𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
13.6K subscribers
202 photos
115 videos
35 files
737 links
ስለ ቴክኖሎጂ እና እስልምና በቻልኩት አቅም አሳዉቃለሁ።
በነፃ ለመማር (Frontend web development)
👉 t.me/abukiweb/615
አላማችን:
👉  t.me/abukiweb/88

ኮምፒዉተር ለመግዛት
👉 t.me/Abuki_Computer
ዌብሳይት ለማሰራት፡
👉 t.me/abukiweb/583
ለጥያቄና ለአስተያየት
👉 @Abukiweb_bot
Download Telegram
የመልካም ነገሮች ሁሉ በር ሁን!
መልካም ነገሮች ሁሉ የሚገቡበት በር መሆን ካልቻልክ ብርሃናቸው የሚሾልክበት መስኮት ሁን!
ይህንንም ካልቻልክ የደከሙ ሰዎች  ወገብና ራስ  የሚደገፉት ግድግዳ ሁን!
    ብቻ ለሆነ ነገር ጥቀም፣ አሻራህን አሳርፍ!
  ዱንያ የማትፈልጋቸው የዱንያ ሸክም ከሆኑት ላለመሆን ጣር!
  ከቻልክ ከቻልክ  አዲስ ነገር ጨምረህ  እለፍ!
t.me/abdu_rheman_aman
👍20👌1
ስብራቶች ሁሉ የነገር መጨረሻዎች አይደሉም፤ እንዲያውም አንዳንድ ስብራቶች የመልካም ጅማሬ ብስራቶች ይሆናሉና ተስፋ አትቁረጥ!
:
ዘግይቶም ቢሆን ከአላህ የሚመጣ ችሮታ ያለፈን ሀዘንና ችግር የሚያስረሳ  ፤ በረከተ ሰፊ እና እጅግ አስደሳች የሚሆን ነውና ፤ አብሽሩ ችሮታውን በትዕግስት ተጠባበቁ!
t.me/abdu_rheman_aman
👍28🥰5🎉1
ጊዜው የምርቃት እንደመሆኑ ለተመራቂዎቸ ስጦታ የሚሆኑ የማያረጁና የማይጠወልጉ
የሪቫን አበባ 🌹በፈለጉት ከለርና ዲዛይን ትሰራለች እዘዟት😊
በተጨማሪም
ረከቦት ሱፍራ የግድግዳ ጌጣጌጥ  ሙሸበክ ሀለዋ ቀሲል እና እርድ ከፈለጋችሁ እንዲሁም የድሬ ጣፋጮችን ከምንጩ ታስልካለች ደውሉላት
በተለይ ወራቤ አ አ ቡታጅራ ሀለባ ቅርብ ነች
ስ ቁ 0987905610

በቴሌግራም ለማግኘት 👇👇
https://t.me/+Y0r7_-phBTwyZWE0
👍11🥰1
"መኖር ማለት አለመሞት ከሆነ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እየኖረ ነው። ግን መኖር ማለት እራስን መሆን፣ ለዓላማ መቆም፣ ህሊናን አለመዘንጋት፣ ፍርድን አለማጓደል፣ ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌላው እራስን መስዋዕት ማድረግ ብሎም አርአያ የሚሆን ነገር ጥሎ ማለፍ ከሆነ ስንቶቻችን ነን በህይወት ያለነው???"

=
t.me/https_Asselefya1
👍21💯6👌3🆒1
ፍቅርህን ፍለጋ!
መንገድህን ወደ አላህ ጀምረህ ከሆነ ገስግሰ!  ይህ ከከበደህ ዱብ ዱብ እያልክ አቅና!  ከደከመህ ተራመድ! ካልቻልክ በዳዴ እየተንፏቀክ ተጓዝ! ግን በፍፁም እንዳትመለስ። እንዲህ የሚለውን የሙሳ ዓለይሂሰላም ቃል ዘወትር አስታውስ
"ጌታዬ ሆይ! «ፍቅርህን ፍለጋ ወደ አንተ ቸኮልኩ» "
t.me/abdu_rheman_aman
👍44💯4🔥3🕊3👌1🤗1
ትንሽ ከጠቀማቹ ብዬ ነዉ ያጋራኃችሁ አብሽሩ !!
👏42👍18🆒1
ኮምፒውተር  ለሌላችሁ ብቻ‼️

ቴክኖሎጂ መተዋወቅ ትፈልጋላችሁ ግን ስልክ ብቻ ነዉ ያላችሁ?

