❇️ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ
#ክፍል_9
ወደ 7 ሰአት ገደማ ሰርገኛ መጣ በእልልታም ተቀበሉት። ምሳ ተበላ ተጨፈረ ኒካም ታሰረ ብናይ አይወጡም ብናይ አይወጡም። የሆነ የሰፈር ህፃን ልጅ መጣና በጆሮዬ " ልክ ቀለበቱን እጅሽ ላይ ሲያጠልቅ እኔን ከልብሽ አውጥተሽ አትጣይኝ ሁሌም አኑሪኝ" የሚል ከ ሀምዛ የተላከ መልእክት ነበር ውስጤ ተረበሸ ግራ ገባኝ እያለቀስኩ ሳለ የ አባ ወንድም አጎቴ መጣ
"እ ኢሙ ተበላ ተጠጣ መዝናኛ እንሂድ እየተባለ ነው ፎቶ ተነስታቹ አመሻሽ ላይ ትመለሳላቹ" ምን ትዝ አለኝ አንዷን ጓደኛችን እንዲህ ብለው ማይሆን ነገር ሰርተዋታል ማለት ወሰዷት እቤታቸው የሷ በቤተሰብ ቢሆንም ወዳዋለች ግን እኔስ?? ሃሃሃሃ በጣም ትሸውዱ የለም እንዴ በል ንገራቸው እንዳልተስማማው
"አረ እንደሱ አያደርጉም ካደረጉማ 20,000 አስይዘናል ይቀጣሉ" ታድያ ለኔ ምን ያደርግልኛል ከሄድኩ በኋላ እናንተ ትበሉበታላቹ ትጠጡበታላቹ በቃ🤷♀ ሲያቅተው አብዱን ጠራው ያው ቀረቤታዬም ከሱ ጋር ስለሆነ ምንም ቢለኝም አምነዋለዋ።
እ አብዱ የሚለው እውነቱን ነው?
"አዎ እውነቱን ነው" አለኝ አይ እንደሱ ከሆነማ እሺ ብዬ ስነሳ ዘወር ብሎ በምልክት እንቢ በይ አለኝ አረ አልፈልግም አልሄድም አልኩ ድጋሜ አጎት ተብዬው ተናዶብኛል ከፈለጋቹ እነሱ ከሄዱ በኋላ እኛ ሄደን እንዝናናለን አልኩት።
እንደዚህ እየተከራከርን 12 ሰአት ሆነ እነ ሀምዛ ቤት ተረብሸዋል ይሄ ነገር የምር እዚህ የሚደርስ አልመሰላቸውም ነበር ማዘርየው አልመጡም መረጃ የሚያመላልስ አለ ከኔ ወደነሱ ከነሱ ወደ እኔ መጨረሻ ላይ ጀማልን ጥሩልኝ ብዬ መጣ።
ቆይ ግን ያምሀል ምን ብላቹ ነበር መጀመሪያ እእእእ
"አንቺ ራሱ ምንድነው የምትይው እኔ ትምህርትሽን ስትጨርሺ እና የማስተካክላቸው ነገሮች አሉ ስጨርስ ብዬሽ አልነበር በአንዴው ምን ተለውጦ ነው ካልወሰድከኝ የምትይው"??
በጣም ደነገጥኩ ምን እንደሚያወራ ራሱ ግራ ገብቶኛል በሰአቱ ለካ ይሄን ሁሉ የሚጠነስሱት የኔ አጎት እና የሱ አባት ነበሩ። አባ እና እማ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም የሱ አባት ልጅቷን ይዘን ካልሄድን ከዚህ ንቅንቅ አንልም አሉ አማም አባም ግራ ተጋብተዋል እኔን ተነሽ ሂጂ እንዳይሉ እጎዳባቸዋለው የመጣውንስ ሽማግሌ እንግዳውን ምን ብለው ተነስታቹ ውጡ ይላሉ? ተያይዘው ወጥተው መስጊድ ሄደው ማልቀስ ጀመሩ። ህዝብም ደሞ መጨረሻውን ሳናይ ንቅንቅ አንልም ብለዋል መሰለኝ የሚወጣም የለም በቆሙበት እርስ በእርሳቸው ይንሾካሸካሉ ትወጣለች አትወጣም የሚለውን በመሀል አባን ጥሩልኝ ስል ነው እንደሌሉ ያስተዋልኩት
ቆይ በአላህ ከኔ ከልጃቸው ሽማግሌ በልጦባቸው ነው የሸሹት? እ ለምንድነው መተው ማያባርሩልኝ ሁሉም እኔን እያየ የሚያለቅስ እንጂ ምንም የሚለኝ ጠፋ።
ማንም ከጎኔ ሊቆም አልቻለም ነበር መጨረሻ ላይ ተሸነፍኩ የተሸነፍኩትም አብዱ መጣና ይዞኝ ባዶ ክፍል ገብተን እንዲህ አለኝ
"በቃ ኢሙ አልቻልኩም ወላሂ ብዙ ጣርኩ አቃተኝ ከዚህ በላይ ምን ላርግልሽ እእ "ስቅስቅ እያለ ነበር የሚያለቅሰው
በቃ አብዱ አንተም ተሸነፍክ ምንም ተስፋ የለኝም ማለት ነው ከጎቴ በሩን እየቀጠቀጠ አንተ ነህ ልጅቷን የምትመክራት ተዋት ትሂድበት ይለዋል
"ኢሙ ሰማሽ አይደል ሁሉም እኔን እየወቀሱኝ ነው ኢሙዬ ከዚህ በላይ መታገል አልችልም ይቅርታ"እያለ እግሬ ስር ወደቀ
የኔ የ ኢማን ህይወት እዚህ ጋር አበቃ ማለት ነው እንጫወታለን ብለን ተጫወቱብን አይደል? አቅፌው መንሰቅሰቅ ጀመርን።
#የመጨረሻው_ክፍል10_.........
#የሚለቀቀው ከታች ባለው ግሩፓችን አድ ስታደርጉ ነው (Add Member) ሁላችሁም የተቻላችሁን Add Member አድርጉ🙏
@achacher
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄

❤2
❇️ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ
#ክፍል_10_የመጨረሻው_ክፍል
አብዱ ከክፍሉ ይዞኝ ወጣና ቦታዬ አስቀምጦኝ ቤቱን ለቆ ወጣ ጀማል መጣና ይዞኝ ወጣ ሰርግ ቤት ሳይሆን ለቅሶ ቤት ነበር የሚመስለው አባም እማም መጡ አይኔን ግን አላዩም ነበር በስራቸው ተፀፅተው ይመስለኛል እያለቀሱ ከቤት ወጣን።
እነሱ ቤት ስንደርስም ሰው በሽ ነው ምንም የቀረ ነገር የለም የታሰበበት ነው የሚመስለው።እኔ ግን ምንም ፊቴ አልተፈታም ተበላ ተጨፈረ ይዞኝ ወደራሱ ቤት አቀናን የኔ ሚዜዎች የለበስከለትን ቬሎ ቀያይረዉልኝ ሄዱ። ሽማግሌ ከተላከበት ቀን አንስቶ እስአ አሁን እንቅልፍ የሚባል አልተኛሁም አልጋው ላይ በተቀመጥኩበት እንቅልፍ ሸለብ አደረገኝ ትንሽ እንደተኛው ነቃ ስል አጠገቤ ጀማል ተቀምጧል ወደኔ ጠጋ ሲል አበድኩ ምን ያላልኩትት ነገር አለ ክፍሉን ለቆ እንዲወጣ ነገርኩት ምንም አላለኝም ወጣ በሩን ከዉስጥ ቆልፌ የሆንኩትን እያስታወስኩ አነባው ከማልቀሴ የተነሳ ፊቴ ፍም መስሏል ራስ ምታት ሊለቀኝ አልቻለም በዛው እንቅልፍ ወሰደኝ.......በማግስቱም ተመሳሳይ ነገር ነበር የተፈጠረው።
በ ሶስተኛው ቀን መልስ ተጠራን በጣም ነበር ደስ ያለኝ እንደዛ ቀን የተደሰትኩበትን ቀን ሁላ አላስታውስም ወላሂ...መልስ ሲባል ያሰብኩት መመለሴን እቤት የምቀር ነገር ነበር ግን አይደለም ሄድን አሪፍ ዝግጅት አድርገው ነበር። 5 ሰአት አካባቢ የተሰጠኝን ስጦታ ጭነን መጣን ትዳር ሲባል የራስን ስሜት ማዳመጥ ብቻ አይደለም የባል ሀቅ የሚባለውም ነገር አለ ምንም ማድረግ አልችልም ላያስችል አይሰጥም አይደል የሚባለው..ወላሂ በዛን ሰአት ጀማልን ቀና ብዬ ሳየው ራሱ ይቀፈኛል ራሴን ጠላዋለው ቢሆንም ግን ምንም አማራጭ አልነበረኝም ቢጃማዬን ቀይሬ አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ እንዳልኩ ጀማል መጣ ሰውነቴን እንደ እሾህ ይወጋኝ ጀመር ከዛን ሰአት በኋላ ምን ይፈጠር ምን ልሁን የማውቀው ታሪክ የለም ብቻ ስነቃ ያስተዋልኩት ማማ ግርግዳውን ተደግፋ ታለቅሳለች ሳሎን ላይ ተዘርሬ ብርድ ልብስ አልብሰውኛል ሁለት ሼኽዎች በግራና በቀኝ ቁርአን ይቀሩብኛል ዙሪያዬ በቤተሰቦቼ ተከብቤያለሁ።.....ከዛን ጊዜ በኋላ ተለከፍኩ ጊዜ እየጠበቀ ህመሜ ይነሳብኛል ቁርአንም ቤት እመላለሳለው።
አንድ ቀን እንደ ወትሮ ቁርአን ሲቀራብኝ እለፈልፍ ጀመር ለካስ የዚ ሁሉ መንስኤ ሀምዛ እና እናቱ ነበሩ ሱብሀንአላህ😔 እኔ በህይወቴ በትዳሬ ደስተኛ እንዳልሆን አስደግመውብኛል ወላሂ ይሄንን ሳውቅ ሀምዛን ከልቤ እርግፍ አድርጌ አወጥቼ ጣልኩት ሀምዛንኮ ሌላ ባገባ ብወልድ ራሱ አልረሳውም ነበር...ፍቅር እንዲህ ነው እንዴ በህይወቴ ምንም ደስታ አልነበረኝም 2 ልጆች አሉኝ ደስታዬ ግን አልነበረም አልሀምዱሊላህ ይሄን ስራቸውን ካወኩኝ በኋላ ቁርአንም መከታተል ስቀጥል ደስታ ወደ ቤቴ ገባ። ጀማል ይሄን ሁሉ ታገሰኝ ሁሌ ያዘነች ሚስት ቤት ውስጥ እያየ ሁሌ ያኮረፈች ሴት እያየ ኖሯል ሆኖም ግን አንድ ቀን እንዲህ ሆኜ ብሎኝ አያውቅም ታገሰኝ ይህንን ሳስብ እሱን ይበልጥ እንድወደውና እንዳከብረው አደረገኝ።
አልሀምዱሊላህ ከዛን ጊዜ በኋላ ደስተኛ ነኝ አሁን ላይ ትምህርቴን ጨርሼ ተመርቄ በተመረኩበት ሞያ ላይ እየሠራው ነው ሶስተኛ ልጄን ወልጃለው ለሁሉም ግን አልሀምዱሊላህ...........
..............ተፈፀመ.............
እስቲህ ለዚህ ምርጥ እውነተኛ ታሪክ ስንት Like የገበዋል Like ያድርጉ👍
#ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @darkniha

👍1
እብዱ ደራሲ ክፍል አንድ
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
...........
ለመኖርም ለመሞትም አልታደለም በመኖር ውስጥ የሞተ፣ ሞተ እየተባለ የኖረ፣ ምስኪን ፍጡር ነው።የማያውቁት ሰዎች ከሩቅ ሲያዩት በፍርሀት ልባቸው ጥለው ይሮጣሉ ከፊሉ መንገድ ይቀይራል፣ከፊሉ በፍርሀት ይጨማደዳል፣ የሚያውቁት ደሞ ከፊሉ እያዘነለት፣ ከፊሉ እያዘነበት፣ በአጠገቡ ማለፍ ሳይሳቀቅ፣ እንዳላወቁት ሳይደነግጥ በአጠገቡ ያልፋሉ።ሁሌ ከእጁ ላይ የማትለየዋ ቡኒ ተስቢህ የማሂር መታወቂያ ነች ሲቀመጥ ሲነሳ ሲተኛ ሲበላ ሁሌም እጁ ላይ አለች። ሲዞር ሳንቲም ሲለቅም ይውል እና የሰፈሩ ወጣቶች በሸራ እና በማዳበሪያ የሰሩለት ቤት ውስጥ ሄዶ ይተኛል። የተቦጫጨቀ ልብሱ እላዩ ላይ ሊያልቅ ትንሽ ቀርቶታል ከማይታየው የሰውነት ክፍሉ የሚታየው ይበዛል ያለፈ ያገደመውን ሳንቲም ይጠይቃል። ግማሹ በሀዘኔታ,ግማሹ ብከለክለው ይመታኝ ይሁን በሚል ፍራቻ, ይሰጡታል። አንድአንድም አለ ሂድ ከዚ! ብሎ ቀልቡን ገፎ የሚያባርረው፧ ለነገሩ ማሂር ቀልብ የለውም! ቀልብ ቢኖረውማ የተቦጫጨቀ ልብሱን በቀየረ፤መንገድ ማደሩን ትቶ ወደቤቱ በገባ፤ ግን የት ነው ቤቱ? ከየትስ ነው የመጣው? ለምንድነው አብዛኛውን ጊዜ እዚህ ሰፈር የሚኖረው? እንደዚ ሲሆን ጠያቂ የለውም? ና ልጄ ብላ የምትሰበስብ እናት ወይ የሚሰበስብ አባት የለውም? ቤተሰቦቹስ? ዘመዶቹስ? የማን ልጅ ነው? ወደ ሰፈሩ የመጣ አዲስ ነዋሪ ፤ለእንግድነት የመጣ ሳይቀር የሚጠይቀው ጥያቄ ነው፤ግን መልስ የለም። ማሂር እዚ መንደር መቶ መዋል ማደር ከጀመረ አምስት አመታትን አስቆጥሯል አንዳንዴ ለተወሰኑ ቀናት ከመንደሩ ይጠፋል ግን እሰይ ተገላገልን የሚለው የለም፡፡ሁሌም አንድሳምንት ቆይቶ ይመጣል የት ይሂድ?ለምን ይሂድ? የሚያውቅ የለም! የመንደሩ ሰው እንደጎረቤቱ ለምዶታል፧ከአይናቸው ሲጠፋ ባይፈልጉትም ይጠይቃሉ የት ሄዶ ይሆን?ብለው ይጨነቃሉ! መኪና ገጭቶት ይሆን? እብድ ነው ብለው ቀጥቅጠውት ይሆን? ማሂር እኮ ግን እብድ አደለም! ሰው አይናካም የጫት ሱስ የለበትም ሰው አያሰቸግርም አይጮህም እንደ እብድ አይለፈልፍም! ትልቅ ሰው ይወዳል እቃ ተሸክመው ካየ ተቀብሏቸው የሚፈልጉበት ቦታ ያደርስላቸዋል። አሁን አሁንማ እነሱም ና እስቲ የኔ ልጅ ይሄን እቃ አድርስ!እያሉ ይልኩት ጀምረዋል። እንቢ አያውቅም አንገቱን እንዳቀረቀረ የተባለበት ቦታ ያደርሳል። የሰፈሩ ጎረምሶች እብዱ ደራሲ ይሉታል ያገኘው ነገር ላይ ይፅፋል ለሰው የማይገባ ለሱ እረፍት የሚሰጠው አይነት ፁሁፍ ወጣቶቹ ይወዱታል እሱም ሳንቲም እንዲሰጡት ስለሚፈልግ ሲያዙት ይታዘዛል እነሱም እጃቸው ለሱ ይዘረጋል ደሞ ብር አይቀበልም ሳንቲም ብቻ፤ ለሊት በሱ አጠገብ ያለፈ ሰው ሳንቲም ሲቆጥር ማየት የተለመደ ነገር ሆኗል፡ምን እንደሚያደርግበት ባያውቁም ይሰጡታል እሱም ይሰበስባል። ህፃናት የሚጫወቱበት ቦታ ላይ አይጠፋም አንድሰሞን ሲመጣ እየፈሩ ይሮጡ ነበር አሁን ይቀርቡት ጀምረዋል አንዳንዴ አብሯቸው ይጫወታል ያጫውታቸዋል አብሯቸው ይስቃል በሳቁ ውስጥ ግን ሁሌም እንባ አለ ቶሎ የማይደርቅ እንባ ሀዘን ስብራት እንዳዘለች የምታስታውቅ እንባ ያነባል ተስፋ የቆረጠ ናፍቆት ያጠቃው ብቸኝነት ያጎሳቆለው ሰው የሚያፈሰውን እንባ እንደጎረፍ ያዘንበዋል ማልቀስ ከጀመረ አያቆምም ግን እሱ እየሳቀ ነው ሚያለቅሰው! ሳቁ ደሞ ከጣራ በላይ ይሰማል፤ ሰዎች ሲያለቅሱ ደሞ ይስቃል፤ ሰፈር ውስጥ ለቅሶ ካለ እዛ ከአካባቢ አይጠፋም ሰዎች በሀዘን እንባቸውን ሲያወርዱ እሱ ግን በደስታ በሚመስል መልኩ ይስቃል በደስታ እንደሚቦርቅ ህፃን ይፈነድቃል እንግድነት ለመጣው ሰው አዲስ ነገር ቢሆንም መንደሩ ግን ይሄን ለምዶታል እና ተውት እብድ ነው ይባላል ።ሰዎች እብድ ነው የሚሉት እቤታቸው አስገብተው ሊያኖሩት የሚፈሩት ዋናው ምክንያታቸው ይሄ ነው። ዛሬ ግን ማሂር የለም እናቶች እንደህፃን የሚልኩት ህፃናቶች የጨዋታ ማድመቂያቸው ወጣቶቹን ሳንቲም እያለ የሚለምናቸው የፈለጉት ቦታ የሚልኩት ማሂር ዛሬ ቦታው የለም። እንደለመደው አንድ ሳምንት ቆይቶ ይመጣል ብሎ ሁሉም እየጠበቀ ነው። እሱ ግን የለም እናት ልጇ ወቶ እንደቀረባት ልጅ ከስራ ሲመጣ ብስኩት ገዝቶ እንደሚያመጣለት አባት ደጅ ደጁን እያዩ ነው አረ ባካቹ እብዱ ደራሲ እኮ ከጠፋ ሳምንት አለፈው እያሉ የወንድማቸውን ያህል የሚጨነቁለት ጎረምሶቹ ፍለጋቸውን ቀጥለዋል።ማሂር ግን የለም ........
ክፍል ሁለት ይቀጥላል.....

እብዱ ደራሲ ክፍል ሁለት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
....................
"ሲሁ ሲሀም ተነሺ እንጂ ስራ ረፍዷል፡ እንደ ቀልድ ሱብሂ በሰዐቱ መስገድ ተውሽ አይደል? እሺ አሁን ብድግ በይ ውሀ ሳልገለብጥብሽ"ብላኝ ወደ ኩሽናዋ ሄደች በጠዋት እንቅልፍ ማልደራደረው እኔ ስልኬን ከአጠገቤ ሳብ አድርጌ ሰዐቱን አየሁት ምክንያቱም ኡሚ ሁሌ ሱብሂ ልትቀሰቅቀኝ ስትፈልግ ስራ ረፍዷል ነው ምትለኝ እንዴት እንደምበሳጭባት! አንዴ ከተነሳው እንቅልፍ ስለማይወስደኝ በተነሳው ሰዐት ነው መስገድ ምፈልገው: እሷ ግን አትሰማኝም "ሱብሂ መስገድ ቀንሽን ሙሉ ደስተኛ እንድትሆኚ ያደርግሻል" ትለኛለች ለኔ ደስታ ሚሰጠኝ የጠዋት እንቅልፍ መሆኑ አይገባትም ግን ላለመጨቃጨቅ ስል"እሺ"እላታለው ኡሚ ግን እሺ ማለቴ የባሰ ያናድዳታል። "ሁሌ እሺ ብቻ እስኪ አንድ ቀን እንኳን ተግብረሽ አሳይኝ" ትለኛለች አሁን አሁንማ ሰለቻት መሰለኝ በስራ ሰዐት ነው ምትቀሰቅሰኝ ግን ምንም ቢሆን ከ12:40 አታሳልፈኝም ነበር፤ዛሬ ግን ረፍዷል ስልኬን ሳየው 1:05 ይላል ውሀ እንደተረጨ ሰው ብርድልብሴን ወርውሬ "ኡሚ ግን ምን ሆና ነው?እስካሁን ያልቀሰቀሰችኝ" እያልኩ እየተነጫነጭኩ ሻወር ለመውሰድ ወጣው።ትላንት ስዞር ስለዋልኩ እና አምሽቼ ስለተኛው ሰውነቴ ዛል ብሏል ሻወር ስወስድ ከለቀቀኝ ብዬ ቀዝቀዝ ባለ ውሀ ሻወር ወሰድኩ ግን ምንምን ስራ የመሄድ ሙዱ ሊመጣልኝ አልቻለም ግን ደሞ ግዴታ ነው!ለሰሙ አልነገርኳትም፤ ይህን እያሰብኩ ስልኬ ጠራ ሰሙ ነበረች
"እ አንቺ ጨራረሽ" አለችኝ "ምን አለ ደና አደርሽ ቢቀድም?" አልኳት "ትላንት አብረን መስሎኝ ያመሸነው በይ ነይ ውጪ እየደረስኩ ነው" ብላ ስልኩን ዘጋችብኝ "ምን አለ እንዳወራ እንኳን እድሉን ብትሰጠኝ ኡፍ ሰሙ ደሞ አሁን ደውዬ አልሄድም ብላት ራሱ ቤት መታ ለኡሚ አቃጥራ ታስወጣኛለች ከነሱጋር ከምንዛዛ ደሞ ብሄድ ይሻለኛል"ብዬ ልብሴን መልበስ ጀመርኩ "አንቺ ልጅ አረ ባክሽ ነይ ውጪ! ሻዩ ቀዘቀዘ እኮ አረ ምን ይሻልሻል በአላህ? ሰው አንድ ቀን እንኳን አያልፍለትም? ጓደኛዬ ትታዘበኛለች እንኳን አትይም እንዴ? አረ ተይ ሲሁ ቀልብ ግዢ ተይ"ኡሚ ምክሯን ልጀምር ነው። "ጨርሻለው ኮ ኡሚ ደሞ ቁርስ አልበላም፤አራበኝም" አልኳት ከክፍሌ ውስጥ ሆኜ፤ "አራበኝም ማለት ምን ማለት ነው? ከእንቅልፍሽ አደል እንዴ የተነሳሽው? ነይ ውጪ እና ቢ!"ቁጣ እና ትእዛዝ የተቀላቀለበት ድምፅ!መልስ ልሰጣት ስል የውጪው በር ተንኳኳ "ይሀው ጓደኛሽ መጣችልሽ ስትንከራፈፊ"ብላኝ በሩን ልትከፍት ወጣች "ኡፈይ አልሃምዱሊላህ ገላገልችኝ"ብዬ ቦርሳዬን አንጠልጥዬ ከክፍሌ ወጣው። ጫማዬን እየፈለኩ እንዳለ ኡሚ መጣች ከውሀላዋ ጓረቤታችን ወይዘሮ አኢሻ ተከትለዋት ገቡ። ፊታቸው ልክ አደለም መርዶ ነጋሪ ነበር ሚመስሉት፤ ኡሚም ተረብሻለች፤አጠገቧ እንደቆምኩ እንኳን አላስተዋለችም፤ "ደሞ ማን ሞተ አይ እኛ ሰፈር አዝራኤል አንዴ ከገባ ካልጠራረገን አይወጣም አደል?"እያልኩ እያሰብኩ ጫማዬን ለብሼ እንደጨረስኩ ሰሙ ደወለች "አረ አንቺ ሴትዬ ነይ ውጪ ያምሻል አ ሰዐት ኮ ረፍዶል ወላሂ ጥዬሽ ነው ምሄደው" ብላ ስልኩን ዘጋችው። እንደተበሳጨች ስለገባኝ ኡሚን "ደና ዋይ ብያት"ልወጣ ወደ ሳሎን ስገባ እሷም ከሳሎኑ ስትወጣ በር ላይ ተጋጨን ግን ትዝም አላልኳት! "ኡሚ ደና ዋይ በቃ ልሄድ ነው" ብዬ እንደለመድኩት ግንባሯን ልስማት ጠጋ ስል አይኖቿ እንደ ጉድ እንባን ያዘንባሉ፤በጣም ነበር የደነገጥኩት "ኡሚ ምንድነው የሆንሽው?ማነው የሞተው!ማን ምን ሆኖ ነው?" መልሷን አልጠበኩም ነበር "ምንም ምንም አደለም ልጄ ሂጂ በይ ወደ ስራሽ በጊዜ ተመለሺ የጊቢውን በር ቆልፈሽ ሱቅ አስቀምጪልኝ።" ብላ ጉንጪን ሳም አድርጋኝ ከቤት ወጣች ጨራርሼ ስለነበር ተከትያት ወጣው።"አይ የኔ ልጅ፣ የኔ የዋህ፣አይ ማሂርዬ" የሚሉ ከአንደበቷ የሚወጣ የለቅሶ ድምፅ ይሰማኛል። ጓረቤታችን እትዬ አይሻም "በልጅነቱ እንደዛ መሆኑ ሳያንስ አይይይ የሰው ልጅ መከራ እናቱ ምን ትል ይሁን አይይ ማሂር" እያሉ ከኡሚ ጋር ተከታትለው ከጊቢ ወጡ.....
ክፍል ሶስት ይቀጥላል .......

