AB Profit Hub
3.74K subscribers
412 photos
66 videos
56 files
1.22K links
Download Telegram
በጣሊያን በ24 ሰዓት ውስጥ 793 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ሪፖርት ተደረገ። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 4,825 ደርሰዋል። በየዕለቱ የሟቾች ቁጥር በመቶዎች እየጨመረ የሚገኝባት ጣልያን ሁኔታው ከቁጥጥሯ ውጭ እየሆነ ይመስላል።

@ethiotech2012
❤️❤️❤️ስለራስህ ከስራህና ከአንተ በላይ የቀረበ ምስክር እንዲኖርህ አትጠብቅ
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
👇
@ethiotech2012
💧ሰዉ ስራህን አይቶ እንዲያደንቅህ አስበህ ከሆነ የምትሰራዉ ራስክን እየገደልክ መሆኑን ተረዳ።

💧በማንኛዉም መስሪያቤት የሚቆጣጠርህ እንጅ ስራህን በነፃነት እንድትሰራ ማመቻቸቱ ቀርቶ በምን መንገድ እንደምትሰራ እንኳን አዉቀቱ የለዉም።
ስለዚህ እርሱን ለማስደሰት ሳይሆን ራስህን ለማበልፀግ፣ የሙያ ስነመግባርህን ለማስከበርና ለህሊናህ ብለህ ስራ።

💧 ኳስ ተጫዉቶ ሳያዉቅ ተጫዋቾችን በቴሌቪዥን መስኮት እየተመለከተ ሲሳደብ፣ ሲተችና አስተያት ሲሰጥ ቆይቶ ቤት ድረስ መጥቶ አንተን ለማብሸቅ የሚታትር ጓደኛ የለህም? ታዲያ ከእርሱ ምን ተማርክ? ከበሮ ሲያዩት ያምር ሲይዙት ያደናግር የሚባለዉን አባባል ዘንግቶ አንተን ሁሌም በጨበጣ ቢተችህ ይገርምሃል? በእርሱ ተነሳስተህ የስራ ተነሳሽነትህን ልትተዉ?? በል በል ዉሾችን ተዉና ግመሏን ሁን!!!

💧 አንድ ቀን ወንበሩን ብትሰጠዉ እንዴት መምራት እንዳለበት የማያዉቅ ሰዉ በምላስ ጦር ሌሎችን ሲወጋ ተመልክተህ አታዉቅም? ታዲያ አቅምህን ራስህ እያወቅክ ለምን የሰዉ ሙገሳ ትጠብቃለህ!??

💧 ተማሪ እያለህ ሰቃይ ተማሪ ሲገኝ "እርሱ እኮ ሸምዳጅ ነዉ።" የሚል ተቀፅላ የተሰጠዉ ተማሪ አታስታዉስም?? ታዲያ ይሄንን እያወቅክ ለምን ሰዉ ስራህን እንዲያሞግስልህ ትጠብቃለህ።

💧ብዙ ነገር ማንሳት ይቻላል። ተወዳጅነትን ለማትረፍ ከሆነ የምትሰራዉ ስራህ ዘላቂ ዉጤትና ለዉጥ አያመጣም። በሰዎች ፍላጎት የተሰፋ ስራ እየሰራህ የሌሎች ስራ አስፈፃሚ ሆነህ ትቀራለህ።

💧 በየደቂቃው አቅምህን አጎልብት። ከስህተትህ ተማርና አሻሽለህ ሞክረዉ። አሁንም ካልተሳካ በሌላ መንገድ ሞክረዉ። ነገሮችን ቀለል አድርገህ ለመስራት አንብብ፣ አጫጭር የዩቱብ ቪድዮችን ተመልከት፣ ሙያህ የሚጋብዝህን ወርክሾፖች ተሳተፍ።

💧 ስራህን በአግባቡ ለህሊናህ ብለህ ስራ። ራስህን በስራህ ገምግም። ሳይንሳዊ ትችቶችን ለማስተናገድ በርህን ክፈት። በጨበጣ ለሚተቹህ አትንበርከክ። ስራህ የአንተ ምስክር መሆኑን ተረዳ።

📖 ብሩህ ተስፋ እንደፃፈዉ
@ethiotech2012
ስንቶቻችን የ #technology_abbreviatios እናቃቸዋለን እስቲ ለዛሬ የተወሰኑትን እንያቸው...

*The most important words*

1.*PAN* - permanent account number.

