𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
13.3K subscribers
200 photos
114 videos
33 files
735 links
ስለ ቴክኖሎጂ እና እስልምና በቻልኩት አቅም አሳዉቃለሁ።
በነፃ ለመማር (Frontend web development)
👉 t.me/abukiweb/615
አላማችን:
👉  t.me/abukiweb/88

ኮምፒዉተር ለመግዛት
👉 t.me/Abuki_Computer
ዌብሳይት ለማሰራት፡
👉 t.me/abukiweb/583
ለጥያቄና ለአስተያየት
👉 @Abukiweb_bot
Download Telegram
ነፃ‼️‼️  የትምህር  እድል ስለ ቴክኖሎጂ በአቡኪ  ለሁሉም ‼️

Aselam aleykum werahmwtulahi weberekatuh

(ቴክኖሎጂን እንወቅ)

ዉድ እህትና ወንድሞች  ሰላማችሁ ባላችሁበት ይብዛ።

ሴቶች አረብ የምትንከራተቱና እዚህ ለታክሲ እና ባስ የምትጋፉ አላህ ከዚህ መንገላታት ይጠብቃቹ።
አላህ ወንዶችን አቅም ሰጥቶን በሀላል ያብቃቃቹ ።

የአሰሪ  ፊት  መከራ  የሆነባቹ እና ስራችሁ አስተማማኝ ያልሆነና   ስራችሁ መደገፍ ለምትፈልጉ  ወንድሞችም  ይህ ትምህርት ወሳኝ ነው ።

አላህ ያግዘኝ እና እኔ አንድ ሀሳብ አስቤያለሁ።



ባላችሁ ክፍት ግዜ ስልካቹን እና ኮምፒውተራቹ በመጠቀም ብቻ እቤት ሆናችሁ ተምራቹ ስራ በኦንላይ  እንድትሰሩ  አስቤያለሁ።

የምትማሩት አንደኛ
👇👇👇

Full Stack Web     Development


እና ሌሎችም ምንም የትምህርት ደረጃ ሳይገድባቹ በአላህ ፍቃድ ሁሉንም ትማራላቹ።

አላህ በሰጠኝ እውቀት ሁሉም በነፃ ነው።

(ትምህርቱም  የተዘጋጁ ኮርሶችን ከዩትብ እና ከሌላ ዌብሳይቶች በማሰባሰብ ቀለል ባለና ለጀማሪዎች በማይከብድ መልኩ ልንሰጣቹ ወደናል።)

(ልብ በሉ ከፍላቹ ለመማር  25000-50000  ይፈልጋል

ብቻችሁ ከጀመራችሁ በመሰላቸትና ቅደም ተከተል ጠብቆ ለመማር ያስቸግራቹና ትተውታላቹ።
ከኛ ጋር ከሆነ ኢንሻአላህ ከጎናችሁ ሆነን እያማከራችሁን ትምህርቱ ትጨርሳላቹ)

(ኮርሶችን ለመውሰድ የወንድማችሁን አቡኪ   ቴክ ቻናል ተቀላቀሉ(ከኡስታዞችና  ከአዋቂዎች በመመካከር የተከፈተ)
ይህን

👇👇  
https://t.me/abukiweb

  https://t.me/abukiweb


https://t.me/abukiweb

የቴሌግራም አድራሻ በመቀላቀል የኮርሱን ተካፋይ ይሁኑ። 
👍8918🥰6🤔5😁1😢1
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
ነፃ‼️‼️  የትምህር  እድል ስለ ቴክኖሎጂ በአቡኪ  ለሁሉም ‼️ Aselam aleykum werahmwtulahi weberekatuh (ቴክኖሎጂን እንወቅ) ዉድ እህትና ወንድሞች  ሰላማችሁ ባላችሁበት ይብዛ። ሴቶች አረብ የምትንከራተቱና እዚህ ለታክሲ እና ባስ የምትጋፉ አላህ ከዚህ መንገላታት ይጠብቃቹ። አላህ ወንዶችን አቅም ሰጥቶን በሀላል ያብቃቃቹ ። የአሰሪ  ፊት  መከራ  የሆነባቹ እና ስራችሁ…

وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا‼️

ይህ ላንተም ላንቺም ለሁሉም የአለም ህዝብ የሚሆን አያ ነው።
አዉ ከኬጅ ተነስቶ እስከ አስራሁለትተኛ ክፍል ተምሮ ከዛም   ኮሌጅ ወይም ዩንቨርሲት ገብቶ  አምስት አመት በሚፈልገውም በማይፈልገውም ፊልድ ገብቶ ተምሮ የወጣ ተማሪ ስራ ማጣት ማለት በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው።

በተለይም ስራ ያጣኸው በአለባበስህና (ኒቃብ /ሂጃብ) በሀይማኖታዊ ትዛዞች(ፂም) ሲሆን የባሰ ያማል።
وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا
ይህን አያ በትክክል ለናንተ ነው።
መዉጫ አላህ እራሱ ያበጅልናል።

እኔ አላህ በፈቀደው የቻልኩት ጥረት አደርጋለሁ።
ትምህርቱ እንዲመቻችላቹ።
ለዌብ ዴቨሎፕመንቱ (evangadi tech (Adugna ) በማነጋገር ከዩትዩብና ሌሎች ዌብሳይቶች በተጨማሪ አጋዥ በማምጣት እጨምራለሁ። )
ደግሞ በጣም ብዙ ወንድምና  እህቶች ባላቸው እስኪል ሊያግዙኝ  እና ከጎኔ እንደሚሆኑ ቃል ገብተውልኛል አልሀምዱሊላህ።

በመቀጠል መቼ ነው የምንጀምረው?
ለሚለው ጥያቄ ወንድም እህቶች ሁሉም ፍላጎቱ ያላቸው ወደዚህ እስኪመጡ ታገሱኝ አሳውቃለሁ።

(በጣም የቸኮላችሁ በክፍያ የሚያስተምር ፈልጋቹ ቀጥሉ) ።

ከኔ ልትረዱልኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር
እንግሊዘኛ እና አማርኛ ኮርሶችን በነፃ እሰጣቹዋለሁ ከዛም በደንብ ሲኪል ከያዛችሁ ቦሀላ teem  ትፈጥሩና ወደ ስራው አለም ትቀላቀላቹ።
አንድ  የምነግራችሁ ነገር ቢኖር አንዴ እስኪሉን ከያዛችሁ ስራ አታጡም በአላህ ፍቃድ።

(ወደ ስራ አለም እንዴት እንደምንገባ  ባወኩት አሳዉቃለሁ👇)
(ለወንድም እህቶች አድርሱልኝ ጀዛኩምላህ ኸይረን)

ይቀጥላል………


ማሳሰቢያ‼️ በተለያየ ቦታ  የevangadi  course እንሸጣለን ከሚሉ ልጆች እንዳትገዙ።
ያለ እሱ ፍቃድ ከሆነ ሀራም ነው መሸጡም መግዛቱም  ‼️

የምታርሙኝ ነገር ካለ
👇👇👇
@abuki211



የቴሌግራም ቻናል
=
https://t.me/abukiweb
👍878👌6🥰3🤔2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጥቆማ‼️
Next class will start on Dec 5th, 2024 - (Full Stack Application Development - MERN Stack)