❤3
እብዱ ደራሲ ክፍል ሶስት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
.......
ሰዐቱ አምስት ሰዐት ሆኗል ሰሙ ጠዋት ስላረፈድኩባት እንደተኮፈሰች ኮምፒውተሯ ላይ አፍጥጣለች። እኔም የማሂር ነገር በጣም ስላሳሰበኝ ቢሮ ከገባው ጀምሮ ከማንም ጋር አላወራሁም እሷንም ቢሆን እንደ ሌላ ቀኑ አልተለማመጥኳትም። ሰሙ ልምምጥ ትወዳለች እኔ ደሞ ይህን ፀባዮን ስለማውቅ እለማመጣታለ፤ ዛሬ ግን ምንም አላልኳትም ቁርስ አለመብላቴን እንኳን ረስቼዋለው። ሰሙም እንደደበረኝ ገብቷቷል፤አስር ጊዜ ስልክ ስደውል በቆረጣ ታየኛለች አጠገቤ መታ ልታወራኝ ፈልጋለች፤ሄጄ አንዴ እንኳን ሰሙ በቃ Sorry ብላት እንደምትመለስ አውቃለው፤ግን በቃ ዛሬ ሙዴ አደለም! የማሂር ነገር አስጨንቆኛል፤ምን አለ ባልመጣው? እቤቴ ሆኜ ምን እንደተፈጠረ እንኳን አውቄ ነፍሴ ትረጋጋ ነበር!
"የኡሚ ስልክ አለማንሳት ደግሞ የባሰ ጭንቀቴን ጨመረው ""ማሂር ምን ሆኖ ይሆን መኪና ገጭቶት ነው? ሰዎች ደብድበውት ነው? ወይስ ሞቶ ነው?"ይህንን ሳስብ ሳላስበው እንባዬ ፈሰሰ።ሰሙ እያየችኝ እንደሆነ እንኳን አላስተዋልኩም "አሀ ሲሁ እያለቀሽ እኮ ነው" ብላ ከወንበሯ ላይ ተስፈንጥራ መታ አጠገቤ ተቀመጠች:እንባዬን ጠራርጌ"sorry ሰሙ" አልኳት "አሁን እሱን ተይው እና ምን ሆነሽ ነው? ኡሚዬ ደና አደለችም እንዴ?ከገባን ጀምሮ ኮ ልክ አደለሽም!" አለችኝ "ምንም ሰሙ ዝም ብዬ ነው" "ኡፍፍ አንቺ ደሞ ችግር አለብሽ ወይስ ሰውዬሽ ናፍቆሽ ነው?" ስትለኝ ሳቄን ለቀቅኩት።
..................................
ሰሙ የሳቄ ምንጭ፤ የጭንቀቴ ማቅለያ ነች። ትውውቃችን የቅርብ ጊዜ ቢሆንም ለሚያያየን የልጅነት ጓደኛሞች እንጂ የአመት ከ6 ወር ትውውቅ አይመስልም። ያወኳት እዚው መስሪያ ቤት ልቀጠር ሲቪ ላስገባ ስመጣ ነው እሷም እንደኔ ልትቀጠር መሆኑ ነው። ድርጅቱ የሚፈልገው ሁለት ሴት ብቻ ነው። እንደኛ ሊቀጠሩ የመጡት ግን ከ50 ይበልጣሉ፤ድርጅቱ የሙስሊም ስለሆነ ግማሽ ያህሉ ሙስሊሞች ናቸው።እኔና ሰሙ ወረፋችን ከፊት እና ከውሀላ ስለነበር ለመግባባት አልተቸገርን፤ የትት ማስረጃችንን የሚቀበለን ሰው አራት ሰዐት ቢሆንም ሚገባው እኛ ግን ወረፋ ለመያዝ ስንል ጠዋት አንድ ሰዐት በቦታው ተገኝተናል። ከሰሙ ጋር ብዙ አወራን፤ እዛ ቦታ ላይ የተገናኘን ሳይሆን አብረን የመጣን ነበር የምንመስለው፤ሰሙን ስላገኘውሀት ደስ ብሎኛል፤ የሚገርመው ደሞ ሁለታችንም የ Accounting ተመራቂ መሆናችን እና የተማርንበት ትት ቤት መገጣጠሙ ነው። ያልተዋወቅነው ሰሙ የማታ ተማሪ ስለሆነች እኔ ደሞ የቀን ተማሪ ስለሆንኩ ነበር።"እራሴ እየከፈልኩ ስለሆነ የማታ ነበር የምማረው"አለችኝ "ዋናው መማርሽ ነው ባክሽ!" አልኳት። እንደዛ እንደዛ እያልን ብዙ ብዙ ነገር አወራ፤ ሲበዛ ግልፅ መሆኗ አስገረመኝ፤ብዙ ጓደኞች ቢኖሩኝም ሁሌም አብሬያት መሆንን ተመኘው፡ አሁን ወረፋችን ደርሷል፤ ሁለታችንም ገብተን ወረቀታችንን አስገባን እና ተያይዘን ወጣን "ሁለታችንም አልፈን አብረን ብንሰራ ደስ ይለኛል" አለችኝ የኔም ፍላጓት ነበርና "ኢንሻአላህ" አልኳት ስልክ ተለዋወጥን እና ተለያየን። ከሰሙ ጋር ቅርርባችን በጣም ጠብቋል እቤት ትመጣለች ኡሚም ወዳታለች የትት ማስረጃ ያስገባንበት መስሪያቤት ስለፈተና ስንጠራ አብረን ነበር የሄድነው ውጤቱ ግን በጣም ዘግይቷል ሁለታችንም ተስፋ ቆርጠናል፤ ቢሆንም ግን አልደበረንም፤ አብረን እንውላለን፤አንዳንዴ ሁላ ሰሙ እኛ ቤት ታድራለች የምትኖረው ብቻዋን ስለሆነ ወደቤቷ ምትሄደው ለአዳር ነው። ቤተሰቧቿ እንደሞቱ እና ከአያቷ ጋር ክፍለ ሀገር እንደኖረች፤የ10ኛ ክፍል ውጤት ሲመጣላት በአጓቷ ልጅ እገዛ አ.አ እንደመጣች እና ከሱ ጋር እንደነበር የምትኖረው፤ ነገር ግን ሚስቱ ክፉ ስለነበረች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንደመጣላት ስታውቅ ከሱ ጋር አጣልታ ከቤት እንዳባረረቻት እና እሱም ከሚስቱ ተደብቆ እንደሚረዳት፤ ስራ እንዳስጀመራት፤የቤት ኪራይ ይከፍልላት እንደነበር፤የማታ ትት ያስመዘገባት እሱ እንደሆነ፤ ከአመት በውሀላ ግን በልብ ህመም እንደሞተ ሁላ በመጀመርያው ቀን ነበር የነገረችኝ። ይህንን ሁላ ስቃይ በልጅነቷ ስለተሸከመች ታሳዝነኛለች ጥንካሬዋ ብርታቷ በጣም ይገርመኛል።አንድቀን እንዲ ሆነ ሰሙ እኛ ቤት ነበር ያደረችው በጠዋት ስልኬ ጠራ ና ተነሳው ሳየው ባለፈው የተፈተንበት ድርጅት ቁጥር ነው ምን አልባት ሰሙ ካላለፈች ሳወራ እንዳትሰማ ብዬ ኔቶርክ እንደተቆራረጠበት ሰው ሄለው እያልኩ ከክፍሌ ወጣው.....
ክፍል አራት ይቀጥላል....

👍2
እብዱ ደራሲ ክፍል አራት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
........
እንደገመትኩት ነበር የሆነው ከድርጅቱ ደውለው ፈተናውን እንዳለፍኩ እና ስራ መጀመር እንዳለበኝ ተነገረኝ። የሀዘን እና የደስታ ስሜት ነበር የተሰማኝ፤ቀስ ብዬ ኡሚ ጋር ሄድኩ እና ነገርኳት ኡሚ በጣም ትጨነቅላታለች "በቃ አትንገርያት ይከፋታል ለሷ ካልተደወለላት ስራው ይቀራል ከፈለገ! እኔ እናታቹ እንድትለያዩብኝ አልፈልግም አሁን ሂጂ እና ቀስቅሻት ቁርስ ደርሷል"አለችኝ።ኡሚ እንደዛ ስትለኝ ቅልል አለኝ ወደ ክፍሌ ስገባ ሰሙ ነቅታለች "ሴትዬ ተነስተሻል እንዴ?ነይ በይ ቁርስ ቀርቧል" አልኳት እና ወጣው ሰሙ ፊቷ ልክ አደለም የተረበሸ ከተማ መስላለች ቁርሱንም በስነስርዐት እየበላች አደለም የሰሙን እንደዛ መሆን ስናይ የኔም የኡሚም ግምት አንድአይነት ነበር "ምነው ሰሙ ደና አይደለሽም እንዴ ፊትሽ ልክ አደለም?" አለቻት ኡሚ "አረ ምንም አልሆንኩም ኡሚ ስቃዥ ነበር ያደርኩት" አለቻት እየዋሸች እንደሆነ ሁለታችንም አውቀናል "አብሽሪ እህቴ ብዬ ሳብ አድርጌ አቀፍኳት" አንገቴ ውስጥ ተወሽቃ "ወድሻለው እሺ ምንም ይሁን ምን ካንቺ አይበልጥብኝም" ስትለኝ ሳላስበው እንባዬ ወረደ ኡሚ ብቸኛ ልጇ ስለሆንኩ እንደዚች አይነት እህት በማግኘቴ በጣም ደስ ብሏታል "አብሽሩልኝ እኔ እናታቹ እያለው ማንም አይለያቹም!"ብላ ሁለታችንንም ሳመችን እና የበላንበትን እቃ አንስታ ወደ ኩሽና ገባች ሰሙም ሱፍራውን ጥቅልል አድርጋ ኡሚን ተከተለቻት ኡሚና ሰሙ በሹክሹክታ ሲያወሩ ይሰማኛል፤ ኡሚ ለሰሙ እየነገረቻት ይሁን? ብዬ በጣም ፈርቻለው። ወሬያቸውን ጨርሰው ከኩሽና ሲወጡ ኡሚ ያለመደባትን "ሂዱ በሉ የሰሙን ቤት ፏ ፏ አድርጋቹ ኑ" ብላ ላከችን "ሰሙም አይ እኔ ብቻዬን እሄዳለው" አለች? "ከመች ጀምሮ? አለች" ኡሚ በመቆጣት ድምፅ እኔም ግራበመጋባት ቀና ብዬ አየውሀት እንደከፋት በጣም ታስታውቃለች ኡሚን በቁጣ አይነት አስተያየት ሳያት"ምን ታፈጪብኛለሽ?ተነሺ ደርሳቹ ኑ" አለችኝ አሀ ሌላ ቀን የሰሙን ቤት አፅድተን እንኳን እንመለስ ስንላት የምን ቤት ነው? የሷ ቤት እዚ ነው! እንደውም እቃውን ጭናቹ ኑ! ነበር የምትለን ዛሬ ምን ተገኘና ነው? በቃ ሰሙ ፈተናውን አላለፈችም!ኡሚም ነግራታለች ለዛ ነው ሰሙም ብቻዬን እሄዳለው ያለችው።ኡፍ ኡሚ ደሞ ምን አጣደፋት ደሞ ከፈለገ ይቀራል ብላኝ አልነበር እንዴ? ብቻ በፍርሀት ስሜት ውስጥ ሆኜ ከሰሙ ጋር ተያይዘን ወጣን። የሰሙ ቤት ከኛ ብዙም አይርቅም፤ሌላ ቀን በእግራችን ነበር ወደሷ ቤት የምንሄደው፤ ዛሬ ግን ሁለታችንም አይደለም እየተጓተትን በእግራችን የመሄድ ታክሲውም ቀርቶብን እቤት ብንቀመጥ ሁላ ደስተኞች ነበረን። ከኡሚ ጋር ላለመነታረክ ነው የወጣነው፤ምንም አላወራንም። አንዴ ብቻ ሰሙ "ሲሁ ከድርጅቱ ደወሉልሽ እንዴ? አለችኝ። በጣም ነው የደነገጥኩት "አይ አረ አልደወሉም ላንቺ ደወሉልሽ እንዴ?" አልኳት "አይ" አለችኝ ብቻ እንደዛ እንደደባበረን የሰሙን ሁለት ክፍል ቤት እንደነገሩ አፀዳድተን ያልታጠበውን እቃ አጥበን ወደቤት ተመለስን።
..........
እቤት ስንገባ ኡሚ ጓረቤት ሰብስባ ዳቦ ደፍታ ቤቱን በዐል አስመስላ ነበር የጠበቀችን።ገና ከበር ስንገባ በእልልታ ጊቢውን አቀለጠችው እኔም ሰሙም ተያየን ሁለታችንንም አቅፋን አለቀሰች ለካስ ሁለታችንም ፈተናውን አልፈን ኖሯል ደስታችን ልክ አልነበረውም ከሳምንት በውሀላ ሁለታችንም ስራችንን ጀመርን አንድ ድርጅት አንድ ቢሮ ላይ ሰሙ አንዳንዴ ቤቷ ብዙውን ጊዜ እኛ ቤት መኖር ጀምራለች።
..................
"ነይ በቃ ምግብ አልበላሁም እየሄድን እነግርሻለው" አልኳት እና የቢሮውን በር ዘግተን ወጣን። ወደ ምግብ ቤቱ ስንሄድ ጠዋት የሆነውን ከሀ እስከ ፖ ነገርኳት ሰሙ ማሂርን እኛ ቤት ስትመላለስ ታውቀዋለች የመጀመርያ ሰሞን ትፈራው ነበር አረ!ጭራሽ ወደሰፈሩ መምጣት አቁማ ነበር ከጊዜ ቡሀላ ግን ማሂር እብድ አደለም! ብላ ትሞግት ጀምራለች። በነገርኳት ነገር አዝናለች፤ የኔ ስሜት ተጋብቷባታል ፤ተፅናንታ ልታፅናናኝ ፈልጋለች:ግን ሁለታችንም ውስጣችን ፈርቷል ማሂር ሞቶ ይሆን? የሁለታችንም ጥያቄ ነው! ግን ማን ይመልስልን? ምግቡን አዘን እንደነገሩ ቀማምሰን ተውነው፤ "ምነው?ምግቡ አልጠፈጣቹም እንዴ?" የሚለው የእማማ ጥያቄ ነበር ከሀሳባችን ያባነነን፡ልክ እንደተመካከረ ሰው እኩል "አረ ይጣፍጣልእማማ!"አልን ንግግራችን ለራሳችን ፈገግ አደረገን እና ሂሳብ ከፍለን ወጣን የሁለታችንም ሀሳብ ማሂር ጋር ነበር ምንም ማውራት አልፈለግንም እናውራ ብንልስ ውስጣችን እየተረበሸ እንዴት ብለን ብቻ በሀሳብ ተጠምደን ወደ ቢሮ በዝግታ እየሄድን የኔ ስልክ ጠራ ኡሚ ነበረች.......
ክፍል አምስት ይቀጥላል.........

🔔ኑዛዜው
አንድ ሰው ይሞታል።17 ግመሎች እና 3 ልጆች ነበሩት።ኑዛዜ ሲነበብ "የግመሎቼን ግማሽ ለመጀመሪያው ልጄ አንድ ሶስተኛውን ለሁለተኛው ልጄ እንዲሁም የግመሎቼን አንድ ዘጠነኛ ለመጨረሻው ልጄ ተናዝዣለሁ"ይላል። ልጆቹ ግራ ተጋቡ ምንድን ነው ማድረግ የሚችሉት? የ17ቱ ግመሎች ግማሽ ለመጀመሪያው ልጅ ይሰጥ ተብሏል የ17 ግማሽ 8 ይሆን እና አንድ ግመል ይተርፋል እና አንዱ ግመል ሊሰነጠቅ ነዉ? ይሄንንም ቢያደርጉ እንኳ መፍትሄ አይሆንም ምክንያቱም የግመሎቹ አንድ ሶስተኛ ደግሞ ለሁለተኛው ልጅ ይሰጥልኝ ብሏል አባትዬው። ይሄም ቢሆን ችግሩን አይፈታውም።የግመሎቹ አንድ ዘጠነኛ ደግሞስ ለሦስተኛው ልጅ ይሰጥ ይላል ኑዛዜው። ግመሎቹ ሁሉ ተቆራርጠው ማለቃቸው እኮ ነው።ለችግሩ መፍትሄ ለማግኘት በመንደሩ የታወቀ የሒሳብ ምሁር ዘንድ አመሩ።ሰውየው በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ቢያስብበትም መፍትሄ ግን ሊያገኝለት አልቻለም።
"እኔ በህይወቴ ቁጥሮችን እንጂ ግመሎችን አካፍዬ አላውቅም ይሄ ተራ ማጃጃያ ነው የሚመስለኝ።ኑዛዜው በትክክል መተግበር ካለበት ግን ግመሎቹን መሰንጠቅ ግድ ነው።" አላቸው ልጆቹ በሰውየው ምክር አልተስማሙም። ግመሎቹ እንዲሰነጠቁ አይፈልጉም። ታዲያ ምን ተሻለ??? ነገሩን በቅርበት ሲከታተል የነበረ አንድ ሰው ወደ እነሱ ጠጋ ብሎ "ከቁጥር ይልቅ ስለ ግመሎች የሚያውቅ ሰው ብታማክሩ ይሻላችኋል" ሲል መከራቸው። እነሱም በሰውዬው ምክር ተስማምተው ስለ ግመሎች የሚያውቅ ሰው ሲፈልጉ አንድ እርጅና የተጫጫነው፣ያልተማረ፣ነገር ግን ከህይወት ልምድ ብልህነትን የቀሰመ አዛውንት አገኙና ችግራቸውን አማከሩት።
አዛውንቱ ሰው ስቆ "አታስቡ ነገሩ ቀላል ነው"አላቸው ከዛም አዛውንቱ የራሱን አንድ ግመል አበደራቸውና የግመሎቹ ቁጥር 18 ሆነ "ከዚህ በኋላ ተካፈሉ" አላቸው። በኑዛዜው መሰረት የግመሎቹ ግማሽ 9 ነውና ለመጀመሪያው ልጅ ተሰጠው፤ደስም አለው። የግመሎቹ አንድ በሶስተኛ 6 ነውና ለሁለተኛው ልጅ ተሰጠው፤ደስም አለው። የግመሎቹ አንድ ዘጠነኛ 2 ነውና ለሶስተኛው ልጅ ተሰጠው፤ደስም አለው።አንድ ግመል ቀረ ሽማግሌው አንድ ግመል አበድሯቸው አልነበር፣ያበደራቸውን አንድ ግመል መልሶ ወሰደ።"አሁን መሄድ ትችላላችሁ" ብሎ አሰናበታቸው፤እነሱም ተደሰቱ።
ተራ እውቀት(Knowledge) ተግባራዊ አይደለም።በልምድ የካበተ ጥበብ(wisdom) ግን ተግባራዊ እና ተጨባጭ ነው። እውቀት ተራ የቃላት ጨዋታ ነው ጥበብ እና ብልህነት ግን ከህይወት ልምድ የተጨለፉ ናቸው።
✍Osho
🙏ውብ ቅዳሜ❤️
#share

