለቂ! ዛሬ እኮ...›› አለችና ሳትጨርሰው ስልኳን አቀብላት ልብሷን መቀያየር ጀመረች።
‹‹ቶሎ ስገጂና ፀጉሬን ታለሰልሺልኛለሽ›› ናርዶስ ከወገቧ ቀና ብላ ተቀመጠችና ልብሷን ለባብሳ በሩን ለመክፈት የምትታገለዋን ሂባን እያየች ቀጠለች ‹‹ስሚ ደሞ ውሀ ያለ አይመስለኝም ለማንኛውም ከዚህ የታሸገ ውሀ ይዘሽ ሂጂ›› ሂባ እንደወጣች ናርዶስ አልጋዋ ላይ ተቀምጣ ዶርሙን በአርምሞ ቃኘችው። እሷ ከተቀመጠችበት አልጋ ፊት ለፊት የሂባ አልጋ እንደተዝረከረከ አፍጥጧል። ከሂባ አልጋ በላይ ሀና አቅሏን ስታ ተጋድማለች። እሷ ያለችበት አልጋ የላይኛው ተደራቢ ላይ ሀሊማ ትገላበጣለች። ከእነርሱ አልጋ ወዲያ ያሉት አራት አልጋዎች ባዶ ናቸው። ናርዶስ ስልኳን ከፈተችና የተላከላትን መልዕክት አነበበች። ኢምራን ነበር። መልዕክቱ ‹‹እንኳን ለዚህ ውድ ቀን አበቃን የኔ ማሮች!›› ይላል። ፈገግ አለች። ኢምራን አሳዘናት። እሱ የደሴ ልጅ ነው። እነሱ ደግሞ የአዲስ አበባ! ከዚህ በኋላ የሚገናኙ አልመስልሽ አላት። ኢምራን የሂባ አፍቃሪ! ከጥንፍፍነቷ ፣ ከቁጥብነቷ በፍቅር የተዋደቀ! እሷም ትወደዋለች። የመጋባት እቅዳቸው የመጀመሪያው ጡብ ዛሬ እንደሚጣል ያምናሉ። ቤተሰቦቿ ለምርቃት ስነ ስርዓቷ ስለመጡ ልታስተዋውቀው አስባለች። እሱም እንደዛው። ‹‹ሚስኪን ኢምራን!›› አለች ናርዶስ እያሳዘናት። ለሂባ ደግሞ ምን ብሎ ልኮላት ይሆን? ማወቅ ፈለገች። ጉልበቷ ጋ የማይደርስ ስስ ቁምጣ በቦዲ እንደለበሰች ወደ ሶኬቱ ጋ ተራመደችና የሂባን ስልክ አንስታ ማንበብ ጀመረች። ‹‹ዛሬ ፈጣሪም ደስ ይለዋል። ዛሬ መልአክት አይከፉም። ዛሬ ከነብስሽ የተዋሀደው ነብሴ ህጋዊ እውቅና የሚያገኝበት የመጀመሪያው ጡብ ይቀመጣል። ደስ ይላል። ስወድድድድሽ!›› ይላል። አንብባ ጨርሳ ፈገግ ስትል ሂባ በሩን ከፍታ ገባች። በሩን ዘግታ ስልኳን ይዛ ወደ ፈገገችው ናርዶስ ተጠግታ አብራት ማንበብ ጀመረች። አንብባ ጨርሳ ስትፈግግ ናርዶስ እየሳቀች ‹‹ቆይ ምን ተዓምር ነው በማርያም? ምንም ሳይቀምስ እንዲህ የሚያክለፈልፈው? በስነ ስርዓት እንኳ አግኝተሽ አውርተሽው አታውቂም እኮ! ሰው በስልክ ብቻ እያወራ ተስፋ ካልቆረጠ አሪፍ ነው የምር!›› አለች። ሂባ መስገጃዋን እያነጠፈች ‹‹የራስሽን ማን ጫሪው አለሽ? በኔ ከምትሻፍጂ ይሻልሽ ነበር›› ‹‹ውይ ሂቡ ለካ አልነገርኩሽም። እናቱን! ለምርቃት አብረን እንተኛ ብሎኝ እኮ ነው። እንደ ኢምራን ስለ ትዳር የሚያስብ መስሎሽ ነው? በቃ ለመጋደም ነው የሚሮጠው የሆነ ተንከሲስ ነው። እሱን ብሎ ኪሩቤል! እኔ ደግሞ እኔ ምኔ የምርቃት ኮፍያ ነው ለምርቃትህ የምትደፋኝ? እመብርሀን እዛዉ ትድፋህ ብዬው መጣሁልሽ›› ሳቀች ፣ ናርዶስ ራሷ ተናግራ ራሷ መሳቅ ይቀናታል።
ሀና ከእንቅልፏ እየተነሳች ‹‹ናርዶስ ደሞ አንቺ ከተነሳሽ ሰው አይተኛማ? ስንት ሰዓት ሆኖ ነው ግን?›› አለች። ‹‹ባክሽ ሂቡ ሱብሂ ልትሰግድ ተነስተን ነው።›› ‹‹አንቺ ምን ቤት ነሽ ታዲያ! ደሞ ሀሊማ አትሰግድም እንዴ? አትቀሰቅሷትም?›› ናርዶስ ፈገግ ብላ ‹‹እሷ ሀይድ ላይ ናት ሶላት የላትም።›› አለች። ሀና በናርዶስ አረብኛ እየተወዛገበች ‹‹ሂባን ውጠሻታል እንዴ ምንድነው አይድ ምናምን?›› ‹‹አንቺ አምስት አመት ሙሉ ከሂባ ጋር ተምረሽ ይኼን አታርፊም? ባክሽ ሀይድ ማለት የወር አበባ ማለት ነው። የወር አበባ ያለባት ሴት ሶላት አትሰግድም ገቢቶ?›› አለች። ሀና ውዝግብ እያለች ‹‹እሱማ ሶላት የላትም አይደል እንዴ የሚባለው! ቆይ ሙስሊም ነሽ እንዴ?›› አለች፡፡ ናርዶስ እየሳቀች ‹‹አዎ በጓደኛዬ ሙስሊም ነኝ።›› አለቻት። ‹‹በቃችሁ አሁን ልስገድበት!›› ሂባ ለመስገድ ተመቻቸች። ናርዶስ ወደ አልጋዋ እየሄደች ‹‹ስሚ ሀይላንዱን ሱትራ አድርጊው! ደሞ አቋረጥሽኝ እንዳትዪ መመላለሴ አይቀርም!›› አለች። ሱትራ ከመስገጃው ፊትለፊት የሚቀመጥ መከለያ ነው። ከመከለያው ወደዛ ሰው መተላለፍ እንዲችል ለመርዳት የሚደረግ ነው። ናርዶስ የእስልምናን አብዛኛዎቹን እሴቶች ምናልባትም ከአንዳንድ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተሻለ ታውቃለች። ሂባ መስገድ ስትጀምር ቤቱ በፀጥታ ተዋጠ።
.
ውብ አምስት አመታት አልፈው የልፋቱ ፍሬ ሊበላ ዛሬ መነሳነሳቸው
ከቀኝ ወደ ግራ ይዞራል። ተመርቃችኋል ይባላሉ። ከዚህ በኋላ የእውነት ከህይወት ጋር መፋጠጥ የሚጀምሩበት ጊዜ ነው። ናርዶስ የኢምራን እና የሂባ ፍቅር እጅጉን አሳስቧታል። ‹‹ናንዬ ምን ትላት ይሆን?›› እያለች በውስጧ ትብሰለሰላለች። ‹‹ስንት ሰዓት ሆነ?›› ሀሊማ ሰግዳ ጨርሳ መስገጃዋ ላይ ተቀምጣ አውራ ጣቷን በጣቶቿ ክርከሮች ላይ እያርመሰመሰች የምትዘክረውን ሂባን እያየች ጠየቀች። ናርዶስ ቀደም ብላ ‹‹አስራአንድ ከሀያ ሆኗል። በቃ ተነሺ እንዘገጃጅ በጊዜ ቦታችሁን መያዝ አለባችሁ ምናምን እያሉ ሲዘፍኑ ነበር!›› አለች። አራቱም ከአልጋቸው ተነስተው ከተጣጠቡ በኋላ ዶርሙ ውስጥ መኳኳሉ ደራ። አንዷ የአንዷን ፀጉር ማስተካከል ፣ አንዷ አንዷን ማለባበስ ..... ውክብ አሉ። ውክቢያው አንድ ሰዓት ሊሞላው ሲቃረብ ተዘገጃጅተው ጨረሱ። ከተዋበው ቀሚሳቸው ላይ የምርቃት ጋወን ደረቡ ፣ ኮፍያ ደፉ። ከሶስቱ አጠር ያለ ቀሚስ የለበሰችው ሀና ብቻ ነች። ናርዶስን ጨምሮ የቀሩት ቁርጭምጭሚታቸውን የሸፈነ አንድ አይነት ቀሚስ ለብሰዋል። የሀና አጠረ እንጂ ተመሳሳይ ነው። በስልካቸው ፎቶ ለመነሳት የሚረዳቸውን ዱላ (Selfi stick) ከስልካቸው ጋር አጠማምደው በተመሳስሎ እንደነገሱ ወደ ምረቃው ስታዲየም ለመውሰድ ተማሪዎችን ወደሚጠባበቀው አውቶብስ አቀኑ። ለየት ያለ ስሜት ውርር ሲያደርጋቸው ይታወቃቸዋል። ከተደረደሩት አውቶብሶች ፊት በአንድ ከኋላ ክፍት መኪና ላይ የተሰቀለው ስፒከር ‹‹እንኳን ደስ አላችሁ›› የሚለውን ታዋቂውን የምርቃት ዜማ ያስደምጣል። እንባ ሲያንቃቸው ተሰማቸው። አምስት አመታትን ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ብዙ መሰናክል አልፈው ያገኟት ቀን ናትና የዛሬው ደስታ የሚያስታውሳቸው ያለፈውን መከራ ነው። አውቶብሱ ውስጥ ገብተው እንደተቀመጡ ኢምራን ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ጥቁር ሰማያዊ ሱፉ ላይ የምርቃት ጋወኑን እንደደረበ ሲፍለቀለቅ መጣ። ናርዶስ ከተቀመጡበት የአውቶብሱ የመጨረሻ ወንበር አይኖቿን በወንበሮቹ መሀል ሰንጥቆ ወደ እነርሱ የሚመጣው ኢምራን ላይ ጥላ ‹‹ሚስኪኑ ውድሽ መጣ!›› አለች። ኢምራን ከሂባ አጠገብ ተቀመጠ። ሁለቱ ጓደኞቹ ከፊት ለፊቱ ተቀመጡ። ፎቶ እየተነሱ እየተሳሳቁ ሀዋሳ ስታዲየም ደርሰው ቦታ ቦታቸውን ያዙ። የተለመደው በተማሪው የማይደመጥ ንግግር እየተደረገ እነሱም መድረክ ላይ ሰው መኖሩንም ዘንግተው ፎቶ በመነሳት ከተጠመዱ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙርን በአንድነት ሳግ እያነቃቸው ዘምረው የምርቃት ስነ ስርዓቱ ተጠናቀቀ። ተመራቂዎቹ ልብ ሰጥተው ያዳመጡት መነሳነሳቸውን ከቀኝ ወደ ግራ አዙሩ ሲባልና መዝሙር ዘምሩ ሲባል ብቻ ነበር። መነሳነሳቸውም ዞረ። መመረቃቸውም ተበሰረ።
የምርቃት ስነ ስርዓቱ እንደተጠናቀቀ ሁሉም ወደ ቤተሰቡ ተበታተነ። የናርዶስ እና የሂባ ወላጆች በአንድነት እየጠበቋቸው ነበር። አበባው ተበርክቶላቸው ምሳ ሊበሉ ወደ ሀይሌ ሪዞርት ለመሄድ ከስታዲየሙ ሲወጡ ኢምራን ከቤተሰቦቹ ጋር ቆሞ ሂባን ሲጠብቃት ተገናኙ። የስልክ ኔትወርክ እጅጉን ያስቸግር ስለነበር ደውሎ ሊነግራት አልቻለም። አጋጣሚ ሆኖ ባያገኛት ኖሮ ምናልባትም ሊገናኙ የሚችሉት ወደ ግቢ ከተመለሱ በኋላ ነበር። ኢምራን ቀድሞ ሁሉንም ነገር ለቤተሰቦቹ ተናግሮ ነበረና ልክ እንዳገኛት ጠርቶ ከቤተሰቦቹ ጋር አስተዋወቃት። አንገቷን እንደደፋች ተዋውቃቸው ቆመው ወደሚጠብቋት ቤተሰቦቿ ተመለሰች። ሂባ ኢምራንን ማታ እራት ሲበሉ ከቤተሰቦቿ ጋር ልታስተዋውቀው አስባለች። ጎረቤታሞቹ የሂባ እና የናርዶስ ቤተሰቦች ድምቅ እንዳሉ ምሳቸውን ለመብላት እና በዛውም ለመዝናናት ወደ ሀይሌ ሪዞርት አቀኑ።
.
