𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
13.3K subscribers
200 photos
114 videos
33 files
735 links
ስለ ቴክኖሎጂ እና እስልምና በቻልኩት አቅም አሳዉቃለሁ።
በነፃ ለመማር (Frontend web development)
👉 t.me/abukiweb/615
አላማችን:
👉  t.me/abukiweb/88

ኮምፒዉተር ለመግዛት
👉 t.me/Abuki_Computer
ዌብሳይት ለማሰራት፡
👉 t.me/abukiweb/583
ለጥያቄና ለአስተያየት
👉 @Abukiweb_bot
Download Telegram
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
እኔ አላህ በፈቀደው የቻልኩት ጥረት አደርጋለሁ።
ትምህርቱ እንዲመቻችላቹ።
ለዌብ ዴቨሎፕመንቱ (evangadi tech (Adugna ) በማነጋገር ከዩትዩብና ሌሎች ዌብሳይቶች በተጨማሪ አጋዥ በማምጣት እጨምራለሁ። )
አብረን እንብላ ማለቴ

አልተረዳቹኝም ማለት ነው በቃ ⁉️

አንድ ሰው ወንድም እህቱን ለመርዳት  ግዴታ ሀብታም መሆን የለበትም።
መቶ ብር ያለው ሰው ባለችዉ ብር ላይ ያለኝን ላካፍል  ቢል ማንም ድሀ ነህና አትስጥ የሚለው የለም።

ልክ እንደዛው ኑ በነፃ የቴክኖሎጂዉ መንገድ ላሳያችሁ ስላችሁ  ግዴታ expert ሰለሆንኩ ሳይሆን ያለኝን  ላካፍላችሁ ማለቴ ነው‼️

በጣም አልፎ የሄደ ሰውማ ምናልባት ዞር ብሎም ላያያችሁ ይችላል‼️


ወላሂ ብዬ የምነግራችሁ ነገር ቢኖር   ይህንን ትምህርት  እራሳቸው በራሳቸው አስተምረው በወር ከ50 ሺብር እስከ ሁለት መቶ ሺ ብር የሚሰሩ ልጆች አውቃለሁ።አዉቃለሁ ለአንዳንዱ ብዙ ነው ለሌሎቻችሁ ትንሽ ገቢ ሊሆን ይችላል።

ግን ዝም ብሎ  በመቀመጥ ምንም ምናመጣው ነገር የለም።
ያለን እውቀት ለወንድሞችና ለእህቶች  እያካፈልን   አብረን መጓዝ ነው።

እኔ ያልኳችሁ  በደንብ ከተረዳችሁኝይ ሀሳብ አስተያየታችሁ ከሰጣችሁኝ ምንም ወደ ኃላ የሚያስቀረን ነገር የለም።
አንድ ላይ ከሆንማ  ገና ብዙ programmer እንፈጥራለን ከ 10,000 በላይ ኢንሻአላህ ።


አጭር እና ግልፅ አማርኛ ልንገራችሁ አምስት አመት ዩንቨርሲቲ ተማራችሁ በዉድ ብር  ከፍላችሁም ተማራችሁ ወይም ኢቫንጋዲ ተማራችሁ  የራሳችሁ ጥረት ካልጨመራቹበት ልፋት ብቻ ነው በፍፁም expert መሆን አትችሉም።

አንድ ላይ ስንሆን

ሁሉም  ተመካክረን  እናልፈዋለን።
ከዲናችን ሳንወጣ ሁሉም እናሳካዋለን በአላህ ፍቃድ


ተረዳችሁኝ⁉️
አዎ👍


የቴሌግራም ቻናል
||
https://t.me/abukiweb
👍199💯16🤔5🥰3
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
የብዙ ወንድም እህቶች ጥያቄ⁉️
መልስ‼️

4 & 5:  እንዴት ነው ምንማረው ? ምንድነው ምንማረው?