እብዱ ደራሲ ክፍል አምስት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
.........
እኔና ሰሙ የደወለችው ኡሚ መሆኗን ስናውቅ በድንጋጤ ቆመን ቀረን መንገድ ላይ ስለሆነ ያለነው ስልኩን ማንሳት አልፈለኩም ኡሚ ስለ ማሂር ምንም አለችኝ ምን መንገድ ላይ ማውራቱን አልፈለኩትም ሰሙም ሀሳቤን ተገራታኛለች ኡሚ ደጋግማ ብትደውልም ቢሮ እስክንገባ ላለማንሳት ወስነናል ሌላ ቀን እያዘገመን ሚያጥርብን መንገድ ዛሬ ግን ረዝሞብናል ሁለታችንም ውስጣችን በፍርሀት ተሞልቷል እንዴትም ብለን ቢሮ ስንደርስ የቢሮውን በር ክፍት አገኘነው ሁለታችንም በድንጋጤ እና በመሰላቸት አይነት አስተያየት ተያየን በቃ ሰውዬሽ መቷል ማለት ነው አለችኝ በሹክሹክታ ይሆናል በቃ ኤጭ ካልጠፋ ቀን በዚ ሰዐት ይመጣል ምኑ ብሽቅ ነው በአላህ አልኳት ስንገባ የሚከተለንን የስራ ብዛት እያሰብኩኝ፤ አለቃችን ከእድሜ ብዙም ከኛ አይበልጥም ነገር ግን ነገረ ስራው ሁላ እንደሽማግሌ ነው መነጫነጭ በጣም ይወዳል ሰሞኑን እቃ ሊያመጣ ወደ ዱባይ ሄዶ ስለነበር ደህና ተገላግለነው ነበር ደሞ ሳይናገር ነው የሚመጣው እሱ እዚ ቢሮ አለ ማለት ማውራት የለ መሳቅ የለ ስልክ ማውራት የለ በፈለጉ ሰዐት መውጣት መግባት የለ ከእኔ ጋር ማ የሆነ ጂኒ አያይዞታል ሲሀም እንዲ ሆነ ሲሀም እንደዛ ሆነ ሲሀም በዚ ገባ ሲሀም በዚ ወጣ በደቂቃዎች ውስጥ 50ጊዜ ነው ስሜን ሚጠራው በሱ የተነሳ ስሜን ራሱ ጠልቼዋለው አንዳንዴማ እዛ ቢሮ ውስጥ ካለእኔ ሰራተኛ ያለ አይመስለውም ሰሙን ከነመፈጠሯ ረስቷቷል ሌላ ቅርንጫፍ ቢኖረውም እሱ ግን ካለዚ ቢሮ ያለው አይመስለውም አሁንማ ጭራሽ ከአጠገባችን ያለውን ቢሮ የራሱ ሊያደርገው እያሳደሰው ነው እሱ እዚ ቢሮ የገባ ቀን እኔ ወደ ሌላ ቢሮ ቀይሩኝ እላለው ወይም ከስራው እለቃለው ስላት ከትከት ብላ እየሳቀች ስለሚወድሽ ነው ኮ ትለኛለች ለዛም ነው ሰውዬሽ ምትለኝ ።እኔ ግን አሁን ከስራው እና ከአለቃችን በላይ የማሂር ነገር በጣም አሳስቦኛል ቢሮ ከገባን በውሀላ ለኡሚ መደወል እንደማልችል ብደውልም በስነስርዐት እንደማላወራት ስላወኩኝ ሰሙን ከመግባታችን በፊት እንደውልላት አልኳት ሰሙ ምንም እንኳን የማሂር ነገር ቢያስጨንቃትም ኡሚን በተጣደፈ አነጋገር ማናገሩን አልመረጠችም እሱ ለምሳ መውጣቱ ስለማይቀር በዛ ሰዐት እንደውላለን ባይሆን እንዳትጨነቅ አለቃችን እንደመጣ ንገሪያት ስራ እንደበዛብን ይገባታል ብላኝ ለኡሚ ደወልኩላት ግን ለማናገር ድፍረቱን ስላጣው ለሰሙ ሰጠውኋት ሰሙ የኡሚን ድምፅ ስትሰማ ፊቷ ተቀያየረ ግን እኔ እንድነቃባት ስላልፈለገች በግድ ለመሳቅ እየሞከረች ነበር ነገሩ ግራ ስለገባኝ ስልኩን ተቀብዬ ኡሚ ደና ነሽ አልኳት ኡሚ ድምፄን ስትሰማ እንደደነገጠች ድምጿ ያሳብቅባታል ከኡሚ ድምፅ ጀርባ ለቅሶም አይሉት ሳቅ የሚመስል ድምፅ ይሰማኛል አሁን ከቅድሙ የበለጠ ልቤ በፍርሀት ልፈነዳ ደርሳለች ደና ነኝ ሲሁ እንዴት ዋልሽልኝ እህትሽ እኮ አለቃቹ እንደመጣ ነገረችኝ ስራ ይበዛባቹሀል በቃ ጠንክሩልኝ ልጆቼ ደና ዋሉ በተመቻቹ ሰዐት ደውሉልኝ በቃ ካልሆነም ቤት ኑ አብራቹ ምትወዱትን ምሳ ሰርቼ ጠብቃቹሀለው ብላ ምንም መልስ እንዳልሰጣት በሚመስል መልኩ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ጠረቀመችብኝ። ይሄ የኡሚ የሁልጊዜ ንግግር እንደሆነ ባውቅም የዛሬው ግን የሀዘን እና የስስት ነገር አለበት። አሁን የበለጠ ልቤ ፈርቷል ቦርሳዬ ውስጥ ባይሆን እና ይ የተመታ ሰውዬ ባይመጣ ኖሮ ወደቤት እሄድ ነበር አሁን ግን ግዴታ ነው መግባት እና ከሰሙ ጋር ወደ ውስጥ ገባን ገና ከመግባታችን እሺ ማጂላኖች በስራ ሰዐት እንኳን አትቀመጡም ብሎ በነገር ለኮሰን ምን አለ አሁን የመጣው ከዱባይ ነው ሰላምታው አይቀልም የተረገመ ሼባ ብዬ በውስጤ ተሳድቤ ወደ ቦታዬ ሄጄ ተቀመጥኩኝ ገና ከመቀመጣችን ይህን የስራ order ጀመረ በቃ እኔና ሰሙ የማሂርን ነገር ባንረሳውም ግን አሁን 75% የሚሆነው ሀሳባችን ስራው ላይ ሆኗል ሳናውቀው ሰዐቱ 9 ሆኗል ለካ አረ ዙሁር እንስገድ አለች ሰሙ በዛውም ምሳ እንብላ አይነት መልእክት በቃ በተራተራ ስገዱ ምሳ ደግሞ እኔ ነኝ ምጋብዛቹ እዚው አብረን እንብለላን ብሎ የኛን ፍቃድ እንኳ ሳይጠይቅ ደውዬ ልዘዝ ብሎ ወጣ ምሳ ሰዐት ላይ ኡሚ ጋር እንደውላለን ብለን የነበረ ቢሆንም ይሄ ሰውዬ ግን ምንም እረፍት ሊሰጠን አልቻለም ሁለታችንም በሰጨት ብለን የየራሳችንን ስድብ አወረድንበት እና በቃ ውዴ ተረጋጊ አላህ ያለው ነው ሚሆነው ብላ ግንባሬን ሳመችኝ እና ለኡዱ ወጣች በተራ በተራ ሰገድን እና ምሳችንን መቶ በልተን ወደ ስራችን ገባን አሁንም እንደቅድሙ በስራ ተወጥረን ሳናውቀው 12 ሰዐት ሆኗል ለካ ኡሚ ደወለች በድንጋጤ ቀና ብዬ ሰሙን አየውሀት አለቃችን ፊትለፊት ስለነበር ማውራት አልቻልንም ዝም ብዬ ስልኩን አንስቼ ወዬ ኡሚ አልኳት አሁን ከቅድሙ ድምጿ መረጋጋት አለው እናንተ ልጆች ቡናው ኮ ቀዘቀዘ አለችኝ መጣን መጣን ኡሚ ልንወጣ ነው አልኳት በዛውም ለሰሙ እንውጣ ለአዩብ ደግሞ ልንወጣ ነው የሚል መልእክት እያስተላለፍኩ ነው። ስልኩን ስዘጋው በቃ ሂዱ ጠዋት በጠዋት ኑ እና ትጨርሱታላቹ አለን ማስጠንቀቂያ መሆኑ ነው እሺ ደና እደር ብለን ተያይዘን ውልቅ ብለን ወጣን ሁለታችንም እቤት እስክንደርስ ቸኩለናል ኡሚ ስለማሂር ምን ትለን ይሆን ማሂር ምን ሆኖ ይሆን.......?
ክፍል ስድስት ይቀጥላል ......

👍3
እብዱ ደራሲ ክፍል ስድስት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
............
አረማመዳችንን ላየ ቶሎ ብለህ ና ተብሎ በማስፈራርያ የተላከ ህፃን ነው ምንመስለው ከእርምጃ በጣም በፈጠነ ከእሩጫ ባልተናነሰ እርምጃ ታክሲ መያዣው ጋር ደረስን ታክሲ ሰልፉ እንደዛሬ ረዝሞብኝ አያውቅም ደሞ ለእልሁ ታክሲውም የለም የምንሰራበት ድርጅት መሀል መርካቶ እንደመሆኑ መጠን በስራ መውጫ ሰአት በጣም ብዙ ህዝብ ነው የሚኖረው ያንን ሁላ ሀልቅ ደሞ ሲኖ ካልጫነው በስተቀር አያልቅም። ደሞ ሚጋፋው ህዝብ ብዛቱ ደና ሰልፍ ይይዙ እና ልክ ታክሲ ሲመጣ ሰልፍ የለ መጋፋት ና መራገጥ! አንዳንዱማ እርግጫው አህያ ያስቀናል!የመገናኛ ታክሲ ብዙ ቢመጣም ህዝቡ ሁላ እዛ ሚሄድ ይመስል ታክሲው አይበቃም ግማሹ በቅጥቅጥ፤ግማሹ በሀይገር ቢሄድም ህዝቡ ግን ምንም ያህል ሊቀንስ አልቻለም እንደውም የጫናቸውን በጀርባ እያመጣ ሚገለብጣቸው ነበር የሚመስለው። ብቻ አሰልቺ ነው እኔ ና ሰሙ ሌላ ጊዜ አደለም ልንራገጥ እና ልንጋፋ ይቅርና ብንገፋ ራሱ ይቅርታ እንጠይቅ ነበር፡ዛሬ ግን መቆም ሁላ ሰልችቶናል ተጋፍተን እንደማይሆንልን እያወቅን መጋፋትን መርጠናል ግን ምንም ሊሳካልን አልቻለም እንደውም አንድ አህያ የሚያስንቅ ሰውዬ እግሬን ረገጠኝ በጥፊ ብለው ሁላ በጣም ደስተኛ ነበርኩ! ደሞ ከሱም ብሶ እያየሽ አትጋፊም?አለኝ ሰሙ ሳቅ መቆጣጠር የሚባል ነገር አልፈጠረባትም ሳታስበው በሰማችው የሰውየው ንግግር ሳቋን ለቀቀችው ና እኔን ከመሀል ጎትታ አወጣችኝ እኔ ለራሴ እግሬን አሞኛል አንቺ ትገለፍጫለሽ አ።?ብዬ ግልምጥ አደረኳት!እሷ ግን አደለም አይዞሽ ልትለኝ ማውራት እስኪያቅታት ትንተከተካለች አሁን ከሰውየው እርግጫ እና ግልምጫ የባሰ የሷ ሳቅ አበሸቀኝ።ችግር አለብሽ ወላሂ አንዴ መሳቅ ከጀመርሽ አታቆሚም አ?ደሞ ምን አለ ሚሳቅበትን ቦታ እንኳን በስርዐት ብታውቂ?ኡሚ እንደዛ ሆና እየጠበቀችን አንቺ እዚ ታሽካኪያለሽ? ገደል ጊቢ ስፈልጊ !ብዬ ሰሙን ጥያት ወደ ታክሲው ሰልፍ ሄድኩ የተናገርኳት ሁሉ በንዴት እና በጭንቀት ብዛት ቢሆንም ጥፋተኛ ነች ብዬ ደምድሜያለው። እሺ በቃ ይቅርታ!ነይ ራይድ እንጥራ? እኔጋ ብር ስላለ እኔ ከፍላለው አለችኝ በተሰበረ ድምፅ ምንም መልስ አልሰጠውኋትም! ሰሙን አስከፍቻታለው ግን አሁን ከሷ በላይ የማሂር ነገር ነው ሚያሳስበኝ ስለዚ መለማመጥም ይቅርታም መጠየቅም አልፈለኩም። ራይዱ በ5 ደቂቃ ውስጥ ያለንበት መጣ እቤት እስክንደርስ በጣም ቸኩያለው የኔ ፍጥነት ደሞ የተለየ ነበር ሹፌሩን ቀይሬው ብነዳ ሁላ ደስተኛ ነኝ ይህን ያህል ያንገበገበኝ ግን ምንድነው? መመለስ ያልቻልኩት ጥያቄ!የትራፊክ መብራቱ 2 ደቂቃ ሳይሆን 2ሰዐት ሆነብኝ፧ ልጅ ጥላ እንደመጣች እናት ነበር ያደረገኝ ሰሙ ግን ተረጋግታለች ፊቷ ቢረበሽም ልቧ በጭንቀት ቢወጠርም የኔን ያህል አልቸኮለችም ግን የረበሻት የኔ ንግግር ይሁን የማሂር ነገር አላወኩም ዝም እንደተባባልን ሰፈር ደረስን ለምን እንደሆነ ባላውቅም ወደሰፈር መግቢያ ጋር ስንደርስ ሰሙ እዚጋ አውርደን አለችው ሌላ ቀን በራይድ ስንመጣ ቤት ያድርሰን የምትል ልጅ ዛሬ ጭራሽ ሰፈር መግቢያው ላይ በቃ ተናዳለች ወደ ቤቷ ልትሄድ ነው ብዬ ስላሰብኩ ምንም ሳልል ወረድኩ እሷም ሂሳቧን ከፍላ ተከተለችኝ። ወደነሱ ሰፈር መግቢያ ቅያስ ጋር ስንሄድ ትሄዳለች ብዬ ነበር ግን እንደፈራሁት አላደረገችም ትንሽ ቅልል አለኝ።ወደ እኛ ሰፈር ስንቃረብ ሰሙ እጄን ይዛ አስቆመችኝ እና እህቴ በጣም እንደጨነቀሽ የማሂርን ነገር ለማየት እንደቸኮልሽ አውቃለው ግን መጀመርያ እራስሽን አሳምኚው ሁሉንም የሚያደርገው አላህ ነው እናም ተረጋጊ ተረብሸሽ ኡሚን እንዳትረብሻት አለችኝ ከኡሚ ጋር በስልክ ያወሩት ነገር ሰሙ ፊቷ ሲቀያየር ኡሚ የኔን ድምፅ ስትሰማ የደነገጠችው ድንጋጤ የሆነ ነገር እንደተፈጠረ አሳመነኝ ሳላስበው ማሂር ሞቷል አይደል ሰሙ ብያት እንባዬ ያለ ገልጋይ መፍሰስ ጀመረ ሰሙ በጣም ደነገጠች ወላሂ ውዴ እንደዛ አደለም እኔ ምንም ማውቀው ነገር የለም የተፈጠረውን ነገር ስለማናውቅ እንጠንክር ብዬ ነው ብላ እሷም እንባዋን ያለ ከልካይ አፈሰሰችው።አሁን ስድቡም ሳቁም ተረስቶ ሁለታችንም በማሂር ሀሳብ ገብተናል ሰሙ ሁሉንም እንዳልተፈጠረ አድርጋ ትታዋለች። እንባችንን ጠራርገን ወደ ሰፈር ገባን ሰፈር ውስጥ ምንም አዲስ ነገር አላየሁም ምን አልባት ዘመድ ስለሌለው ይሆን? እቤት ስንገባ ኡሚ እቤቱን አጫጭሳ ቡና አፍልታ እየጠበቀችን ነበር ሱፍራ ላይ ሰሙ ምትወደውን የክትፎ ጥብስ በአንድ ሰሀን እኔ የምወደውን እሩዝ በአንድ ሰሀን ሻይ አድርጋ እየጠበቀችን ነው የማየውን ነገር ማመን አልቻልኩም ኡሚን የጠበኳት እያለቀሰች አዝና ምናምን ነበር ግን ከጠበኳት በተቃራኒ ነበር ያገኘውሀት እኔና ሰሙ ተያየን ብቻ የኡሚ እንደዚ መሆን ሁለታችንንም አረጋግቶናል ግቡ እንጂ ምን ይገትራቹሀል፤ እናንተን ስጠብቅ ቡናውን እኮ ቀቀልኩት አለችን ሁላታችንም ሰላም ብለናት ቦርሳችንን ጥለን እጃችንን ልንታጠብ ወደ ውስጥ ገባን ሰሙም እኔም ግራ ቢገባንም ኡሚ ስላቻኮለችን ምንም ሳንል ወደ ሳሎኑ ተመለስን በሱፍራው ዙርያ ተቀምጠን ምግብ መብላት ጀመርን ኡሚ ማሂርን ከነመፈጠሩ የረሳችው ትመስላለች እኔ እና ሰሙ ግን ማሂርን ማሰብ አላቆምንም ኡሚን መጠየቅም ፈርተናል ምን አልባት ማሂር እኛ እንደገመትነው ሆኖ ቢሆን እና ኡሚ እሱን ለመርሳት ቢሆንስ እንደዚ እያደረገች ያለችው? ኡሚ ቀኑን ሙሉ የሰራችውን ሁሉ እያወራችህን ነበር ግን አንዴም ቢሆን ስለ ማሂር አላነሳችም በጣም ግራ ገብቶኛል አሁን ግን ልጠይቃት ወስኛለው እኔ ምልሽ ኡሚ ወዬ አለችኝ በጣም እየፈራው ቢሆንም ማሂር እንዴት ሆነ? አልኳት የፈራሁት አልቀረም ኡሚ እንባዋን ያለከልካይ አወረደችው ሰሙ እና እኔ ድንጋጤ አደነዘዘን በተቀመጥንበት ደርቀን ቀረን ተነስተን እንኳ ኡሚን ለማማበል አልደፈርንም .......
ክፍል ሰባት ይቀጥላል....

እብዱ ደራሲ ክፍል ሰባት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
............
ትረፊ ያላት ነፍስ አሉ ጋሽ አህመድ ብቻ አልሃምዱሊላህ ተርፏል ባይባልም አልሞተም ። የመኪና አደጋ ነበር የደረሰበት ነገር ግን ሹፌሩ አላህ የመረቀው ወጣት ስለሆነ ትቶት አልሄደም እሱ ወድያው ሀኪምቤት ባይወስደው ኖሮ አይተርፍ ብቻ አልሃምዱሊላህ ብላ እንባዋን ጠራረገች።እሺ አሁንስ እንዴት ሰሙ ነበር የጠየቀችው ዶክተሮቹ ማንም የማይገባበት ክፍል አስተኝተውት ማንም አላየውም እነዚ እነማናቸው እዛ ታች የሚቀመጡት ጎረምሶች? እነ ኡስማንን ነው ኡሚ?አልኳት አዎ! እነሱም ካላየነው አናምንም ብለው ቢበጠብጡም የባሰ ከሀኪምቤቱ ተባረሩ አረ እንደውም ማስጠንቀቂያ ሳይሰጣቸው አይቀርም እዚ በር ላይ ትደርሱ እና ሳይባሉ ሁላ አይቀርም አለችን እኔና ሰሙ በረጅሙ ተንፍሰን እኩል አልሃምዱሊላህ አልን በጣም ተጨንቀን እንደነበር የገባት ኡሚ ልጆቼ ለሰው ልጅ መጨነቅ እኮ የኢማን ግማሽ ነው አለችን ኡሚ ሁሌም እኛን ለማስፈራራት ሆነ ለማደሰት በራሷ ሀዲስ እንደምትፈጥር ስለምናውቅ ሳቃችንን ለቀቅነው ምን ያስገለፍጣቹሀል ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እኮ ናቸው ያሉት አለችን አይ ኡሚዬ ሀዲሶችሽ ብዛታቸው ብለን ተሳሳቅን።ሰሙ አረ አልሃምዱሊላህ ብቻ እንኳን ተረፈ እኛማ ኮ በጣም ተጨንቀን ነበር የሲሁ ደሞ ይባስ ስትል ኡሚ ቀበል አድርጋ ቆይ አንቺ ከመች ጀምሮ ነው እንደዚ አስተዋይ የሆንሽው እ አለችኝ ሾርኒ መሆኑ ነው ።አይ ኡሚዬ ወላሂ ለእኔም ግራ የገባኝ እሱ አደል ከልክ በላይ ነው ኮ የተጨነኩት ኡፍ ዋናው እንኳን አልሞተ ደሞ ማን ያውቃል አላህም የኔን ጭንቀት አይቶ ይሆናል ያተረፈው አልኩ በማልገጥም በጉራም አይነት ነገር እሺ የኔ ወልይ ሰላቱን በስነስርዓቱ በሰገድሽው ወገኛ አለች ኡሚ ። ኡሚ ስለ ሰላት ከተነሳ በዛውም የምክር አገልግሎቷን እንደምትጀምር ስለማውቅ እሷ ከጀመረች ደግሞ አቶ ሰሚራ እንደምትከተላት ስለገባኝ በሉ ልረፍበት ስብሰለሰል ነው የዋልኩት ብዬ ብድግ አልኩ ሰይጣንሽ ተነሳብሽ አ አለችኝ ኡሚ ሁሌም እንደዚ ስለማደረግ ለምዳዋለች ሰሙም እኔ በቃ ቤት ልሂድ ስትል መለስ አልኩ የምን ቤት ነው ወላሂ ዛሬማ እዚ ነው ምታድሪው እንደውም በጠዋት ተነስተን ማሂርን ጠይቀን ነው ወደስራ ምንገባው አልኳት ኡሚም እንድትሄድ ስለማትፈልግ አዎ ብላ ሰሙን አሳመነቸት እና ቤት አደረች።
....................
ቀናት ቀናት እየተኩ ማሂር ሀኪም ቤት ከተኛ 15 ቀን ሆኖታል ዶክተሮቹ ከ1 ሳምንት ቡሀላ እንደሚወጣ ነግረውናል የሰፈሩ ሰው እኛ ስላለን ነው መሰለኝ ብዙም አይመጡም እነ ኡስማን ወደ ሀኪም ቤቱ መግባት ስለተከለከሉ እኛን ነው ሚጠይቁት መድሀኒት ምናምን ሲያስፈልግ ገዝተው አምጥተው ለኛ ይሰጡናል ለነገሩ ማሂርን የገጨውም ሰውዬ ኡሚ እንዳለችው ጥሩ ሰው ነበር እሱ ነበር የሚያድርለት ሁሌም አዉፉ በለኝ እያለ የማሂርን እጅ ይዞ ያለቅስ ነበር ማሂር ግን አረ ምን አደረከኝ እንደውም ኮ ለመኖሬ ሰበብ ሆንክልኝ ይለው ነበር እሱም ቢሆን አሁን የግራ እግሩ ስለተጎዳ በዊልቸር ይሂድ እንጂ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ደና ነው።ኡሚም ምግብ እየሰራች እሱን መካደም የዘውትር ልማዷ አድርጋዋለች እኔና ሰሙም ወይ ጠዋት ወደ ስራ ስንሄድ ወይ ስንመለስ እንጠይቀዋለን መንገዳችን ስለሆነ በቀን አንዴ ሳናየው አንውልም እሱም ደስተኛ ነው አእምሮውም ቢሆን ወደ ራሱ ተመልሷል ኡሚን እማ እያለ መጥራት ጀምሯል እሷም ቢሆን አላሰፈረችውም የእናት ያህል ትንከባከበዋለች። ነገር ግን ለሁላችንም ጥያቄ የሆነብን እና ለመናገር የፈራነው ነገር ቢኖር ማሂር ከሀኪም ቤት ከወጣ በውሀላ እዛ ማዳበርያ ውስጥ ነው ሚመለሰው ወይስ ምንድነው ሚሆነው ዶክተሮቹ ደሞ ቢያንስ መድሀኒቱን እስኪጨርስ እንክብካቤ እንደሚያስፈልገው እና ለአእምሮ ህመሙ ምክንያት ብቸኝነት ሰው ማጣት እና ጭንቀት እንደሆነ ነግረውናል መጀመርያ አካባቢ ማሂርን የገጨው ማሂርን እንደሚወስደው አስበን ነበር እሱ ግን ኡሚን ለለብቻዋ ጠርቶ እዚ ሀገር እንደማይኖር እና ለመዝናናት እንደመጣ ከ15 ቀን በዉሀላ ወደ አሜሪካ እንደሚመለስ ነግሯታል ኡሚም በሰዐቱ እሺ አታስብ እንዳለችው እና የሚያስፈልገውን ነገር ለማድረግ እና በአላህ ስም አደራ እንዳላት ነግራናለች ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ ኡሚ ግራ ተጋብታለች ጓረቤቷቿም ቢሆኑ በሀሳቧ አልተስማሙም እንዴት የማታውቂውን ለዚያውም እብድ ወደ ቤትሽ ታስገቢያለሽ እያሉ ይወተውቷት ጀምረዋል ሰኢድም ወደ ሀገሩ ሄዷል ማሂር ከሀኪም ቤት ሊወጣ3 ቀን ብቻ ቀርቶታል። ማን ያኖረው ይሆን? ማን ጋ ያርፍ ይሆን? መልስ የታጣለት ጥያቄ.......
ክፍል ስምንት ይቀጥላል.....