Web Development ምን እንደሆነ ማወቅ ትፈልጋላችሁ?
ቀላል ይሁን ወይም ከባድ ማወቅ ትፈልጋላችሁ?

አንድ ሀሳብ ላካፍላችሁ በጥሞና አንብባችሁ ወስኑ🛑

Full Stack Web Development ማለት ምን ማለት ነው⁉️⁉️

መልስ ይህ በደንብ አንብቡት👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/abukiweb/335
https://t.me/abukiweb/335
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

ይህን አንብባችሁ ስትጨርሱ እርግጠኛ ነኝ ፁሁፉ ግልፅ ባይሆንላችሁም እንኳን ትንሽ ውስብስብ ትምህርት እንደሆነና ግዜ ፡ ትኩረት እና ከልብ የመነጨ ፍላጎት እንደሚያስፈልግ ግልፅ ነው!!
===========

እና የብዙዎች ጥያቄ ወደሆነዉ ነጥቤ ስመለስ፦ ይህን ዉስብስብ ትምህርት በስልክ መማር ይቻላል ወይ⁉️⁉️⁉️⁉️

መልሱ፦ እኔ ከተረዳሁትና የመጀመሪያ ዙር አቡኪ ቴክ ላይ ከተማሩ ተማሪዎች ሳስተምር የገጠሙኝ ሁኔታዎች አንፃር ልመልስ፣


መማር የሚቻለዉና ቀላሉ HTML & የተወሰነ Basic CSS ብቻ ነዉ። ከዛ በተረፈ እኔ በጣም ብዙ App ሞክሬያለሁ ግን ብዙም አያስኬድም።ከዛ ከፍ ካለም  ከፁሁፍ መማር ብቻ ነው።ምን አልባት w3shool ላይ እዛው websitu ላይ የተወሰነ Run ሊያደርግልን ይችላል።

===

ስለዚህ አሁን ምን ተረዳችሁ በስልክ በደንብ መማር የሚቻለዉ የ Web Developmnet መግቢያ ጫፉን ብቻ ነዉ! ማለትም HTML & CSS ።

ይህ ማወቅ ጥቅሙ ምንድነዉ⁉️

1  )) አብዛኛዉም ሰው Coding በጣም ከባድና የማይቻል አርጎ ስለሚስለዉ በስልኩ ቢያንስ መግቢያውን አይቶ እንዲወስን ያደርገዋል።

2  )) ካላስፈላጊ ወጪ ይገላግለዋል ማለትም አንድ ሰው ይህ ትምህርት ይሆነኛል ብሎ ኮምፒዉተር ገዝቶ ከዛ ከሱ ሙድ ጋር የማይሄድ ከሆነ በመሀል ያቆማል።ያ ወጪ በመሀል ይባክናል። በዚህ የተወሰነ ካየውስ መግቢያውን አይቶ ከተመቸዉ ከወደደዉ እና ከኔ የሚሄድ ትምህርት ነዉ ብሎ በራሱ ከተማመነ እዛኔ መቀጠል ይችላል።
3  )) በስልኩ የሚማረው  ምንም እንኳን መግቢያ ቢሆንም ወደቴክኖሎጂው አለም መቀላቀሉ በይፋ ያዉጃል
4 )) ሌላው ጥቅም ግዜ በማይረባ ነገር ምሳሌ፡ በቲክቶክ ወይም ኳስ በማየት ከሚባክን መማሩ የተሻለ ሆኖ ዮወሰዳል!!……………


እኔ የምመክራችሁ ትምህርቱ ይከብዳል ብላችሁ ለምታስቡ ወይም ጭራሽ ምንነቱ ለማታዉቁት ምንም ካለመማሩ በስልክ መማሩ የተሻለ ነዉ።ከዛ ትምህርቱ ከገራላችሁ ወስናችሁ ወደ ኮምፒዉተር መሸጋገር ቀላል ነዉ።
እንዲሁም ለልጆች ከዚህ ቢጀምሩ እመክራለሁ።

============
እንደዚህ ከሆነ አሁን አንተ በስልካችን ታስተምረናለህ ወደሚለው ጥያቄ ልምጣ!!

አዉ ግን የማስተምራችሁ ይህን ፁሁፍ በደንብ ተረድታችሁ በስልክ የምትማሩት ለ web Developmnet መግቢያ part ብቻ መሆኑን አዉቃችሁ ነዉ።
==========

መስፈርቶች👇👇
እነዚህን ጥያቄዎች መልሳችሁ ወደ ሚቀጥለዉ ሂደት እለፉ‼️

1 )) ከላይ ባያቹት መሰረት በስልክ መማር የምትችሉት ዋና ዋና ነገር መሆኑ በደንብ ግልፅ ነዉ??