ዉድ ወንድምና እህቶች የኢቫንጋዲ ኮርሶ ስኮላር እድሉ ሞክሩ‼️

ግልፅ እንዲሆንላቹ  እስከመጨረሻዉ እዩት።
የ 1800$  ትምህርት ነው ስኮላር ካሸነፋችሁ በነፃ የሚሰጣችሁ።

በችኮላ የማይሆን ነገር ፅፋችሀ እንዳታስገቡ። ጥርት ያለና በደንብ ግልፅ የተብራራ ፅሁፍ ፅፋች ላኩ‼️

ዩትዩብ  app ካላችሁ ደሞ በዚ ገብታችሁ እዩት።

https://youtu.be/ERHq5wfm57I?si=PHcOYw8w0A2yEIZC

ከላይ ያለው ዩትዩብ ለሌላቸ እንዲሆን ብዬ ነው።

የቴሌግራም ቻናል
=
https://t.me/abukiweb
👍28🫡1
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️ pinned «ነፃ‼️‼️  የትምህር  እድል ስለ ቴክኖሎጂ በአቡኪ  ለሁሉም ‼️ Aselam aleykum werahmwtulahi weberekatuh (ቴክኖሎጂን እንወቅ) ዉድ እህትና ወንድሞች  ሰላማችሁ ባላችሁበት ይብዛ። ሴቶች አረብ የምትንከራተቱና እዚህ ለታክሲ እና ባስ የምትጋፉ አላህ ከዚህ መንገላታት ይጠብቃቹ። አላህ ወንዶችን አቅም ሰጥቶን በሀላል ያብቃቃቹ ። የአሰሪ  ፊት  መከራ  የሆነባቹ እና ስራችሁ…»
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
ጥቆማ‼️ Next class will start on Dec 5th, 2024 - (Full Stack Application Development - MERN Stack) ዉድ ወንድምና እህቶች የኢቫንጋዲ ኮርሶ ስኮላር እድሉ ሞክሩ‼️ ግልፅ እንዲሆንላቹ  እስከመጨረሻዉ እዩት። የ 1800$  ትምህርት ነው ስኮላር ካሸነፋችሁ በነፃ የሚሰጣችሁ። በችኮላ የማይሆን ነገር ፅፋችሀ እንዳታስገቡ። ጥርት ያለና በደንብ ግልፅ…
ወንድምና እህቶች ይህን አስተካክላቹህ  በመላክ አግዙኝ ።

online
የመማር እድሉ  ባታገኙ ቢያንስ  በጣም ምርጥ የሆኑ ቪድዮዎችና አጋዥ ፅሁፎች ይሰጣችኃል በነፃ  ለዛውም ቅደም ተከተሉ የጠበቀ።
በፊት የሚያግዛችሁ ላይኖር ይችል ነበር አሁን እኮ ከአላህ ቦኃላ እኛ አለን።ስለዚህ እባካችሁ Full Stack Web Dev… የመማር ፍላጎት ያላችሁ ሁላችሁም ላኩ።

አላማችሁ ለማሳካት ከአላህ ቦኃላ ትንሽዪ  ሰበብ አድርሱ ለጀመርነው
አብረን የመሄድ ጉዞ በእጅጉ ያግዘናል።

(pc የለኝም ብላችሁ መላክ እንዳትተውት )

ስለናንተ የሚገልፅ ፅሁፍ ፅድት አድርጋችሁ ላኩለት።

ከከበዳችሁ ጠይቁኝ  መመሪያውና አፃፃፉን እሰጣችኃለሁ።

@abuki211

[ይችን ችግራችሁ ለማለፍ ከናንተ የሚጠበቀው
ዱዓ ፣ሰበብ ማድረስ እና በአላህ ተወክሎ በትዕግስት መኖር ነው።]

የቴሌግራም ቻናል
=
https://t.me/abukiweb
👍625😢3🥰1🏆1
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️ pinned «፡ وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا‼️ ይህ ላንተም ላንቺም ለሁሉም የአለም ህዝብ የሚሆን አያ ነው። አዉ ከኬጅ ተነስቶ እስከ አስራሁለትተኛ ክፍል ተምሮ ከዛም   ኮሌጅ ወይም ዩንቨርሲት ገብቶ  አምስት አመት በሚፈልገውም በማይፈልገውም ፊልድ ገብቶ ተምሮ የወጣ ተማሪ ስራ ማጣት ማለት በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው። በተለይም ስራ ያጣኸው በአለባበስህና (ኒቃብ /ሂጃብ)…»
አላማችን ባጭሩ🛑🛑

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاتة


በመጀመሪያ አላህ ሁሉም እህት ወንድሞች  የተስተካከለ እና ያማረ ህይወት እንዲያኖራቸውና መጨረሻቸው አሳምሮ ጀነተል ፊርዶስ እንዲወፍቃቸው  እለምነዋለሁ።

በመቀጠል ሁላችሁም እንድትገነዘቡትና እንድረዱት የቻናሌን አላማ በትንሹ ላሳውቃችሁ።
1 በኢኮኖሚ ምክንያት  ከቴክኖሎጂው የራቁ ወንድም እህቶች በነፃ ቴክ ማስተዋወቅ ነው።
ማለትም፦
ቴክኖሎጂ እንዴት እንጠቀም?
ቴክኖሎጂ እንዴት ከዲን ጋር እናስኪድ?
ቴክኖሎጂ ለልጆቻችን በምን መልኩ እናስተምር?
ቴክኖሎጂ እንዴት ገንዘብ እንስራበት?
እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች መልስ እንድታገኙበት እጥራለሁ።