ይቀጥላል...

@achacher share
👍1
የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል ሁለት
(ፉአድ ሙና)
.
የሂባ አባት አቶ ጀሚል እና እናቷ ወ/ሮ ዘምዘም የሂባን ታናሽ ወንድም ኢክሪማን አስከትለው ነበር የመጡት። የናርዶስ አባት አቶ ገበየሁ እና እናቷ ወ/ሮ ዘርፌ ደግሞ የናርዶስን የአክስት ልጅ ኤደንን ይዘው መጥተዋል። ሀይሌ ሪዞርት ገብተው ምሳቸውን ከበሉ በኋላ ናርዶስ ዙሪያውን ጠረጴዛውን የከበቡትን ቤተሰቦቿን እና ጎረቤቶቿን እያየች ‹‹የዛሬውን ቀን ልዩ የሚያደርገው ...›› ስትል ሁሉም ትኩረታቸውን ወደሷ አደረጉ። የሂባ እናት ወ/ሮ ዘምዘም ፈገግ ብለው ‹‹ናርዶሴ እስኪ እንደውም እኔን አስቀድሚኝ ለየት የሚያደርገውን እኔ ልናገር›› አሉ።
‹‹እሺ ናንዬ ምን አለ አንቺ ጋ?››
‹‹እኔ ጋ ያለውማ .... የዛሬዋ ተመራቂያችን ቀጣይ ሙሽራ መሆኗ የሚበሰርበት መሆኑ ነው። ከተመለስን በኋላ ለሂባችን ኒካህ እናስራለን።››
ናርዶስ ፈገግታዋን ግራ መጋባት እየወረሰው ፣ ሂባ የኢምራንን ጉዳይ ነግራቸው ይሆን ብላ ግራ እየተጋባች ወደ ሂባ ስትዞር የሂባ ፊት በአንዴ ደም ሲለብስ አስተዋለች። የፊቷን የተፈጥሮ ቅላት ቁጣዋ ሲያግዘው ፍም መሰለ። ናርዶስ ያሰቡት ኢምራንን የማስተዋወቅ እቅድ እየተጨናገፈ እንደሆነ ተሰማት። ድምጿ እየተሰባበረ ‹‹ከማን ጋር ነው የምታስረው?›› አለች። ወ/ሮ ዘምዘም የሂባ መቆጣት ፣ የናርዶስ መደናገጥ ግራ እየገባቸው ‹‹ዚያድ የጋሽ ሳሊም ልጅ ፣ ዋናው መንገድ ጋ መኪና መሸጫ ያለው አወቃችሁት? ባለፈው ሽማግሌ ልኮ ነበር። ያው በምንም አይታማም እሱ! ለነሀሴ ብለነዋል። ትምህርታችሁ ላይ እንድታተኩሩ ብለን ነው ያልነገርናችሁ!›› አሉ። ናርዶስ ሂባ የመናገር አቅሟ መሰለቡን ልብ ካለች በኋላ ለመከራከር ወደ ወ/ሮ ዘምዘም ዞረች፡፡
‹‹ግን እኮ ናንዬ ሂባ የምትወደው ሰው አለ። ዛሬ ልታስተዋውቃችሁ አስባ ነበር።›› አቶ ጀሚል ጣልቃ ገቡ፡፡ ‹‹አይ ናርዶሴ የናንተው ቢጤ ተማሪ ይሆናል እኮ ይኼኔ!››
‹‹አዎ ነው ጋሼ። ሂባ ከወደደችው ተማሪ ይሁን ሌላ ምን ለውጥ አለው? ደሞ ተመራቂ ነው።››
‹‹አይሆንም ገና በእግሩ እስኪቆም ማገዶ ይፈጃል። እስከዛ ደግሞ የሷ እድሜ አይቆምም። ፍቅር ምናምን እያላችሁ ድራማ አትስሩ። እኛ ስንጋባ ጭራሽ የት እንተዋወወቅ ነበር? አይደል እንዴ ገበየሁ? ዘምዘሜ?›› ወደ ግራ እና ቀኝ እየተዟዟሩ ድጋፋቸውን በአይናቸው ለመኑ። ‹‹ልክ ነው ጨዋታ አያስፈልግም። አሁን ልጅ አይደለሽም አግብቶ መሰብሰብ ነው። ቤተሰብ ያመጣው ነው ደሞ ጥሩ!›› ጋሽ ገበየሁ ተደረቡ።
ሂባ ድምጿን ሳግ እያጠረው ‹‹እንዴ ገብሽ አንተም?›› አለች። ኤደን ክርክራቸውን በደምብ ካዳመጠች በኋላ ጥያቄዋን ሰነዘረች። ‹‹እንዴ ሰው ካልወደደው ሰው ጋር እንዴት ይኖራል?›› ወ/ሮ ዘምዘም እና አቶ ገበየሁ ለመልስ ተሽቀዳደሙ። ‹‹ከተጋቡ በኋላ መውደዷ የት ይቀራል?›› ጋሽ ገበየሁ የሰነዘሩት መልሳማ ጥያቄ ነበር።
‹‹ባትወደውስ?››
‹‹ትወደዋለች።›› በአንድነት ጮኹባት።
‹‹የምወደው ልጅስ?›› ሂባ ቀዩ ፊቷ ላይ ካሉት ሁለቱ ትላልቅ አይኖቿ የእንባ ዘለላዎቿ እየተሽቀዳደሙ በመጠኑ ሰልከክ ያለውን አፍንጫዋን አቋርጠው ከእንጆሪ ከንፈሮቿ ላይ እያረፉ ጠየቀች።
‹‹ከአሁን በኋላ ልጅነት የለም ወደድኩ ምናምን አይሰራም። አዲስ አበባ ስንሄድ ትረሺዋለሽ። ደሞ የዘንድሮ ፍቅር!›› ወ/ሮ ዘምዘም እንደመቆጣት እያሉ ተናገሩ።
ወ/ሮ ዘርፌ እና ኢክሪማ ዝም ብለው ከመከታተል ውጪ ቃል አልተነፈሱም። ሁለቱም ውስጥ ተመሳሳይ ስሜት አለ። የምትወደውን ብታገባ ደስ ይላቸዋል። ሆኖም ግን ጉዳዩ ሽማግሌ ተልኮ ቀን የተቆረጠበት ስለሆነ መቃወማቸው ለውጥ እንደሌለው አስበው ዝምታን መርጠዋል። ናርዶስ የፈራችው እንደደረሰ ገባት። ድሮውንም የወ/ሮ ዘምዘምን ፀባይ ስለምታውቅ እንቅፋት እንደምትሆን አስባ ነበር። በዚህ ፍጥነት ይሆናል ብላ ግን አልገመተችም።
.
