ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቤቴ
114 subscribers
535 photos
4 videos
13 links
ለፕሮፋይል የሚሆኑ የቤተ ክርስቲያን ይዘት ያላቸው ፎቶዎች መገኛ
Download Telegram
​​​​​​አክፍሎት

በሰሙነ ሕማማት ዕለተ አርብ ከስግደት በሗላ ምዕመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ ሰዓት/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡

ከአርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው። አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታችን፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውሃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡

ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬ ኔዎስ፣ አውሳብዮስ የተባሉ ጸሐፍት፣ ሐዋሪያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውሃ በቀር እንደማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋሪያት ሌሎቹንም እንድያከፍሉ እንዲያሳስቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻላቸው ቢያንስ ከአርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የኛ ቤተክርስቲያን ትምህርትም ይሄው ነው፡፡

ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት
https://t.me/abreshpp_seilatmgegna
"ሕማማት" ክፍል 33
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
👉 የኢየሱስን ልብስ ገፈፉት
ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
https://t.me/abreshpp_seilatmgegna
ንሴብሆ ለእግዚአብሔር
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
ንሴብሖ

ንሴብሖ /2/ ለእግዚአብሔር /2/ 
ስቡሐ ዘተሰብሐ /4 
እናመስግነው /2/ እግዚአብሔርን /2/ 
ምስጉን ነው የተመሰገነ /4/ 

ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን
ህይወት የሚሰጠን መና ነው ምግባችን

አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል መከራም ቢበዛ
ሃይላችን ጌታ ነው የዓለም ቤዛ

ከአለት ላይ ውሃ ፈልቆ እንደጠጣነው
ይህን ታላቅ አምላክ ኑ እናመስግነው
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል

አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተናው ቢበዛ
ሃይላችን ጌታ ነው የዓ
#ሼር

https://t.me/abreshpp_seilatmgegna