2 ሴቶች፦
ሴቶች በተለይም በኒቃብና በሂጃብ ምክንያት ከትምህርታቸው የራቁ ተመርቀውም ስራ ያላገኙ
ስራቸው እኽቲላጥ የበዛበት እና ከነሱ ጋር አብሮ የማይሄድ ስራ የሚሰሩ በአጠቃላይ  መፍትሄ ለማበጀት ትልቅ ህልምና ሀሳብ አለኝ።
፡እንዴት ሳይሳቀቁ ይማሩ?
፡እንዴት ለነሱ ሚሆን ትምህርት ያግኙ?
እነዚህና የመሳሰሉ እህቶቻችን ችግሮች ከናንተ ወንድም እህቶች ጋር በመነጋገር መፍትሄ መፈለግ።
[ስፖንሰር በማፈላለግ ከትምህርታቸው የተገለሉ እህቶች programming እዲማሩ አደርጋለሁ   ኢንሻአላህ እየሞከርኩም ነው።]

3 ትምህርታቸው ጨርሰው  ተመርቀው ስራ ያልተመቻቸላቸው ወንድምና እህቶች ወደስራው አለም እንዲገቡ ቡድን ፈጥረን በተፈጠረላቸው ቡድን በተመረቁበት ስራ ተመድበው   እርስበርስ ተመካክሮ መፍትሄ ለማበጀት እንጥራለን።
4  የተለያዩ ውድ ኡስታዞቻችን ወደ ቻናሉ በመጋበዝ ከቴክኖሎጂ ያለን ቅርርብ ምን መሆን እንዳለበት ዳዕዋ ማድረግ።

5  ሀላልና አዋጭ የሆኑ የቴክ ትምህርቶች እና ስራዎች  በመጠቆም እድሉን ለወንድም እህቶች  ማመቻቸት ።

እና ሌሎችም ………(ሁሉም ሚሳካው በአላህ ፍቃድ ነው)

ሀሳቤ ከተመቻችሁ👍

የምጨምሩልኝ ሀሳብ ካለ በውስጥ ጠቁሙኝ።

በአንድነት ችግሮቻችን እንፈታለን።

በመጨረሻም  ታገሱ በዱዓም በርቱ።

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ 

አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና ታገሱ።

ለሌሎች ይጠቅማል ካላችሁ ሼር‼️

የቴሌግራም አድራሻ
=
https://t.me/abukiweb
👍36921👏14🏆6🕊4👌2🆒1
በምችለዉ ሰበብ ማድረስ ነው።‼️

የእናንተ ዱዓ አይለየን።

በተለይም ዉጭ ያሉ ስራ ያጡ እህቶች አላህ ይሁናቸው። በዱዓ በርቱልን።
👍60🥰4
የብዙ ወንድም እህቶች ጥያቄ⁉️

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاتة

ስለ ትምህርቱ 👇

1: freelancing (እንዴነው ቤት ሆነን መስራት የምንችለው?)

2  እንግሊዘኛ አላውቅም እንዴት ነው  መማር ምችለው?

3  መቼ ነው መማር ምንጀምረው?

4  እንዴት ነው ምንማረው?

5  ምንድነው ምንማረው?

6  በስልክ መማር ይቻላል?

7  ዩንቨርሲቲ ላይ ያለን ተማሪዎች ምን ትመክረናለህ?

8 ተመርቀን ስራ የሌለን ብዙ ነን እንዴት ነው ስራ ምናገኘው?


9  በጣም ብዙ ጥያቄዎች ተጠይቀናል የተመለሰላቹ 👍
አሳዩን።

የነዚህና ሌሎች ወሳኝ ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ በዚህ ሳምንት ጠብቁን።
 
[( فَاسْأَلُوا أَهْلَ الذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ   )]

በተረፈ የፈለጋቹትን ጉዳይ ጠይቁን አማክሩን አላህ ከፈቀደ እንመልሳለን እኛም ካላወቅነው የእውቀት ባለቤቶች እንጠይቅላቹዋለን። በቻላችሁት ቁጥብና ግልፅ አድርጉት።