2. *PDF* - portable document format.

3. *SIM* - Subscriber Identity Module.

4. *ATM* - Automated Teller machine.

5. *IFSC* - Indian Financial System Code.

6. *FSSAI(Fssai)* - Food Safety & Standards
Authority of India.

7. *Wi-Fi* - Wireless fidelity.

8. *GOOGLE* - Global Organization Of Oriented Group Language Of Earth.

9. *YAHOO* - Yet Another Hierarchical Officious Oracle.

10. *WINDOW* - Wide Interactive Network
Development for Office work Solution.

11. *COMPUTER* - Common Oriented Machine.

Particularly United and used under Technical
and Educational Research.

12. *VIRUS* - Vital Information Resources
Under Siege.

13. *UMTS* - Universal Mobile Telecommunications System.

14. *AMOLED* - Active-matrix organic light-emitting diode.

15. *OLED* - Organic light-emitting diode.

16. *IMEI* - International Mobile Equipment Identity.

17. *ESN* - Electronic Serial Number.

18. *UPS* - Uninterruptible power supply.

19. *HDMI* - High -Definition Multimedia
Interface.

20. *VPN* - Virtual private network.

21. *APN* - Access Point Name.

22. *LED* - Light emitting diode.

23. *DLNA* - Digital Living Network Alliance.

24. *RAM* - Random access memory.

25. *ROM* - Read only memory.

26. *VGA* - Video Graphics Array.

27. *QVGA* - Quarter Video Graphics Array.

28. *WVGA* - Wide video graphics array.

29. *WXGA* - Widescreen Extended Graphics Array.

30. *USB* - Universal serial Bus.

💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

⚠️መረጃዎችን ለወዳጅዎ 👥 ያጋሩ።

********
🌐ዘመኑ #የቴክኖሎጂ ነው 📲 ከዘመኑ ጋር አብረው ይዘምኑ💻

🚪📥📤@ethiotech2012
👨‍💻 🔐@ethiotech2012
#EthiopianCOVID19MonitoringPlatform

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኢጀንሲ “የኢትዮጵያ የተቀናጀ የኮሮና ቫይረስ መከታተያና መቆጣጠሪያ ሲስትም” አዘጋጀ። አዲስ የተዘጋጀው ሲስተም ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት የምታደርገውን ጊዜ የማይሰጥ ርብርብ የሚያግዝ መሆኑንም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

👉@ethiotech2012
👇
YouTube:-www.youtube.com/c/techbyabraham
#ፈረንሳይ
1ኛ ሳምንት - 12
2ኛ ሳምንት - 191
3ኛ ሳምንት - 653
4ኛ ሳምንት - 4499
#ኢራን
1ኛ ሳምንት - 2
2ኛ ሳምንት - 43
3ኛ ሳምንት - 245
4ኛ ሳምንት -4747
5ኛ ሳምንት - 12729
#ጣሊያን
1ኛ ሳምንት - 3
2ኛ ሳምንት - 152
3ኛ ሳምንት - 1036
4ኛ ሳምንት - 6362
5ኛ ሳምንት - 21157
#ስፔን
1ኛ ሳምንት - 8
2ኛ ሳምንት - 674
3ኛ ሳምንት - 6043
#ኢትዮጵያ
10ኛ ቀን - 11

🙄 ቀጣዮቹ ቀናት ለኢትዮጵያ በጣም ወሳኝ ናቸው። ቫይረሱን ጠንካራ እርምጃዎች ወስደን ማስቆም ካልቻልን ወደማንወጣው ቀውስ ውስጥ እያመራን ነው። በዚች ደቂቃ እንኳን ስንቶቻችን በየታክሲው፣ በየባቡሩ፣ በየመንገዱ፣ በስራ ቦታ፣ በት/ቤቶች የጤና ባለሞያዎች የመከሩንን እየተገበርን ነው??
#Share JOIN #Share
የሚባለውን የሚሰማ ከከፋው አደጋ ይድናል!

- አትጨባበጡ
- ተራራቁ
- አትሰባሰቡ
- የእጃችሁን ንፅህና ጠብቁ
- አስገዳጅ ካልሆነ አርፋችሁ ቤታችሁ ተቀመጡ
- በጋራ ለመዝናናት ጊዜው አሁን አይደለም
- በቡድን እራት ለመብላት ጊዜው አሁን አይደለም
- የጤና ባለሞያዎችን ምክር ስሙ፣ ተግብሩ

ለእራሳችሁ፣ ለቤተሰባችሁ ጤና አስቡ!