2 )) ትምህርቱ ለመከታተል ምንያክል ቁርጠኛ ናችሁ??

3 ))  ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥራችሁ!!
4 )) መመዝገቢያዉ ሶስት መቶ ከፍላችሁ ሁለቱም ወር በነፃ ለመማር ከፈለጋችሁ ብቻ
በዚህ መልሶቹን ይላኩልኝ
👇👇
@AbukiComputer
@AbukiComputer

መማር ለሚፈልግ ሼር
||
ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb
👍2961👏1
ወጣትነት

ወጣትነት ማለት ምን ማለት ነው?

ወጣትነት ጥንቃቄ የሚፈልግ በብልሀት የምናልፈው ልክ እንደፒስታ መንገድ መንገጫገጮች የሚበዛው የስኬት ወይም የውድቀት መንገድ ነው።ይህንን ፒስታ በፈለግነው ማርሽ፣በፈለግነው ፍጥነትና በፈለግነው ነዳጅ ልክ የምንሽከረከርበት ከሆነ ወይ ይገለብጠናል ወይ ይጥለናል ወይ ይከሰክሰናል ከባሰ ደሞ ይገለናል ነገር ግን በጥንቃቄ በሚፈለገው ፍጥነት መጠን፣በሚያስፈልገው ማርሽ ባላንስ አርገን ማለፍ ከቻልን በአላህ ፍቃድ የሚፈለገው ቦታ ላይ ይደረሣል።

     ©LIJ_MUAZ
👌30👍10🆒4👏2
ዘዉድ ቴክ (Zewd Tech)🛑

በጣም ሲበዛ ዉሻታምና አታላይ ተቋም ነዉ‼️

ማንኛዉም ይህን ፁሁፍ ያነበበ ሰዉ በዚህ እና መሰል ድርጅቶች መሸወድ የለበትም።

በጣም ብዙ መረጃዎች ሳሰባስብ ቆይቼ ነበር እስከዛሬ እና እባካችሁ መስሊሞች በዚህ ድርጅት እንዳትሸወዱ‼️አጭበርባሪዎች ናቸዉ‼️

ግሩፓቸዉ ላይ  ማስታወቂያዉ እንደሚታየዉ

"👉በ 25% ቅድመ ክፍያ ብቻ 4 ስልጠናዎችን ወስደው በ ወር እስከ 30ሺ ብር የሚያስገኙ የስራ እድል የሚያገኙበት…"  ይላል እና ይህ ሙለ ለሙሉ ዉሸት ሲሆን ምንም አይነት የስራ እድል እንደማያመቻቹ የደረሱኝ መረጃዎች ያመለክታሉ!

ሲጠየቁም እያስተካከልን ነዉ ምናምን ብለዉ ያታልላሉ!!
እኔ እስከ ማቀዉ እነሱ ጋር ተምሮ አንድም ስራ ያስያዙት ሰዉ የለም!
ሲቀጥል የትምህርት አሰጣጥ  ጥራታቸዉ በጣም የወረደና በአግባቡ እንደማያስተምሩ ነዉ የሰማሁት!
~
በዚዉ አጋጣሚ ማወቅ ያለባችሁ ነገር ማንኛዉ የonline እስኪል ስትማሩ እንደዚህ በአጭር ግዜ ተምራችሁ ወጥታችሁ  በወር 30,000  ብር እሰራለሁ ብላችሁ እንዳትጠብቁ!!

አንዳንድ ማስታወቂያ የሚሰሩ ሰዎች ብር እስከተከፈላቸው ድረስ ምንም ሀላል ይሁን ሀራም: እዉነት ይሁን  ዉሸቱ ሳይለዩ ነዉ የሚስተዋዉቁት ። ስለዚህ ገንዘባችሁም ግዜያችሁም ከማባከን ተጠንቀቁ ለማለት ነዉ።

==
ይህን መረጃ ሼር አርጉትና ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከንደዚህ አይነት ዘራፊዎች ታደጉት!!

ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb
https://t.me/abukiweb
👍52👏6🏆4🆒2
#reposted
~
አቡኪ  ይህ መልክት ከጠቀማቸዉ ለቻናልህ ተማሪዎች አድርስልኝ።

እኔ የድሀ ልጅ ነኝ በዛ ላይ ገጠር ነዉ ያለሁት  እና ፉልስታክ  መማር ከጀመርኩ ስድስት ወር ሊሞላኝ ነዉ። ትንሽዬ የገጠር ከተማ  ላይ "ሊስትሮ" እየሰራሁ  ነዉ እራሴ የማስተምረዉ።

ሁሌም ጠዋት ከፈጅር እስከ አንድ ሰዓት የትምህርት ሰዓቴ ነዉ።

ከአንድ ሰዓት ጀምሬ እስከ ቀን አሱር ድረስ ስራ ላይ ነኝ። አሱሬን  ሰግጄ ሁሌም ሰፈራችንወደ ሚገኘዉ ላይብሬር ሄጄ መፅሀፎች አነባለሁ።በኤርፎን ቪድዮዎችን እከታተላለሁ። ከመግሪብ በኃላ እስከ ኢሻ ቂርዓት አለብኝ።ከ ኢሻ በኃላ እራቴን በልቼ  ወደ ትምህርቴ እመለሳለሁ። ከምሽቱ አምስት ሰዓት እተኛሉሁ አንዳንዴ ላረፍድም እችላለሁ።
በነገራችን ላይ wifi የለኝም። አንድ ቀን የቀን ነፃ ጥቅል ከቴሌ ገዝቼ የምፈልጋቸዉ ቪድዮዎች ሁሉም ዳዉንሎድ አደርጋለሁ። ቢያንስ ለሳምንት የማያቸዉ የለያዪ ቲቶሪያሎች እና ፕሮጀክቶች አወርዳለሁ። እንዲህ እንዲህ እያልኩ አሁን Backend ላይ ደርሻለሁ። አላህ ካለ ቀጣይ ሳምንት Backend ጨርሼዉ database እጀምራለሁ አልሀምዱሊላህ።
~
የብዙ ሰዎች ችግር   ነዉ ብዬ የማስበዉ ኢንተርኔት እና ወጥነት ማጣት ነዉ እና በእቅድ ያለመጓዝ።

እኔ የምመክራቸዉ ፡ እቅድ አዉጡ እቅድ አዉጡ እቅድ አዉጡ በጣም ወሳኝ ነዉ።ዝም ብላችሁ አትጀምሩት ስኬቱን እና ዉድቀቱን አመዛዝኑ  ። አላህ ያዙ ዒባዳችሁ  ላይ በርቱ። የሆነ ያስቸገራችሁ ቦታ ለሚያዉቁ ሰዎች ጠይቁ። Html መጨረስ ለናንተ እንደ ስኬት ዉሰዱት።ቲክቶክ እና መሰል  ሰዓት የሚጨርሱ ነገሮች አታብዙ። ከቻላችሁ በግሩፕ ተጓዙ ። ዋናዉ ነገር ትዕግስት ይኑራችሁ። ለዚህ ነገር ለመማሪያ ቢያንስ ሁለት አመት እና ወደ ስራ ለመግባት  የተወሰነ ልትታገሱ እንደሆነ እወቁ።

አላህ ካለ አንድ ቀን እዚዉ ቻናል ላይ የመጨረሻ ወጤቴ እና የደረስኩበት ደረጃ አሳዉቃችኃለሁ።አላህ ሁሉም ነገር ገር እንዲያደርግልኝም በዱዓችሁ አስታዉሱኝ አላህ ያስታዉሳችሁ።
ይኸው ነው‼️
👍66🏆19👏10🆒2👌1
እስካሁን Abuki Tech ላይ የተማርነዉ  የFull Stack Web Development ትምህርት የ TERM ONR ሙሉ ቪድዮ ከ Note ጋር አንድላይ አድርጌላችዋለሁ።
በስልክ ፤ በኮምፒዉተር እና የተሰሩ ፕሮጀክቶችን  ሁሉንም በአንድ ላይ እዚህ ያገኙታል።

ይህን ይጫኑ
👇👇
Term One
Term One
🎉10👍9👏3
ማስታወሻ
ክረምት እንደ መሆኑ በየፊልዱ አሰልጣኝና አስተማሪ ይበዛል።
ከዚህ አንፃር አንዳንድ ሀሳቦች እና ምክሮች እነሆ🫴

1. በመጀመሪያ ፍላጎታችሁን ለዩ!
መጀመሪያ ምን መማር እንደምትፈልጉ እና ለምን እንደምትማሩ ለራሳችሁ ግልጽ አድርጉ። ይህ ክህሎት ለወደፊት ህይወታችሁ (ትምህርት፣ ስራ) እንዴት እንደሚጠቅማችሁ አስቡ። የምትማሩት ነገር እውነተኛ ፍላጎት የሚያጭርባችሁ  ነው ወይ?