የምንማረው በቴሌግራም ሢሆን በዋናነት የኛ ስራ የሚሆነው ኮርሶቹን ቅደም ተከተላቸው በጠበቀ መልኩ ለናንተ በነፃ መስጠት ነው።
( ስፖንሰር ሲገኝ በአላህ ፍቃድ በአካልም እናስተምራለን በዱዓ አግዙን )
(የወንድና ሴት ግሩፕ እለየዋለሁ ለደህንነታቹ   ሲባል)

ትምህርቱ በአላህ ፍቃድ አንዴ አይደለም   አስተምረን  ምናቆመው ስለዚህ በዚህ ዙር የተመቻቸላችሁ  ትማራላችሁ ቀጣይም ስንጀምር ደግሞ አሁን ያልተመቻቸላቹህ   ትቀጥላላቹ።

እናንተ የሚመቻችላቹ ወቅት ትመርጣላቹህ ምዝገባው ሲጀምር።

ከብዙዎቹ በመጣልኝ አስተያየት የተለያየ ዘርፍ ከሚሆን አንዱ ላይ ወጥረን በመማር ልምዳችን ከፍ ማድረግ ነው።
ስለሆነም አሁን Abuki Tech ላይ ቪድዮዎችን ለመስጠት ያሰብነው  የ Full Stack Web Developemnt ነው።
(ፍላጎታችሁ   ሌላ ዘርፍ ካላችሁ ለናንተም ሙሉ ቪድዮ ይሰጣችኃል )

ሌላው ቪድዮ መስጠት ብቻ ሳይሆን ጥናት ፕሮግራም ተመቻችቶዋል  ምክንያቱ በጣም ብዙ ወንድምና እህቶች እናንተን ለማገዝ ፍቃደኛ ስለሆኑ።

አካሄዳችንም የሚሆነው
computer ምንድነው ?
እንዴት ነው የሚሰራው ?
ከሚሉ ጥያቄዎች በመጀመር
programming እንቀጥላለን።
html,
Css ,Bootstrap
Javascript እያልን እንቀጥላለን።

FREE

የሌሎችንም ጥያቄዎች መልስ እለቃለሁ በትዕግት  ጠብቁኝ።

ሼር በማድረግ አግዙን

የቴሌግራም ቻናል
=

https://t.me/abukiweb
👍142👌8👏3🤝3
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
የብዙ ወንድም እህቶች ጥያቄ⁉️
መልስ
1: freelancing (እንዴነው ቤት ሆነን መስራት የምንችለው?)


ማንም የኛ መልክ ግድ አይለውም
ማንም የኛን ቁመት አይመለከተውም
ማንም ብሄራችን አይጠይቅም
ማንም ዘመድ አይጠይቀንም
ማንም ማስያዣ የመንግስ ሰራተኛ አይጠይቀንም

ግን

ሁላቸውን አንድ ነገር ይጠይቁናል

ችሎታህን ወይም ልምድህ
ከዚህ በፊት ምን ሰርተሀል/ሰርተሻል?
ለዚህ መልስ ካለህ በርግጠኝነት ስራውን ትሰሩታላችሁ።

ምን ምንድነው ሚሰራው?
web Devlopment
App Developmet
Video Editing
Graphcis Disgning
Content Creating


በጣም በጣም ብዙ ሀላል የሆኑ ስራዎች አሉ ከኛ ችሎታ ብቻ ሚጠይቁ‼️

በተለይም በዚህ ወቅት ለሴቶች እምመክረው የonline freelancing ስራ ነው።



ፅድት ያለ Portfolio አዝጋጅተህ ስራህን ማመልከት ብቻ ነው።


የተወሰኑ አሪፍ freelancing Websitoch.ልጠቁማቹህ 

1: Upwork: upwork.com


2. Freelancer: freelancer.com


3. Fiverr: fiverr.com

4.LinkedIn: linkedin.com

5: የኢትዮጵያ👇👇👇afriworkamharic


ሼር በማድረግ ያግዙን🤝

የቴሌግራምቻናል
=
https://t.me/abukiweb
👍66👏6💯5
በዱንያ ስትኖር ‼️
መልካም ፍሬ ዝራ
መልካም ንግግርን አብዛ
መልካም አስተሳሰብ ይኑርህ