ጎን ለጎን ሆነን ብዙ እንጓዛለን በአላህ ፍቃድ።

ሼር በማድረግ ለወንድም እህቶች አድርሱልን።

https://t.me/abukiweb
👍110🥰16
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
እኔ አላህ በፈቀደው የቻልኩት ጥረት አደርጋለሁ።
ትምህርቱ እንዲመቻችላቹ።
ለዌብ ዴቨሎፕመንቱ (evangadi tech (Adugna ) በማነጋገር ከዩትዩብና ሌሎች ዌብሳይቶች በተጨማሪ አጋዥ በማምጣት እጨምራለሁ። )
አብረን እንብላ ማለቴ

አልተረዳቹኝም ማለት ነው በቃ ⁉️

አንድ ሰው ወንድም እህቱን ለመርዳት  ግዴታ ሀብታም መሆን የለበትም።
መቶ ብር ያለው ሰው ባለችዉ ብር ላይ ያለኝን ላካፍል  ቢል ማንም ድሀ ነህና አትስጥ የሚለው የለም።

ልክ እንደዛው ኑ በነፃ የቴክኖሎጂዉ መንገድ ላሳያችሁ ስላችሁ  ግዴታ expert ሰለሆንኩ ሳይሆን ያለኝን  ላካፍላችሁ ማለቴ ነው‼️

በጣም አልፎ የሄደ ሰውማ ምናልባት ዞር ብሎም ላያያችሁ ይችላል‼️


ወላሂ ብዬ የምነግራችሁ ነገር ቢኖር   ይህንን ትምህርት  እራሳቸው በራሳቸው አስተምረው በወር ከ50 ሺብር እስከ ሁለት መቶ ሺ ብር የሚሰሩ ልጆች አውቃለሁ።አዉቃለሁ ለአንዳንዱ ብዙ ነው ለሌሎቻችሁ ትንሽ ገቢ ሊሆን ይችላል።

ግን ዝም ብሎ  በመቀመጥ ምንም ምናመጣው ነገር የለም።
ያለን እውቀት ለወንድሞችና ለእህቶች  እያካፈልን   አብረን መጓዝ ነው።

እኔ ያልኳችሁ  በደንብ ከተረዳችሁኝይ ሀሳብ አስተያየታችሁ ከሰጣችሁኝ ምንም ወደ ኃላ የሚያስቀረን ነገር የለም።
አንድ ላይ ከሆንማ  ገና ብዙ programmer እንፈጥራለን ከ 10,000 በላይ ኢንሻአላህ ።


አጭር እና ግልፅ አማርኛ ልንገራችሁ አምስት አመት ዩንቨርሲቲ ተማራችሁ በዉድ ብር  ከፍላችሁም ተማራችሁ ወይም ኢቫንጋዲ ተማራችሁ  የራሳችሁ ጥረት ካልጨመራቹበት ልፋት ብቻ ነው በፍፁም expert መሆን አትችሉም።

አንድ ላይ ስንሆን

ሁሉም  ተመካክረን  እናልፈዋለን።
ከዲናችን ሳንወጣ ሁሉም እናሳካዋለን በአላህ ፍቃድ


ተረዳችሁኝ⁉️
አዎ👍


የቴሌግራም ቻናል
||
https://t.me/abukiweb
👍199💯16🤔5🥰3
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
የብዙ ወንድም እህቶች ጥያቄ⁉️
መልስ‼️

4 & 5:  እንዴት ነው ምንማረው ? ምንድነው ምንማረው?

የምንማረው በቴሌግራም ሢሆን በዋናነት የኛ ስራ የሚሆነው ኮርሶቹን ቅደም ተከተላቸው በጠበቀ መልኩ ለናንተ በነፃ መስጠት ነው።
( ስፖንሰር ሲገኝ በአላህ ፍቃድ በአካልም እናስተምራለን በዱዓ አግዙን )
(የወንድና ሴት ግሩፕ እለየዋለሁ ለደህንነታቹ   ሲባል)

ትምህርቱ በአላህ ፍቃድ አንዴ አይደለም   አስተምረን  ምናቆመው ስለዚህ በዚህ ዙር የተመቻቸላችሁ  ትማራላችሁ ቀጣይም ስንጀምር ደግሞ አሁን ያልተመቻቸላቹህ   ትቀጥላላቹ።