እብዱ ደራሲ ክፍል ስምንት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
.................
ቀኑ ጁመዐ ነው ማሂር ከሀኪም ቤት የሚወጣበት ቀን በመሆኑ በጠዋት መነሳት አለብን ስራ እንደማንገባ ለአለቃችን ነግረነዋል እሮብ ለት ከኡሚ ጋር አውርተን ማሂር እስኪሻለው እኛ ቤት እንዲሆን ከዛ ቡሀላ ደሞ ሰሙ እኛ ቤት መታ እሱ እዛ ሊኖር ተስማምተናል ሰሙ ዛሬም እኛ ቤት ነው ያለችው ወደ ቤቷ ከሄደች ሳምንት አልፏታል ኡሚ በጠዋት ጉድ ጉድ ማለት ጀምራለች ማሂር ሳይሆን ሙሽራ ሚመጣባት ነበር ምትመስለው መነሳታችንን እንኳን ልብ አላለችም ደና አደርሽ ኡሚ አልኳት ውይ ተነስታቹሀል እንዴ? በሉ ቶሎ ቁርሳቹን ብሉ ና ማሂር ጋ ሂዱለት ደሞ እንደይከፋው አለችኝ እህ ኡሚ ደሞ ገና 8 ሰዐት ነው እኮ ይወጣል የተባለው አይደል ሰሙ?የተነገርኩትን ለማረጋገጥ፡ አንገቷን በአውንታ ነቀነቀችልኝ አይይ ቢሆንም ልጄ የሀኪም ቤት ጣጣ አያልቅም እሱን እስክትጨራርሱ 10 ሰዐትም በመጣቹ ...........................
ሰአቱ 7:30 ሆኗል ማሂር ጋር ከገባን አራት ሰዐት አለፈን ሰሙ እንደገባን አንቺ ማሂር ጋር ቁጭ በይ እኔ መጨረስ ያለብንን ነገር ልጨርስ አለችኝ በሀሳቧ ተስማምቼ እኔ ማሂር ጋር ቁጭ ብያለው ሰሙም አልተመለሰችም ወረፋው በጣም ብዙ ነው ብቆይ እንኳን እንዳታስቡ ማሂርን አዳብሪው የሚል መልእክት ከሰአታት በፊት ስላከችልኝ አልተጨነኩም ሰኢድ ወጪውን ሙሉ ልኮልን ስለነበር ብር አልተቸገረንም ከገባው ጀምሮ ከማሂር ጋር ብዙም አላወራንም። ሊወጣ 30 ደቂቃ ቀርቶታል ሰሙ እስካሁን አልመጣችም ኡሚ እንዳለችው እስከ 10 መቆየታችን በቃ መቀመጡ በጣም አሰልችቶኛል ስልኬ ቻርጅ ስለዘጋ ሰሙን ማግኘት አልችልም የት ይሆን ያለችው ወጥቼ አልፈልጋት ነገር የሀኪም ቤቱ መግቢያና መውጫ ብዙ ነዉ ደሞ እሷ ስትመጣ እኔ ስሄድ ብንሸዋወድስ? ይህን እያብሰለሰልኩ
ሲሁ የሚል ድምፅ ከሀሳቤ አባነነኝ ማሂር ነበር የጠራኝ ወዬ አልኩት አጠራሩ አስደንግጦኛል ኡሚ እናንተ ቤት እንደማርፍ ነግራኛለች ግን እቤት ከመግባታችን በፊት ወደራሴ ቤት መሄድ እፈልጋለው እቤቴ?አልኩት በመደናገጥ አይነት ማሂር አጠያየቄ ስለገባው ፈገግ ብሎ እሺ ማዳበሪያዬ ጋር ከመልሱ ይልክ ፈገግታው አስደንግጦኛል ሌላ ቀን አይደርስም ? አሁን ይሁንልኝ በአላህ አጠያየቁ የህፃን ልጅ ነበር የሚመስለው እሺ እንደፈለክ ግን አንተ ከመኪና መውረድ ስለማትችል እኔ ምትፈልገውን ትነግረኛለህ እኔ አመጣልሀለው አልኩት፤በሀሳቤ ስማማት አልፈለገም ግን ደሞ ከመኪና ለመውረድ የግድ ሰው እንደሚያስፈልገው ያውቃል አይሆንም ቢል እኛን ማስቸገር ነው እሺ በቃ ወረቀቶች ናቸው ታመጪልኛለሽ ግን ሲሁ ልመንሽ? አለኝ ጥያቄው ያስደነግጣል እንደደበረው ስለገባኝ እኔ ምለው የሀገር ጉዳይ ነው እንዴ ብዬ ቀለድኩበት ፈገግ ብሎ ዝም አለ የማሂር ዝምታ ያስፈራል።! መጣው ሰሙን ልፈልጋት ብዬ ብድግ ብዬ ወጣው አወጣጤ እንዳልኩት ሰሙን ለመፈለግ ሳይሆን የማሂር ዝምታ አስፈርቶኝ ነው ወጥቼ ኮሪደሩ ላይ ቆምኩኝ ሳይታወቀኝ በሀሳብ ጭልጥ ብያለው የማሂር ፈገግታ ሲናገር እርጋታው የዝምታው ማስፈራት እና ማዳበሪያ ውስጥ ስላለው ወረቀት...... ሲሁ የሚለው የሰሙ ድምፅ ከሀሳቤ አባነነኝ እህ አልኳት የት ሄድሽ ደሞ ምነው ማሂርን ጥለሽው ወጣሽ እ ልፈልግሽ ወጥቼ ኮ ሰሙ የሆነ ነገር እንደሆንኩ ገብቷታል አትዋሺ ሲሁ ማሂር ምን ብሎሽ ነው አለችኝ ስለነገረኝ ነገር ነገርኳት እና ምን ችግር አለው በራይድ ስለሆነ የምንሄደው እዛው ጋር ስንደርስ እናወረደዋለን አለችኝ እሺ በቃ እንዳልሽ ጨረሽ አሁን አ እንሂድ አልኳት አይ ቆይ ትንሽ ይቀረኛል ሰኢድ ደውሎ ማሂርን አገናኚኜ ስላለኝ ነው የመጣሁት ብላኝ ወደ ውስጥ ገባች ተከትያት ገባው ሰሙ ማሂርን ከሰኢድ ጋር አገናኝታቸው በቃ አውርተው ሲጨርሱ ስልኬን ተጠቀሚበት እንዳይደብርሽ እኔ ልጨራርስ ትንሽ ነው የቀረኝ ብላኝ ሄደች ማሂር ከሰኢድ ጋር ለ30 ደቂቃ አወራ እንደዚ ለረጅም ደቂቃ ሲያወራ ለመጀመርያ ጊዜ አየሁት ንግግራቸውን በተመስጦ ነበር ስሰማ የነበረው አይደለም 30 ደቂቃ 1 ደቂቃ ያወራ አይመስልም እርግት ብሎ ነበር ሚያወራው እሺ ዋአለይክሰላም ሰያ እናወራለን በቃ ብሎ ስልኩን ዘግቶ ለኔ አቀበለኝ ተቀብዬው ሰሙ ስልክ ላይ ባፈጥም ስለ ማሂር ግን ማሰብ አላቆምኩም ነበር ላወራው ብፈልግም ግን ምን እንደማወራው ግራ ገብቶኛል ሰሙ ስላመጣችው ሀሳብ ልነግረው ፈለሰጊዪለው ግን ደሞ እንዳትነግሪው ቦታው ላይ ወስደን ነው ምናሳየው ብላ አስጠንቅቃኛለች እሱም አያወራም እኔም አላወራም በዝምታ ተውጠን ሁለታችንም በሀሳብ ነጉደናል ሲሁ ግን ልመንሽ? የሚለው የማሂር ጥያቄ ምንም ከጭንቅላቴ ሊወጣ አልቻለም ፤ ሰሙ 12:30 ሲሆን የማሂርን የሀኪም ቤት ጉዳይ ጨራርሳ መጣች ራይድ ደውለን ጠርተን ማሂርን በዊልቸር እየገፋው ሰሙ እቃዎቹን ሰብስባ ከሀኪም ቤት ወጣን የራይዱን ሹፌር ሰሙ ቀድማ ቦታውን ነግራው ስለነበር የማሂር ሸራ ጋር አቆመን ማሂር እየሆነ ባለው ነገር ግራ ተጋብቷል እሱ የገመተው ወደቤት እየሄድን እንደነበረ ነው ይሀው እንውረድ እና ምትፈልገውን ነገር ውሰድ አለችው ሰሙ ፊቱ በአንዴ በደስታ ተሞላ በሹፌሩ እገዛ ማሂርን ከመኪና አውርደን ዊልቸሩ ላይ አስቀመጥነው ዊልቸሩን እየገፋ ወደናፈቀችው ቤቱ ማዳበርያው ገባ የሚፈልገው ነገር ካለ እንድታግዢው ተከተይው አለችኝ እኔ ግን ሲሁ ልመንሽ ያለኝ ነገር ስላለ አይ ሰሙ አጋዥ ቢፈልግ ይጠራን ነበር እዚው እንጠብቀው አልኳት መኪና ውስጥ ተቀምጠን 30 ደቂቃ ሆኖናል ማሂር እስካሁን አልመጣም ልቤ በጣም ተጨንቆል ከሱ ሌላ ምንም ማሰብ አልቻልኩም አረ ይሄ ልጅ ቆየ አለ ሹፌሩ መልስ አልሰጠሁትም ተነሺ እስቲ ሲሁ እይው በአላህ አለችኝ ሰሙ እግሯ ላይ ያስቀመጠችው ነገር ስለነበረ ለመነሳት አልተመቻትም እሺ ቆይ ትንሽ 10 ደቂቃ እንየው እና እሄዳለው አልኳት ሰሙ ማሂር ልመንሽ ወይ እንዳለኝ ስላልነገርኳት እንጠብቀው ስላት ብስጭት አለች መልስ አልሰጠችኝም 10 ደቂቃው አልፎ 15 ደቂቃ ጠበቅነው እሺ አሁንስ አለች ሰሙ አሁን ግን ከሷ ይበልጥ ማሂር ለምን ቆየ የሚለው ነገር እኔን አሳስቦኛል 10 ደቂቃ እንዳለፈው ባውቅም ሂጂ እስኪሉኝ ነበር የጠበኩት እሺ መጣው በቃ ልየው ብዬ ከመኪናው ወረድኩ የምን መጣው ነው ይዘሽው ነይ እንጂ ኡሚኮ እየጠበቀችን ነው ነው አለችኝ ትዛዝ መሆኑ ነው እሺ እሺ አመጣዋለው ብዬ ወደ ማሂር ማዳበርያ ሄድኩ።የማሂር ማዳበርያ ጋር ስደርስ ያገኘሁት ግን ያልጠበኩት ነው ..........
ክፍል ዘጠኝ ይቀጥላል ........

👍4
እብዱ ደራሲ ክፍል ዘጠኝ
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
..............
የማሂር ቤት ፈራርሳለች ቦታው በብዙ ሳንቲሞች ተሞልቷል የወዳዳደቁ ብዙ ወረቀቶች እና ጥቂት ልብሶች ይታዩኛል ማሂር አልኩት ከውሀላው ሆኜ ከዊልቸሩ ወርዶ መሬት ላይ ዝርግፍ ብሎ ተቀምጧል እጁ የደረሰበትን ወረቀቶች እና ሳንቲሞች ይሰበስባል ስጠራው የሰማኝ አይመስለኝም ወደእሱ በጣም ቀረብኩኝ አይኖቹ እንባ ያጎርፋሉ ከወዳደቁት ነገሮች ውስጥ የሆነ ነገር እንደሚፈልግ ስለገባኝ ምንድነው እኔ ልፈልግልህ አልኩት ተስፋዬን ማንነቴን ፍቅሬን አለሜን ፈልጊልኝ? አለኝ መልስ ሳልሰጠው ሄጄ ተጠመጠምኩበት ማሂር አሳዘነኝ አብሬው አለቀስኩ ሁሌም ከአጠገቡ እንደማልለይ እጁን ይዤ ለራሴም ለሱም ቃል ገባሁለት። ልመንሽ ሲሁ?አለኝ ከየት የመጣ ድፍረት እንደሆነ ባላውቅም ጉንጩን ስሜ እመነኝ ማሂ ከገባህበት የተስፋ መቁረጥ ስሜት ከብቸኝነት እኔ አወጣሀለው ድጋሚ ተጠመጠምኩበት እሺ ያጣሁትን ፍቅር ስ ትመለሽልኛለሽ? መልስ ልሰጠው ቀና ስል ሰሙ መጣች ሲሁ ፣ማሂር ምንድነውየሆናቹት በአላህ? ምን ተፈጥሮ ነው? ለምንድነው ማሂር መሬት ላይ የተዘረገፈው? ሰሙ የኛን መልስ ሳትፈልግ ቆይ ሹፌሩን ልጥራው ብላ ወደ መኪናው በረረች ማሂርን ቀና ብዬ የስስት አየሁት አመሰግናለው አለኝ ከወደቁት ነገሮች ውስጥ የቻልነው ያህል ወረቀቶችን እና ልብሶችን ሰበሰብን፡ ሰሙ ሹፌሩን ይዛው መጣች ና ማሂርን ከተቀመጠበት አንስተው ዊልቸሩ ላይ አድርገው እየገፉ መኪና ውስጥ አስገቡት እኔም የማሂርን ንብረቶች ይዤ ተከተልኳቸው ማሂር ተቀምጦበት የነበረበት ቦታ ላይ የማሂርን ቡኒ ተስቢህ አገኘውሀት አሁን ልሰጠው ስላልፈለኩ አንገቴ ውስጥ አስገብቼ በሂጃቤ ሸፈንኩት ሰሙ መኪና ውስጥ እያለን ስለተፈጠረው ነገር ሁሉ እየጠየቀችን ነበር ማሂር ስለተፈጠረው ነገር እያስረዳት መንገዳችንን ቀጥለናል እኔ ግን ምንም መልስ አልሰጠውኋትም እኔ በሀሳብ በዚች ቅፅበት ውስጥ በኔና ማሂር መሀከል ስለተፈጠረው ነገር እያሰብኩ ነበር ምን ሆኜ ነው ግን ? በብዙ ጥያቄዎች እንደተሞላው እቤት ደረስን ኡሚ የሰፈሩን ሰው ሰብስባ ማሂርን በእልልታ እንደ ሙሽራ ተቀበለችው።
......................................................................
ማሂር ተቀይሯል አለባበሱ መልኩ ሁሉም ነገሩ በተቦጫጨቀ ልብስ የማውቀው ማሂር በጠቆረ ፊቱ ማውቀው ማሂር በሀዘኑ ሲስቅ በደስታው ሲያለቅስ ማውቀው ማሂር ዛሬ ፍፁም ሌላ ሰው ሆኗል በምድር ላይ ከሱ ሌላ ቆንጆ፤ ከሱ ሌላ አይንአፋር፤ ከሱ ሌላ ተናጋሪ፤ ከሱ ሌላ ተጫዋች፤ ከሱ ሌላ ቁምነገረኛ፤ከሱ ሌላ ወንድ ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ ተቀይሯል! ሀሳቤ ሁላ ተቆጣጥሮታል የሚናገራቸው ቃላቶች ከባድ ሆነው ለመረዳት የሚቀሉ ቀልዶቹ አለ የተባለን ቀልደኛን የሚያስንቁ ናቸው ቁምነገሩ ግን ይከብዳል በመሀል ጣል የሚያደርጋቸው ንግግሮች ከአእምሮ በላይ ናቸው ።
አንቺ ልጅ ምን ሆነሻል ሰሞኑን ልክ አደለሽም እኮ! ታውቆሻል አ? ደሞ ከየት ያመጣሽው የቀን እንቅልፍ ነው ቆይ? ወይስ ከዚ ክፍል እንዳትወጪ ብሎ ያስጠነቀቀሽ ሰው አለ? አንቺ ሲሀም ተነሺ ኮ ነው ምልሽ!የኡሚ ድምፅ ነበር እንቅልፍ ባይወስደኝም ቀን ቀንም ቢሆን ከክፍሌ መውጣት ከተውኩ ሳምንት ሊሆነኝ ነው ስራም ቢሆን ገብቼ አላውቅም ኡሚን ላግዛት ነው በሚል ሰበብ ለሳምንት አስፈቅጃለው ሰሙንም ቢሆን አለቃችን አስጠልቶኛል ስራውን ለቅቄ ከኡሚ ጋር ከምጣላ እረፍት ልውሰድና እመለሳለው ለኡሚ ግን እንዳትነግሪያት ብዬ አስጠንቅቄያታለው ሰሙን ካወኳት ጀምሮ አንድም ቀን ዋሽቻትም ሆነ አታልያት አላውቅም ነበር አሁን ግን ማሂር አሸነፈኝ ብዙ ጊዜ ከስራ ስትመጣ ሁሉንም ነገር ልነግራት እወስን እና መልሼ እፈራለው እሷም ምታወራኝ ነገር እንዳለ ሁሌ ትነግረኛለች እኔ ግን ስለእኔ እና ስለማሂር ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ በሰበብ እያደረኩ ቀጠሮዋችንን ሰርዛለው ደግሞ እሷም ብትሆን እንደ በፊት ብዙ እቤት መምጣት አቁማለች እኔም አልጠየኮትም ኡሚ ምንሆና ነው ተጣልታቹ ነው ብላ ስትጠይቀኝ አደለም ሰሞኑን ብቻዋን ስለሆነች ስራ ስለሚበዛባት እቤት አምጥታ ነው ምጨርሰው እዚ ደሞ አይመችም ብያታለው ባይዋጥላትም ብቻ ደና ትሁን ግድ የለም ብላ ተቀብላኛለች ኡሚ ስራ ማልገባው ባለፈው ሳምንት ስራ ስለበዛብን አለቃችን በተራ በተራ እረፉ እንዳለን ነው ምታውቀው። እሺ ኡሚ እነሳለው ትንሽ እራሴን ስላመመኝ ነው ኮ! ስንት ቀንሽ ነው እራሴን ስቲ?ነይ ተነሺ በይ ሀኪም ቤት እንሂድ! አለችኝ አሁን ይሻለኛል ትንሽ ተኝቼ ልነሳ ብያት በብርድልሴ ተጠቀለልኩ፤ እሺ ሌላው ቢቀር ተነሺና ይህን ልጅ አጫውቺው አረ ተይ ምን ይልሻል? እሺ ትንሽ ልተኛ እና እነሳለው አልኩ እኮ ደሞ አንቺ አለሽ አይደል ብያት እንቅልፍ እንዳሰከረው ሰው ብስጭጭት አልኩ ኡሚ ከኔጋ መጨቃጨቅ ከሰለቻት ቆይቷል አንቺ እኮ እኔን አልሰማም ካልሽ ቆይተሻል! ብላ በብስጭት በሩን ወርውራው ሄደች። የኡሚ መበሳጨት ከምንም ሳልቆጥር በሃሳብ ወደማሂር ተመለስኩ ኡሚ እንቅልፍ እንዳበዛው ታስብ እንጂ እኔ ግን ማሂር ከመጣበት ምሽት ጀምሮ የሰላም እንቅልፍ አልተኛሁም ማሂር የመጣ ቀን ማታ ተስቢሁን ልሰጠው ከመኝታ ቤት ወደሱ መኝታ ቤት ሄጄ ስለ ተፈጠረው ማሂር ስላለኝ ነገር ስለነገረኝ ታሪክ እያሰብኩ አይደለም እንቅልፍ ምግብም ኡሚ አንዳትቆጣ ለነገሩ ነው ምቀማምሰው ........
ክፍል አስር ይቀጥላል ......#share