የዛራኸው ፍሬ ማንም ቢያጭደው መልካም እስከሆነ ድረስ

በዱንያም በአሄራም አትራፊ ነህ

[[فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ]]

የቴሌግራም ቻናል
||
https://t.me/abukiweb
👍49🏆5🆒1
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
የብዙ ወንድም እህቶች ጥያቄ⁉️
መልስ

ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ምን ትመክራለህ⁉️

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاتة


programming መማር  አይደለም ለዩንቨርሲት ተማሪ  ለማንኛውም ማህበረሰ የሚመከር የትምህርት ዘርፍ ነዉ በተለይ  በአሁኑ ግዜ።
ሴቶች በተለይ ትኩረት እንድትሰጡት እመክራለሁ።
ምክንያቱም ከተመረቃችሁ ቦኃላ ፈተናው እናንተ ላይ ስለሚጠና ነው።

ምንአልባት የገባችሁት አሪፍ ካምፓስ ከሆነ  ኮምፒዉተር  የማግኘት እድላችሁ ከፍ ስለሚል
በየትኛው ፊልድ ብትሆኑ Medicine; Engineering;Economics ; Law; Finance and Accounting
ወይም ሌላ ቢሆንም በተመቻቸላችሁ አጋጣሚ ተማሩ።

መማር ከጀመረችሁ በኃላ ግን‼️

1 : እዛዉ ግቢ ዉስጥ ቲም ፍጠሩ

2 : ምንግዜም ቢሆን ግዜያችሁ በማይጠቅሙ ነገሮች አታባክኑ።

3 : ጓደኛ ምረጡ በጣም ወሳኙ እንደዉም ይሄ ነው። መልካም ጓደኛ ለዱንያም ለአኼራ በጣም ወሳኝነት አለው።

4 :  ችሎታው ካላቸው ልጆች ትስስር በመፍጠር የከበዳችሁን ጥያቄዎች ጠይቁ።

5 : ትኩረት ሰጥታቹ በራሳችሁ ላይ ስሩ።

ዩንቨርሲቲ የገባችሁት ከባድ ሀላፊነት ለመሸከም መሆኑ አትዘንጉ


የቤተሰብ ፣ የማህበረሰብ እና የራሳችሁ ነብሲያ ከናንተ ብዙ ነገር ሚጠብቁ አካላት ናቸዉ።

በመጨረሻም ግን አስታዉሱ ሁሉም የሚሳካልን አላህን ከያዝን እና እላህ ከፈራን ነዉ።


[[ وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا ۝ وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ ۚ وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ بَالِغُ أَمْرِهِ ۚ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لِكُلِّ شَيْءٍ قَدْرًا ]]

አደራ አደራ ሶላታችሁ ላይ በርቱ።
ከትምህርቱ ጎን ለጎን ለዲናችሁም ትኩረት ስጡ።

ይቀጥላ……
ከተሳሳትኩ አርሙኝ
👇👇👇👇👇
@abuki211


ይጠቅማል ካላችሁ ሼር በማረግ አግዙኝ።

የቴሌግራም ቻናል።
=
https://t.me/abukiweb
👍80👌5💯5🏆2🤝2
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
2  እንግሊዘኛ አላውቅም እንዴት ነው  መማር ምችለው?
🛑መሸሽ መፍትሔ አይሆንም🛑

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاتة
(መልስ ለ2 እና 6)
ለኛ ኢትዮጵያዉያን  ወደ ቴክኖሎጂዉ አለም ለመግባት የሚከለክሉ ምክንያቶች በጣም ብዙ ናቸዉ። ትልቅ  እንቅፋት ተደርጎ የሚወሰደዉ ግን እንግሊዘኛ  ቋንቋ አለመቻል እና የመማሪያ ቁሳቁሥ አለመሟላት ናቸው።