እናንተ የሚመቻችላቹ ወቅት ትመርጣላቹህ ምዝገባው ሲጀምር።

ከብዙዎቹ በመጣልኝ አስተያየት የተለያየ ዘርፍ ከሚሆን አንዱ ላይ ወጥረን በመማር ልምዳችን ከፍ ማድረግ ነው።
ስለሆነም አሁን Abuki Tech ላይ ቪድዮዎችን ለመስጠት ያሰብነው  የ Full Stack Web Developemnt ነው።
(ፍላጎታችሁ   ሌላ ዘርፍ ካላችሁ ለናንተም ሙሉ ቪድዮ ይሰጣችኃል )

ሌላው ቪድዮ መስጠት ብቻ ሳይሆን ጥናት ፕሮግራም ተመቻችቶዋል  ምክንያቱ በጣም ብዙ ወንድምና እህቶች እናንተን ለማገዝ ፍቃደኛ ስለሆኑ።

አካሄዳችንም የሚሆነው
computer ምንድነው ?
እንዴት ነው የሚሰራው ?
ከሚሉ ጥያቄዎች በመጀመር
programming እንቀጥላለን።
html,
Css ,Bootstrap
Javascript እያልን እንቀጥላለን።

FREE

የሌሎችንም ጥያቄዎች መልስ እለቃለሁ በትዕግት  ጠብቁኝ።

ሼር በማድረግ አግዙን

የቴሌግራም ቻናል
=

https://t.me/abukiweb
👍142👌8👏3🤝3
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
የብዙ ወንድም እህቶች ጥያቄ⁉️
መልስ
1: freelancing (እንዴነው ቤት ሆነን መስራት የምንችለው?)


ማንም የኛ መልክ ግድ አይለውም
ማንም የኛን ቁመት አይመለከተውም
ማንም ብሄራችን አይጠይቅም
ማንም ዘመድ አይጠይቀንም
ማንም ማስያዣ የመንግስ ሰራተኛ አይጠይቀንም

ግን

ሁላቸውን አንድ ነገር ይጠይቁናል

ችሎታህን ወይም ልምድህ
ከዚህ በፊት ምን ሰርተሀል/ሰርተሻል?
ለዚህ መልስ ካለህ በርግጠኝነት ስራውን ትሰሩታላችሁ።

ምን ምንድነው ሚሰራው?
web Devlopment
App Developmet
Video Editing
Graphcis Disgning
Content Creating


በጣም በጣም ብዙ ሀላል የሆኑ ስራዎች አሉ ከኛ ችሎታ ብቻ ሚጠይቁ‼️

በተለይም በዚህ ወቅት ለሴቶች እምመክረው የonline freelancing ስራ ነው።



ፅድት ያለ Portfolio አዝጋጅተህ ስራህን ማመልከት ብቻ ነው።


የተወሰኑ አሪፍ freelancing Websitoch.ልጠቁማቹህ 

1: Upwork: upwork.com


2. Freelancer: freelancer.com


3. Fiverr: fiverr.com

4.LinkedIn: linkedin.com

5: የኢትዮጵያ👇👇👇afriworkamharic


ሼር በማድረግ ያግዙን🤝

የቴሌግራምቻናል
=
https://t.me/abukiweb
👍66👏6💯5
በዱንያ ስትኖር ‼️
መልካም ፍሬ ዝራ
መልካም ንግግርን አብዛ
መልካም አስተሳሰብ ይኑርህ

የዛራኸው ፍሬ ማንም ቢያጭደው መልካም እስከሆነ ድረስ

በዱንያም በአሄራም አትራፊ ነህ

[[فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ]]

የቴሌግራም ቻናል
||
https://t.me/abukiweb
👍49🏆5🆒1
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
የብዙ ወንድም እህቶች ጥያቄ⁉️
መልስ

ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ምን ትመክራለህ⁉️

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاتة


programming መማር  አይደለም ለዩንቨርሲት ተማሪ  ለማንኛውም ማህበረሰ የሚመከር የትምህርት ዘርፍ ነዉ በተለይ  በአሁኑ ግዜ።
ሴቶች በተለይ ትኩረት እንድትሰጡት እመክራለሁ።
ምክንያቱም ከተመረቃችሁ ቦኃላ ፈተናው እናንተ ላይ ስለሚጠና ነው።

ምንአልባት የገባችሁት አሪፍ ካምፓስ ከሆነ  ኮምፒዉተር  የማግኘት እድላችሁ ከፍ ስለሚል
በየትኛው ፊልድ ብትሆኑ Medicine; Engineering;Economics ; Law; Finance and Accounting
ወይም ሌላ ቢሆንም በተመቻቸላችሁ አጋጣሚ ተማሩ።