እብዱ ደራሲ ክፍል አስር
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
.....................
ቀኔን ምሽት ያደረገው፤ምሽቴን ከእንቅልፍ ያራቀው፤ስራ እንድጠላ ያደረገኝ፤ ስለራሴ ፣ስለ ቤተሰቦቼ ማሰብ ትቼ ስለ አንድ ሰው ማሰብ እንድጀምር፤በእሱ ውስጥ እንድኖር፤ በእሱ ውስጥ እንድሞት፤ ስለሱ አስቤ እንዳለቅስ፤እሱን አስቤ እንዳለቅስ፤ እሱ ሲኖር የምኖር፤ እሱ ሲሞት የምሞት፤ ያህል እንዲሰማኝ ያደረገው እሱ ነው። "ማሂር" አባቴን በልጅነቴ ስለሆነ ያጣሁት ስለወንድ ልጅ ፍቅር በየትም በኩል መረዳት ለኔ ከባድ ነበር አባቴም፣ ወንድሜም፣ እናቴም፣ እህቴም፣ ዘመዴም ኡሚ ነበረች። ከጊዜያት ቡሀላ ግን ሰሙ የእህትነቱን ቦታ ተካችልኝ። አሁን ግን ስለወንድ ልጅ ፍቅር ማሰብ ጀምሬ እነሱን ረስቻቸዋለሁ
ማሂር ሁለመናዬን ከተቆጣጠረው እንደ ቀልድ ሳምንት አለፈው። ከሀኪምቤት የመጣ ቀን ማታ ሰሙ ወደቤት ልሂድ ብላ ወደቤቷ ሄደች ኡሚም ሰሞኑን እዚ ስለነበረች ልታስገድዳት አልፈለገችም ሸኝቻት ስመለስ ኡሚ "ሲሁ ትንሿን ክፍል ለማሂር አንጥፌለታለው በቃ ይረፍ አስገቢው ወደ ክፍሉ" አለችኝ እና ዊልቸሩን እየገፋው ወደ ክፍሉ አደረስኩት በሩ ላይ ስንደርስ "ደና እደሪ የኔዋ ሲሁ አመሰግናለው" ብሎኝ ከኔ ምንም መልስ ሳይጠብቅ ዊልቸሩን እየገፋ ወደክፍሉ ገባ። ውስጤ በድንጋጤም በደስታም ተሞላ "የኔዋ ሲሁ" የምትለዋ የማሂር ንግግር ውስጤን ሰርስራ ገብታለች ወደክፍሌ ገብቼ ማሂርን አለማሰብ አልቻልኩም አብሬው መቀመጥ ከሱ ጋር ማውራት ፈለኩኝ ግን እኮ መሽቷል ደሞ እንዴት ክፍሉ እገባለው ኡሚ ብታየኝ ምን ትለኛለች ምንድነው ምታስበው ከራሴጋር ሙግት ገጠምኩኝ ደሞስ ሄጄ ምን ፈልገሽ መጣሽ ቢለኝስ ምን እለዋለው እሱ ጋር ለመሄድ ምክንያቶችን ብፈልግም ሳይሳካልኝ ስለቀረ ለመተኛት ወሰኜ ቢጃማዬን ለመቀየር ተነሳሁ ሂጃቤን ሳወልቅ አንገቴ ላይ አድርጌው የነበረው የማሂር ተስቢህ ትዝ አለኝ እናቱ ቆይታበት የመጣችለት ህፃን ልጅ ያህል ነበር የፈነደኩት ተስቢሁን ከአኔገቴ ላይ አወለኩት እና ሂጃቤን አስተካክዬ ለበስኩት ሌላ ቀን እንደነገሩ ጣል አድርጌው ምወጣው ሂጃብ ዛሬ አደራረጉ ሁላ ጠፋብኝ መስታወት አጠገብ ቆሜ እራሴን ስመለከተው በጣም የተዝረከረኩ አስጠሊታ ሴት የሆንኩ መሰለኝ ልብሴን መቀየር ፈለኩኝ ባሏ ፊት ለመጀመርያ ጊዜ የምትቀርብ ሴት ትመስል መሽሞንሞን መቀባባት ፈለኩኝ ግን እሺ ከዛስ? ማሂር ተኝቶ ቢሆንስ ተተስቢሁን ተቀብሎኝ ዞር ብሎ ባያየኝስ? ግንኮ የኔዋ ብሎኛል! ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ ማሂር ቀን ባየኝ ልብስ እንዲያየኝ አልፈለኩም ብቀያይር ደሞ ለሱ ብዬ እንደሆነ ያውቅብኛል ምክንያቱም መሽቷል አ በዚ ሰዐት የትም እንደማልሄድ ያውቃል እንደዚማ ፊት አልሰጠውም ቀለል ያለ ልብስ ፍለጋ የቁምሳጥኑን ከፈትኩት ከተንጠለጠሉት ልብሶች መሀከል ኡሚ ሰሞኑን የገዛችልኝን ጁመዐ ለብሰዋለው ብዬ ያስቀመጥኩትን ሺቲ አየሁት ኡሚ እና ሰሙ ለብሼ አሳይቼያቸው በጣም እንደሚያምርብኝ ነግረውኛል ስለዚህ ይህን ልልበስ ምክንያቱም ማሂር የማታ ስለሚመስለው አይጠራራጠርም ብዬ ከልብስ ውስጥ ስቤ አወጣሁት ልብሴን ቀያይሬ ቀለል ያለ ዝነጣ ዘንጬ ኡሚ እንዳታየኝ እያልኩ ዱዐ እያደረኩ ከክፍሌ ወጣው ኮቴዬን አጥፍቼ ስወጣ ሳሎኑ ጭልምልም ብሏል የኔና የማሂር ክፍል ብዙም አይራራቅም የኡሚ ግን ወደኩሽናው መግቢያ ነው ወደማሂር ክፍል ከመሄዴ በፊት ኡሚ እንደተኛች ቼክ ላደርግ ወደኡሚ ክፍል ተራመድኩ ብትወጣ እንኳን ሚጠጣ ውሀ ፈልጌ ነው እላታለው ሺቲዬን እንዳታየው ረዘም ያለ የመኝታ ጋወን ደርቤበታለው ኡሚ እንደተኛች ለማጣራት የኩሽናውን በር ከፈትኩት ኡሚ ሌላ ቀን አደለም የኩሽናው በር ተከፍቶ ኮቴ ስትሰማ ነበር ብድግ ምትለው ዛሬ ግን ቀኑን ሙሉ ሽርጉድ እያለች ስለዋለች አልሰማችኝም የኡሚን መተኛት አረጋግጬ ወደ ማሂር ክፍል አመራው የማሂር ክፍል ደርሼ ማንኳኳት ብፈልግም ምን አልባት ኡሚ ልትሰማ ትችላለች ብዬ ስላሰብኩት የበሩን እጀታ ዝቅ አድርጌ ወደ ገባው ወደክፍሉ ስገባ ማሂር ወረቀቶቹን እያገላበጠ ነበር እና በድንጋጤ ነበር ወደበሩ የዞረው ድንጋጤውን ሳይ አንኳክቼ አለመግባቴ አሳፈረኝ" ውይ ሲሁ አንቺ ነሽ እንዴ ኡሚ መስላኝ ወላሂ እንዴት እንደደነገጥኩ" " ይቅርታ ማሂ እ... ተስቢህን ኮ ቅድም አንስቼ አንገቴ ላይ አድርጌው ሳልሰጥህ ረስቼው..... ተንተባተብኩ "ችግር የለውም የኔዋ ደሞኮ ነገ እንሂድ ልልሽ ነበር ተስቢሄን ልንፈልገው ወላሂ አመሰግናለው ሲሁዬ ብሎ ሊቀበለኝ እጁን ዘረጋ ተስቢሁን መስጠት አልፈለኩም ሁሌም በዚ ተስቢህ ምክንያት እያደረኩ ወደሱ መሄድ እፈልጋለው ግን በቃ ግዴታ መስጠት ስለነበረብኝ ይሀው ብዬ የዘረጋው እጁ ላይ አስቀመጥኩለት ተስቢሁን ሳመው እና በረጅሙ ተነፈሶ ወደኔ እየተመለከተ ለኔ ይሄ ተስቢህ ብዙ ትርጉም አለው እሺ ሲሁ ይሄ ተስቢህ ለኔ አደራ ነው" ስለተስቢሁ ማወቅ ፈለኩኝ ንገረኝ ማለት ግን አልደፈርኩም ማሂር ተስቢሁን አስቀምጦ አልጋው ላይ ወደበተነው ወረቀት አቀረቀረ። ነይ ተቀመጪ እንዲለኝ ውስጤ ቢፈልግም ከዚ በላይ መቆየቱ ለኔም ጥሩ አደለም ብዬ ስላሰብኩ ደና እደር በቃ ልሂድ "ደና እደሪ የኔ ሲሁ እንቅልፍሽ ካልመጣ ግን ብትቀመጪ ደስ ይለኛል ትንሸ ማወራሽ ነገር አለኝ" አለኝ። ያለምንም መግደርደር ነበር እሺ ያልኩት አጠገቡ እንድቀመጥ አልጋውን አጠገብ ያለውን ወረቀቶች ሰበሰበልኝ እኔግን አጠገቡ መቀመጥ አልፈለኩም ከክፍሉ ጠርዝ ላይ የነበረውን ወንበር ሳብ አድርጌ ፊትለፊቱ ተቀመጥኩ የበለጠ እንዳየው አይን አይኑን እያየው እንዳወራው ማሂር ንግግሩን ጀመረ .....
ክፍል አስራአንድ ይቀጥላል

እብዱ ደራሲ ክፍል አስራአንድ
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
ማሂር ንግግሩን ጀምሯል እኔ አይን አይኑን እያየው በሙሉ ልቤ ላዳምጠው ተዘጋጅቻለው። "ሲሁዬ እስቲ በህይወትሽ ምን አተሽ ምን ጎሎሽ ያውቃል"? ንግግሩን በጥያቄ ነበር የጀመረው ደንገጥ ብዬ "እ ምንም አልሃምዱሊላህ ማሂሬ ሁሉ ነገሬን እናቴ ሞልታልኛለች ስለዚህ ምንም አልጎደለበበኝ" አልኩት ሳወራ አይን አይኔን እያየኝ ስለነበረ እየተንተባተብኩ ነው የመለስኩለት "ታድለሽ የኔዋ ስለዚህ አንቺ ኮ ሁሉም አለሽ በቃ"አለኝ አቀርቅሮ፤ እያለቀሰ እንደሆነ ያወኩት አጠገቡ ባለው ወረቀት ላይ እንባው ጠብ ሲል ነው ደነገጥኩኝ ምን ልበለው? ግራ አጋባኝ! አጠገቡ ሄጄ ቁጭ ብዬ "ማሂሬ ስለአንተ ምንም ነገር አላውቅም ግን አንድ ነገር ልንገርህ ከአሁን ቡሀላ ምንም አይነት የብቸኝነት ስሜት እንዲሰማህ አልፈልግም ሁሌም ቢሆን እኔ አለው እኔ ያንተ ነኝ የግልህ ነኝ" የሱ ልሆን ሳጠይቀኝ ተስማምቻለው ምን ሆኜ ነው ግን? " ማሂርን አባብላለው ብዬ የባሰ ሆድ አስባስኩት መሰለኝ ሳብ አድርጎ አቅፎኝ እንደ ህፃን ልጅ ተንሰቅስቆ አለቀሰ፤ አብሬው አለቀስኩ ማባበል፣ አይዞህ ማለት ስችል እንባው አስነባኝ፤ህመሙ አሳመመኝ፤ ሳይነግረኝ ቁስሉ፣ብቸኝነቱ፣ ስብራቱ ገባኝ። የኔው ማሂር አሳዘነኝ፤ እኔ ከሱ ባስኩኝ ትከሻው ላይ ተደፍቼ ተንሰቀሰኩኝ። ማሂር ከትከሻው ላይ ቀና አደረገኝ "የኔዋ ሲሁ በቃሽ አታልቅሺ ታምሜ አሳመምኩሽ አደል? አለኝ መልስ አልሰጠሁትም እስከዛሬ ስላላወኩት ተፀፅቻለው፤ ካለሱ የኖርኩባት እድሜዬ በከንቱ ያለፈ መሰለኝ፤እስከዛሬ በሰፈር ስመላለስ አንድ ቀን እንኳን ዞር ብዬ ያላየሁት ሰውዬ ዛሬ አለሜ ሆኖ ታየኝ ፤በጣም በጥቂት ቀናት ውስጥ ማሂርን ያለምንም ማንገራገር ልቤን ሰጥቼዋለው እሱ ምን እንደሚያስብ እንኳን ምንም አላውቅም።" ሱሁ" ሲለኝ ከሀሳቤ ባነንኩ የት ሄደሽ የኔዋ ምንድነው ምታስቢው "ምንም ምንም" አልኩት "ስሚኝ የኔዋ አንቺ ፣ሰሙ ፣ኡሚ እኔን እንደ አዲስ ህፃን ነው የፈጠራቹኝ ፤ከዘቀጠ ማንነቴ፤ ከብቸኝነቴ ፣ከስብራቴ ነው የጠገናቹኝ፤ግን ሲሁ ፈራለው፤ እንዳላጣቹ ፈራለው፤ ሁሉም ሰው ኮ የኔ ነህ፤ የትም አንሄድብህም፤ እንወድሀለን እያሉ ነወ ጥለውኝ የሄዱት" እንባው እየፈሰሰ ነው። "እናቴ፣አባቴ፣ ሀዩ፤ ሁሉም ሁሉም እኮ ይወዱኝ እንደነበር ነው የሚነግሩኝ አሁን ግን የሉም እና እናንተንም እንዳላጣቹ ፈራለው" በእንባ የታጀበ ንግግር " "አይዞህ የኔ ማሂ አታጣንም አንተ ጥለከን ካልሄድክ እኛ የትም አንሄድም ሁሌም ከጎንህ ነን አልኩት" ፊቱ ላይ ያለገደብ የሚወርደውን እንባ እየዳበስኩ ።ማሂር አሁን ተረጋግቷል ያለገደብ የሚወሩዱ የነበሩ እንባዎቹ ወደከረጢታቸው ተመልሰዋል ፤ከሰዓታት በፊት ሲያለቅስ የነበረው ማሂር አሁን እየሳቀ ነው፤ ሳቁ ህመምን ብቸኝነትን ያስረሳል ፤ሁሌም ሲስቅ ማየትን ተመኘው። ከአጠገቡ የበታተናቸውን ወረቀቶች እየሰበሰበ "በነገራችን ላይ የግጥም አፍቃሪ ነኝ እናም እሞካክራለው አንቺስ የኔዋ?" ቀና ብሎ አየኝ ስለግጥም አንድቀን እንኳን አስቤ ማላውቀው እኔ "አረ ግጥም" አልኩት በመገረም አይነት "ምነው አይመችሽም እንዴ?" " አረ ሳይሆን ቦታ ሰጥቼ አንብቤም አዳሜጬም አላውቅም ለዛ ነው" "እሺ ቆይማ እንደውም አንድ ለምን አላነብልሽም ብሎ የሰበሰበውኝ ወረቀት ድጋሚ በታተነው
እኔ ግን ቆይ ማነኝ?
ለመኖር ያልታደልኩ
ለሞት ያልተመረጥኩ
አለ አይሉኝ ነገር
ወይ አይቀብሩኝ ችግር
ሰው መሆኔን ማላምን ከሰው የተገኘው
ማን እንደሆነ ማላውቅ እኔን እዚህ ያስገኘው
አርግዘው ወለዱኝ ወይስ ከላይ ጣለኝ?
ከመንገድ ተገኘው ወይስ ተናፈጡኝ?
እኔ ግን ቆይ ማነኝ?
አለሁ ባይ የሌለኝ ተርቤ ስጠማ
ያፈቀረውን ሰው ልቤ የተቀማ
እኔ ማን ብሆን ነው?
ከሰው ተለይቼ ስቃዬ የበረታው?
በየትኛው ጥፋቴ እንደዚ ምቀጣው?
አምላክ ምን በድየው?
በሰፊው ሜዳ ላይ ብቻዬን የተወኝ?
ከሰው ተፈጥሬ ብቻዬን ያስቀረኝ?.......
በማሂር ግጥም ውስጥ ታሪኩ ቁልጭ ብሎ ይታያል ለኔ ግን ጎልቶ የታየኝ" ያፈቀረውን ሰው ልቤ የተቀማ" የምትለው ነበረች ማሂር ልቡ ውስጥ አንድ ሴት እንዳለች ልቤ ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ ሆኗል ያበደውም በሷ እንደሆነ ልቤን አሳምኜዋለው። እንባ እና እልህ ሲተናነቀኝ ይታወቀኛል፤ " እንዴ ሲሁ ለግጥሜ አስተያየት አሰጪም እንዴ?" "ያው ግጥም ብዙም ስለማላውቅ እኮ ምን ማለት እንዳለብኝ ስላላወኩ ነው" ብዬ አስቀየስኩት "እሺ የኔዋ ችግር የለውም በቃ እና ስለእኔ ትንሽም ቢሆን አወቅሽ አደል በግጥሜ ውስጥ" አለኝ "አዎ አዎ" አውቄያለው ማፈቅራት ሴት አለች እወቂው እያለኝ ነበር የመሰለኝ። ከዚ በላይ መቆየት አልፈለኩም "በቃ ደናእደር ማሂር እንቅልፌ እየመጣ ነው ጠዋት ስራ ስለምገባ ልተኛ" ብየው መልሱን ሳልጠብቅ ድንገት ብድግ አልኩኝ ማሂር በአካዃኔ ግራ ተጋብቷል "እሺ ደና እደሪ የኔዋ" ሲለኝ የባሰ አናደደኝ ጥየው የክፍሉን በር ወርውሬ በፍጥነት ወደክፍሌ ሮጥኩ አልጋዬ ላይ ተዘርሬ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ ማሂርን ያጣሁት መሰለኝ፤ ያንቺ አደለሁም ያለኝ መሰለኝ፤ አለምን ጠላውሀት፤ አግኝቶ ማጣትን አወኩ፤ አመመኝ፣ ተሰበርኩ............
ይሄ ነበር የዛን ቀኑ ክስተት ከስራ አስቀርቶ ምግብ አስትቶ ክፍሌ ውስጥ የቆለፈኝ ስለእናቴ ግድ እንዳይሰጠኝ ያደረገኝን ያቺን ምሽት ጠላውሀት እራሴን ያጣሁበት የተረገመች ምሽት.............
ክፍል 12 ይቀጥላል .......

እብዱ ደራሲ ክፍል አስራሁለት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
ከክፍሌ ለምግብ ብቻ መውጣት ከጀመርኩ ዛሬ ሳምንት ሆኖኛል ኡሚ ምንም እንኳን በሁኔታዬ ብትናደድም በጣም ተጨንቃለች እራሴን ከዚ ሙድ ለማውጣት በጣም ታግያለው ግን አልቻልኩም! ሰሙ እኛ ቤት መምጣት በጣም ቀንሳለች፤ኡሚ ደግሞ የኔን እንደዚ መሆን ከሰሙ ጋር አያይዛዋለች ፤ተጣልተን የደበቅናት ነው የመሰላት። እኔንም ሰሙንም አናግራን በመሀላችን ምንም የተፈጠረ ነገር እንደሌለ ብንነግራትም የኔ ፀባይ መለወጥ፤ የሰሙ እቤት አለመምጣት ተጨምሮ አላመነችንም። ማሂርም ቢሆን በሁኔታዬ ግራ ተጋብቷል፤ አናግሬው አላውቅም፤ በኡሚ ፊት ብቻ ዝም ብዬ ለመቀላቀል ያህል አወራዋለው፤ ምግብ ልበላ ወደሳሎን ስሄድ አይንአይኔን እንደሚያየኝ ባውቅም ቀና ብዬ የማየት ድፍረቱን አጥቻለው፤ ሊያናግረኝ ቢፈልግም በኡሚ ፊት ምንም ማለት እንዳለበት ግራ ገብቶት ዝምታን መርጧል ኡሚ ደሞ ማሂርን የመድሀኒት ሰዐት ላለማሳለፍ ለደቂቃ ከቤት አትወጣም፤ በጣም ነው ምትንከባከበው፤ሁለቱም በኔ ባህሪ መለወጥ ግራ ተጋብተዋል። እኔም ከዚ ሙድ ለመውጣት እና ከዚ በላይ ኡሚን ማስጨነቁ እየረበሸኝ ስለሆነ ለሰሙ ሁሉንም ነገር ልነግራት ቆርጫለው። እሷም ልታወራኝ ትፈልጋለች ስለዚህ ፈልግሻለው ሳይሆን "ልታወሪኝ የፈለግሽው ምንድነው? ነገ ተገናኝተን እናውራ"የሚል መልዕክት ለሰሙ ልኬላት ለቅዳሜ ተቀጣጥረናል።
..................................
ዛሬ ቀኑ ቅዳሜ ነው አምስት ሰዐት ላይ ከሰሙ ጋር ቀጠሮ ስለነበረን ቀደም ብዬ ነው የተነሳሁት፤ ነፃ ሆነን እንድናወራ እሷ ቤት ነው የተቀጣጠርነው፤ በጠዋቱ ሽርጉድ እያልኩ ነው፤ ኡሚ የዛሬ ሁኔታዬ ገርሞት ቆማ እያየችኝ ነው እኔ ለሰሙ ምን ብዬ ነው ምነግራት? በሚል ሀሳብ ተወጥሬ ኡሚን አላየውሀትም ነበር "ደና አደርሽ ሲሁ? አልሃምዱሊላህ ዛሬ ደና ነሽ ፊትሽም መለስ ብሏል" አለችኝ ኡሚ እንደዛ ስትለኝ በጣም ነበር የደነገጥኩት ለካ ይህንን ያህል አስጨንቄያታለው፤ሳላስበው እንባዬ ወረደ ትላንት ላወኩት ወንድ ኡሚን ይህንን ያህል ማስጨነቄ አበሳጨኝ ሮጬ ሄጄ አቀፍኳት "ይቅርታ አድርጊልኝ እናቴ" ኡሚ ተከትላኝ አለቀሰች "ምንድነው የሆንሽው አለሜ? ምን ነካብኝ? ንገሪኝ እስቲ ምንድነው የተፈጠረው እ? ከሰሙ ጋር ተጣልተሻል አይደል? ለዛ ነው እንደዚ የሆንሽው እሷም ማትመጣው ? "እንዳልሆነ አንገቴን በአሉታ ነቀነኩላት "እሺ ምንድነው? ንገሪኝ ከዛ ሽማግሌ አሰሪሽ ጋር ተጣልተሽ ነው?" በጥያቄ አጣደፈችኝ "ኡሚዬ ዛሬ በጣም ደና ነኝ ይሀው አሁን ሰሙ ጋር ልሄድ ነው ደሞ ቃል እገባልሻለው ሁሉም እንደበፊቱ ይመለሳል ከአሁን ቡሀላ እንደዚ አልሆንም ብዬ ግንባሯን ሳም አደረኳት።ኡሚ ልነግራት ያልፈለኩት ነገር እንዳለ ብትረዳም ልታስጨንቀኝ ግን አልፈለገችም "እሺ ሲሁ ብቻ አንቺ ደና ሁኝልኝ አላህ ይጠብቅሽ የአይኔ ማረፊያ ብላ እቅፍ አደረገችኝ ከኡሚ ጋር እየተሳሳቅን ልብስ እየመረጠችልኝ ብዙ አወራን በመሀል "ማሂር እንዴት ነው መድሀኒቱ ለውጥ አለው አይደል?" አልኳት "አዎ ሲሁ ለውጥ አለው በጣም: ግን ባንቺ ነገር በጣም ተጨንቋል ብታይ ምስኪን ልጅ ነው አላህ ይጠብቀው" ከዚ በላይ ስለ ማሂር መስማቱን አልፈለኩም "ኡሚ ሰዒድ ይደውላል ግን?" ወሬ ማስቀየሻ ነበር "አዎ ሰኢድም ቢሆን እየደወለ ይጠይቀዋል ያወራሉ ከኔጋም ጥሩ ወዳጅ ሆነናል እንደውም ባለፈው የኔ ስልክ እንቢ ብሎት ባንቺ ቢደውልም ስልክሽን አላነሳሽለትም ሁሌ ነው ስላንቺና ስለሰሙ ሚጠይቀኝ እሱም በጣም በጎ ሰው ነው አንዳንዴማ አላህ ለማሂር የላከው መላኢካ ነው ሚመስለኝ" ኡሚ እንደዛ ስትል ሳቄን ለቀኩት አይ እናቴ አንቺ ኮ ሰው አትውደጂ ጭራሽ መላይካ አደረግሽው" ሳቄን ማቆም አልቻልኩም "ድሮም እኮ የኔ ነገር ምንም አይዋጥልሽም በይ ደና ዋይ ደሞ ሰሙን ይዘሻት ነይ ምቶዱትን ምግብ ነው ሰርቼ ምጠብቃቹ እዚ ጉሊት እቃ ገዝቼ ልምጣ" ብላኝ ወጣች። ኡሚ ሰው ስትወድ ከልቧ ነው። ኡሚ ለሰው ያላትን ውዴታ እያሰብኩ የስልኬ ጥሪ አስተጋባ ሰሙ ነበረች።"እስካሁን አልወጣሽም አ አንቺ ኮ በቃ ለቀጠሮ አትመቺም ሰሙ ተቆጣች " አይደለም ኮ እህቴ ከኡሚ ጋር እያወራን ሰዐቱን ሳላውቀው ሄዶ ነው" ሰሙ ከኡሚ ጋር ስላት እርግብ አለች "ውይ እንደው ሰበብ አያጣሽ ነይ በቃ ውጪ እሺ አሁን" ብላ ስልኩን ዘጋችው። ልብሴን በፍጥነት ለባብሼ ወጣው ማሂር መጅሊስ ላይ ቁጭ ብሎ የሆነ የሆነ ነገር እየሞነጫጨረ አላስተዋለኝም ነበር ኡሚ ምን ያህል ስለእኔ እንደተጨነቀ የነገረችኝ ትዝ ብሎኝ አሳዘነኝ በማያውቀው ነገር እሱን ማስጨነቄ ተፀፀትኩ በዝግታ ከአጠገቡ ሄጄ ተቀመጥኩ በድንጋጤ ቀና ብሎ ባለማመን አስተያየት አየኝ "ማሂር ምን ያህል እንዳስጨነኳቹ አቃለው በቃ አለ አይደል አንዳንዴ የሰው ልጆች ስንባል... ንግግሬን አቋረጠኝ "ሲሁ አሁን እንዴት ነሽ?" " በጣም ደና እንደሆንኩና ለኡሚ የገባሁላትን ቃል ገባሁለት "የኔዋ ዋናው አንቺ ደና ሁኚ ደሞ ስሚኝ ቃል አትግቢ እሺ" ንግግሩ እንዳዘነበኝ ያስታውቃል ሁሉንም ነገር ልነግረው ለራሴ ቃል ብገባም መጀመርያ ግን ለሰሙ ላማክራት ወስኛለው ከዚ በላይ ከማሂር ጋር መቆየቱ እሱን ማሳመም ስለመሰለኝ "በቃ ማሂር ስለኔ አትጨነቅ አሁን ሰሙ ጋር ልሄድ ነው ስመጣ አወራሀለው ብዬ ከቤት ወጣው። ...
ቃል አትግቢ የምትለዋ የማሂር ቃል ምን ያህል እንዳዘነብኝ ጥሩ ማሳያ ሆናኛለች እቤት የመጣ ቀን ማታ የገባሁለትን ቃል አስታወስኩ ላልየው ላርቀው፤ ግን አንድ ቀን እንኳን አብሬው አልነበርኩም። ማሂር ግን ቃሌን ያፈረስኩበትን ምክንያት ሲያውቅ ይቀበለኝ ይሁን?
ክፍል አስራሶስት ይቀጥላል .......