ሂባ እጅጉን ግራ ገብቷታል። ህልሟ ሁሉ ሲተን ታያት። ሁሌም ከአእምሮዋ የማይጠፋው የኢምራን ንግግር ታወሳት። ‹‹ሳገባሽ አንቺ የኔ ነሽ። እኔም ያንቺ ብቻ ነኝ። ለአካልሽ ብቻ ሳይሆን ለህልምሽ መፋፋት እና መሳካትም አጋርሽ እሆናለሁ። ሁሌም አዕምሮሽን ለማርካት የምታደርጊውን ጥረት አግዝሻለሁ። ከሁሉም በላይ እረዳሻለሁ። የአልጋ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነገር ባልሽ እሆናለሁ።›› ነበር ያላት። ለሱ ያላትን ፍቅር ካፈረጠሙባት ንግግሮቹ ዋነኛው ይኼ ነበር። ህልሟ በትዳር ምክንያት እንደማይጨናገፍ ፣ በኬሚካል ኢንጅነሪንግ መስክ ለመድረስ ያለመችው ከፍታ ላይ ልትደርስ ማረጋገጫ ሰጥቷት ነበር። እንደሱ ማንም ሊረዳት እንደማይችል ታውቃለች። ዛሬ ተራራውን ህልሟን በአንዴ ዱቄት የሚያደርግ ዱብዳ ወድቆባታል። ያላት ምርጫ ሁለት ነው። ቤተሰቦቿን አሊያም ኢምራንን መክዳት። ሁለቱም ከብዷታል።
የሀይሌ ሪዞርት ቆይታቸውን እንደጨረሱ በቀጥታ ያመሩት ወደ ፍቅር ሀይቅ ነበር። ናርዶስም ሂባም ስሜታቸው ቢረበሽም ቤተሰቡን ላለማስቀየም ሲሉ አብረው ለመሆን እየሞከሩ ነው። ፍቅር ሀይቅ ሲደርሱ በርካታ ተመራቂዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው ሀይቁ ላይ እየተንሳፈፉ ነበር። ፍቅር ሀይቅ አይን ማየት የሚችለው ያህል ተንጣሎ ፣ ከውስጡ በበቀለው ሳር ተውቦ ፣ አሳ ፣ ጉማሬ ፣ ዘንዶውን አቻችሎ በውስጡ እንደያዘ በጨዋ ደንብ እንግዳዎቹን ያስደስታል።
ለግማሽ ሰዓት ያህል የሚለበልበውን የሀዋሳን ፀሀይ ሀይቁ ዳር ቆመው ካስተናገዱ በኋላ ጀልባው ላይ ወጥተው መንሳፈፍ ጀመሩ። ዳክዬዎች ፣ የተለያየ አይነት ቀለም ያላቸው አሞራዎች ብዙ ብዙ የተፈጥሮ ጥበቦችን ይታዘባሉ። ሂባ እና ናርዶስ ግን የሂባ ደስታ መነጠቅ ብቻ ይታያቸዋል። የጀልባው የመጨረሻው ወንበር ላይ ተቀምጠው ማንሾካሾክ ጀመሩ።
‹‹ሂቡ ምን አሰብሽ?››
‹‹ጨንቆኛል ምንድነው ማድረግ ያለብኝ?››
‹‹በቃ ለኢምራን የተፈጠረውን በእርጋታ አስረጂው!››
‹‹ምን ብዬ? ክጄሀለሁ ብዬ?›› ሳታስበው ድምጿ ከፍ አለ። ቤተሰቦቿ በተፈጥሮ ውበት ተደምመው በጩኸት እያደናነቁ ነበርና አልሰሟትም።
‹‹ድምፅሽን ቀንሺ! አልከዳሽውም እኮ! በቃ የተፈጠረውን ንገሪው። ትሞቻለሽ እንዴ? ወይስ ሌላ ያሰብሽው አማራጭ አለ?››
‹‹እሱ እኮ በጣም ነው የሚወደኝ።››
‹‹እና ይዘኸኝ ጥፋ ልትይው ነው?››
‹‹አላውቅም። ምንም ቢሆን ግን አባዬ እንዲያዝንብኝ አልፈልግም፡፡ እኛን እዚህ ለማድረስ የሆነውን አውቃለሁ፡፡ እሱን መካድ አልችልም፡፡››
ሁለቱም በሀሳብ ሰጠሙ። ኢምራንን እንደበደሉት ተሰማቸው።
‹‹ይዘኸኝ ጥፋ ብለው ራሱ ወዴት ይዞኝ ይጠፋል? ለራሱ ከቤተሰብ ድጎማ አልተላቀቀም። እኔም እንደዛው።››
‹‹ቢችል ኖሮ ናንዬን እና እኛን ትተሽ ልትጠፊ ነበር?›› ናርዶስ ተቆጣች።
‹‹እኔንጃ ናርዲዬ››
‹‹ያን ያህል እንኳ ራስ ወዳድ አይደለሽም።››
ዝምታ ወረሳቸው። ናርዶስ ፊቷ ደመነ። ለወትሮ በፈገግታ የሚሰረጉደው ጉንጯ እንደጨለመ ሰረጎደ። አነባች። ሂባ በድንጋጤ ‹‹ናርዲ እንዴ?›› አይኖቿ በተማፅኖ ተቁለጨለጩ። ተቃቀፈው አነቡ። ይህ ሁሉ ሲሆን ከወ/ሮ ዘርፌ እና ከኢክሪማ በቀር ያያቸው አልነበረም።
.
የምርቃታቸው ቀን ደስታ በሂባ ስብራት ተቸልሶ እንደደበዘዘ አለፈ። በቀጣዩ ቀን ከሰዓት በኋላ የሁለቱም ቤተሰቦች ወደ አዲስ አበባ በአንድነት ተመለሱ። ሂባ እና ናርዶስ መጨራረስ ያለባቸውን የመልቀቀያ ፎርም ማስሞላት ስላለባቸውና ጊዜያዊ ድግሪያቸውን (temporary degree – Tempo) መቀበል ስለሚኖርባቸው አብረዋቸው አልሄዱም።
ማክሰኞ ጠዋቱን ኢምራን ሴቶች ዶርም መጥቶ አስጠራቸው። ያለፉትን ቀናት በተደጋጋሚ
ሲደውል ስልክ አላነሱለትም ነበር። የሂባን ቤተሰቦች ለመተዋወቅ ቋምጦ ስልኳን በጉጉት ሲጠብቅ ቢውል ቢያድር ህልም ሆኖ ቀረበት። ውስጡ በጣም ተረብሿል። ናርዶስና ሂባ ሺቲያቸውን እንደለበሱ ናርዶስ በነጠላ ፀጉሯን ሸብ አድርጋ ፣ ሂባ ደግሞ ሂጃቧን ራሷ ላይ በደንቡ ጠምጥማ ከሴቶች ዶርም መግቢያ ትንሽ ፈንጠር ብሎ የቆመው ኢምራን ጋ ሄዱ።
ኢምራን ሂባን እንዳየ ፊቱ በፈገግታ ደመቀ። ለሁለት ቀን ዘግታው እንደቆየች ሁሉ ሳይረሳው አልቀረም።
ሂቡዬ" ቢጎርሳት ደስ ይለዋል።
‹‹ኢምሩ ... ›› ሳግ ተናነቃት።
‹‹ናርዲ›› ተቁለጨለጨ።
‹‹እ ሰውየው››
የሂባን የአይን ክዳን እንባዋ አሸነፈው። ተርገበገበ። እንባዋ ጉንጮቿ ላይ ተኛ። አተነፋፈሷ ፈጠነ። ትከሻዋ ከፍ ዝቅ ማለት ጀመረ። ተንሰቀሰቀች። ናርዶስ ሂባን አቅፋ ማባበል ጀመረች። ኢምራን ጨረቃ ላይ የተጣለ መሰለው። ሁሉም ነገር አዲስ ሆኖበታል።
‹‹ሂባዬ? ምን ሆንሽብኝ?›› እንባው ቢታገለውም ወንድ መሆኑን አስታወሰው። ወንድ ሆኖ ሰው ፊት ማልቀስ ከመንጋው ባህል ጋ ይጋጫል ሲል አሰበ።
ናርዶስ ሂባን ትንሽ ካረጋጋቻት በኋላ ማስረዳት ጀመረች።
‹‹ኢምሩ ታፈቅርሀለች ግን ቤተሰቦቿ ከሌላ ሰው ጋር ጋብቻዋን ተዋውለው ጨርሰዋል። ሳትወድ በግዷ ካንተ ተነጥቃለች።›› በአጭሩ አረዳችው።
ኢምራን ጭንቅላቱ ሲከብደው ተሰማው። ቁጢጥ አለ። እሱ እኮ ኒካህ ካሰሩ በኋላ የት መኖር እንዳለባቸው ከእናቱ ጋር ተከራክሯል። እንዲህ ያለ ዱብዳ ይገጥመኛል ብሎ በፍፁም አላሰበም። እህቶቹ ኒካሁ ከታሰረ በኋላ ቶሎ ወደ ደሴ ይዟት እንዲመጣ ቃል አስገብተውታል። ጉጉታቸውን አላበርድም ብሎ ግን ጭራሹን አልገመተም ነበር። የለበሰው ቱታ እና ቲሸርት ሰውነቱ ላይ የሌለ ፣ የተራቆተ የተራቆተ ፤ ልቡ አካባቢ ንፋስ የገባ መሰለው። ሆዱ ተረበሸ። እንባው አሸነፈው። ሂባ እንባውን ስታይ መንሰቅሰቋ በረታ። ሰው እስኪታዘብ ድረስ ረዥም ሰዓት ባሉበት ረግተው አነቡ። ናርዶስም አብራ ታነባለች።
ኢምራን እንባውን ጠራርጎ ከጨረሰ በኋላ ‹‹ሂባዬ የሚለወጥ ነገር ካለ በማንኛውም ሰዓት ንገሪኝ። ሁሌም እወድሻለሁ። የሚያገባሽ ሰው እድለኛ ነው። የምር ... ደሞ እንደሚያስደስትሽም ተስፋ አደርጋለሁ። መልካም ህይወት ሂባዬ ... መልካም ህይወት!›› ትቷቸው ወደ ወንዶች ዶርም ሩጫ በሚመስል እርምጃ ተፈተለከ። ሂባ መንሰቅሰቋ በረታ። ናርዶስ አብራ እያለቀሰች አቅፋ እያባበለቻት ወደ ዶርም ገቡ።
ሂባ ፈጣሪ የቸራትን ውብ እድል ያበላሸች መሰላት።ቤተሰቦቿ አበሳጯት። ፍርሀት ፍርሀት አላት። ‹‹ለምን ሳፈቅረው ይኼን አላሰብኩም? ለምን ሲወደኝ ሁኔታዎች ምቹ አለመሆናቸውን አልተገነዘበም?›› ራሷን ጠየቀች። ፍቅር በምክንያት ይከሰት ፣ በስሌት ይፈጠር ይመስል። መልሱ ለራሷም አልገባትም። የገባት አንድ ነገር የወደደችውን እና የወደዳትን ሰው ለቤተሰቧ ደስታ ብላ መሰዋቷን ነው። ግን ደግሞ ….. ትፈራለች።
.