ለምሳሌ:
ኮዲንግ (Coding) መማር የምትፈልግ ከሆነ፣ ለምን እንደሆነ እወቅ? ለምን? ያበላል ተብለህ ነዉ?ወደ ቴክ መቀላቀል ፈልገህ ነዉ?ለምን? መልስ ይኑርህ

2. የስልጠናውን ይዘትና አስተማሪውን መርምር!

የተለያዩ ስልጠናዎች የተለያዩ ትምህርት አሰጣጦች አሏቸው።
የትምህርት ይዘት: ስልጠናው የሚሸፍናቸው ርዕሶች ከፍላጎትህ ጋር ይሄዳሉ? የትምህርቱ ጥልቀትስ ምን ያህል ነው?

የአሰልጣኙ ብቃት: አስተማሪው በዚያ መስክ ምን ያህል እውቀትና ልምድ አለው? የቀድሞ ተማሪዎች ምን ይላሉ? የማስተማር ብቃቱስ እንዴት ነው? ጠይቅ እና ድረስበት


የማስተማር ዘዴ: ትምህርቱ በቲዎሪ ላይ ያተኮረ ነው ወይስ ተግባራዊ ልምምድ ያበዛል?

3. ዋጋውንና ተመጣጣኝነቱን እይ!

የስልጠናው ክፍያ ከሚሰጠው ጥቅም እና ጥራት ጋር የሚመጣጠን መሆን አለበት።

የጠየቁት ክፍያ ተመጣጣኝ ነው? ከሌሎች ተመሳሳይ ስልጠናዎች ጋር አወዳድር።


4. የቀድሞ ተማሪዎችን ጠይቅ!

ከሌሎች ሰዎች የምትሰበስበው መረጃ ትክክለኛውን ምርጫ ለማድረግ ወሳኝ ነው።

ስልጠናውን ወስደው ከነበሩ ሰዎች ጋር አውራ። ምን ተማሩ? ስልጠናው ምን ያህል ረዳቸው?


5. የስልጠናውን ሰዓትና ቀን ተመልከት!
የስልጠናው ጊዜና ቅርጽ ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴህ ጋር የሚስማማ መሆን አለበት።

ሰዓትና ቀን: የስልጠናው ሰዓትና ቀን ከሌሎች ፕሮግራሞችህ ጋር ይጋጫል ወይ?
ኦንላይን ወይስ በአካል:?

እነዚህን ነጥቦች ከግምት በማስገባት፣ ለዚህ ክረምት ምርጥ የሆነ ስልጠና መምረጥ ትችላለህ።

መልካም የክረምት ግዜ ይሁንላችሁ

ለሚጠቅመዉ ሰዉ ሼር አርግ
ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb
https://t.me/abukiweb
👍1411👌1
ሰካራም ምሁሮች!
በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሐፊዘሁሏህ
ይድረስ ለአሁን ግዜ ለሰካራም ምሁሮች‼️

((…የወርቁዋ ወርቅ ልብስ መሆኑ ዘንግተዋል…))

ሼር ይደረግ ይድረሳቸዉ

[{ ኡስታዛችን፦አላህ እድሜያችሁን ያርዝምልን።}]

የቴሌግራም ቻናል👇
https://t.me/abukiweb
https://t.me/abukiweb
👍24👌4💯4👏3🥰1🎉1
እስቲ ይህን እዩት በስልክ ለመማር ያሰባችሁ 4000 ሰው ተምሮበታል
👇👇👇👇
https://youtu.be/KY_4Fer5n0w?si=A1UkanqOurOFdmmF
~
ይህንን ተመዝግባችሁ ለመማር👇👇
https://t.me/abukiweb/822

መማር ለሚፈልግ ሼር

ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb
👍5
ይህን የኮምፒዉተር ተማሪዎች የተማሩበት ሲሆን 6200 ሰው ተምሮበታል
👇👇👇
https://youtu.be/qb93EjLQ46M?si=NmbVXVniYPE_27KT

ይህን ተመዝግባችሁ ለመማር
👇👇👇👇
https://t.me/abukiweb/811

መማር ለሚፈልግ ሼር

ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb
👍3
ያ ኢላሂ ፡
ወንድ ልጅማ አይቸግረው!

ኢማኑም ይመር።አቅሉን ይስተካከል።
~
አላህዬ አንተዉ አስተካክልለን🤲
👍150💯20👌5🥰3🤔3