AAU Tutorial
7.66K subscribers
1.18K photos
10 videos
523 files
984 links
This channel is designed to share information and to support AAU students.
For any comment or suggestion use: @haile_my
Download Telegram
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።
Exam stress coping
Social science department placement has been released on portal.
⬆️Announcement for extension students.
የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ለሁሉም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና እንደሚሰጥ ተገለፀ።
-----------------------------------------

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱም በተቋማት ተጠያቂነትና የመረጃ ፍሰትን ለመዘርጋት እንዲሁም ውጤታማ እና ቀልጣፋ ሥራ እንዲያከናወኑ ያስችላል በተባለ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ መዋቅር ላይ ያተኮረ ነው።

በመንግስትም ሆነ በግል የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ወደሚፈለገው ደረጃ ከፍ ለማድረግ በቀጣይ የትምህርት ዘመን የመውጫ ፈተና ለሁሉም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ሊሰጥ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርቱ ማህበረሰብ ከፖለቲካ ነፃ ሆነው ሃሳባቸውን የሚያንሸራሸሩባቸው ተቋማት መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ አክለውም ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀት፣ የምርምርና የአዳዲስ ሃሳቦች መፍለቂያ ከመሆናቸው አንፃር ተልዕኳቸውን በብቃትና በውጤታማነት ለመፈፀም ይችሉ ዘንድ የተጀመረው የመዋቅር ሪፎርም ሥራ አንዱና ወሳኝ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የአካባቢውን ማህበረሰብ ሕይወት ሊቀይሩ በሚቻሉበት መልኩ ከተልዕኳቸው ጋር አጠናክረው የሚሄዱበትን ጉዳይ ለይተው መሥራት እንደሚገባቸውም ገልፀዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ በተዘጋጀው የዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ መዋቅር ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡

©MoE
To get more information join via the link below:
https://t.me/aaututorial
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች በሙሉ !!!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ቮሊቦል ክለብ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመወዳደር ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ምርጥና ተወዳዳሪ ሴት ተጨዋቾችን አወዳድሮ መቅጠርና ቡድናችንን ማጠናከር ስለምንፈልግ፣ ቮሊ ቦል መጫወት የምትችሉ ሴት ተማሪዎች (ስፖርተኞች) ከየካቲት 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምራችሁ በተማሪዎች ዲን ጽ/ቤት የክበባትና ስፖርት ማስተባበሪያ ቢሮ በመምጣት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
መስፈርት፡-
1. ቁመቷ 1.70 እና በላይ የሆነ፣
2. በግቢው ውስጥ ምንም አይነት የሥነ-ምግባር ችግር የሌለባትና ለስፖርት ህግ ተገዥ (ዲስፕሊንድ) የሆነች፣
3. ክለቡ በሚያደርጋቸው ልምምዶች ላይ ለመገኘት የምትችል መሆን ይጠበቅባታል።
ማንኛዋም የመጫወት ብቃት ያላት ሴት ተጨዋች መሳተፍ የምትችል መሆኗን እንገልጻለን፡፡
ሠላም እንዴት ናቹህ?
ትራንስፓረንሲ ኢትዮጵያ 4 ኛ ዙር ሥልጠናውን በመጭው ቅዳሜ Ethical Leadership በሚል ርእስ የሚሠጥ በመሆኑ እስካሁን የባለፉትን ሥልጠና ሥትከታተሉ የቆያችሁና 3ኛ ዙር ሥልጠና ላይ የተካተታችሁ ተማሪዎች ከወዲሁ እንድትዘጋጁ ስንል እናሣሥባለን።
BGI Ethiopia’s internship program, BGI-XP!

Seeking to select competent second year university students and give them practical experience and exposure, BGI, one of the biggest, leading companies in Ethiopia has created BGI-XP. Register using the Google form.

And, please come to FB Hall on Tuesday (February 15).

የቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ የሙያ ክሂሎት ልምምድ ፕሮግራም - ቢ.ጂ.አይ.-ኤክስ.ፒ.!

ዐቅም እና ፍላጎት ያላቸውን የሁለተኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማብቃትና የሙያ ክሂሎት ልምምድ ለመስጠት በሀገራችን ውስጥ ግዙፍ ከሆኑት ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ ቢ.ጂ.አይ.-ኤክስ.ፒ. የተሰኘ የሙያ ክሂሎት ፕሮግራም አዘጋጅቷል።

መሥፈርቱን የሚያሟሉ ተማሪዎች በየዓመቱ እስከምርቃታቸው ድረስ ሁለት ወራትን ከአምስቱ የቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ ፋብሪካዎች በአንዱ ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ ተከታታይ የሙያ ክሂሎት ልምምድ እንዲያገኙ ይደረጋል። በልምምዱ ኺደት ችሎታቸውንና ትጋታቸውን ያስመሰከሩ ተማሪዎች ከልምምዱ በሁዋላ ድርጅታችንን ይቀላቀላሉ። ከታች ይመዝገቡ።


https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSf3WKLps-LAJZI9oTOwsfSsIYaQttoXwor3mlKv-gSDMbuIPA/viewform
Job Title: Female tutor for grade 4 student

Company: Private

Job Type: Hourly

Description: We would like to hire a female tutor for a grade 4 student. Teaching or tuition experience is required. The tutor is expected to work in the mornings for two hours, four times a week. Place of tuition is around 4 Kilo. Fill out the form below to apply.
https://forms.gle/tpnLeeK6xmzRmZTZ8
Living near 4 Kilo is a requirement.