ይቀጥላል...


fuadmu
@achacher share
የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል ሶስት
(ፉአድ ሙና)
.
በሰውኛ አዕምሯቸው ፈፅሞ ባልታሰበ ፣ በፈጣሪ መዝገብ ምድር እና ሰማይ ከመፈጠራቸው ሀምሳ ሺህ ዓመታት ቀድሞ በተከተበ ምክንያት ከሶስት አመት የትዳር ህልሟ ከኢምራን ጋር መለያየቷ እውን ሆነ። የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለተመራቂ ተማሪዎቹ የትምህርት ማስረጃቸውን አስረክቦ ግቢውን በተወሰነ ቀነ ገደብ ለቀው እንዲወጡ የሚያሳስብ ማስታወቂያ ለጠፈ። ኢምራን የስብራቱን ወሬ ከተረዳ ወዲያ ረቡዕ ማታ ድረስ ከናርዶስ ጋር እንጂ ከሂባ ጋር ስልክ አልተደዋወለም ነበር። ሀሙስ ጠዋቱን ግቢውን ለቀው መሄዳቸው መሆኑ ሲገባው የሞት ሞቱን ሂባ ጋር ደወለ። ዶርም ውስጥ ብቻዋን ነበረች። ናርዶስ ልትተጣጠብ ከሄደች አልተመለሰችም። ሀና እና ሀሊማ ትናንት ማታውን ወደየቤታቸው ሄደዋል። ስልኩን አንስታ ዝም አለች።
‹‹ሂባ››
‹‹ኢ...ም...ሩ››
‹‹ቻው ልልሽ ብዬ ነው። አላህ ይጠብቅሽ እሺ። ቻው!››
እንባዋን መቆጣጠር አቃታት። ‹‹ኢ ... ም ... ሩ ... አላህ ይጠብቅህ›› ተንሰቀሰቀች።
ኢምራን እንባዋ ተጋባበት። ‹‹አታልቅሺ እሺ ሂባዬ ፣ አላህ አላለውም በቃ! አታልቅሺ›› ንግግሩ በሳግ ተገታ።
ረዥም ሰዓት ለቅሶ ተደማመጡ። ናርዶስ ወደ ዶርም ስትገባ ሂባ ስልክ እያናገረች ስታነባ አገኘቻት። ስልኩን ተቀብላ ተመለከተችው። ኢምራን መሆኑን ስትረዳ ወደ ጆሮዋ አስጠግታ ‹‹ኢምሬ በቃ አሁን ራሳችሁን መጉዳት የለባችሁም። በቃ ያለቀ ጉዳይ ነው።›› አለችና ተሰናብታው ስልኩን ዘጋችው። ሰሞኑን ሂባን ማባበል ቋሚ ስራዋ ሆኗል።
ሶስት ሰዓት ሲሆን ሀዋሳን ለቀው ወደ አዲስ አበባ ተጓዙ። ሻሸመኔን አልፈው ወደ ዝዋይ ሲጠጉ ሂባ ራሷን ማጠንከር አቃታት። ተርበተበተች። ናርዶስ በምታውቀው ሁሉ የማፅናኛ መንገድ እያባበለቻት ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ ተወልደው ወዳደጉባት ፣ ክፉውንም ደጉንም አብረው ወዳሳለፉባት የህብረቀለማት ውህድ አዲስ አበባ ገቡ።
.
ሀሙሱን ወደ አዲስ ከገቡ ጀምሮ የሁለቱም ቤተሰብ በአንድነት እሁዱን ምርቃት ለመደገስ የሚያደርገውን ሽር ጉድ ሲያግዙ ነበር። በድግሱ ቀን ደግሞ የሂባ የወደፊት ባል ይመጣል። ጁምዓ እና ቅዳሜ አልፈው የሰፈር ሰው ለጉድ በጉጉት የሚጠብቀው የሁለቱ አብሮ አደጎች የጋራ የምርቃት ድግስ መካሄድ ጀመረ። አብሮአደጎቻቸው ፣ ዘመድ ፣ የሰፈር ሰው ስጦታውን ያጎርፈዋል።
አመሻሹን የሂባ አዲሱ እጮኛ ዚያድ ድግሱን ታደመ። ዝግጅቱ ሊጠናቀቅ ገደማ ቤተሰቦቿ አስጠርተው አስተዋወቋት። የወርቅ ሀብል አንገቷ ላይ አጠለቀላት። በርግጥ ከዚህ በፊት በአይን ታውቀዋለች። ወንዳወንድነቱ ፣ መልኩ እንዲሁም ኪሱ እጅጉን ቆንጆ ናቸው። ለሂባ ግን በኪሱ እስክሪፕቶ ብቻ የሚይዘው ባለጎራዳ አፍንጫው ኢምራን እጅጉን የተመረጠ ነው።
ከናርዶስ ጋር ሆነው ትንሽ ካጫወቱት በኋላ ተሰናብቷቸው ሄደ። ልክ ከዚያድ ጋር እንደተለያዩ ናርዶስ ፍልቅልቅ እያለች ‹‹አንቺ wow የሌለ ቀሽት አይደል እንዴ?›› ትከሻዋን ቸብ አደረገቻት።
‹‹ለራሱ ነው ባክሽ!››
‹‹ከዚህ በኋላ እኮ ያንቺም ነው!››
‹‹እኔንጃ እስኪ አላህ ያግራው ነው የሚባለው!››
‹‹ያመቻቸዋል አይዞን!›› ተመልሰው ወደ ድንኳኑ ገቡ።
ሂባ ሰፈሩ ውስጥ እጅጉን ትከበር ስለነበር የሰፈሯ ጎረምሶች አንድም ቀን ለየት ባለ መልኩ አናግረዋት አያውቁም። ረዥም አመታት አብረው ስለኖሩ እንደወንድም እና እህት የመተያየት ጥሩ ባህል አዳብረዋል። ዛሬም ለድግሱ ከሚሯሯጡት መካከል አብዛኛዎቹ የሰፈሯ ጎረምሳዎች ናቸው። አብርሀም ፣ ሰኢድ እና ከድር የሰፈራቸው ልጆች ሳይሆን እህቶቻቸው የሚመረቁ ያህል ዝግጅቱን ለማሰማመር ከቅዳሜ ጀምሮ እየተንደፋደፉ አሉ።
በበርካታ ሰዎች ጥረት ድግሱ እጅጉን ባማረ መልኩ ሲጠናቀቅ ለእድምተኞቹ ከሀያ ቀናት በኋላ ሂባ እንደምትሞሸር ተበሰረ። የታዳሚው ደስታ እጅጉን ከፍ አለ።
*
የማይፈለግ ቀንን ያህል ፈጥኖ የሚደርስ የለም። የነሀሴ መምጣት ሂባን በእጅጉ እያሸበራት ነው። ከምትወደው ሰው ምናባዊ እቅፍ ተነጥላ ካልለመደችው ሰው ጋር መኖር ልትጀምር ነው። በየመሀሉ ከዚያድ ጋር እየተገናኙ ስለ ጋብቻው ይመክራሉ። ካገባች በኋላ የመማር እና የመስራት ፍላጎት እንዳላት ስትነግረው ብዙም አልተዋጠለትም ነበር። ከብዙ ውይይት በኋላ ግን በሀሳቧ ተስማማ። ሰርጉ ሊደረግ አንድ ሳምንት ሲቀረው ለመጨረሻ ጊዜ ኢምራንን ለማውራት ፈለገች። እጆቿ እየተንቀጠቀጡ ደወለችለት። ሶስቴ ከጠራ በኋላ ተነሳ።
‹‹ኢምሩ››
‹‹ሂባዬ››
‹‹ኢ .....›› ለቅሶዋ አደናቀፋት።
‹‹ሂባ ጋብቻው ቀረ በይኝ በአላህ››
‹‹አ ል ቀረም ኢምሩ ..... አልቀረም!››
‹‹ታዲያ እንዴት ደወልሽልኝ?››
‹‹ምናልባት ከዚህ በኋላ .... ድምፅህን ካልሰማሁ ብዬ ነው›› ድምጿ ጥልቅ ብሶት አለው።
‹‹ሁሌም ዱዓ አደርግልሻለሁ..... አይዞሽ እሺ! ደሞ አላማሽን እንዳትረሺ ትልቅ ቦታ ላይሽ እፈልጋለሁ።›› መለቃቀስ ጀመሩ። መለያየታቸው እውን መሆኑ ላይቀር ፤ እጅጉን አነቡ።
ውስጧ ላይ ሁለት ወቀሳ አለ። ለምን ከጅምሩ አብሬው ሆንኩ የሚለው የመጀመሪያው ሲሆን ከዳሁት የሚለው ደግሞ ሁለተኛው ነው።
የሰርጉ ቀን ደረሰ። የኒካህ ስነ ስርዓቱ ሀሙስ እለት ተካሄደ። ሽማግሌዎች መጥተው ከሂባ ቤተሰቦች ጋር ከተወያዩ በኋላ በአምስት ሺህ ብር ጥሎሽ ኒካህ ታሰረ። ይኼን ሰሞን ናርዶስ ከሂባ ጎን አትለይም። አብሮአደጓ ልትሞሸር መሆኑ ለሷም የሚዋጥ አልነበረም። ካገባች በኋላ ሌሎች አላማዎቿን ማሳካት ይሳናታል የሚለው ስጋት እጅጉን እየረበሻት ነው። ሆኖም ግን የስራ ማስታወቂያዎች በወጡባቸው ቦታዎች ሁሉ ከማመልከት አልቦዘኑም።
ከቅዳሜው ምሽት ጀምሮ ይኸው እስከዛሬው የሰርግ ቀን ድረስ የሴቶቹ ጭፈራ ደርቷል። የሚገጠሙት ግጥሞች ሲደመጡ ከልብ የሚፋቀሩ ሰዎች ሰርግ እንጂ በቅጡ የማይተዋወቁ ሰዎች ጋብቻ አይመስልም።
‹‹ለምነህ ለምነህ ተሀጁድ ሰግደህ፣ እንዲሁም አልቀረህ ሂቡን አገኘህ፣›› የሚሉት ስንኞች ግን ሙሽራውን ሳያስቁት አልቀሩም።
*