@ethiotech2012
ውድ ቤተሰቦቻችን በመጨረሻ ይህን እናስታውሳችሁ፦

- እጃችሁን በውሃና በሳሙና አዘውትራችሁ ታጠቡ ወይም አልኮል ባለው የጀርም ማጽጃ /ሳኒታይዘር/ እጃችሁን አፅዱ፤

- ሳል እና ማስነጠስ ካለባቸው ሰዎች ቢያንስ በ2 ሜትር ወይም በ2 እርምጃ ራቁ፤

- እጃችሁን ሳይታጠቡ አይናችሁን ፣ አፋችሁን እና አፍንጫችሁን አትንኩ፤

- ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች አትሂዱ፤

- በእጅ መጨባበጥ አቁሙ፤

- ማህበራዊ ርቀታችሁን ጠብቁ፤

- አስፈላጊ ካልሆነ በቀር ከቤታችሁ አትውጡ፤

- ወጣቶች እየተሰባሰባችሁ አትዋሉ፤

- ወቅቱ የምንዝናናበት አይደለም ተቆጠቡ፤

- ያልበሰሉ የእንስሳትና የአሳ ምግቦችን አትመገቡ፤

- ከምንም በላይ የጤና ባለሞያዎችን ምክር አዳምጡ፤ ተግብሩ፤

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!

@ethiotech2012
‼️ሀገራዊ ጥሪ COVID19 😷 በተመለከተ
👇
@ethiotech2012

👉እንደምታቁት ኮሮና ቫይረስ በዓለም ብሎም በሀገራችን የተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

ብዙ ሰዎች እየተጠቁ ያሉት ደሞ በመረጃ እጦት እንደሆነ በተደጋጋሚ እየተነገረ ነው።

ስለዚ ሁላችንም እንደ አንድ ዜጋ እዚህ ቻናል ላይ የሚለጠፋትን ወይንም POST የሚደረጉትን መረጃዎች ለሌሎች #Forward ወይንም #ሼር በማረግ ህይወት ይታደጉ።

ማን ያውቃል እናንተ ከዚህ ቻናል Forward ወይንም #ሼር ባረጋችሁት መረጃ ብዙ ሰው በቫይረሱ ከመያዝ ሊተርፍ ይችላልና እባካችሁ POST የሚደረጉትን ሼር ማረግ አትዘንጉ

‼️እስኪ ካሁን በኀላ POST የሚደረጉትን መረጃዎች ሼር አረጋለው የሚል 👍

@ethiotech2012👈
🖍አስርቱ ˝የመ˝ ሕጎች - ለኮሮና‼️

👉መታጠብ (በሳሙና / በሳኒታይዘር )
👉መጉመጥመጥ (ውሀ ለብ አርገህ በትንሽ ጨው)
👉መጥረግ (በአልኮል )
👉መራራቅ (ስትቆሙ/ስትቀመጡ )
👉መታቀብ (ከመጨባበጥ /ከንክኪ )
👉መተው (ስብሰባ/ህዝብ የሚበዛበት ቦታ
👉መቀመጥ (ቤትህ /ሆቴል ውስጥ )
👉መመገብ (በሽታ ለመቋቋም )
👉መከታተል (መረጃን ከታማኝ ምንጭ )
👉መፀለይ (ወደ ፈጣሪ )

VIA የዶክተር አለ 8809

#SHARE ይደረግ
#TIGRAY

የትግራይ ክልል መንግሥት ባለፈው ሳምንት የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ለመግታት ካወጠው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ አለመግባባት አንድ ወጣት በፖሊስ መገደሉ ተገለጸ።

ግድያው የተፈጸመው ናዕዴር አዴት በሚባል ወረዳ ውስጥ መሆኑን የአካባቢው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር የማነ ኪዳነማሪም አረጋግጠዋል።

ግድያው የተፈጸመው ቅዳሜ መጋቢት 19/2012 ዓ.ም ናዕዴር አዴት ወረዳ ውስጥ ልዩ ቦታው ጅራ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ሲሆን፤ ምክንያቱም በወጣው አዋጅ መሰረት ፖሊስ በመጠጥ ቤት ነበሩ ሰዎች እንዲበተኑ በማድረግ ላይ በነበረበት ጊዜ በተፈጠረ አለመግባባት እነደሆነ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከአቶ ተመሥገን ጥሩነህ መግለጫ ፦