መማር ከጀመረችሁ በኃላ ግን‼️

1 : እዛዉ ግቢ ዉስጥ ቲም ፍጠሩ

2 : ምንግዜም ቢሆን ግዜያችሁ በማይጠቅሙ ነገሮች አታባክኑ።

3 : ጓደኛ ምረጡ በጣም ወሳኙ እንደዉም ይሄ ነው። መልካም ጓደኛ ለዱንያም ለአኼራ በጣም ወሳኝነት አለው።

4 :  ችሎታው ካላቸው ልጆች ትስስር በመፍጠር የከበዳችሁን ጥያቄዎች ጠይቁ።

5 : ትኩረት ሰጥታቹ በራሳችሁ ላይ ስሩ።

ዩንቨርሲቲ የገባችሁት ከባድ ሀላፊነት ለመሸከም መሆኑ አትዘንጉ


የቤተሰብ ፣ የማህበረሰብ እና የራሳችሁ ነብሲያ ከናንተ ብዙ ነገር ሚጠብቁ አካላት ናቸዉ።

በመጨረሻም ግን አስታዉሱ ሁሉም የሚሳካልን አላህን ከያዝን እና እላህ ከፈራን ነዉ።


[[ وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا ۝ وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ ۚ وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ بَالِغُ أَمْرِهِ ۚ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لِكُلِّ شَيْءٍ قَدْرًا ]]

አደራ አደራ ሶላታችሁ ላይ በርቱ።
ከትምህርቱ ጎን ለጎን ለዲናችሁም ትኩረት ስጡ።

ይቀጥላ……
ከተሳሳትኩ አርሙኝ
👇👇👇👇👇
@abuki211


ይጠቅማል ካላችሁ ሼር በማረግ አግዙኝ።

የቴሌግራም ቻናል።
=
https://t.me/abukiweb
👍80👌5💯5🏆2🤝2
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
2  እንግሊዘኛ አላውቅም እንዴት ነው  መማር ምችለው?
🛑መሸሽ መፍትሔ አይሆንም🛑

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاتة
(መልስ ለ2 እና 6)
ለኛ ኢትዮጵያዉያን  ወደ ቴክኖሎጂዉ አለም ለመግባት የሚከለክሉ ምክንያቶች በጣም ብዙ ናቸዉ። ትልቅ  እንቅፋት ተደርጎ የሚወሰደዉ ግን እንግሊዘኛ  ቋንቋ አለመቻል እና የመማሪያ ቁሳቁሥ አለመሟላት ናቸው።

ግን እነዚህ ችግሮች ለመፍታት ከቴክኖሎጂዉ በመራቅና ቴክኖሎጂዉ  የማይደርስባቸዉ  ስራዎች ላይ መግባት እንደ አማራጭ እንወስደዋለን‼️

  ይህ ትልቅ ስህተት ነው ምክያቱም አሁን ላይ ሁሉም ስራዎች ላይ ግድ ስለሆነ‼️

በጣም የሚገርመው እኛ ከሱ ብንሸሽም እሱ ግን ቀን በቀን ወደ እኛ እየመጣብን ነው ።

አስቡት አሁን  ያለስልክ መኖር ምንያክል ከባድ እንደሆነ ።

በትንሹ በስልካችን ብቻ👇👇
የትም  ሆኖን ቁርዓን እንቀራበታለን
ኪታቦች እንቀራበታለን
የአዛን ወቅት አዛን እንሰማበታለን
ቂብላ  እናይበታለን
ተማሪዎች መፅሀፎች  እናነብበታለን
ከቤተሰብ እንዘያየርበታለን።
በሞባይል ባንኪንግ ብራችን  እናቀሳቅስበታለን…………
👆👆ብቻ ተግባሩ ተዘርዝሮ አያልቅም))

[[‼️ሁሉም  በሚባል መልኩ ደሞ የምንጠቀመዉ  አፕልኬሽን በእንግሊዘኛ ነዉ‼️]]