ኢምራን በጠዋቱ ተነስቶ ከተማውን ሲያካልል ቆይቶ ለደሴ ከተማ መገለጫ እስከመሆን የደረሰችው አንድ ለእናቷ የመሰለች ደ ሴ የሚል ፅሁፍ ግንባሯ ላይ የተለበደባት ባለ ገፀ–መስታወቷ ህንፃ አቅራቢያ ደረሰ። በዚህ ህንፃ ከሂባ ጋር ተበሻሽቀዋል። ደሴን እያወደሰ ሲያወራ ‹‹እኔ እኮ ደሴ ሲባል ሁሌ ያንን ፎቅ ስትፖስቱ ደሴ ከተማ ናት ወይስ ፎቅ ብዬ ይምታታብኛል።›› ብላው ለሁለት ቀን ተኳርፈዋል። ናርዶስ በዚህ ሳቢያ ማኩረፉ አናዷት ‹‹ስማ አንተ ደሴ ስንተኛ ፎቅ ላይ ነው የምትኖረው?›› ብትለው እሷንም ደርቦ ዘግቷታል። ሆኖም የፍቅር ነገር ሆኖበት ተወልዶ ያደገባት ደሴ ላይ ብትቀልድም ሂባን ከደሴ ማሳነስ አልሆነለትም። ነቆራቸውን ችሎ ታርቋቸዋል። ግና ዛሬ ነቋሪዎቹ ትተውት ሄደዋል። ደሴ ደግሞ እንደ እናት እቅፍ በሴት ቀይረኸኛል ሳትል ብሶቱን ያረግብባት ዘንድ አዝላዋለች። ህንፃውን አሻግሮ እየተመለከተ ‹‹ደሴ ያንቺ ግፍ ይሆን እንዴ ወዳንቺው የመለሰኝ?›› ሲል በልቡ ቀባጠረ። ደሴ አትሰማውም። ደሴ መንሳትም ፣ መቸርም አትችልም። ደሴ ግዑዝ ናት። ግን ለማጣቱ ሰበብ ፈለገ። ራሱን ጥፋተኛ የሚያደርግበት ፣ ፍቅሩን ነፃ የሚልበት ምክንያት ፈለገ። እውነታውን እንደወረደ መቀበል ከበደው። ፈጣሪ የወሰነው ነው ብሎ ልቡን ማሳረፍ ጠጠረው። የተሻለውን ይሰጠኛል ብሎ ለማሰብ መካሪ አጣ። ቤተሰቦቹ ዛሬም ‹‹ያቺን ሸጋ መች ነው የምታመጣት?›› እያሉ ይጨቀጭቁታል።

ዛሬም ‹‹እዚሁ ደሴ ኑሩ ብንላት እንቢ ትለን ይሆን?›› ‹‹ከጓሮ ያ
ለችውን ግቢ ብንተውላቸው እኮ አስፋፍተው ይሰሯትና እዚሁ ከኛው ጋ ይኖራሉ!›› እያሉ ይወያያሉ። ሁሉም ነገር ነበር መሆኑን አልሰሙም።
*
እነሂባ ቤት የተጠራው እድምተኛ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በረሀብ ተቀጣ። ሙሽራው በበርካታ መኪናዎች ታጅቦ ሲደርስ የበርካታው እድምተኛ ፊት በረሀብ ከስሎ ነበር። ‹‹ምነው ባልመጣን ኖሮ!›› የሚሉም አልጠፉም። ከቤታቸው ባላጡት ምግብ ጠሪ አክብረው ባዶ ሆዳቸውን ቢመጡ ጨጓራቸው እስኪጎዳ ድረስ አስራቧቸው። ሙሽራው መጥቶ ከብፌው ካነሳ በኋላ የተቀጣው ህዝብ እያጉተመተመ ከብፌው ዙሪያ ተኮለኮለ። ምግቡ ተበልቶ ሰዉ ረገብ ካለ በኋላ ሰዓቱ አስራአንድ ሰዓት ማለፉን አመለከተ። የሂባ አባት የልጃቸውን ክንድ ይዘው ለሙሽራው አስረከቡ። በእልልታ ፣ በጭብጨባ ፣ በግጥም ታጅባ ከልጅነት እስከ እውቀት ከኖረችበት ከወላጆቿ ቤት በቅጡ ወደማታውቀው የባሏ ቤት መሄዷ እውን ሆነ። በናርዶስ እና በሌሎች ሁለት የሰፈሯ ልጆች ሚዜነት እንደታጀበች ወደ ሙሽራው ቤት አቀናች። መንደሩ በመኪና ጥሩምባ ተናወጠ።
*
ኢምራን የአስርን ስግደት አረብ ገንዳ መስጂድ ከሰገደ ወዲያ ከመስጂዱ ሳይወጣ ረዥም ሰዓት ተቀምጦ ነበር። ቁርዓን መቅራትም አላሰኘውም። ከአረብ ገንዳ መስጂድ ውጪ ላይ የመኪናው ጥሩምባ ሲበረታ ምን እንደሆነ ለማየት ከመስጂዱ ወጣ። የረፈደባቸው ሙሽራዎች የአስር ሰላት ለመስገድ መምጣታቸው ነበር። ሙሽራዎቹ ወደ መስጂድ ሲገቡ እሱ ከመስጂዱ የግቢ በር ጋር ደርሷል። በር ላይ መፅሀፍት እና ካሴት የሚሸጠው ልጅ የከፈተው የቁርዓን ድምፅ ጆሮውን መታው። ‹‹ወኢን ሚን ሸይኢን ኢላ ዒንደና ኸዛኢኑሁ ፤ ወማ ኑነዚሉሁ ኢላ ቢቀደሪን መዕሉም›› የሚል የቁርዓን አንቀፅ ነበር። ‹‹ከካዝናዎችም (መክፈቻቸው) እኛ ዘንድ ያልሆነ ምንም ነገር የለም ፤ በተወሰነም ልክ እንጂ አናወርደውም፡፡›› ነበር የቁርዓኑ ትርጉም። ኢምራን ‹‹የሂባ ካዝናም አንተ ጋ አለ?›› ሲል በልቡ ፈጣሪውን ጠየቀ። ‹‹ስንት ሂባ አለህ? ካዝና ሙሉ? ካዝናህ ምን አይነት ነው?›› ዘላበደ። አዲስ የደስታ መንፈስ ወረረው። ‹‹ጌታዬ ሌላም ሂባ አለው!›› እየተንደረደረ ከአካባቢው ተሰወረ። አዲሱን ግኝቱን ለእህቱ መናገር አለበት። ‹‹ጌታዬ እኮ ብዙ ሂባ አለው። በተወሰንልኝ ጊዜ ይሰጠኛል።›› ሊላት ቤታቸው ወዳለበት ወደ ዳውዶ ሰፈር ተቻኮለ። እርሱ ያፈቀራት ሂባ ግን ዛሬ ወደ ባሏ ቤት ሄዳለች።
.
ይቀጥላል ...

fuadmu
@achacher share
👍1
የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል አራት
(ፉአድ ሙና)
.
የወንዱ ቤተሰብ ውክቢያ ሲገባደድ ፣ የአዳራሹ የእራት ስነ ስርዓት ሲጠናቀቅ ፣ ቀኑ ጨለምለም ሲል ፣ ጨረቃ ስትፍነከነክ ፤ ሙሽራዎቹ የጫጉላ ጊዜያቸውን ወደ ‘ሚያሳልፉበት ፣ ቀጣይ ህይወታቸውን ወደሚመሩበት አዲሱ ቤታቸው ሄዱ።
ከጣሊያን ሰፈር ጥቂት ራቅ ብሎ ወዳለው ወሎ ሰፈር አቀኑ። ዚያድ ወትሮውንም ጣሊያን ሰፈር አይኖርም። አንዳንዴ ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ ቢመጣ ነው።
በሚዜዎቻቸው እንደታጀቡ የመኪናው ጥሩምባ የቀኑን ያህል ባይበዛም እያስተጋባ ወሎ ሰፈር ደረሱ። ናርዶስ አብሮ አደጓን እንዲህ በቀላሉ ትታ ወደ ሰፈሯ መመለስ ከበዳት። ግን ደግሞ ግድ ነው። ከዚህ በኋላ ያለው ስነ ስርዓት አጃቢ አይሻም። ተመልካች አይፈቅድም። ዛሬ በመተፋፈር ውስጥ የሚደሰቱበት ቀን ነው። ምናልባት የሂባ ደስታ ሙሉ ላይሆን ይችላል።
የሂባን ቬሎ የያዘችው የናርዶስ ታናሽ እህት ሁለቱ አብሮአደጎች ተቃቅፈው ሲላቀሱ ስታይ አነባች። ሚዜዎቿ በተራ በተራ እያቀፉ ተሰናበቷት። መጨረሻ ላይ ናርዶስ ‹‹ሂቡዬ ይኼ አዲስ ምዕራፍ ነው። ፈተናው የሚወጣው ከዚህ ምዕራፍ ስለሆነ የቀድሞውን ምዕራፍ ማጥናት አይኖርብሽም። ከቻልሽ ቀደሽ ጣይው።›› አለቻት። ዚያድም ከሚዜዎቹ ጋር እየተሰነባበተ ነበር።
‹‹ናርዲ ፕሊስ እየመጣሽ አጫውቺኝ። መልመድ በጣም ይከብደኛል!›› ሂባ ተነፋረቀች።
የሷ ሚዜዎች የተንጣለለውን ግቢ ለቀው በወንድ ሚዜዎች መኪና ወደየቤታቸው ተሸኙ።
ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም። ሚዜ ያጅባል እንጂ አብሮ አይተኛም። ወላጅ ይድራል እንጂ አብሮ አይኖርም። በህይወቷ ላይ የፈረዱ ሁሉ አሁን ከሷ ጋር የሉም። እሷ እና ባሏ ብቻ! ሰፋ ያለው ግቢ ውስጥ አንድ ሰፊ ባለ አንድ ፎቅ ህንፃ ፈገግ ብሎ ቆሟል። ጣሊያን ሰፈር ላደገችው ለሷ ምናልባት ገነትን ያስታውስ ይሆናል።