እብዱ ደራሲ ክፍል አስራአራት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
...................................
የሰሙ ፊት እንደ ፀደይ አበባ እንደፈካ እኔም በማስመሰል ፈገግታ ውስጥ ሆነን እቤት ገባን ኡሚ ቤቱን ፏ አድርጋ ቡና እየቆላች ደረስን ማሂር አንድ ጥጉን ይዞ ከኡሚ ጋር የቀለጠ ወሬ ይዘው እየተሳሳቁ ነው፤ ኡሚ ምን ብላው ወይም እሱ ምን ብሏት እንደሆነ ባላውቅም የሁለቱም ሳቅ ከውጭ ይሰማ ነበር፤ ማሂር ሲስቅ ሳየው ደስ አለኝ ፈገግታው ናፍቆኝ ነበር "አረ ምንድነው እንደዚ መሳቅ እስቲ ንገሩን እና እንሳቅ"አለች ሰሙ እየተቀላቀለቻቸው "አረ አሰላምአለይኩም ይባላል መጀመርያ ደሞ ነይ እንጂ ሰላም በይኝ ስንት ጊዜያችን ነው ከተገናኘን" ሰሙ ኡሚን ሰላም ማለት እንዳለባት እንኳን ዘንግታዋለች ከተቀመጠችበት እየተነሳች"አፉ በይኝ ኡሚዬ እናንተ እኮ ናቹ ቀልቤን ወስዳቹት..." ማስተባባያ መሆኑ ነው ይሄ ሁላ ሲሆን በሩን ተደግፌ እያየውዃቸው ነበር "ነይ እንጂ ጊቢ ሲሁ ለምን ቆምሽ ወይስ...." ማሂር ነበር "መጣው ልብሴን ልቀይር" ብዬ ወደክፍሌ ገባው፤ ከክፍሌ ስወጣ ሰሙና ኡሚ ምሳ እያቀራረቡ ስለነበር እኔ ለማሂር የእጅውሀ አመጣሁለት ጎንበስ ብዬ ሳሰጥበው "አጎንብሶ ሚያሳጥብ ባል ይስጥሽ" ሳቄን ለቀቀኩት "ምን ያስቃሻል አግኝተሽ ነው?" "አረ አይደለም እንደሽማግሌ ምርቃትህ ገርሞኝ ነው እንጂ"፤ "ማነው ደሞ ምርቃትን የሽማግሌ ያደረገው?" እየተከራከርን እነ ኡሚ ምግቡን ይዘው መጡ "አረ ተይ ወሬው አያምልጥሽም ማስታጠቢያውን አስቀምጪው ሆ ስትስቂ ልጁ ላይ እንዳትገለብጪበት" ኡሚ እንደዛ ስትለኝ ውሀው ማሂር ላይ ቢገለበጥ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ሳስበው የባሰውኑ አሳቀኝ "በቃ ችግርሽ እኮ ይሄ ነው መሳቅ ከጀመርሽ አታቆሚም ሆ ነይ ሰሙዬ ተቀበያት ጤነኛ አደለችም እኮ" ሰሙ ከእጄ ላይ ማስታጠቢያውን ተቀብላኝ እጄን አስታጠበችኝ "አጎንብሶ ሚያስታጥብ ባል ይስጥሽ" አልኳት ቤቱ በሳቅ ተሞላ ኡሚ ሳቋን ማቆም አልቻለችም ቅድም ሲያስቀኝ የነበረው የማሂር ምርቃት እንደሆነ ስነግራቸው ደሞ የባሰ ሳቃቸውን ለቀቁት "እሺ ታስቂብኛለሽ አ ሲሁ ያገጣጥመን ብቻ ባልሰራልሽ" አለኝ ማሂ እኔና ሰሙ ሳቃችንን ማቆም አልቻልም እየተያያን ፈይሰልን እያሰብን እንስቃለን "ዝም በላቸው ልጄ እነሱ ከተገናኙ ማቆሚያ የላቸውም ደሞ አግኝታቹ ነው ጎንበስ ብሎ የሚያስታጥብ ባል? ላንተም ሁረልዐይን የሆነችውን ይስጥህ የኔ ወርቅ" "አሚን" አልን ሶስታችንም "ኑ በሉ ምግቡን እንብላ ቅረቡ" አለችን ኡሚ እየሳቅን እየተጫወትን ኡሚ ያፈላቸውን ቡና እየጠጣን እያወራን ኡሚ ስለ ድሮ የሚያዝናኑ ታሪኮቿን እየነገረችን እኛ እየተማርንም እየተዝናናም ማሂር እየቀለደ ሰሙ እና እኔ ከጣራ በላይ እየሳቅን ሳናውቀው መግሪብ ደረሰ የመስጂዱ ኢማም አዛን ማለት ሲጀምሩ እንስገድ በሉ ተነሱ አለች ኡሚ"፤ " እሺ ከሰገድን ቡሀላ ግን አንድ ዜና ስላለን እዚሁ እንገናኛለን ሰሙ ልትነግረን ምትፈልገው ነገር አለ" አልኳቸው ሁሉም በሀሳቤ ተስማምተው ለኡዱ ተበታተንን ። ከመግሪብ ሰላት ቡሀላ ሁላችንም ሳሎን ተሰባስበናል ኡሚ እና ማሂር ሰሙ ምትነግረንን ነገር በጉጉት ነበር ሚጠብቁት ሰሙ ደሞ ፈርታለች ምን ብላ መጀመር እንዳለባት ግራ ስለገባት አንቺ ንገሪያቸው በሚመስል አይነት ቀና እያየች ታየኛለች ኡሚ ሁለታችንም መጀመር እንደፈራን ስለገባት "እሺ ሰው ቀጥሮ የምን መሽኮርመም ነው ጀምሩ አ" ብላ አሸማቀቀችን። ሰሙ ቀይ ስለሆነች በፍርሀት ፊቷ ሲቀላ ታየኝ " ምን መሰላቹ ቤተሰቦቼ " አጠገቤ ስለነበረች በእጆቼ ትከሻዋን ያዝ አድርጌ "ፈይሰል ሰሙን ሊያገባት ይፈልጋል" ኡሚ ልክ እኔ ሰሙ ስትነግረኝ እንደነበረው አይነት ስሜት ነበር የተሰማት፤ ማሂር ደግሞ አዲስ ስም ስለሆነበት ምንም ለማለት አልደፈረም። ሰሙ እና እኔ እየተቀባበልን ሁሉንም ነገር አስረዳናቸው ሁለቱም በጣም ደስተኛ ሆነዋል ኡሚ ቤቱን በእልልታ አቀለጠችው ሰሙን አቅፋት አለቀሰች "አንድም ነገር እንዳታስቢ እኔ እናትሽ ሰፈር ጉድ የሚልበትን ሰርግ ነው ደግሼ ምድርሽ" አለቻት ሰሙ አለቀሰች ለቅሶዋ የደስታ ነበር "በዛሬ ቀን አረ የምን ለቅሶ ነው በአላህ ደሞ አያሳስብሽ እኔ ወንድምሽ ደሞ ቅብርር ብዬ ነው ሽማግሌዎቹን የምቀበልልሽ" ሰሙ በማሂር ንግግር በጣም ተደንቃለች። ወንድ ልጅ ላይ አይደለም ልትጠመጠም ይቅርና ለሰላምታ እጇን ማትዘረጋ ልጅ ማሂር ላይ ሄዳ ተጠመጠመችበት እሱም እቅፍ አደረጋት "ወላሂ ሰሙ በዚች ምድር ላይ እንደ እኔ ና አንቺ እድለኛ ሰው የለም አላህ ቤተሰቦቻችንን ወስዶ ባዶ ሜዳ የጣለን ሲመስለን እናትም አባትም እንድትሆነን ኡሚን እህትም ወንድም እንድትሆነን ሲሁን ሰጠን" አላት እና አለቀሰ ኡሚም ሶስታችንንም አቅፋ አለቀሰች "አላህ ለኔም ባሌን ወስዶ ልጄን ብቻዬን ባሰድግም እሷ እህት እና ወንድም በሚያስፈልጋት ሰዐት፤ እኔም አጋዥ በሚያስፈልገኝ ሰዐት እናንተን ሰቶኛል ከጌታዬ በታች ለኔ ያላቹኝ እናንተ ናቹ፤ እናንተ ከአሁን ቡሀላ እህት እና ወንድም ናቹ፤ በመሀከላቹ ምንም ሸይጣን እንዲገባ አትፍቀዱ፤ አንዳቹ ለአንዳቹ ከኔ የተሰጣቹ አደራ ናቹ" ብላ ግንባራችንን ሳመችን። ...
ገና ሽማግሌው ሳይላክ ለሰሙ ሰርግ ፕሮግራም ስናወጣ፤ የፈይሰልን ነገረስራ እያሰብን እየሳቅን፤ ማሂር የፍቅር መቀስ እያለ ሲያበሽቀኝ፤ ኡሚ ስታግዘው፤ ሰሙ ለኔ አግዛ እንደውም እህቴን ስላናደዳት አላገባውም እያለች ለኔ ጥብቅና እየቆመች..... ብቻ ስንስቅ ስንጫወት ሰዐቱን ሳናውቀው ረፈደ "እንተኛ በሉ ከዚ ቡሀላ ብዙ ሀሳብ አለብን" ብላ ኡሚ ተነሳች ሰሙ ተከትላት ሄደች እኔም ማሂርን ደግፌው ወደ ክፍሉ ልወሰድው አነሳሁት። ማሂር አሁን ዊልቸር መጠቀም ትቷል ኡሚ ስትሆን እሷን ላለማስቸገር ብቻ ነው ዊልቸር ሚጠቀመው እጁን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጎ ወደ ክፍሉ ሄድን "የኔዋ ሲሁ መቼ ነው ወክ ይዘሽኝ ምትወጪው ግን አለኝ? አጠያየቁ የልመና ነበር አሳዘነኝ "ነገ ማሂዬ ነገ እንደውም በጠዋት ወተን ፈታ ነው ማደርግህ ደሞ ላወራህ ምፈልገው ነገር አለ" ፊቱ በደስታ ፈካ "እሺ ትንሿ እስኪነጋ በጉጉት ነው ምጠብቀው ደሞ አመሰግናለው" ብሎ ጎንበስ ብሎ ግንባሬን ሳመኝ። ማሂርን ወደ ክፍሉ አስገብቼ ልተኛ ስገባ ሰሙ ስልክ እያወራች ነበር ከፈይሰል ጋር እንደሆነ አልጠረጠርኩም፤ በሰሙ ቀናሁባት ከማሂር ጋር እንደዚ ማወራበት ቀን ናፈቀኝ፤ ሳላስበው አይኔ እንባ አቀረረ፤ ሰሙ እንዳታየኝ ስለፈለኩ ተጠቅልዬ ተኛው ለረጅም ሰዐት እንቅልፍ አልወሰደኝም ነግቶ ማሂርን እስካወራው ቸኩያለው..........................
ክፍል አሰራአምስት ይቀጥላል....

እብዱ ደራሲ ክፍል አስራሶስት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
ሰሙ ቤቱን ፏ አድርጋ የምግብ አይነት ሰርታ በጉጉት እየጠበቀችኝ ነው። ልክ የምስራች ተናጋሪ ፊቷ በደስታ ተሞሎቷ፤ ፊቷ ፍክት ብሎ የጠዋትን ፀሀይ ታስንቃለች፤ እኔ ደሞ በተቃራኒው፤መንገዴ በሙሉ በማሂር ሀሳብ ተወጥሬ ስለነበር ፊቴ እንደደመና ጭፍግግ ብሏል። የሰሙን በደስታ እንደዛ መፍነክነክ ሳይ እንዳልረብሻት ስለሰጋው በግድም ቢሆን ለመሳቅ እየሞከርኩ ነው። ማስመሰል የሚባል ነገር ባይኖር ግን እንዴት ነበር ከሰዎች ጋር የምንኖረው? ማስመሰለን የሰጠን አምላክ ነው ወይስ ሰይጣን? ብቻ ከየትም ተሰጠን ማንም ሰጠን ለሰው ልጆች ከመርሳት ቀጥሎ የተሰጠ ስጦታ ነው። ማመስገን አለብን ወይስ? ማስመሰላችን ለፅድቅ ወይስ ለሃጢኣት? ግን እኮ ማስመሰል መኖር ነው ለመኖር ማስመሰል ግዴታ ነው! የሰው ልጅ ባያስመስል እና ትክክለኛ ስሜቱን መደበቅ ባይችል እዚች ምድር ላይ ሚስጥር የሚባል ነገር አይኖርም ነበር። ሚስጥር ከሌለ ጎደኝነት፣ ቤተሰብ ሁሉ ነገር የለም፤ አለም በሚስጥር የተሞላች ናት፤ የምንወደውን ሰው የምንለየው በምንነግረው ሚስጥር ነው፤ ለማንወደው ወይም፤ ለማንቀርበው ሰው ስሜታችንን አናጋራውም፤ ስሜታችን ሚስጥራችን ነው፤ ሚስጥራችንን ለመደበቅ የግድ ማስመሰል አለብን ስለዚህ ማስመሰልን ስለሰጠን ማመስገን አለብን። ማስመሰል ባይኖር ስንት ላበላሸው የምችላቸውን ነገራቶች አሰብኩና "አልሃምዱሊላህ" አልኩኝ ከልቤ ስለነበር ለካስ ሳይታወቀኝ ጮክ ብያለው "ሲሁ በሀሳብ ጥለሽኝ መብረርሽ ሳያንስ ብቻሽን ማውራት ጀመርሽ?" ለካስ ከራሴ ጋር ሙግት ገጥሜ ሰሙን ረስቻታለው "ውይ እህቴ ወላሂ እንደማስብ ታውቂያለሽ የሰው ልጅ ማስመሰልን የተሰጠው ከማን ነው ማለት በማስመሰሉ ይጠየቅበታል ወይስ ይፀድቅበታል?" ሰሙ እንደዚ ስፈላሰፍ አይታኝም ሰምታኝም ስለማታውቅ የአግራሞት ሳቅ ሳቀች" ደሞ ከመች ጀምሮ ነው መፈላሰፍ የጀመርሽው በአላህ? ለማንኛውም እንደኔ ሀሳብ ማስመሰል የሸይጧን ስራ ነው ምክንያቱም..... አላስጨረሰኳትም ከሰሙ ጋር ክርክር ጀምሬ አንድ ቀንም አሸንፊያት ስለማላውቅ ክርክሩ ረዝሞ እኔም ልሰማው ምፈልገውን እሷም ልትነግረኝ የምትፈልገውን ነገር እንዳያስቀርብኝ ስለፈራው" በይ ነይ ሴትዬ እርቦኛል ምሳውን እንብላና ምትነግሪኝን ንገሪኝ" ብዬ ወሬዋን አቋረጥኳት።ሌላ ቀን ወሬዋን ሳቋርጣት ማመን ስለማትፈልጊ ሁሌም የራስሽን ሀሳብ ትናገሪ ና ትሸሺያለሽ፤ በዚ ፀባይሽ ደሞ ሀቅን እየራቅሽ መሆኑን አትርሺ፤ መሸነፍን ሳይሆን ማስረጃ መቀበልን አስቢ........ ብዙ ብዙ ነገር በዛውም ምክሯን ትቀጥል ነበር በተለይ ኡሚ ካለችማ ፈረደብኝ ዛሬ ግን ምንም አላለችኝም እንደውም ስላቋረጥኳት ደስ ያላት ነው ምትመስለው..............
ከሰሙ ጋር ምሳ እየበላን ብዙ አወራን ስለ ማሂር ስለ ኡሚ ስለ መስሪያቤት አወራን እስከአሁን ግን አወራሻለው ያለችኝን ነገር ምንም አልጀመረችልኝም ምክንያቱም ምንም ለየት ያለ ነገር አላየወራችም ስለ ማሂርም ቢሆን ከደህንነቱ ሌላ ምንም ነገር አልጠየቀችኝም ወሬው እኔ ካሰብኩት ውጪ እንደሆነ ሳውቅ የማወቅ ጉጉቴ ጨመረ።
እኔ ምልሽ ግን ሰሙ "እስካሁን እኮ ነግርሻለው ያልሽኝ ነገር አልነገርሽኝም" አልኳት ሰሙ እንደማፈርም እንደመሳቅም ብላ"ሆድሽን ቆረጠሽ አደል እሸይ የት አባሽ" ሳቀች ሳቋ የእውነት ነበር ከልብ የመነጨ የደስታ ሳቅ ቀናሁባት እንደሷ ደስተኛ ባልሆንም ለሷ ደስታ ተከትያት ሳኩ ለደስታዋ ተደሰትኩ ሰሙ አሁን ልትነግረኝ ትዘጋጅታለች ስታወራ ሚያቋርጣት ስለማትፈልግ አውርታ እስክትጨርስ ምንም አይነት ጥያቄ እንዳልጠይቃት አስጠነቀቀችኝ "እሺ ባለመርከቧ ኸድር"(ከሙሳ(ዐ.ሰ) ጋር በመርከብ ሲሄዱ ምንም ጥያቄ እንዳይጠይቋቸው ያስጠነቋቸው ታላቅ ሰው ናቸው) ብዬ ሳኩባት ሁሌም እንደዚ ስለምላት ቀልዴን ብዙም ቦታ አልሰጠችውም ወሬዋን ጀመረች.....
"ምን መሰለሽ እህቴ አንቺ ስራ ባልገባሽባቸው ቀናቶች ብዙ አዲስ ነገር ተፈጥሯል ማለቴ በኔ ና በፈይስ መሀል".. ሰሙ ፈይስ ነው ያልሽው? ፈይሰል እኮ የኛ አለቃ ያ ሼባ? ማለቴ ምን አገናኛቹ? ምን? ምንድነው ጭራሽ እኮ እያቆላመጥሽው ነው?" ሰሙን በድንጋጤ በጥያቄ አጣደፍኳት ፊቷ በአንዴ ሲለዋወጥ ንግግራን ስላቋረጥኩ እንደተነደደችብኝ ስለገባኝ ተረጋጋው "ሰሙዬ ግራ ስለገባኝ ነው እኮ ማለት ፈይሰል እና አንቺ አስቤው አላውቅም ይቅርታ በቃ አላቋርጥሽም" ወሬውን ለመስማት ከቅድሙ የበለጠ ስለጓጓው ሰሙን ተለማምጬ ይቅርታ ጠይቂያት ከአሁን ቡሀላ ባቋርጣት እንደማትነግረኝ አስጠንቅቃኝ ንግግሯን ቀጠለችልኝ....... "ይሀውልሽ ሲሁ በአጭሩ ፈይሰል ሊያገባኝ ይፈልጋል አንቺን እንደዛ የሚያደርግሽ ስራ የሚያበዛብሽ እኔን እየተንከባከበ መሆኑ ነበር ሊነግረኝ ቢፈልግም ብቻዬን የሚያገኝበትን አጋጣሚ አላገኘም ሁሌም ሲያየኝ ካንቺ ጋር ነኝ ታስታውሺ እንደሆነ ስልክ እኔጋ ከደወለ አንቺ እንዳለሽ አንቺ ጋር ከደወለ እኔን እንዳለው ሳያጣራ አይዘጋውም ነበር የፍቅር መቀስ ሆነሽበት ነው የጠመደሽ እኮ ብላ ሳቋን ለቀቀችው ነገሩ ግራ ነበር የገባኝ ግን ሳስበው የፈይሰል ነገረ ስራ መጣብኝ እና አብሬያት ሳኩኝ "አሁን ወሬዬን ጨርሻለው ከፈለግሽ የፈለግሽውን ጠይቂኝ" አለችኝ አይን አይኔን እያየች "እህቴ አንቺ ደስተኛ ነሽ ግን ማለት ለባልነት ብቁ ነው ብለሽ መርጠሽዋል መስፈርትሽን አሟልቷልሻል እ?" "አዎ ሲሁ ላገባው ፍቃደኛ ነኝ" እቅፍ አድርጌ ሳምኳት፡ ፊቷ ሁላ ነበር በደስታ የፈካው፤ ሰሙ አስተዋይ ሴት ናት ይህንን100% እርግጠኛ ነኝ፤ ፈይሰልም ቢሆን ይነጫነጭ እንጂ በዲኑ ጠንካራ ወንድ ነው የንጭንጩ ምክንያት ደሞ ዛሬ ተገልፆልኛል። ጥሩ ሰው ስለገጠማት ለሷ እኔ ደስተኛ ሆንኩኝ። ሰሙን አውርቻት እኔም ደስታዬን ከልቤ ማድረግ ብፈልግም እንደዚ ደስተኛ ሆና እያየውሀት ስለ ማሂር ነግሬያት ላስከፋት አልፈለኩም። ይህንን ዜናማ ለኡሚ መናገር አለብን ብዬ አጣድፌ ከቤቷ ይዣት ወጣው። በልቤ ግን ለማሂር ሀሉን ነገር ልነግረው ወስኛለው፤ ድብብቆሹን ከዚ በላይ መቀጠል ለኔም ፣ለሱም፣ ለኡሚም ህመም መሆኑን ተረድቼዋለው ሁሉንም ነግሬው መልሱ ምንም ይሁን ምን ለመቀበል እራሴን አዘጋጅቻለው... ሰሙ ለኡሚ ደስታዋን እኔ ለማሂር የልቤን ለመንገር ከሰሙ ቤት ተያይዘን ወጣን........
ክፍል አስራአራት ይቀጥላል.........