ግን እነዚህ ችግሮች ለመፍታት ከቴክኖሎጂዉ በመራቅና ቴክኖሎጂዉ  የማይደርስባቸዉ  ስራዎች ላይ መግባት እንደ አማራጭ እንወስደዋለን‼️

  ይህ ትልቅ ስህተት ነው ምክያቱም አሁን ላይ ሁሉም ስራዎች ላይ ግድ ስለሆነ‼️

በጣም የሚገርመው እኛ ከሱ ብንሸሽም እሱ ግን ቀን በቀን ወደ እኛ እየመጣብን ነው ።

አስቡት አሁን  ያለስልክ መኖር ምንያክል ከባድ እንደሆነ ።

በትንሹ በስልካችን ብቻ👇👇
የትም  ሆኖን ቁርዓን እንቀራበታለን
ኪታቦች እንቀራበታለን
የአዛን ወቅት አዛን እንሰማበታለን
ቂብላ  እናይበታለን
ተማሪዎች መፅሀፎች  እናነብበታለን
ከቤተሰብ እንዘያየርበታለን።
በሞባይል ባንኪንግ ብራችን  እናቀሳቅስበታለን…………
👆👆ብቻ ተግባሩ ተዘርዝሮ አያልቅም))

[[‼️ሁሉም  በሚባል መልኩ ደሞ የምንጠቀመዉ  አፕልኬሽን በእንግሊዘኛ ነዉ‼️]]

መፍትሄው፡
አስተሳሰባችን ማስተካከል።
ቴክኖሎጂን ማወቅ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ መሆኑ  መገንዘብ።
እንግሊዘኛ ማወቅ አማራጭ ሳይሆን  ግዴታ እየሆነ መሆኑ ማወቅ።
ቴክኖሎጂ  መማር ለሙስሊሙ  ማህበረሰብ ትልቅ ጥቅም እንዳለዉ መገንዘብ።
እናንተ ባይመቻችላችሁ ለወደፊት ለልጆቻችሁ ማሰብ።

ከላይ  ለቀረቡልኝ ጥያቄዎች  መልስ  መግቢያ ነዉ።
መልሱ አላህ ባገራልኝ መልኩ  መፍትሄ  እንዲሆነን በማሰብ  እፅፍላችዋለሁ።

((ግን ባጭሩ  የኔ መልስ  በአላህፍቃድ ሁላችንም ከተጋገዝን እንችለዋለን ነው👍)

እቀጥላለሁ  ኢንሻአላህ

ሼር በማድረግ ያግዙኝ🤝

ቻናሉ ለመቀላቀል👇👇

https://t.me/abukiweb
👍82🏆6💯2🤔1
በስልካችሁ መማር የምትችሉባቸዉ application እጠቁማችዋለሁ ኢንሻአላህ።

ሁሉም አፕልኬሽኖች ነፃ ናቸዉ።

ሼር🤝
ቻናሉ ለመቀላቀል👇👇
https://t.me/abukiweb
👍45🥰8
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በስልክ መማር ይቻላል

በሀኪም ምክንያት ታማሚ ተስፋ  ሊቆርጥ ይችላል‼️
በአስተማሪ ምክንያት ተማሪ ተስፋ ሊቆርጥ ይችላል‼️
በመካሪዉ ምክንያት ተመካሪው ተስፋ ይቆርጣል
‼️
እና ወንድሜ የመማር
ፍላጎት ላለዉ ሰዉ ተስፋ አታስቆርጥ ‼️

የሆነ ነገር ለማድረግ ወይም ለመወሰን ስንፈልግ የምናማክረዉ  ሰዉ ለይተን እንወቅ።

የምንጠይቀዉ አካል ምንም ባያደርግልን እንኳን በአላህ ፍቃድ ነገ ሊሳካ ይችላል ብሎ ተስፋ የሚሰጠን ቢሆን ይመከራል።

ለማንኛዉም  በኢኮኖምያችን(pc መግዛት ባለመቻል) ምክንያት ከትምህርቱ ከምንርቅ ያለን አማራጭ እነዚህን አፕልኬሽኖች ከፕሌይ ስቶር መተግበሪያ ላይ በማዉረድ እና በዌብሳይታቸዉ ገብተን በደንብ መለማመድ ነዉ።

https://www.w3schools.com

https://getmimo.com/ 


እነዚህና ከላይ ቪድዮ ላይ ያሉ አፕልኬሽኖች ጨምረዉ(Acode ,Web School Offline, ሌሎችም)በደብ የሚያግዙዋችሁ ናቸዉ።

ዋናዉ እና ዋናዉ ነገር ለትምህርቱ ያላቹህ ጉጉት እና ትኩረት‼️ ይወስነዋል
በነዚህ አፕልኬሽኖች ትልልቅ ፕሮጀክቶች መስራት ባያስችላችሁም  ግን ዋና ዋና የሚባል እዉቀቶች ትይዙበታላችሁ።
html,Css,Javascript.እና የመሳሰሉት።

እናንተ በዱዓ በርቱ ሰበቡንም አድርሱ እንጂ አላህ ደሞ ኮምፒተሩም ሊሰጣችሁ ይችላል።

ሌላዉ ደግሞ ግዴታ ዉድ ኮምፒተር ለመግዛት አታስቡ ለመማር ከሆነ የ10,000 እስከ 15,000  የሚገኙ ዲስክቶፖች  መግዛት ትችላላችሁ።

የኮምቲተርና የመማሪያ ክላሶች  ስፖንሰር ሲገኝ ደሞ  ምንም የመግዛት አቅም ለሌላችሁ የተወሰናችሁ እህቶች  Frontend በአካል ትማራላችሁ ኢንሻአላህ።

አጠቃቀሙ አብረን እናያለን።

ሼር በማድረግ አግዙኝ🤝

ቻናሉ ለመቀላቀል👇👇

https://t.me/abukiweb
👍75🥰9👏3🤝2
"በእውቀት ከሚበልጣችሁ ዘንድ ተማሩ።
በእውቀት የምትበልጡትን ደግሞ አስተምሩ።
ይህን ስታደርጉ ያላወቃችሁትን ታውቃላችሁ። ያወቃችሁትን ታፀናላችሁ።"

ኢማሙ ሻፊዒይ ረሒመሁላህ
••
[አልሙቀፋ አልከቢር: 5/226]