ወደ ፎቁ ወጡ። ያማረ መኝታ ክፍል ውስጥ አስር ሰው የሚያስተኛ የሚመስል ግዙፍ አልጋ በፅጌረዳ አበባ ተጊጦ እየተሽኮረመመ አያቸው። አፈሩ። ዝምታውን ለመስበር ያህል ዚያድ ወደ ቁምሳጥኑ እየጠቆመ ‹‹የመኝታ ልብሶች እዛ ውስጥ አሉ።›› አላት።
‹‹እሺ!››
ኮቱን ፣ ሱሪውን እና ሸሚዙን አውልቆ አንዱ ቁምሳጥን ውስጥ ገባ። ደነገጠች። ‹‹ዚያድ›› ተጣራች። ‹‹ሻወር ልወስድ ነው።›› ድምፁ ከሩቅ ተሰማት። ከቁምሳጥኑ መች እንደወጣ ግራ ገባት። ልብሶቿ ወዳሉበት ቁምሳጥን ተጠግታ ቁምሳጥኑን ከፍታ ፈዘዘች። እጅግ በጣም ብዙ የሚያማምሩ ልብሶች አፈጠጡባት። ገና የራሷን ልብሶች አላመጣቻቸውም። እዚህ ያሉት በዚያድ እና በቤተሰቦቹ የተሸመቱ ናቸው። በልቧ ‹‹ሀብታም ቀልብ የለውም!›› አለችና ተሸክማው የዋለችውን ቬሎ አወለቀችው። ቀይ ቀለል ያለ ስስ የመኝታ ቀሚስ ለበሰች። ከላዩ ስስ ጋውን ደረበችበት። ፀጉሯን ጀርባዋ ላይ ለቀቀችው። አልጋ ላይ ትንሽ ከተቀመጠች በኋላ ዚያድ የገባበትን ተዓምረኛ ቁምሳጥን መክፈት አማራት። ጠጋ ብላ ስትከፍተው ከውስጡ ቀጭን አረንጓዴ በር አገኘች። በዝግታ ከፈተችው። ተዓምር የምታይ መሰላት። በውብ መብራቶች የተሽቆጠቆጠ ውብ መታጠቢያ ቤት ፣ የመታጠቢያ ገንዳ ፣ ስቲም ደነገጠች። ከድንጋጤዋ መለስ ስትል ባሏ መለመላውን ከገንዳው ውስጥ ተዘርሮ በሀፍረት ተመለከታት። አዲስ ነገር እንዳየች ደነገጠች። ዞራ በገባችበት በር ወጣች። ዚያድ እንድትመለስ እየጠራት ነበር። አልሰማችውም። አትሰማውምም።
*
ኢምራን ከምሽቱ አምስት ሰዓት ሲል ናርዶስ ጋር ደወለ። ናርዶስ ከቤተሰቦቿ ጋር ስለ ወንዱ ቤት ዝግጅት አውርታ ገና ክፍሏ ገብታ ከአልጋዋ ማረፏ ነበር። ስልኩን ስታየው እንባዋ አነቃት። ትንሽ ከተከዘች በኋላ አነሳችው።
‹‹ኢምሬ!››
‹‹ናርዲ›› ድምፁን ሳግ አጥሮታል። አልቅሶ እንደነበር ገባት።
‹‹እንዴት ደወልክ?›› መምሸቱን ለመጥቀስ አልማ የሰነዘረችው ነበር።
‹‹ሂባዬ በሰርጓ ቀን .... አምሮባት ነበር? እ ደስ ብሏት ነበር? እሱን ልጠይቅሽ .....›› ሳግ አቋረጠው።
‹‹ኢምሬ ማማሩን ሁሌም ቆንጆ ናት ታውቃለህ! ደስታውን ግን አይመስለኝም። ካንተ ተለይታ የማታውቀውን ሰው እያገባች እንዴት ደስ ይላታል?››
‹‹ለማታውቂው ሰው ሰጥተሻት መጣሽ አይደል?›› ድምፁ ወደ ለቅሶ ተንደረደረ። አርዕስት ልታስቀይረው ሞከረች።
‹‹እስከዚህ ሰዓት ድረስ ለምን አልተኛህም?››
‹‹እንቅልፍ አልወስድ አለኝ ...... ናርዲ! ሂባ ከሌላ ሰው ጋር እንደተኛች እያሰብኩ መተኛት ከበደኝ!›› አርዕስቱ ላይ የሙጥኝ አለ።
የኢምራን ሀዘን እሷንም አመማት። አለቀሰች። ማልቀሷ የሱን ብርታት ይበልጡኑ እንደሚያከስመው ረሳች። አብሯት መነፋረቅ ጀመረ።
‹‹ግን ናርዲ ..... ለኔ ይኼ ይገባኝ ነበር? እ? ንገሪኝ ናርዲ እኔ ለሷ እንዲህ ነበርኩ?›› ተንሰቀሰቀ። ለቅሷቸው ጋብ እንዳለ ናርዶስ ልታፅናናው ሞከረች። ‹‹ኢምሬ አሁን ራስህን አረጋጋ በቃ! ሁሉም ነገር ሆነ እኮ አይደል? አንተ ጥሩ ልጅ ነህ ፣ የተሻለ ታገኛለህ!›› አንዴ በማፅናኛዋ ሲስማማ ፣ መልሶ ሲያፈርሰው ለአንድ ሰዓት ያህል ካወሩ በኋላ ተሰነባበቱ።
ናርዶስ ስልኩን ከዘጋችው እና የኢምራንን መልካምነት እያሰበች ከተከዘች በኋላ ሂባ አሁን ከባሏ ጋር መተኛቷን አስባ ፈገግ አለች። እጆቿን ወደ ራስጌዋ ለጥጣ መብራቱን አጠፋችው። ወፍራም ጨለማ ክፍሏ ውስጥ ነገሰ። የኢምራን ሀዘን መሰላት።
*
ሂባ ከእንቅልፏ ስትነቃ በመኝታ ቤቱ መስኮት በኩል ብርሀን ከመጋረጃው ጋር መታገል ጀምሮ ነበር። በጣም ደነገጠች። ሌላ ጊዜ የንጋት ስግደት የምትሰግደው ጨለማው ሳይሸሽ ነበር። በቀኝ ጎኗ በኩል ዚያድ ተኝቷል። ከወገቧ ቀና ብላ ተቀመጠች። እሱ ይቀሰቅሰኛል በሚል እሳቤ ስልኳን ሳትቀጥር መተኛቷ አበሳጫት። ደግሞ የሰርጉ ውክቢያ ፣ ማታ የተፈጠረው የሁለቱ የአልጋ ላይ ልፊያ አድክሞት እንደሆነ አሰበች። የቀኝ እጇን መዳፍ ጭንቅላቱ ላይ አሳርፋ እየደባበሰችው ‹‹ተነስ ሀቢቢ! ሰላት እያለፈን ነው!›› አለች። ሁለቴ እንደጠራችው ከእንቅልፉ ተላቀቀ። ቀና ብሎ አያትና ፈገግ አለ። ጎሮሮውን ለመጥረግ ሞከረ።
‹‹ግቢ ሻወር ውሰጂ መጣሁ!››
ተነስታ ማታ የለበሰችውን የመኝታ ልብስ መፈለግ ጀመረች። ትንሽ ከፈለገችና ዚያድ ከአልጋው ስር አንስቶ ካቀበላት በኋላ ሰውነቷ ላይ ጣል አድርጋ የቁምሳጥኑን በር ከፍታ ወደ ተዓምረኛው ሻወር ቤት ገባች። ዚያድ አላስቻለውም ተፈናጥሮ ከአልጋው ተነስቶ ተከትሏት ገባ። ማታ በእጅጉ አፍራው እንዳልነበር ጠዋቱን ራቁቷን ክፍሉ ውስጥ የመራመድ ድፍረት ከየት እንዳመጣች ግራ ገብቷታል። የማታው መተፋፈራቸው ጠፍቷል። ከግማሽ ሰዓት ቆይታ በኋላ ከመታጠቢያ ቤት ወጡ። ልብሳቸውን እንደነገሩ ለባብሰው በአባወራው መሪነት የንጋት ስግደትን ከመኝታ ክፍላቸው ሰገዱ። ሰግደው ሲጨርሱ አንድ ሰዓት ሆኖ ነበር። በቅርብ አመታት ህይወቷ የንጋትን ስግደት ይህን ያህል ያዘገየችበት ጊዜ ትዝ አይላትም። በተለይ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ከባሏ ጋር በተኛችበት ለሊት የጌታዋን ሀቅ ማጓደል አትፈልግም ነበር። ከመስገጃው ላይ በርከክ ብላ እንደተቀመጠች ኢምራን ያላት ትዝ አላት።
‹‹የሰርጋችን ምሽት ላይ የለሊት ስግደት ለመስገድ የምንነሳው የንጋት ስግደት ከመድረሱ ከአንድ ሰዓት በፊት ነው። ሰላሳውን ደቂቃ እንሰግድበታለን። ሰላሳውን ደቂቃ ደግሞ አንቺን ስለሰጠኝ በግንባሬ ተደፍቼ አመሰግንበታለሁ።›› ድምፁ ጆሮዋ ላይ አቃጨለባት። ‹‹የእውነት ከእሱ ጋር ብሆን የዛሬው ለሊቴ እንዲህ አይሆንም ነበር?›› ስትል ራሷን ጠየቀች። ‹‹ያለፈው ምዕራፍ ፈተና ላይ አይመጣም።›› የሚለው የናርዶስ

ንግ

ግር
ትዝ ሲላት ራሷን ወደ አሁን መለሰች። ዚያድ የመኝታ ክፍሉን በር እየከፈተ ነበር።
‹‹ወዴት ነው?››
‹‹ቁርስ መዘጋጀቱን አይቼ ልምጣ!››
‹‹እንዴ ሌላ ሰው አለ እንዴ?››
‹‹ሰራተኛ አለች እኮ!››
‹‹በቃ እኔ ልሂዳ የዛሬ ቁርሳችንንማ እኔ ነኝ የምሰራው!››