😁1
እብዱ ደራሲ ክፍል አስራአምስት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
ጨረቃ ለፀሀይ ቦታዋን ለቃ ስናፍቃት የነበረችው እሁድ እነሆ ከች ብላለች አርፍደን ስለነበር የተኛነው ማንም ከእንቅልፋችን አልተነሳንም ነበር
የሰሙ የስልክ ጥሪ ነበር ከእንቅልፌ ያነቃኝ ሰሙ ማታ ከኔ ቡሀላ ነው የተኛችው ስልኳ ሲጠራ በስጨት ብላ ተነስታ "ማነው በዚ ለሊት ሚደውለው?" ብላ ስልኳን አነሳችው
"ሄለው" አለች በደከመ ድምፅ "ምነው እስከአሁን አልተነሳሽም እንዴ?" ፈይሰል ነበር እሱ መሆኑን ስታውቅ በደንብ ከእንቅልፏ ነቃች .................
ሁላችንም ለቁርስ ተሰበስበናል ፤ማሂርን በጨረፍታ ሳየው ያ ምወድለትን ፈገግታውን ይለግሰኛል እያሽኮረመመኝ ነው ወይስ? ከቁርስ ቡሀላ ሰሙ ለኡሚ ዛሬ ከፈይሰል ጋር ቀጠሮ እንዳላቸው ነግራት ወታለች ኡሚም ምትሄድበት ቦታ እንዳለ አስቀድማ ተናግራለች እኔና ማሂር ግን መናገር ፈርተናል የት ምትሄዱት? ለምንድነው ምትሄዱት? ብንባል መልሳችን ምን ሊሆን ነው? ማሂር ውጩን ናፍቋል ቢሆንም ግን ለኡሚ ከሲሁ ጋር ልውጣ ማለቱ ከብዶታል እኔም እንደዛው፤ ግን እኮ አሁንም ብቻችንን ነን፤ ሰሙም ኡሚም ቶሎ አይመለሱም ሌላው ቢቀር ምናወራበትን ሰዐት እናገኛለን አሁን ያልገባኝ ማሂር ከኔ ጋር መሆኑን ነው ወይስ ውጭ መቶ አየር መቀየሩን ነው ሚፈልገው?
"ሲሁዬ በቃ ልሂድ እንዳይደብራቹ እሺ ምሳም ሰርቻለው ዋ ደሞ እዛ ክፍልሽ ተቀርቅረሽ ወንድምሽን በረሀብ እንዳትቀጭዉ እኔ አረፍዳለው ባይሆን ፀሀዩ በረድ ሲል እስቲ ወጣ ብላቹ አየር ውሰዱ ልጁን እኮ የቁም እስረኛ አደረግሽው በሉ ደና ዋሉ ማሂሬ እንዳይደብርህ እሺ" ብላ ኡሚ ወጣች በሩን ልዘጋ ተከትያት ወጣው.........
የመጅሊሱ ጥግ ላይ ተቀምጦ እንደለመደው ይፅፋል ላወራው ብፈልግም ምን ብዬ መጀመር እንዳለብኝ ስላላወኩ ዝም ብዬዋለው አይኔን አንዴ እሱ ላይ፤ አንዴ ስልኬ ላይ፤ አንዴ ደሞ ቲቪው ላይ እያንከራተትኩ በማሂር ሀሳብ ሰምጫለው
"ሲሁ" ከነበርኩበት የቀን ህልም አባነነኝ "አቤት" የድንጋጤ ነበር "እንወጣለን ብለን ስላልወጣን ደበረሽ እንዴ ዝም አልሽኝ እኮ" "አረ አልደበረኝም ማሂ እንደውም አንተ ከወጣህ ረጅም ጊዜ ስለሆነህ አንተ ይከፋሀል ብዬ እያሰብኩ ነበር" አልኩት "አረ ሲሁ እኔኮ ካንቺ ጋር መዋሉን ነው ምፈልገው" ልቤ በደስታ ዘለለች፤ተነስቼ ጥምጥም ብልበት ፍላጎቴ ነበር፤ እኔን የተሰማኝ የተሰማው መሰለኝ፤ ስሜቴን የተጋራ፤ ሳልነግረው የተረዳኝ ስለመሰለኝ የበለጠ ወደድኩት፤ በፍቁሩ ውስጥ ተሸሸጌ አለምን መርሳት ፈለኩ፤ ግን ኡሚስ? ወንድምሽን አደራ ብላኝ እኮ ነው ከቤት የወጣችው ግን ምን ችግር አለው? ማሂር እኮ እውነት ወንድሜ አደለም ባፈቅረውስ? በዚ ፀባዩ፤ በዚ ውበቱ ባፈቅረውስ ይፈረድብኛል? እብድ አፈቀረች፤ መሄጃ መጠጊያ የሌለውን አፈቀረች ይሉኝ ይሆን? ኡሚስ ብትሆን እሱ ኮ እናትም አባትም ዘመድም የለውም ምኑን አውቀሽው ምታገቢው ትለኝ ይሆን? ግን እኮ ኡሚ ማሂርን ትወደዋለች! ብቻ ምንም ይሁን ምን ማንም ምንም ይበል ምን ማሂርን አፍቅሬዋለው፤ እሱን የኔ ከማድረግ ምንም አያግደኝም። በደቂቃ ውስጥ ይሄ ሁሉ ሀሳብ ይሄ ሁላ ድፍረት ቆራጥነት፤ ፍቅር እንዲ ነው ለካ ሚያደርገው ያጠንክራል ከሰው አልፎ እራስን ያስክዳል..........
አጠገቡ ያለውን ወረቀት ጥቅልል አድርጎ ሲወረውርብኝ ነው ከሀሳቤ የባነንኩት "ዛሬ ግን በሰላም ነው? በጣም መመሰጥ አብዝተሻል በአላህ ንገሪኝ እና እስቲ እኔም እንደዚ በሀሳብ ያበረረሽን ነገር ተጋርቼሽ አብሬሽ ልብረር እ ሲሁ?" አጠያየቁ የልምምጥ ነው፤ ዝም ብዬ አየሁት አየኝ፤ ለሰከንዶች ተያየን፤ በማሂር አይን ውስጥ ሰርጋችንን፤ ከሱ ምወልዳቸውን ልጆች፤ ፍቅርን፣ ውበትን፤ ብዙ ውብ ነገሮችን አየሁ ግን ደሞ ባይሆንስ? ማሂር የኔ ባይሆንስ? ኡሚ ባትፈቅድስ? ሳላስበው እንባዬ ወረደ እሱን ማጣቱን ሳስበው አመመኝ "ሲሁ አለቀሽ ኮ?" ደንግጧል አጠገቤ መቶ ሊቀመጥ የመጅሊሱን እጅ ይዞ ሲነሳ ቀድሜው ሄጄ አቀፍኩት አረጋጋኝ በነዛ የሴት እጅ በሚያስቀኑ እጆቹ እንባዬን አበሰለኝ ተረጋጋው "ሲሁ ንገሪኝ በቃ እኔ ከዚ በላይ መታገስ አልችልም እኔ ከመጣሁበት ቀን ጀምሮ የዛን ቀን ማታ ድንገት ተነስተሽ ጥለሽኝ መውጣትሽ ሳይቀር ሳምንቱን ሙሉ በዝምታ የቀጣሽኝ ለምንድነው? አሁንስ ለምንድነው ምታለቅሺው? ንገሪኝ ሲሁ ያለበዛ ከዛሬ ጀምሮ ወደነበርኩበት ህይወት እመለሳለው ያገኘሁትን እኔነት አትቀሚኝ እባክሽ ሲሁ እባክሽ" እያለቀሰ ነበር፤ በኔ ምክንያት ሳምንቱን ሙሉ እንደዛ መሆኑ አሳዘነኝ፤ አሁን ግን ቆርጫለው፤ ማሂር ወደነበረበት ከሚመለስ ሁሉንም ነገር ልነግረው እቅፉን ለቅቄ ከፊት ለፊቱ አይኑን እያየው ተቀመጥኩ.....
ክፍል አስራስድስት ይቀጥላል ......

እብዱ ደራሲ ክፍል አስራስድስት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
............
የማሂር አይን በእንባ ተሞሎቷል ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት፤ እንባው የደስታ ነው ወይስ የሀዘን? አላውቅም! ብቻ እኔ እያወራው ነው፤ እስክጨርስ ምንም ጣልቃ እንዳይገባ አስቀድሜ አስጠንቅቄው ስለነበር ስሜቱን በፊቱ ገፅ እያስነበበኝ ነው፤ አንዴ ፈገግ፣ አንዴ ሀዘን፣ እንባ፣ ተስፋ እና ተስፋ መቁረጥ ምን እያሰበ እንደሆነ መገመት እስኪያቅተኝ ድረስ በየሰከንዱ የፊቱ ገፅ ይለዋወጣል፤ ሲስቅ በመናገሬ እፎይታ ይሰማኛል፤ ልቤ ተደስታ ሳጨርስ ወድያው ፊቱ ሀዘን ይለብስና በመናገሬ እንደፀፀት ያደርገኛል፤ ግን ደሞ አንዴ ጀምሬዋለው እና ምንም ሆነ ምንም መጨረስ አለብኝ። ማሂርን አስተውዬ ካየሁባት የሀኪም ቤት ቅፅበት እስከ አሁኑ ደቂቃ ሙሉ ታሪኩን ነገርኩት፤ስጨርስ ትልቅ ሸክም ከላዬ ላይ የወረደ ያህል ነበር የቀለለኝ፤ ለነገሩ እንዴት አይቅለለኝ? መልስ የሌለው ጥያቄ፤ መፍትሄ የሌለው መንስኤ፤ ሳቅ ና እንባ፤ እያስመሰሉ መኖር፤ መከፋት፣ ብቸኝነት፣የወደዱትንማጣት...እነዚን ሁላ ነበር እኮ ያለማንም አጋዥ ተሸክሜ የነበረው። ህፃን ልጅ በበዐል ዋዜማ ልብስ ተገዝቶለት የጠዋቷን ፀሀይ በጉጉት እንደሚናፍቃት፤ እናት ከረጅም አመት ቡሀላ ወደቤቱ የሚመለሰውን ልጇን ደጅ ደጁን እያየች በጉጉት እንደምጠብቀው ነበረ የማሂርን ምላሽ በጉጉት ስጠብቅ የነበረው "አይ ወይም አዎ" ይህንን ብቻ ነበር የፈለኩት አይ ቢለኝስ ምንድነው ሚፈጠረው? አዎ ቢለኝስ?....ፍርሀቴ ጨምሯል፤ ሲሁ ግን ኮ ኡሚ ....? አላስጨረስኩትም ለኔ በዚ ሰዐት የኡሚ ፍቃድ፤ የሰፈር ሰው ወሬ፤ የማሂር ብቸኝነት.... ምንም ነው "ማሂ እኔ ያንተን መልስ ነው ምፈልገው" አልኩት ፍርሀቴ ከቅድሙ አሁን የበለጠ ጨምሯል ትንሽ ዝም አለኝና ቀና ብሎ በስስት እያየኝ "እኔማ እኮ ቆየው የኔ ካደረኩሽ የኔዋ" ልቤ በደስታ ዘለለች ማሂር እኮ የግሌ ነሽ አለኝ ማሂ እኮ ልክ እኔ እንደምወደው ይወደኛል እንደማስበው እንደምሳሳለት ይሳሳልኛል፤ የኔው ማሂ ኮ በቃ የኔ ሆነ፤ ካፈቀርኩት በላይ አፈቀርኩት፤ አለም በእጃችን የያዝን ያህል በደስታ ጮቤ ረገጥን፤ ለካ ደስታም ያስለቅሳል! ተቃቅፈን ተላቀስን፤ ምን አለ ከእቅፉ ሳልወጣ አመታት በነጎዱና ዘመናት ባለቁ፤ ቀና ብዬ አይኑን ማየት ፈርቻለው እነሆ ዛሬ የማሂር ፍቅረኛ የወደፊት ሚስቱ እኔደምሆን ከሱ ያረጋገጥኩበት፤ በህይወቴ ለመጀመርያ ጊዜ ለወንድ ልጅ ልቤን አሳልፌ የሰጠሁበት፤ ከኡሚ እና ከሰሙ ሌላ ሰው እንደሚወደኝ እርግጠኛ የሆንኩበት ልዩ ቀን ነው ይቺ ቀን የኔ ናት መቼም የማረሳት ውብ እና ድንቅ እለት። በዝምታ ተወጥናል ደረቱ ላይ ደገፍ ብያለው፤ ምን እናውራ? ሰዎች ግን ፍቅረኛ ሲሆኑ ምንድነው ሚያወሩት? እንደሌላ ጊዜው ስለኡሚ፣ ስለቤተሰብ፣ ስለምን? ሰሙን ደውዬ ልጠይቃት ይሆን? እሷ ከፈይስ ጋ በመጀመርያ ቀን ምን ነበር ያወሩት?......
እንዴ ማሂ እኮ ፍቅረኛ ነበረችው! ድንገት ሳላስበው በሀሳቤ ሀዩ ብልጭ አለችብኝ፤ መጠየቅ ፈለኩ ግን ፈራው! ቢከፋብኝስ? ስለሀዩ ብቻ ማንሳቱ ስለከበደኝ ከተደገፍኩት ደረቱ ላይ ቀስ ብዬ ቀና አልኩና "ማሂ ግን መቼ ነው ስለቤተሰቦችህ ምትነግረኝ?" "አንቺ የፈለግሽበት ቀን" እርጋታው፤ ትህትናው። "አሁን፣ ዛሬ፣ አንተን ማወቅ ምፈልገው ዛሬ ነው፤ ያለፈ ህይወትህን፤ ያሳለፍካቸውን ጨለማዎች ከዛሬ ቡሀላ ብቻህን እንድትሸከማቸው ስለማልፈልግ ውስጥህ የቆጠረውን፤ ልብህን የሰበረውን፤ ያሳመመህን ህመም ንገረኝ እና ልካፈልህ" በስስት እያየሁት ነበር.......
" አላሁ አክበር... አላሁ አክበር...." የመስጂዱ ኢማም በማይኩ አስተጋቡ ለካስ ዙሁር ደርሷል...
"እሺ ነግርሻለው መጀመርያ ግን ዙሀር እንስገድ ከዛ ምሳ እንብላ።" ፍቃድ እና ትዕዛዝ ነበር አነጋገሩ "እነ ኡሚ እንደሚያረፍዱ ባውቅም ሳይነገረኝ ሚመጡ መሰለኝ፤ ሰላቱም ምግቡም ኮ በውሀላ ይደርሳል፤ ለምን መጀመርያ አይነግረኝም? ብስጭት አልኩበት እሱ ግን በሰላቱ አይደራደርም፤ ኡሚ ይህንን ፀባዩ በጣም ነው ምትወድለት እንደውም አንድ ቀን ስለ ዲን እየተወራ "ማሂሬ ግን ማነው እንደዚ ጠንካራ ያደረገህ?" ብላ ጠየቀችው "አባቴ ነው ኡሚዬ እሱ በጣም ጠንካራ ነበር በዱንያም በዲኑም እናም ሁሌም እንደዚ ይለኝ ነበር "አላህን ካላመሰገንከው የሰጠህ ያንስብሀል፤የሌላውን ታያለህ፤ ህይወት ትመርሀለች፤ መንገድ ይጠፋብሀል፤ ደስታ ካንተ ይርቃል። ልታመሰግነው ምትችለው ደሞ በሰላትህ ነው፤ ልጄ ምንም አድርግ ምንም ሰላትህን ግን አደራ" ይለኝ ነበር " ፊቱ ሀዘን ሲለብስ ኡሚ ደንግጣ ወሬውን አስቀየረችው......
ማሂ ሰግዶ ጨርሷል፤ ሰላት ስላልነበረኝ አልሰገድኩም፤ እሱ እስኪሰግድ ኡሚ የሰራችልንን ምሳ አቀራረብኩ እና አብረን በላን፤ ጉርሻ አሎድም ከኡሚ ውጭ ለማንም እሺ ብዬ ጉርሻ አልቀበልም ምን አልባት አንዳንዴ ሰሙን፤ ዛሬ ግን ከማሂ እጅ ጎረስኩ ጭራሽ እጄን አስሮ እሱ ብቻ እንዲያጎርሰኝ ፈለኩ፤ ቅብጠት ወይስ ፍቅር? በልተን ስንጨርስ የበላንበትን አነሳሳሁ እና የእጅ ውሀ ይዤለት መጣው፤ አስታጥቤው ስጨርስ "ጎንበስ ብሎ ሚያስታጥብ ባል ይስጥሽ ግን እኮ እኔ ጎንበስ ማለት አልችልም ሲሁ" እሱ እየቀለደ ነበር እኔ ግን ሁለት ስሜት ነው የተሰማኝ ሀዘን እና ደስታ፤ ባልሽ ነኝ ግን ጎንበስ ማለት አልችልም፤ ባሌ እንደሚሆን ቢነግረኝም በእግሩ ምክንያት እንደዚ ስላለ ከፍቶኛል "ደና ነህ እኮ አሁን ለምን እንደዚ ትላለህ ደሞ በደንብ ይሻልሀል" አረ ሲሁ ወላሂ ስቀልድ ነው ባይሆን የያዘሽውን አስቀምጪ እና ነይ ከማሂር ጋር ላስተዋውቃቹ" አነጋገሩ ሌላ ሰው ሚያስተዋውቀኝ ነበር የሚመስለው ማስታጠቢያውን ቁጭ አድርጌ ኡሚ ከምግብ ቡሀላ ያስለመደችንን ሻይ በፔርሙዝ አፍልታ አስቀምጣ ስለነበር ከኩሲ ጋር ይዤ ማሂር ጎን ቁጭ አልኩኝ ሻይ ቀድቼ ስሰጠው "እሺ እመቤት ሲሀም የኡሚን አደራ በደንብ እየተወጡ ነው እናመሰግናለን" ድምፁን ጎርነን አድርጎ ስለነበር ያወራው አሳቀኝ "እሺ አቶ ማሂር ምስጋናዎትን ተቀብያለው" አልኩት "እሺ ለሌሎች ወይዘሪት የኔ ወይዘሮ ከማሂር ጋር ለመተዋወቅ ዝግጁ ነሽ?" አንገቴን ነቅንቄ አውንታዬን ገለፅኩለት። እሱም እንደ ሰሙ ነው፤ ሰው ሲያወራ ያዳምጣል፤ እሱም ሲያወራ እንዲያቋርጡት አይፈልግም፤ "ጥያቄ ካለሽ መጨረሻ ላይ ነው ምትጠይቂኝ በቻልኩት መጠን እንድትረጂኝ አድርጌ እነግርሻለው ተስማማን አይደል?" ብሎ እጁን ዘረጋልኝ በመስማማት ጨበጥኩት፤ ሰው ቢያየን የሆነ የትልቅ ድርጅት ስምምነት ምናደርግ ነበር ምንመስለው። ማሂ ታሪኩን ሲነግረኝ እንደሚያለቅስ እርግጠኛ ስለነበርኩ ከተቀመጥኩበት ሸርተት ብዬ የመጅሊሱ መከዳ ላይ ጋደም አልኩኝ እሱም ተረድቶኛል መሰል እግሩን አስተካክሎ እግሩ ላይ አስተኛኝ አሁን ጀርባዬን ሰጥቼዋለው ንግግሩን ለማዳመጥ ምንም ነገር እንዲረብሸኝ ስላልፈለኩ አጠገቤ የነበረውን የቲቪ ሪሞት አንስቼ ቴሌቪዥኑን አጠፋሁት ስልኬንም ዘጋው አሁን ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ ነኝ .........
ክፍል አስራሰባት ይቀጥላል ......