ሼር🤝
ቻናሉ ለመቀላቀል👇
https://t.me/abukiweb
👍78🤝9👌8🥰5
ማህበራዊ ሚዲያን ለዲንም ለዱንያም መጠቀም
~
ማህበራዊ ሚዲያን ሃይማኖታችንን ለመማማር መጠቀም ትልቅ ስኬት ነው። ነገር ግን እዚህ ላይ መቆም አይገባም። ሁሉም እንደተገራለትና እንደ ተሰጥኦው ወገኑን በመርዳት ላይ ቢተጋ መልካም ነው። የህክምና እውቀት ያለው ጠቃሚ ትምህርቶችን ያሰራጭ። የስራ ፈጠራና ጠቃሚ የቢዝነስ ሃሳቦች ያሏችሁ ችላ ሳትሉ የምክር አገልግሎት በመስጠት ወገናችሁን እርዱበት። ኤሌክትሮኒክስ ወይም ሌላ ቴክኖሎጂ ተኮር እውቀቱ ያላችሁ መረጃ በመስጠት ማገዝ ትችላላችሁ። በሌሎችም ዘርፎች እንዲሁ። በተናጠል የሚከብድ ከሆነ ተመሳሳይ ሙያ ያላቸው ተቀናጅተው ቢሰሩት ብዙ ህዝብ መጥቀም፣ ብዙ አጅር ማፈስ ይቻላል።
ከዚህም አልፎ ማህበራዊ ሚዲያን ለነፃ ግልጋሎት ብቻ ሳይሆን ቢዝነስን ለማቀላጠፍ መጠቀምም ይገባል። የራስንም ይሁን የሌሎች ወንድም እህቶችን ምርትና ሌሎች አቅርቦቶችን፣ ሙያና አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ፣ ግብይት ማከናወን፣ ዛሬ እየታየ እንዳለው ድለላ መስራት፣ ተቋማትንና የሚሰጡትን አገልግሎት ማስተዋወቅ፣ ... አስፈላጊ እንቅስቃሴ ነው። ስለዚህ የገባችሁበትም፣ ዝንባሌው ኖሯችሁ እያሰባችሁ ያላችሁም በታማኝነትና በሃላፊነት ለመጥቀምም ለመጠቀምም ነይታችሁ ስሩ።
ባይሆን አላህን ፍሩ! ውሸትን ተጠንቀቁ። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
”يا مَعشرَ التُّجّارِ ! إياكُم والكذبَ“
እናንተ ነጋዴዎች ሆይ! ውሸትን ተጠንቀቁ!" [ሶሒሑ ተርጊብ: 1793]

ብዙ ነጋዴዎች በተለይ በዚህ ዘመን አመፅ የነገሰባቸው፣ ዱንያ አላህን ከመፍራት የጋረዳቸው ሆነዋል። ወደ ዲን የቀረቡ የሚባሉት እንኳ ከሌሎች የተሻሉ መሆን እያቃታቸው ነው። ያስተውሉ! ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
إن التجار يبعثون يوم القيامة فجارا، إلا من اتقى الله وبر وصدق
“ነጋዴዎች በትንሳኤ ቀን አመፀኞች ሆነው ነው የሚቀሰቀሱት። አላህን የፈራ፣ መልካምን የሰራ እና እውነትን ያወራ ሲቀር።" [አሶሒሓህ፡ 994]

IbnuMunewor


የቴሌግራም ቻናል፦

https://t.me/abukiweb
👍30
يَاأيَُهَا الَُذِينَ آمَنُوا إذَا نُودِيَ لِلصَُلَاةِ
مِنْ يَوْمِ الْجُمُعَةِ  فَاسْعَوْا إلَی ذِکْرِ اللَُهِ 
وَذَرُوا الْبَيْعَ ذَلِکُمْ خَيْرُ  لَکمْ إنْ کُنْتُمْ تَعْلَمُونَ


የዉመል ጁመዓ

https://t.me/abukiweb
👍30💯8
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
አላማችን ባጭሩ🛑🛑 اسلام عليكم ورحمة الله وبركاتة በመጀመሪያ አላህ ሁሉም እህት ወንድሞች  የተስተካከለ እና ያማረ ህይወት እንዲያኖራቸውና መጨረሻቸው አሳምሮ ጀነተል ፊርዶስ እንዲወፍቃቸው  እለምነዋለሁ። በመቀጠል ሁላችሁም እንድትገነዘቡትና እንድረዱት የቻናሌን አላማ በትንሹ ላሳውቃችሁ። 1 በኢኮኖሚ ምክንያት  ከቴክኖሎጂው የራቁ ወንድም እህቶች በነፃ ቴክ ማስተዋወቅ ነው። ማለትም፦…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እቅዳችን ላይ ሞት እንጨምርበት🛑

እንለፋለን ግን አንድ ቀን ወደ አኼራ መሄዳችን አይቀርም።

አብሽሩ ለዲናችሁ ብላችሁ ከሀራም እርቃችሁ ችግር ላይ ያላችሁ ወንድምና እህቶች።

በዱንያም ደስታ በአኼራም ደስታ እንድታገኙ ነብዪ(صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ)
አብዝተዉ የሚጠቀሙት ዱዓ አብዙ👇👇👇👇

رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْآخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ

ግን   ይህ ሁሉ ለፍተን ሞት እንዳለብን ስናዉቅ ዱንያ ላይ ቆይታችን አጭር እና ብልጭልጭ መሆንዋን እንገነዘባለን።

ይድረስ ሀራሙን ላለመስራት ችግር ላይ ላሉ ወንድም እህቶች።

እኛም ሰበቡን እናደርሳለን
በአላህም እንመካለን አላህ ያግዘን🤲

ሼር በማድረግ ያግዙን🤝

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/abukiweb
👍62🤝3👏2
ለኡማዉ በምትችለዉ ጠቃሚ ሰዉ ሁን 🤝

ግን መጥቀም ካልቻልክ ከጉዳት  እራቅ 🤝

መልካም ሁን ወላሂ ደስተኛ
ትሆናለህ🤝
ምስጋና ሙገሳ እና ዝና አትመኝ🤝

ሌላዉ በቻልከዉ ማህበረሰብህ ለመደገፍ ስትነሳ አዛ ይበዛብሀልና
ታገስ🤝

ሴቶችን አክብር ተንከባከብ ምክንያቱም የነብዩ (صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ)አደራ ናቸዉና🤝

ሼር በማድረግ ያግዙኝ🤝
ቻናል👇
https://t.me/abukiweb
👍82🏆8💯7👏1
የወንድና ሴት ግሩፕ ለይቼዋለሁ‼️

👉ትምህርቱ አንድ አይነት ነው ሁለቱም ጋር ነፃ ነዉ‼️

ሁለቱም የለየሁበት ምክንያት ፦

1  የእኽቲላጥን  በር ላለመክፈት በኡስታዞች በተሰጠኝ ምክር መሰረት።

2  አስጠኚ የሆኖ ሴቶችና ተማሪዎች ያለምንም እፈረት ተዋዉቀዉ ተግባብተዉ ትምህርቱ ስኬታማ ሆኖ እንዲቀጥል በማሰብነዉ።

3 ሴቶች በሴቶች ዳዕዋ ስለሚኖር መለየቱ ግድ ነዉ።

4 በተረፈ በመማሪያ ክላሶቻችሁ በሁለታቹም በኩል እራሳችሁ ጠብቁ።

5 ወደ ግሩፑ መግቢያ የሆኑ መስፈርቶች በዚህ ሳምንት አሳዉቃችሁና  መማር የምትፈልጉ ትምህርታቹ የምጀምሩ ይሆናል ኢንሻአላህ።


ከላይ በግሩፕ የምታይዩት ቁጥር እናንተን ለማገዝ እና ለማስጠናት የተስማሙ ወንድምና እህቶች ናቸዉ።
አላህ ኸይር ጀዛቸዉ ይክላቸዉ።

[[የevangadi Scolarship የላካችሁ አዲስ መረጃ እዚህ ላይ ተለቆዋል ገብታቹ እዩ። https://youtu.be/IrUHoXLx0G4?si=X76jzc47hLuzCDKa ]]

ሀሳብ ካላችሁ በዉስጥ አሳዉቁኝ።

ሼር በማድረግ ያግዙኝ🤝
የቴሌግራም ቻናል
=
https://t.me/abukiweb
👍123👏13👌12🤝7💯3🤔2
𝐀𝐛𝐮𝐤𝐢 𝐓𝐞𝐜𝐡~በነፃ‼️
Photo
የነፃ‼️ ትምህርቱ መመዝገቢያ መስፈርት‼️
اسلام عليكم ورحمة الله وبركاتة

( በዚህ ዙር ምንማረዉ Web Development👉 Basic computer skills :Html,Css,Javascript,Node.Js..…………))