መፍትሄው፡
አስተሳሰባችን ማስተካከል።
ቴክኖሎጂን ማወቅ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ መሆኑ  መገንዘብ።
እንግሊዘኛ ማወቅ አማራጭ ሳይሆን  ግዴታ እየሆነ መሆኑ ማወቅ።
ቴክኖሎጂ  መማር ለሙስሊሙ  ማህበረሰብ ትልቅ ጥቅም እንዳለዉ መገንዘብ።
እናንተ ባይመቻችላችሁ ለወደፊት ለልጆቻችሁ ማሰብ።

ከላይ  ለቀረቡልኝ ጥያቄዎች  መልስ  መግቢያ ነዉ።
መልሱ አላህ ባገራልኝ መልኩ  መፍትሄ  እንዲሆነን በማሰብ  እፅፍላችዋለሁ።

((ግን ባጭሩ  የኔ መልስ  በአላህፍቃድ ሁላችንም ከተጋገዝን እንችለዋለን ነው👍)

እቀጥላለሁ  ኢንሻአላህ

ሼር በማድረግ ያግዙኝ🤝

ቻናሉ ለመቀላቀል👇👇

https://t.me/abukiweb
👍82🏆6💯2🤔1
በስልካችሁ መማር የምትችሉባቸዉ application እጠቁማችዋለሁ ኢንሻአላህ።

ሁሉም አፕልኬሽኖች ነፃ ናቸዉ።

ሼር🤝
ቻናሉ ለመቀላቀል👇👇
https://t.me/abukiweb
👍45🥰8
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በስልክ መማር ይቻላል

በሀኪም ምክንያት ታማሚ ተስፋ  ሊቆርጥ ይችላል‼️
በአስተማሪ ምክንያት ተማሪ ተስፋ ሊቆርጥ ይችላል‼️
በመካሪዉ ምክንያት ተመካሪው ተስፋ ይቆርጣል
‼️
እና ወንድሜ የመማር
ፍላጎት ላለዉ ሰዉ ተስፋ አታስቆርጥ ‼️

የሆነ ነገር ለማድረግ ወይም ለመወሰን ስንፈልግ የምናማክረዉ  ሰዉ ለይተን እንወቅ።

የምንጠይቀዉ አካል ምንም ባያደርግልን እንኳን በአላህ ፍቃድ ነገ ሊሳካ ይችላል ብሎ ተስፋ የሚሰጠን ቢሆን ይመከራል።

ለማንኛዉም  በኢኮኖምያችን(pc መግዛት ባለመቻል) ምክንያት ከትምህርቱ ከምንርቅ ያለን አማራጭ እነዚህን አፕልኬሽኖች ከፕሌይ ስቶር መተግበሪያ ላይ በማዉረድ እና በዌብሳይታቸዉ ገብተን በደንብ መለማመድ ነዉ።

https://www.w3schools.com

https://getmimo.com/ 


እነዚህና ከላይ ቪድዮ ላይ ያሉ አፕልኬሽኖች ጨምረዉ(Acode ,Web School Offline, ሌሎችም)በደብ የሚያግዙዋችሁ ናቸዉ።

ዋናዉ እና ዋናዉ ነገር ለትምህርቱ ያላቹህ ጉጉት እና ትኩረት‼️ ይወስነዋል
በነዚህ አፕልኬሽኖች ትልልቅ ፕሮጀክቶች መስራት ባያስችላችሁም  ግን ዋና ዋና የሚባል እዉቀቶች ትይዙበታላችሁ።
html,Css,Javascript.እና የመሳሰሉት።

እናንተ በዱዓ በርቱ ሰበቡንም አድርሱ እንጂ አላህ ደሞ ኮምፒተሩም ሊሰጣችሁ ይችላል።

ሌላዉ ደግሞ ግዴታ ዉድ ኮምፒተር ለመግዛት አታስቡ ለመማር ከሆነ የ10,000 እስከ 15,000  የሚገኙ ዲስክቶፖች  መግዛት ትችላላችሁ።

የኮምቲተርና የመማሪያ ክላሶች  ስፖንሰር ሲገኝ ደሞ  ምንም የመግዛት አቅም ለሌላችሁ የተወሰናችሁ እህቶች  Frontend በአካል ትማራላችሁ ኢንሻአላህ።

አጠቃቀሙ አብረን እናያለን።

ሼር በማድረግ አግዙኝ🤝

ቻናሉ ለመቀላቀል👇👇

https://t.me/abukiweb
👍75🥰9👏3🤝2