ከመስገጃው ላይ ተነስታ ወደ በሩ ተጠጋች። አቅፏት ወደ ታች ወረዱ። እግረ መንገዷን አይኗ ቤቱን በደንብ ቃኘው። በርካታ ክፍሎች አሉ። ምድር ላይ ያለው የእንግዳ መቀበያ ክፍል እጅጉን ሰፊ ከመሆኑም በተጨማሪ በሚያምር አረቢያን መጅሊስ ተፈርሿል። በልቧ በየክፍሉ ስለምትሰቅላቸው አዳዲስ ፍሬሞች አሰበች። እስከዛሬ ይኼን በሚያክል ቤት ውስጥ ብቻውን መኖሩ አሳዘናት ፣ ገረማትም። ወደ ማብሰያ ክፍሉ ስትገባ አንዲት አጠር ያለች መልከመልካም ሰራተኛ ቁርስ ለማብሰል ስትንደፋደፍ አየቻት። ወደ ኋላዋ ዞር አለችና እንግዳ መቀበያ ሳሎኑን እየጠቆመች ‹‹በቃ አባወራው እዛ ይጠብቁን!›› ብላ ፈገግ አለች።
ሰራተኛዋ አዲሷን እመቤቷን በፈገግታ እና በአክብሮት ተቀብላ ትዕዛዟን መከተል ጀመረች። ከጥቂት መንጎዳጎድ በኋላ ምርጥ ፈጢራ ሰሩ። በማር ለውሰው እንደጨረሱ ለአይን በሚስብ መልኩ አቀራረቡት። ሰራተኛቸው ፋንታዋን ወደ ክፍሏ ይዛ ሄደች። የቤቱ ንግስት ከንጉሷ ጋር ፈጢራውን እየቆረሱ ፣ እየተጎራረሱ ፣ እየተቅለሰለሱ ቁርሳቸውን በሉ። በልተው እንደጨረሱ ዚያድ ‹‹ሀቢባ›› ብሎ ሰራተኛዋን ተጣራ። ሂባ ለመጣራት ፈልጋ ስሟን ስለማታውቀው ራሷ ተነስታ ልታነሳሳ ስትል ተረድቶ በሰበቡ ስሟን ማስተዋወቁ ነበር።
የዛሬውን ውሏቸውን መኝታ ክፍላቸው ውስጥ ለማሳለፍ ከጅለዋል። ማታውን ውጪ እራት ሊጋብዛት ቃል ገብቷል። ቁርስ በልተው ከተቀመጡበት ሳሎን እንዳሉ ስልኳ ‹‹አንሱኝ›› እንደሚል ህፃን የአረቢያ መጅሊሱ መከዳ ላይ ሲፍነከነክ ከዚያድ እቅፍ ወጥታ ቁጥሩን አየችው። ኢምራን ነበር። ያለፈው ምዕራፍ። የዚህኛው የህይወት ፈተና ላይ እሱን ማጥናት አይጠቅምም። መደወሉ በጣም አስደነገጣት። ፊቷ ላይ እንዳያስታውቅ በፈገግታ ለመሸፈን ከሞከረች በኋላ ስልኳን ዘጋችው። የሲም ካርዷን መቀየር እንዳለባት አመነች። ኢምራን ያለፈው ምዕራፍ ነው። ለዚህኛው ምዕራፍ ፈተና አይረዳም። ቢረሳም ግድ የለም። ሁሉም ቃል ተገፍቶ ባለጊዜ መከበር አለበት። ኢምራን ከህይወቷ መፋቁ ግድ ነው። ከስልኳ ልትጀምረው አሰበች። ባሏን ማስከፋት የለባትም።
.
ይቀጥላል ...

fuadmu
@achacher share
የሂባዋ ናርዶስ
ክፍል አምስት
(ፉአድ ሙና)
.
ስራ ማፈላለግ እንደነበረበት ያውቃል። አንዳንዴም ለአንዲት ሴት ብሎ ይኼን ያህል መጎዳት እንዳልነበረበት ከመካሪዎቹ ጋር ይስማማል። ከደቂቃዎች በኋላ ግን ሂባ አንድ ሴት አይደለችም ሲል ራሱን ወደ ቁጭቱ ይመልሳል። ‹‹ሂባዬን ማንም አይተካትም!›› ሲል ይነፋረቃል። የሰርጓ ቀን የሰማውን የቁርዓን አንቀፅ ደግሞ አላስታወሰውም። ለእህቱ ሊነግራት ሄዶ የነበረ ቢሆንም ተስፋው ቤት ሳይደርስ ተንኖ በቁጭት ተተክቶ ነበር። ጌታው የሂባ አይነት እንስቶች ካዝና እንዳለው አምኖ መፅናናት ከበደው።
ሂባ ወደ አዲሱ ቤቷ ከገባች ሶስት ቀናት አልፈዋል። በሰርጓ በነጋታው ስልኳን በተደጋጋሚ ሲሞክር አልነሳ ብሎት ነበር። ‹‹ባልሽን ወደሽዋል? እኔን ረስተሽኛል?›› ብሎ ቢጠይቃት ደስ ይለዋል። ረስታው እንደሆን ቢያንስ መርሳት እንደሚቻል ይረዳል። ያለፉትን ሁለት ቀናት ስልኳን ቢሞክርም ዝግ ነው። ሀሙስ ጠዋቱን እናቱ ከሂባ ጋር ብትኖሩበት ያለችውን ከዋናው ቤት ጓሮ ላይ ያለውን ሰርቪስ ቤት በዋናው ቤት መስኮት ለረዥም ሰዓት ፈዝዞ ይመለከታል። ሂባ ልጃቸውን አቅፋ የቤቱ በር ላይ ቆማ ታየችው። ቤቱ ውስጥ ሲላፉ .... ፈገግ አለ። ‹‹ኢምሬ ስልክህ ....›› በእድሜ ከሶስት አመት የበለጠ የማታንሰው እህቱ ኸድጃ ብቻውን መፈገጉ እያሰጋት ስልኩን አቀበለችው። የማያውቀው ቁጥር ነበር። በልቡ ሂባ እንድትሆን ፀለየ። እየፈራ ስልኩን አነሳው። የሌላ ሰው ድምፅ መስማት አልፈለገም። ቀጭን የሴት ድምፅ ‹‹ሄሎ›› አለው። የሂባን ድምፅ መሰለው። ቀጭኑ ድምፅ ቀጠለ። ‹‹አቶ ኢምራን አህመድ ጀሚል?››
‹‹አዎ ማን ልበል?››
‹‹ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኬሚካል ኢንጅነሪንግ ዲፓርትመንት ነበር››
‹‹እሺ ምን ልታዘዝ?››
‹‹የአመቱ የዲፓርትመንታችን ትልቁ ውጤት ያንተ ነው። ግቢው ደግሞ በዚህ አመት ምሩቅ ማስቀረት ስለፈለገ አንተን ሌክቸር እንድትሆን ጠርቶሀል።››
‹‹ደስ ይለኛል!›› አቋረጣት።
‹‹መልካም በኢሜል አድራሻህ የላክነውን ተመልከተውና በተጠቀሰው ቀን በአካል ተገኝተህ ሪፓርት አድርግ!››
ስልኩ ተዘጋ። የኢሜል አድራሻውን መመልከት እንደነበረበት ረስቷል። ሂባን ማጣቱ አስረሳው እንጂ የትምህርት ክፍላቸው ትልቁ ውጤት የእሱ እንደሆነ ያውቅ ነበር። ደስ አለው። ቢያንስ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ መኖር ደስ ይላል። ሂባ የእርሱ ባትሆንም ወደ እሷ ቀረብ ብሎ መኖር ሰላም ይሰጠው መስሎታል። የስልኩን የኢንተርኔት አገልግሎት አብርቶ ኢሜሉ ላይ የተላከለትን መልዕክት ተመለከተ። በሁለት ሳምንት ውስጥ ወደ ሀዋሳ መጓዝ አለበት። ከሂባ ጋር በፍቅር የተያየበት ፣ ተማሪ ሆኖ የተቀመጠበት መማሪያ ክፍል ውስጥ ሊያስተምር ነው።
*
ሂባ የአዲሱ ቤቷ ሳሎን ውስጥ መጅሊሱ ላይ የተቀመጠችውን ናርዶስን በሀፍረት እያየች ‹‹ስልኬን አልጠየቀሽም?›› አለች።
‹‹እንደቀየርሽ ያወቀ አልመሰለኝም እንጂ ይጠይቀኝ ነበር። ምን ሆና ነው ስልኳ ዝግ ነው ምናምን ነበር ያለኝ።›› ናርዶስ ሂባ አሁንም ስለ ኢምራን ማሰቧ አሳዝኗታል። የወሬውን አቅጣጫ ለመቀየር ፈለገች።
‹‹ስሚ ሂቡ የናንተ ፈተና በዚህ ሳምንት መጨረሻ ነው ብለዋል። መዘጋጀት አለብሽ።››
‹‹እንዴ ሳልጠይቅሽ አንቺ የተወዳደርሽበትስ? ውጤት አልተለጠፈም?››
‹‹ባለፈው ሳምንት ፈትነውን እንዴት አሁን ይለጥፋሉ? መቆየቱ አይቀርም። ባይሆን አንቺ ተዘገጃጂ ለፈተናው .....››
‹‹ኢምራን እዚህ ለምን አይሞክርም? እዛ እኮ ስራ አያገኝም›› ዞራ ወደ ኢምራን ተመለሰች።
‹‹ውይ ሳልነግርሽ ባለፈው ሳምንት ሀሙስ ደውሎ ግቢ ሌክቸር እንዲሆን እንደጠሩት ነግሮኝ ነበር እኮ!››
‹‹ወላሂ በይ? ደስ ሲል።›› ሂባ ፊቷ በደስታ ብርሀን ደመቀ። ናርዶስ አሁንም ወሬውን መቀየር እንዳለባት ተሰማት።
‹‹ስሚ ሂቡ ዜዶ የት ሂዶ ነው?››
‹‹ባክሽ ስራ ብሎ ወጥቷል። ያው እዛ መኪና መሸጫው ይሆናላ!››
‹‹ለምን አንዳንዴ አብረሽው አትሄጂም? ቤት ከምትቀመጪ ብታግዢው ይሻላል።››
‹‹መች ይቀራል ብለሽ ነው?›› ሂባ በልበ ሙሉነት መለሰች።
*
ኢምራን ከግቢው ከተጠራ በኋላ ሳምንት ከጥቂት ቀናት ደሴ ቆይቶ ወደ ሀዋሳ ተጓዘ። አዲስ አበባን አቋርጦ ሲያልፍ እንባው ታገለው። ወርዶ ቢያንስ እንኳ ናርዶስን ስለ ሂባ ቢጠይቃት ደስ ባለው ነበር። ግን ደግሞ ከዚህ በላይ ራሱን መጉዳት አይኖርበትም። የሂባን አዲስ ህይወት መበጥበጥም እንደማይገባ አሰበ። ፍቅር የሚባለው ስሜት ቀፈፈው። ‹‹ድሮም የሴት ልብ የባለጊዜ ነው!›› በሂባ አስታኮ በጅምላ ፈረጃቸው። ‹‹ከተመቻቸው ሁሉ ይለምዳሉ! የራሳቸው ነብስ ራሱ የእነሱ አይደለም። መጀመሪያ ቤተሰብ ሲቀጥል ደሞ ባል ያዝበታል። ተለጣፊ ሁላ!›› ስብራቱ ጥላቻ ወለደ። በተጓዘበት መንገድ ሁሉ ያሰበው የፍቅርን መጥፎነት ነው። ማፍቀር እንዳልነበረበት …… በፍላጎቱ ያፈቀረ ይመስል በማፍቀሩ ተፀፀተ።

ሀዋሳ ደርሶ የተከራየው ፔንሲዮን ክፍል ውስጥ ጥቂት ካረፈ በኋላ በወረቀት ላይ ‹‹ሴት ልጅ እናትህ ስትሆን አማራጭ ስለሌላት ነው ፣ እህትህም ስትሆን ተፈጥሮ አስገድዷት ነው። ሚስትህ ስትሆንም ቤተሰቧ ፈርዶባት ነው። አንድም ቀን በራሷ ላይ የመወሰን አቅም የሌላትን አካል አታፍቅር!›› ብሎ ፃፈና ከአልጋው እግርጌ ትይዩ ያለው ግድግዳ ላይ ለጠፈው።
ፅሁፉን በአትኩሮት ከተመለከተው በኋላ ‹‹ስለራሳቸው ራሳቸው እንዳይወስኑ የመሆናቸው ውድቀት ግን የማህበረሰቡ ወይስ የእነርሱ ጥፋት?›› ከራሱ ጋር ተጨቃጨቀ። ‹‹አላገባም! የምወደውን ሰው ዳሩኝ ቢሉ ምን ሐጢአት አለው?››
‹‹ቤተሰብ አይናችሁን ላፈር ይላቸዋላ!››
‹‹ይበላ! ስህተቱ የቤተሰብ እስከሆነ ድረስ እንዴት ለስህተት ይንበረከካሉ?››
‹‹እምቢ ቢሉ ማን ጋር ይወድቃሉ? የራሳቸው ኢኮኖሚያዊ አቅም አልዳበረማ! ሁሌም ጥገኛ ናቸው።››
‹‹ለምን ማህበረሰቡ ምርጫቸውን አያከብርም? ለምንስ የመሻቱ ባሪያ ያደርጋቸዋል?››
‹‹ማህበረሰቡ ባሪያ አላደረጋቸውም! ሁሌም የሚመረጥላቸውን ይወዳሉ። ከእነሱ ምርጫ የቤተሰባቸውን ምርጫ ያምናሉ። የቤተሰባቸው ምርጫ መጥፎ ቢሆን መዘዙን ቤተሰቡ እንዲወጣው ብለው! የእነሱ ምርጫ ሆኖ ቢከፋና አንድ ነገር ቢሆኑ የማህበረሰቡ ምላስ አያስቀምጣቸውማ! ሀላፊነት ሸሽተው ነው!››
‹‹ቀድሞ ማህበረሰቡ በራስ መተማመናቸውን ሰልቦታላ!››
ከራሱ ሀሳብ ጋር መከራከሩ አደከመው። ፀሀይ ከገባ በኋላ የሚሰገዱትን ሁለት ስግደቶች በአንድነት ሰገዳቸው። ጥቂት ከተብሰለሰለ በኋላ አልጋው ውስጥ ገብቶ ተጠቅልሎ ተኛ።
***
ሂባ በቻለችው አቅም ሁሉ ባሏን ለማስደሰት እየሞከረች ነው። ኢምራንን ከውስጧ ለማውጣት የስልኳን መስመር በመቀየር ግንኙነታቸውን ደምድማለች። የወደደችውን ባታገኝም ያገኘችውን ለመውደድ መጣር ጀምራለች። ሁሉ ነገሯን ለዚያድ አሳልፋ ሰጥታዋለች።
ዚያድ ሁሌም ጠዋት ጠዋት ሲወጣ ከአንድ ሺህ ብር ያላነሰ ለወጪ ያስቀምጥላታል። ሰሞኑን አይኑ ቦግ እያለ አምሽቶ መምጣት ጀምሯል። ከጋብቻ በፊት አልፎ አልፎ እንደሚቅም ነግሯት ነበር። ለመተው እንደሚሞክርም ቃል ገብቷል። ጋብቻቸው ወር እንኳ በቅጡ ሳይሞላው መመለሱ ከፋት።
ማታውን ወደ መኝታ ክፍላቸው ሲገባ በአጭር ቀሚስ ሰውነቷን ገላልጣ ፣ በውብ ሽቶ መኝታ ክፍሉን እና ገላዋን አጥና ጠበቀችው። አይኑን ቦግ አድርጎ ሲያያት እሷን አልፎ አልጋውን ብቻ የሚያይ መሰላት። ረጋ ባለ ድምፅ ‹‹ዚያዴ መቃም ከፈለግክ እስከምትተወው ለምን እዚሁ አትቅምም?›› አለችው።
‹‹ኧረ አቆማለሁ እኮ! ግን በአንዴ ይከብዳላ?››

ወንድነቱን ፈለገ
ች። እንዳይከፋት አብሯት ለመተኛት ሞከረ። ግን የልቧን ማድረስ አልቻለም። ተልፈሰፈሰ።
የንጋት ስግደት ደርሶ የስልኳ አላርም ሲንጫረር ተነሳች። ተነስቶ እንዲሰግድ ብትቀሰቅሰውም በፍፁም መነሳት አቃተው። ሁሌም ከሰገደ እንኳ አንድ ሰዓት ከሆነ በኋላ ነው። እሱንም በሷ ውትወታ። ሰሞኑን ግን ቅሞ ስለሚመጣና ከግማሽ ለሊት በላይ እንደፈጠጠ ስለሚያሳልፍ ከሁለት ሰዓት በፊት መነሳት ተራራ ይሆንበታል። የሂባ ልብ እጅጉን ቢከፋም እስከሚላመደው ነው በሚል ተስፋ ራሷን ታፅናናለች። የባሏን መንሸራተት ለማንም አልተናገረችም።
እንዲነሳ ብትወተውተውም ሊነሳ አልፈቀደም። ለሊት ያጣውን እንቅልፍ ቀጠለ። ወደ ምድር ወርዳ ባሏን የሚጠግን ቁርስ ለመስራት ከሰራተኛዋ ጋር ተንደፋደፈች።
ከረፈደ በኋላ ከእንቅልፉ ተነስቶ ተጣጠበና ወደ ታች ወረደ። ቁርስ በአይነት በአይነቱ ቀርቦ ነበር። ከሚስቱ ጋር እየተጨዋወቱ መብላት ጀመሩ። ልቧ ቅሬታ እንዳዘለ ነው።
‹‹ዜዶ ሰገድክ?››
‹‹ፀሀይ ወጣ .... ከዚህ በኋላ ....?›› የጠቀለለችውን ጉርሻ ሳህኑ ላይ መለሰችው ‹‹ዚያድ ይኼ እኮ ቀላል ነገር አይደለም!››
‹‹አዎ እስተካከላለሁ እኮ ኢንሻአላህ ዱዓ አድርጊልኝ!››
ሆድ ባሳት። ሰው እንዴት መሰረታዊ ስለሆነ ጉዳይ ይጨቃጨቃል? ኢምራን ትዝ አላት። ለለሊት ስግደት ስንት ሰዓት መነሳት እንዳለባቸው ሲጨቃጨቁ ታወሳት። አሁንም ግን ተስፋዋ አልሞተም።
‹‹ዛሬ ስራ ቦታ ብመጣ ደስ ይለኛል። ..... ማለቴ አብሬህ ብውል››
‹‹ከፈለግሽ ..... አብረን መሄድ እንችላለን።››
‹‹አሁን ፈተና አለኝ። ከዛ ስወጣ ልደውልልህ?››
‹‹የምን ፈተና?››
‹‹የስራ››
‹‹ምን ያደርግልሻል ቆይ? ቢቀርብሽስ? የገንዘብ ችግር የለብንም እኮ አይደል?››
‹‹እንዴ ዜዶ የዛ ሁሉ አመት ልፋቴስ? ለመመረቅ ብቻ አይደለም እኮ የተማርኩት። የራሴ ሙያ እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ። መድረስ ያለብኝ ቦታ አለ።››
‹‹ቆይ በወር ስንት ይከፍሉሻል?››
‹‹ለጀማሪ እንኳ ከስድስት ከሰባት ሺ የሚበልጥ አይመስለኝም።››
‹‹እኔ በየወሩ አስር ሺ ብር ልስጥሽ አርፈሽ ተቀመጪ!››
ማስረዳት ታከታት። ለገንዘብ ብቻ እንደማይሰራ ልትነግረው ደከማት።
‹‹ቆይ ከመጋባታችን በፊት ተስማምተን የለ እንዴ? መማርም መስራትም እንደምችል ተስማምተናል አይደል?››
‹‹አዎ ግን ምክንያትሽ አሳማኝ አይደለማ! እዚህ ምንም አልጎደለብሽም ከማንም ጋር እዛ መንዘላዘሉ አይጠቅምሽም።›› ከተጋቡ እንዲህ ጠንከር ያለ ንግግር ተናግሯት አያውቅም። ከፋት። አኮረፈች። እንባዋ አይኖቿ ላይ አኮበኮበ። ተነስታ ወደ መኝታ ክፍሏ ሮጠች።
‹‹ይኼ ሰው ቤተሰቦቼ ያሉኝ ..... እኔም የገመትኩት አይነት አይደለም እንዴ?›› መኝታ ክፍሏ ውስጥ ያለው መስታወት ላይ አፍጥጣ ራሷን ጠየቀች።
.
ይቀጥላል ...

fuadmu
@achacher share