በዚህ ዙር መመዝገብ ያልቻላቹህ ወይም
በስራ ፤ በትምህርት ፤በቂርዓት ፤በህመም፤እና  መሰል  ምክንያቶች  አሁን  መመዝገብ  ያልተመቻቸላቹ  አላህ  ካለ ቀጣይ  ከአምስት ወር ቦኃላ  ሁለተኛ  ዙር   ቅድሚ    ሰጥተን  እንመዘግባቹዋለን


ዋና መስፈት‼️
1  ለትምህርቱ በቂ ግዜ ያላቹ ቢያንስ በቀን  3 ሰዓት
2  አሪፍ ኢንተርኔት ያላችሁ (ጥቅልም) ቢሆን ችግር  የለዉም
3 ፡ ኮምፒዉተር  ቢኖራችሁ ይመከራል ካልሆነ ስፖንሰር ስናገኝ በአካል ትማራላቹህ
4 ፡ በትዕግስ  ትምርቱ  የመጨረስ ወኔ ያላቹህ
5 ፡ ማታ በጥናት  ሰዓት  ላይቭ መግባት   የምትችሉ።
6 ፡ የሚሰጡ  ፕሮጀክቶች በተሰጣችሁ ሰዓት ማጠናቀቅ  የምትችሉ
7 ፡  በስልክ ዋናዋና እዉቀት ብቻ መያዝ እፈልጋለሁ የምትሉ

8 በዚህ ሳምንት ፎርም ይላክላቹና መስፈርቱን የምታሟሉ ትመዘገባላቹ እራሳችሁን አዘጋጁ።
((ያልገባችሁን ለመጠየቅ ግን ሙሉዉን ሳታነቡ አትምጡ።))

ሼር በማድረግ አግዙኝ🤝


ቻናሉ ለመቀላቀል
👇👇👇👇

https://t.me/abukiweb
👍136🤔6🏆4
ሰዎች በሀራምና በማይረባ ነገር ተጠምደዉ ባሉበት ወቅት

በሀላል መንገድ ለዱንያዉ ለአኼራዉም በሚለፋ የአላህ ባሬያ ላይ የአላህ እዝነት ሰላምና በረከት ይዉረድ


((ዱዓም ኢባዳ ነዉና ዱዓ አብዙ🤝))

ቻናሉ ለመቀላቀል
👇
https://t.me/abukiweb
👍126🥰11🤝2💯1
🛑اسلام عليكم ورحمة الله وبركاتة

ከዚህ በመቀጠል  አላህ ካለ በዚህ ቻናል የምንለቅላችሁ፡ 

👉ለዱንያም ለአኼራችን የሚጠቅሙ ምክሮች፤ሀዲስ፤ቁርዓን እና ቴክኖሎጂ ነክ ነገሮች እንለቅላችኃለን።
👉ኡስታዞች በመጋበዝ
ስለ ቴክኖሎጂ ሙስሊሞች  ዳዕዋ ማድረግ።
👉 በኦንላይን መስራት የምንችላቸዉ ስራዎች መጠቆም ፡መመካከር ።
👉 በተለይም ለሴቶች የኦንላይን ስራ እንዴት መስራት እንደሚችሉ በዘርፋ ልምድ ያላቸዉ ሰዎች በመጋበዝ ልምዳቸዉ መካፈል።
👉 ተመራቂ ተማሪዎች ስራ እንዲያገኙ  ስራ ሲገኝ መጠቆም፡

👉  በየዘርፋ ያሉ አካላት አንድላይ በማድረግ ተነጋግሮ ችግራቸዉ የሚፈቱበት መንገድ መጠቆም
👉እኛ እናስባለን አላህ ይፈፅማልና አላህ እንዲያግዘን ዱዓ ማድረግ🤝


ሼር በማድረግ ያግዙኝ🤝

ቻናሉ  ለመቀላቀል
👇👇👇

https://t.me/abukiweb
👍61🏆6🤝4🥰2