- የኮሮና ቫይረስ ካለባቸው ሁለቱ (2) ግለሰቦቹ ጋር ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ 70 ሰዎች ወደ ለይቶ ሕክምና ክትትል ማድረጊያ ገብተዋል።

- ተጨማሪ ከግለሰቦቹ ጋር ንክኪ እንደነበራቸው የተገመቱ ሰዎችን የማፈላለጉ ሥራ ቀጥሏል።

- በባሕር ዳር፣ እንጅባራ፣ አዲስ ቅዳምና ቲሊሊ ከተሞች የተላለፈው የእንቅስቃሴ ገደብ የቫይረሱን የተጋላጭነት መጠን ለመቀነስ እንጅ ሙሉ በሙሉ ነፃነትን የሚጋፋ እገዳ ለመጣል ታስቦ አይደለም።

- በሌሎች ከተሞች መሠል የእንቅስቃሴ ገደብ ውሳኔ እንዲተገበር የሕዝብ ጥያቄ አለ። የሕዝቡን ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነት ለመቀነስ ሲባል በየተዋረዱ ያሉ ኮማንድ ፖስቶች ተግባራዊ ያደርጋሉ።

- ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ለማገዝ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች አገልግሎት እንዲሰጡ ተዘጋጅተዋል።

ምንጭ፦ አብመድ
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 44 ደረሰ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 164 ሰዎች ውስጥ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋገጠ።

በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል 26ቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ መሆናቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

ዛሬ በቫይረሱ የተያዙት ግለሰብ የ65 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ የዱከም ከተማ ነዋሪና የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ግለሰቧ ተጓዳኝ ለሆነ በሽታ ወደ ህክምና ተቋም ከሄዱ በኋላ የቫይረሱን ምልክት በማሳየታቸው ነው ምርመራ የተደረገላቸው።

በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንድ ግለሰብ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ይገኛሉ።
#BREAKING

በኢትዮጵያ ሁለተኛው ሞት ተመዘገበ!

በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በሀገራችን በዛሬው እለት #ሁለተኛ ሰው ህይወት ማለፉን ስገልጽ በከፍተኛ ሀዘን ነው።

ታማሚው በለይቶ ማቆያ ከመጋቢት 24 ጀምሮ ህክምና ሲደረግላቸው የነበርና ከገቡበት ቀን ጀምሮ በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል ላይ የነበሩ ናቸው። በዚህም የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በእራሴና በጤና ሚንስቴር ስም እየገለጽኩ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።

#ጤና_ሚንስትር #ዶር_ሊያታደሰ
👇
@ethiotech2012
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DrTedrosAdhanomGhebreyesus

በሁለት (2) የፈረንሳይ ተመራማሪ ሐኪሞች የተሰጠውን የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ መሞከር አለበት የሚል ሃሳብ የዓለም ጤና ድርጅት ጄነራል ዳይሬክተር " ዘረኛ" ሲሉ ተችተዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም " አፍሪካ ለማንኛውም ክትባት መሞከሪያ አትሆንም፣ መሆንም የለባትም" ብለዋል።

የሕክምና ባለሙያዎቹ ክትባቱ መሞከር ስላለበት ጉዳይ አስተያየት የሰጡት በቴሌቪዥን ይካሄድ በነበረ የቀጥታ ክርክር ወቅት ነው። ይህ የሐኪሞቹ አስተያየት ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን አፍሪካውያንንን " መሞከሪያ አይጥ" አድርጎ ማሰብ ነው ብሏቸዋል።

ከዚህ አስተያየት በኋላ አንዱ ህክምና ባለሙያ ይቅርታ ጠይቀዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ስለኮሮና ቫይረስ መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት ስለጉዳዩ ሲጠየቁ መናደዳቸው ተስተውሏል።

ከዚያም " የቅኝ ግዛት አብሾ" አልለቀቃቸውም ሲሉ መልሰዋል። "በ21ኛው ክፍለ ዘመን ከሳይንቲስት እንዲህ አይነት አስተያየት መስማት የተዋረደ፣ አሳፋሪ ነው።

እንዲህ ዓይነት ነገርን በማንኛውም ሁኔታ እናወግዛለን። እናም የማረጋግጥላችሁ ነገር ይህ በጭራሽ አይሆንም" ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia