ኢትዮ አድስ ሚድያ
356 subscribers
69 photos
1 video
10 files
49 links
አዳድስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ
Download Telegram
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር ስምምነት ሳይደረስ የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል ተገለጸ

ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ላይ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ ዛሬ ለግልና መንግስተዊ ላልሆኑ ትምህርት ቤቶች ባስተላለፈው ሰርኩላር ደብዳቤ ከወላጆች ጋር ስምምነት ላይ ሳይደረስ የ2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምንም ዓይነት የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል አስታውቋል፡፡

ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ የግል ትምህርት ተቋማት የክፍያ ጭማሪውን በተመለከተ ከወላጆች ጋር በነበረ ውይይት ስምምነት ላይ መድረስ ያልተቻሉባቸው መድረኮችን በአካል ተገኝቶ ማረጋገጡን አመልክቷል፡፡ የክፍያ ጭማሪውን በተመለከተ ከተማሪ ወላጅ ተወካዮች እና ከባለሥልጣኑ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጥ አቅጣጫ ብቻ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

  ---ETHIO-MEREJA---
  
T.me/ethio_mereja
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምረቃ መርሐግብር ላይ መሳተፍ የሚችሉት የመዉጫ ፈተናዉን ያለፉ ተማሪዎች ብቻ ናቸዉ - የትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፈተና አስተዳደር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ሚኒስቴሩ የፈተና ቀናትን ያሳወቀ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምረቃ መርሐ ግብር ቀናቸዉንም ወስኗል። በዚህም መሰረት ተቋማቱ የተማሪዎቻቸዉን የምረቃ መርሐግብር ከ ሐምሌ 11 እስከ 16 ባሉት ቀናት ማከናወን እንዳለባቸዉ አሳስቧል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይም መሳተፍ የሚችሉት የመዉጫ ፈተናዉን ያለፉ ተማሪዎች ብቻ መሆናቸዉን ጠቅሷል።

በሌለ በኩል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ  የ12ኛ ክፍል ሬሚዲያል መርሐግብር ተማሪዎቻቸዉን ዉጤት እና ለመጀመሪያ አመት የዩኒቨርስቲ ተማሪነት መብቃታቸዉን እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲያሳዉቁኝ ማለቱን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

የ 2015 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከ ሐምሌ 19 እስከ 30 መመዘኛዉን የሚወስዱ እንደመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጅታቸዉን ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ለፈተናዉ ብቻ መሆን እንዳለበት ገልጿል። በ2015 አመት የመዉጫ ፈተና ለመዉሰድ የተመዘገቡ እጩ ምሩቃን እና ባለፉት አመታት የህግ ትምህርት የመዉጫ ፈተና ወስደዉ ማለፊያ ዉጤት ያላስመዘገቡ ተማሪዎች ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እንዲፈተኑና ሐምሌ 10 ቀንም ዉጤታቸዉ የሚታወቅበት መሆኑን ጨምሮ አሳዉቋል።

  ---ETHIO-MEREJA---
 
T.me/ethio_mereja
Try Answer.AI now! Take a photo of any problem and get an instant answer with AI. Plus, you can ask AI any other questions too! Download through my referral link to get 15 free extra uses. Don't miss out, give it a try today!
https://answerai.page.link/67rz1NWMqmghQX8P7
Forwarded from ATC NEWS (MuJa. M)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የክፍት ሥራ ቦታ አመልካቾች ምዝገባ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው የክፍት ሥራ ቦታ ማስታወቂያ መሠረት የአመልካቾች ምዝገባ የሚያካሂድበት ጊዜ ከነሐሴ 15-19/2015 ዓ/ም ሲሆን የምዝገባው ቦታን ጨምሮ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
Forwarded from ATC NEWS (MuJa. M)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የክፍት ሥራ ቦታ አመልካቾች ምዝገባ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው የክፍት ሥራ ቦታ ማስታወቂያ መሠረት የአመልካቾች ምዝገባ የሚያካሂድበት ጊዜ ከነሐሴ 15-19/2015 ዓ/ም ሲሆን የምዝገባው ቦታን ጨምሮ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news