Abel Birhanu የወይኗ ልጅ
29.5K subscribers
4.21K photos
148 videos
11 files
1.1K links
ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! ለሃሳብ አስተያየት ይህንን ይጠቀሙ!
@abel21bot
Download Telegram
👉ሰበር ዜና‼️

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲ ከኃላፊነታቸው ተነሱ። ኮሚሽኑንን ከዘጠኝ ወራት በላይ በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲ መነሳታቸው ተገልጿል፡፡

ኮሚሽነሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር የኮሚሽኑን የቀድሞ ሃላፊ አቶ ይህደጎ ሥዩምን ተክተው የተሾሙት።

ሜጀር ጄኔራል ደግፌ፣ ከኃላፊነታቸው በድንገት የተነሱበት ዝርዝር ምክንያት ለጊዜው ባይታወቅም፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. የደረሳቸው የስንብት ደብዳቤ ግን ‹‹በጡረታ›› የሚል መሆኑ ታውቋል፡፡

ላለፉት ዘጠኝ ወራት ኮሚሽኑን ሲመሩ ቆይተው፣ ከሚያዝያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡
👆 በቢሾፍቱ አቅራቢያ የዛሬ አንድ ወር በተከሰሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞች ዛሬ የመታሰቢያ ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የመታሰቢያ ስነ ስርዓቱ የተከናወነው በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ውስጥ ነው።
(ፎቶ፦ ሰለሞን ሙጬ - ከአዲስ አበባ )
"በነጩ ቤተ-መንግስት የተነሳው ፎቶግራፍ ደርሷል:: ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካደረጉት ንግግር:- በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ወዳጅነት ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን:: እንኳን ወደ ዋሽንግተን በደህና መጣህ! የሚለው ይገኝበታል::

እኔም ለነበረው ደማቅ ስነ-ስርዓት እና መልካም አቀባበል የከበረ ምስጋና በማቅረብ በተለይ አገራችን በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት ያላት መሆኑን አስረድቻለሁ::"

Via Amb. Fitsum Arega
እንደምን አደርሽ እናት ሀገር ኢትዮጵያዬ 💚💛❤️
የተባረከ ቀን ይሁንልን !
#Abel_Birhanu_የወይኗ_ልጅ
ሼር
#Breaking

የሶዳን ጦር የሀገሪቱን ብሄራዊ ራዲዮ ጣቢያ መያዙ ተሰምቷል።

የሀገሪቱ ጦር በብሄራዊ ራዲዮ ጣቢያው መግለጫ ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል።

ከዚያ በተጨማሪም የካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዝግ መደረጉ ተነግሯል።

የሀገሪቱ ብሄራዉ የቴሌቪዥን ጣቢያም የሀገሪቱ ጦር በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ወሳኝ የሆነ መግለጫ ይሰጣል ሲል አስታውቋል።

በርካታ የሱዳን ጦር ተሽከርካሪዎችም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የሚገኙበት ቤተ መንግስትን ከበው መቆማቸውን ነው ምንጮች የገለፁት።

ለወራት ፕሬዚዳንት አልበሽር ስልጣን እንዲለቁ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩ በርካታ ሱዳናውያን የሀገሪቱ ጦር እየወሰደ ያለውን እርምጃ ተከትሎም አደባባይ ላይ በመውጣት ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑ ነው የተነገረው።

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተደረገባቸው እንደሆነ ይታወሳል።

ምንጭ፦ www.aljazeera.com
#ሰበር_ዜና

የሱዳን ጦር ፕሬዚዳንት አልበሽርን ከስልጣን በማንሳት ስልጣኑን መቆጣጠሩን አስታወቀ።

በዚህ መሰረትም ሀገሪቱን ለሁለት ዓመታት የሚያስተዳድር የሽግግር መንግስት መቋቋሙን የሀገሪቱ መከላካያ ሚኒስትር አስታውቋል።

በተጨማሪም ለሶስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ነው የተገለጸው።

ጦሩ ፕሬዚዳንት አልበሽርንም በቁጥጥር ስር ማዋሉም ተገልጿል።
#FakeImagesAlert

የሱዳን እንፎርሜሽን ሚንስተር ሀሰን ኢስማእል ከተደበቁበት ጉድጓድ በዚህ መልኩ በቁጥጥር ስር ዉለዋል የሚል ዜና በብዛት ሶሻል ሚዲያ ላይ ተዘግቧል፡፡ ነገር ግን ፎቶው ከመስከረም ጀምሮ ሶሻል ሚዲያ ላይ የነበረ ሲሆን በእኛ ሀገር ያለው ችግር በሌላም ዓለም የተለመደ ነው ያስብላል፡፡
እናንት ያገሬ ልጆች ~ እሳቱን ለማጥፋት እየታገሉ ነው!

#ETHIOPIA | እሳቱን ባላችሁበት ሆናችሁ መታገል ለምትፈልጉ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የቀረበ መልእክት

አዲስ አበባ ላላችሁ የተፈጥሮ ተቆርቋሪ የስሜን ወዳጆች በሺህ የሚቆጠር የስሜን ሰው እሳቱን ለማጥፋት እየደከመ ነው።

"እኛ ምን እናድርግ?!" ለምትሉ ለእነኚህ ከቤታቸው ወጥተው ነበልባል ሥር ውለው ለሚያድሩ ወገኖች ምግብና ውሃ መግዣ ማውጣት ከቻላችሁ ስሜንን ለመታደግ እሳቱን እንደተፋለማችሁ ቁጠሩት።

እነኚህ ሁለት የሂሳብ አካውንቶችን መጠቀም ትችላላችሁ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
Simen mountain national park zelaki,
acc.no 1000067261578

ወይም በደባርቅ ወጣቶች በተከፈተው
የኅብረት ባንክ
አካውንት ቁጥር 2060416618965015
Belayneh Abebe and or simon assefa and or Thomas Jejaw

የቻላችሁትን መደገፍ ትችላላችሁ።

ከደቡብ አፍሪካ ሄሊኮፕተር እስከሚመጣ ድረስ ዝም አይባል ነገር ...