እብዱ ደራሲ ክፍል አስራሰባት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
...... "ይሀውልሽ የኔዋ ያንቺ ማሂር አሁን ከምታቂው በላይ ተወጫዋች ሳቂታ ነበር፤ ሰዎችን ያምናል፤ ይወዳል ብቻ ለራሱ ሳይሆን ለሰው ነበር የሚኖረው፤ ተወለዶ ያደገው በውቢቷ ባህርዳር መሀል ከተማዋ ላይ ጊዬርጊስ ነበር፤ እናት እና አባቱ የተገናኙት ፈለገህይወት በሚባል ሆስፒታል እሱ እህቱን ሊያሳክም በሄደበት እናቴ ደሞ የልብ በሽተኛ ነበረች እና ለክትትል በሄደችበት ነበር። ሁለቱም ወጣት ነበሩ አባቴ ስለሚስቱ ሲናገር "ባህርዳር ላይ እሷን አይቶ ያልደነገጠ የአዳም ልጅ የለም" ይለኝ ነበር አባቴ እናቴን ሚስቱ ለማድረግ በጣም ብዙ ለፍቷል፤ ቤተሰቦቿ የልብ ህመምተኛ ስለነበረች እንድታገባ አይፈልጉም ነበር፤ ለምን እንደሆነ ገባሽ አ? ልጅ ትወልዳለች ብለው እኮ ነው ዶክተሮቹም ቢሆኑ አስጠንቅቀዋቸዋል፤ ማርገዟን ሳይሆን በምትወልድበት ጊዜ ትንፋሽ ያጥራታል ብለው ሰግተው ነው እነሱ እኮ ልክ ነበሩ ምን አለ እሺ ብትል? ደሞኮ ገና 20 አመቷ ነበር" እያለቀሰ እንደሆነ ከድምፁ መረዳት ችያለው ማባበል ግን አልቻልኩም እስኪጨርስ መጠበቅ ፈልጌያለው ሲሁ እናቴ አባቴን ካገባችው በውሀላ እኔን አርግዛኝ ወደ ሀኪም ቤት ስትሄድ ዶክተሩ ምን እንዳላቸው ታውቂያለሽ? "አቶ አህመድ እና ወይዘሮ ሱመያ ልጃቹ በሚወለድበት ሰዐት ለሚፈጠረው ነገር ሀላፊነቱን ትወስዳላቹ" ብሎ መፈረሚያ ወረቀት ሰጣቸው፤ አየሽ ይሄ ሁላ እኮ እኔን ወደዚች ምድር ለማምጣት ነው ቆይ ባልወለድስ? ምናለበት እኔ ሳልወለድ እነሱ እየተዋደዱ ቢኖሩ?" ከዚ በላይ መቀጠል አልቻለም ሳግ ተናነቀው እኔም እስከመጨረሻው ልሰማው ብፈልግም ሲያልቅስ አልቻልኩም እንደ ህፃን ልጅ አቅፌ አባበልኩት "ይቅርታ የኔዋ" አለኝ እንባውን ጠራረገ እና ቀጠለ ትከሻው ላይ ደገፍ ብዬ ተቀመጥኩ "እናቴ ለዶክተሩ ምን አለችው መሰለሽ? "ዶክተር እኔ አሁንም ሆነ ነገ መሞቻዬን የምጠባበቅ ሰው ነኝ ወደውጭ ሀገር ሄጄ እንድታከም ብትፅፉልኝም ባሌም ሆነ ቤተሰቦቼ ያንን የማድረግ አቅም ስለሌላቸው ቢያንስ ለምስኪኑ ባሌ እኔን ማስታወሻ አንድ ልጅ ልስጠው፤ እኔ በነፍሴ ልዋጭ ለባሌ ልጅ ልሰጠው ፍቃደኛ ነኝ ወደ አባቴ ዞራ አደራ ልጄን!አደራ ማስታወሻዬን፤ አደራ ቃሌን" አለችው ተቃቅፈው አለቀሱ ዶክተሩም ተከትሏቸው አለቀሰ አባቴ ሚስቱን እንደሚያጣ ሲያስብ ሀዘኑ ልክ አጣበት እያለቀሰ ልጃቸውን እንደሚንከባከብ ቃል ገባላት ...ይሄ በተፈጠረ በሶስተኛው ሳምንት እናቴ ምጧ መጣ ሀሙስ ለሊት ለእናቴ ቤተሰቦች፤ ለአባቴ እህት፤ ለአባቴ፤ የማግኘት እና የማጣት ለሊት ነበረች። ጨረቃ ቦታዋን ለፀሀይ ልታስረክብ ጥቂት ሲቀራት፤ እናቴ ከተኛችበት ክፍል የልጅ ለቅሶ ተሰማ፤ ይደሰቱ ወይስ ይከፉ? ዶክተሮቹ መሯሯጥ ጀመሩ አንዱ ወደውስጥ አንዱወደ ውጭ አባቴ ስለሚስቱ ቢጠይቃቸውም የሰጡት መልስ ቢኖር "እንኳን ደስ አለህ ወንድ ልጅ ተወልዶልሀል" ብቻ ነበር ሚስቴስ? እናቴስ? ህይወቴስ?ምን ሆነች እንደፈራሁት ጥላኝ ሄደች? ሀሳቧ ሞላላት? እንደምትሞት ዶክተሮቹ ስለነገሩት የልጁን ድምፅ ሲሰማ ሚስቱ ለልጇ ትንፋሿን ሰጥታ እሷ እንዳሸለበች ነው ያሰበው። አዎ ሲሁ እናቴ ህይወቷን ለኔ ልዋጭ ሰጥታ እሷ አሸልባለች ለኔ ህይወቷን ሰጥታ እሷ ሄዳለች ....... አባቴ ለብዙ ጊዜ ሰብር ማድረግ አቅቶት ነበር ማን እንዳረጋጋው ታውቂያለሽ? ያኔ ለሚፈጠረው ነገር ሀላፊነቱን ውሰዱ ብሎ ያስፈረማቸው በፍቅራቸው ቀንቶ ያለቀሰው ዶክተር ነበር፤ እናቴ በሞተች በ3ወሩ ያ ዶክተር አባቴ ጋር መቶ የዛን እለት የነበረውን ክስተት አስታወሰው፤ "እውነት አንተ ሱመያን ምትወዳት ከሆነ ቃልህን ጠብቅላት አትርሳ ህይወቷን አሳልፋ የሰጠችህ እሷን የምታስታውስበትን ልጅ ለመስጠት ብላ ነው"... ታውቂያለሽ ሲሁ ይሄ ዶክተር እኛ ቤት ከመምጣቱ በፊት አባቴ እኔን ማየት አይፈልግም ነበር፤ እህቱ ነበረች ምትንከባከበኝ፤ ሌላ ቤተሰብ ደሞ የላቸውም እናት እና አባታቸውን በልጅነታቸው ነበር ያጡት፤ የእናቴ ቤተሰቦች ልጃችንን አንተ ነህ የገደልካት ብለው ሊያዩት እንኳ አይፈልጉም ነበር።...ከዛ ቀን ቡሀላ ግን አባቴ እኔን እንጂ ሌላውን ሁሉ ተወዉ፤ ምፈልገው ነገር እንዳይጎድልብኝ ከሰው እንዳላንስበት በጣም ታታሪ ሰራተኛ ሆነ፤ እሱ እየሰራ ይመጣል አክስቴ ፋጡማ እኔን ትንከባከበኛለች።
ቀናት በቀናት ተተክቶ፤ ወራት አልፈው፤ አመታት ተቆጥረው፤ እኔም አስራአምስተኛ አመቴ ላይ ደርሻለው፤ የጉርምስና ዘመን፤ አባቴ በተርቢያ ስለሆነ ያሳደገኝ እንደሌሎች ልጆች አስቸጋሪ ጎረምስክ የምባል አልነበርኩም፤ በዛ አመት ነበር በህይወቴ ለመጀመርያ ጊዜ የሀዘንን ትርጉም ያወኩት። እናቴን ያስረሳችኝ፤ እናቴ እንደሆነች ማውቀውን፤ውዷን አክስቴን ሞት ወሰደብኝ፤ እኔና አባቴ ብቻ ቀረን አባቴ ሀዘኑ ቢበረታበትም እኔን ለማፅናናት ሲል ዋጥ አድርጎት ነበር፤
አንድ ቀን ምን ሆነ መሰለሽ? ከት/ት ቤት ስመጣ በሩ ገርበብ ብሎ ተከፍቶ ነበር፤ ሌላ ቀን ከት/ት ስመጣ የምጠብቀኝ አክስቴ ነበረች፤ እሷ ከሞተች ቡሀላ ቤቱ ዝግ ነበር ሚሆነው፤ ሲሁዬ የለመድሽውን ሰው ከለመድሽበት ቦታ ማጣት ምን ያህል እንደሚያም መልመድ ከብዶኝ ነበር፤ ከሆነ ጊዜ ቡሀላ አባቴ ተመላላሽ ሰራተኛ ቀጥሯል ግን እሷ ምትመጣው በሳምንት 3 ቀን ነው ሰኞ እሮብ ቅዳሜ ነው ዛሬ ደሞ አርብ ነው መታ ቤቱን አፅድታ አልጋችንን አነጣጥፋ ምግብ ሰርታ ፍሪጅ ውስጥ አስገብታልን ሚታጠብ ልብስ ካለ አጥባ ትሄዳለች አንዳንዴም እኔ እስክመጣ ጠበቃ መክሰስ አብልታኝ አጫውታኝ ትሄዳለች። ዘይነብ ነበር ስሟ በጣም ጥሩ ሴት ናት፤ ዛሬ ግን ምንም ልትሰራ አትመጣም እኛ ቤት ማትመጣ ቀን ሌላ ቦታ ትሰራለች ሁለት ልጆች አሏት ሀያት እና ኢምራን ይባላሉ። አባታቸው ጥሏቸው ስለሄደ እሷ ናት ልጆቿን ምታሳድገው፤ አባቴም ስለምታሳዝነው ከደሞዟ ላይ ጨምሮ ነው ሚሰጣት፤ ሀያትና ኢምራንንም እኛ ቤት ይዛቸው ትመጣለች አብረን እናጠናለን እንጫወታለን። ኢምሩ ገና 8 አመቱ ሲሆን ሀዩ ደሞ 13 አመቷ ነው፤ ደሞ ስታምር! ልክ አባቴ ለእናቴ ሚጠቀማቸውን ቃላት እኔም ለሀዩ እጠቀመው ነበር፤ እኛ ቤት ብዙ ጊዜ ሚመጡት ቅዳሜ እና እሁድ ነበር፤ አቤት እነሱ የመጡ ቀን ደስታዬ! አባቴም ይህንን ስለሚያውቅ ሁሌ ስትመጪ አምጪያቸው ይላቸው ነበር፤ ዛሬ ግን አርብ ነው ቢመጡም በዚ ሰዐት አይመጡም አርብ አርብት/ት ቤታቸው ጥናት ስላለ ያመሻሉ፤ አባቴም ቢሆን ከስራ ማታ ነው ሚገባው፤ እና በሩ ለምን ተከፈተ? ልቤ እየፈራ ወደ በሩ ተጠጋው.......
ክፍል አስራስምንት ይቀጥላል.......

እብዱ ደራሲ ክፍል አስራስምንት
✍️በመغፊራ ቢንት ፉላን
ገርበብ ያለውን በር ከፍቼ ስገባ ከአባቴ መኝታ ቤት ውስጥ የለቅሶ ድምፅ ተሰማኝ፤ የክፍሉን በር እጀታ ዝቅ አድርጌ የክፍሉን በር ከፍቼ ገባው፤ አባቴ የፎቶ አልበም አቅፎ በጉልበቱ በርከክ ብሎ ይንሰቀሰቃል፤ ሌላ ቀን ከምመጣበት ሰዐት ቀደም ብዬ ስለሆነ የመጣሁት ሲያየኝ ደነገጠ፤ የያዘውን አልበም ወደአልጋው ላይ ወርውሮ እየሮጠ መቶ ተጠመጠመብኝ "ምን ሆነህ ነው? ለምንድነው በዚ ሰዐት ከት/ት የመጣሀው?" ስለደነገጠ ከአይኑ ሚወርደው እንባ ሁላ በሰከንዶች ደረቁ፤ አባቴን አረጋግቼ ት/ት ቤታችን ስብሰባ ስለሆነ ጥናት የለም ብለው እንደለቀቁን ነገርኩት አላመነኝም ት/ት ደውሎ አረጋገጠ። "ታውቂያለሽ ሲሁ አባቴ ለኔ እናቴም እህቴም ወንድሜም ዘመዴም ሁሉ ነገሬ ነው። እናት ለልጇ ከምትሳሳለት በላይ፤ እሱ ለኔ ይሳሳልኝ ነበር፤ ከት/ት ቤት እስክመጣ እንኳን ይጨንቀዋል፤ የት/ት ቤት አስተማሪዎቼ ሁላ በጣም ነው ሚገረሙበት፤ በቀን በትንሹ ሶስት ጊዜ ደውሎ ስለደህንነቴ፣ ምግብ እንደበላው ያረጋግጥ ነበር፤ አባቴ ሲያለቅስ ስላየሁት ደነገጠ "ዩኒፎርምህን ቀይረህ ና በጊዜ ከመጣህማ አሪፍ መክሰስ ነው ምጋብዝህ፤ ሊያረሳሳኝ እንደሆነ ገብቶኛል፤ እኔ ግን የሚያለቅስበትን ምክንያት ለማወቅ ቆርጫለው። አባቴን እጁን ይዤ አጠገቡ ያለው ወንበር ላይ ቁጭ አደረኩት "የኔ አባት አንተ ለኔ አለሜ ነህ፤ አላህ ከሰጡኝ ስጦታዎች ሁሉ አንተ በጣም የላክ ነህ፤ አሁን ደሞ ኮ ትልቅ ልጅ ሆኜልሀለው፤ አውቃለው እናቴ ከሞተች በዉሀላ እኔን እንዳይከፋኝ ህመምህን እየደበክ እንደሆነ፤ ከዚ ቡሀላ ግን በቃ ደስታህንም ሀዘንህንም የመካፈል ግዴታ አለብኝ" አልኩት ፍቃደኛ ባይሆንም ግን በግድ እንዲነግረኝ አደረኩት። ያኔ ነው አሁን እነ ላንቺ የነገርኩሽን ነገር ሁሉ አባቴ የነገረኝ ምወዳት ፋጢማ አክስቴ እንጂ እናቴ አለመሆኗን ያወኩት ያኔ ነው፤ አስራአምስት አመት ሙሉ እናቴ እንደሆነች የማውቃት ሴት እናትህ አደለችም ብሎ መናገር ምን ይሉታል ቆይ? ለጊዜው ውስጤን ማሳመን ቢከብደኝም እየቆየ ግን አባቴ እንደዛ የሚያሞግሳትን እናቴን የማየት ጉጉቴ ከፍ አለ፤ ግን የውሀ ሽታ ሆነችብኝ ... እናም ሲሁዬ ከዛ ቡሀላ እኔና አባቴ አባት እና ልጅ ብቻ ሳይሆን በጣም ሚዋደዱ ጎደኛሞች የሚያስቀኑ ወንድማማቿች ሆንን እልሻለው። እሺ ልቀጥል ወይስ ሌላ ቀን ይሁንልሽ ? ስልኬን ሳብ አድርጌ ሰዐቴን ተመለከትኩኝ ገና 9:05 ነው ስለዚህ ገና ነው ያው እሁድ አይደል ቀኑ እንደዚ በቀላሉ አያልቅም፤ "አንተ ካልደከመህ እኔ አንተን መስማቱ አይደክመኝም" "እኔም ለሚስቴ ማውራት አይሰለችኝም እኮ" ብሎ ግንባሬን ሳም አደረገኝና ቀጠለ
"እናም የኔዋ ህይወት በኔና በአባቴ በኩል ይበልጥ እየጣፈጠች አያጓጓች ቀጥላለች፤እኔም ከአባቴ እሱም ከኔ ሌላ አልን ፤አባቴ ለኔ ብቻ አነበረም አባት የነበረው የዘይነብን ልጆች ኢምሩን እና ሀዩ በጣም ነበር ሚንከባከባቸው፤ እነሱም ከነበሩበት ቤት ለቀው እኛ ግቢ ውስጥ አባቴ ሁለት ክፍል ቤት ሰቷቸው እየኖሩ ነው። የነሀዩ እናት የሌላውን ቤት ስራ ትታው ለኛ ቤት ብቻ መስራት ጀምራለች፤ እኛም ብንሆን እንደሰራተኛችን አናያትም፤ አባቴ ሁሌም ነበር ሚያስጠነቅቀኝ "እኔም ብሆን የነሀዩ እናት ስለሆነች የኔም እናት ናት" እለው ነበር፤ ደሞ ኮ እሷን ባስከፋት ሀዩ ታዝንብኛለች ሀዩ ደሞ አይደለም ሊከፋት እየሳቀች እንኳን እንባዋ ከአይኗ ሲወርድ ይከፋኛል ስለዚህ ለአባቴ ብዬ ሳይሆን ለሀዩ፣ለፍቅሬ ለኔሴት፣ ለየዋኋ፣ ለቆንጅየዋ፣ ለልእልቷ፣ ስል ነበር ወ/ሮ ዘይነብን ምንከባከባት" ውስጤ በቅናት ሲቃጠል ይታወቀኛል፤ ማሂር መናደዴን እንዳያውቅ ከአይኑ ለመደበቅ መጀመርያ እንዳደረኩት እግሩ ላይ ጋደም አልኩኝ "አላህ ግን መርሳትን ባይሰጥን ምን ነበር ምንሆነው? የኔና ሀዩ ግንኙነት እኮ ጣም የጠበቀ ነበር ከት/ት ቤት ስንመጣ አንድላይ፤ ምግብ ምንበላው አንድ ላይ፤ በቃ ሁሉ ነገራችን አንድላይ ነበር፤ ሱቅ እንኳን ስንሄድ አንድ ላይ ነበር ምንሄደው አይ ሀያቲ! እኔኮ ከሀዩ ጋር ፍቅር እንደያዘኝ ሳላውቅ ነው በፍቅር ክንፍ ያልኩት ሶስት አመት ሙሉ እንዳፈቀርኳት ሳይሆን እንደምወዳት ብቻ ነበር የማውቀው። ሀዩን እንዳፈቀርኳት ያወኩት የዩኒቨርስቲ ውጤት መቶ አ.አ ደርሶኝ ስመጣ ነው፤ ሲሁ ቤተሰቦቼን መለየቱ ለኔ በጣም ከባድ ነበር፤ በተለይ እሷን የመጀመርያ መንፈቀአመት ላይ ነበር ሁሉንም ነገር ተረዳሁት። ሲሁ አባቴ ጓደኛዬ ነው ብዬሽ የለ? ለእረፍት ወደ ባህርዳር ስመለስ ለአባቴ ሁሉንም ነገር ነገርኩት፤ አባቴ ደስተኛ ነበር የሆነው ሀዩን በጣም ነው ሚወዳት ደሞ በደንብ ስለሚያውቃት ምንም ቅር አላለውም ነበር "ግን እሷ እሺ ካለችህ ምታገባት የዩኒቨርስቲ ት/ት ከጨርስክ ቡሀላ ነው እኔ ለዘይነብ ነግራታለው አንተ ለሀያት ትነግራታለህ" ብሎኝ ተስማማንና በተባባልነው መሰረት ሀዩ ከት/ት ቤት ስትመጣ ጠብቄ ወክ እናድርግ ብያት ተያይዘን ወተን ሁሉንም ነገር ነገርኳት። ሲሁ ሀዩ ኮ መናገር ፈርታ ነው እንጂ እሷም ከኔበላይ ታፈቅረኛለች፤ በቃ ምን አለፋሽ ከዛ ቡሀላ እኔና ሀዩ መተፋፋፈር፣ መነፋፈቅ፣ 24ሰዐት በስልክ ማውራት ጀመርን ክንፍ አልንልሽ፤ እኔ የሶስተኛ አመት ተማሪ እያለው ሀዩ ደሞ የሁለተኛ አመት ተማሪ እያለች የሀዩ እናት በጣም ታመመች የዛን ጊዜ ት/ት ትቼ አብሬያት ብሆን መሆን ፈልጌ ቢሆንም ሀዩና አባቴ ት/ት ማቋረጥ ስለሌለብኝ ከለከሉኝ። ወ/ሮ ዘይነብ በየሰው ቤቱ እየሄደች የምትሰራው ስራ በጣም ጓድቷት ነበር ግን አልሃምዱሊላህ ከቤት ባትወጣም ቶሎ ተሻላት። አባቴ ሚስቴን በብር ምክንያት ነው ያጣሁት ከዚ ቡሀላ ማንም ሰው በብር ሲቀጣ ማየት አልፈልግም ብሎ ቆርጦ ተነስቶ ስለነበረ በጊዜው የሁለት ድርጅት ባለቤት ሆኖ የቲሞችን ይረዳ ነበር። ሲሁ እዚች ምድር ላይ እንደኔ እድለኛ የለም፤ በጣም ማፈቅራት ምታፈቅረኝ፤ ለኔ የሚኖር አባት፤ እንደ ኢምሩ አይነት ቅመም ወንድም፤ እንደ ወ/ሮ ዘይነብ አይነት እናት አላህ ሰቶኛል። በቃ በጣም ደስተኛ ነበርኩ በት/ት ማልደራደር ጠንካራ የኢንጂነሪንግ ተማሪ ነበርኩ፤ ሀዩም ብትሆን የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ነበረች እሷ ግን ዩኒቨርስቲ አልሄደችም እዛው ባህርዳር ነበር ምትማረው ሁለታችንም የማዕረግ ተማሪ ለመሆን ነበር ምንማረው ...... ህይወት እያጓጓች የአባቴ ካፒታል ቀን በቀን እየጨመረ፤ የኔና የሀዩ የትዳር መምሰረቻ እና መመረቂያችን ጊዜ ደረሰ፤ እኔ አምስት አመቴን ጨርሼ ሀዩ አራት አመቷን ጨርሳ አባቴና ዘይነብ ለምርቃት እና ለሰርግ ሽርጉድ እያሉ ነው፤ ሀዩ የግል ዩኒቨርስቲ ስለነበር ምትማረው እኔ 1 ሳምንት ቀድሜያት ነበር ምመረቀው፤ አባቴ ሰርጋችንንም ምርቃታችንንም አንድ ላይ በአንድ ቀን ማድረግ ስለፈለገ ባህርዳር ላይ አለ የተባለውን አዳራሽ ተከራይቷል፤ ልብሱንም አሰርቶ ቀኑን እየተጠባበቀ ነው፤ ኢምሩም ለኔ ሚዜ ሊሆን ከሁለት ጊቢ ከማውቃቸው ከመሀመድ እና ከአብዱሰላም ጋር ሱፍ አሰፍቷል፤ የሀዩ እናትም አባዬ አለ የተባለ ሀበሻ ቀሚስ አሰርቷላት ቀኑን በጉጉት እየጠበቀች ነው፤ ሀዩም ቬሎዋንም የምርቃት ልብሷን አዘጋጅታለች እኔም ሁለት ሱፌን አሰፍቼ በጉጉት እየጠበኩ ነው፤ ደሞ በማዕረግ ነው ምመረቀው ግን ለማንም አያውቅም ሰርፕራይዝ ላደርጋቸው ስለፈለኩ አልተናገርኩም ጓደኞቼንም ቢሆን አስጠንቅቄያቸዋለው። ምርቃቴ ቅዳሜ ነበር ጁመአ አባዬ እና ሀዩ አ.አ ስለሚገቡ አልጋ ይዤላቸው እየጠበኮቸው ነበር፤ ሀዩ መንገዱን እያየ